የአእምሮ በሽታ ( ፐርሰናሊቲ ዲሶርደር)

Issues and Articles of General Interests including topics related to religion

Postby እናመሰግንሃለ » Wed Feb 29, 2012 11:30 pm

ጌታ wrote:ውድ ሳይካትሪስት ቆቁ

ሁላችንም በምናምነው እምነት እርግጠኞች ከሆንንና በቂ ዕውቀት ካለን እንደፀዋር ዓይነቱን ተጠራጣሪ እና ጠያቂ ተገቢ ምላሽ በመስጠት አፍ ማስያዝ መቻል ያለብን ይመስለኛል:: አለበለዚያ ውግዘትና ስድብ ካበዛን ጥያቄውን በመመለስ ፈንታ ጥርጣሬውን እናበዛበታለን:: አጥጋቢ መልስ ካላገኘ አታውቁም ቢል ያማኑኤል ሰው አያደርገውም::

ስለሆነም ዕውቀት ያላችሁ ሁሉ ይህን ተጠራጣሪ ወንድማችንን እና እሱም ተጠራጣሪ ሊያደርጋቸው የሚችሉ መሐል ሰፋሪዎችን ለመታደግ በቂ ምላሽ ስጡት:: ካላወቃችሁም የሚያውቁን ጠይቃችሁ ከተጠራጣሪነት ወደ አማኝነት ለውጡት:: ለዚህም እግዜር ይርዳቹ::


ጌታ:

አንተና ጸዋር የሚያመሳስላችሁ አንድ ነገር አለ::

ያም: ሁለታችሁም ለአንድ ሃይማኖታዊ ጥያቄ ወደየትም የማያስኬድ የመጨረሻ መልስ ሲሰጣችሁ "አሃ! እንደዛ ነው እንዴ? ገባኝ" በማለት ፈንታ "ሺት! በዚህ በኩል አልተሳካም! ሌላ ጥያቄ ፈልጌ ልምጣ" በሚል አስተሳሰብ ትንፋሻችሁን ዋጥ አድርጋችሁ ለትንሽ ጊዜ ትጠፉና በሌላ ጥያቄ ትመለሳላችሁ:: ለመሆኑ ታስታውሳለህ ዐውቆ በሚሳሳትና ሳያውቅ በሚሳሳት መሃል ስለሰጠሁህ ትንታኔ? ታስታውሳለህ ስለክርስትናና ስለሌሎች "ሰላማዊ" መሳይ የሩቅ ምስራቅ እምነቶች ልዩነት ስለሰጠሁህ ትንታኔ? ታስታውሳለህ ክርስቶስ ጠላታችሁን ውደዱ ሲል ምን ማለቱ እንደሆነ በማብራራት ስለሰጠሁህ ትንታኔ? ታስታውሳለህ አመንዝራዪቱን ሴት ደካማው የሰው ፍጡር ባይወግራትም እግዚአብሔር ግን ንስኃ ካልገባች በቀር ሊወግራት ብቻ ሳይሆን በገሃነምም ሊያቃጥላት መብቱም ዳኝነቱም ዕውቀቱም ትክክለኛነቱም እንዳለው የሰጠሁህን ትንታኔ? ከያንዳንዳቸው ከነዚያ ፖስቶች በኋላ እኮ "ተስማምተናል: ገባኝ" በማለት ፈንታ "ውይ ለካ መጽሐፍ ቅዱስ በጭፍን በማመን እንጂ በመጠየቅ አይረዱትም?" የሚል ዓይነት የማላገጥ መልስ ሰጥተህ ነው ሽንፈትህን ሸውደህ ለማለፍ የምትሞክረው? ወይም ደግሞ ገባኝም አልገባኝም ተቀብያለሁም አልተቀበልኩምም ሳትል ዝም ብለህ ትጠፋለህ:: ከዚያ መልሰህ ደግሞ ያንኑ ጥያቄ ያንኑ ንባብ ፖስት ታደርጋለህ- በሌላ ውይይት መሃል::

ጌታ ያንተ አካሄድ እኔን ስለገባኝ: ቢያንስ እኔ: ጠያቂና ተረጂ ለመመምሰል የሚሞክሩ ፖስቶህች ሳነብብ ምን ያህል የዚያ ተቃራኒ በመሆንህ ልታዘብህ እንደምችል በመገመት: ለራስህ ሕሊና እውነተኛ ለመሆን ስትል: ወንድ ሁንና ጭምብልህን አውልቀህ በመናፍቅነትህ ሳታፍር እንደ ኢ-አማኒነትህ በጸዋር አይነት ድፍረት ተገለጥ!!! ዕድሜህ ቢሄድም በጉርምስናህ ወራት የነበረህ ድፍረት እንጥፍጣፊውም ቢሆን አጥንትህ መቅኖ ውስጥ አይጠፋም ብዬ ተስፋ አደርጋለሁ::
እናመሰግንሃለ
ዋና ኮትኳች
ዋና ኮትኳች
 
Posts: 824
Joined: Mon Jun 01, 2009 8:07 pm

Postby ፀዋር » Wed Feb 29, 2012 11:50 pm

ቆቁ wrote:አራቱ እንሳሳት የሚታመኑ ናቸው የሚል ነገር ከየት ነው ያመጣኽው ?


ሰላም ሳይካትሪስታችን :D
አሁንም ቅንጥብጣቢ ነው ያለው? ጭንቅራት ስጋ የለም? :D
እንደበሽተኛህ እና አንተም እንደ ሀኪሜ እስኪ አስረዳኝ በዚህ አምድ ምን ስል ስለ እንስሳት አወራሁ :?: በሌላ አምድ ያነበብከውን እዚህ እያመጣህ ከሆነ እኔ ሀኪምህ አንተ በሽተኛዬ ነው መሆን ያለብን:: ውይይቱን ከፈለግክ በቦታው አስተናግድሀለሁኝ:: ጤነኛ መሆንህን ግን ማወቅ እፈልጋለሁ:: Show me? :lol:
ፀዋር
ዋና ኮትኳች
ዋና ኮትኳች
 
Posts: 507
Joined: Tue Feb 16, 2010 12:40 pm

Postby ቆቁ » Fri Mar 02, 2012 8:25 pm

ጸዋር ወደጄ
ስማ እኔ ነኝ ሳይካትሪስቱ አንተ ነህ ?

ይሄ እኮ ነው የናርዚስቲክ ፐርሶናሊቲ ዲሶርደር

በኔ የሕክምና ጣቢያ ምርመራው የሚካሄደው በዋርካ ላይ ከሰፈረው ጽሁፍ ነው እንጂ
በመዶሻ የኒ ጀርክ እንቅስቃሴን በመውሰድ
ወይም ከቬይንህ ላይ ደም በመቅዳት
ወይም ፐርጋቲቭ በማጠጣት
ወይም ባርየም ሶልት በማስዋጥ የሚካሄድ ምርምር እንዳልሆነ እንዴት ማወቅህ ተዘነጋህ

ወደ ዋናው ነጥብ
አራቱ እንስሳት ስትል ለመሆኑ ያነበብከው በትክክል ገብቶህ ነው ?

በአራቱ እንስሳት አምናለሁ ያለህ ማነው ወይስ ሀሉሲኔሽን ውስጥ ነው የምትገኘው ?
ሳይካትሪስቱ ቆቁ
ቆቁ
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 4027
Joined: Sun Sep 21, 2003 9:57 am
Location: united states

Postby ቆቁ » Fri Mar 02, 2012 9:18 pm

ወዳጄ ጸዋር
Who wrote the Bible በሚለው ጽሁፍህ ላይ
ኦሪት ዘዳግም ምእራፍ 34ን አስመልከተህ ያዙኝ ልቀቁኝ እያልክ መሆንህን ሳይካትሪስቱ ቆቁ እየተመለከተ ነው::

እስቲ ተጠየቅ

ምእራፍ 34 ብቻ ላይ በማተኮር ሙሴ ሌሎቹን ጽሁፎቹን አልጻፋቸውም ለማለት ምን ማስረጃ አለህ ?

በምእራፍ 34 ላይ የተገለጸው የሙሴ የመጨረሻ ጊዜ ነው

ለመሆኑ በአንተ ቀዌ ጭንቅላት ሙሴ እስከ እለተ ሞቱ ድረስ ብእርና ወረቀት ይዞ ይጉዋዛል የሚል ጽሁፍ የት ላይ ነው መርቅነህ ወይም ሐሉሲኔሽን ውስጥ ገብተህ ያነበብከው ?

ከምእራፍ 34 በፊት በተጻፉት የሙሴ ጽሁፎች ላይ ስለ ሙሴ ስለ ራሱ የተጻፈ አንበሀል ?

ጸዋር ወዳጀ
ይህ ዘዳግም ምእራፍ 34 ባይጻፍ ኖሮ ከኦሪት ዘፍጥረት እስከ ዳግም ድረስ ያሉት ጽሁፎች በሙሴ ተጻፉ አልተጻፉም በማለት ሊያከራክር የሚችል ነጥብ አለው ለማለት ያስደፍራል ?


ሳይካትሪስቱ ቆቁ
ቆቁ
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 4027
Joined: Sun Sep 21, 2003 9:57 am
Location: united states

Postby ሱልጣን » Sat Mar 03, 2012 1:53 pm

ፈላስፋው ቆቁ የጥንቱ የጠዋቱ
እንደምን አለህ?
ስምህን ካኘው ዘንድ ሰላም ልበልህ ብየ ነው
አየ ዋርካ!!!!! ቁም ነገር እንዳማረን ...............
እኛስ አረጀን...ይብላኝ ለወጣቱ :roll:
HONESTY~TRUSTWORTHINESS~SINCERITY
''Whoever is carless with in small matters....
Cannot be trusted in important affairs''
ሱልጣን
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 261
Joined: Wed Sep 03, 2003 11:38 am

Postby ቆቁ » Tue Mar 06, 2012 5:52 pm

ሰላም ሱልጣን

ተረጋግቶ መወያየት ተረጋግቶ መደማመጥ ከቀረ ሰነበተ

እኔ ከፈላስፋነት ወደ ሳይካትሪነስት መቀየሬ ስለ ሁኔታው ግልጽ ሳያደርግልህ አይቀርም

ፐርሶናሊቲ ዲሶርደር ያለባቸው ሰዎች በዋርካ ላይ ብቅ ብቅ ማለት ከጀመሩ ሰንበትበት አሉ እኮ

ዛሬ ኦርቶዶክሱን ነገ ሙስሊሙን ከነገ ወዲያ የገዛ እናቱንና አባቱን የሚኮንን ናርዚስቲክ ፐርሶናሊቲ ዲሶርደር በዋርካ እየታየ ነው

ይህ ዲሶርደር ያው ሳይካትሪስቱ ቆቁ አንዳንድ በዚህ በሽታ የተለከፉትን ግለሰቦች እያስመለከተ ያስቀምጠዋል::

ለምሳሌ ጸዋር
"" ለውጥ ያስፈልጋል .. ብሎ ጀምሮ ክርስቲያኒቲ ይውደም በማለት ላይ ይገኛል

ስለ ነቢይ እና ነቢያት ለማብራራት ሞክሯል በዚህ ሙከራው እሱ ጸዋር ያለፈ ጊዜ ነቢይ ለመሆን እየሞከረ ነው ::

የጸዋር ነቢይነቱ እንደ ድመት ሽንት : ወደ ሁዋላው ነው
ይህ ነው ፐርሶናሊቲ ዲሶርደር ማለት
ሳይካትሪስቱ ቆቁ
ቆቁ
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 4027
Joined: Sun Sep 21, 2003 9:57 am
Location: united states

Postby ፀዋር » Tue Mar 06, 2012 6:44 pm

ቆቁ wrote:ለምሳሌ ጸዋር
"" ለውጥ ያስፈልጋል .. ብሎ ጀምሮ ክርስቲያኒቲ ይውደም በማለት ላይ ይገኛል

ስለ ነቢይ እና ነቢያት ለማብራራት ሞክሯል በዚህ ሙከራው እሱ ጸዋር ያለፈ ጊዜ ነቢይ ለመሆን እየሞከረ ነው ::

የጸዋር ነቢይነቱ እንደ ድመት ሽንት : ወደ ሁዋላው ነው
ይህ ነው ፐርሶናሊቲ ዲሶርደር ማለት
ሳይካትሪስቱ ቆቁ


ሠላም ቆቅነት

"ባይብልን የጻፈው እ/ር አይደለም" ብሎ መከራከር እንዴት "ክርስቲያኒቲ ይውደም ማለት ነው" ተብሎ እንደሚተረጎም ባውቅ ደስ ይለኛል:: ለውጥ ያስፈልጋል? በትክክል ያስፈልጋል:: ክርስቲያኒቲን በማውደም ሳይሆን ባለበት ድከመቶቹን በማረም:: ለምሳሌ ክርስቲያን ሁሉ እ/ር ነው ብሎ ከሚያምነው ውጪ በባዕድ አምልኮ ጊዜውን: ጉልበቱንና ገንዘቡን ከመጨፍጨፍ ሊቆጠብ ይገባል:: ለተክልዬ: ለሳምሪ: ለሚካኤል: ለጥብርኤል: ለግብርኤል: ለጊዮርጊስ: ለመነኮሳት: ለማርያም: ... ወዘተረፈ በየወሩና በየአመቱ የሚደረግ የአምልኮትና የድግስ ርብርቦሽ መቆም አለበት:: ተስፋ ሊጣልበት በማይገባ ነገር ላይ ትውልዱ ተስፋ ጥሎ: እጅና እግሩን አጣጥፎ በመቀመጥ; ሰርቶ መብላት ሲችል በምጽዋት: ነጻነቱን አስከብሮ መኖር ሲችል በጭቆና እየተረገጠ መኖር ይብቃ! ሊል ይገባል:: ስለዚህ ለውጥ ያስፈልጋል:: እውነተኛ ለውጥ ከፈለግን ደግሞ በቅድሚያ የለውጥ እንቅፋት ይወገድ::

ባይብል በእ/ር አልተጻፈም ብዬ መከራከሬም "የለውጥ ያስፈልጋል" መፈክሬ አካል ነው:: እያንዳንዱን ቃል ከእ/ር እንደሆነ ማመን ማለት: አንደኛ የእ/ርን አዋቂነት መገዳደር: ሁለተኛ የሰው ልጅን የአስተሳሰብ አድማስ አፍኖ ማስቀረት ማለት ነው:: የሰው ልጅ እንኳንና ከቅዱሳን መጻህፍት ይቅርና (በፍርሀት ተሸብቦም ቢሆን) ከራሱ ታሪክም የሚማርና የሚያመዛዝን ፍጡር ነው:: ስለዚህ ጠቃሚ የሆኑትን ትምህርቶች እየተከተለ ምንም አይነት ምክንያታዊነት የሌላቸው ባዶ ትረካዎችን ለታሪክ ወደ ጎን እየተወ ህይወቱን መምራትና ስልጣኔውን መግራት ይገባዋል:: That's how all religions, through out the history of man, evolved.

በሀዮች አንድ የሚሉት ነገር አላቸው:: የሙሴ ህግና ትንቢት በሙሴ ዘመን ለነበረው ትውልድ እንደመረዳቱ ብቃት ከእ/ር የተሰጠ ትምህርትና መመሪያ ነው ይላሉ:: ያ ትምህርትና መመሪያ ለዚህ ዘመን ትውልድ አይመጥንም:: እንኳንና ለዚህ ዘመን ትውልድ ቀርቶ ከ2000 አመታት በፊት ለነበረውም አይመጥንም ነበር ይላሉ:: ስለማይመጥን ደግሞ እ/ር በሌላ ነብይ (ክርስቶስ) በኩል ዘመኑን የሚመጥን የተሻሻለ ትምህርትና የህይወት መመሪያ (አዲስ (ቃል) ኪዳን) ሰጠ:: ዛሬ የሰው ልጅ የአስተሳሰብ አድማሱ ሲሰፋ ደግሞ እንዲሁ አንድ መሲህ ላከልን ብለው ያምናሉ:: ያ መሲህ - ቡሀኡላህ ነው:: የበሀይ እምነት መስራች ነው:: የመጨረሻው መሲህ ነው ብለውም ያምናሉ:: የመጨረሻ ሲባል ከሱ ብኋላ የሚመጣ የለም ማለት አይደለም:: ወደፊትም እንዲሁ ዘመኑን የሚመጥን ነቢይ ይነሳል:: ዛሬ በምድር ላይ ያሉት ሁሉም እምነቶ እ/ር ወደዚች ምድር በላካቸው ነቢያት አማካኝነት የተመሰረቱ ናቸው ብለው ያምናሉ:: ቡድሀ: ሙሀመድ: ክርስቶስ: ክሪሽማ: ወዘተ ወዘተ ወዘተ ... የተለያዩ ሀይማኖት የሆኑበት ምክንያት ከአለማችን ስፋት አንጻር ህዝቡ ተበታትኖና ተራርቆ ይኖር ስለነበረ ነው:: ዛሬ አለም በሰው ልጅ የአስተሳሰብ አድማስ መስፋት ምክንያትና በቴክኖሎጂ ምጥቀት እንደ አንዲት ቀበሌ (ቪሌጅ) የምትታይበት ሁኔታ ስላለ ትውልዱ አንድ መሆን በአንዲት ጥላ ስር መቆም አለበት ብለው ያምናሉ:: ክርስቲያን ሙስሊም ቡድሂዝም ሂንዱይዚም ... የሚባል የሽፋን ስም ተወግዶ በአንድ ጥላ ስር በመሰባሰብና ለሰላምና ለአንድነት በመዘመር ትውልድ ሁሉ የአንድ አባት አባላት የአንድ ሀይማኖት ተከታይ የሚሆንበትን የእምነት ክሪድ ይዘው ይንቀሳቀሳሉ::

እንግዲህ ይህ የሚያሳየን ከጠባቧ የያኔዋ የእስራኤል ምድር ጀምሮ እስከዛሬ ድረስ የሰው ልጅ ሀይማኖት እንዴት evolve እያደረገ እንዳለ ነው::

የኛ አገር እምነትም ባለበት የሚቆምበት ምንም ምክንያት የለም:: ለወጥ ከፈለግን መጀመሪያ መለወጥ ያለበትን እንለውጥ:: እንቅፋቱን እናስወግድ::

(ፕሊስ ሀሳብህን አስር ቦታ ሳትቀነጣጥብ ለመረዳት እንዲመች ወጥ አድርገህ ጻፍ)

ሠላም
ፀዋር
ዋና ኮትኳች
ዋና ኮትኳች
 
Posts: 507
Joined: Tue Feb 16, 2010 12:40 pm

Postby ቆቁ » Wed Mar 07, 2012 5:10 pm

ጸዋር ወዳጄ
ምንድነው ስልጣኔ ?

ስልጣኔ የሰው ልጆች ስራ ነው: ይህ የሰው ልጆች ስራ ደግሞ በተለያየ እምነታቸው የፈጠሩት ስራ ነው::

ቡድሀ በለው ክርስቲያኑ ወይም እስላሙ በጠቅላላው የተለያየ ሐይማኖት ተከታይ በሙሉ ነው ለዚህ አንተ ሲቪላይዜሽን ወይም ስልጣኔ ለምትለው ነገር በጋራ የተሰለፈው::


እንዳንተ አባባል ክርስቲያኒቲ ወደ ሁዋላ ጎተተን
እስልምና ወደ ሁዋላ ጎተተን የሚል የተዘዋዋሪ አነጋገር
የፐርሶናሊቲ ዲሶርደር ውጤት ነው::

ከዛም አልፈህ አነጣጥረህ የኢትዮጵያን ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን ነው ለመዝለፍ የምትንጠራራው ከዛ ደግሞ አለፍ ትልና የኢትዮጵያን ሙስሊሞች ለመጥረብ ነው አካሄድህ

በመጀመሪያ በፐርሶናሊቲስ ዲሶርደር የምትመራ መሆንህ የሚካተተው ሌላውን በመንቀፍ ለዛውም በማታውቀው ነገር እኔ ከሁላችሁም እበልጣለህ በማለትህ ይሆናል

የሐገራችን የኢትዮጵያ ችግር የእምነት ጉዳይ አይደለም የናርዚስቲክ ፐርሶናሊቲ ዲሶርደር ችግር ነው::

መጽሓፍ ቅዱስን እግዚአብሄር አልጻፈውም
ቁርዓን አላህ አልጻፈውም እያልክ በመደነስ ላይ ትገኛለህ

የማንንም እምነት ሳትወቀስ እስቲ የአንተን በጎ አስተሳሰብ ወርውርልን


ስልጣኔ የምትለው ከግብጽ ፒራሚድ እስከ ዛሬው የኮምፑውተር ዘመን አድርሶናል ይህ ደግሞ በማንኛውም እምነት ላይ ተጽእኖ አልነበረውም

እስልምና ክርስትና በስልጣኔ ላይ ተጽእኖ ቢኖረው ኖሮ ዛሬ አይንህ እስከሚጠፋ የምትጠቀጥቀው ኮምፑተር ባልተፈጠረ ነበር::


ስማ በዚች ምድር ላይ ተስፋ ያስፈልጋል
ያለተስፋ መኖር እንደማይቻል ፓወርፉል የሆኑት ሳይንቲስቶች እነ አልበርት አንስታይን የጻፉት የተናገሩት ነገር ነው::

የሰው ልጅ ያለተስፋ ኖረ ማለት እንዳንተ ናርዚስቲክ ፐርሶናሊቲ ዲሶርደር ውስጥ ተዘፈቀ ማለት ይሆናል::
በመጨረሻው ሰዓት ዝብርቅርቅ ውስጥ መግባት ማለት ይሆናል::

እግዚአብሄር መጽሓፍ ቅዱስን አልጻፈውም ስትል ምን ማረጋገጫ አለህ ?

እግዚአብሄር ዩኒቨርስን አልፈጠረውም ስትልስ ምን ማረጋገጫ አለህ ?

ዩኒቨርስ እንደ መጽሐፍ ቅዱስ እንተሮፕይ ወይም ካኦቲክ ነው

ነገር ግን በሰው ልጆች ሕይወት ላይ ያለፉት ሁላ ተመዝግበውበታል ::

መጽሐፍ ቅዱስ ላይ ከተጻፈው ውጭ በአሁኑ ዘመን አንድም ነገር የለም"

ጦርነት በለው ውይም ሽርሙጥና በለው ወይም እብደት በለው ወይም ጤንነት በሙሉ በዚህ ቅዱስ ቃሉ ላይ ሰፍረው ይገኛሉ::

እግዚአብሄር ቢጽፈው ኖሮ ሁሉም ትክክል ይሆናል የሚል የቀዌ አስተሳሰብ ይዘህ መምጣትህ ትልቅ ሕክምና የሚያስፈልገው መሆኑን ሳካትሪስቱ ቆቁ ያምናል


የዩኒቨርስ መስፋት የግራቪቲሽናል ፎርስ የማእበል መፈጠር የእሳተ ገሞራ መፈጠር የመሬት መሽከርከር የፕላኔቶች ተሳስቦ መኖር
የመሬት ከጁፒተር ማነስ የጸሐይ መንቦልቦል ዛፍ ከሳር መብለጡ የአበቦች ልዩነት እረ ስንቱ

ለምን አበቦች ሁላ ጽጌረዳ አበቦች አልሆኑም ?

ለምን እንስሳት ሁላ ሰዎች አልሆኑም? የሚል ዝብርቅርቁ የወጣበት ናርዚስቲክ ፐርሶናሊቲ ዲሶርደር ማለት ይህ ነው::

የአንተ አፍንጫ የኔ የሳይካትሪስቱ አፍንጫ እና የዋለልኝ አፍንጫ መለያየቱ: የአንተ ጉንጭ እና የስልኪ ጉንጭ ከዛም የማነው ደግሞ የዛ ልጅ ጉንጭ መለያየቱ ምን ይባላል ?

ለምን እግዚአብሄር ዋለልኝና እና ጸዋር አንድ አድርጎ አልፈጠረም ?

እንደውም ዋለልኝና ጸዋርን እግዚአብሄር አልፈጠረም ?

ለመሆኑ እግዚአብሄር ወይም አላህ ማነው? ብለህ ለመቀዣበር የሚያንጠራራህ ይህ የናርዚስቲክ ፐርሶናሊቲ ዲሶርደር ነው
ሳይካትሪስቱ ቆቁ
ቆቁ
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 4027
Joined: Sun Sep 21, 2003 9:57 am
Location: united states

Postby ቆቁ » Mon Mar 12, 2012 7:23 pm

ጸዋር ወዳጄ

ሐይማኖት ወደዚያ ሳይንስ ወደዚህ ብሎ የቀደደልህ ማነው ?


ሳይንስ ያለ ሐይማኖት ወይም ከሐይማኖት በፊት ሳይንስ ሳይሆን ሳይህንስ ከሐይማኖት ወይም ከእምነት በሁዋላ የተገኘ የሰው ልጆች ስራ ነው::


ይህም ማለት ያለ እምነት ሳይንስ ቦታ አልነበረውም ማለት ይሆናል

ጋሊሊዮ መነኩሴ ነበር:
መንድሊቭ መነኩሴ ነበር
ሁለቱንም መነኩሴዎች ብትመለከታቸው ለእግዚአብሄር ያላቸውን እምነት ጠብቀው ነው ጋሊልዮ የመሬትን መዞርና የግራቪቲሽናል ፎርስን ሳይንቲፊክ ውጤት የቀመረው

መንድሊቭ የጀነቲክ ቲዎሪ የቀመረው ገዳም ተቀምጦ ነው::
ዛሬ የኔና የአንተ ከዛም አልፎ የስልኪና የዳግማዊ አፍንጫ የማይመሳሰለው በዚህ በሜንዲሊቭ ቲዎሪ በጀነቲክ ቲዎሪ አማካይነት ነው

መንድሊቭና ጋሊሊዮ ብቻ አልነበረም
ዛሬ ጭንቅራትህ እስኪዞር ድረስ የምትቀመቅመውን ቢራ እና አረቄ በኬምስትሪ አጠናቀው የደረሱበት የካቶሊክ መነኮሳት ናቸው::
የጊርና የብሎን ወይም የሌላ መካኒካል ይሆኑ ነገሮች ሁላ ከዛም አልፎ ለእንፋሎት ሞተር መነሳት ምክንያት የሆኑት የገዳም መነኮሳት ናቸው::

እነዚህ የገዳም መነኮሳት ለእግዚአብሄር ያላቸው ፍቅር ግን በዚህ መካኒካል ወይም ኬሚካል ወይም ፊሲካል ወይም ባዮሎጊካል ግንኝት አንድም አልተናወጠም::

የፈጣሪ ስራ እጅግ የተራቀቀ ነው በማለት ነው እምነታቸውን የቀጠሉት

"" ለውጥ ያስፈልጋል "" ስትል እኔም እንደዚህ ያለ ለውጥ ለማምጣት የምትፈልግ ወንድሜ መስለኽኝ ሐሳብ እየሰጠሁ ለመወያየት ሞክሬ ነበር


አሁን ግን ሳይህ ናርዚስቲክ ፐርሶናሊቲ ዲሶርደር ውስጥ የምትገኝ ወንድሜ መሆንህ ተገንዝቤአለሁ

ሳይካትሪስቱ ቆቁ
ቆቁ
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 4027
Joined: Sun Sep 21, 2003 9:57 am
Location: united states

Postby ሀዲስ » Sun Mar 18, 2012 8:07 am

ጠያቂውና ፈላስፋው ቆቁ:- ጥያቄዎችህን እንደ ድሃ አጥር ራቅ ራቅ አድርገህ ከመትከል ብቻ ወደ መጠነኛ አገላለጽ ስለ ተሸጋገርክ ደስ ብሎኛል::

ምናልባት የአእምሮ ሁኩት ከተጠናወታቸው ህሙማን ጋር ብዙ ሠዓታት ስለምታሳልፍ ይሆናል የምትደበላልቀው:: ስለ እብደት ስታወራ ራስክን እየጠበቅ ይሁን:: ሳይካትሪስቶች ባለ በሌለ ኃይላቸው ስለ እብደት ሲያወሩ መጠንቀቅ እንዳለባቸው አንብቤአልሁ:: እንዳይንሸራተቱ ሊሆን ይችላል:: ቆቁ ሆይ:- ዋርካ እኮ አሁን ጤና ናት:: ጨረቃ ዋርካንም ታደምቃለችና ስለ ዋርካ ጤንነት አሁን ብዙ አትጨንቅ:: ተጨንቀህ ከማስጨነቅ እውቀትህን አካፍለን:: ፈላስፋዎች አስተማሪ ናቸው:: አንተ ጠያቂና አስጨናቂ ብቻ አትሁን:: መልስ የሌለው አሪፍ ጥያቄ ምን ዋጋ አለው? (አሪፍ ጥያቄ ስትል ምን ማለትህ ነው ብለህ ናልኝ አሉ ደሞ)

ልጅ ፀዋር:- አንተም በፈንታህ አላማህን ግልፅ አድርግ:: እንደ በዓሉ ግርማ የኔ ሃይማኖት ሕይወት ናት የሚል ፈሊጥ ይዘህ እዚህ ጥያቄዎችህን በክብር የሚያስተናግድልህ የምታገኝ አይመስለኝም:: መቃብርህም አይታወቅልህም:: ልክ እንደ በዓሉ! እውቀትህን ለማካፈልና ታዳሚውን ኢምፕረስ ለማድረግ የ "ሃይማኖት"ን ርዕስ መምረጥህ ብልህነት አይመስለኝም::

መልካም ትምሕርት
ሀዲስ
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 231
Joined: Sat Dec 18, 2004 6:29 am
Location: united states

Postby ፀዋር » Sun Mar 18, 2012 11:25 pm

ሀዲስ wrote:
ልጅ ፀዋር:- አንተም በፈንታህ አላማህን ግልፅ አድርግ:: እንደ በዓሉ ግርማ የኔ ሃይማኖት ሕይወት ናት የሚል ፈሊጥ ይዘህ እዚህ ጥያቄዎችህን በክብር የሚያስተናግድልህ የምታገኝ አይመስለኝም:: መቃብርህም አይታወቅልህም:: ልክ እንደ በዓሉ! እውቀትህን ለማካፈልና ታዳሚውን ኢምፕረስ ለማድረግ የ "ሃይማኖት"ን ርዕስ መምረጥህ ብልህነት አይመስለኝም::


ምን መሰለህ ሀዲስ, ዛሬ የምትኖርባት ምድር (አገር) አገራችን ኢትዮጵያን ጨምሮ ያቆያት ምን እንደሆነ ታቃለህ? እነዚህ "መቃብራቸው ያልታወቀላቸው" ጀግኖች ናቸው:: የት ይሙቱ, እንዴት, በማን ... ምንም ሳይታወቅ በየስርቻው ተጥለው እስከዘላለሙ ያሸለቡ ጀግኖች ናቸው:: ለአላማ ኖሮ ከመሞት በላይ የበለጠ ነገር ምን አለ? የህይወት ሙላት ሞት ነው! ደቂ እስጢፋ እውነትን ስላስተማሩ ብቻ በቁማቸው ተቃጥለዋል:: የዚህን ቤ/ክ/ያን ታሪክ ትንሽ ብታውቅ እንዴት ልትንገበገብ እንደምትችል አትጠይቀኝ:: ይህን ስልህ የተሳሳት ግንዛቤ እንዳትይዝ:: ታሪካቸውን አይደለም ዛሬ የምነወቅሰው ወይም ተጠያቂ የምናደርገው:: ታሪኩ የሁላችንም እንደመሆኑ መጠን ታሪኩ ላይ ጸብ የለንም:: የሆነው ሆኖ አልፏል:: ፍልሚያችን "የትላንቱን የድንቁርና መንገድ የግድ ካልተከተልን ሞተን እንገኛለን" ከሚሉት የዛሬ ቄሶቻችን ጋር ነው:: ያም ሆኖ ጦር መሰበቅ ድሮ ቀረ:: ዘመኑ የብዕር ነው:: በብዕርህ ትዋጋለህ:: እየጠየቅክ: ብዥታን እየፈጠርክ: እያፍረከረከው ትቀጥላለህ:: አንድ ቦታ ላይ የግዱን እጁን ይሰጣል::

ሠላም
ፀዋር
ዋና ኮትኳች
ዋና ኮትኳች
 
Posts: 507
Joined: Tue Feb 16, 2010 12:40 pm

Postby ሀዲስ » Mon Mar 19, 2012 9:14 am

ፀዋር ሠላም ላንተ:-
የዛሬ ቄሶቻችን ከምትላቸው ጋር የያዝከው ክርክር እምነትን ከማጥላላት ጋር ብሎም ሃይማኖትን ውድቅ በማድረግ ላይ የተመርኮዘ ባይሆን የያዝከው ጉዞ ብዙዎችን ሊስብና ሊያሳትፍ ይችላል ብዬ አስባለሁ:: ድምጽ ያለው ክርክር ማቅረብ ትችላለህ:: አርት ኦፍ ዲቤት ዋርካ ላይ ዜሮ ነው....ሞቷል....አንተ ልታነሳው ከፈለክ ግን የሌላውን ሃይማኖት ገለህ መሆን የለበትም:: ያመኑበትን ሳትሸረሽር መልዕክትህን ማስተላልፈ የምትችልበትን ፎርሙላ ፈልግ:: ....no matter how stupid they are, believe in positive thinking... እነዚህ 'ኮ መጽሀፋችሁ በማን ተጻፈ? ስላልክ ሙሄ....ሙሐመድ እያሉ የሚጠሩህ የሩቅ ግን የአገራችን ሠዎች ናቸው:: በአንድ በኩል እርግጥ ዙሪያቸውን አማትረው የሚያስተውሉ: የሚያደምጡ: የሚማሩና የሌላውን የግል እምነት የሚያከብሩ ስላይደሉ ምንም አይነት ፎርሙላ ለነሱ አይገጥምም ይሆናል:: የሌላውን ሃይማኖት የማያከብር ደግሞ የሱን ሃይማኖት እውነታ እየተነተኑ ሪአክሽናቸውን መፈተኑ አስፈላጊ የሚሆንበት አጋጣሚ ይፈጠራል::

ዲጎኔ (አሻሽሎ ማለት የነበረበት) ሁላችሁም ያገር ልጆች ናችሁ .... :)
ሀዲስ
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 231
Joined: Sat Dec 18, 2004 6:29 am
Location: united states

Postby እናመሰግንሃለ » Mon Mar 19, 2012 2:45 pm

ወይኔ...! ሰበር ዜና...! ጸዋር ለክርስትና ሃይማኖት የተሰዉት ደቂቀ እስጢፋኖሳውያንን ሲያንቆለጳጵስ ተያዘ:: :lol: :lol: :lol:

ጸዋር እንደከተበው...

ለአላማ ኖሮ ከመሞት በላይ የበለጠ ነገር ምን አለ ? የህይወት ሙላት ሞት ነው ! ደቂ እስጢፋ እውነትን ስላስተማሩ ብቻ በቁማቸው ተቃጥለዋል :: የዚህን ቤ /ክ /ያን ታሪክ ትንሽ ብታውቅ እንዴት ልትንገበገብ እንደምትችል አትጠይቀኝ ::


ከዚህ ውጪ ምን ላነብብ እመኝ ይሆን! :lol: :lol: :lol:

የሚገርመው እኮ እነዚሁ ደቅ እስጢፋ ከቤተክህነት ፖለቲከኞች አልፈው ግብጥ አገር ያሉ መሐመዳውያን አገረ-ገዢዎችን ያርበደበዱና ለነርሱም ያላጎበደዱ ጀግኖች መሆናቸው ነው:: (እህየው! ሀዲስ ሊናደድ ነው! :lol: )

ጸዋር እስከዛሬ ኤቴዪስትም ዴዪስትም ስትባል ነበረ:: አሁን ሳስበው እርሱም ይበዛብሃል:: ዝም ብለህ እንደለማኝ ፍርፋሪ ከተለያየ ኮርነር የተለቃቀመ ጸረ-ተዋሕዶ ፕሮፓጋንዳ ጋርቤጅ ነህ:: ለምን ኦርቶዶክስ ተዋሕዶን መቃወም እንደፈለግህ ራሱ ለራስህም አልገባህም:: ላይህ ላይ ያለው ጥብርኤል እንደጉድ ነው የሚጋልብህ ጃል! :lol: :lol:

እስቲ አሁን መጽሐፍ ቅዱስን እግዚአብሔር አልጻፈውም ብሎ የሚከራከር ሰው...እንደገና መልሶ በመጽሐፍ ቅዱስ ሊትራል አተረጓጎም ላይ ያላቸው እምነት ከቤተክህነትና ቤተመንግሥት ስታተስኮ በልጦ እስከመስዋዕትነት ያደረሳቸውን ደቅ እስጢፋኖስን ያንቆለጳጵሳል? :lol: :lol:

ገብቶሽ ሳለ 'ምታደርቂኝ አሉ አብዬ! እንደዛሬ ስቄም አላውቅ!!
እናመሰግንሃለ
ዋና ኮትኳች
ዋና ኮትኳች
 
Posts: 824
Joined: Mon Jun 01, 2009 8:07 pm

Postby ፀዋር » Mon Mar 19, 2012 2:46 pm

ሀዲስ wrote: ያመኑበትን ሳትሸረሽር መልዕክትህን ማስተላልፈ የምትችልበትን ፎርሙላ ፈልግ:: ....no matter how stupid they are, believe in positive thinking...


ሠላም ሀዲስ

መልካም አስተያየት ነው የሠነዘርከው:: ተግባራዊ ባላደርገውም እኔም የማምንበት ይህን ነበር:: ግን ምን ታደርገዋለህ እነዚህ ሰዎች ሀሳብን በአግባቡ ማስተናገድ አይችሉም:: ከሁለት አመት በላይ ሊሆነኝ ነው ዋርካ ስሳተፍ:: መሳተፍ ከጀመርኩበት የመጀመሪያ ሳምንት ጀምሮ እስከቅርብ ጊዜ ድረስ አንተ በምትለው እና እኔም በማምንበት መልኩ ቀስ እያልኩ ለማወያየት እሞክር ነበር:: ሰዎቹ ግን የሚቀድማቸው ብልግና ነበር:: የስድብ መዓት እላዬ ላይ ይቆልሉታል :lol: ሲጠየቁ እንደማይወዱ ስለማውቅ ራሳቸውን በስድብ ለመደበቅ ሲሞክሩ ብዙም አይደንቀኝም ነበር:: "ለውጥ ከፈለግን በመጀመሪያ እኛው እንለወጥ" በሚለው አምዴ እምነታቸውን ወደ ጎን ትቼ በቀጥታ መጥፎና ትክክል ያልሆኑ ልማዶች ላይ አነጣጥሬ ስጽፍና ሌሎች የጻፏቸውን እያመጣሁ ሳስነብብ ነበር:: ከቄሶቹ ጀምሮ ምንም ሳይገባቸው ልማዱን እምነት አድርገው በጨበጣ የሚከተሉ አማኝ "ፖለቲከኞች" ድረስ እንደጉድ ወረዱብኝ :lol: የሚገርምህ ሁሉም ትክክል እንዳልሆነ ያውቁታል ግን ደግሞ ለምን ተደፈርን የሚል የትምክህተኞች ስሜት ነው መሰል አይኔን ግንባር ያድርገው ብለው ሲያሰኛቸው ፐርሰናል አታክ ሲያሰኛቸው ደግሞ ከዛም አለፍ ብለው የማይመለከተኝን የሰውን እምነት በፈጣጣ መዛለፉን ተያያዙት:: ራሳቸውን ወጥመድ ውስጥ እየከተቱት ነበር:: ባስጠነቅቃቸውም አሁንም ሊሰሙኝ አልቻሉም:: በዚህም ምክንያት እኔን ያገኙ መስሏቸው አንዴ ጴንጤዎችን ሌላ ጊዜ ተሀድሶዎችን ደግሞ ሌላ ጊዜ ኤቲስቶችን ደግሞ ሰንበት ብለው ሙስሊሞችን ...በቃ ማንም አልቀራቸውም እንዲሁ ከመሬት እየተነሱ ሲዛለፉ ሰነበቱ:: በዚህ ጊዜ ነበር ለካስ እምነታቸውን አያውቁም ኖሯል ብዬ "መስታወት ቤት ውስጥ የሚኖር ሰው ከሰው ቤት ድንጋይ መወርወር እንደሌለበት" ለማሳየት የተነሳሁት:: በዚህ ሰዓት ግን ለየላቸውና ጠቅለለው አበዱ - በጅምላ :lol: በዚህ ሰዓት የተገነዘብኩት ነገር ቢኖር አንደኛ እምነታቸውን ምንም እንደማያውቀትና ሊታደጉት እንደማይችሉ ሲሆን ሁለተኛውና የባሰው ደግሞ ለማወቅም አለመፈለጋቸው ነው:: እምነትህን ጠንቅቀህ ሳታውቅ ዘብ መሆን ይቅርና ከእምነቱ ጋር መዝለቅ መቻልህም ያጠራጥራል :lol: ይሄ ሁላ እምነቱን ጥሎ የሚኮበልለው ትውልድ ምን ስለሆነ ይመስልሀል :?: በዘልማድ ይከተለዋል እንጂ እምነቱ ምን እንደሆነ ጠንቅቆ ስለማያውቅ እኮ ነው:: ትንሽ መጽሀፉን ያነበነቡ ሰዎች ሲያገኙት ቶሎ እጁን ይሰጣል :lol: - በዛውም ወደ ካቶሊክ, ፕሮቲስታንት, ሙስሊም, ኤቲስት እያለ ይኮበልላል :lol:

ሠላም
ፀዋር
ዋና ኮትኳች
ዋና ኮትኳች
 
Posts: 507
Joined: Tue Feb 16, 2010 12:40 pm

Postby ቆቁ » Mon Mar 19, 2012 7:47 pm

ሀዲስ ወዳጄ

ጥያቄዎቹ እንደ ሐብታም አጥር በመቻልና በቦቢ የታጠሩ ወይም ከግምቡ ላይ የብርጭቆ እና የጠርሙስ ስባሪ ወይም የሽቦ ጋጋታ የሌለበት ማንም ሳያፈነድድና ሳያሰላ እንዲገባበት ነበር::

ከተበላሹ ሰዎች ጋር መነታረክ ያበላሻል
ካበዱ ሰዎች ጋር መጨቃጨቅ ያሳብዳል

በዚህ ዋርካ መድረክ ከስንቱ እብድ ጋር እና ቀዌ ጋር የተላተምኩ ይመስልሀል ?

ብዛቱና ቁጥሩ ዋርካ ይቁጠረው

ያንኛውን እብድ ስታክም ሌላው እብድ ብቅ ይላል

ስለሆነም አጥብቄ ስመራመር ነገሩ ሁላ አንድ ነጥብ ላይ ተቀምጦ አገኘሁት

ናርዚስቲክ ፐርሶናሊቲ ዲሶርደር

የኔ ብቻ ነው አሪፉ
የኔ ብቻ ነው ትክክሉ
እኔ ብቻ ነኝ የማውቀው
ሌላው ደንቆሮ ነው

ጸዋር ወዳጄ ዛሬ ደግሞ ወደ ደቀ እስጢፋኖስ ማለትም ወደ ፕሮፈሰር ጌታቸው ሓይሌ ጽሁፍ መመለስህ ይሆን ?

ወይ በሽታ !!!
ሳይካትሪስቱ ቆቁ
ቆቁ
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 4027
Joined: Sun Sep 21, 2003 9:57 am
Location: united states

PreviousNext

Return to Warka General

Who is online

Users browsing this forum: No registered users and 3 guests