menzewu wrote:የእማሆይ ፒያኖ ጫወታ በታም የሚመስጥና የሚያዝናና ነው. ስላመጣህው አመሰግናለሁ.
እምሆይ ጽጌ የከቲባ ገብሩ ልጅ እና የወ/ሮ ስንዱ ገብሩ እህት ናቸው. እየሩሳሌም ነው መሰለኝ አሁንም ያሉት. እጅግ ሲበዛ መንፈሳዊ እና ጥሩ እናት/እ ህት ናቸው
ሠላም menzewu
ስለአስተያየትህ አመሰግናለሁኝ
እኔም ይህ 'ቤት አልባው ከርታታ' የተባለውን የእማሆይን የፒያኖ ቅንብር ሁሌ ባዳመጥኩት ቁጥር በጣም ከመመሰጥም አልፎ ብዙ መልእክቶችን እየነገሩን እንደሆነ አስባለሁኝ
'ቤት አልባው ከርታታ' የተሰኘው ቅንብር በብዙዎች ዘንድ ተወዳጅ ቢሆንም የተወሰኑ ሰዎች ግን በሙዚቃ አይን በትክክል ያልተዋቀረና ብዙም ትርጉም የሌለው ነው ይላሉ....በበኩሌ ያለኝ የሙዚቃ እውቀት በጣም ትንሽ ቢሆንም ሙዚቃ ከኖታዎች በላይ ረቂቅ ነው ብዬ አስባለሁኝ....ህይወትስ ራሱ የተዘበራረቀ አይደል አንዴ :?: የእማሆይ ከየውብዳር እስከ ፅጌማርያም ያለው ጉዞስ በምን ቀመር ይገለፃል...በልጅነታቸው ያሳለፉት የተደላደለ አስተዳደግና የቀለም ትምህርት በስዊዘርላንድ እና በእቴጌ መነን....የግዞት ጊዜያት በጣሊያን....የሙዚቃ ትምህርት በግብፅ....የአስተዳደር ስራ በውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር እና የሙዚቃ ዳይሬክተርነት በክቡር ዘበኛ....በ19 አመታቸው አለም በቃኝ ብለው ለምነና ወደግሸን ማርያም ቀጥሎም ጎንደር ከዛም እየሩሳሌም....ይህ ነው ሙዚቃቸው :!: ወይ ለእኛ ወይ ለፈጣሪያቸው አልያም ለሁለታችንም የሆነ መልእክት በለሆሳስ እየነገሩን ያሉት......
በነገራችን ላይ የበፊቱ በአሜሪካ የኢትዮጵያ አምባሳደር የነበሩት ዶ/ር ሳሙኤል አሰፋም የእማሆይ እህት የወ/ሮ ስንዱ ገብሩ ልጅ ናቸው
ከምስጋና ጋር