የዳሞት ግጥሞች

Topics related to cultures, arts, languages, arts such as humor, music, traditional literary genres of poems, ግጥም ፣ ቅኔ ፣ ተረትና ምሳሌ)

የሞተ እዉነት

Postby ዋኖስ » Tue Sep 06, 2011 3:22 pm

ለመላዉ ኢትዮጵያዉያን/ያት እንዲሁም አፍቃሬ-ኢትዮጵያዉያን በሙሉ:-

እንኳን ለ2004 ዓ.ም. በሰላም በጤና አደረሳችሁ! መጪው አዲስ ዓመት የሰላም የጤና የደስታ የስራ የጥጋብ ዘመን እንዲሆንላችሁ እመኛለሁ:: ለዓለም ሰላምን ለሀገራችንም ምሕረትን ያዉርድልን! አሜን::
የሞተ-እዉነት!
የፈረሱን ጉልበት በኮርቻዉ

የፀበልተኛን መና በስልቻዉ

የመጽሐፍትን ጥበብ በሽፋኑ

የሰውን ማንነት በወገኑ

የቂቤን ጥራት ከላሚቷ

የነገዋን ሚስት ከእናቷ

ቀረ ድሮ መገመት

እዉነት በሰዉ ልጆች ዉስጥ ሳይሞት::

ዛሬማ እዉነት ሞቶ ከዉስጣችን

እንኖራለን "የሞተ-እዉነት" ተሸክመን::

ዳሞት
ዋኖስ
ዋና ውሃ አጠጪ
ዋና ውሃ አጠጪ
 
Posts: 1552
Joined: Tue Nov 16, 2004 2:39 pm
Location: Mars

መልካም ጳጉሜን @ አዲስ አምት

Postby ዚና » Tue Sep 06, 2011 7:26 pm

ዝነኛው ገጣሚ የደጋ ዳሞቱ እንኳን አብሮ አደረሰን አዲሱ አመት የሰላም የደስታ የፍቅር ይሁንልን ሰላም ለኢትዮጵያ ህዝብ በመላይሁን አሜን ዚና ከዝቋላ ገዳም ስር ደዘ
ዚና
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 203
Joined: Sun Mar 06, 2005 9:19 pm
Location: united states

Postby አባዊርቱ » Wed Sep 07, 2011 6:01 pm

አቦ አንተም እንኩዋን አደረሰህ ዳሞት ወ ዋኖሴ!
ሰላሙን እንደምን አለህልኝ? አለሁልህ 'የሞተውን እውነት' አዝዬ! አይ ገጣሚ, ጀግና እናት ወልደውሀል!

ሰላሙን ወንድሜ
አድናቂህ ኤታማዦሩ ነኝ!
አባዊርቱ
ዋና ኮትኳች
ዋና ኮትኳች
 
Posts: 800
Joined: Mon Feb 23, 2004 4:11 am

ምርጫ ለአዋጅ

Postby ዋኖስ » Thu Sep 15, 2011 3:57 pm

ምርጫ ለአዋጅ


ከእንጨት መሃል ወይንን፣

ከወንዝ መካከልም ዮርዳኖስን፣

….....ከሃገራት እስራኤልን፣

ከታነፁ ምኩራባት ቤተ-መቅደስን፣

….....ከመንጋዎች መካከልም በግን፣

ከሰዉ ልጆችም ሁሉ ድንግል ማርያምን፣

….............................የመረጥክ አምላክ፤

…...................በኑሮ ዉጣ ዉረድ ሂደት፣

…...........................የሸክላን ዕቃ በእሳት፣

…..................የሰዉን ልጅ ልቡና በእሳቦት፣

…..........እንዲፈተኑ ማድረግሕ፤ ዕለት በዕለት፣

እንዳንረሳ ነው ሥራህን፤ የፈፀምከዉን ስለእዉነት።


ዳሞት
ዋኖስ
ዋና ውሃ አጠጪ
ዋና ውሃ አጠጪ
 
Posts: 1552
Joined: Tue Nov 16, 2004 2:39 pm
Location: Mars

ደህና ሰንብት!

Postby ዋኖስ » Wed Oct 26, 2011 12:43 am

ደህና ሰንብት!"


"ከድሕነት ወፌ-ላላ" የእግር ብረትን ሠብሮ

"ነበልባሉን የሰዉ ፊት" በቃሕ! ብሎ ሰዉሮ

"ድሕነት ደህና ሰንብት!" ላለ ጌታ

መክሊት እጣዉን አስዉቦ

"ተመስገን! ማለትን ብቻ መክፈል ነው እርሡ አይጠይቅም ጉቦ::


ዳሞት!
ዋኖስ
ዋና ውሃ አጠጪ
ዋና ውሃ አጠጪ
 
Posts: 1552
Joined: Tue Nov 16, 2004 2:39 pm
Location: Mars

Postby መካልት » Sat Oct 29, 2011 11:30 pm

መቸም ግጥም. ግጥም አርጎ ትዝታ እና ስሜትን ፈንቅሎ የሚያስተነፍስ ከስድ ንባብ ይልቅ አይምሮን ፈትሾ ጨምቆ ጭነትን የሚያራግፍ ትልቅ የስነጥሁፍ ስራ ነዉ:: ለክፍሉ ባለቤት እንዲሁም ተሳታፊዎች በምታቀርቡት ስራ ላመሰግን እወዳለሁ። እኔም የተወላገደ ያላለቀ ግጥም ስለግጥም ጀባ ብያልሁ

ለሚያነበዉ ግራ ዉስጠ ወይራ ነዉ
ግጥምን ለማያዉቅ ላላስተዋለዉ
ስሜቱን በዉስጡ ለሚያብሰለስለዉ
ዉስጡ እያለቀሰ ማዉጣት ለተሳነዉ
አዝኖና ተክዞ ዉስጡ ተበላሽቶ
መተንፈስ ተስኖት እነ እንትናን ፈርቶ
ከሚያብድ ከሚሰቃይ በዉስጡ አምቆ
ግጥም መፍትሄ ናት ከሚኖር ተጨንቆ

.
ተጣፈ ከመካልት 29/10/2011
መካልት
አዲስ
አዲስ
 
Posts: 36
Joined: Sun Apr 04, 2010 2:43 pm

Postby ኦኑፈያሮ » Sun Oct 30, 2011 6:42 am

....
Last edited by ኦኑፈያሮ on Sun Oct 30, 2011 6:56 am, edited 1 time in total.
ኦኑፈያሮ
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 170
Joined: Thu Aug 04, 2005 1:52 pm

Postby ኦኑፈያሮ » Sun Oct 30, 2011 6:48 am

ዋ ! አለ አሞራ

ዛቻ ይሁን ፍራቻ አልገባኝም ብቻ
ዋ እያለ ሲሄድ አየሁት ተማሮ
ዳግም ላይመለሰ ተራራውን ዞሮ
እንደመጻፉ ቃል አያጭድ አይዘራ
አርፎ እንደመብላት ምን ነካው አሞራ
የባንክ ቤት ብድር የለበት ዋስትና
ምኑ ተነክቶ ነው እንዲህ የነሳው ጤና
ለትምህርት መሳሪያ ለልጆች ቀለብ
ልብስ አለቀ አይል ለምንም አያስብ
ውሀ ስልክ ኤሌትሪክ የለበትም ጣጣ
ዋ ብሎ ኮብልሎ ምነው ካገር ወጣ
ማህበራዊ ኑሮ እድር ህክምና
ልደግስ ልሰርግ ብሎ መች ያውቅና
የኑሮ ውድነት የዋጋ ንረቱ
ስኳሩ ቢጠፋ ቢጨምር ዘይቱ
ጤፍ ሽ ቢገባ ስንዴና ሽንኩርቱ
ዘጠና ብር ቢሸጥ አንዱ ኪሎ ሥጋ
ተወደደ ብሎ ብሎ አያስብ አይሰጋ
እንደመጻፉ ቃል አያጭድ አይዘራ
አርፎ እንደመብላት ምን ነካው አሞራ
ዛቻ ይሁን ፍራቻ
አልገባኝም ብቻ
ዋ እያለ ሲሄድ አየሁት ተማሮ
ዳግም ላይመለስ ተራራውን ዞሮ
የለበት ግልምጫ ክፉ ደግ አይሰማ
ሸሚዝ ሱሪ ጃኬት አያስብ ለጫማ
ሲመሽ ወደ ጎጆው መውጣት ነው ሲነጋ
ከፍ ቢል ቢጨምር የቤት ኪራይ ዋጋ
ለሱ ምኑም አይደል በፍጹም አይሰጋ
እንደመጻፉ ቃል አያጭድ አይዘራ
አርፎ እንደመብላት ምን ነካው አሞራ
ኦኑፈያሮ
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 170
Joined: Thu Aug 04, 2005 1:52 pm

Postby ምክክር » Sun Oct 30, 2011 8:37 am

ኦኑፈያሮ wrote:ዋ ! አለ አሞራ

ዛቻ ይሁን ፍራቻ አልገባኝም ብቻ
ዋ እያለ ሲሄድ አየሁት ተማሮ
ዳግም ላይመለሰ ተራራውን ዞሮ
እንደመጻፉ ቃል አያጭድ አይዘራ
አርፎ እንደመብላት ምን ነካው አሞራ
የባንክ ቤት ብድር የለበት ዋስትና
ምኑ ተነክቶ ነው እንዲህ የነሳው ጤና
ለትምህርት መሳሪያ ለልጆች ቀለብ
ልብስ አለቀ አይል ለምንም አያስብ
ውሀ ስልክ ኤሌትሪክ የለበትም ጣጣ
ዋ ብሎ ኮብልሎ ምነው ካገር ወጣ
ማህበራዊ ኑሮ እድር ህክምና
ልደግስ ልሰርግ ብሎ መች ያውቅና
የኑሮ ውድነት የዋጋ ንረቱ
ስኳሩ ቢጠፋ ቢጨምር ዘይቱ
ጤፍ ሽ ቢገባ ስንዴና ሽንኩርቱ
ዘጠና ብር ቢሸጥ አንዱ ኪሎ ሥጋ
ተወደደ ብሎ ብሎ አያስብ አይሰጋ
እንደመጻፉ ቃል አያጭድ አይዘራ
አርፎ እንደመብላት ምን ነካው አሞራ
ዛቻ ይሁን ፍራቻ
አልገባኝም ብቻ
ዋ እያለ ሲሄድ አየሁት ተማሮ
ዳግም ላይመለስ ተራራውን ዞሮ
የለበት ግልምጫ ክፉ ደግ አይሰማ
ሸሚዝ ሱሪ ጃኬት አያስብ ለጫማ
ሲመሽ ወደ ጎጆው መውጣት ነው ሲነጋ
ከፍ ቢል ቢጨምር የቤት ኪራይ ዋጋ
ለሱ ምኑም አይደል በፍጹም አይሰጋ
እንደመጻፉ ቃል አያጭድ አይዘራ
አርፎ እንደመብላት ምን ነካው አሞራ


ዊው የሚያሰኝ ድንቅ የግጥም ሥራ::
እንዲህ ቀለል ባለ አማርኛ ግጥማ ግጥሞች ዘርገፍ ብለው ሲወርዱ ጉሮሮን አይዙም ....ቁርቁር ብለው ይወርዳሉ ማለቴ ነው:: ቪቫ ኦኒ!
Be nice to yourself
ምክክር
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 326
Joined: Thu Jun 26, 2008 10:10 am
Location: Super Earth

Postby ኦኑፈያሮ » Mon Dec 05, 2011 2:38 pm

ቀድሞ ቀረ !

ያኔ ነበር ማዘን አካሌ ገርጥቶ

ጉልበቴ እየራደ የምቀምሰው ጠፍቶ

አንጄቴ ተጣብቆ ላልቶ ቀበቶዬ

መልኬ ተቀይሮ ተገፎ ጥላዬ

እህል ብቻ ሳይሆን ሠው ተርቦ አይኔ

ፈጥኖ ያልደረሰ ያልቆመ ከጎኔ

ደም አንብቶ ቢያለቅስ ደረት ቢደልቅ

ምንም ፋይዳ የለው እንባ አይሆንም ሥንቅ

አርባም አያስፈልግ ተጽናኑ ይበቃል

አፈር ባልለብስ እንጅ ከሞትኩኝ ቆይቷል
ኦኑፈያሮ
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 170
Joined: Thu Aug 04, 2005 1:52 pm

ሰላም

Postby ዋኖስ » Sat Feb 04, 2012 12:09 am

የቤቴ ቁልፍ ጠፍቶ በስንት መከራ ቤቴ ተከፈተ መሰላችሁ!:: እንዴት ከረማችሁ:


“በቃል-አሽክላ” የታሠሩ ዓይኖች፤

በደረቅ ሌሊት አጋማሽ፤ የፍቅር አምላክ አንዣቦ፣

ተመልከት አለኝ! ዓይንሽን ድርጊት ሥራሽን ታዝቦ።

ልብሽ ኮብልሎ፣ ሸሽቶ ፅናት፣እምነትሽ ሲናድ፣

የእምቧይ-ካብ ሲሆን ሲፈርስ፤ የደም ግለትሽ ሲበርድ።

ታዩኝ ዓይኖችሽ በልሜ፤ የፍቅር አጥር ሲሰብሩ፣

“በቃል-አሽክላ” ታሥረዉ በሕልም ዓለም ዉስጥ ሲበሩ።

በሕልም-ዓለም ዉስጥ በረዉ፤

“የሕልም ጎረምሳ” ሲቀዝፉ፣

ጉሙ፤ ጭጋጉ ባፈነሽ፤ ልቤ ወደብ ላይ ባረፉ፤

ማዬት እንድችል በዉኔ በእምባሽ-ጎርፍ ሃይል ሲዳፉ።

ዳሞት ከዳሞት!
ዋኖስ
ዋና ውሃ አጠጪ
ዋና ውሃ አጠጪ
 
Posts: 1552
Joined: Tue Nov 16, 2004 2:39 pm
Location: Mars

Postby ኦኑፈያሮ » Wed Apr 04, 2012 7:14 am

እያንገራገረ ሕዝቡን እያባባ

አበው እያዘኑ ወጣት እያባባ

እየተቃወሙ እየጮሁ እነ አባ

ዜናው ባለማቀፍ እየተስተጋባ

ድንገት ሳይታሰብ ስኳር ገዳም ገባ

ከፍ ከፍ ብሎ ለዛውም ዋልድባ

ሲጠፋ ሲሰወር ሲደበቅ ቆይቶ

ባቍሙ ጠንክሮ በውሳኔው ጸንቶ

አመክሮ ሳይዝ ድንገት ገዳም ገብቶ

ጣፋጭ የነበረው ሊመርር ነው ከቶ

ለሱ የሚስማማ ስንት ቦታ ሞልቶ

ስኳር እሳት ሆኖ ከገበያ ጠፍቶ

ሊቀመጥ ነው አሉ መቃብር ቤት ገብቶ

ምን ይውጥሽ ይሆና ከንግዲህ መርካቶ

አባቶች ምን አሉ በዋልድባ ያሉ

ባባቶች አጽም ላይ ሸንኮራ ሲተክሉ

ከተቀበረበት እየፈነቀሉ

በደም የበቀለ ሸንኮራ ሊበሉ

ኧረ እግዚኦ በሉ

ይህስ ጥሩ አይደለም

ካቅም በላይ ሆኖ ሕዝቡ ቢበደልም

አባቶች ዝም በሉ ይረሱት ግዴለም

ዋልድባ በጾሙ ምነው ተፈተነ

በገዳሙ ልማድ ትንሽ ከታዘነ

ጸሎቱ እንደወጉ ከተከናወነ

ውሎ አድሮ ይሟሟል ስኳር ስለሆነ
ኦኑፈያሮ
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 170
Joined: Thu Aug 04, 2005 1:52 pm

Postby ዋኖስ » Sat Aug 25, 2012 5:28 pm

እንዴት ከረማችሁ!

የመድበሌን አቧራ ላራግፍ ስገባ ሸረሪት ወሮታል! ይገርማል:: ለመሆኑ ወዳጄ ኦኑፈያሮ የት ገባ ይሆን?
ዋኖስ
ዋና ውሃ አጠጪ
ዋና ውሃ አጠጪ
 
Posts: 1552
Joined: Tue Nov 16, 2004 2:39 pm
Location: Mars

Postby ኦኑፈያሮ » Sun Aug 26, 2012 7:13 am

ሰላም ዋኖሴ ! አማን ነህ ዎይ ዎዳጄ ?

ተጠየቅ !


ተጠየቅ አንተ ሠው እንዳሻሮ ቆሎ ሰው የምታምሰው

ተጠየቅ አንተ ሠው ለሆድህ ያደርከው

እውነትን በሃሰት ካባ የሸፈንከው

ሥጋው ይበላና ይጣላል አጥንቱ

እዳም ይከፈላል እየሰነበቱ

በሽታም ይድናል ሲገኝ መድሃኒቱ

ለሆድ አድሮ ክህደት አይጠፋም ትዝብቱ

በልጅነት ቧርቀህ ያደግክባትን ሀገር

ሀ ብለህ ተምረህ ደርሰህ ለቁምነገር

ክፉ ደጉን ለይተህ የኖርክባት ምድር

ተድረህ ተኩለህ ወልደህ የሳምክባት

የጥንቷም የጧቷም እምዬ ኢትዮጵያ ናት

የነአይበገሬ ሀገር ያገር ክብር መኩሪያ

በውስጥም በውጭም ዘብ የቆሙ እነዚያ

የወገን መከታ ያገር ቅርስ መኩሪያ

እኔ ሙቼ ትኑር አገሬ ኢትዮጵያ

የሚሏት ልጆቿ በኖሩባት ምድር

ሀገርን ከድተህ ለሆድህ ስታድር

ከሃገር ከወገን ጥቅም በልጦ ታይቶህ

በደማችን ስትነግድ በእህት በወንድምህ

አሁን ቢያስደስትህ ይህ እኩይ ተግባርህ

ከሥም ስም ይሸታል በማሉን ዘንግተህ

ከፍርድ አታመልጥም ተጠየቅ ነው የምልህ
ኦኑፈያሮ
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 170
Joined: Thu Aug 04, 2005 1:52 pm

Postby ኦኑፈያሮ » Mon Oct 15, 2012 7:44 am

ነበር ገደል ይግባ !

በተፈጥሮ ሒደት በዘመናት ዱካ

አንድ ትውልድ አልፎ ሌላው ግን ሲተካ

ያለፈው ትውልድ ገድል..መና ሆኖ እንዳይቀር

ለተተኪው ትውልድ ቅርሱን ለመዘከር

ያለፈው ሲወራ ሲባል እንዲህ ነበር

ሙታንን ቀስቅሶ ሕያዋኑን መቅበር

ከሆነ ለዚህ ግብ ታሪክ መወራቱ

ታሪክ ገደል ይግባ በታሪክነቱ

ይቅር የት አባቱ

የተፈጥሮ ሕግጋት የማይበግራቸው

ከመቃብር በላይ የቀረ ስማቸው

እኒያ የጥበብ ሰዎች አለም ያወቃቸው

በተደጋጋሚ እኛ እንደሰማነው

ታሪክን የሰሩት በዘመናቸው ነው

ህግጋቷን ጥሰው ተፈጥሮንም ንቀው

በዚህ ትውልድ ላይ ሙታን ተንሰራፍተው

ዳግም ሲኖሩባት ስማቸውን ተክለው

ዝናና ገድላቸው እንደ ጉድ ሲወራ

እንዲህ ነበር ሲባል ስላለፈው ትውልድ ውዳሴው ሲደራ

ነበር የሚለው ቃል ከተዘወተረ

ታሪክ እያወሩ ታሪክ መስራት ቀረ

ለዚህ ግብ ከሆነ ታሪክ መሰራቱ

ታሪክ ገደል ይግባ በታሪክነቱ
ኦኑፈያሮ
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 170
Joined: Thu Aug 04, 2005 1:52 pm

PreviousNext

Return to Warka Culture and Literature - ዋርካ ባህልና ሥነ ጽሑፍ

Who is online

Users browsing this forum: No registered users and 0 guests