የአማርኛ ስነ ጽሁፍ ስብስቦች በድረ ገጽ

Topics related to cultures, arts, languages, arts such as humor, music, traditional literary genres of poems, ግጥም ፣ ቅኔ ፣ ተረትና ምሳሌ)

Re: ወሸላ...

Postby ሾተል » Thu Jul 14, 2011 12:55 am

ቅዥቢው wrote:ሾተል ሁለት አፍ ያለው ሰይፍ ማለት ነው::አምባቸው ሾተል ግን ሁለት አፍ ያለው እንከፍ ነው::ሾተል እውነት እውነት እልሃለሁ የቁም በድን ነህ...በአንድ ራስ ሁለት ምላስ ባንድ ጭልፋ ሁለት ድስት ባንድ እግር ሁለት አገር...አየ ያንተ ነገር::ለነገሩ የእግርህ ነገር ከተነሳ 'ንኳ ቁላህ ቢጨመር ስድስት እግር ያለው አጂፕ እንደ ማለት ነው...የወላሞ ቁላ...
ለማንኛውም በአገር ቤት ጉዞህ ወቅት ጠንቀቅ በል...የአዋሳው ገብርኤል ርዕስ ደብር መምሬ እንዳይላሉ ጎሽሜ የጉዞህን ዜና ሰምተው:"ሾተል የተባለ የሽንት ቤት መወልወያ የመሰለ የፈረንጅ ሽንት ቤት ወልዋይ ወላዋይ ወሸላ የነምሳ ነቀርሳ ወደ አዋሳ እየመጣ ነውና በተገኘበት እንደ እብድ ዉሻ ተቀጥቅጦ እንዲገደል"በማለት ትእዛዝ ማስተላለፋቸውን "አሞራ ገደል"የተሰኘው ሳምንታዊ ጋዜጣ ምንጭ ጠቅሶ ዘግቧል...እናም ጠንቀቅ...ውይ ቅዥቢው ....ሰደብከኝ በቃ ?እኔ ደግሞ እንደፉከራህ ጉድ ታፈላለኽ ብዬ ሳበቃ የህጻን ስድብ መለማመጃ ታደርገኝ ?አንጎለ ህጻን ::

እኔ ነኝ ያለች ቺክ እየነጨሁ ምን አይነት ቱባ ዱባ ስድብ ያዥጎደጉድብኝ ይሆን ብዬ ስጠብቅ ስድብ የሚመስል ነገር ትሞነጫጭር ?ይድፋኽ .....ክፍት ቂጥ ::

ብለን ካንተ ጋር ያለኝን ንትርክ ለጊዜው ላቁምና የዛሬ ከችካኔ ጋር ያሳለፍኩትን ጨዋታ በጢቆው ላጫውትኽ ::

በቃ የገባት ያራዳ ልጅ ጡተ አጎጥጉጤ ነበረችና መቼም ያራዳ ልጅ ይግደለኝ አይደል የሚባለው በቃ እኔ ሁሉንም ነገር ሳደርጋት እሷ ከስሜቷ ጋር ሆና ለታሪክ ለሁለታችንም ይቀመጥ ዘንዳ በሞባይል ስልኩዋ ፊልም ትቀርጽ ነበር ::እኔም እንደዚሁ ::እንደገና በሌላ ዳይሜንሽን ደግሞ ሌላ ካሜራ ::እንደተነጋገርነው ሁለታችንም የቀረጽነውና ከገጠምናቸው የተለያዩ ካሜራዎች የተቀረጹትን ፊልሞች በጉደኛው ኢዲት አድርገን የብድ 3D ፊልም አድርገነው በቃ እnEና እሷ የስሪ ዲ መነጽር አድርገን በሌላ ቀን ፊልሙን እናየዋለን ::

አቤት አጎጥጉጤ ....አቤት ጥእምናው ወደር የሌለው በጄልም እንደጉድ ቸስ ማለት የሚያስቸግር ፑናኒ ::ዛሬ አለሜን አሳየችኝ ::እኔም ጁፒተሯን አሳየሁዋት ነው የሚባል እንጂ እንደ ሙናዬ በምኞት ፈረስ እየጋለቡ ያልተፈጠረ የቢሆን አለም ታሪክ መጻፍ አይደለም::ወንድ የሆነ ግዳጅ ይጥላል::አርክቶ ያረካል::አስደስቶ ይደሰታል::ቀኑን ከቀኗ ጋር ደብሎ ቀናቸው ያደርጋሉ::ቆይ እስቲ ከብድ በላይ ምን አለም አለ?

እረ ቆይ ማነው ሙናዬ የሚሉት ከናቱ ጋር ለሀሜት ተዘርፍጦ የሚቀመጥ ወንዱ ሴቱ የሴት አንቴና ዛሬ እንዳሸነው ሲነሳ ሲወድቅ የአንቴናውን ባለቤት ስናንቀጠቅጣት ...ስናስጮኻት ....ስናስነዝራት እንደዋልነው አድርጎ የማያውቅ ከብታችን ትላንት በጻፈው ጽሁፍ ክብርነታችሁ ሴት አይነጭም ሲል ነበር ....ምልክ አለ አይደል ስቲል እስካሁን ባይ ዘወይ ኤንይ ወይስ ኦቨር ኤጇን በቅርብ ጊዜ ውስጥ ያወጀች ገና ያልታሸሽ ቺክ እንደ ባግዳድ እንደተቆጣጠርን ያውቅ ዘንድ በቅርብ ሰአት ውስጥ ፎቶ ለጥፈንለት ግብረ መዳፍ ወ እጀ ጭፍጭፍ አለም ውስጥ እንከተዋለን ::ይኽ አንተንም ስለሚመለከት ዋናው እጅኽ ውሎ ይግባ እንጂ ወሲበ መዳፍ ትፈጽም ዘንድ ፎቶውን እንድታይ እንፈቅድልሀለን ::

ማን ይፈራል ፑናኒ ማን ይፈራል ...ማን ይፈራል ከ ቆነጃጅት ጋር መዋል ማን ይፈራል ....ማንም ቺክ ብትሆን እምቢ አትለንም ማን ይፈራል ?ጅንጀና ውሎ ይግባ ::ጸባይ ውሎ ይግባ ::ድፍረት ውሎ ይግባ ::አጀናጀኑ እኮ ነው ሰውን የሚያሰጥ ....አደራረጉ እኮ ነው በደስታ የሚያስደግም...እንደገና የሚያስደግም....በስተመጨረሻ ኪሎ ቀንሶ ተንጠራርተው የጻፉት አንድ ቁጥር መሆን ነው::..እህ እኅ እህ እኅ ...

ለፎቶው እንመለሳለን ::

በዚህ አጋጣሚ እንሰት እንሰሳው ልትነጭ ነው ብለኽ የጠየቅከን ምን መንጨት ብቻ ሁለታችንም የፖርኖ ስታር ሆንን ...እራሳችንን እየቀረጽንና እየተቀራረጽን ነው የዛሬው ደግሞ ::ገቢቶ ነገር ያራዳ ልጅ ስለነበረች በቃ ምኑ ቅጡ .....ያልቀረጽነው ድርጊትና ቦታ የለም ::

ሾተል ነን .........እንኩዋን ወዳገርቤት ለመሄድ ቀኑን ያስቀየርነው ::ፍሬሽ መሽኛሽ ወርቅ ያመልጠን ነበር ::ፍሬሽ ስንል በእድሜ ሳይሆን በፑናኒ ጽዳትና አጠባበቅ እንዲሁም እንክብካቤም ጭምር ነው ::ልጅት ለትማስ ወርቋ ያደረገችው እንክብካቤ ኤ ፕላስ ያሰጣታል ::ለዛውም ህጋዊ የእድሜ ነጻነቷን ያወጀች .......እንኩዋን የተፈጠርን ::እንኩዋን አንቡላና ትንባሆ ሳይሆን የሴት ብልት ያስወደደን ...እንቋቅ ድድድድድድድድድ....ነው ያለው መለስ?እኛም እንቋእ...ትትትትትትት
_________________
እሰይ ተመስጌን አምላኬ ለካስ በክብርነቴ እራሴን ሆኜ እኔነቴን ፈልጌ አግኝቼዋለሁ !?
ሾተል
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 9653
Joined: Thu Jan 13, 2005 9:42 pm
Location: Vienna-Austria

Re: ወሸላ...

Postby እንሰት » Thu Jul 14, 2011 6:15 am

ሾተል wrote:ሾተል ነን .........:ልጅት ለትማስ ወርቋ ያደረገችው እንክብካቤ ኤ ፕላስ ያሰጣታል ::
_________________

ደሞ ብለህ ብለህ የሌል አማርኛ ታወራ ጀመር ደሞ ትማስ ወርቅ ምንድን ነው? ከመቸ ወዲህ ነው ወርቅ የሚማሰው? ከተማሰማ ምኑን ወርቅ ሆነ? አፈር ነው አትልም... አይ አማርኛ ፈጣሪ
እንሰት
ውሃ አጠጪ
ውሃ አጠጪ
 
Posts: 1213
Joined: Sun Jan 30, 2005 1:14 am
Location: united states

የእስልምና መጻህፍት

Postby እንሰት » Mon Jul 18, 2011 4:34 pm

ቴክኖሎጂ ምስጋና ይግባውና በምንም አጋጣሚ ልናገኝ የማንችላቸውን መጻህፍት እጃችን እንዲገቡ አስችሎዋል::

ስምንት በአማርኛ የተጻፉ እንዲሁም በትግሪኛና በሶማሊኛ የተዘጋጁ መጻህፍትን ከዚህ ድረ ገጽ ያግኙ::

[url]http://www.islamicbook.ws/armenian/
[/url]
[url]http://www.islamicbook.ws/tigrinya/
[/url]
[url]http://www.islamicbook.ws/somali/
[/url]

Eight freely downloadable amharic books
The islamicbook is a website that facilitates access to islamic

books that are freely readable over the Internet. It also aims

to encourage the development of such online books, for the

benefit and edification of all.
እንሰት
ውሃ አጠጪ
ውሃ አጠጪ
 
Posts: 1213
Joined: Sun Jan 30, 2005 1:14 am
Location: united states

ሀመር መጽሄት በድረ ገጽ

Postby እንሰት » Mon Jul 18, 2011 4:45 pm

ሁለቴ ሰላምታ አንዱ ለነገር ነው ቢባልም እኔ ግን በሰላም ነው ብቅ ያልኩት:: ማህበረ ቅዱሳን ለረጅም ጊዜ ሲያዘጋጀው የነበረውን ሐመር መጽሄትን ከነግምጃ ቤቱ በድረ ገጽ እነሆ ብሎናል::

ማያያዣው ከነዜናው

[url]http://hamer.eotc-mkidusan.org/index.php?option=com_content&task=blogcategory&id=83&Itemid=67
From 1985 onwards
[/url]ለ18 ዓመታት ትምህርተ ሃይማኖታዊ ክርስቲያናዊ ሕይወትን፣ ማኅበራዊ ኑሮንና ሌሎች ተያያዥ ጉዳዮችን ምዕመኑን ስታስተምር የዘለቀችው ሐመር መጽሔት ለራሷ የሚያገለግል መካነ ድር ተዘጋጀላት፡፡የመካነ ድሩም አድራሻ(URL) http://hamer.eotc-mkidusan.org ነው።

በቀደመው ጊዜ ብዙ የተደከመባቸውና ዋጋ የተከፈለባቸው የኅትመት ውጤቶች ምዕመናን እንዲጠቀሙበት ታስቦ እንደተሠራ በማኅበረ ቅዱሳን የኤሌክትሮኒክስ ሚዲያ ሓላፊ ዲ/ን ዘላለም ቻላቸው ተናግረዋል፡፡

ለወደፊቱም የሚወጡትን የመጽሔቷን ዝግጅቶች በሽፋን /cover/ ገጽ በማስተዋወቅ ሥርጭቷን ከፍ የማድረግና በዚህም ስብከተ ወንጌልን የማስፋፋት ተልዕኮን የበለጠ ማሳለጥን ዓላማ ያደረገ እንደሆነ የገለጹት ዲ/ን ዘላለም ቤተ ክርስቲያን በየዘመናቱ የጽሕፈትና የመገናኛ ቴክኖሎጂውን በቀዳሚነት ስትጠቀም ቆይታለች፡፡ አሁን ደግሞ የሰዎች ኢንተርኔትን የመጠቀም እውነታ ቤተ ክርስቲያንን ተወዳዳሪ ሊያደርጋት ይገባል በማለት አያይዘው አስረድተዋል፡፡

source:http://www.eotc-mkidusan.org/site/index.php?option=com_content&task=view&id=704&Itemid=1
እንሰት
ውሃ አጠጪ
ውሃ አጠጪ
 
Posts: 1213
Joined: Sun Jan 30, 2005 1:14 am
Location: united states

አማርኛ እና የኢትዮጵያ አንድነት

Postby እንሰት » Fri Jul 22, 2011 7:23 pm

ሰላም ሰላም
ፍትህ ጋዜጣ በድረ ገጽ
http://www.fetehe.com/

ለቅምሻ ያህል

አማርኛ እና የኢትዮጵያ አንድነት

በሙሉነህ ወ/ትንሳኤ

ኢህአዴግ ኢትዮጵያን ከተቆጣጠረ በኋላ አሉታዊ የሚባሉ እርምጃዎችን መውሰዱ የሚታወቅ ነው፡፡ ከነዚህም መካከል በእኔ እምነት ዋና ዋናዎቹን ለማስታወስ ያህል ኤርትራን አስገንጥሏል፤ ኢትዮጵያን ወደብ አልባ አድርጐአል፤ ህዝቧን በጐሳ ከፋፍሎ ለእያንዳንዱ ብሔረሰብ ..የመገንጠል መብት.. ሰጥቶአል፡፡ ብዙ ጊዜ የማይጠቀሰው ኢህአዴግ ሌላው ሀገሪቱን ለማዳከም ወስዷቸዋል ብዬ ከማስባቸው ስልቶች መካከል የአማርኛ ቋንቋን ማዳከም ነው፡፡
የአማርኛ ቋንቋ የሺ ዓመታት የእድገት ታሪክ ያለው የኢትዮጵያ ብሔረሰቦች የእርስ በእርስ መግባቢያ ቋንቋ (Lingua Franca) ነው፡፡ የቋንቋ ተመራማሪው ግርማ አውግቸው ደመቀ ስለ አማርኛ ቋንቋ እንዲህ ብሎ ጽፎአል፤
“Amharic has served as lingua Franca in the multilingual Ethiopian nation for more than a millennium… Amharic is the second most widely spoken Semitic language next to Arabic. According to the latest reports, Amharic is spoken approximately by 80 percent of the Ethiopian population as a first and second language” (The Origin of Amharic, 2009)::
ይህ ወደ አማርኛ ሲመለስ የአማርኛ ቋንቋ የብሔረሰቦች የእርስ በእርስ መግባቢያ ቋንቋ በመሆን ከአንድ ሺ ዓመታት በላይ ያገለገለ ሲሆን ከኢትዮጵያ ህዝብ ሰማኒያ በመቶው በአፍ መፍቻ ቋንቋነት እና እንደ ሁለተኛ ቋንቋ ይጠቀምበታል ማለት ነው፡፡ ከአንድ ሺ ዓመታት በፊት አማራ የሚባል ብሔረሰብ ለመኖሩ ማረጋገጫ ለማግኘት እጅግ አስቸጋሪ ነው፤ ይሁን እና እነ አቶ መለስ ዜናዊ አማርኛ የአማሮች ቋንቋ ነው በሚል እሳቤ ይህን ከፍተኛ የባህላዊ እድገት ውጤት የሆነውን የብሔረሰቦች የእርስ በእርስ መግባቢያ ቋንቋ (Lingua Franca) ለማዳከም የረቀቀ አሉታዊ ስልት እንደቀየሱ መገመት ይቻላል፡፡ ሰኔ 4/2003 በወጣው ..አውራምባ ታይምስ.. ጋዜጣ ላይ አቶ መለስ በ1982 በቅርቡ ከዚህ ዓለም በሞት ከተለዩት ፓል ሄንዝ ጋር ባደረጉት ምስጢራዊ ውይይት ላይ ..የአማራ የበላይነት ማክተም አለበት.. ብለው እንደነበር ተገልጿል፡፡ በጣም የሚገርመው እንደ ቃለመጠይቁ ከሆነ አቶ መለስ አማሮችን ጨቋኝና ተጨቋኝ ብለው ለመከፋፈል መሞከራቸው ነው፡፡ በዚህም መሰረት ከአማሮች መካከል በተለይ በሸዋ አማራ ላይ አነጣጥረዋል.. የብሔር አመለካከት ከሆነ መላ ብሔሩን (አማሮችን በሙሉ) ማቀፍ ሲገባው የሸዋ አማራ ላይ ማነጣጠራቸው ራሱ አንድ ችግር እንዳለ ያሳያል፡፡ ጠ/ሚኒስትሩ የሚጠሉት ብሔሩን ሳይሆን የሸዋን ህዝብ ነው እንዴ ብዬ እንድጠይቅ አስገድዶኛል፡፡ ይህ ደግሞ ከረጅሙ የኢትዮጵያ ታሪክ ስናየው በጐጃም፣ በጐንደር፣ በሸዋ፣ በትግራይና በወሎ መካከል የነበረውን የውስጥ የስልጣን ሽኩቻ ያስታውሰኛል፡፡
በአሁኑ ጊዜ አማርኛ ተጠናክሮ የሚነገርባቸው የጐሳ ክፍሎች አማራና ደቡብ ሲሆኑ በከተሞች ደግሞ አዲስ አበባና ሐዋሳ ናቸው፡፡ በሌላ በኩል በትግራይ፣ በኦሮሚያ፣ በአፋር፣ በሶማሊያ ወዘተ የአማርኛ ቋንቋ እየተዳከመ መጥቷል፡፡ እርግጥ በሁሉም ክልሎች አማርኛ እንደ አንድ ትምህርት ሆኖ ይሰጣል፤ ግን አጠቃቀሙ በእጅጉ ስለቀነሰ ተዳክሞአል፡፡ አማርኛ ሁሉንም የኢትዮጵያ ብሔረሰቦች በኢትዮጵያዊነት ጥላ ስር አሰባብስቦ አንድ ህዝብ ለማድረግ ያደረገው አስተዋፅኦ በታሪክ እጅግ ከፍተኛ ነው፡፡ ይህንን ታሪካዊ የጋራ ባህል ግንባታ ሂደት ለመቀልበስ አማርኛ የአማሮች ቋንቋ ነው በሚል የተሳሳተ ግንዛቤ ኢህአዴግ ቋንቋን መሰረት ባደረገው የፌደራል ስርዓት ውስጥ አደጋ ላይ የሚጥል አስተሳሰብ መሆኑ ተደጋግሞ የተነገረ ጉዳይ ነው፡፡ ነገሩን ይበልጥ ግልፅ ለማድረግ እስኪ እዚህ ላይ አቶ መለስ እና ፓል ሄንዝ ያደረጉትን ውይይት በከፊል እንጥቀስ፤

ፓል ሂንዝ፡- የነገዋን ኢትዮጵያ እንዴት ትገልፃታለህ?
መለስ፡- ህዝቦቿ የራሳቸውን መብት በራሳቸው እንዲወስኑ መብቱ ሊሰጣቸው ይገባል፡፡ የአማራ የበላይነት ማክተም አለበት፡፡
ፓል ሄንዝ፡- የአማራ የበላይነት ስትል አልገባኝም? የአንተ አመለካከት ይህ ከሆነ በቅርቡ በትጥቅ ትግል የተቆጣጠራችኋቸው አካባቢዎች አሉ (ላስታ፣ ጋይንት፣ ሳይንት፣ መንዝ፣ መራቤቴና ሌሎቹን መጥቀስ ይቻላል..፡፡ በእነዚህ አካባቢዎች የሚኖሩ ህዝቦች አማሮች አይደሉምን?
መለስ፡- እነዚህ የተጨቆኑ አማሮች ናቸው፡፡ ስለአማራ የበላይነት ስንነጋገር የሸዋ አማራ ማለታችን ነው፡፡ አንድ ህዝብ በሌላው ህዝብ ላይ የበላይነቱን የሚያሳይበት ሁኔታ ማክተም አለበት (ምንጭ አውራምባ ታይምስ ሰኔ 4/2003..፡፡
ከላይ እንደተመለከተው ከአንድ ሺ ዓመታት በፊት አማራ የሚባል ብሔረሰብ ለመኖሩ ምንም ማረጋገጫ የለም፤ በመሆኑም አማርኛ የአማሮች ቋንቋ ነው ለማለት የሚያስችል ተጨባጭ ማስረጃ የለም፡፡ በአስራ ስድስተኛው ክፍለ-ዘመን መጀመሪያ ላይ የተሰራ ካርታ ባሺሎ (Bashilo) ወንዝ አካባቢ አማራ የሚባል አውራጃ መኖሩን ያሳያል፡፡ ይሁንና ይህ አካባቢ ጐጃምን፣ ቤጌምድርን፣ ላስታንና ሌለ የአማራ አውራጃዎች የሚባሉትን ስፍራዎች የሚያካትት አልነበረም፡፡ አማራ የሚባል ብሔረሰብ ከነበረ ይህ ብሔረሰብ የተፈጠረው አማርኛ ከተፈጠረ ከብዙ መቶ ዓመታት በኋላ መሆን አለበት.. አማርኛን የአማራ ቋንቋ ነው ከማለት ይልቅ የአክሱማውያን ወራሾች ቋንቋ ነው ማለቱ ይቀላል፡፡ በዚህ እሳቤ መሰረት አማርኛ የሳቢያንና (Sabean) የግዕዝ ወራሽ ቋንቋ፣ ኢትዮጵያ ደግሞ የአክሱምና የአቢሲኒያ ወራሽ ሀገር ናት ማለቱ ያስኬዳል..
በመሆኑም አማርኛ የሚዛመደው ከኢትዮጵያዊነት ጋር እንጂ ከአማራዊነት ጋር አይመስለኝም.. አቶ መለስ ለሸዋ አማሮች ጥሩ አመለካከት የላቸውም ማለት አማርኛ ቋንቋ ላይ ተፅዕኖ ማድረግ አለባቸው ማለት አይደለም፡፡ ለዛውስ የሸዋ አማሮች ያሏቸው የሸዋ ኦሮሞዎችን አለማካተታቸውን እንዴት ማረጋገጥ ይቻላል? በእኔ እምነት ይህ ሁሉ የሚያመለክተው ኢህአዴግ የፖለቲካ ርዕዮት የተመሰረተባቸው ፅንሰ ሀሳቦችና መርሆዎች በጣም ደካማ መሆናቸውን ነው፡፡ ኢህአዴግ ደካማ ርዕዮት ኢትዮጵያዊነትን ለሺ ዓመታት ተሸክሞ ለአሁኑ ትውልድ ያደረሰውን የአማርኛ የባህል መቀነት በጣጥሶ እንዲጥለው መፍቀድ ያለብን አይመስለኝም፡፡ ያለምንም ተጨባጭና አሳማኝ ማስረጃ የአማራ ብሔረሰብን ..አውራ ጨቋኝ ብሔር.. ነው ብሎ መፈረጅ አግባብ አይመስለኝም፡፡ በተመሳሳይ ..የጨቋኞች ቋንቋ.. የሚፃፍበት ነው ብሎ የግዕዝ ፊደል ለኢ ትዮጵያውያን ባዕድ በሆነው ላቲን (Latin) ፊደል እንዲተካ ፈቀደ (ለሚፈልጉ ብሔረሰቦች ..፡፡ እድሜ ከሰጠን ኢህአዴግ የያሬድን ሙዚቃ፤የዘርያዕቆብን ፍልስፍና ደግሞ በምን እንደሚተካው ለማየት እንበቃ ይሆናል.. ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር.. ቸር ይግጠመን..

source: http://www.fetehe.com/mulunhe%20144.html
እንሰት
ውሃ አጠጪ
ውሃ አጠጪ
 
Posts: 1213
Joined: Sun Jan 30, 2005 1:14 am
Location: united states

Re: የእስልምና መጻህፍት

Postby እንሰት » Fri Aug 12, 2011 3:52 pm

እንሰት wrote:ቴክኖሎጂ ምስጋና ይግባውና በምንም አጋጣሚ ልናገኝ የማንችላቸውን መጻህፍት እጃችን እንዲገቡ አስችሎዋል::

ስምንት በአማርኛ የተጻፉ እንዲሁም በትግሪኛና በሶማሊኛ የተዘጋጁ መጻህፍትን ከዚህ ድረ ገጽ ያግኙ::

[url]http://www.islamicbook.ws/armenian/
[/url]
[url]http://www.islamicbook.ws/tigrinya/
[/url]
[url]http://www.islamicbook.ws/somali/
[/url]

Eight freely downloadable amharic books
The islamicbook is a website that facilitates access to islamic

books that are freely readable over the Internet. It also aims

to encourage the development of such online books, for the

benefit and edification of all.

ዛሬም እንደ በቀደሙ እስልምናና ታሪካችንን እያዛመደ አክብሮት የሚሰጣቸው መጣጥፎች ከዚሀ ድረ ገጽ ያንብቡ::
[url]<http://www.asehama.com[/url]

ለመግቢያ ያክል ስለ አባ ጅፋር የተጻፈውን እነሆ!

ለ57 ዓመታት ህዝብና ግዛታቸውን በዲን ያስጠበቁ ንጉስ

ፈገግታና ቀልድ አይለያቸውም፡፡ መዝናናትና ማዝናናት ይወዳሉ፡፡ የባህል ስፖርት ውዳጅ ናቸው፡፡ በተለይማ በፈረስ ጉግስ ጎበዝ ናቸው፡፡ በወቅቱ ከንጉሶች የሚወዳደራቸው አልነበረም፡፡ በዚህ የተማረኩት አፄ ሚኒሊክ እንኳ ሸልሟቸዋል ይባላል፡፡ የጦር ውርወራና የገና ጨዋታም ይወዳሉ፡፡ ከዚህ ውጪ በጣም ቸርና ደግ እንደነበሩ ተመስክሮላቸዋል፡፡ ለተቸገረ ያዝናሉ፡፡ ማዘን ብቻም አይደለም ወደ እሳቸው የቀረበ ችግርኛን ዳግም የድህንነት ችግር እንዳያገኘው አድርገው ያቋቁሙታል፡፡ ችግርና ድህንነት ያገኘውን ሰው ከዚህ ሁኔታ ካላወጡ ያማቸዋል፡፡ የህሊና ረፍት አያገኙም፡፡ እናም ሳይለግሱ አይሰነብቱም፡፡ እርዳታ ሲያደርጉ አይሰስቱም፡፡ እለታዊ ችግር መፍቻ ሳይሆን በዘላቂነት ከድህነት ለመውጣት የማያበቃ መቋቋሚያን በመስጠት የሚረኩ ንጉስ ናቸው፡፡ እናም ድህነት ያገኘው ሰው ወደ እሳቸውሲመጣ ርስት፣ በቅሎ፣ ፈረስ፣ አህያ፣ ልብስና፣ ሙሉ የቤት እቃ ይሰጠዋል፡፡

እንደንጉስ ኩራትና ማንአለብኝነት አይሰማመቸውም፡፡ በእኩልነት፣ በሠላም፣ በፍትህ፣ በመፋቀርና በመዋደድ ላይ የተመሰረተ ማህበረሰብ ለመፍጠር ያደረጉት ጥረት በወቅቱ ከነበሩ የኢትዮጵያ ንጉሶች ሁሉ ለየት ያደርጋቸዋል፡፡ የእሳቸው ቤተሰቦችም ከህዝቡ ጋር ተቀላቅለው በነፃነት ይኖራሉ፡፡ እንደማንኛውም ህዝብ ወንዝ ወርደው ልብሳቸውን በእንዶድ ያጥባሉ፡፡ ይህም በንጉስነታቸው ከህዝቡ የተለየ እርከን እንዲኖራቸው ካለመፈለጋቸው የመነጨ ነው፡፡ አስተዳደጋቸውም ሆነ ንግስናቸው ከህዝብ ጋር ነበርና፡፡

እኚህ ንጉስ የተወለዱት በኢትዮጵያ አቆጣጠር 1860 ነበር፡፡ ከእናታቸው ጌኔ ጉማይቲ እንደተወለዱ መሐመድ የሚል ስም ወጣላቸው፡፡ ይህ የትውልድ ስማቸው ነው፡፡ ትንሽ አደግ እንዳሉ ደግሞ በአገሬው ባህል መሰረት የልጅነት ስም ወጣላቸውና ቱላ ተባሉ፡፡ ቱላ ማለት ረጅም ወይም ትልቅ ተራራ እንደማለት ነው፡፡ በኦሮምኛ፡፡ የልጅነት ስም ከባህሪና ከቁመት እንዲሁም ከመልክ ገፅታ ጋር በተያያዘ ማውጣት ባህል ነበር፡፡ እናም እሳቸው ቱላ የተባሉት ረጅም ቁመት ስለነበራቸው ነው፡፡ ስስተኛና የመጨረሻ ስማቸውን ያገኙት 15ዓመት ሲሞላቸው ነበር፡፡ በዚህ ወቅት የሚሰጠው ስም ከማዕረግ ጋር የተያያዘ በመሆኑ እሳቸውአባ ጅፋር ተባሉ፡፡ ጅማ ሲነሳ አባጅፋር መነሳታቸው አይቀርም፡፡ ዛሬም ድረስ ጅማና አባጅፋር የአንድ ሳንቲም ሁለት ገፅታ ናቸው፡፡

የጅማው ንጉስ አባጅፋር የሚታወቁባቸው ዋናዋና ጉዳዮች አሉ፡፡

በንግድ ከጎረቤት አገሮች ጋር በነበራቸው ግንኙነት ፖሊሲያቸው፣ የእስልምና ዲን እውቀት እንዱስፋፋ በማድረጋቸው፣ የእደጥበብ እነጨትና ብረታ ብረት ሙያ ስራን በማጠናከርና በማስፋፋት ረገድ እጅግ በርካታ ስኬታማ ተግባራትን አከናውነዋል፡፡ እናም በኢትዮጵያ እስልምናን በማስፋፋት ረገድ የነበራቸውን ሚና ለአንባብያን ለማካፈል ወደድን፡፡

የጅማ አስተዳደርን የመሰረቱት የአባጅፍር እናት ጌኔ ጉማይቲ እንደነበሩ ይነገራቸዋል፡፡ እስልምናን ወደ ጅማ ያስገቡት የጎንደር መሻኢኮች ናቸው፡፡ መሻኢኮቹ በወቅቱ የጎንደሩ ንጉስ አፄ ዩሀንስ አስተዳደር ስላልተመቻቸው ወደ ጅማና ወደ ሌሎች ምዕራብ ኢትዮጵያ አካባቢዎች በመፍለሳቸው ምክንያት ኃይማኖቱን ይዘው መጡ፡፡ በዚህ ወቅትም ጌኔ ጉማይቲ ጥሩ አቀባበል እንዳደረጉላቸው ይታወቃል፡፡ ጥሩ የዲን መሠረት ነበራቸውና መሻኢኮች እስልምናን በግዛታቸው እንዲያስፋፉ አስፈላጊውን ድጋፍ ሁሉ ያደርጉላቸው ነበር፡፡

ይህን ተከትሎ ጌኔ ጉማይቲ በኢትዮጵያውያን አቆጣጠር በ1875 የጅማን አስተዳደር ለልጃቸው አባ ጅፋር አስተላለፉ፡፡ ከዚህ ጊዜ ጀምሮ አባጅፋር እስልምናን ለማስፋፋት የዲን እውቀትን በሁሉም የጅማ ግዛቶች አካባቢ ለማስፋፋት የሚያስችሉ ተግባራትን በማከናወናቸው ታላቅ ተቀባይነትን አገኙ፡፡ በግዛታቸው በሚገኝ በእያንዳንዱ ወረዳ መስጊድና የመድረሳ ትምህርት ቤቶችን አቋቁመዋል፡፡ በየመድረሳው የቁርአን፣ፊቂህ፣ ሲረቱል ነበውያ የመሳሰሉ ሃዲሶችን የሚያስተምሩ ሼኮች ከሌሎችን ከሌሎች የአገሪቱ አካባቢዎች ለማሰመጣት የዲን ትምህርት እንዲስፋፋ አድርገዋል፡፡ ከምፅዋ፣ይፋት ዳናና ሌሎችም አካባቢዎች ላስመጧቸው ሼኮች ርስት፣የቤት ሰራተኛ የአመት ቀለብና አልባሳት በመመደብ ጭምር ዕውቀት እንዲስፋፋ ያላቸውን ፍላጎት አሳይተዋል፡፡ የተለያዩ ኪታቦችንና ሃዲሶችን ከግብፅ፣ አል አህዛር፣ ዛንዚባር፣ ሂጃዝና የመን በማስመጣት የዲን እውቀትን 㗹ዳርሰዋል፡፡ወደ ቤተ መንግስታቸው የሚመጡ የወረዳ አስተዳዳሪዎችም እስልምናን ከማስፋፋት አንፃር የሰሩትን ስራ ከመጠየቅ ጀምሮ አመራር እስከመስጠት ቁርጠኛ አቋም እንደነበራቸው የሚነገርላቸው አባጅፋር የዲን ትምህርትን ከማስፋፋትአንፃር የላቀ ውጤት ያመጡትን አስተዳዳሪዎች በመሸለም ያበረታታሉ፡፡

በተጨማሪም በወቅቱ የጅማ ክፍለ ሃገር ዋና ከተማ በሆነችው ጅሬን አንድ ትልቅ የዲን ትምህርት ማእከል በማቋቋም ከየወረዳው የመጡ የዲን ተማሪዎች ጠንካራ የተደራጀ እውቀት እንዲጨብጡ አድርገዋል፡፡ አባጅፋር በቤተመንግስታቸው ጎበዝ የዲን ተማሪዎችን በማስጠራት ያበረታታሉ፡፡ በተለይ ቁርአን የሃፈዙ (ተሃፊዘል ቁርሃን) ለሆኑ የቅኔ መቀበያ የሚባለውን የቤተመንግስታቸውን ሽልማት ይሰጣሉ፡፡ ሽልማቱ እስከ 100 የማርትሬዛ ዶላር የደረሰ ነበር፡፡ ይህ ደግሞ በአሁኑ ዘመን የኢትዮጵያ 100ሺብር ማለት ነው፡፡ ሃዲስ የሸመደዱ የነብዩን (ሰ.ዐ.ወ) ታሪክ በግጥም የሚያቀርቡ ወ.ዘ.ተ የዲን ተማሪዎችንም በመሸለም ያበረታሩ ነበር፡፡

የአገሬው ሰው በኢባዳ እንዲበረታቱ በማድረጋቸው በየመስጊዱ ከኢሻ ሰላት ስግደት በውኃላ ልዩና ቋሚ የሆነ የኢባዳ ፕሮግራም ይዘጋጅ እንደነበርም ይነገራል ፡፡

እስከ ፈጅር ወይም (ሱብህ) ሰላት መዳረሻ ድረስ ሌቱን ሙሉ ይደረጉ ከነበሩት ኢባዳዎች መካከል ቁርአን መቅራት፣ሰለዋት፣እስቲግፋርና ተውበት፣የተሰቢህ ተህሊልና ተህሚድ ዚክሮችን በጋራ ወይም በጀመአ ማስተጋባት ዋና ዋናዎቹ ነበሩ፡፡

ከሱቢህ ሰላትበኃላ በሚዘጋጅ የቡና ስነ ስርዓት ሌሊቱን ቁርአን የሃፈዙ ካሉ የማበረተቻ ሽልማት የሳጣቸዋል፡፡ ይህ ሁሉ የአባጃፍር ጥረት የእስልምና ኃይማኖት እንዲስፋፋና ጥሩ ዲን ያለው ማህበረሰብን ለመገንባት የተደረገ ነው፡፡ በዚህም ተግባራቸው ህዝቡ በወቅቱ ለነበረው የእሳቸው አስተዳደር ልዩ ፍቅር እንደነበረው ይነገራል፡፡

ኢስላም የሚያስተምረውን መልካም ስነ ምግባር በህዝባቸው ዘንድ በማስረፃቸው እንደ ዝሙት፣ ስርቆት፣ክህደት፣ግድያ፣የመሳሰሉ ወንጀሎች አይፈፅሙም፡፡ በይዞታና በአንዳንድ ማህበራዊ ግንኙነቶች የሚፈጠሩ አለመግባባቶችን የሚፈቱት ሹራ በመቀመጥ ነው፡፡ በዚህ ሹራ አማካይነት መልካም ምክሮችን ውይይቶችን ያደርጋሉ፡፡ መፍትሄም ያገኛሉ፡፡ በአስተዳደር ደረጃም በየወሩ ቋሚ የሆነ ስብሰባ በሁሉም ቀበሌዎች ይደረጋል፡፡ ችግሮቹ ካሉ መፍትሄ ይሰጥባቸዋል፡፡ የተጣላ ካላ ይታረቃል፡፡ የታረቀ ይሸለማል፡፡ ለዚህም ነው አባጅፋር የሰላም ንጉስ የሚባሉት፡፡ በሰላም፣በፍቅርና፣በመዋደድ ላይ የተመሰረተ የህዝብ አንድነትን ለመፍጠር ሁሌም ይጥሩ ነበር ለህዝባቸው መብት መከባበርና ለእኩልነታቸው መረጋገጥ አመቺ የአስተዳደር ሥነ ስርዓትፈጥረዋል፡፡

ለዚህ ስኬት ያበቃቸው የእስልምና ኃይማኖትን ህግን በወቅቱ ከነበረው ባህላዊ የአስተዳደር ስርዓት ጋር አጣጥመው ተግባራዊ ባደረጉት የአስተዳደር ስልት እንደሆነም ይነገርላቸዋል፡፡ በጥቅሉ በጅማ እስልምና እንዲስፋፋና እንዲጠናከር ያደረጉት አስተዋፅኦ የተሳካ አስተዳደር መልካም ስነ ምግባርን የተላበሰ ዜጋ ለማፍራት ያስቻላቸው አባ ጅፍር ለዲኑ መጠናከር የአገሪቱ መሻኢኮች ወደ ግዛታቸው በማስገባት ተጠቅመውባቸዋል፡፡ የጎንደረ መሻኢኮች ወደ ምዕራቡ ኢትዮጵያ በመፍለሳቸው እስልምና ወደ ጅማ ሲገባ እናታቸው ለኃይማኖቱ መስፋፋት ያደረጉት ጥረት ይበልጥ አጠናክረው በመቀጠላቸው ተሳክቶላቸዋል፡፡ የአገር ውስጥ አሊሞችንና መሻኢኮችን በማፈላለግ በመተዋወቅ ለዲኑ መስፋፋት በትብብር ከነሱ ጋር መስራታቸው ጥረታቸውን ይበልጥ ፍሬያማ አድርጎታል፡፡ ከጎንደር ሸህ ጌታ ኤልያስ፣ከወሎ መርሳ አባጌትየ፣ከሸዋ፣ሸህ ጫሌ ከጉራጌ የሸህ ሱልጣን አባት ከሆኑት የቀጥበሬው ሸህ፣ከአብሬት ሸህ ቡሽራና ከሌሎችም ዳኢዎችና አንዮች ጋር የነበራቸው ትውውቅ ለአብነት መጥቀስ ይቻላል፡፡

አባጅፋር በውጪ አገራት ከሚገኙ ኡለማዎች ይልቅ በአገር ውስጥ በወቅቱ ከነበሩት ሸኮችና ዑለማዎች ጋር የተሳካና ውጤታማ ግንኙነት የነበራቸው በመሆኑ በንግስና ዘመናቸው ሙሉ ጊዜ ለዲኑ መጠናከርና መስፋፋት ያከናወኗቸውን ተግባራት ፍሬያማ እንዳደረጉላቸውም ይነገራል፡፡ ይህ ለዲኑ ያበረከቱት አስተዋፅኦም በኢትዮጵያ እስልምና ታሪከ ውስጥ ትልቅ የማይተካ ሚና የነበራቸው ንጉስ ለመሆን አብቅቷቸዋል፡፡ በስልጣን ዘመናቸው መገባደጃ አካባቢ የወረዳ አስተዳዳሪዎቻቸውን፣ሚኒስትሮቻቸውን፣ ዘመዶቻቸውንና ሌሎች የቅርብ ወዳጆቻቸውን በመሰብሰብ ‹‹እናንተ ዱንያ ላይ ቤትለመስራት ትሽቀዳደማላችሁ እስቲ ይልቁንም አአኺራ አብረን የምንገባበትን ቤትየወቅፍ መዋጮ አውጡና እንስራ›› አሏቸው አሉ፡፡ ተሰብሳቢዎቹም ግራ በመጋባት እንዴት አኺራ ላይ ቤት መስራት እንደሚቻል ለአባጅፍር ጥያቄ አቀረቡ፡፡ እሳቸውም በወቅፍ በሚሰበሰበው ገንዘብ ለአበሻ ሃጃጆች መካና መዲና ላይ ማረፊያ የሚሆን ቤት እንገነባለን፡፡ በዚህም የጅማም ሰው ሆነ መላው የአበሻ ሙስሊም ለሃጅ ሲሄዱ ሳይንገላታ ማረፍ እንደሚችልና አከሏህም የሚያገኘው አጅር ከፍተኛ እንደሚሆን አስረዷቸው፡፡ በዚህ አሳባቸው ሁሉም ተስማሙ፡፡ ያላቸውን አወጡ፡፡ ሴቶችም ጌጦቻቸውን ሳይቀር ሰጡና 75ሺህ የማርትሬዛ ዶላር ተሰበሰበ፡፡ አባጅፋር በወቅፍ ያሰባሰቡትን ገንዘብ ታማኝ ባለሟል ከቤተመንግስታቸው አስፈልገው በበቅሎና በፈረስ አስጭነው ወደ መካ ላኩ፡፡ በምፅዋ በኩል፡፡ ከሁለት ወራት ጉዞ በውኃላ ገንዘቡ በሠላም ወደመካ ደረሰ፡፡ መሬት ተገዛና የመካን አሽዋ እንደብሎኬት በመጠቀም ሚስማርና ሌሎችም አስፈላጊ የግንባታ እቃዎችን ከጅዳ ተገዝተው ሃጃጆጀች በብዛት በሚያርፉባቸው ሶስት የመካና መዲና አካባቢዎች የሃጃጆች ማረፊያ ቤቶች ተሰሩ፡፡ ቤቶቹን የሚጠብቁና የሚያሰተዳድሩ ስዎቸ መርጠው በመላክ ሃጃጆች በዝቅተኛ ዋጋ እንዱያርፍባቸው በማድረግ የሚገኘውን ገቢ ለጠባቂዎች ደሞዝ፣ ለፅዳትና ሌሎች እድሳትሥራ የሚውልበትን ሁኔታ አመቻቹ፡፡

የጅማ እዝብ ንጉሱ ለዲኑ ባደረጉት አስተዋፅኦ ይበልጥ ተደሰቱ በዚህ ድንቅ ሃሳባቸው ብዙዎቹ ዛሬም ድረስ ይናገራሉ፡፡

በአሁኑ ወቅት ድሮ በእሳቸው የተሰሩት የአበሻ ሃጃጆች ማረፊያ ቤቶቸ ተሽጠው በምትካቸው ለተመሳሳይ አላማ የሚውሉ አንድ ባለ ዘጠኝ አንድ ባለ ሶስት ፎቅ እንፃዎች ደርበልና ደኑብ አዚዝያ አካባቢዎች ተገዝተው እሳቸው በዚያን ዘመን በተመኑት ክፍያ ዛሬም ድረስ አገልግሎት እየሰጡ ይገኛሉ፡፡

አባ ጅፋር በአፄ ሚኒሊክ፣ልጅ እያሱ፣ዘውዲቱና፣ተፈሪ መኮንን የሸዋ ስልጣን ጊዜ በአስተዳደራቸው ላይ ጣልቃ እንዳይገቡባቸውና በጅማ ሌላ ኃይማኖት ሰርጎ እንዳይገባ በብልሃትና በሰላማዊ ውይይት አሳምነው ውል ስምምነት እንዲፈርሙ አድርገዋል፡፡ በዚህም በስልጣን ላይ በነበሩባቸው ተከታታይ 57 አመታት ግዛተቸውንና ህዝባቸውን በኢስላም አንፀዋል፡፡ አስጠብቀዋል፡፡ አስተዳደራቸው የአገሩን ባህልና የኢስላምን መሰረታዊ ህጎች መነሻ ያደረገ በመሆኑ ለረዥም አመታት የህዝብ ተቃውሞ ሳይገጥማቸው በሰላም እንዲያስተዳድሩ አስችሏቸዋል፡፡ በመጨረሻም ኃይለስላሴ የሚኒሊክን የአስተዳደር ፖሊሲ በመቀየራቸው ሁኔታዎች ተለዋወጡና አስተዳዳራቸው አደጋ ገጠመው፡፡ ኃይለስላሴ የሸዋን ስልጣን ይዘው ኢትዮጵያን አንድ አድርገው ያለስልጣን ክፍፍል በጠቅላይ ግዛት በማስተዳደራቸውና አባጅፍር ይህን ለመከላከል ወታደራዊ አቅም ስላልነበራቸው አስተዳደራቸው አከተመ፡፡

ይህን ተከትሎም ኃይለስላሴ ጅማን እንደተቆጣጠሩ በቤተክርስቲያን አስተከሉ፡፡ ሚሲዮኖች በተለያየ ምክንያት ጅማ ከገቡ በኃላ የተለያዩና ኃይማኖቶችም መስበክ ጀመሩ በእሳቸው ጊዜ ያልነበሩ እንደ መጠጥ፣ጫት፣ሲጋራና ሌሎች ያልተለመዱና በኢስላም የተከለከሉ የንግድ ስራዎችም እየተበራከቱ መጡ፡፡ በወቅቱ የአገሬው እዝብም መቻቻልንና ትህግስትን ባስተማረው ቁርሃንና ሃዲስ እየታገዘ ከሌሎች ኃይማኖቶች ተከታይ የሕብረተሰብ ክፍሎች ጋር በመቻቻል ዲኑን ጠብቆ መኖር ችሏል፡፡

ከዚህ በኃላ የጅማው አባጅፍር እድሜያች በመግፋቱ በ1932 በመሞታቸው በወቅቱ የንጉሳውያን ቤተሰቦች መቀበሪያ ከነበረውና ‹‹አፌርታማ›› እየተባለ ከሚታወቀው ስፍራ የቀብር ስነ ስርዓታቸው ተፈፀመ፡፡ በዚህ ስፍራ አቅራቢያ መስጂድ የሚገኝ ሲሆን ቦታው በታሪካዊነቱ ዛሬም ድረስ ይጎበኛል፡፡

እናም አባ ጅፍር ቢያልፉም ለዲን እውቀት መስፋፋትና መጠናከር በግዛታቸውም አካባቢ ሆነ በአገር ደረጃ ለእስልምና እድገት በህይወት ዘመናቸው ያከናቀወኗቸው ተግባራት አመርቂ ውጤት በማምጣታቸው ይታወሳሉ፡፡ ከመታወስም ባለፈ ሙስሊሙ እብረተሰብም ሆነ የአገራቸው ኡለማዎች ለዲን መስፋፋትና መጠናከር እየደረጉ ላለው ጥረት ትልቅ ትምህርት የሚሰጥ መሆኑን መረዳት ይቻላል፡፡ በመጨረሻም አባ ጅፍር ለዲኑ ያበረከቱትን አስተዋፅኦ በሚመለከት ዋና ዋና ተግባራቸውን በማስታወስ መረጃ በመስጠት ትብብር ላደረጉልን የአባ ጅፍር የልጅ ልጁ የሆኑት አባቢያ በአላህ (ሰ.ወ) እና አንባቢያን ስም፡፡ ምስጋናችን ይድረስ እንላለን፡፡

ምንጭ አል-ኢስላም መፅሄት
እንሰት
ውሃ አጠጪ
ውሃ አጠጪ
 
Posts: 1213
Joined: Sun Jan 30, 2005 1:14 am
Location: united states

Re: የእስልምና መጻህፍት

Postby ተድላ ሀይሉ » Sun Aug 14, 2011 12:50 am

እንሰት wrote:

እንሰት:-

ወይ ጉድ !!!! ታሪክ እንደ ጸሐፊው መሆኑን ለመገንዘብ ከዚህ የበለጠ ምን ማስረጃ አለ !

አባ ጅፋር በምሥራቅ አፍሪቃ ትልቁ የባርያ ነጋዴ ነበሩ :: እስልምናን አልቀበልም ያለ ሁሉ በባርነት ይሸጥ ነበር :: ይህ ዕጣ-ፋንታ በአባ ጅፋር ባሪያ ፈንጋዮች እጅ የገባ ሁሉ ዘር ሣይለይ (አማራ ሆነ የም : ጋሞ ሆነ ወላይታ : ዳውሮ ሆነ ከፊቾ ወይም ጉራጌ) ብቻ ክርስቲያን የሆነውን በሙሉ በባርነት እያስፈነገሉ ይሸጡ ነበር:: ይህንን ታሪክ እስኪ የየም : የከፊቾና የሌሎችንም የአካባቢውን ማኅበረሰብ ተወላጆችን ጠይቅና ተረዳ ::

ሌላው አስገራሚ ነገር:- የአባ ጅፋር የልጅ-ልጅ-ልጅ የሆነው አባ-ቢያ ከኦነግ መሪዎች አንዱ ሲሆን 'ነፍጠኛ አማራ ቅኝ አደረገን' ብሎ በኢትዮጵያ ላይ ከሸፈቱት አንዱ ነው :: ይህ ነው የታሪክ ሥላቅ :- የባሪያ ነጋዴ የልጅ-ልጅ-ልጅ ቅድመ-አያቱ ባሪያ አድርጎ ሲሸጣቸው የነበሩትን የልጅ-ልጅ-ልጆች ገዙኝ ብሎ ሲከሥ ::

አክባሪህ ::

ተድላ
ተድላ ሀይሉ
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 4903
Joined: Fri Mar 17, 2006 2:45 pm
Location: ኢትዮጵያ

Re: የእስልምና መጻህፍት

Postby እንሰት » Sun Aug 14, 2011 6:32 am

ተድላ ሀይሉ wrote:

... ላደረጉልን የአባ ጅፍር የልጅ ልጁ የሆኑት አባቢያ በአላህ (ሰ.ወ) እና አንባቢያን ስም፡፡ ምስጋናችን ይድረስ እንላለን፡፡

ተድላ[/quote]

ውድ ተድላ እነሱ ባይጽፉ ለማነጻጸር የሚሆን ነገር ምን ይገኛል? አንተ በጻፍከው ተጨማሪ የባርያ ንግዱና እስልምናን ማስፋፋቱ ብቻ ሳይሆን ትምህርት በአረቢኛ ቁዋንቁዋ በማድረጋቸውም ጭምር ከሚኒልክ "አገሩን የአረብ አገር አድርገህው ከሆነ ንገረኝ" የሚል የወቀሳ ደብዳቤ ሁሉ ደርሷቸው ነበር:: አላማዬ ድረ ገጹ የሚነበብ የሚያወያይ ነገር አለው ለማለት ነበር::

ሰናይ ሰንበት
እንሰት
ውሃ አጠጪ
ውሃ አጠጪ
 
Posts: 1213
Joined: Sun Jan 30, 2005 1:14 am
Location: united states

Re: የእስልምና መጻህፍት

Postby እንሰት » Sun Aug 14, 2011 6:38 am

ሰናይ ሰንበት[/quote]

ውድ ተድላ
ስለ አባ ቢያ አንስተህ ነበር አባ ቢያ ብቻ ሳይሆን ከሌሎቹም ጋር ቢሆን የሚወራረድ ሂሳብ ይጠፋል ብለህ ነው:: የግል ምኞቴ አብሮ ለመኖር ሲባል እንደ ደቡብ አፍሪቃው በእርቅና ይቅርታ ቢሆን እመኛለሁ::
እንሰት
ውሃ አጠጪ
ውሃ አጠጪ
 
Posts: 1213
Joined: Sun Jan 30, 2005 1:14 am
Location: united states

Re: የእስልምና መጻህፍት

Postby ተድላ ሀይሉ » Mon Aug 15, 2011 4:31 am

እንሰት wrote:ውድ ተድላ እነሱ ባይጽፉ ለማነጻጸር የሚሆን ነገር ምን ይገኛል? አንተ በጻፍከው ተጨማሪ የባርያ ንግዱና እስልምናን ማስፋፋቱ ብቻ ሳይሆን ትምህርት በአረቢኛ ቁዋንቁዋ በማድረጋቸውም ጭምር ከሚኒልክ "አገሩን የአረብ አገር አድርገህው ከሆነ ንገረኝ" የሚል የወቀሳ ደብዳቤ ሁሉ ደርሷቸው ነበር:: አላማዬ ድረ ገጹ የሚነበብ የሚያወያይ ነገር አለው ለማለት ነበር::

ሰናይ ሰንበት

በዳግማዊ አፄ ምኒልክ የአገዛዝ ዘመን አባ ጅፋር አረብኛን የጅማ አካባቢ የትምህርት ቋንቋ አድርገው ነበር :: በልጅ-ልጅ-ልጃቸው አባ ቢያ ኦነግ ውስጥ ደግሞ አረብኛ የኦነግ አንዱ የሥራ ቋንቋ ነው :: ስለዚህ ነገሩ 'የዘሬን ብለቅ ያንዘርዝረኝ :' ነው ::
ውድ ተድላ
ስለ አባ ቢያ አንስተህ ነበር አባ ቢያ ብቻ ሳይሆን ከሌሎቹም ጋር ቢሆን የሚወራረድ ሂሳብ ይጠፋል ብለህ ነው:: የግል ምኞቴ አብሮ ለመኖር ሲባል እንደ ደቡብ አፍሪቃው በእርቅና ይቅርታ ቢሆን እመኛለሁ::

እዚህ ላይ አንድ የሣትከው መሠረታዊ መርሆ አለ :: በደቡብ አፍሪቃ የእርቅና የሰላም ሂደት የተከናወነው በአፓርታይድ ዘመን የትኛውም ወገን የሰብዓዊ መብትን በሚመለከት የሠራው ወንጀል ካለ በተጎጂዎቹ ፊት ቀርቦ ሃጢያቱን ተናዝዞ ለወደፊቱ ከማንኛውም የፖለቲካ ሥራ ራሱን ሊያገልል ተስማምቶ ነው :: በዚህ ሂደት አብዛኞቹ የአፓርታይድ አገዛዝ ዋና ዋና ሹሞች በእርቅ ሂደቱ አልፈው አሁን ሰላማዊ ኑሮ መኖር ችለዋል :: ያንን ያላደረጉ ወይም ያልፈቀዱ እስር ቤት ናቸው :: በኢትዮጵያችን ግን ከትውልድ ወደ ትውልድ ባንዶችና ጨፍጫፊዎች በቁጥርም በበላይነትም እየገዘፉ ሄደዋል :- በተለይ የፋሽስት ኢጣሊያ ወራሪዎች ከአገራችን በአርበኞች ትግል ከተባረሩ በኋላ :: ይህንን እያየህ እንዴት የደቡብ አፍሪቃ ዓይነት የሰላም እና የዕርቅ ሂደት እንዲህ በቅርቡ እንድታይ ተመኘህ ? ይህንን የምልህ ምኞትህ መጥፎ ምኞት ስለሆነ አይደለም :: እኔ ሥጋቴ ይህንን ምኞት 'ላም አለችኝ በሰማይ ....' እንደተባለው እየሆነብኝ ስለመጣ ነው ::

አክባሪህ ::

ተድላ
ተድላ ሀይሉ
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 4903
Joined: Fri Mar 17, 2006 2:45 pm
Location: ኢትዮጵያ

Re: የእስልምና መጻህፍት

Postby እንሰት » Tue Aug 16, 2011 11:41 pm

ምን አማራጭ አለን?
መቸም ይቅር ማለት እኮ መርሳት እንዳልሆነ ትገነዘባለህ::

ተድላ ሀይሉ wrote:
እንሰት wrote:ውድ ተድላ እነሱ ባይጽፉ ለማነጻጸር የሚሆን ነገር ምን ይገኛል? አንተ በጻፍከው ተጨማሪ የባርያ ንግዱና እስልምናን ማስፋፋቱ ብቻ ሳይሆን ትምህርት በአረቢኛ ቁዋንቁዋ በማድረጋቸውም ጭምር ከሚኒልክ "አገሩን የአረብ አገር አድርገህው ከሆነ ንገረኝ" የሚል የወቀሳ ደብዳቤ ሁሉ ደርሷቸው ነበር:: አላማዬ ድረ ገጹ የሚነበብ የሚያወያይ ነገር አለው ለማለት ነበር::

ሰናይ ሰንበት

በዳግማዊ አፄ ምኒልክ የአገዛዝ ዘመን አባ ጅፋር አረብኛን የጅማ አካባቢ የትምህርት ቋንቋ አድርገው ነበር :: በልጅ-ልጅ-ልጃቸው አባ ቢያ ኦነግ ውስጥ ደግሞ አረብኛ የኦነግ አንዱ የሥራ ቋንቋ ነው :: ስለዚህ ነገሩ 'የዘሬን ብለቅ ያንዘርዝረኝ :' ነው ::
ውድ ተድላ
ስለ አባ ቢያ አንስተህ ነበር አባ ቢያ ብቻ ሳይሆን ከሌሎቹም ጋር ቢሆን የሚወራረድ ሂሳብ ይጠፋል ብለህ ነው:: የግል ምኞቴ አብሮ ለመኖር ሲባል እንደ ደቡብ አፍሪቃው በእርቅና ይቅርታ ቢሆን እመኛለሁ::

እዚህ ላይ አንድ የሣትከው መሠረታዊ መርሆ አለ :: በደቡብ አፍሪቃ የእርቅና የሰላም ሂደት የተከናወነው በአፓርታይድ ዘመን የትኛውም ወገን የሰብዓዊ መብትን በሚመለከት የሠራው ወንጀል ካለ በተጎጂዎቹ ፊት ቀርቦ ሃጢያቱን ተናዝዞ ለወደፊቱ ከማንኛውም የፖለቲካ ሥራ ራሱን ሊያገልል ተስማምቶ ነው :: በዚህ ሂደት አብዛኞቹ የአፓርታይድ አገዛዝ ዋና ዋና ሹሞች በእርቅ ሂደቱ አልፈው አሁን ሰላማዊ ኑሮ መኖር ችለዋል :: ያንን ያላደረጉ ወይም ያልፈቀዱ እስር ቤት ናቸው :: በኢትዮጵያችን ግን ከትውልድ ወደ ትውልድ ባንዶችና ጨፍጫፊዎች በቁጥርም በበላይነትም እየገዘፉ ሄደዋል :- በተለይ የፋሽስት ኢጣሊያ ወራሪዎች ከአገራችን በአርበኞች ትግል ከተባረሩ በኋላ :: ይህንን እያየህ እንዴት የደቡብ አፍሪቃ ዓይነት የሰላም እና የዕርቅ ሂደት እንዲህ በቅርቡ እንድታይ ተመኘህ ? ይህንን የምልህ ምኞትህ መጥፎ ምኞት ስለሆነ አይደለም :: እኔ ሥጋቴ ይህንን ምኞት 'ላም አለችኝ በሰማይ ....' እንደተባለው እየሆነብኝ ስለመጣ ነው ::

አክባሪህ ::

ተድላ
እንሰት
ውሃ አጠጪ
ውሃ አጠጪ
 
Posts: 1213
Joined: Sun Jan 30, 2005 1:14 am
Location: united states

የቆዩ ሙዚቃዎች በድረ ገጽ

Postby እንሰት » Thu Aug 25, 2011 7:07 pm

...
Last edited by እንሰት on Fri Aug 26, 2011 7:40 am, edited 1 time in total.
እንሰት
ውሃ አጠጪ
ውሃ አጠጪ
 
Posts: 1213
Joined: Sun Jan 30, 2005 1:14 am
Location: united states

Re: የቆዩ ሙዚቃዎች በድረ ገጽ

Postby እንሰት » Thu Aug 25, 2011 7:21 pm

እንሰት wrote:ይህ ድረ መረብ ለኛም ይለፍላችሁ ነው መሰለኝ አሁንማ የማያመጣው ጉድ የለም:: ቆየት ያሉ የኢትዮጵያ ዘፈኖችን ማድመጥም የማናውቃቸውን ስማቸው ሲጠራ ሰምተን እንኩዋን የማናውቅ ዘፋኞችም መሰማት ጀምረዋል አጃኢብ ነው::

አንድ አዲስ ትሬንድም ብቅ እያለ ነው:: እነዚህን ዘፈኖች የሚያሰባስቡ የትውልደ አውሮፓ እና አሜሪካ ሰዎች መሆናቸው ነው:: በገዛ ዳቦዬ ማለት ይህ አይደል?

http://mitmitta.tumblr.com/[/url]
http://radiodiffusion.wordpress.com/category/ethiopia/
http://www.bernos.com/blog/2007/02/13/o ... goodies-i/
http://www.bernos.com/blog/2007/02/14/t ... y-special/
http://www.bernos.com/blog/2007/04/03/o ... ddies-iii/
http://www.bernos.com/blog/2007/04/20/o ... oodies-iv/
http://www.bernos.com/blog/2007/05/23/o ... goodies-v/
http://www.bernos.com/blog/2009/02/13/o ... oodies-vi/
http://www.bernos.com/blog/2007/06/07/o ... dies-v-ii/[/url]
እንሰት
ውሃ አጠጪ
ውሃ አጠጪ
 
Posts: 1213
Joined: Sun Jan 30, 2005 1:14 am
Location: united states

አዲስ ብሎግ

Postby እንሰት » Fri Jun 01, 2012 9:17 pm

ፕሮፌሰር መስፍን የሚጽፉዋችው መጣጥፎች ካልፈው ወር ጀምሮ በብሎግ መቅረብ ጀምረዋል::

http://mesfinwoldemariam.wordpress.com/
እንሰት
ውሃ አጠጪ
ውሃ አጠጪ
 
Posts: 1213
Joined: Sun Jan 30, 2005 1:14 am
Location: united states

Postby እንሰት » Tue Jul 31, 2012 4:58 pm

ሰላም ለሰነ ጽሁፍ አፍቃሪያን
ወግ ያላት ወግ የምታስነብብ ብሎግ አገኘሁና ብታዩዋት በማለት ማያያዣውን አመጣሁ::

http://bewaye.wordpress.com/

ለቅምሻም እንዲሆን እነሆ አንዱ ጽሁፍ
ወሬኛው ማስታወሻ

ቅድመ ታሪክ…

ለኑሮ የሚያስፈልጉኝ ሦስት ነገሮች ናቸው፤ ምላስ፥ ብር እና ሥልጣን።

=======

መጠጥ ቤት ተቀምጠናል፤ እኔ፥ ቆስጠንጢኖስና እስከዳር።

ከነዚህ ሰዎች ጋር ለምን እንደውል ይገርመኛል።

በእድሜ በጣም ይበልጡኛል። ከዚያም ባሻገር ቆስጠንጢኖስ ስለ ብር፥ ንግድ ምናምን ካልሆነ ሌላ ወሬ አይችልም። እስከዳር ደሞ እራሱን ለአምባሳደርነት ያጨ፥ እኔ የማላውቀው እሱም የማያውቀኝ ፖለቲከኛ/ባለስልጣን የለም ባይ የባህል ፖለቲከኛ ነው።

ሁለቱንም አንድ የሚያረጋቸው ጉራቸው ነው። ይቺን ስለማውቅ እነሱን በቀላሉ አሾራቸዋለሁ።

ቆስጠንጢኖስ ጋር ስሆን ስለሚያከናውናቸው የልማት ስራዎች፥ ስለፈጠራቸው የስራ እድሎች…እያነሳሁ አሞግሰዋለሁ። “እንዳንተ አይነት የስራ ሰዎች ናቸው የዚችን ሀገር ኢኮኖሚ ከማጥ ዉስጥ የሚያወጡት።” እለዋለሁ። ቃላቶቼን እንደቀኑ ሁኔታ እለዋውጣቸዋለሁ እንጂ ለሁለቱም ተመሳሳይ ነገር ነው የምላቸው። እነሱ መስማት የሚፈልጉትም ይህንን ብቻ ነው። እንዲያ ስላቸው ታዲያ ትንሽ እንደመሽኮርመም ያረጋቸውና ያሰኘኝን ይጋብዙኛል።

እኔን ለመጋበዝ ሁለቱ ይጣላሉ። ከዚያ ለየብቻ ሲያገኙኝ አንዱ ሌላኛውን እንዴት “ስቁንቁናም” እንደሆነ ያወሩኛል። በሆዴ ስቃለሁ።

እኔ በሰላሳዎቹ መጀመሪያ የምገኝ፥ ያላገባሁ እና ሥራ አጥ ነኝ። በቅርቡ ነው ተመርቄ ከዩንቨርሲቲ የወጣሁት፤ ግፋ ቢል አራት ዓመት ቢሆነኝ ነው። ትምህርት አይሆነኝም፤ እኔም አልሆነው። ግን በቤተስብ ግፊት እንደሰው ወግ ይድረሰው ተብዬ ዩንቨርሲቲ ገባሁ። እነሱ ሲያባርሩኝ እኔም ሳቋርጥ የአራት ዓመቱን ትምህርት በዘጠኝ ዓመት ፉት አደረግኩት። እኔ የተመረቅኩ ቀን የመሬት መንቀጥቀጥ፥ ሱናሚ ይነሳል የተዘጉ መቃብራትም ይከፈታሉ፥ ብርሃናት ይከስማሉ ተብሎ ነበር፤ አልሆነም።

በዉጤቴ ለምረቃ ብቁ ሆኜ አይደለም፤ “ያንተ ከዚህ መውጣት ለቤተስብህም ለኛም እፎይታ ነው፤ አንተም ትገላገላለህ” ተብሎ እንጂ። (በሆዳቸው ግን “ኢትዮጵያ ግን አራት እግሯን ትብላ” ሳይሉ አይቀርም)

የእድሜዬን ሢሦ ያህል ከዩኒቨርሲቲ ተቆራኝቼ ያሳላፍኩ ነኝ። ትልቁ ብርታቴ የነበረው አርቆ አሳቢ፥ አስተዋይነቴ ሳይሆን ምላሴ ነበር። ይህን ችሎታዬን በደንብ አውቀዋለሁ። በዚህም ከብዙሃኑ ተመራቂ እለያለሁ።

በዚህም ችሎታዬ በተማሪነቴ ዓመታቶች ሁሌም በሴቶች እንደተከበብኩ ነበር። ይህን የሚያዩ ወንዶች ሁላ ደሞ ወዳጅነቴን አጥብቀው ይሹታል። ከጠጪዎች፥ አጫሾች፥ ቃሚዎች፥ ሃሜተኞች ፥ “ምሁራኖች” …ጋር በቀላሉ መቀራረብ እችላለሁ። የጫትና እና የጨብሲ ያወጣሁባቸው ቀናቶችን ትንሽ ባሰላስል ቆጥሬ እደርስባቸዋለሁ።

ምረቃ አልፎ ስራ አደን ሲጀመር ታዲያ ብሩሃኑ ሲቪ ይዘው ሲሯሯጡ እኔም እየዞርኩ ማውራት ቀጠልኩ። ግን ስራ እንዲህ በጥረት የሚገኝ አልሆነም፤ ጥቂቶች ሲያገኙ ቀሪው የጆሊ ባርን ደጅ አጨናነቀው። ብዙውም ተሰደደ፤ ሀገራችንም በምሁራን ፍልሰት ቀዳሚ ተባለች። “ያልተሰደደ ምሩቅ ጆሊ ባር ይገናኛል” ተባለ።

ትንሽ ዱብ ዱብ ብዬ ማስታወቂያ ሚኒስቴር ዉስጥ የሆነ ስራ አገኘሁ፤ በነእስከዳር በኩል። የስራዬን መጠሪያ በወጉ አላውቀውም፤ ግን ያው ወሬ አቀባይነት ነው። ይሄ ደሞ የተመረቅኩበት ነው። ይቺ ሀገር እንደዉም ለኔ አይነቱ ነው ሰፊ የስራ መስክ ያላት። ሰልችቶኝ ተውኩት በኋላ፤ ደሞዙም አይረባም።

ከፈለኩ ግን ከዚህም የተሻለ ሹመት እንደማገኝ እርግጠኛ ነኝ።

*

እኩዮቼ ወይ ተሰደዋል ወይ አግብተዋል።

እዚህ ካሉት ወዳጆቼ ጋር ስገናኝም ደሞ ባይተዋርነት ይሰማኛል። ወሬው በሙሉ “ማኔ እንዳገባ ሰማህ?”፥ “የተስፉ ሰርግ ቀውጢ ነበር።”፥ “ሄለን እና ኪዳኔ ቀለበት አሰሩ አይደል?”…አልፎ አልፎ ደሞ “ፍቅሩና ፍቅርተ ተለያዩ እኮ”…።

ትዳር፥ ልጅ…ወዘተ ገና የኔ መዝገበ ቃላት ውስጥ አልገቡም፤ እናም ቶሎ ወሬው ይሰለቸኛል።

ነገራቸው በሙሉ “የኛ ተግባር ማግባት፥ ማግባት አሁንም ማግባት ነው” ይመስላል። ገና የማግባታቸውን ዜና አንብበን ደሞ በወጉ ገና “እንኳን ደስ አላችሁ” ሳንል የልጃቸውን ፎቶ ፌስቡክ ላይ እናያለን። እንዴት ነው ነገሩ? Express Delivery ተጀመረ እንዴ? በልዩ ትዕዛዝ ይቻላል? ወይስ ዘጠኝ ወር ሲባል የማውቀው ነገር ስህተት ነበር? (ማለቴ የሳይንስ ትምህርት ላይ ድሮም ቀሺም ነበርኩ)። ይህን ሁሉ የምቀባጥረው ታዲያ ይኼ ሁላ ሴት በእርግዝና ምክኒያት ትዳር መሰረተች ብሎ ማሰቡ ስለከበደኝ ነው።

አልያም ደሞ መጋባታቸውን በሰማን ሰሞን መለያየታቸውንም ያበስሩናል። “የእርግዝና ምርመራው ተሳስቶ ነበር ማለት ነው” ብዬ አስባለሁ።

በዚህ በዚህ ብቻ የተነሳ በተቻለኝ መጠን ከእኩያዎቼ ጋር ብዙ ላለመገናኘት እጥራለሁ።

እንግዲህ በዚህ መሃል ነው ከነቆስጠንጢኖስ ጋር የተቀራረብኩት።

በነሱ መሃል እኔ የውቅያኖስ እንቁ፥ የምሁር ፍፃሜ ነኝ። እኔ የምናገረው ጥልቅ ዋጋ አለው፤ እናም ይሰሙኛል። እንዲያም ሆኖ ግን የፖለቲካ ነገር ላይ እስከዳር፥ የብር ጉዳይ ላይ ደሞ ቆስጠንጢኖስ “ከኔ ወዲያ ላሳር” ባይ ስለሆኑ ምንም ቢሆን ጣልቃ አልገባም። ከሚልተን ፍሪድማን ባልንጀሮች ነን ቢሉ፥ ዲሞክራሲ ተወልዶ ያደገው ኢትዮጵያ ነው ቢሉ፥ ቀለበት መንገድ በማሰራት አዲስ አበባ ከአፍሪካ ቀዳሚ ሆነች ቢሉ፥ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ሲታመሙ ዉሃ ማቀብላቸው እኔ ነኝ ቢሉ…አልከራከርም።

በነዚህ ጉዳዮች እነሱን “ተሳስተሃል” ማለት ከአውርቶ አደር መርህ አንጻር “ሾላ እርግፍ፥ እርግፌን” ቆርጦ እንደ መጣል ነው።

*

ቁጭ ብለን እየጠጣን ታዲያ ገነት መጣች። ገነት እድሜዋ ወደአርባ ገደማ የሆነ፥ ከዱባይ ከመጣች ጀምሮ የመዋቢያ ቤት ከፍታ ራሷን የምታስደዳድር፥ ትዳር የሚባል ነገር የምትሸሽና እየዞረች መዝናናት የምትወድ ነች። ልጠጣ ወጥቼ (የትም ሰፈር ይሁን) እሷን ያላየሁበት ጊዜ ብዙ አይደለም።

በፈገግታ ከሩቁ ሰላም ብላን ባዶ ጠረጴዛ ፈልጋ ቁጭ አለች።

ሁለቱም እንደመቁነጥነጥ አደረጋቸው። ሁኔታቸውን ሳይ በሁለት ጣቴ አገጬን ዳበስ ዳበስ እያደረግኩ ሳቅ አልኩኝ። ሁለቱም ባለትዳር፥ የልጆች አባት ናቸው። ይኼው ግን ከኔ እኩል ሴት ባለፈችን ቁጥር አንገታቸው ይጠመዘዛል። ሁለቱም እኮ ያባቴ እኩያ ይሆናሉ። ለምን አታገባም የሚለው የወላጆቼ ዉትወታ ይህን ሳይ ይገርመኛል።

ግን ሁለቱም ደፍረው ሴት ማናገር አይሆንላቸውም።

ተነስቼ ወደገነትጋ ሄድኩና “እዛጋ አድናቂዎች አፍርተሻል። ለምን አትቀላቀይንም?” አልኳት።

ገነት አይደለም ከነሱ ከኔም ጋር እንደማትወጣ አውቃለሁ። እሷ ወጣት(ሃያዎቹን) ወንዶችን እያሳደደች፥ በስደት ስትንከራተት ያመለጣትን የራሷን ወጣትነት መልሳ ለመያዝ የምትታትር ሴት ናት።

“አባቶችህ ናቸው?”

“የእንጀራ” አልኳት።

“ግን ምን አገኝ ብዬ?”

“ነፃ መጠጥ እና ለኔ ዉለታ፤ እናም ደሞ አሪፍ መደበሪያ ይሆኑሻል” እንደመሳቅ ብዬ ጠቀስኳት።

ከገነት ጋር በደንብ እንተዋወቃለን፤ ትንሽ እንደማንገራገር ብላ እሺ አለችኝና ተቀላቀለችን።

መሳሳቴ ዘግይቶ ነው የገባኝ፤ ሁለቱም ሰበብ እየፈለጉ መነታረክ ጀመሩ። እኔ ነኝ የምጋብዛት በሚል ተጀምሮ ከጎኗ ለመቀመጥ በሚደረግ ስስ ግብግብ ተቀጣጥሎ ወደቃላት ልውውጥ ተሸጋገረ። ሁለቱም ግን እሷን በወጉ ሊያናግሯት አልቻሉም።

ገነት ወዲያው ነው የገባት፤ ትጫወትባቸው ጀመር። ቆስጠንጢኖስን ቀስ ብላ ትተሻሸው ጀመር፤ ሰበብ እየፈለገች እሱን መነካካት፥ በተናገረው ሁሉ መሳቅ ጀመረች። እስከዳር አንገቱ ላይ ያለው ሰንበር መሰል የደም ስር መነፋፋት ጀምሯል። ተነስቶ መታጠቢያ ቤት ሄደ።

ይሄኔ ቆስጠንጢኖስ ወደጆሮዬ ጠጋ ብሎ “አየህ ሲቃጠል? አይረባም እኮ። እንደምበልጠው አምኖ አይቀበልም?” አለኝ

ገነት “እኔ ደክሞኛል፥ መሽቷልም ደሞ። ታክሲ ፈልጌ ነው ወደ ቤት የምሄደው፤ ልነሳ” አለች።

“በታክሲ ከምትሔጂ የኔን መኪና ዉሰጂ።” አለና ቆስጠንጢኖስ ቁልፉን አስጨበጣት።

እንደመደንገጥ አልኩ። ጅል እንደሆነ አውቃለሁ፤ ይህን ያህል ይደድባል ብዬ አልጠበኩም ግን።

“ኧረ ባክህ? ነፍስ አኮ ነህ” ብላ ተቀበለችው፤ ቀብረር ሲል አየሁት።

በመሃል እስከዳር ተመለሰ፤ ቆስጥንጢኖስ በተራው ተነስቶ ሄደ። ጥቂት ቆይታ ባይኗ ጠቅሳኝ ተነስታ ተከተለችው። ገነት ክፋት አታውቅም እንጂ በዚህ ሰዓት ሁለቱን ከፈለገች በእግር ቁሉቢ ልትልካቸው ትችላለች፤ በተለይ ቆስጠንጢኖስን።

እሷን ስለፈለጋት አይመስለኝም፤ እንዲሁ ሀብት እንዳለው፥ እንደሚችል ለማሳየት ሲል ብቻ ነው። እንደውም አብረን እንደር ብትለው ራሱን ስቶ የሚወድቅ ሁሉ ይመስለኛል።

“ይሄን ጉረኛ ሰውዬ አየኸው እንዴት እንዴት እንደሚያጎበድድላት? ሰው ሚስቱና ልጆቹን ሰው አገር ልኮ እንዲህ ይቀብጣል?” አለኝ እስከዳር። የቆስጠንጢኖስ ሚስትና ሁለቱ ልጆቹ እንግሊዝ ለእረፍት ሄደዋል።

ቀጠለና “ይሄው ትዳር ከመሰረትኩ ወዲህ ከሌላ ሴት ጋር ሂጄ እንዳማላውቅ ታውቃለህ?” አለኝ።

“አትለኝም!” አልኩት ምንም እንደማያውቅ፤ ለምን እንደሚዋሹኝ አይገባኝም።

“ልሙት እልሃለሁ! ይሄው አስራ ሰባት ዓመቴ”።

“ዋው!” ላለመሳቅ እየታገልኩ።

እነገነት ተመለሱ። ቆስጠንጢኖስ ፊቱ ቀልቷል፤ እንደተቀመጠ መጠጡን ባንድ ትንፋሽ ጨለጠውና ወደ እስከዳር ዞሮ “እንዴት ነህ ጃል?” አለው።

ወደገነት ዞሬ ጠቀስኳት። “ምናባሽ አርገሺው ነው?” አልኳት ቀስ ብዬ

ሳቅ አለችና “መታጠቢያ ቤት ሳሯሩጠው ነበር”

“ምን?!”

“ይዤ ልስመው ስል ደንግጦ መሮጥ ጀመረ” እንደዚህ ሳቄን ለመቆጣጠር ታግዬ አላውቅም።

ምሽቱ ተገባዶ ለመውጣት ስንዘጋጅ ቆስጠንጢኖስ ወደኔ ጠጋ ብሎ “ዛሬ አንተ ቤት ነው የማድረው” አለኝ።

“ለምን?” አልኩት ግራ ገብቶኝ።

“የቤቴን ቁልፍም አብሬ ነው የሰጠኋት እኮ፤ ወይ ቁልፉን ትቀበልልኛለህ?”
እንሰት
ውሃ አጠጪ
ውሃ አጠጪ
 
Posts: 1213
Joined: Sun Jan 30, 2005 1:14 am
Location: united states

PreviousNext

Return to Warka Culture and Literature - ዋርካ ባህልና ሥነ ጽሑፍ

Who is online

Users browsing this forum: No registered users and 3 guests