@ ..... ጀግና ለሕይወቱ እንደማይሣሣ አምባሣደር እምሩ አስገንዝበውናል :: አብርሃ ደቦጭና ሞገስ አስገዶም እኒያን 7 ወይም 10 (ታሪኩን እንደዘገቡት ጸሐፊዎች አቀራረብ ቁጥራቸው ስለሚለያይ ) ቦምቦች በፋሽስት ጣሊያኑ ጄኔራል ግራዚያኒ እና አጀቦቹ ላይ ከወረወሩ በኋላ ያደረጉት ነገር ቢኖር የራሣቸውን ሕይወት ለማዳን መሸሽ ነበር :: ሽሽታቸው የተደመደመው ከኢትዮጵያ ግዛት ሊወጡ ሲሉ ጠረፍ ላይ እንደሆነ ተጠቁመናል
እነዚህ ሰዎች ለህይወታቸው ቢሳሱ ኖሮ ቀድሞውኑ አርፈው ይቀመጡ ነበር......አንተ አቅልለህ 7 ወይም 10 በማለት የጠቀስካቸውን ቦንቦች በፋሽስቱ አውራ ላይ በቅርብ ርቀት ሆነው ለመወርወር የቻሉ ሰዎች እንዴት ለህይወታቸው የሚሳሱ ፈሪዎች እንደተባሉ ሊገባኝ አይችልም...........አላማቸው ግራዝያኒ ነበር......የቻሉትን ያህል ሞከሩ........አልሆነላቸውም ቀድመው ባዘጋጁት መንገድ በስምኦን ርዳታ ለጊዜውም ቢሆን ማምለጥ ቻሉ.........እንደ በግ ተይዘው መታረድ ነበረባቸው የሚለው ጉዳይ ማንን በምን መልኩ ሊጠቅም እንደሚችልም አይገባኝም.......ጥይት ሲተኮስብህ ከለላ ፈልጎ ከጥይቱ መዳን ፈሪ የሚያስብል ከሆነ .....የፈሪን ትርጉም በጥልቀት ማጥናት ሊኖርብን ነው ማለት ነው....ለመሆኑ አያድርገውና ፊት ለፊትህ ጠላትህ ሊገድልህ በግላጭ አግኝቶህ አልሞ ቢተኩስብህ ደረትህን ገልብጠህ ትቀበለዋለህ ወይስ ባገኘከው አጋጣሚ ተጠቅመህ ከተጋረጠብህ አደጋ ለማምለጥ ትሞክራለህ?
በተለያየ ምክንያት ኢህአዴግ እንዳያስረን እንዳይገድለን ፈርተን ተሰደድን በማለት በሺዎች የሚቖጠሩ ራሳቸውን የፖለቲካ ስደተኞች ብለው የሚጠሩ ከአገራቸው በሚወጡበትና በስደት ምድር እንደ ጀግና በሚታዩበት ዘመን የፋሽስቱን አውራ ግራዝያኒን በቦንብ አቁስለው በመላ አገሪቱ እንደ አውሬ ቀን ከሌት የሚታደኑ ሁለት ሰዎች አገራቸው ጠረፍ ላይ ተይዘው መገደላቸው ፈሪ ተብለው መፈረጃቸው የሚገርም ነው :?
በተቃራኒው እነርሱን እንዲያመልጡ የረዳቸው አጋራቸው ስሞዖን አደፍርስ እስከመጨረሻው ድረስ በዓላማው ጸንቶ በፋሽስት ጣሊያኖች የሚደርስበትን ሥቃይ ሁሉ ተቀብሎ ሞትን ፊት ለፊት ተጋፍጧል :: ከሕፃንነቴ ጀምሮ ሥሰማው የኖርኩት 'አብርሃ ደቦጭና ሞገስ አስገዶም የሚባሉ ጀግኖች በግራዚያኒ ላይ ቦምብ ጥለው አቆሠሉት ...' ሲባል እንጂ ስምዖን አደፍርስ የሚባል ጀግና ያን ያህል መስዋዕትነት መክፈሉን ሠምቼ አላውቅም :: 'ሠምቼ አውቃለሁ ' የሚል ሰው ካለ ማስረጃውን አቅርቦ ይሞግተኝ :: እንዲያውም የአሁን ዘመን ታሪክ ጸሐፊዎች ባያስታውሱት ኖሮ ከእነጭራሹም እንደዚያ ያለ ሰው መፈጠሩንም የሚያስታውስ ሰው አይኖርም ነበር :: ታዲያ የእነ 'አብርሃ ደቦጭና ሞገስ አስገዶም ' ተግባር 'የጀግንነት ተግባር ነው ' ካልን ለምን የስምዖን አደፍርስ ሥም አብሮ ሲወደስ አልኖረም ? እርሱ ቲፎዞ ስለሌለው ይሆን ? ወይስ ከዚህ ፕሮፓጋንዳ ጀርባ ሌላ የተወሣሠበ ፖለቲካ ይኖር ይሆን ?
የስምኦን አደፍርስ ድርሻ የሚናቅ አልነበረም...ህይወቱን የሚያስከፍል ታላቅ ስራ ነው የሰራው.........ለምን ስሙ እንደማይጠቀስ አይገባኝም......ስሙ ከነሱ ጋር መነሳት ነበረበት........ሆኖም የሱ ስም ያለመጠቀሱ የነሱን ስራ አያሳንሰውም.........እዚህ ላይ ምንም አይነት ፖለቲካ የለም....የታሪክ ፀሀፊዎች ለአስመላጩ መስጠት የሚገባቸውን ትኩረት ሳይሰጡ በሁለቱ ሰዎች ላይ ብቻ ትኩረት ማድረጋቸው ስህተት ነው........ያ ማለት ግን በምንም ምክንያት የነአብርሀና ሞገስን ታሪክ ለውጦ ፈሪ ሊያገርጋቸው አይችልም
ለሁለተኛው ጥያቄ የሚቀርበው መልስ ለጀግና ተግባር ትክክለኛው መመዘኛ ሊሆን ይችላል ብዬ አምናለሁ :: አንድ ሰው በግል ዕምነቱ አንድ ትልቅ ተግባር ሊፈፅም ይነሣል :: ያንን ተግባር በመፈፀሙ ተጠቃሚም ይኖራል : ተጎጂም ይኖራል :: ተጠቃሚዎቹ 'ጀግና ' ሲሉት ተጎጂዎቹ 'ጨካኝ ' ይሉታል :: የሰውዬው ተግባር ከሁለቱም ውጪ የሆነ ያልተፈለገውን ውጤት ያመጣ ከሆነ ደግሞ የቀቢፀ -ተስፋ ድርጊት እንጂ ጀግንነት አይሆንም :: ሰውዬው ያሠበውን ተቃራኒውን ውጤት ካመጣ እንዲያውም ከንቱ ጀብደኝነት እንጂ የጀግንነት ተግባርም ሆኖ መቆጠር አይኖርበትም ::
ይህ እንግዲህ ያንተ አስተያየት ነው.........ጀግኖች የተባሉትን በተለይም የጦር ሜዳ ጀግኖችን ብትጠይቅ ግን የምታገኘው መልስ የተለየ ነው.........ጀግና ምንም እንኳን የተለያየ አላማ ኖሯቸው ቢዋጉም ሌላውን ጀግና አይንቅም.....ይህ እውነት ነው....ጣልያኖች ሳይቀር ..የራስ አሉላን ጀግንነት መስክረዋል....የደጃዝማች ባልቻ አባ ነፍሶን ወንድነት እሬት እሬት እያለ እየመረራቸውም ቢሆን አውርተውታል......የአንዳንድ የደርግ የጦር መሪዎችን ጀግንነት በአድናቆት የሚገልፁ የወያኔ ኮማንደሮች አጋጥመውኛል....በተቃራኒው ደግሞ ያንዳንድ የወያኔ ኮማንደሮችን ብቃትና ጀግንነት በአድናቆት የሚገልፁ የደርግ መኮንኖችም አሉ.......;...የቀቢፀ ተስፋ እርምጃ የሚባለው አረቦቹ ቦንብ ታጥቀው በሰላማዊ ህዝብ መሀል ፈንድተው የሚሞቱት አይነትን ነው......ያ ጀግንነት አደለም.........በመርዝ ጭስ ሳይቀር ተጠቅሞ የአገሪቷን ህዝብ ለመጨረስ ግዳጅ ተሰጥቶት የመጣን አረመኔ መሪን ለመግደል የሞከሩ ሰዎች ከጀግኖችም በላይ ጀግኖች ናቸው
ከላይ ብዙዎቻችሁ በስሜት የእኔን ኃሣብ ልጣጣጥሉት ስትዳዱ አስተውያለሁ : ቁስላቸው የተነካ የሹምባሽ ልጆችም ተንጨርጭረዋል
ያንተ ሀሳብኮ የእግዚአብሄር ቃል አይደለም.......ብዙዎች ካንተ ጋ አለመስማማታቸው ራሱ ሀሳብህን እንድትመረምር ያደርግሀል እንጂ......ለምን እኔ ያልኩትን እንደ ገደል ማሚቶ አላጋባችሁም ማለትን ምን አመጣው?......ሌሎች ያላቸውን ሀሳብ መግለፅ መሞከራቸው ራሱ አስገርሞሀል.......ለመሆኑ "የኔን ሀሳብ ለማጣጣል የምትዳዱ" ብለህ ለማለት አንተ ማን ነህ?.........የሹም ባሽ ልጅ የሹም ባሾች አለቃን (ግራዝያኒን) ሊገድሉ የሞከሩትን የሚያወግዝ ይመስለኛል........ግራዝያኒ ላይ ግድያ ያደረጉትን ሰዎች በግልፅ እየወረፍክ ብቻ ሳይሆን እያወገዝክ ያለከው ደሞ አንተ ብቻ ነህ :cry:
እስኪ አስቡት በእነ አብርሃ ደቦጭ ድርጊት አሣብቦና አስታክኮ ፋሽስት ጣሊያን በፈፀመው የጅምላ ጭፍጨፋ ምክንያት
@ ..... በሥንት ድካም ኢትዮጵያ ካስተማረቻቸው ወጣቶች መካከል በዚያ አጭር ጊዜ ግማሽ ቁጥር ያላቸውን ማጣት ቀላል ነበር ?
እነ አብርሀ ና ሞገስ ያንን ባያረጉ ኖሮ ፋሽስቱ ጭፍጨፋ አያካሄድም ነበር ማለትህ ነው? ከየካቲት 12 በፊትበግራዝያኒ አመራር ሰጪነት ያለቁት በሺዎች የሚቆጠሩ ኢትዮጵያውያንስ ሰዎች አይደሉም......ጣልያንስ ያን ቀን ብቻ ለዛውም አዲስ አበባ ውስጥ ብቻ ነው ጭፍጨፋ ያደረገው?.......አንተን የሚያሳዝንህ ከተማሩት ወጣቶች አብዛኞቹ ማለቃቸው ብቻ ነው......በየ ክፍለ ሀገሩ እልፍ አእላፍ ሚስኪን ድሀ ያልተማሩ ገበሬዎችስ ከነ ደሳሳ ጎጆዎቻቸው በተኙበት በቦንብ እየተደበደቡ መጋየታቸውስ አያሳዝኑህም?.............ወደድንም ጠላንም ጣልያን የመጣው ሊያሰለጥነን ሳይሆን ባርያ አርጎ ሊገዛን ነበር.........ይህንን የሰለጠነ አረመኔ ሰራዊት ለመጋፈጥ ደግሞ ዋጋ መክፈል ነበረብን.......ዋጋ ከፈልን...አርበኞቻችን ባላቸው አቅምና እውቀት ተጠቅመው ተዋጉ.......የትግል ስልታቸው ኮላተራል ዳሜጅ አልነበረውም ማለት አይቻልም.......ይህን ኮላተራል ዳሜጅ መቀነስ ይችሉ ነበር ሌላ ጉዳይ ነው...ዋናው ጉዳይ ግን መታገል ካለባቸው ይህ ኮላተራል ዳሜጅ መከፈሉ አይቀሬ ነበር.......በጊዜው በነበራቸው እውቀት ደግሞ የተከተሉት ስልት ደግሞ በጦር ት. ቤት አካዳሚ ላልተማሩ ባገር ፍቅር እና አልገዛ ባይነት ስሜት ተነሳስተው ለተዋጉ ሰዎች ፈፅሞ መጥፎ አልነበረም
በአርበኞችስ ትግል ላይ የፈጠረው የአመራር ክፍተትስ ?
ይህንን አንተ ገና ስታነሳ ሰማሁ....አርበኞችመሪዎቻቸው ሲወድቁ በየቀያቸው የጎበዝ አለቃ እየሾሙ ሲዋጉ እንደነበር ነው ሲነገር የሰማሁት.........ቀድሞውኑስ ማዕከላዊ የሆነ የተደራጀ አንድ ወጥ አመራር የት ነበራቸውና ነው........ልክ ትልቅ ክፍተት እንደተፈጠረ የሚነገረው?
..... በዚያ ድርጊት ምክንያት በተፈጠረው የተማረ ኃይልና የሠለጠነ የጦር አመራር እጅጉን መመናመን ሣቢያ የተከሠቱት ችግሮች እኮ አገሪቱ ከፋሽስቶች በአርበኞቿ ትግል ነፃ ከወጣች በኋላ ያፈጠጡ ችግሮች ሆነው ቀጥለዋል
በዚህ ችግር እነ አብርሀ ና ሞገስ እንዴት ተጠያቂ ሊሆኑ እንደሚችሉ አይገባኝም......ከባዕድ አገዛዝ ነጻ ከሆንን በህዋላ ወታደራዊ መሪዎችንና ምሁራኖችን ለመፍጠር ከስክራች መጀመር ነበረብን....የነበሩንን በጣት የሚቆጠሩ ምሁራንና የጦር ሰዎች በጦርነቱ ምክንያት አጥተናል........መላው አገሪቱን ጣልያን በነዚህ ሁለት ሰዎች ምክንያት የወረረ ይመስል እንዲሁም ሁሉንም ነገር በነሱ ምክንያት ነው የሆነው ብሎ ማሰብ እብደት ብቻ ነው
ከ 1933 ዓ .ም . በኋላ የተማረ ኃይል ለማዘጋጀት ምን ያህል ድካም ጠየቀ ?
@ ..... በአስተዳደርስ ረገድ የአፄ ኃይለሥላሤ አገዛዝ በአመዛኙ በባንዶችና በሥደተኞች እየታገዘ አርበኞችን በማግለል ይበልጥ ፈላጭ ቆራጭ ፍጹማዊ የዘውድ አገዛዝ ሆኖ ለመቀጠል ተመቸው ::
አብርሀና ሞገስ ቦንብ ባይወረውሩ ኖሮ የተማረ የሰው ሀይል እጥረት አይኖርብንም ነበር.........የሚገርም አባባል ነው............ጣልያንን አርበኞች ባይነካኩት ኖሮኮ በሌሎች አፍሪካ አገሮች እንደታየው ለዘመናት ቅኝ ገዢ ሆኖ ይቀመጥ ነበር.......አርበኞችምኮ ጫካ ገብተው ባይዋጉ ኖሮ እነሱም ዘመዶቻቸውም አያልቁም ነበር....ቀጥሎ የምፅፍልህን ነገር በደንብ አስተውልና አንብበው
:!: :!: ..መርከብ በወደብ ላይ መልህቁን ጥሎ እስከቆመ ድረስ ምንም አይነት አደጋ አያጋጥመውም.......መርከብ የተሰራው ግን ወደብ ላይ እንዲገተር አደለም :!: :!:
ለነጻነት የሚከፈል መስዋዕትነት ትርፍ እንጂ ኪሳራ አይደለም.........