ካለፈው አመት ጀምሮ አንጎሌን ሲበጠብጠኝ የነበረን ሳንካ ላካፍላችሁ:: አስሊዬ ኤክስ.ፒ ሲኖረው, ለብዙ አመታት ያላንዳች ችግር ሲሰራ ቆይቶ ድንገት ከአምና ጀምሮ አልፎ አልፎ በገዛራሱ ይባትል ጀመር:: ብተላው እጅግ የከረረ ከመሆኑ የተነሳ የአስሊው ቁሳቁስ ለምሳሌ ሲ.ፒ.ዩ እና ሜሞሪ የመሳሰሉ 100% ተይዘው ሌላ ከተጠቃሚው የሚመጣ አንዳችም ሥራ በማይሰሩብት ሁኔታ ታቅበው አያቸዋለሁ:: አስሊው በዚህ ሁኔታ ለ 1.30 ሰአታት ያህል በራሱ ብቻ ሲሯሯጥ ይቆይና ጋብ ይላል:: ይህ ሁኔታም በቀን እስከ 5 ግዜ ይደግማል, ማለት ኡደታዊ ይዘት አለው ማለት ነው:: ስሰራበት ቆይቼ ሳንካው ሲጀምር ጥዬ እስኪጨርስ መጠበቅ ይኖርብኝ ነበር:: በጣም የሚያበሳጭ እክል ነበር::
ለብዙ ግዜ ምክንያቱን ልረዳው አልቻልኩም ነበር, ኦ.ኤስ ኡን ጠርጌ አውጥቼ እንደገና እንዳልገጥም ብዙ ሰሪ-ተሰኪዎች (application software) አሉት:: እነሱን ዳግም መግጠም አልችልም, ወይ የበሁር ሲዲ ግልባጮች የሉኝም ወይ ከሰው ተውሼ የገጠምኳቸው ናቸው
አንዴ "ታስክ ማኔጀር" ውስጥ ስመለከት ይህ ሳንካ በጀመረ ቁጥር የሚነሳ አገልጋይ (ሰርቪስ) ልብ አልኩ:: wuauclt.exe ይባላል:: ከሱም ጋር አብሮ ከ ኦ.ኤስ ጋር የሚመጣ svchost.exe የሚባል አገልጋይም አብሮ ይነሳል:: የነዚህን ሁለት አገልጋያት የአስሊ ቁስ አጠቃቀም ይዘት ስመለከት 100% ሆኖ አገኘሁት:: ስለዚህ መገንዘብ የቻልኩት ምንድን ነው, እነዚህ ሁለት አገልጋያት በኡደታዊ ሁኔታ እየተነሱ አስሊዬን የሚያዣብሩት መሆኑን ነው:: ችግሩ የሁለቱንም ስም አለም-መረብ ላይ ፈልጌ ሳጣራ የ ኦ.ኤስ ክፍል እንደሆኑና በተለይ wuauclt.exe የሚባለው አገልጋይ የ ኦ.ኤስ አዝማኒ (MS update) ክፍል እንደሆነ ተረዳሁ:: ያ ከሆነ ይህ አገልጋይ እኔ በመረጥኩት ሰአት እይተነሳ ከ MS የተለቀቀ ዝማኔ መኖሩን አረጋግጦ, አስፈላጊውን አውርዶ ለተጠቃሚው በማሳወቅ ይገጥማል እንጂ በዘፈቀደው እየተነሳ ተጠቃሚውን ማጉላላት እንደሌለብት አወቅሁ:: ይህ ችግር ወይ የአስልዬ ማለት የ አስሊ-ደዌ (Virus) ነው ወይ የ MS ችግር ነው:: ለማንኛውም የ ኦ.ኤስ ዝመና ምርጫ የሚስተጥበት ሳጥን ላይ ሄጄ ይህንን ዝመና ምርጫ በሙሉ ስዘርዘው ሳንካው ተወገደ:: የሳንካው ኡደታዊ ምስረቃ አቆመ::
በነገራችን ላይ እዚህ ገጽ ሄጄ ነው ብዙ መረጃ ያገኘሁት:: እንደምታነቡትም MS ችግሩ የራሳቸው መሆኑን አምነው መፍትሄ ለመስጠትና ለማውጣት ቃል ገብተዋል::
http://social.answers.microsoft.com/For ... dcf9a9a03b