ሰላም የጃማ ጦስኝ ቤት ታዳሚዎቸ::
መቸም ዓመት በዓል ሲቃረብ ሽር ጉዱ መከራ ነው:: የስጦታ እቃ ለመግዛት የሚደረገው ውጣ ውረድ ከሱቅ ሱቅ መንከራተቱ አይጣል:: እኛማ እጥፍ እጥፍ ዓመት በዓል ነው የምናከብረው::
እኔም ለእናንተ ለወዳጆቸ የማቀረበውን ስጦታ ለማቅረብ ከሱቅ ሱቅ ተንከራትቸ በስንት መከራ ትሆናለች ያልኳትን ሽምቸላችሁ ብቅ:-
ልጂቷ ከቻይና ጓደኛዋ አርግዛ ትወልዳለች:: የተፍለቀለቀችው ድንቡሽቡሽ ከአንድ ዓመት በኋላ በጠና ትታመምና ሳትድንላት ቀርታ ሞተቸባት ::
አንጀቷ የተቃጠለው እናት :- ልጄ ልጄ ልጄ; እኔ እኮ ገና ስትረገዢ አውቄዋለሁ እንደማታድጊልኝ አውቄዋልሁ እያለች አብዝታ ስታለቅስ ግራ የገባቸው ወዳጅ ዘመዶች እንዴ እንዴት አርገሽ ነው ገና ስታረግዥ እንደማታድግ ያወቅሽው? ቢሏት :-
ምን ድሮስ የቻይና እቃ ለጊዜው ነው እንጅ መች ይበረክታል :: ብላ እርፍ::
በሉ ቸር ይግጠመን::
እህታችሁ የጃማ ጦስኝ