Topics related to cultures, arts, languages, arts such as humor, music, traditional literary genres of poems, ግጥም ፣ ቅኔ ፣ ተረትና ምሳሌ)
by ዝንቱ » Thu Aug 05, 2010 5:52 pm
ደራሲ ዋናው ያንን ሰውየ እባክህ ጋብዘው:: ዊ ወንት ቱ ኖው ሞር አባውት ሂም:: ባይሆን ወጭውን እጋራለሁ::
I am black, yet beautiful!
-
ዝንቱ
- አዲስ

-
- Posts: 24
- Joined: Thu Jul 15, 2010 6:56 pm
- Location: MARS
by ዋናው » Mon Sep 27, 2010 10:10 am
ከብዙዎች ውስጥ...... ብቻን ሆነህ ለመፍዘዝ
በራስ ቅያስ ለመጥመዝመዝ
እንዳንተነትህ ላለማዘዝ
እንደርሱነቱ ላለመታዘዝ
.
.
.
ራስህን አክብረህ ስሜትህን ስታግዝ
መምሰል ተማርና
ጆሮ ብቻ ሁንና
እንዳልገባው ስማና
አንዳንዴም ሌላዉን ሁን
-ዳዴ በል እንደገና::
ጥበብ ከእኔ የበለጠ ጠንካራ ናት እኔ እንደምፈልገው ሳይሆን እሷ እንደፈለገችው ታደርገኛለች::
-
ዋናው
- ዋና አለቃ

-
- Posts: 2799
- Joined: Tue Dec 16, 2003 5:29 pm
- Location: ሕልም ዓለም
-
by ዋኖስ » Mon Sep 27, 2010 4:26 pm
ጉድ! ጉድ!
የት ከርመዉ ነው? ግን ጠምዝዘው ጠምዝዘው ያመጧት! ቅቅቅ አጀብ!
ሰላም ነዎት ግን?
ከብዙ ብዙ ሰላምታ ጋር!
ዳሞት
-
ዋኖስ
- ዋና ውሃ አጠጪ

-
- Posts: 1552
- Joined: Tue Nov 16, 2004 2:39 pm
- Location: Mars
-
by myshkin » Mon Sep 27, 2010 5:02 pm
ዋናው: "የተዋቡ እጆች" አሉህ
-
myshkin
- መንገደኛ

-
- Posts: 3
- Joined: Mon Sep 27, 2010 4:54 pm
by ዋናው » Mon Oct 04, 2010 1:46 pm
መሪጌታ እንዴት ነዎ? አይዪ ይሄ መንደር'ኮ ያደግኩበት ሁሉ አልመስልህ አለኝ ... ኸረ 'ስቲ ዋርካን ዋርካን የሚያሰኝ ምናምንቴ አጫጭሱብኝ....
myshkin ላድናቆትዎ ምስጋናዬ ይድረስዎ::
ጥበብ ከእኔ የበለጠ ጠንካራ ናት እኔ እንደምፈልገው ሳይሆን እሷ እንደፈለገችው ታደርገኛለች::
-
ዋናው
- ዋና አለቃ

-
- Posts: 2799
- Joined: Tue Dec 16, 2003 5:29 pm
- Location: ሕልም ዓለም
-
by ዋናው » Mon Oct 04, 2010 2:17 pm
ብዙ አልተቀየርክም
ፀጉርህም አልሸሸ
-ወይም አልሸበተ
ፊትህም እንዳለ ነው
-ወዙን እንዳሸተ
ቄንጤኛ ሆንክን'ጂ
-አቋምህስ መች ጎበጠ?
ዕድሜህ ቢተልቅም
-ወጣት ነው አሕምሮህ
እንደትላንቱ ያስባል
-ብዙ ዘመን ኖሮ
ጎልምሰው ለጎረመሱ
ጥበብ ከእኔ የበለጠ ጠንካራ ናት እኔ እንደምፈልገው ሳይሆን እሷ እንደፈለገችው ታደርገኛለች::
-
ዋናው
- ዋና አለቃ

-
- Posts: 2799
- Joined: Tue Dec 16, 2003 5:29 pm
- Location: ሕልም ዓለም
-
by ዋናው » Tue Nov 02, 2010 1:58 am
ዋርክዬ እኔም እንደ አያዋኖስ ከነልጆቼ ስላገኘሁሽ ደስብሎኛል ወላጅና አሳዳጊዎችሽ ልባቸው ስለራራልሽ ምስጋና ይግባቸው
ግን ለሌላ ጊዜ እንደክፉ ጎረምሳ በዛው ኩብልል ከማለት... ማስጠንቀቂያ መንገር ይልመድብሽ ምነው... ዋርኪት ሰባት ዓመታት አብረን ቆይተን አሁን መደባብቅ'ስቲ ምን አመጣው...
ጥበብ ከእኔ የበለጠ ጠንካራ ናት እኔ እንደምፈልገው ሳይሆን እሷ እንደፈለገችው ታደርገኛለች::
-
ዋናው
- ዋና አለቃ

-
- Posts: 2799
- Joined: Tue Dec 16, 2003 5:29 pm
- Location: ሕልም ዓለም
-
by sleepless girl » Tue Nov 02, 2010 5:20 pm
እሚገርም ነው ግን ከምር..........መላመድ መጥፎ ነገር ነው.......ለማንኛውም ጉድ ቱ ሲ ዩ ሂር ዋንቾ................. :wink:
Nothing is impossible!!
-
sleepless girl
- ዋና ውሃ አጠጪ

-
- Posts: 1510
- Joined: Sun Feb 19, 2006 3:56 am
- Location: near u!
by ዋናው » Fri Feb 25, 2011 2:07 pm
ፀጉርህ ሲከዳህ
-የዚህ ሃገር ውሃ... አልክ
ቦርጭ ስታበቅል
-በእሕሉ አላከክ
ይሉንታ ስትከዳ
-ስልጣኔ ነው አልክ
ለወገን መጥላትህ
-ምን ምክኒያ ሰጠክ?
ጥበብ ከእኔ የበለጠ ጠንካራ ናት እኔ እንደምፈልገው ሳይሆን እሷ እንደፈለገችው ታደርገኛለች::
-
ዋናው
- ዋና አለቃ

-
- Posts: 2799
- Joined: Tue Dec 16, 2003 5:29 pm
- Location: ሕልም ዓለም
-
by ጦምኔው » Fri Feb 25, 2011 3:59 pm
ዋናው wrote:ፀጉርህ ሲከዳህ
-የዚህ ሃገር ውሃ... አልክ
ቦርጭ ስታበቅል
-በእሕሉ አላከክ
ይሉንታ ስትከዳ
-ስልጣኔ ነው አልክ
ለወገን መጥላትህ
-ምን ምክኒያ ሰጠክ?
ሲተያዩ አንገት መድፋት
መች ሆነና ወገን መጥላት
ሠላምታዬን ካዲስነት
ፈገግታዬን ከፋርነት
............መቁጠሩ ነው
የወገኔ ከንቱነቱ
የሚያሸሸኝ ከብሽቀቱ::
-
ጦምኔው
- ዋና ውሃ አጠጪ

-
- Posts: 1529
- Joined: Sun Jan 14, 2007 10:40 pm
- Location: Right here
by ዋኖስ » Fri Feb 25, 2011 7:04 pm
የለም! የለም!
በዕርስዎ አልስማማም::
ወዲሕ ነዉ ነገሩ:
የኛ መጠላላት በጀርባ መዞሩ::
ድሮም`ኮ ከጥንት የኛ ወግ `ሚደምቀዉ:
አንድም የሠርግ ቀን ሌላም ቀብር ላይ ነው::
ከዚሕ ዉጭ አበሻ በሩቅ አይደል ፍቅሩ!!
የጎሪጥ-መንጥሮሕ መሸሽ ከሠፈሩ::
አሻግረሕ ተኩሰሕ በሩቅ እያየኸው:
ማናገር ፈልገሕ ጉዳይሕን ልትነግረዉ:
ስልኩን በእጁ ይዞ ቁጥር ተመልክቶ:
አንተነትሕን አዉቆ : ስልክህን ለይቶ:
ይጠረቅምሐል በስልክ ተንጠራርቶ::
ታዲያ! እሄ ፍቅር ነው? ይንገሩኝ ይበሉ:
መልስ ካለዎ ልስማ አንድ ሁለት ይጣሉ::
ዋናው wrote:ፀጉርህ ሲከዳህ
-የዚህ ሃገር ውሃ... አልክ
ቦርጭ ስታበቅል
-በእሕሉ አላከክ
ይሉንታ ስትከዳ
-ስልጣኔ ነው አልክ
ለወገን መጥላትህ
-ምን ምክኒያ ሰጠክ?
-
ዋኖስ
- ዋና ውሃ አጠጪ

-
- Posts: 1552
- Joined: Tue Nov 16, 2004 2:39 pm
- Location: Mars
-
by ዋናው » Tue Mar 22, 2011 1:36 am
ጦሜክስ እና አይዋ ጥሩ ምላሽ ነው::
ጥበብ ከእኔ የበለጠ ጠንካራ ናት እኔ እንደምፈልገው ሳይሆን እሷ እንደፈለገችው ታደርገኛለች::
-
ዋናው
- ዋና አለቃ

-
- Posts: 2799
- Joined: Tue Dec 16, 2003 5:29 pm
- Location: ሕልም ዓለም
-
by ዋናው » Tue Mar 22, 2011 1:43 am
የደሕና ቤተ-ሠብ
የወላጆቹን ማንነት መርምረው ጠይቀው
ከሃብታም ቤተ-ሠብ
-ማደጉን አጣርተው
የልጁን ድክመት
-አጢያቱን ሠርዘው
የደሕና ቤተ-ሠብ ልጅ ነው አሉት
-ሀብቱን ማሕረግ አርገው
ደሕና ቤተ-ሠብ
-ከሆነ የአብታም ማሕረግ?
ምን ስም ሊሠጠው ይሆን
-በድሕነትን ማደግ....?
ዋናው
ጥበብ ከእኔ የበለጠ ጠንካራ ናት እኔ እንደምፈልገው ሳይሆን እሷ እንደፈለገችው ታደርገኛለች::
-
ዋናው
- ዋና አለቃ

-
- Posts: 2799
- Joined: Tue Dec 16, 2003 5:29 pm
- Location: ሕልም ዓለም
-
by ዋናው » Tue Mar 22, 2011 1:53 am
.
እዛ ላሳደግከኝ ጋሼ
እዚህ ላገኘሁ ታናሼ
እዛ ሳለን
ደጅ አትቁም ብለህ
-'ንደታላቅ ገሰጽከኝ
አርፈህ ተማር ብለህ
-ዛሬን ናፈቅክልኝ
አንተን ባየሁ ጊዜ
-አንገቴን ደፋዉኝ
እዚህ ሳገኝህ
ተመኘሃት የእቅፌን ኮረዳ
እንደዱባ አበባ ማምሻዉን ልትፈነዳ
አልገባህም አልከኝ
-ዘመኔን አፍቅሬ ራሴን 'ንድከዳ
'ንኳንም አልገባኝ ጋሼ
ምን ሊጠቅመኝ ብዘምን
-ባንድግሬ አንክሼ
ምንስ ሊፈይደኝ
-ብቆም ከዕድሜዬ አንሼ?
ግድ የለህም ጋሼ
አሁንም ወጣት ነህ እኔ ላርጅብህና
-አንተ ሁን ታናሼ::
ዋናው
ጥበብ ከእኔ የበለጠ ጠንካራ ናት እኔ እንደምፈልገው ሳይሆን እሷ እንደፈለገችው ታደርገኛለች::
-
ዋናው
- ዋና አለቃ

-
- Posts: 2799
- Joined: Tue Dec 16, 2003 5:29 pm
- Location: ሕልም ዓለም
-
by ዋናው » Mon Jun 27, 2011 11:13 am
ቀበቶህን አጥብቅ
ወንድነትህ በዘመን 'ንዳይነጠቅ
ቀበቶህን አጥብቅ
ሱሪህ አወላክፎህ
-አጕጉል 'ንዳትወድቅ
ቀበቶህን አጥብቅ
እንደፔንግኡኢን ስትዳህ
-ልጅህ እንዳይሳቀቅ
ግዴለም ይቅርብህ
-ቀበቶህን አጥብቅ
........................ለሰሜን ለንደን 40ቲነሮች
ጥበብ ከእኔ የበለጠ ጠንካራ ናት እኔ እንደምፈልገው ሳይሆን እሷ እንደፈለገችው ታደርገኛለች::
-
ዋናው
- ዋና አለቃ

-
- Posts: 2799
- Joined: Tue Dec 16, 2003 5:29 pm
- Location: ሕልም ዓለም
-
Return to Warka Culture and Literature - ዋርካ ባህልና ሥነ ጽሑፍ
Who is online
Users browsing this forum: No registered users and 1 guest