በትንሽ ማስተካከያ ልጀምር:: ስሜ ሓያት ሳይሆን ሓየት ነው::
ለዛ ነው ሴት የመሰልኩህ:: ቃሉ ትግርኛ ነው:: ብዙ ትርጉም አለው:: አንደኛው ትርጉሙ ግን 'አይበገሬ' ለማለት ነው :lol:
ሀያት ራሱ በትግርኛ ሲሆን በትክክል የሚጻፈውና ፕሮናውንስ የሚደረገው ሓያት ሲሆን ነው:: ሐያት, ሀያት, ወይም ሃያት አይባልም:: በአማርኛ ሁሉም ተመሳሳይ ናቸው:: በግዕዝና በትግርኛ ግን ሀ, ሃ, ሐ, ና ሓ የተለያየ አነባበብ ስላላቸው በተለያየ ሁኔታ እንጠቀምባቸዋለን::
በቅርብ ጊዜ ያነበብኩትን አንድ ድረገጽ ልጋብዝህ:: ጠቃሚ ነገሮችን ታገኝበታለህ:: ከዚህ በፊት ካላነበብከው ማለት ነው::
http://www.filepie.us/?title=Ge%27ez_alphabet
ሌላው ይህ መንግስት ስልጣን ከያዘ ብኋላ ባንዴራና የፖለቲካ ስርዓቱን ብቻ አይደለም የቀየረው:: ፊደሎቻችን ላይም መለስተኛ ጣልቃ ገብነት አሳይቷል:: ከትግርኛው የፊደል ገበታል (which was exactly the same as Amharic alphabet) አንዳንድ ፊደሎችን አንስቷል:: ከአማርኛውም እንዲሁ የተነሱ አሉ መሰለኝ:: ከትግርኛ ሠ, ኅ እና ጸ ተነስተዋል:: በአዲሱ ስርዓተ ትምህርት የተማረ የትግራይ ተወላጅ እነዚህን ፊደላት አያውቃቸውም:: ወይም የጥንት ናቸው ብሎ ያስባል:: ምሳሌ እዚህ ዋርካ ብንወስድ ዳግማዊ ዋለልኝ የሚባለው ውርጋጥ ወያኔ 'ሠ' ን ሲጠቀምባት አታይም:: የሆነ ነጥብ በቅደም ተከተል ለማቅረብ ሲፈልግ ሀ, ለ, ሐ, መ ብሎ ረ ነው የሚለው:: ይህ ሠ ንጉሡ ስለሚባል የንጉሡን ስርዓት እንዳያስታውሳቸው ፈርተው ያነሱት ይመስላል :lol: 'ኅ' ደግሞ በግዕዙ ከእግዚአብኄርና ከኃይሉ ጋር የሚያያዝ ነገር ስላለው ለኤቲስቶች የሚመች አልሆነም:: የመጨረሻው ጸ ከ ፀ ጋር ድግግሞሽ በመሆኑ ምክንያት የተነሳ ይመስለኛል::
(ካልተሳሳትኩ ጸ ን ከትግርኛው ሲያነሱት ፀ ን ደግሞ ከአማርኛው አነሱት:: በዛ ምክንያትም መሰለኝ አንተም ይቺን ፀ እንደተረሳች ያያሀት::
ስለዚህ የፊደል ገበታው ፀ ያለበት ከሆነ ትግርኛ, ጸ ያለበት ከሆነ ደግሞ አማርኛ ነው እንበል እንዴ :?: )
BelayTekalign wrote:እመቤት ሓያት 11
ጥያቄውን ያቀረብኩት እኮ መጽሐፉ በመከልከሉ እርግጠኛ ስላልሆንኩ ነው ። ምናልባት አንች ስለጉዳዩ የተሻለ ዜና ካለሽ ብታወጊኝ ።
ገዛ ሓያት የሜለውን ፊርማሽን ተከተልኩ .
http://hayet11.blogspot.com/ስለ አንች ለማወቅ ፈልጌ ሳይሆን ሓ እንደዝያ ስትፃፍ አይቻት ስለማላውቅ ነው . በትርፍ ጊዜየ ግዕዝ አጠናለሁ . ሓ የምትባለውን ፊደል ያገኘኋት የቁራን አረብኛ መስጊድ ላይ ከ5 አመት ተማሪዎች ጋር ስቀራ ነው . ሐ . ፀ . ሠ ንም ከነዘመዶቻቸው አገኘኋቸው . እነዜህ ድምጾች በአማርኛው ጠፍተዋል . በትግሬ እና በትግሬ ምናልባትም በብሌን ይኖሩ ይሆናል .
May I switch to English...
Hebrew and Qoranic Arabic languages resemble our Ge'ez in a lot of ways. Some scholars suggest that Ge'ez is the mother tongue to Arabic, Aramaic (Jesus' toungue) and to Hebrew because some of its semantics are close to the west Semantic language like Akadian, Sumerian who had died by the time Hebrew and Arabic became languages. I don't want to crowd your literature forum with trivia but I think that ሓ has a lot to say for itself.