ማርቆሶች ተሰብሰቡ

Topics related to cultures, arts, languages, arts such as humor, music, traditional literary genres of poems, ግጥም ፣ ቅኔ ፣ ተረትና ምሳሌ)

ማርቆሶች ተሰብሰቡ

Postby ለማ12 » Sat Jun 16, 2012 2:27 pm

እዚህ ላይ እስኪ ማርቆስ ብ1975 ጀምሮ የነበራችሁ ተስብሰቡና እናውራ.

በተልይም የድብዛውን ትምህርታችንን እንወያየው.
ለማ12
ውሃ አጠጪ
ውሃ አጠጪ
 
Posts: 1105
Joined: Sat Jun 16, 2012 9:46 am

Postby ሙዝ1 » Tue Jul 24, 2012 5:55 pm

75 ትንሽ ራቅ አለ .... ፍሬንዴ ...
እስኪ ከ80ዎቹ አጋማሽ ጀምሮ ማዉራት የሚችል ካለ ጎራ ይበል ....

አሁን ኪነ ጥበቡን እየመሩት ካሉት የነ በዉቀት ስዩም ዘመን .... ሚዲያዉን እነ ኤልሳቤጥ እና አበባየዉ የአዲስ አድማሷ .... የነሱ ዘመነ ሰዎች አላችሁ? አሪፍ አሪፍ ትዝታዎች ይኖሩናል .... ድብዛን ጨምሮ :wink: ... ከአብማ ጠላ .... እስከ ሸዋ በር መናፈሻ .... ከኪዳነ ምህረት ..... እስከ የኮቼ የሚዳቋ አደን (እነ ዉቃዉ የከተማ ልጆች ስለ ሚዷቋ አደን ሲወራ ትልቅ ጀብድ ይመስላችሁ ይሆናል) .... ከዉትርን እስከ ዉሰታና አባይም የዋና እና የዉሀ እናት አደን ለቺኮች ,,,, ... ,,, አቦ .... ገጠር እንደማደግ ጣፋጭ ነገር ይኖር ይሆን? :wink:
አይን ሁሉን ቢያይም አጠገቡ ያለዉን ቅንድብ አይቶ አያዉቅም ...
ሙዝ1
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 3128
Joined: Wed Feb 22, 2006 9:25 am

Postby ለማ12 » Tue Jul 24, 2012 7:51 pm

በል እሽ የሆኑ ነገሮችን ጠቁመሀል ግን ወጣት ስትሆን አትቀርም ሆኖም ግን ከጠቀስካቸው ውስጥ በእውቀቱን በቅርብ አዲስ አበባ ሎምባርድያ አግንቸው ምሳ ነገር ሞክረናል ይሁን እንጂ ትንሽ ወጣትነት አያጣችሁም ለመሆኑ እስኪ ገጠር ያልከው እስክየት ነው ?


የሸዋብሩ ገ ጠላ ብዙም አይደለም እንዲያውም አብማም ጠፍቷል:
እኛ የነበርነው ዮሀንስ የድብዛ ዳይሬክተር በነበረብት ጊዘኤ ነው:
እስኪ ብዙ ሳልቀባጥር መግቢያ ነገር ስጠኝ:

ከቺኮችም ብትጠቅስልኝ ሳላውቅ አልቀርም


እኔን ያስተማሩኝእነ ጌቸው አበሹ
እነ አለማየሁ እንግሊዘኛ ዝቅ ብለው ደግሞ እነ


ደሳለኝ አስፋው በል አንተም የበኩልህን በል


የምፈራው መጨረሻ አንድ ብልህእኛል እንዳትለኝ ነው

ያ ሁሉ አልፏል ባስቀይምህም እርሳው:

ብዙ ሳልናገር እስኪ ለዚህ መልስ :
ለማ12
ውሃ አጠጪ
ውሃ አጠጪ
 
Posts: 1105
Joined: Sat Jun 16, 2012 9:46 am

Postby ሙዝ1 » Wed Jul 25, 2012 9:03 am

ሰላም ለማ12
አዎ የማስታዉሳቸዉን መምህራን ነዉ የጠቀስከዉ .... ድብዛ 2 አመታት ተምሪያለሁ 85/86 በኛ ዘመን አቆጣጠር.... ለቫኬሽን ግን ብዙ ክረምቶችን አያቶቼ ጋ አሳልፊያለሁ .... ከኔ ዘመን ሰዎች አሁን በትንሹም ቢሆን ወደ ሚዲያዉ የገቡትን ነዉ የጠቀስኩልህ .... እንጂ በየቢሮዉ ትላልቅ ደረጃ የደረሱ ብዙዎቻችንም አባቶች ሁነናል .....ከበዉቄ ጋ አንድ ባች ነን .... ... አባቱን ታስታዉሳቸዉ ይሆን? እንግሊዝኛ መምህር ጋሽ ስዩም? በጣም ቀልደኛ ነገር ነበሩ :wink:

ጌታቸዉ አብሾ .... ኬሚስትሪ አስተማሪ .... አሁንም አለ አያቶቼ ጋ ስሄድ አይቸዋለሁ ... ደሳለኝ አስፋዉ እንግሊዝኛ መምህሩ ይሆን? .... ሁሌም በከረባት ሽክ የሚል በኢህአፓ ሰበብ የተደበደበና የዛ ዉጤትም ወደ ሲጋራዉና ቅምቀማዉ ዘዉ ብሎ ያስገባዉ ግን ጂኒየስ ይመስላል ....

እኔ ስማር ርዕሰ መምህር የነበረዉ አቶ አስራት ነዉ (ስሙን ያልረሳሁት ቆንጆ ቆንጆ ሴት ልጆች ነበሩት እነ መለሰች አስራት እና ትንሿ ስሟን አላስታዉሰዉም :wink: ) .... ... ከርዕሰ መምህሩ በላይ ዘበኞች ይፈሩ የነበረ ይመስለኛል .... መንግስቴ ... አበበ ምናምን አይነት ስም ያላቸዉ ...

ከማስታዉሳቸዉ መምህራን .... ጋሽ ምንላርግህ ... ሀሀሀ ... ስሙ ራሱ ደስ የሚል ነዉ ባህሪዉም ከሌሎች መምህራን ለየት ይላል ..... የሱ ወንድ ልጁ አንድ ክፍል ቢቀድመኝም ጓደኞች ነበርን አሁንም ነን ... ደረጀ ምንላርግህ የኒዉ አቢሲኒያ ኮሌጅ ሼር ሆልደር ነዉ ሙሉ የሙዚቃ አልበም እንደሰራ አዉቃለሁ ነጠላ ዜማዉን እንደቀለቀቀም እንዲሁ .... ሙሉዉንም አልበም ምናልባትም ጀባ ይለን ይሆናል ... ...

ገጠር የምትለው የቱን ነዉ ላልከኝ ....
ከ11ዱ የደብረማርቆስ ቀበሌዎች ዳር ዳር ያሉትን .... ቀቢ ለአስተርዮ ማርያም ሄጃለሁ ..... የቦ ሾላ ለመልቀም .... ወንቃ ጎተራዉን ለማየት :wink: የኮቼ ና ዳሊጋዉ ለሚዳቋ አደን ... እንድማጣ በሩቁ ነዉ ማዉቀዉ ... እናም በስቴዲየሙ በኩል ያሉ እነ አራት መከራከር :wink: ..... አይበቃህም እንዴ?

ለማ ...
የእዉነቴን ነዉ ማወራህ .... ብዙ ቦታዎችን አይቻለሁ ኑሪያለሁም (ከሀገር ዉጭም ሀገር ዉስጥ ያሉ ትላልቅ ከተሞችም) ... .... እንደ ማርቆስ የምወደዉ ከተማ የለም ... በነገርህ ላይ እድሜዉን ከሰጠኝ የጡረታ ጊዜዬን የማሳልፈዉ እዛዉ ነዉ የሚሆነዉ .... ከወዲሁ አሪፍ ቪላ ሰርቻለሁ:: ቂቂቂ ... አጠቃላይ ወጭዉን ብነግርህ ትስቃለህ :lol: .... ከአዲስ አበባ ጋ ስታስተያየዉ በጣም ትንሽ
አይን ሁሉን ቢያይም አጠገቡ ያለዉን ቅንድብ አይቶ አያዉቅም ...
ሙዝ1
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 3128
Joined: Wed Feb 22, 2006 9:25 am

Postby ለማ12 » Wed Jul 25, 2012 1:05 pm

ተ ሰው?ሰላም ሙ

አዎ ሰወችንም ነገሮችንም ነካካሀቸው


ምላርግህ ሽፈራው አስተምሮሀል????? ቅቅቅቅቅአቶ አስራት በኔ ጊዤ ምክትል ርሰመምህር ነበር

አሁን ግን እሱ ሞቷል የሚገርመው አባቱ አሉ
የጋሽ አስራት አባት አቶ አድማሴን ታውቃቸው አለህ ?


አንድ ጊዜ ቀብለ 4 ማለትም እነሱ ሰፈር አንድ ልጅ ራሱን ሰቅሎ ሞተና ሲመርቁ


የሳቸው ትንሹ ልጅ በጣም ረባሽ ስለነበር ምን አሉ መሰለህ?
በጣም ነው የሚያሳዝነው ጎብዝ ልጅ ነበር አሉና እንግዲያማ የኔ ልጅ ይቺን ይሞክራታል እዚህም ድረስ ወንድ ነት ብለው ልቅሶኛውን አስቀዋል
እነም እንደአንተ ማርቆስን በጣም ነው የምወደው የጥራሀውን ገጸር ሁሉ አውቀዋለሁ በተልይ 4 መከራክር የሚባለውን ሄጀ አይቸዋለሁ በጣም ደስ ይላል
አዎ ደሳለኝ አስፋው እኔን አስተምሮኛል ግን በኢሀፓ ተደብድቦ በጨ እንደማለት ብሏል በጣም ፈኒ ነውያስተምሩን የነበሩ በሙሉም ባይሆን አሉ ግን በጣም ተጎሳቁለውል


ጌታቸው አበሹ በጣም የምወደው አስተማሪዬ ነበር ምሽቱ ሞታበታለች አሁን:


አላገኝሁትም

እኛ እንጫወት የነበረው ከን ሄለን ሰሎሞን: ከነ ሙሉጎጃም........

ያያስራት ልጆች መልከ መልካም ቢሆኑም ለጥብስ አልደረሱም ነበር:
የደብረ ማርቆስ ዩንቨርስቲወሰታ ትምህርት ቤት አጠገብ ነው የተሰራው ብዙም የሚያስደስት አይደለም


ማርቆስ ቡና ቤት ፈርሶ እየተሰራ ነው ማን እንደሚሰራው አላውቅም


ጨሞጋ የሚሉት ትምህርት ቤት ነበር ከከተማ ልጆች ጋር ድብድብ ነበር አይ ጊዜ በጣም ነው ትዝ የሚልርኝ

ማርቆስ 11ዱን ቀበሌ በደብ ከማወቄም በላይ ሳልባልግበት ያለፍኩት ያለ አይመስለኝም:

አንድ ጊዜ ከአበባው አላምረው ጋርክርክር ገጥሜ የሳቁት ትዝ ይለኛልመንግስቴ የሚባለው ዘበኛ በጣም ይፈራኝና ይወደኝ ነበር አሁን ወያኔ ሆኖ የቀበሌ ተመራጭ ነው


አንተ አልደርሰክባቸው ይሆናል አባ ቸኮል የሚባሉ ዘበኛችን ነበሩ ድብዛ በጣም ቀልደኛ ነበሩ በተልይ ቺኮችን ሲፎግሮ ያስቁኝ ነበር:
ለማ12
ውሃ አጠጪ
ውሃ አጠጪ
 
Posts: 1105
Joined: Sat Jun 16, 2012 9:46 am

Postby ሙዝ1 » Wed Jul 25, 2012 1:48 pm

ሀሀሀሀ .... አቶ አድማሴ የተናገሩት በሳቅ ገደለኝ .... ከነ አክሰንታቸዉ የሰማሁት ነዉ የመሰለኝ ...

እስኪ ስለ ቺኮች ,,,, ያዉ እኔ መፈጠሬን ከሚያስወድዱኝ የአምላክ ፍጥርታት .... አንዳኔ የአምላክ ምርጥ ስጦታዎችም እንደሆኑ ይሰማኛልና እስኪ ወጋችንን በነሱ ላሟሸዉ .... ... ማርቆስ እኔም እንዳንተ ሁሉንም ቀበሌ አዳርሻለሁ ..... ለቺክ ብዬ ተካንቻለሁ :wink:

ሄለን ሰለሞን ..... ማርቆስ 2 ሄለን ሰለሞኖችን አዉቃለሁ ... አንዷ ኤርትራዊ የጦርነቱ ጊዜ ከነቤተሰቦቿ እንደሄደች ሰምቻለሁ ፍቅር አስጨራሽ ስትማር አንድ ሁለቴ ሸኝቻታለሁ :lol: .... ሁለተኛዋን ግን በአካል አላዉቃትም .... ስለዉበቷ በጣም የሚወራላት .... ማርቆስን በዉበቷ መአዛ ያወደች .... ብዙዎቹ የሰገዱላት ነበረች ሲባል እሰማለሁ .... ያኔ ኢሮፕ እንደምትኖርም ታናሽ እህቷ ሰናይት ሰለሞን በኩራት አጫዉታኛለች (ስለነ ሰኒ ግሩፕ ካወካቸዉ በሰፊዉ እንቀዳለን) .... ወንድሜ የነ ሰኒ ወንድማቸዉ አንዱ ዘፋኝ ነዉ .... ካሴት ምናምን አዉጥቷል ሲባል ሰምቻለሁ ..... አንዱን ግን አዉቀዋለሁ ስፖርተኛ ነገር ... ስሙ ካልተሳሳትኩ ታዲዎስ? .... አዎ ፊቱን ግን እስከመቸዉም አልረሳዉም ከሲኒማ ቤቱ ጀርባ ከእህቱ ጋ ስቀድ አይቶን ማጅራቴን አንጠልጥሎ አይኑን ያጉረጠረጠብኝን አልረሳዉም .... ሰኒን ባለፈዉ አመት ይመስለኛል ሂልተን አዲስ ተገናኝተናል ... በመከራ ነዉ ያስታወሰችኝ

ሙሉጎጃም? .... ይሄ ስም በብዛት አለ ጎጃም ዉስጥ አንተ የምትላት ኤፍሬም ታምሩ የዘፈነላት ነች? ቂቂቂ ስቀልድ ነዉ ....
አይን ሁሉን ቢያይም አጠገቡ ያለዉን ቅንድብ አይቶ አያዉቅም ...
ሙዝ1
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 3128
Joined: Wed Feb 22, 2006 9:25 am

Postby ለማ12 » Wed Jul 25, 2012 7:48 pm

ሰላም ሙ
እባክህ ያገሬን ትዝታ አታስነሳብኝ.

አዎ ሄለን አንተ የሸኘሀት ሳትሆን ሁሉንም ያሰግድችው ባሪያ ናት የጥበበ ሰሎምን እህት:: በል ተወው ይህን ገባ ብዬ ካወራሁ ብዙው ሰዉ ስለሚያውቀኝ እንግደልህ ነው የሚሉኝ የድሮው ጉልበቴ የለ: ቅቅቅሙሉጎጃም ያልኩህ ብዙ ናቸው ግን የትኛዋን ላውጋህ በተልይ ሙሉጎጃም የመረብ ካስ ለመጫወት ትሞክር ነበር ይህን ስልህ ዋናዋን የመረብ ካስ ተጫዋች ማለቴ አይደለም ውንዋን ደሳለኝ አስፋው ያደረጋትን ልንገርህ


በጣም ስለምትኮራ ደግሞ ተማሪ ላወጣ ነው እያለች ስትፈክር እነ ዮሴፍ ደሳለኝ አስገድደው ስኒማ ቤቱ ውስጥ እንዲያመጣላቸው አድርገው የፈጸሙባት ግፍ ይህ ነው አይባልም ፊልም ማየት ትወድ ነበር:
እጨለማ ቤት አስገብቶ አስረከባቸው: ከዚያ የሆነውን መገመት ትችላለህ:

እን ወይዝሪት ሰኒን አውቃቸዋለሁ ግን ብዙም አልጠጋቸውም ነበር አንዱ ዘሎ ተነክሮ ስለነበረ ነው:


የወይዝሮ ማርታ ልጆችም ነበሩ እረ ስንቱ................................
ለማ12
ውሃ አጠጪ
ውሃ አጠጪ
 
Posts: 1105
Joined: Sat Jun 16, 2012 9:46 am

Postby ሙዝ1 » Thu Aug 02, 2012 9:35 am

ሰላም ለማ12
እትዬ ማርታ ያልካቸዉን አላወኳቸዉም ...

ጋሽ ምንላርግህን ያስተማረህ ይመስለኛል. ... በመልካም ከማስታዉሳቸዉ መምህራኖቼ አንዱ ነዉ .... ትንሽ ወጣ ያለ ባህሪ ነበረዉ .... 9ኛ ክፍል እንግሊዝኛ አስተምሮኛል ቂቂቂ ለዛ ነዉ እንግሊዝኛ በጣም ጎበዝ የሆንኩት :lol: ... ከምር ግን ጥሩ እንግሊዝኛ ተናጋሪ እንድንሆን ፍላጎቱ አሁንም ድረስ ይገርመኛል .... አልተጠቀምንበትም ....

ስለሱ ከማስታዉሰዉ ,,,
በ1992 በተካሄደዉ የህዝብ ተወካዮች ምርጫ የግል ተወዳዳሪ ነበር .... ምልክቱም ጀበና :lol: እንዳሁኑ ሳይሆን ያኔ በኢህአዴግ ተቃዋሚነት ተወዳዳሪ ያልነበረን ጎረምሶች ነበርንና በግሩፕ በተማሪ ሀቅማችን ከአዲስ አበባ ደ/ማርቆስ ድረስ ሄደን ጋሽ ምንላድርግህ እንዲመረጥ ሎቢ እናደርግ ነበር ,,, ... ,,, ዉጤቱ ጥሩ አልነበረም ... ብዙም ሳይቆይ እንዳረፈ ሰማሁኝ ... በጣም ነበር ያዘንኩት

የ9ኛ ክፍል ተማሪ በነበርኩበት ወቅት እንግሊዝኛ አስተምሮኛል .... ያዉ ቅምቀማ ላይ በጣም ይታማ ነበርና .... የእንግሊዝኛ ቃላት እየሰጠ አረፍተ ነገር ስሩ ይለናል ... ... ዲፊካልት በሚለዉ ቃል አረፍተ ነገር ስሩ ... የሚል ነገር እንደነብረዉ አስታዉሳለሁ .... በፍጥነት ሰርቼ ቁጭ እንዳልኩኝ ጨረስክ? አዎ ቲቸር .... እሽ አንብበዉ .... ድሪንኪንግ አልኮሆል ኢዝ ዲፊካልት አልኩኝ .... ተማሪዉ በሳቅ ወደቀ .... ካሽ ምንሌም ... ተዉንጂ ጎበዝ ትንሽ ትንሽማ ምንም አይልም አለ ሌላ ሳቅ .... ኤኒዌይ በጣም የሚመቸኝ አስተማሪ ነበር ...

ትንሽ ስለ ከተማዉ ወጣቶች ....

የዛ አካባቢ ወጣት ሲበዛ ጀብደኛ ነዉ ልበል? :wink: ይሄ ጀብደኝነት ሌላ አካባቢ በመጥፎ የሚነሳ ነዉ .... በግሩፕ መደባደብ ... በግሩፕ ሴት ማዉጣት .... ምናምን ብዙም አስነዋሪ አልነበረም .... አሁን እንኳን እንደዛ አይመስለኝም .... ከላይ ሲኒማ ቤት ዉስጥ ያደረጋችሁትን ስታወራ እዉነትነቱን ምንም አልተጠርጠርኩም :wink: ... ቂቂቂ ደብረማርቆስ ሲኒማ ቤት .... ጨለማ ቤቷንም አስታወስኩኝ .... አንዴ ጩጬ እያለሁ ክረምት ለማሳለፍ ሄጄ ... የሆነ አሪፍ ፊልም ማስታወቂያዉ ተለጥፎ አየሁ ... እናም መግቢያዉ 1 ብር ነዉ:: ቂቂቂ አያቶቼን 1 ብር ለፊልም ስል .... ቂቂቂ .... አቤት የጮሁት .... አንደኛ የብሩ ብዛት .... ቂቂቂ .... ሁለተኛ ለፊልም? የዱሩዬነት መገለጫ ነዋ :wink: ..... ሌላ ጊዜ ሳለቅስ እናቱ ናፍቃዉ ነዉ ምናምን ተብሎ የምፈልገዉ ነገር ይደረግ ነበር ያኔ ግን ተዉት ያልቅስ .... ምን አይኑ ዳር ቤት አልተሰራ :lol: ...

እኔ ያንቺ ወንድም ታዲያ ያኔም የምፈልገዉን ነገር ከማድረግ ወደ ሗላ ማለት መሸነፍ ነዉ ሚመስለኝና ሄጄ ፊልም መግባት እፈልጋለሁ ብር ግን የለኝም አልኳቸዉ .... አስፈራርተዉ ሊያባርሩኝ ፈለጉ .... ቂቂቂ ንቅንቅ አላልኩም ... .... የፈለጋችሁትን የጉልበት ስራ እሰራለሁ ... አዳራሹንም አጸዳለሁ ... ወንበር አስተካክላለሁ ምናምን ብዬ ድርቅ ስል ..... ሁኔታዬ ግርም ብሏቸዉ በል እሽ ግባና አጽዳ ተባልኩ .... ቂቂቂ አጸዳሁ :wink: እንደዉም የአቀማመጥ ስትራቴጂ ሁሉ ቀይሼ እንዲህ ብታደርጉት አሪፍ ነዉ ... አንዱ አንዱን አይከልልም አይነት ምክር ቂቂቂ ምናልባት 10 ወይንም 11 እድሜ ላይ ብሆን ነዉ .... ሙሉ ክረምቱን በነጻ :wink: ... ችግሩ አንድ ፊልም በተደጋጋሚ ለ1 ወር ሊታይ ይችላል

እስኪ ሁሌም ስለማስታዉሰዉ አደን ትንሽ ቆይቼ እቀዳለሁ ...
አይን ሁሉን ቢያይም አጠገቡ ያለዉን ቅንድብ አይቶ አያዉቅም ...
ሙዝ1
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 3128
Joined: Wed Feb 22, 2006 9:25 am

Postby ለማ12 » Thu Aug 02, 2012 1:20 pm

ሰላም ነው ሙ?


አዎ የሚያስቅ ነው ያደረከው ወሮ ማርታን ያልከኝ ማርታ ሀይሌ ቡና ቤት ማለቴ ነበር እንልፈው ለጊዜው


አንድ ጊዜ ያደረግነውን ልንገርህ በ3ኛው ክፈለ ጊዜ እስፖርት ነበረን ከዚያም ወጥተን ወደ እስፖርት ስንሄድ እሽንት ቤቱ ዝንድ ስንደርስ ዘመን አደምን ማለትም ያባ አደምን ልጅ አገኘነው እኔም ጥጋበኛ ስለነበርኩ አሁን እግርህን ወደላይ እራስህን ወደታች አድርጌ ሽንት ቤት ሳልከትህ ብር አምጣ አልኩት ቅቅቅቅቅ የሀብታም ልጅ ነውና : እሱም ሳያቅማማ ያለውን 10 ብር ሰጠን በኛ ጊዜ ይህ በጣም ብዙ ነው ያነን ይዘን እስፖርት ቆየንና በዚያው ወደጠላ ቤት መረሽን በሙሉ ሴቶችንም ጨምረን ቅቅቅቅ ስንቀመቅም ውለን በመጨረሻ ማለትም በ6ኛው ክፍለ ጊዜ ተሰልፈን አንዲቱን በእንስራ ጠላ አሸክመን ገባን በ6ኝውም ክፍለ ጊዜ እርሻ ነበረንና መምህሩም መስፍን በጉ ነው የሚባለው ይዘን እንድይከሰን አንገራገርነውና ዝም አስባልነው: ቅቅቅቅቅቅ
ይህ አልበቃ ብሎን ሲደወል ሰንደቅ አላማ የምናወርድ እኛ ነን ብለን ተሰለፍን: አንዱ ሰንደቅ አላማውን ሊአወርድ ሲሞክር እሱስ ወደላይ ነው የሚስበው : ቅቅቅቅ... ዘምረን ስንጨርስ ሰንደቅ አላማው እዚያው ነው እናም ተማሪው ሳቀብን ረሰ መምህሩ አሰፋ ስለሽ ይባል ነበር አሁን ምንም ችግር የለም ነገ እንነጋገራለን ብሎ ዝም አለን: ቅቅቅቅቅ.
እኛም ተማሪዉን እየመራን መሀል ከተማ ድረስ እየለፈልፍን ቀጠል እስከ እንስራው ጠላ ጨምሮ:
ቅቅቅቅቅ....

በነጋው የጠበቀንን መለስ ብዬ አጫውትህ አለሁ:
ለማ12
ውሃ አጠጪ
ውሃ አጠጪ
 
Posts: 1105
Joined: Sat Jun 16, 2012 9:46 am

Postby -...- » Thu Aug 02, 2012 6:54 pm

ከየቦ ማርያም አካባቢም ሰላም ብለናችሁ አለን ለማለት ያህል ነው
ሞቼ እየተነሳሁ ልሙት እንደገና
አንድ ሞት ላገሬ አይበቃትምና
-...-
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 401
Joined: Thu Feb 09, 2012 8:36 pm

Postby ሙዝ1 » Thu Aug 02, 2012 8:51 pm

-...- wrote:ከየቦ ማርያም አካባቢም ሰላም ብለናችሁ አለን ለማለት ያህል ነው


ሀሀሀ ሰርጎ ገብ አለመሆንህን ለማረጋገጥ እስኪ የየቦ ጎረቤቶችን ዘርዝርልን ... :wink:

ለማ 12

በሳቅ ነዉ የገደልከኝ .... ታየኝ'ኮ ጠላ በእንስራ አሸክማችሁ ትምህርት ቤት ግቢ ዉስጥ .... ለዛ'ኮ ነዉ የዛ አካባቢ ወጣት ጀብደኛ ነዉ ያልኩት ... ... በተለይ ከነበርኩበት ቦታ ጋ ሳስተያየዉ ብዙ ይሚገርሙኝ ነገሮች አሉ...

ትንሽ ስለ አደን
መጀመሪያ የመሳሪያ ድምጽና ተኩስ ሰምቼ የተለማመድኩት ሰንተራን አልፈህ ያሉ የአያቴ ገባሮች .... ገባርነታቸዉን አሁንም ድረስ መተዉ የማይፈልጉ ክፍሎች (አማራ አምራን ያስገብር ነበር ብል በብሄር ደረጃ ተበደልን የሚሉ ምን ይሉ ይሆን? :wink: እነዚህ የዋህ ሰዎች አሁንም ድረስ በህይወት ያሉት የዛ ትዉልድ ሰዎች ሴት አያቴ በህይወት ስላለች እሸት እየተሸከሙ ይመጣሉ ብል ማን ያምነኝ ይሆን? አምላክ የተመሰገነ ይሁን መሆን ያለብኝን ያክል ሁኘላቸዋለሁ ) ... ,,, ... እድሜየ 10 ሳይደርስ ይመስለኛል .... ለዛዉም አብዛኛዉን መንገድ በእግሬ እንድጓዝ ተደርጌ .... የቆመ ኢላማ ተሰጥቶች ተኮስኩ ... ከድምጹ የመሳሪያዉ እርግጫ ሀሀሀ (መሳሪያዉ አልቤን ነበር) .... ለአደን ወደ አባሊባኖስ ምናምን ስሄድ ነዉ አጭር ሚኒሽር የታጠኩት .... ያኔ ተጀመረ ...

በጣም የምውደዉ አደን ግን ... ደብረ ማርቆስ ከተማዉ ዉስጥ ካሉ የእድሜ እኩዮቼ ጋ ... ሀይለኛ የሚባሉ የሰፈር ዉሾችን ይዘን ዉትርንን ተሻግረን በምኞትና በጀብድ ረሀብ ወደ ዳሊጋዉ ጫካ .... የካምፕ ልጆችን ካልፈራን ደግሞ 15ኛ ሻለቃ (ስለነሱ ልጆች የዋርካዉ ሾተል የሆነ ነገር ይለን ይሆናል :wink: ሚስጥር አወጣሁ ይሆን? ) ጀርባ ካለዉ ጫካ ዉስጥ ወይንም ወርቅነህ የማነ ጫካ (ከማርቆስ ጸበል አካባቢ) .... ሚዳቋ ... ጥንቸል ... ካገኘን አራዉጠን ይዘን እየጨፈርን ወደ ሰፈራችን የምንሄደው ... ካመለጠችን ዉሻዎቻችንን እየገረፍንና እየተርገምን የምንመለሰዉ ... .... ለምንድን ነበረ የማይርበን? ምናልባት ጠሗት 3 ሰዐት ላይ የሄድን አደናችን ካልተሳካ እስከ ምሽቱ 2 ሰዐትም ልናምሽ እንችላለን .... ያዉ ክረምት እንደምሄድ ነገሪያችሗለሁ አይደል? ቂቂቂ ዉትርን ከሞላብንም መሻገር አንችልም እዛዉ ከጅብ ጋ ተፋጠን ማደር ....

ቆቅም እናጠምድ ነበር .... ዋዉ ወጥመድ አጠማመድ በራሱ ሳይንስ ነበረዉ ቂቂቅ... የአንገቷ ማስገቢያ ነገር አዘጋጅተን ጥሬ እንበትናለን ... እሱን ለመልቀም አንገቷን ስታሰግ ነዉ የምትንጠልጠለዉ ... ..
አይን ሁሉን ቢያይም አጠገቡ ያለዉን ቅንድብ አይቶ አያዉቅም ...
ሙዝ1
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 3128
Joined: Wed Feb 22, 2006 9:25 am

Postby ሀሪከን2 » Fri Aug 03, 2012 3:34 am

አንች ሰውየ ግን ግርማ የሚሉት ልጅ ወይስ ዴኒልሰን ትሆኝ ይሆን :lol:
ጽንፈኝነትን አጥብቀን እንቃወማለን :lol:
each mind is a different world
ሀሪከን2
ውሃ አጠጪ
ውሃ አጠጪ
 
Posts: 1039
Joined: Fri Oct 31, 2008 3:59 am

Postby ሙዝ1 » Fri Aug 03, 2012 6:04 am

ሀሪከን2 wrote:አንች ሰውየ ግን ግርማ የሚሉት ልጅ ወይስ ዴኒልሰን ትሆኝ ይሆን :lol:
ጽንፈኝነትን አጥብቀን እንቃወማለን :lol:


ሀሀሀሀ ... ሀሪክ ሌባዉ ... :wink: እግዚአብሄርን አንድ ሁለት ሙከራ ብትሞክር ጋማ ትለኛለህ :wink:

ግርማ ከበደ (ሶቅራትስ) UNHCR አሶሳ ሰራተኛ ነዉ ... ... እንደበፊቱ እንዳይመስልህ ... ሀሀሀ እሱን አይደለሁም .... ግን በጣም በጣም ግዋደኛዬ

ዴኒልሰን (ዝናቡ :wink: ያ የምናዉቀዉ ዝናዉ አሁን የለም ... ከሳምንት በፊት ተገናኝተን ነበር ሁለተኛ ድግሪዉን እየሰራ ነዉ) ,,, .... በነገርሽ ላይ ሁለቱም ደብረ ማርቆስ የቀበሌ 6 ልጆች ናቸዉ :wink:

እዛኛዉ ቤት 11 እና 12 ያልሽዉ ተሳስተሻል ወይንም ተሳስቻለሁ ... ሁሉንም ሲርየስሊ አትዉሰጅዉ :wink:

አመዳም ነገር ነህ .... ይሄ ምኑ ነዉ ጽንፈኝነት? ... ደግሞ እዛኛዉ ቤት የአዲስ አበባ ልጅ ምናምን ያልከዉ ከየታባክ አምጥተህ ነዉ? ማርያምን የአዲስ አበባ ልጅ አይደለሁም :lol: ... አለመሆኔም ያጣሁት ነገር ምናልባት በከተማ አዉቶብስ እየተመላለሱ አለመማር ወይንም ሜዳ አጥተዉ አስፋልት ዳር ኳስ መጫወት .... .... ቂቂቂ እስኪ አስበዉ .... የአዲስ አበባ ልጆች በክረምት ዳጥ ያድጣሉ? :wink: ..እንቆቆ ... አጋም .. ቀጋ ...ለቀማ ወደ ጫካ ይሄዳሉ? ... ሽመለ ቀንድዮሽ ይጫወታሉ? .... በአንዳዉላና በደባይ ጦርነት ይገጥማሉ? :wink: ....
Last edited by ሙዝ1 on Fri Aug 03, 2012 9:20 am, edited 2 times in total.
አይን ሁሉን ቢያይም አጠገቡ ያለዉን ቅንድብ አይቶ አያዉቅም ...
ሙዝ1
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 3128
Joined: Wed Feb 22, 2006 9:25 am

Postby ለማ12 » Fri Aug 03, 2012 7:05 am

[/u]ሰላም የቤቱ ታዳሚዎ

እኔማ አውቄው ውሀው ደፍርሶ አለ ዘመዳችሁ በሉ ተሰብሰቡ:

አንተ የየቦው እስኪ ስለ ጋሽ መኮነን ዘበናይ ትንሽ ንገረን:


በሉ የጋሽ አሰፋን ታሪክ ልጨርስልችሁ
በነጋው የጥዋት ተማሪዎች ነበርንና ብዥታው ለቆን ስለአደረ በስነ ስራቱ ተሰልፈን ሳለ ሰንደቅ አላማው ተከብሮ ሲያልቅ መጣና በሉ እናንተ ትንበርከኩ አለን እአም እኛም ያደረግነውን ስለምናውቅ ተንበረከክን: ቅቅቅቅቅ
እሱም በያዘው ዱላ( ወባይ ) እየተከተለ ይደውለን ጀመር እንድይደርስብን ስንፈጥን ቀደም ይልና ዝግ በሉ እያለ ይወርድብናል ዝግ ስንል ደግሞ ፈጠን በሉ እያለ ይወርድብናል: ቅቅቅቅቅ
እስከ 2 ክፍለ ጊዜ ወደክፍል ስንገባ የለበስነው ዩኒፎርም ከጥቅም ውጪ ሆኖ ቁጭ አለ እኛም ገብተን አንማርም ብለን አሻፈረን አልን መምህሩ ሊከሰን ሲል በሩን አስገብተን ዘጋንበት ይህ መምህር አሁን አሜሪካ ነው ያለው: ቅቅቅቅቅ...


አሁን ግን ስብስባችሁ ስለአስፈራኝ ብዙ ከመናገር ላቆም ነው:
ይዚህን ርእሰመምህር ግፍ በሚቀጥለው እጨምራለሁ በጣም ግፈኛ ነበር : ቅቅቅቅ እኛም ጥጋበኞች ነበርን
የሚቀጥለውን ጠብቁ:...
ለማ12
ውሃ አጠጪ
ውሃ አጠጪ
 
Posts: 1105
Joined: Sat Jun 16, 2012 9:46 am

Postby ሙዝ1 » Fri Aug 10, 2012 5:58 pm

ሰላም ለማ .... በሰላም ነዉ የጠፋኸዉ?

የያኔዋን ማርቆስ ሳስብ ምን ትዝ አለኝ መሰለህ? ፎቶ ቤቶቿ .... ቂቂቂ ሁሉም በአንድ መስመር ላይ ይገኛሉ ... ከፖሊስ ጣቢያዉ እስከ በግ ገበያዉ .... ...
ማርስ .... ሙሉአለም ... ሀይሌ .... በየነ አምዴ .... የሁሉም ፍቶዎች ስቱዱዮዉ ተመሳሳይ ነዉ ..... የሆነች መደገፊያ ያላት ወንበር .... ከወንበሯ ፊት ልፊት በትንሽዬ ጠረጴዛ አርቲፊሻል አበባ ... .... አርቲፊሻል የሴት ጸጉር .... መነጽር (የሳይትም ሊሆን ይችላል ..... ብቻ የሆነ ሰዉ ትጠቅሞ የጣለዉ መሆን አለበት ) ..... ክብ ማርልቦሮ ቆብ (ለምንድን ነበር ማርልቦሮ የተባለዉ?) ... በመጋረጃ የሚጋረድ የግድግዳ ስዕል ..... ጉርድ ፎቶ ለመታወቂያ አይነት ነገር ሲሆን መጋረጃዉ ይዘጋል .... በተረፈ ያች የጀርብ ዛፍ የበዛባት ጀማሪ ሰዐሊ የሳላት የግድግድ ስዕል ትከፈታለች

እነዚህ ፎቶ ቤቶች ሳስታዉስ ሁሌም ተመልካች አለማጣታቸዉ ግርም ይለኛል .... ቂቂቂ .... አንዳንድ ሰፈሮች እንደዉም ለቅምቀማ ያልደረሱ ጉብሎች (ልጆች) ከመዝናኛ ፕሮግራሞቻቸዉ አንዱ ከተማ ሄዶ ፎቶ ማየት ሳይሆን ይቀራል? .... ብዙ ጊዜ ፎቶዎች አይቀየሩም ... ሰርግ ምናምን ካልነበረ .... ያም ሆኖ ዛሬም ነገም እነዛን ፎቶዎች መመልከት አንዱ የመዝናኛ አካል ነዉ::

አዲስ ሸራ ጫማ በቁምጣ የለበሰ ፍንዳታ .... ሳስበዉ ፎቶ ሲነሳ ዋናዉ ታርጌቱ አብዛኛዉ የእድሜ እኩዮች ፎቶ የማየት ልምድ እንዳላቸዉ ስለሚያቅ አዲሷን ሸራ ጫማ እንቁልልጭ ለማለት ይመስለኛል ... ቂቂቂ ፎቶ አነሳሱ የማርልቦሮዉን ቆብ አድርጎ .... አበባዉን በእጁ ይዞ ትንሽ በርከክ .... የጥቅሻ ያክል የምትታይ ግማሽ ፈገግታ .... የፎቶቤቱን መነጽር በቄንጥ ሰክቶ .... ሌላዋ ደግሞ ትናንሽ የቤተሰቦቿን አባላት ይዛ እሷ ከመሀል ... ሌሎቹ ከጎን ተግተልትለዉ ..... አንዳንዶቹ ሆያ ሆዬ ብለዉ ባጠራቀሙት ፍራንክ .... ከጨርቅ የተሰራችዉን ኳስ በረኛዉ ወይንም የሰፈሩ ጉልቤ ይዞ ይጋደምና ሌሎች በሁለት ረድፍ ተደርድረዉ ...

ሰርግ ከነበረ ደግሞ ከሙሽሪት ቤት እስከ የራባ ,,,, ከዛ ሙሽራዉ ቤት ድረስ ያሉ ፎቶዎች ልክ እንደ ኤግዚቢሽን ለህዝብ ክፍት ይሆናሉ :lol: .... እነ ሀሪከን ታዲያ እየተመላለሱ አንድ ሳምንት የፎቶዉ ቀለም እስከሚል አፍጥጠዉ ይዉላሉ
አይን ሁሉን ቢያይም አጠገቡ ያለዉን ቅንድብ አይቶ አያዉቅም ...
ሙዝ1
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 3128
Joined: Wed Feb 22, 2006 9:25 am

Next

Return to Warka Culture and Literature - ዋርካ ባህልና ሥነ ጽሑፍ

Who is online

Users browsing this forum: No registered users and 1 guest