ፈገግ...ፈገግ....ፈገግታ...ላንድ..አፍታ!!!

Topics related to cultures, arts, languages, arts such as humor, music, traditional literary genres of poems, ግጥም ፣ ቅኔ ፣ ተረትና ምሳሌ)

Postby feredewnetu » Sun Feb 05, 2012 10:36 pm

ባልና ሚስቱ የተጋቡበትን 45ኛ አመት መላው ቤተስቦቻቸውን ልጆቻችውን የልጅ ልጆቻቸውን ስብስበው አያከበሩ ሳለ ጋዜጠኛው በመደነቅ አንዴት ነው አንዲህ ለረጅም ዘመን ትዳራችሁ ሊቆይ የቻለው ምን ድነው ሚስጥሩ? ቢላቸው ባልየው ገና ያኔ ኣራተኛ ልጃችንን አንደወልድን ክጋብቻ መፈታት የፈለገው ወገን ልጆችንም ይዞ አንዲሄዽ ስለተስማማን ነው::
feredewnetu
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 235
Joined: Thu Sep 24, 2009 6:29 pm

Postby ENGEDA1967 » Sat Apr 14, 2012 10:01 am

ምነው ጠፋችሁ ???????????????
ENGEDA1967
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 475
Joined: Fri Aug 27, 2004 11:09 pm
Location: united states

Postby ተድላ ሀይሉ » Sun May 20, 2012 9:30 pm

ሰላም ወገኖቼ :-

እስኪ ይህቺ ቤት አቧራ እንዳይውጣት አንድ ልበል ::

ወያኔ አዲስ አበባ በገባ ሠሞን የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች የተቃውሞ እንቅስቃሴ ያደርጉ ነበር :: ታዲያ በአንደኛው ቀን ከላይ ከስድስት ኪሎ ጀምሮ እስከ አራት ኪሎ ባሉ ግቢዎች የሚማሩ ተማሪዎች ሠልፍ ሲወጡ የወያኔ ወታደር ይመጣና በኃይል ይበትናቸዋል :: የወያኔ ወታደሮች መንገድ ላይ ሲጓዙ የነበሩትንም ሰዎች መታወቂያ እያዩ ሲለዩ ከእነዚያ መካከል ሦሥት ከተለያዩ ግቢዎች የመጡ ተማሪዎች ያጋጥሟቸዋል :: የተመላለሷቸው ቃሎች እንዲህ ነበሩ :-
  የወያኔ ወታደር :- ኣታ ኬት ኖው ?
  ተማሪ 1 :- ከአራት ኪሎ

  የወያኔ ወታደር :- ኣታ ኬት ኖው ?
  ተማሪ 2:- ከአምሥት ኪሎ

  የወያኔ ወታደር:- ኣታ ኬት ኖው?
  ተማሪ 3:- ከFBE
  የወያኔ ወታደር :- ቧ : አጮርባሪ : በኪሎ አትጠራም : ... ተማሪው ትንሽ የሠደፍ ጡጫ ቀምሶ ወደ እሥር ቤት ...

ተድላ
የወያኔ ሕገ -አራዊት አንቀፅ 39 ኢትዮጵያን የመበታተኛ ፈንጂ ነው !
ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር !!!
ተድላ ሀይሉ ዘብሔረ -ኢትዮጵያ ::
ተድላ ሀይሉ
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 4903
Joined: Fri Mar 17, 2006 2:45 pm
Location: ኢትዮጵያ

Postby መልከጻዲቅ » Thu May 24, 2012 12:47 pm

ሰላም ሰላም ለዚች ቤት ደንበኞች ፈረደ , ተድላ እንግዳ እንዲሁም እንደኔ ከዋርካ በተለያየ ምክንያት ለጠፋችሁ የፈገግታ ቤት ወዳጆች ይሁን. :lol: መጻፉም ሊጠፋብኝ ነው መሰለኝ. :D ውድ ተድላ እቺን ቤት ከተደበቀችበት ስላወጣህ አመሰግናለሁ:: 8) አረ ሁላችንም አብረን አንጥፋ..እነ .ዱዲ ,ፋፊ መላጣ , ፈረደ , ሌሎችም ያለጠቀስኩአችሁ ቀልድም ባይኖር አለን በሉ.. :wink: ለዛሬ አዲስ ቀልድ ባይኖረኝም ያለፉትን ቀልዶች ሳነብ ለትውስታ ያሳቀችኝን መልሼ ላቅርብ..
ሰውየው ሆስፒታል ሄዶ ዶክተሩን "" ዶክተር ሰውነቴን ሁሉ ያመኛል "" አለው :: ዶክተሩም "" እስቲ ምንህ ጋ ነው የሚያምህ "" አለው :: ሰውየም በጣቱ በሙሉ የሰውነት ክፍሎቹን እየነካ የነካው ቦታ በሙሉ እንደሚያመው ነገረው :: ዶክተሩም መረመረውና "" ወንድም ጣትህ ተሰብሯል "" አለው :: :lol:
መልከጻዲቅ
ዋና ኮትኳች
ዋና ኮትኳች
 
Posts: 899
Joined: Wed Aug 08, 2007 11:45 pm

Postby feredewnetu » Thu May 24, 2012 6:06 pm

ስላም ውገኖቼ መልኬ ታዲያስ? አንክዋን ብቅ አልክ ዘንድሮ የሚያስቅ ነገር ጠፋ አኮ ኮመዲያኑ ሁሎ ሞዛዛ ሆኑ ወይስ አኔ ካልኮረክሩኝ አልስቅ ደረጃ ላይ ደረስኩ በተለይ ከአገር ቤት የሚቀርቡት ግርም የሚሎ ሆነዋል ዲያስፖራውም ብሶበታል በቃ የኢትዮጵያ የኮመዲ አምላክ ርቆናል ይታረቀን ነው ሌላ ምን ማረግ ይቻላል:: ይህውላችሁ ሴትየዋ ህጻኑ ልጅዋን ይዛ በታክሲ ተሳፍራ ስትሄዽ ዝናብ አየዘነበ መንገድ ላይ መአት ልጃገረዶች ተደርድረው ያየው ልጅ አንዴ አማዬ አነዚህ ደግሞ በዚ በዝናብ መንገድ ላይ ቆመው ምን አያረጉ ነው ብሎ አናቱን ቢጠይቃት አይ ማሙሽ አነሱ ባሎቻቸውን ከሥራ ሲመለሱ አየጠበቁዋቸው ነው ብላ ስትመልስለት የታክሲው ሹፌር ጣልቃ በመግባት ለምን ትዋሽዋለሽ አውንቱን አትነግሪውም በማለት ማሙሽ አነዚ ያየሀቸው ሴቶች በሙሎ ሴተኛ አዳረዎች ናቸው በገንዘብ ከወንድ ጋራ ይተኛሉ አሁን የሚተኝዋቸውን ወንዶች አየጠበቁ ነው ብሎ ይመልስለታል:: አናትየው በባለ ታክሲው መልስ ተናዳ ልጅዋን ነገር ለማረሳሳት በሞመከር ላይ አያለች ልጁ በመገረም " ለመሆኑ የሚወልድዋቸው ልጆች ምን ይሆናሉ? ብሎ ሲጠይቅ አናትየው 'የታክሲ ሾፌር" ብላው አርፍ::
feredewnetu
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 235
Joined: Thu Sep 24, 2009 6:29 pm

Postby መላጣ » Tue Jul 17, 2012 4:48 pm

እስቲ ይህችን ቤት ሞቅ ደመቅ ደመቅመቅ እናርጋት :o

ባልና ሚስት ሁለቱም በዘጠና እድሜ ክልል ውስጥ የሚገኙ ናቸው ከቤት ወተው ሲሄዱ ሲሄዱ በቃ ምን ልበላችሁ ሲሄዱ ሲሄዱ ሲሄዱ ሲሄዱ okey ሲመለሱ እነግራችኌለሁ:: አሃሃሃ!
መላጣ
ዋና ኮትኳች
ዋና ኮትኳች
 
Posts: 606
Joined: Fri Feb 27, 2004 10:30 am

Postby feredewnetu » Wed Jul 18, 2012 1:15 am

መልኬ የከፈተውን ቤት ሳይዘጋ ስለጠፋ መላጣ አሳስቦህ ብቅ ማለትህ ትልቅ ነገር ነው ስውየው የነካውን አንጃ አኔ ወደ ዋርካ ብቅ የምለው አንዳንዴ ለመሳቅ ነበር አንጂ ሌላ ውስጥ ማኖ አንደነካ አይደለም አንደው ፈገግ አንድትሎ ከትቸር ብርሀኑ ቤት ከማይመቱ ግጥሞች በትንሹ ላካፍላችሁ

አር ተውን በቃ ንግሱን አጽድቀናል
ከዚ ሌላ ደግሞ ምን አለ የቀረ


ልብሴን አጠብኩና ከደጅዋ ባስጣው
ወዳኝ ነው መስለኝ ተራምዳው አለፍች


ሒዳችሁ ንግርዋት መታመሜን ከቶ
አስዋ ገድየላትም ውሽማ ይዛለች


አፋፍ ላይ ቆሜ አንች ሆይ ብላት
ውይ አንቶኔ ብላ ልብዋ ሊፈነዳ
feredewnetu
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 235
Joined: Thu Sep 24, 2009 6:29 pm

Postby recho » Wed Jul 18, 2012 4:21 am

ፈረደ እውነቱ ...

እኔ ምናቃለሁ ጉዳይ እንዳላት
ባልዋ ይጠይቃት ሲፈልግ

እዛ ማዶ ጋራ ምን ይንኮሻኮሻል
ፌደራል አይደለምሁ ምናገባኝ

አንድ ጥርስ አላት
ደግሞ መዋጮ አምጡ ልትል ነው ማስተከያ

መቀጠል ይቻላል ...
"ሰነፍ በልቡ። አምላክ የለም ይላል በሥራቸው ረከሱ ጐስቈሉ በጎ ነገርን የሚሠራ የለም " መዝሙረ ዳዊት ምእራፍ 14:1
recho
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 3171
Joined: Mon Sep 20, 2004 12:28 pm
Location: Earth

Postby መላጣ » Wed Jul 18, 2012 4:38 pm

አንታራም ግጥም እገጥማለሁ ብዬ
የማልችልበትን ቀበጣጠርኩና
ተመልሼ መጣሁ አገገምኩኝና::

ቀደም ብዬ የገለጽኩላችሁ በዘጠናው የድሜ ክልል የሚገኙ ባልና ሚስት ከሄዱበት ተመልሰው ቤት ከገቡ በኌላ ሶፋ ላይ እየተዝናኑ ቲቪ ለማየት ሲከፍቱ ካለ ድምጽ በስተቀር ምንም ስዕል ማየት ስለተሳናቸው ቲቪ ወደሚሰራ ሰራተኛ ጋ በመደወል ፈጠን ብሎ በመምጣት ቲቪውን እንዲሰራላቸው ይጠይቃሉ::

ቲቪ ሠራተኛውም በተባለው መሰረት ቤት እንደደረሰ ሲመለከት ባልና ሚስቱ መነጽራቸውን አርገው ሶፋ ላይ ቀጭ ብለው ያገኛቸዋል:: ወደ ቲቪውም ሲመለከት ተበላሸ ያሉት ያለምንም ስህተት ሰዕሉም ሆነ ድምጹ ጎልቶ ይታያል ይሰማልም:: ትንሽ ካሰበ በኌላ ችግግራቸውን ስለተረዳ የባልየውን መነጽር ለሚስቱ የሚስቲቱን ለባልየው ለውጦ ሲያደርግላቸው ቲቪውን በጠራ መልኩ በማየታቸው "ጎበዝ እንዲህ ነው እውቀት ደግሞ ፍጥነትህ" በማለት የተቸገረበትን ብር አሽገው ሸኙት ይባላል:: ካረጁ አይበጁ የሚለው ተረት ይህ ሳይሆን ይቀር????
መላጣ
ዋና ኮትኳች
ዋና ኮትኳች
 
Posts: 606
Joined: Fri Feb 27, 2004 10:30 am

Postby መላጣ » Tue Jul 24, 2012 6:57 pm

ሱፐርማን አንድ ቅዳሜ ምሽት መዝናናት ስላማረው እንደ ተለመደው ልብሱን ለባብሱ ባየር ላይ እየተወናጨፈ እያለ አርቆ ወደታች ሲመለከት ሱፐር ሴት በቤት ውስጥ በሰፊ አልጋ ላይ በጀርባዋ ተንጋላ እግሮቹውን ወደላይ ስቅላ ይመለከታል:: በዚህን ጊዜ በፍጥነት በተወሰኑ ሴኮንዶች ገብቼ ብወጣ ልታውቅ አትችልም በማለት እንዳሰበው አድርጎ ተመለሶ ይበራል:: በዚህን ወቅት ሱፐር ሴቷ የሆነ ነገር እንደሆነ ስለተረዳች ምንድነው እሱ? ብላ ስትጠይቅ የማይታየው ሰውዬ ""ኧረ እኔ እንጃ ብቻ ቂጤን በጣም ነው ያመመኝ"" ብሏት አረፈው: :lol:
መላጣ
ዋና ኮትኳች
ዋና ኮትኳች
 
Posts: 606
Joined: Fri Feb 27, 2004 10:30 am

Postby ብሩክ ቀን » Tue Jul 24, 2012 10:39 pm

እስኪ እኔም አንድ ልበል

ሰውዬው ባለቤቱን ይጠረጥራት ነበር፡ ከእለታት አንድ ቀን ጥርጣሬውን ለማረጋገጥ ፈለገና መስክ መሄዴ ነው ብሎ ለሚስቱ ነገራት እሷም ዘወትር እንደምታደርገው ለውሽማዋ ባልዋ መስክ እንደሚሄድ ነግራው ቀጠሮ ይይዛሉ። ባልም ከቤት ግቢ ውስጥ ባለው አታክልት ውስጥ ሆኖ ሁኔታን መከታተል ይጀምራል። ጥርጣሬው እውነት ነበር። ምሽት ላይ ውሽሜ ሁለት ጓደኞቹን አስከትሎ እንደለመደው ወደቤት ይገባል። ሁለቱ ጓደኞቹ የሆነ ነገር ከተፈጠረ እረዳትእንድሆት ነበር ያስከተላሸው።
ሆኖም ባል ጥሩ ዝግጅ አድርጎ ስለነበር ሁኔታውን በንቃት እየተከታተለ ነበር ። ውሽሜ ወደውስጥ ገበቶ መላውን ለመመልምል ውስጥ ገባ ሁለቱ ውጭ ቀሩ ሆኖም ባል ሽጉጥ ይዞ ስለነበር መነቀሳቀስ ሳይችሉ በቁጥር ሰር ያውላቸዋል። ውሽሜም ከመያዝ አላመለጠም።

ቀጥሎ የሆነው ነገርአስገራሚ ነበር
ባል ውሽሜንና ሁለት ጓደኞቹን በቁጥጥሩ ስር ካደረገ በኃላ የሚከተውን ጥያቂ አቀረበላቸው።
ግቢው ውስጥ ካለው ፍራፍሬ አንዱን ቆርጠው እንዳመጡ ያዛቸዋል። የመጀመሪያው ሙዝ ይዞ መጣ፤ ሙዙንም በቂጡ እንዳስገባ ባል ያዘዋል እሱም እንደምንም ብሎ ያስገባል።
የሚቀጥለው ብርቱካን ይዞ ይመጣል እሱም በተመሳሳይ መልኩ በቂጡ ብርቱካኑን እንድያ ስገባ ይታዘዛል። ነገር ግን ለማስገባት እየታገለ እያለ ድንንገት በሳቅ ፍርስ ይላል። ባልም በነገሩ ተገርሞ ምን እንደሚያ
ስቀው ይጠይቀዋል። ሰውየውም ሶስተኛው ጓደኛው ዱባ እየቆረጠ እንደሆነ ይነግረዋል። እውነትም በጣም ያስቃል።
እንደት ሊያስገባው ነው :?: አዘነንኩለት ። :lol: :lol:
ብሩክ ቀን
አዲስ
አዲስ
 
Posts: 25
Joined: Mon May 28, 2012 11:13 am

Postby feredewnetu » Wed Jul 25, 2012 5:18 pm

ከሆሊውድ አንድ ቡድን ስለ ቀነኒሳ በቀለ ታሪክ የሚገልጽ አንድ ዶክመንተሪ ፊልም ለመስራት አንድ ቡድን ወደ አርሲ በቆጂ ከተማ የቀነኒሳ ትውልድ ቦታ ይሄዳል ከዚያም ቡድኑ ከየት አንዴት ለመጀመር አንደሚችሉ ጥናት ሲያደርጉ አንደ ህይሌ ገ/ሥላሤ ከት/ቤት ወደ ቤቱ አየሮጠ ሲመላለስ አንዳልሆነ ይረዳሉ ምክንያቱም የነ ቀነኒሳ መኖሪያ ቤት የሚገኘው ከት/ቤቱ ጀርባ ስለሆነ ቅርብ በመሆኑ:: ከዚያ ተገርመው የቀነኒሳን አብሮ አደግ ልጆች ይስበስቡና አንዴት ነው ቀነኒሳ አንዲህ በሩጫ አሪፍ ሊሆን ይቻለው በልጅነቱ ምን የትለየ ነገር ያደርግ ነበር? ብለው ሲጠይቁ ከቀነኒሳ አብሮ አደግ ጉዋደኞች መሀል አንዱ ብድግ ብሎ " ድሮ ልጆች ሆነነ ኩኩሉ(ድብብቆሽ) ስንጫወት ቀነኒሳ ከበቆጂ አስላ ሄዶ ነበር የሚደበቀው ለዚህ ነው አንዲህ አሪፍ ርዋጭ ሆኖ የቀረው ብሎ አርፍ::


በዚህ አጋጣሚ -
ለለንደኑ አሎምፒክ ለአትሌቶቻችን መልካሙን ሁሉ አመኘላሁ!!
feredewnetu
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 235
Joined: Thu Sep 24, 2009 6:29 pm

Postby ቢተወደድ » Thu Jul 26, 2012 11:47 am

አሪፍ ነች ተላ:

እስቲ እያፈላለክ ጨምርባት; የሚገርመው የጠብኩት አይነት ጆክ ነው ያካፈልከን:: እርግጠኛ ነኝ ከዛ ሌላ አይነት ጆክ የምታውቅ አይመስለኝም::

ተድላ ሀይሉ wrote:ሰላም ወገኖቼ :-

እስኪ ይህቺ ቤት አቧራ እንዳይውጣት አንድ ልበል ::

ወያኔ አዲስ አበባ በገባ ሠሞን የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች የተቃውሞ እንቅስቃሴ ያደርጉ ነበር :: ታዲያ በአንደኛው ቀን ከላይ ከስድስት ኪሎ ጀምሮ እስከ አራት ኪሎ ባሉ ግቢዎች የሚማሩ ተማሪዎች ሠልፍ ሲወጡ የወያኔ ወታደር ይመጣና በኃይል ይበትናቸዋል :: የወያኔ ወታደሮች መንገድ ላይ ሲጓዙ የነበሩትንም ሰዎች መታወቂያ እያዩ ሲለዩ ከእነዚያ መካከል ሦሥት ከተለያዩ ግቢዎች የመጡ ተማሪዎች ያጋጥሟቸዋል :: የተመላለሷቸው ቃሎች እንዲህ ነበሩ :-
  የወያኔ ወታደር :- ኣታ ኬት ኖው ?
  ተማሪ 1 :- ከአራት ኪሎ

  የወያኔ ወታደር :- ኣታ ኬት ኖው ?
  ተማሪ 2:- ከአምሥት ኪሎ

  የወያኔ ወታደር:- ኣታ ኬት ኖው?
  ተማሪ 3:- ከFBE
  የወያኔ ወታደር :- ቧ : አጮርባሪ : በኪሎ አትጠራም : ... ተማሪው ትንሽ የሠደፍ ጡጫ ቀምሶ ወደ እሥር ቤት ...
ተድላ
When we do it right No-one remembers,
When we do it wrong No-one forgets.
ቢተወደድ
ዋና ውሃ አጠጪ
ዋና ውሃ አጠጪ
 
Posts: 1965
Joined: Tue Jul 21, 2009 3:21 pm
Location: Dabra Za`Yet

Postby feredewnetu » Sat Jul 28, 2012 11:51 pm

አለሙና ዘነበ በጉርብትና ይኖራሉ አለሙ ዶሮ ግቢው ውስጥ አያረባ ሲሆን የሚኖረው ዘውትር ዶሮዎቹ አንቁላላቸውን ግቢ ውስጥ ነው የሚጥሎት አንድ ቀን በአጋጣሚ አለሙ ወደ ጉዋሮ ብቅ ሲል የሱ ዶሮ ዘነበ ግቢ ውስጥ ገብታ አንቁላል ሜዳው ላይ ስትጥል ና ዘነበ አንቁላሉን ብድግ አርጎ ሲወስድ ያያው አለሙ ተው ተው የኔ ንብረት አኮ ነው አንተ መውስድ አይገባህም ቢለው ዘነበ አይ ይሔ የነ ግቢ ነው አንጂ ያንተ አይደለም ብሎ አልስጥም ቢለው አለሙ ይናደድና አይ ልክ አይደለም ከፍለክ ዳኛ ጋ አንሂድ ይለዋል ከዚያ ዘነበ ዳኛ ጋ መሄድ ስላልፈለግ በል አንቁላሉ የማን አንደሆነ ለመፍረድ ዳኛ ጋ መሄዽ አያስፈልግነም በርግጫ አንድ ግዜ ቆለጥ ላይ አንመታታና ከሁለታችን ለመነሳት ብዞ ጊዜ የውስደበት ተሽናፊ ይሆናል ቢለው አለሙ አኔ መጀመሪያ ነው መሄዽ የምፈልገው ብሎ የወታደር ጫማ ያደርግና ተንድርድሮ ዘነበን ቆለጡን ይለዋል ከዚያ ዘነበ ከግማሽ ስአት በሁዋላ ይነሳና ከፊት ለፊት ብረት ያለው ጫማውን አርጎ ለመማታት ሲዘጋጅ አለሙ አይ ገደየለም አንቁላሉ ውስድ ብሎት አርፍ::
feredewnetu
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 235
Joined: Thu Sep 24, 2009 6:29 pm

Postby መላጣ » Tue Jul 31, 2012 7:44 pm

አንድ አነስ ያለ ልጅ የሚኖረው ቤት ካባት ከናቱ ጋር ብቻ ሳይሆን ካያቶቹም ጭምር ነው:: ልጁ ምሽት ላይ ሊተኛ ሲል አዘውትሮ አባትየው ልጁ ክፍል ውስጥ የሚያጉረመርም ነገር ያዳምጣል:: አንድ ቀን ምን ይሆን ብሎ ቀስ ብሎ ወደ ልጁ ክፍል በመሄድ ተደብቆ ሲሰማ ልጁ ከመተኛቱ በፊት "ፈጣሪ አምላኬ ሆይ! እናቴን ጠብቅልኝ አባቴንም ሴቷን አያቴንም ጠብቅልኝ ግን ወንዱን አያቴን አሰናብትልኝ" አሜን ብሎ እንደሚተኛ ይገባውና በልጁ ፀሎት በጣም ይገረማል:: ጠዋት ቤተሰብ ከንቅልፍ ሲነሳ ወንድ አያት ሞተው ይገኛሉ ጉድ ይባላል ይለቀሳል ቀብርም ይካሄዳል::

ይህ በሆነ በ 15 ቀን ልጁ እንደተለመደው "" ፈጣሪ አምላኬ ሆይ! እናቴን ጠብቅልኝ አባቴንም ጠብቅልኝ ግን ሴቷን አያቴን ሸኝልኝ"" የሚለውን ፀሎት አባት ሲሰማ መደናገጥና መረበሽ ያመጣል ሁኔታውን እሱ እንደሰማ ለማንም ትንፍሽ ሳይል ይተኛል:: ጠዋት ሲነጋ ሴት አያት ሞተው ይገኛሉ ይለቀሳል ቀብር ይካሄዳል በቤታቸው ኃዘን ብቻ ሳይሆን ባባት ላይ ትልቅ መደናገጥ ይመጣል::

አያት በተሸኙ በሳምንቱ እንደተለመደው ልጁ ከመተኛቱ በፊት ""የለመንኩህን የማትነሳኝ አምላኬ ሆይ! እናቴን ጠብቅልኝ ግን አባቴ ቀጣፊ አመንዝራ ጫት ቃሚ ነውና ደብረህ ደባብረህ አሰናብተህ ሲዖል ክተትልኝ"" የሚለውን ቃል ሲሰማ አባት በፍርኃት እንቅልፍ የምትባል ነገር ሳያይ ካሁን አሁን ሟች ነኝ በማለት እየሰጋ በጠዋት ወደስራው በመሄድ እሱነቱን ሳያምን በጭንቅ ተጠምዶ በቡካት ሞትን እያሸተተ መምሸቱ አይቀር ስራውን እንደጨረሰ አርፍዶ ቤት ይደርሳል::

ባልም ቤት እንደደረሰ ለባለቤቱ ዛሬ የኔ ቀን አይደለም በኃሳብ ጭንቀት ውስጥ ገብቼ እንዲሁ ሳይመቸኝ ነው የዋልኩት ለዚህም ነው አርፍጄ የመጣሁት ብሎ ሲነግራት ባለቤት በጣም በመቆጣት ስጨነቅ ሳይመቼኝ ትላለህ እኔ ምን እንዳጋጤመኝ ሳታውቅ "" የዚህ መንደር ፖስታ አመላላሽ ሰውዬ በሬ ላይ ድፍት ብሎ ሲቀር"" በማለት ደረቷን ነካ ነካ ስታደርግ ""አይ! አዋቂው የንጀራ ልጄ መጪው ፀሎትህ ለናትህ"" ለካ ጉዱ ከሷ ነው ብሎ እንደወጣ ቀረ ይባላል::
መላጣ
ዋና ኮትኳች
ዋና ኮትኳች
 
Posts: 606
Joined: Fri Feb 27, 2004 10:30 am

PreviousNext

Return to Warka Culture and Literature - ዋርካ ባህልና ሥነ ጽሑፍ

Who is online

Users browsing this forum: ረሀቦት and 4 guests