ኢትዮጵያውያን የጥበብ ሰዎች-ከሐርቫርድ እስከ

Topics related to cultures, arts, languages, arts such as humor, music, traditional literary genres of poems, ግጥም ፣ ቅኔ ፣ ተረትና ምሳሌ)

Postby ተድላ ሀይሉ » Wed Apr 11, 2012 5:24 pm

ሰላም ውድ ኢትዮጵያውያን ወገኖቼ :-

የተከበሩ ሜትር አርቲስት አፈወርቅ ተክሌ ማረፋቸውን የሚያረዳ መርዶ ተሠምቷል :: እግዚአብሔር ነፍሣቸውን ይማር ::

ምንጭ:- ሔኖክ ያሬድ : ሪፖርተር ጋዜጣ : ረቡዕ ሚያዝያ 3 ቀን 2004 ዓ.ም.:: ሰበር ዜና፦ ታላቁ ሠዓሊ የዓለም ሎሬት ሜትር አርቲስት አፈወርቅ ተክሌ አረፉ ::

እጅግ የተከበሩ የዓለም ሎሬት ሜትር አርቲስት አፈወርቅ ተክሌ ማክሰኞ ሚያዝያ 2 ቀን 2004 ዓ.ም. ሌሊት በካዲስኮ ሆስፒታል በ80 ዓመታቸው አረፉ፡፡

በኢትዮጵያ ዘመናዊ ሥነ ጥበብ ታሪክ ፋና ወጊ የሆኑት ሜትር አርቲስት አፈወርቅ ባደረባቸው ሕመም ምክንያት ሆስፒታል የገቡት ባለፈው እሑድ እንደነበረ የቅርብ ምንጮች ለሪፖርተር ገልጸዋል፡፡

ሥርዓተ ቀብራቸውን በተመለከተ ጸሐፌ ተውኔት አያልነህ ሙላቱ ያሉበት ኮሚቴ እየመከረ መሆኑን ለማወቅ ተችሏል፡፡ የሕይወት ታሪካቸው እንደሚያመለክተው፣ ሜትር አርቲስት አፈወርቅ ተክሌ ቅዳሜ ጥቅምት 12 ቀን 1925 ዓ.ም. በታሪካዊቷ አንኮበር ከተማ የተወለዱ ሲሆን፣ በ1940 ዓ.ም. ወደ እንግሊዝ በመጓዝ ከፍተኛ ትምህርታቸውን ተከታትለዋል፡፡

ለስድስት አሠርት አቅራቢያ ያህል በሥነ ጥበብ ሥራዎቻቸው ገናና የነበሩት ሎሬት አፈወርቅ ከቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ ሽልማት ድርጅት በ1956 ዓ.ም. በሥነ ጥበብ የተሸለሙትን ጨምሮ በርካታ ዓለም አቀፍ ሽልማቶችን ተቀዳጅተዋል፡፡
ተድላ
የወያኔ ሕገ -አራዊት አንቀፅ 39 ኢትዮጵያን የመበታተኛ ፈንጂ ነው !
ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር !!!
ተድላ ሀይሉ ዘብሔረ -ኢትዮጵያ ::
ተድላ ሀይሉ
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 4903
Joined: Fri Mar 17, 2006 2:45 pm
Location: ኢትዮጵያ

Postby ችበሀ » Mon Apr 16, 2012 2:06 am

ከታዋቂው የቤተክህነት ሰው አለቃ ደስታ የሚወለዱት ገብረክርስቶስ ደስታ, በጅሮንድ ጥበበ ደስታ, ተድላ ደስታና በደርግ ጊዜ ለተወሰነ ጊዜ ያገር አስተዳደር ሚኒስትር ሆኖ ሸውዶ ወደመኖሪያው ጀርመን እንደተመለሰ የሚነገርለት ሌላው ልጃቸው በሙሉ በኢትዮጵያ ታሪክ ውስጥ ጎላ ያለ ስፍራ አላቸው
የገብረ ክርስቶስ ጥበብ አድማስን ተሻግሮ የወጣ ቢሆንም ሁሉም ልጆቻቸው በተለያየ ሙያ አገራቸውን በክፍተኛ ሥፍራ አገልግለዋል
ያባቴ ወዳጅ የነበሩት በጅሮንድ ጥበበ ብርሀናቸን አጥተው እቤት ቢውሉም ስላገራቸውና ስለአለም ሁኔታ ሲያወሩ የማይሰለቹ አዋቂውንና ህጻናቱን እንደዕድሚያቸው በሚገባቸው መንገድ በማስረዳት ልዩ ያገር ፍቅር እንዲሰርጽ የማድረግ ችሎታ ነበራቸው

በጅሮንድ ጥበበ ወንድማቸው ከመንግሥቱ ንዋይ ጋር ወግኖ ስለነበር ከቀኃሥ አገዛዝ በደረሰባቸው ቁንጥጫ እስከህይወታቸው ፍጻሜ ቢስቃዩም የኢትዮጵያን ታሪክ ግን በጨዋታቸው ውስጥ ሁሉ ሳያስገቡ አያልፉም ነበር (ዛሬ ታሪክ ለማውራትም ለማዳመጥም የማይፈልግ ጉድ ሳይበዛብን ማለተ ነው)
በልጅነት ዕድሜዬ ከሳቸው አንደበት የሰማሗቸው ያገራችን ታሪኮች አሁን ድረስ አይረሱኝም
ሰላም እንሰንብት
ችበሀ ነኝ

ዘንጉ1 wrote:ባለቅኔ እና ሰአሊ ወይስ ሰአሊ እና ባለቅኔ አንዳንዴ ምን ብለን እንደምንጠራው እንቸገራለን:: ገብረ ክርስቶስ በኢትይጵያ የዘመናዊ ጥበብ አባትነት ዋነኛው ተጠቃሽ ነው:: በተለይ አብስትራክት ተብሎ የሚፈረጀው የስአል ዘርፍ ወደ ከኢትዮጵያውያን ጋር በማስተዋወቅ ግንባር ቀደሙ ነው::
ገብረ ክርስቶስ ብዙዎቹ ያለ እድሜው የተቀጨ አርቲስት እንደሆነ ያምናሉ::
እስቲ የምወደውን የገበረ ክርስቶስ ግጥም እነሆ ብያለሁ:

ፍቅር ጥላ ሲጥል
በገና
ቢቃኙ:
ሸክላ
ቢያዘፍኑ:
ክራር
ቢጫወቱ:
ለሚወዱት
ምነው
ሙዚቃ
ቢመቱ:
ቢቀኙ
ቢያዜሙ
ቃል ቢደረድሩ:
ጌጥ
ውበት
ቢፈጥሩ:
ቤት
ንብረት
ቢሰሩ:
አበባ
ቢልኩ:
ምነው
ቢናፍቁ:
አገር
ቢያቋርጡ
ቢሄዱ
ቢርቁ:
አመት
ቢጠብቁ:
ዘመን
ቢጠብቁ:
ለሚወዱት ምነው......
ችበሀ
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 164
Joined: Sun Nov 09, 2003 10:46 pm

Postby ተድላ ሀይሉ » Mon Apr 16, 2012 2:53 am

ችበሀ wrote:ከታዋቂው የቤተክህነት ሰው አለቃ ደስታ የሚወለዱት ገብረክርስቶስ ደስታ, በጅሮንድ ጥበበ ደስታ, ተድላ ደስታና በደርግ ጊዜ ለተወሰነ ጊዜ ያገር አስተዳደር ሚኒስትር ሆኖ ሸውዶ ወደመኖሪያው ጀርመን እንደተመለሰ የሚነገርለት ሌላው ልጃቸው በሙሉ በኢትዮጵያ ታሪክ ውስጥ ጎላ ያለ ስፍራ አላቸው
የገብረ ክርስቶስ ጥበብ አድማስን ተሻግሮ የወጣ ቢሆንም ሁሉም ልጆቻቸው በተለያየ ሙያ አገራቸውን በክፍተኛ ሥፍራ አገልግለዋል
ያባቴ ወዳጅ የነበሩት በጅሮንድ ጥበበ ብርሀናቸን አጥተው እቤት ቢውሉም ስላገራቸውና ስለአለም ሁኔታ ሲያወሩ የማይሰለቹ አዋቂውንና ህጻናቱን እንደዕድሚያቸው በሚገባቸው መንገድ በማስረዳት ልዩ ያገር ፍቅር እንዲሰርጽ የማድረግ ችሎታ ነበራቸው

በጅሮንድ ጥበበ ወንድማቸው ከመንግሥቱ ንዋይ ጋር ወግኖ ስለነበር ከቀኃሥ አገዛዝ በደረሰባቸው ቁንጥጫ እስከህይወታቸው ፍጻሜ ቢስቃዩም የኢትዮጵያን ታሪክ ግን በጨዋታቸው ውስጥ ሁሉ ሳያስገቡ አያልፉም ነበር (ዛሬ ታሪክ ለማውራትም ለማዳመጥም የማይፈልግ ጉድ ሳይበዛብን ማለተ ነው)
በልጅነት ዕድሜዬ ከሳቸው አንደበት የሰማሗቸው ያገራችን ታሪኮች አሁን ድረስ አይረሱኝም
ሰላም እንሰንብት
ችበሀ ነኝ

ሰላም ችበሀ:-

እባክህ አንዳንዴ ብቅ እያልክ እንደዚያ ያሉ በጽሑፍ ላይ ያልዋሉ የአገራችንን ታሪኮች አካፍለን ::

ተድላ
የወያኔ ሕገ -አራዊት አንቀፅ 39 ኢትዮጵያን የመበታተኛ ፈንጂ ነው !
ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር !!!
ተድላ ሀይሉ ዘብሔረ -ኢትዮጵያ ::
ተድላ ሀይሉ
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 4903
Joined: Fri Mar 17, 2006 2:45 pm
Location: ኢትዮጵያ

Postby ተድላ ሀይሉ » Sat Apr 21, 2012 2:50 am

ሰላም የጥበብ አፍቃሪዎች :-

ሟቹ ምኒልክ ወሠናቸው ራሱ በደረሣቸው ግጥሞችና ዜማዎች የኢትዮጵያን ሙዚቃ ከፍተኛ ደረጃ ካደረሡት ቀዳሚው ነው :: ዛሬ ከመቃብር ጠርተን ልናመጣው የማንችለው : ነገር ግን ትቶልን ባለፋቸው የሙዚቃ ሥራዎቹ ምንጊዜም የማይረሣ ትዝታ ትቶልን አልፏል :: በሕይወት እያለ በተደረገለት ቃለ-መጠይቅ ትዝታዎቹን ያካፍለናል :: የምኒልክን ነፍስ ይማር ብያለሁ ::

ምንጮች:-
1 ..... Interview with Menelik Wosenachew ( Gash Jembere ) Part 1

2 ..... Interview with Menelik Wosenachew ( Gash Jembere ) Part 2

3 ..... Interview with Menelik Wosenachew ( Gash Jembere ) Part 3

4 ..... Interview with Menelik Wosenachew ( Gash Jembere ) Part 4

5 ..... Interview with Menelik Wosenachew ( Gash Jembere ) Part 5

6 ..... Interview with Menelik Wosenachew ( Gash Jembere ) Part 6


ተድላ
የወያኔ ሕገ -አራዊት አንቀፅ 39 ኢትዮጵያን የመበታተኛ ፈንጂ ነው !
ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር !!!
ተድላ ሀይሉ ዘብሔረ -ኢትዮጵያ ::
ተድላ ሀይሉ
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 4903
Joined: Fri Mar 17, 2006 2:45 pm
Location: ኢትዮጵያ

Postby ኤዶም* » Thu Apr 26, 2012 7:09 pm

ከ50 አመታት በላይ በሺዎች የሚቆጠሩ ወገኖቻችንን በመርዳት ያሳለፉት ዶ.ር ካትሪን በዛሬዋ ዕለት የኢትዮጵያዊነትን የክብር ዜግነት ከአገሪቷ መሪ በክብር ተቀብለዋል.........ለኚህ ድንቅ ምግባረ ሰናይ ዶክተር ክብር ባርኔጣዬን አንስቻለሁ

http://www.diretube.com/articles/read-e ... 1488.html#
ኤዶም*
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 362
Joined: Sun Sep 18, 2005 11:55 pm
Location: ethiopia

Postby ተድላ ሀይሉ » Sun Jun 10, 2012 8:10 pm

ሰላም የጥበብ አፍቃሪዎች :-

ኪነት ምንድን ናት? ለዚህ መልስ የሚሆን መጣጥፍ በፕሮፌሠር መሥፍን ወልደማርያም ቀርቧል :: እስኪ ከራሣችሁ ዕይታ አንፃር አስተያየታችሁን አክሉበት ::

ምንጭ:- መሥፍን ወልደማርያም (ፕሮፌሠር) : ፍትህ ጋዜጣ : አርብ ሰኔ 1 ቀን 2004 ዓ.ም.:: ኪነትና ነፃነት::

በደርግ ዘመን በአዲስ አበባ ማዘጋጃ ቤት አዳራሽ የኪነት ስብሰባ ተካሂዶ ነበር፤ እንጉርጉሮ በምትል ትንሽ የግጥም ጥራዝ ሳይሆን አይቀርም ለስብሰባው ተጋብዤ ነበር፤ በዚህ ስብሰባ ላይ አቶ አያልነህ ሙላትና ዶር. ኃይሉ አርአያም አስተናጋጆች እንደነበሩ አስታውሳለሁ፤ የመክፈቻው ንግግር ሥርዓት እንዳበቃ መድረኩ ለአስተያየት ሲከፈት የመጀመሪያው ጠያቂ እኔ ነበርሁ፤ ‹‹በመድረኩ ላይ የተባለው ሁሉ በትክክል ገብቶኝ እንደሆነ ለማረጋገጥ እፈልጋለሁ፤ ስለዚህም አንድ ጥያቄ ላቅርብ፤›› ብዬ- ‹‹ኪነት ማለት አዝማሪነት ማለት ነው ወይ?››-- ብዬ ተቀመጥሁ፤ በሦስቱም የስብሰባ ቀኖች ‹‹ኪነት አዝማሪነት ነው ወይ?›› የሚለው ጥያቄ እየተነሣ ቆየ፤ አዝማሪነት ስትል ምን ማለትህ ነው ብለው የጠየቁ ነበሩ፤ በቀለለ አማርኛ ልገልጽ አልችልም በማለት እስከ ሦስተኛው ቀን ቆየሁ።

አንድ ሎሌ እየተውዘገዘገ ርእዮተ ዓለምንና አብዮትን የሕይወት ካባ አስመስሎ ‹‹ከርእዮተ ዓለሙ ውጭ ምን አለ!›› እያለ አለማወቁን አሳወቀ፤ ኪነት አዝማሪነት ነው፤ አዝማሪነት ኪነት ነው ማለቱ ነበር፤ ሌሎችም ኪነትንና አዝማሪነትን ለማጋባት የቃጣቸው ሎሌዎች ነበሩ፤ አንዳንዶች ግራ ገብቶአቸው ለቡና ስንወጣ የጠየቁኝ እንደታምራት ሞላ ያሉ የኪነት ሰዎች ነበሩ፤ በእውነቱ እዚያ ውስጥ ከነበሩት ውስጥ ማንኛውም ቢሆን በልቡናው ኪነትንና አዝማሪነትን መለየት ያቃተው የነበረ አልመሰለኝም።

በሦስተኛው ቀን ተነሣሁና በአንዲት ልጅ ፍቅር ተወጥሬ አንድ ግጥም ብጽፍ ርእዮተ ዓለሙ ወይም አብዮቱ በእኔና በልጅቱ መሀከል በምን ቀዳዳ ይገባል? ሕይወት አይቆምም፤ ይቀጥላል፤ ርእዮተ ዓለም ግን በርእዮተ ዓለም ይለወጣል፤ ለአብዮትም አብዮት አለው በማለት ሎሌዎቹን አስደንግጬ ድርሻዬን ተወጣሁ!

ኪነት ነፃነት ነው፤ ኪነት የፈጣሪነት ጥበብ ነው፤ ኪነት ውበት ነው፤ ኪነት ደስታና ሳቅ ነው፤ ኪነት ሐዘንና ለቅሶ ነው፤ ነፃነት፣ የፈጣሪነት ጥበብና ውበት የኪነት መለያ ባሕርዮች ይመስሉኛል፤ ኪነት በሰው ልጅ ውስጥ የፈጣሪው እስትንፋስ መኖሩን የሚገልጽና ፈጣሪነትን ከፈጣሪው የሚጋራበት ስጦታም ችሎታም ነው፤ እንደዚህ ያሉ ሰዎች የአንድ አገር ዓይንና ጆሮ፣ አእምሮና ኅሊና ናቸው፤ የአንድ አገር ሕዝብ የሥልጣኔ ደረጃ በእንደዚህ ያሉ ሰዎች ብዛትና በድንበር-ዘለል ተጽእኖአቸው ይለካል፤ ለምሳሌ ፈረንሳይ የኪነት ሰዎችን ከየትም የመሳብ ችሎታዋ ወደር የሌለው ነው፤ እንዲሁም አሜሪካ በሙሉ ባይባልም ኒው ዮርክ የኪነት ሰዎችን የሚስብ ከተማ ነው።

በኢትዮጵያ ያለውን ሁኔታ አቶ ሐዲስ ዓለማየሁ ፍቅር እስከመቃብር ውስጥ በጥሩ መልኩ በጉዱ ካሣ ያመለከቱት ይመስለኛል፤ ክፉ መልኩ ግን አስቀያሚ ነው፤ ዘፈኖች የሚታሰሩበት አገር ነው፤ የኪነት ሰዎች የሚታሰሩበት አገር ነው፤ መጻሕፍትን ማቃጠልም እናውቅበታለን፤ አሁን ደግሞ ከየመሥሪያ ቤቶች ቤተ መጻሕፍት እያወጡ መጻሕፍትን መሸጥ ፈሊጥ ሆኖአል፤ በአጠቃላይ የፈጠራ ሰዎችን ከነፈጠራቸው ማፈን የሚወራረሱት ልማድ ሆኖአል፤ ከተለመደውና ከተፈቀደው ወጣ ያለ ነገር ወይ ለእስር ወይ ለስደት ይዳርጋል፤ በእውነቱ ከሆነ ኪነት የሚሰደድ አይመስለኝም፤ የኪነት ሕይወቱም ሆነ ሞቱ በነፃነት ነው፤ የተሰደደ ኪነት የሬሳ ጭፈራ ነው።

በብዙ አገሮች ኪነትን የሚደግፉ ሀብታሞች አሉ፤ በኢትዮጵያም አቶ መሀመድ አላሙዲ የዘፋኞች አለኝታ መሆኑ ይነገራል፤ አንድ ሰው መኖሩ የጠቅላላውን ጨለማ አይገፈውም።

ግራም ነፈሰ ቀኝ ራሱን ነፃ ያላወጣ ኪነት ከአዝማሪነት ይቆጠራል፤ አዝማሪነት ከመዝፈን ጋር ብቻ የተያያዘ አይደለም፤ ውዳሴንም ሆነ ገድልን ለወፍራም እንጀራ የሚጽፍ አዝማሪ ነው፤ በሌሎችም ሙያዎች ያው ነው።

አዝማሪነት የፈጣሪነት ጥበብንና ውበትን ሊይዝ ይችል ይሆናል፤ ነፃነት ግን ለአዝማሪነት የባሕርዩ አይደለም፤ ጥቅምን አይቶ የሚነሣ አዝማሪነትና ያለምንም ምኞት አፍአዊ ሁኔታዎች በሚቀሰቅሱት ሀሳብና ስሜት በጥልቀት ነፍሱ ሲነካ ነፍሱን ቧጥጦ የሚወጣው ኪነት አንድ ሊሆኑ አይችሉም።
በአንድ ዓይነት ኪነት ላይ ያለውን የባህል አጥር እየጣሱ ስሜታቸውን በመጠኑም ቢሆን የሚገልጹ ሰዎች ነበሩ፤ አዝማሪዎች፣ አልቃሾችና እረኞች፤ በተረፈ ግን ኢትዮጵያ የኪነት አገር ለመሆን አልታደለችም፤ ነፃነት ሲመጣ ኪነት ይነግሣል፤ ችጋርም ይጠፋል።

ተድላ
የወያኔ ሕገ -አራዊት አንቀፅ 39 ኢትዮጵያን የመበታተኛ ፈንጂ ነው !
ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር !!!
ተድላ ሀይሉ ዘብሔረ -ኢትዮጵያ ::
ተድላ ሀይሉ
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 4903
Joined: Fri Mar 17, 2006 2:45 pm
Location: ኢትዮጵያ

Postby እምቢ ለሀገር » Mon Jun 11, 2012 7:48 pm

ጤና ይስጥልኝ ጋሽ ተድላ :!:

ስለ ኪነ-ጥበብ ምንነት ጠለቅ ያለ እውቀት ባይኖረኝም ትንሽ ለማለት ወደ ቤትህ ጐራ ብያለሁ:: ለእኔ ኪነት እውነት ናት::ይችን እውነት ደግሞ በተለያዩ መንገዶች የሚናገሯት..የሚገልጿት..የሚያሳዩዋት..ሰዎች አሉ::የኪነ-ጥበብ ሰዎች ወይም ከያኒያን ልንላቸው እንችላለን::

በመጀመሪያ ይች እውነት ምንድን ነች?..

ለእኔ እውነት:- ፍቅር ናት! ፍቅር ደግሞ..ሩህሩህ:ታጋሽ:ቅን:አስተዋይ:ነጻ አውጭ:ለሌሎች እንጅ ለራሷ የማትፈልግ:ለጋስ:ኩሩ:ደፋር:...........ናት:: የኪነ ጥበብ ስዎች ይች እውነት በአንድ ማሀበርሰብ ውስጥ ተዛብታ ሲያዩ በአላቸው ተሰጥዎ ተጠቅመው ጥብቅና ይቆሙላታል::ሰዎች ሲያጓድሏት እነርሱ ይሞሏታል::ሲዛንፏት ያስተካክሏታል::ሲያጠወልጓት ያለመልሟታል::ውበቷ እንዳይረግፍ ይንከባከቧታል::ሲገፈትሯት ይደግፏታል::ያለቦታዋ እንዳያውሏት ማህበረሰቡን ያስጠነቅቃሉ:: ማህበርሰቡ ስለ እውነት እንዲኖር ይመክራሉ::እውነትን ሲያደርግ ያሞግሳሉ:: ስለ እውነት እንዳይደክም ያበረታታሉ:: እውነትን ሲረሳ ያስታውሱታል:: ስለ እውነት እንዲታገል ያደፋፍሩታል::..........

እውነትን ከሚጠመዝዝ ባለጉልበተኛ እና ሀብታም ጋር ሁነው የእርሱን ሃሳብ የሚያስተጋቡ ብሎም የሚደግፉ እውነትን አፈር ድሜ ሲያበላት.. እልል የሚሉ.. ለኔ እነዛ ሰዎች የኪነ-ጥበብ ሰዎች አይደሉም:: የኪነ ጥበብ ሰው ለመሆን ስለ እውነት ብቻ እና ብቻ መስራት አለባቸው::

እውነትን አዛብቶ..እውነትን እያደማ..በእውነት ላይ የሚያፌዝ..ጉልበተኛ መሪ ግድብ ሰርቻለሁ እና ተቀኙልኝ ሲል.. ሲንድረደሩ መጠው የሚሽሞነሙኑ(ቅንድብህ ያማረ እያሉ የሚጮኹ) እነርሱ..ልክ ጠጅ ቤት ውስጥ ለመሸለም ማሲንቆውን ከሚመታው አዝማሪ ለይቸ አላየውም:: እንዴውም እርሱ ይሻላል::

ለእኔ እንግዲህ ኪነት ይችን ትመስለኛለች...

እምቢተኛው :!:
ETHIOPIA ETHIOPIA ETHIOPIA
እምቢ ለሀገር
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 262
Joined: Mon Feb 13, 2012 5:08 pm

Postby ተድላ ሀይሉ » Tue Jun 12, 2012 5:20 am

ሰላም 'እምቢተኛው' :-

ስለ ኪነት ባቀረብከው አገላለጽ እስማማለሁ :: ኪነት ለአንድ ብቻ የጥበብ ሙያ የተሠጠ የተጸውዖ ሥም አይደለም :- ሁሉንም የጥበብ ዘርፎች ያቅፋል :: ሥዕል መሣልን : ሐውልት መቅረፅን : ዜማ መቀመርንና መጫወትን : ማንጎራጎርን : መወዛወዝን (እስክስታ : ዳንስ) : ግጥም መግጠምን : መቀኘትን : የድርሰት መድበል መጻፍን : በተለያዩ የስፖርት ዓይነቶች ክህሎትን ማሣየትን : ወዘተርፈ ... ስለዚህ ከእነዚህ የጥበብ ዘርፎች አንዱ አዝማሪነት ነው :: አዝማሪነትን አቃልለን ለሥድብነት ባንጠቀምበት እመርጣለሁ :: ምክንያቱም ሌላ ቃል ፍለጋ ሥንባዝን መሠረታዊ የሆነውንና ሙያው የሚጠይቀውን የጥበብ ክህሎት ወደጎን እንዳናደርገው እፈራለሁ :: ውዳሤ ከንቱ የሚያበዙ አዝማሪዎችን እኮ ሙያቸውን ሣይሠድቡ በምግባራቸው መመዘን ይቻላል :- ለምሣሌ ይኼ (ይህቺ) ውዳሤ ከንቱ የምትደረድር አዝማሪ እንጂ ውስጠ-ወይራ አዋቂ አዝማሪ አይደለም (አይደለችም) ማለት ይቻላል :: ሙያን በሙያነቱ ካከበርነው ግን መጠሪያው ሥድብ ሊሆን የሚችልበት ምክንያቱ አይታየኝም :: የእኔ አተያይ እንደዚህ ነው ::

ተድላ
የወያኔ ሕገ -አራዊት አንቀፅ 39 ኢትዮጵያን የመበታተኛ ፈንጂ ነው !
ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር !!!
ተድላ ሀይሉ ዘብሔረ -ኢትዮጵያ ::
ተድላ ሀይሉ
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 4903
Joined: Fri Mar 17, 2006 2:45 pm
Location: ኢትዮጵያ

Postby ተድላ ሀይሉ » Thu Jun 14, 2012 6:38 am

ሰላም የሙዚቃ ጥበብ አፍቃሪዎች :-

በምንም መለኪያ ቢመዘን ሙሉ ኢትዮጵያዊ የሆነው የሬጌ ሙዚቃ ንጉሥ ቦብ ማርሌይ ስለጥቁር ሕዝብና በተለይም ስለኢትዮጵያ ገናናነት እንዳዜመ አልፏል :: በሕይወት የኖረው ለ36 ዓመታት ቢሆንም ሥራው ግን ዓለምን ቀይሯል :: የዚህን ታላቅ የጥበብ ሰው ታሪክ የሚዘግብ ታሪካዊ ፊልም ከ1 ዓመት በፊት በይፋ የተመረቀ ሲሆን በዩ-ቲዩብ ስላገኘሁት እንድትመለከቱት ጋብዣችኋለሁ ::

ምንጭ:- Uploaded by RasParchie on Mar 4, 2011. BOB MARLEY - Life History of A Legend.wmv.

ተድላ
የወያኔ ሕገ -አራዊት አንቀፅ 39 ኢትዮጵያን የመበታተኛ ፈንጂ ነው !
ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር !!!
ተድላ ሀይሉ ዘብሔረ -ኢትዮጵያ ::
ተድላ ሀይሉ
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 4903
Joined: Fri Mar 17, 2006 2:45 pm
Location: ኢትዮጵያ

Postby ተድላ ሀይሉ » Tue Jan 08, 2013 4:39 pm

ሰላም ነገደ-አርበኛ ዘዋርካ:-

ድሮ ኢትዮጵያውያን የዕድሜ ባለፀጋዎችን ትልቅ ሥፍራ በምንሠጥበት የታሪካችን ዘመን በአገራችን የዕድሜ በረከት ነበር:: ኮሚኒዚም-ወ-ናዚዝም በአገራችን በሠፈኑበት ባለፉት 40 ዓመታት ይህ ፀጋ ከአገራችን ሕዝብ ላይ ተፈፍፈዋል:: ሆኖም አሁንም 100 ዓመት ዕድሜን የደፈኑ ጎምቱ አረጋውያን አሉን : ያውም በሥደቱ ዓለም::

እኒህ አረጋዊ አባት ሚካኤል የተሻወርቅ ይባላሉ : ዴንቨር (ኮሎራዶ ግዛት : አሜሪካ) እንደሚኖሩ በፊልሙ ላይ ተገልጿል:: ታዲያ እኒህ አባት እንኳን 104 ዓመት የሞላቸው ሊመስሉ ገና ሌላ 20 ዓመታት የሚኖሩ ይመስላል:: ለዚህ የዕድሜ ፀጋ እንዴት ሊበቁ እንደቻሉ ሲጠየቁ በቀን አንዴ ብቻ ምግብ እንደሚመገቡ : ዘወትር የአካል እንቅስቃሴ እንደሚያደርጉ (ግማሽ ማይል ወይም 800 ሜትሮች ያህል) : ከሁሉም በላይ "የዕለት እንጀራዬን ሥጠኝ" ብለው ሠርክ ፀሎት እንደሚያደርሱና ሥራ መሥራትም እጅግ ወሣኝ መሆኑን ይገልጻሉ:: ሙሉ ቃላቸውን ከሚከተለው አድራሻ ታገኙታላችሁ::

ምንጭ:- PokJournal, Mon Jan 7, 2013. 104-yr-old walks mall everyday for 12 years.

ተድላ
የወያኔ ሕገ -አራዊት አንቀፅ 39 ኢትዮጵያን የመበታተኛ ፈንጂ ነው !
ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር !!!
ተድላ ሀይሉ ዘብሔረ -ኢትዮጵያ ::
ተድላ ሀይሉ
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 4903
Joined: Fri Mar 17, 2006 2:45 pm
Location: ኢትዮጵያ

Postby ተድላ ሀይሉ » Mon Jun 10, 2013 12:35 pm

ሰላም ነገደ-አርበኛ ዘዋርካ:-

ሠሞኑን በምድረ-አሜሪካ ኢትዮጵያን በጥሩ የሚያስጠሩ ሦሥት ታላላቅ ኢትዮጵያውያን ለሕዝብ እይታ በቅተዋል:-

ዶ/ር መንበረ አክሊሉ

ፋናዬ ይርጋ

በፀጋው ታደለ


በተቃራኒው ደግሞ የትግሬ-ወያኔዎች ለ22 ዓመታት በኢትዮጵያ ያስፋፉትን የልቅ-ወሲብ ባህላቸውን በቴሌቪዥን በአደባባይ ወኪላቸውን ሠንደቅ ዓላማቸውን አልብሠው አስመርቀዋል::

ኢትዮጵያዊነት እና ትግሬ-ወያኔነት ይህን ያህል የሠማይ እና የመሬት ያህል የተራራቁ እና ፍፁም ሊቀራረቡ የማይችሉ እሴቶች መሆናቸውን በአደባባይ ያየንበት ወቅት...

ተድላ
የወያኔ ሕገ -አራዊት አንቀፅ 39 ኢትዮጵያን የመበታተኛ ፈንጂ ነው !
ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር !!!
ተድላ ሀይሉ ዘብሔረ -ኢትዮጵያ ::
ተድላ ሀይሉ
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 4903
Joined: Fri Mar 17, 2006 2:45 pm
Location: ኢትዮጵያ

Postby ቢተወደድ » Fri Jul 05, 2013 3:50 pm

አንተ ጠብደል መሀይም ትግሬ የምትለዋን ቃል ተወት አርገህ ሌላውን እንደፈልክ:: ሽንፍላ

ተድላ ሀይሉ wrote:ሰላም ነገደ-አርበኛ ዘዋርካ:-

ሠሞኑን በምድረ-አሜሪካ ኢትዮጵያን በጥሩ የሚያስጠሩ ሦሥት ታላላቅ ኢትዮጵያውያን ለሕዝብ እይታ በቅተዋል:-

ዶ/ር መንበረ አክሊሉ

ፋናዬ ይርጋ

በፀጋው ታደለ


በተቃራኒው ደግሞ የትግሬ-ወያኔዎች ለ22 ዓመታት በኢትዮጵያ ያስፋፉትን የልቅ-ወሲብ ባህላቸውን በቴሌቪዥን በአደባባይ ወኪላቸውን ሠንደቅ ዓላማቸውን አልብሠው አስመርቀዋል::

ኢትዮጵያዊነት እና ትግሬ-ወያኔነት ይህን ያህል የሠማይ እና የመሬት ያህል የተራራቁ እና ፍፁም ሊቀራረቡ የማይችሉ እሴቶች መሆናቸውን በአደባባይ ያየንበት ወቅት...

ተድላ
When we do it right No-one remembers,
When we do it wrong No-one forgets.
ቢተወደድ
ዋና ውሃ አጠጪ
ዋና ውሃ አጠጪ
 
Posts: 1965
Joined: Tue Jul 21, 2009 3:21 pm
Location: Dabra Za`Yet

Previous

Return to Warka Culture and Literature - ዋርካ ባህልና ሥነ ጽሑፍ

Who is online

Users browsing this forum: Google [Bot] and 0 guests