መጀመሪያ በዋርካ ስንተዋወቅ!

The Love Forum (love, relationship) (የኔ ቆንጆ እንተዋወቅ :-)

Postby ዱክበር » Thu Mar 08, 2007 9:24 am

ሰላም የዋርካ ወዳጆች!

የዚህ ቤት አላማ ትውውቃችን እንዴት እንደነበር በማስታወስ ወዳጅነታችንን ለማጠንከር እንዲረዳ ነበር:: አሁን ግን የተገኙትም ወዳጆች መጠፋፋት ስለጀመሩ ለማፈላለጊያነትም እንጠቀምበት መሰለኝ እስቲ ካላችሁበት ወጣ በሉ:-

እኔውነኝ (አንዱ ኝ ካነሰ ባለሁለቱ እኔውነኝኝ)
ፉፊ
እድላዊት
አራትኪሎ
ባለሱቅ
.
.
.

አለን በሉ እስቲ ...

ባለንበት ቸር ይግጠመን::
ዱክበር
አዲስ
አዲስ
 
Posts: 35
Joined: Tue Jan 25, 2005 8:10 am
Location: ethiopia

Postby ~~~~~ » Sun Aug 22, 2010 2:51 am

ሚኦቲዬ አልሽልኝ ምነው ጠፋሽ?
~~~~~
አዲስ
አዲስ
 
Posts: 14
Joined: Mon Feb 04, 2008 5:09 pm

Postby ቤዛ » Mon Oct 04, 2010 2:26 am

ዱክበር wrote:ሰላም የዋርካ ወዳጆች!

የዚህ ቤት አላማ ትውውቃችን እንዴት እንደነበር በማስታወስ ወዳጅነታችንን ለማጠንከር እንዲረዳ ነበር:: አሁን ግን የተገኙትም ወዳጆች መጠፋፋት ስለጀመሩ ለማፈላለጊያነትም እንጠቀምበት መሰለኝ እስቲ ካላችሁበት ወጣ በሉ:-

እኔውነኝ (አንዱ ኝ ካነሰ ባለሁለቱ እኔውነኝኝ)
ፉፊ
እድላዊት
አራትኪሎ
ባለሱቅ
.
.
.

አለን በሉ እስቲ ...

ባለንበት ቸር ይግጠመን::

እስኪ ትዝ ከሚሉኝ ጥቂቶቹን::

ምርቃና: ትንሽ ይነታረካል ፖለቲካም ይወዳል እኔ ደሞ አይገባኝ ስለማልነታረከው ደህና ነበርን ቂቂቂ
ቲቲ: ከሁሉ ጋ ሰላማዊና ስው ሲጣላ አስታራቂም ነበረች::
ቕቕቕ: (እንደዚህ አይነት ፊዳል የበዛበት) በውነት በጣም ተጫዋች ሰው ነበር
ካርተር: እሱ ደሞ አንዱ የዋርካ ጎደኛዬ ነበር የት ገባ?
ቤቲ: ለዛ ያለት ልጅ ነበረች
ስንት አሉ ስማቸው ጠፋኝ አይ ለዛ ያለው ጨዋታ ነበር ያን ዘመን ያስቸገረውን ባውንስ እናደርግና ቀደዳ ነበር::
ሌሎቹን ሳስታውስ መለስ እላለሁ::
ቤዛ
ጀማሪ ኮትኳች
ጀማሪ ኮትኳች
 
Posts: 87
Joined: Wed Nov 12, 2003 5:39 pm

Postby ጩጉዳ » Mon Oct 04, 2010 3:42 am

እኔ የማልረሳት ዋርካ ቻት ሩም ከኩባ ሀቫና በኩባ ባንዲራ የምትገባ ልጅ ናት:: ስሟን ረስቻለሁ ስፓኒሽና አማርኛ እየቀላቀለች ነበር ቻት የምታደርገው:: በናታችሁ ስሟን የምታስታውሱ ካላችሁ አብሲኒያ ? ኢትዮ አዲስ ? ሀበሻ ? ብቻ ኒኳ ከነኚ ስሞች ጋር የተያያዘ ነው:: ሁሌ ስለ አገር ቤት ትዝታ ነበር የምታወራው:: ግን ያለችበትን ኪዩባን በጣም እንደምትወድና ያንን አገር ለቃ እንደማትሄድ ትናገር ነበር::
መታገስንና መቻልን የመሰለ ብቀላ የለም ::
ጩጉዳ
ውሃ አጠጪ
ውሃ አጠጪ
 
Posts: 1267
Joined: Mon Jan 31, 2005 6:40 am
Location: Studio City, Wilson Republic

Postby wolfi » Wed Oct 06, 2010 3:38 pm

እያንዳንድሽ ዋርካ ውስጥ አውቅሽ የነበረ ከአለም ጥግ እስከ አለም ጥግ ያለሽ የነበርሽ የምትኖሪ ቺክም ሆንሽ ዱድ እንዴት ከርመሻል ከዋርካ ቻት ሩም በሁዋላ?እኔ ዎልፊ ነኝ የዱሮው የጠዋቱ አሁንም ያበባ ምንጣፍ እንደመሰልኩ እንዳለሁ አለሁ ሁልሽም በጣም ናፍቀሽኛል የምትወጂኝም የማትወጂኝም በሙሉ እስኪ ብቅ ብቅ እያልን የዱሮውን እንጨዋዋት በኡራኤል. ቀድሞ መልስ ለመለሰ በጣም ይወደኝ የነበረ ፍጥረት ነው.

ወይ ጉድድድድድድድድድድድድድድድድድ አሁን እንዲህ አልፎ ሳነበው እንዴት ደስ ይላል ጉድ ጉድ ጉድ በል ጎንደር.
wolfi
አዲስ
አዲስ
 
Posts: 15
Joined: Fri Sep 19, 2003 7:21 am

Postby wolfi » Mon Oct 11, 2010 7:49 pm

ወቸው ጉድ የዱሮ ሰው በሙሉ ጭሮዋል ማለት ነው ወይስ ስትግደረደሩ ነው መልስ የማትሰጡኝ? የዱሮ ሰውን የበላ ጅብ ጩህ እረ በአዛኚቱ በእመብርሀን
wolfi
አዲስ
አዲስ
 
Posts: 15
Joined: Fri Sep 19, 2003 7:21 am

Postby መንኮራኩር » Tue Oct 12, 2010 12:54 pm

ለድሮው ኒካቸው ፓስወርዱ ጠፍቶባቸው የአሁኑኑ ማንነታቸው ላለማስፎገር በአይናቸው ሃይ ብለውሃል::
Peace has to be created, in order to be maintained. It is the product of Faith, Strength, Energy, Will, Sympathy, Justice, Imagination, and the triumph of principle. It will never be achieved by passivity and quietism.

Dorothy Thompson:
መንኮራኩር
ዋና ኮትኳች
ዋና ኮትኳች
 
Posts: 637
Joined: Tue Mar 28, 2006 7:05 am

Postby ኤልሳ* » Tue Oct 12, 2010 7:36 pm

wolfi wrote:ወቸው ጉድ የዱሮ ሰው በሙሉ ጭሮዋል ማለት ነው ወይስ ስትግደረደሩ ነው መልስ የማትሰጡኝ? የዱሮ ሰውን የበላ ጅብ ጩህ እረ በአዛኚቱ በእመብርሀን


ሰላም ብያለሁ ሻሮንንን....
ኤልሳ*
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 196
Joined: Thu Jul 27, 2006 10:30 pm

እኔ ማን ነበርኩ...

Postby ጁዲ » Fri Oct 15, 2010 3:35 am

ቅቅቅቅቅ.....ወይኔ እኔ ማን ነበርኩ .....በሽማም ቅዱሽ ውልፍ.....አለህ ባገር......እንደው መልካም እና ዱክበርን ምርቃና ምን ዋጥኣቸው? ሰማ ......በቃ ተወው.........

ውቻ................
ጁዲ
አዲስ
አዲስ
 
Posts: 40
Joined: Wed Jun 30, 2004 10:12 am
Location: united arab emirates

Postby ሙዝ1 » Sat Oct 16, 2010 5:17 pm

ህምምም ጊዜዉ ይሮጣል ... 2006 ... በኛ 1998/9 .... ያኔ ማህበራዊም ሆነ ሙያዊ የኢንተርኔት መድረኮችን በተደጋጋሚ እጎበኝ ነበር .... ዋርካንም እንደዚሁ ... ሁሉም ግን ጊዚያዊ ነበሩ ... ዋርካም ከዛኔዉ ስሜት ባለፈ ዛሬም ድረስ ጎራ እንድል የሚያደርግ ትስስር መነሻዉ ምን እንደነበረ አይገባኝም ... ሙዝ1 በሚባለዉ ገጸ ባህሪ መግባት ጀመርኩ ... ወደድኩት .... ዉቃዉ እንዳለዉም የኔ የግሌ ፎረም እስከሚመስለኝ ድረስ ተመላለስኩበት .... ወደመጨረሻዉ አካባቢ (ግን መጨረሻዉ የቱ ነዉ ሀ ሀ ሀ) ...ወደመጨረሻዉ አካባቢ ግን በኔና በሙዝ1 መካከል ያለዉ ልዩነት መጥበብ ሲጀምር አላምረኝ አለ ... እኔማ እኔ ነኝ ከዋርካ ዉጭም አለሁ ... እኖራለሁ ... አዲስ አይነት ፍሌቨር ፍለጋዉ በሙዝ1 በኩል ካልሆነ በኔ መፍጠር አልችል አልኩኝ ... እናም መጥፋት አበዛሁ ....

ለቆይታየም ቀዳሚ ወዳጆቼ ምናልባትም ላጣቸዉ የማልፈልጋቸዉ ኒኮች የራሳቸዉ አስተዋጾ ነበራቸዉ ... አንዳንዶቹን እንደዉም በአካል ማግኘት ደረጃ ደረስኩ ... መልካም አልነበሩምና መልካም የመሰሉኝን አደረኩ ... ሁሌም ግን ዋርካን ሳስብ የማልረሳቸዉ

ገራገሩ አክየ .... ጌታ ከምን እንደምመድበዉ ሁሌም እቸገራለሁ ቢሆንም ግን በራሱ መንገድ የዋርካ ጸሀይነት ባህሪ ነበረዉ .... ትህትና2 ዋዉ ትቴዉ ህምምም ምን ማለት እችላለሁ ... ሱዋቭ ....

ሪች ... አንቺንማ በአዲስ መስመር ነዉ ምጽፍሽ ... ሀሀሀ ... ፍቅር የሆንሽ ልጅ ...

ማህዲ ... ሆ ሆ ... ያንቺዉ ደግሞ ጠንከር ያለ ነበር ...

ሞኒ ...

አልማጩ ሀሪከን ...

ፓንሪዚኮ .... የሆነ ቀን ከድክሞ ጋ ሁነን እኛም እንደ ፓኑ ቢራችንን እየቀመቀምን እኔም አንዳንዴ እንደማደርገዉ ሮዝማን ላይቴን እያቦነንኩ ዋርካንና ዋርካዊያንን ስናማ .... ትክክለኛ ማንነቱን የሚገልጽ ፓኑ እንደሆነ እያማነዉ ነበር ....

ደጉ .... ሀሀሀ .... ሳናዋራ ሳንግባባ እንቀር ይሆን?

እነ ምርቃናና ቻትሩማዊያን ....
አይን ሁሉን ቢያይም አጠገቡ ያለዉን ቅንድብ አይቶ አያዉቅም ...
ሙዝ1
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 3128
Joined: Wed Feb 22, 2006 9:25 am

ወይ ዋርካ...

Postby melkam » Tue Mar 25, 2014 12:34 pm

....የቤቱ ባለቤት...ዱክ ቤቱን ከሰራው ከስድስት አመታት በሁዋላ ...ከመጨረሻው ፖስት ደሞ ሁለት አመታት አልፈው ስሜን ሰምቼ ብመጣ የሚቀየመኝ አይኖርም መቼም....ግን በጣም ብዙ ምርጥ ልጆች ያሳወቀኝ ዋርካ ቻት በጣም ደስስስ የሚል ቤት እንደነበር ብዙ መልካም ሰዎችን ያወኩበት ቦታ ስለመሆኑ እመሰክራለሁ....አሁንማ ግዜውም ራቀ እኔም እርጅና መጣና... አለ ያ ደስ የሚል ዘፋኝ....
ብዙውን ማስታወስ አቅቶኛል...በዛው ልክ አልረሳም ብሎ ውስጤ የቀረ ስንት አለ!!!... እስቲ ትንሽ ትውስታዬን ይዤ እመለሳለሁ........
melkam
አዲስ
አዲስ
 
Posts: 11
Joined: Thu Dec 16, 2004 12:25 pm

Previous

Return to Warka Intimate - ዋርካ ፍቅር

Who is online

Users browsing this forum: No registered users and 0 guests