የአማርኛ ስነ ጽሁፍ ስብስቦች በድረ ገጽ

Topics related to cultures, arts, languages, arts such as humor, music, traditional literary genres of poems, ግጥም ፣ ቅኔ ፣ ተረትና ምሳሌ)

Postby Gosa » Thu Aug 02, 2012 5:16 pm

ወዳጄ እንሰት!!
ትንሽ ዱብ ዱብ ብዬ ማስታወቂያ ሚኒስቴር ዉስጥ የሆነ ስራ አገኘሁ፤ በነእስከዳር በኩል። የስራዬን መጠሪያ በወጉ አላውቀውም፤ ግን ያው ወሬ አቀባይነት ነው። ይሄ ደሞ የተመረቅኩበት ነው። ይቺ ሀገር እንደዉም ለኔ አይነቱ ነው ሰፊ የስራ መስክ ያላት። ሰልችቶኝ ተውኩት በኋላ፤ ደሞዙም አይረባም።


ጽሁፉን ወደ ስራ ሊሄድ ጥቂት ደቂቃ ሲቀረኝ ነው ያየሁት:: ሳልጨርስ መውጣት አቅቶኝ ትንሽ ደቂቃ አስረፈድከኝ:: በጣም ደስ የሚል ታሪክ ነው:: ታንክስ ብሮ!!!
We must learn to live together as brothers or perish together as fools.
Martin Luther King, Jr.
Gosa
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 377
Joined: Mon Nov 21, 2011 2:43 pm
Location: ethiopia

Postby እንሰት » Thu Aug 02, 2012 8:52 pm

ወንድም ጎሳ
ለምስጋናው እጅ ነስቻለሁ:: የኔ ድርሻ እንኩዋን እንደነ ጎሳ ያሉ ጣፊዎችን ስራ ማስተዋወቅ ነው::
ዋናው ምስጋና ለደራሲዎቹ ነው::
እንሰት
ውሃ አጠጪ
ውሃ አጠጪ
 
Posts: 1213
Joined: Sun Jan 30, 2005 1:14 am
Location: united states

Postby እንሰት » Mon Sep 10, 2012 7:37 pm

እንኩዋን ለዘመነ ማቴዎስ አደረሳችሁ:: ዛሬ አመጣጤ አይጋ ፎረም የሙሉጌታ ጸጋዬን የባለቃኔው ምህላ የግጥም ስብስቦች እነሆ ስላለን ማያያዣውን ለማመላከት ነው::

ሙሉጌታ ፈርጀ ብዙ ባለሙያ ነበር:: አሙዋሙዋቱ እንዴት እንደሆነ አላውቅም የምታውቁ ታሪክ ስለሆነ ብታሳውቁን ደስ ይለኛል::

http://www.aigaforum.com/articles/Yebaleqine-Mehela.pdf
እንሰት
ውሃ አጠጪ
ውሃ አጠጪ
 
Posts: 1213
Joined: Sun Jan 30, 2005 1:14 am
Location: united states

ግሎባል ቮይሰስ

Postby እንሰት » Thu Sep 13, 2012 5:15 am

እንደምን ከረማችሁ
ግሎባል ቮይሰስ ይሰኛል ድረ ገጹ:: አንድ ስለ ቻይና አእና አፍሪካ የጻፈውን አገኘሁና ልጨኝነቱ ስለማረከኝ ላስትዋወቃችሁ አመጣሁት::

ቻይና በአፍሪካ፤ እውነተኛው ታሪክ
ትርጉሙ የተለጠፈው 10 መስከረም 2012 14:01 GMT · ዋናውን ጽሁፍ መመልከቻ [en]
ጸሐፊ
Ndesanjo Macha
ተርጓሚ
befeqe
አገራት China, Kenya, Zambia
አርዕስት ዕድገት, ዓለም አቀፍ ግንኙነቶች, Politics, ምጣኔ ሃብት እና ቢዝነስ, የዜጎች መገናኛ ብዙሐን
ቋንቋዎች English
ይህ ጽሑፍ የሚጎኝበት ሌላ ቦታ:
Français · La véritable histoire de la Chine en Afrique
English · China in Africa: The Real Story


የሕትመት ቅጂ
ሒቢስከስ የቻይና እና አፍሪካ ግንኙነትን በተመለከተ ነገረ ውይይቶችን በመስመር ላይ ለማስተጋባት የተፈጠረ ‘የዓለም ድምጾች’ (Global Voices) ፕሮጀክት ነው፡፡ በተለይም ደግሞ በሁለቱም ክልሎች ያሉ ጦማሪዎች እና ከዚያም ውጪ ያሉትን የጋራ ውይይትን ለማበረታታት ይሠራል፡፡

የቻይና ትኩረት በአፍሪካ ላይ በከፍተኛ ፍጥነት የጨመረው ባለፉት ጥቂት ዓመታት ሲሆን አሁን አገሪቱን የአፍሪካ ትልቋ የንግድ ሸሪክ አድርጓታል፡፡ “በቻይና እና አፍሪካ መካከል የተደረገው የንግድ ልውውጥ ባለፉት 5 የ2012 ወሮች ውስጥ የዓመት ለዓመት ንፅፅሩ በ22 በመቶ ሲያድግ መጠኑ 80.5 ቢሊዮን ዶላር ደርሷል ” በማለት የቻይና የንግድ ሚኒስቴርን ጠቅሶ ማይክ ኪንግ ጽፏል፡፡

የዚህ ፕሮጀክት አካል እንደመሆኑ፣ በቻይና-አፍሪካ ግንኙነት ላይ ያተኮሩ ጦማሮችን እና የማሕበራዊ መገናኛ ብዙሐን ትኩረቶችን በመደበኛነት እንዘግባለን፡፡ ዛሬም፣ ቻይና በአፍሪካ፤ እውነተኛው ታሪክ የሚለውን በዲቦራ ብሮቲጋም (የThe Dragon's Gift: The Real Story of China in Africa ድራሲ) የተጻፈውን ጦማር እናስነብባችኋለን፡፡
http://am.globalvoicesonline.org/2012/09/65

ስለ እኛ
የተሻሻለው 9 መስከረም 2012 8:18 GMT
‘የዓለም ድምጾች’ (Global Voices) በዓለም ዙሪያ ለእናንተ ሪፖርቶችን እና የዜጎችን መገናኛ ብዙሐን ከየስፍራው ለማድረስ በአንድነት የሚሰሩ፣ ትኩረቱን በተለይ በመደበኛው መገናኛ ብዙሐን ተደማጭነት ባጡ ድምጾች ላይ ያደረገ ከ500 በላይ ጦማሪዎችን እና ተርጓሚዎችን የያዘ ማኅበራዊ ስብስብ ነው፡፡

‘የዓለም ድምጾች’ የመስመር ላይ ውይይቶችን ማጠቃለል፣ ግልጽ ማድረግ እና ማስጮኽ ይፈልጋል - ሌሎች መገናኛ ብዙሐን ችላ የሚሏቸው ሰዎችና ቦታዎች ላይ በማተኮር፡፡ በየትኛውም ቦታ ያሉ ድምጾች እንዲደመጡ አማራጮችን፣ ተቋማትን እና ግንኙነታቸውን ለማጠናከር እንሰራለን፡፡

እልፍ ሰዎች እየጦመሩ፣ ጡመራውን እያስተጋቡ እና ፎቶና ቪዲዮዎችን ጨምሮ ሌሎችንም መረጃዎች በዓለም ዙሪያ በመበተን ላይ ይገኛሉ፡፡ ነገር ግን የት እንደሚገኙ ለማያውቅ ሰው የተከበረውን እና ትክክለኛውን ድምጽ ወይም መረጃ የት ማግኘት አስቸጋሪ ነው፡፡ የዓለም አቀፉ በጎ ፈቃደኞች ጸሐፊ ቡድናችን እና የትርፍ ሰዓት አርታኢዎቻችን ‘የዓለም ድምጾች’ ላይ በሚያሰፍሯቸው ጉዳዮች ዙሪያ ያሉ የጡመራ መድረኮች ንቁ ተሳታፊ ናቸው፡፡

‘የዓለም ድምጾች’ በኔዘርላንድ Stichting Global Voices የተባለ ትርፋማ ያልሆነ ድርጅት አባል ነው፡፡ ቢሮ የለንም፣ ነገር ግን ምናባዊ የበይነመረብ ማኅበረሰብ ፈጥረን በብዙ የሰዓት ዞኖች ልዩነት ውስጥ አብረን እየሰራን ነው፤ በአካል የምንገናኘው ሁኔታዎች ሲፈቅዱ ብቻ ነው (ብዙ ጊዜ በስብሰባ)፡፡ የምንተማመነው ወጪያችንን ለመሸፈን በሚሰጡን ድጎማዎች፣ ስፖንሰር አድራጊዎ፣ አርትኦት ኮሚሽኖች እና ልገሳዎች ነው፡፡

ፕሮጀክቶቻችን

‘የዓለም ድምጾች’ በበጎ ፈቃደኛ ተርጓሚዎች ከ30 በላይ በሚሆኑ የዓለም ቋንቋዎች ተተርጉመዋል፡፡ እነዚህ ተርጓሚዎች ሊንጉዋ የሚባል ፕሮጀክት መስርተዋል፡፡ በተጨማሪም፣ ‘የዓለም ድምጾች’ በመስመር ላይ የሚያሰሙት ድምጽ ለሚታፈንባቸው ሕዝቦች የለውጥ ወትዋች(Advocacy) ድረአምባም አለው፡፡ በማንሰራራት ላይ ያሉ ድምጾች (Rising Voices) የምንለውም፣ በተለይ በታዳጊ አገራት ላይ ያተኮረ፣ አፈናና ተጽዕኖ እየደረሰባቸው ያሉ ዜጎች ድምጻቸው እንዲሰማ የምንሰራበት ፕሮጀክትም አለን፡፡
http://am.globalvoicesonline.org/about
እንሰት
ውሃ አጠጪ
ውሃ አጠጪ
 
Posts: 1213
Joined: Sun Jan 30, 2005 1:14 am
Location: united states

ሴትና ፈጣሪ ከጲላጦስ 2001

Postby እንሰት » Mon Sep 17, 2012 4:45 am

ሴትና ፈጣሪ ይሰኛል ርእሱ
ደራሲው ጲላጦስ (ሃይለ ጊዮርጊስ ማሞ) ሲሆን የታተመው በ2001 ነው።
እኔ አንብቤው ወደድኩት። ፈልጋችሁ አንብቡት ልዩ የግጥም መድበል ነው።
እጅህ ከምን ለምትሉ።

1.ሃጢአት
አዘንሽብኝ አሉ ፊቴ ስለዞረ
ታለቅሻለሽ አሉ አይኔን <<ስላወረ>>
ምን ላድርግ ብለሽ ነው
ሲያስፈራሩኝ ዋሉ
<<እንኩዋን የተመኘ ያያት አመንዝሮዋል>> ብሎ ሄዶዋል አሉ።

2. ተመሳስሎ
ሴትን ሲያበጃጃት አምላክ ተቀምጦ
የልቡዋን አሰራር ከዝሆን አብልጦ
እንደነበር አወቅሁ የቀረጸው ለእሱዋ
ሴትም እንደዝሆን አቁሳይዋን ባትረሳ።

3.ሴትና ፈጣሪ
ከፈጣሪህ በላይ ውደደኝ አለችኝ
እሱን በመፈለግ ስደክም እያየችኝ

እኔኑ አምልክ አለኝ እሱም ተደብቆ
ህይወቴ እንደጫማ በእሱዋ መንገድ አልቆ።

እናም ግራ ገባት ነፍሴ መሃል ሆና
አምላኬ ከሴት ጋር እየተቀናና።

እኔ አጂኢብ ብያለሁ። የምትሉትን በሉ።
እንሰት
ውሃ አጠጪ
ውሃ አጠጪ
 
Posts: 1213
Joined: Sun Jan 30, 2005 1:14 am
Location: united states

Postby ተድላ ሀይሉ » Mon Dec 10, 2012 2:13 am

ሰላም ለኢትዮጵያ ሥነ-ጽሑፍ ታዳሚዎች :-

ሰላም ለቤቱ ባለቤት ወንድሜ 'እንሰት' :-

ይህንን ድረ-ገፅ አንዳንድ መረጃዎችን ሣፈላልግ አገኘሁትና ቦታው እዚህ ይሆናል ብዬ አመጣሁት::

ምንጭ:- EthioReaders

ተድላ
የወያኔ ሕገ -አራዊት አንቀፅ 39 ኢትዮጵያን የመበታተኛ ፈንጂ ነው !
ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር !!!
ተድላ ሀይሉ ዘብሔረ -ኢትዮጵያ ::
ተድላ ሀይሉ
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 4903
Joined: Fri Mar 17, 2006 2:45 pm
Location: ኢትዮጵያ

Postby እንሰት » Mon Dec 10, 2012 6:16 am

thank you ተድላ
በ ኤክስፕሎረር ሊንኩ አልከፍት አለኝ እስኪ መላ ፈልግ::

ተድላ ሀይሉ wrote:ሰላም ለኢትዮጵያ ሥነ-ጽሑፍ ታዳሚዎች :-

ሰላም ለቤቱ ባለቤት ወንድሜ 'እንሰት' :-

ይህንን ድረ-ገፅ አንዳንድ መረጃዎችን ሣፈላልግ አገኘሁትና ቦታው እዚህ ይሆናል ብዬ አመጣሁት::

ምንጭ:- EthioReaders

ተድላ
እንሰት
ውሃ አጠጪ
ውሃ አጠጪ
 
Posts: 1213
Joined: Sun Jan 30, 2005 1:14 am
Location: united states

Postby ተድላ ሀይሉ » Mon Dec 10, 2012 5:48 pm

እንሰት wrote:thank you ተድላ
በ ኤክስፕሎረር ሊንኩ አልከፍት አለኝ እስኪ መላ ፈልግ::

ተድላ ሀይሉ wrote:ሰላም ለኢትዮጵያ ሥነ-ጽሑፍ ታዳሚዎች :-

ሰላም ለቤቱ ባለቤት ወንድሜ 'እንሰት' :-

ይህንን ድረ-ገፅ አንዳንድ መረጃዎችን ሣፈላልግ አገኘሁትና ቦታው እዚህ ይሆናል ብዬ አመጣሁት::

ምንጭ:- EthioReaders

ተድላ

ሰላም ወንድሜ እንሰት:-

በ'Mozilla FireFox browser' ብትጠቀም ይህንን ድረ-ገፅ በአማርኛ ቋንቋ ማንበብ ትችላለህ::

ተድላ
የወያኔ ሕገ -አራዊት አንቀፅ 39 ኢትዮጵያን የመበታተኛ ፈንጂ ነው !
ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር !!!
ተድላ ሀይሉ ዘብሔረ -ኢትዮጵያ ::
ተድላ ሀይሉ
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 4903
Joined: Fri Mar 17, 2006 2:45 pm
Location: ኢትዮጵያ

Postby እንሰት » Mon Dec 10, 2012 6:39 pm

ግሩም ድረ ገጽ ነው::
በድጋሚ ምስጋና

ተድላ ሀይሉ wrote:
እንሰት wrote:thank you ተድላ
በ ኤክስፕሎረር ሊንኩ አልከፍት አለኝ እስኪ መላ ፈልግ::

ተድላ ሀይሉ wrote:ሰላም ለኢትዮጵያ ሥነ-ጽሑፍ ታዳሚዎች :-

ሰላም ለቤቱ ባለቤት ወንድሜ 'እንሰት' :-

ይህንን ድረ-ገፅ አንዳንድ መረጃዎችን ሣፈላልግ አገኘሁትና ቦታው እዚህ ይሆናል ብዬ አመጣሁት::

ምንጭ:- EthioReaders

ተድላ

ሰላም ወንድሜ እንሰት:-

በ'Mozilla FireFox browser' ብትጠቀም ይህንን ድረ-ገፅ በአማርኛ ቋንቋ ማንበብ ትችላለህ::

ተድላ
እንሰት
ውሃ አጠጪ
ውሃ አጠጪ
 
Posts: 1213
Joined: Sun Jan 30, 2005 1:14 am
Location: united states

የኢትዮጵያ ሳይንስ አካዳሚ

Postby እንሰት » Thu Dec 27, 2012 6:44 am

የኢትዮጵያ ሳይንስ አካዳሚ
http://www.eas-et.org/
contact address.

EAS Secretariat
Around Gulele branch of Commercial Bank of Ethiopia
The old historic building of the late Blaten Geta Hiruy Wolde Selassie
PO Box 32228
Addis Ababa, Ethiopia

E-mail:
eassecretariat@gmail.com or
eas@eas-et.org

Phone:
(+251) 11 2595745
(+251) 11 2595750

EAS in Brief
The Ethiopian Academy of Sciences is an autonomous, non-profit, non-governmental organization established in March 2010 by a group of prominent scholars who wish to promote the Sciences to flourish and bring about development, prosperity and improved health services for the people of Ethiopia. The Academy aims to advance the development of all the sciences, including the natural sciences, mathematics, health sciences, agricultural sciences, engineering, social sciences and humanities, fine arts and letters. It plans to do this by providing evidence base and non-partial advise to the Ethiopian Government on matters related to science, technology and innovation, organizing conferences and workshops on significant national issues, awarding prizes in recognition of excellence and publishing reports, journals as well as other periodicals and books. The Academy closely works with the relevant government ministries, universities and other organizations in its effort to achieve its goals.


Membership to the Academy falls into four categories, namely; Founding Fellows, Fellows, Associate Fellows and Honorary Fellows. The current Academy membership consists of 49 Founding Fellows who were selected based on a set of selection criteria that include recognition of their academic achievements, international stature and contributions at the national and international levels, including publications. In addition, their contribution for the growth of knowledge in Ethiopia has been assessed. Fellows, as well as Associate and Honorary Fellows are elected on an annual basis.


All members serve the Academy on voluntary basis through working groups and other standing committees to be established as deemed necessary. Two Standing Committees for Finance and Public relations have already been established.


The major objectives of the academy include:
To advise the Government of Ethiopia on issues pertaining to the quality and relevance of the sciences, in particular on issues related to science education in Ethiopia;
To promote the advancement of basic and applied sciences and to enhance innovative technologies;
To promote, support and recognize excellence in scientific research achieved by Ethiopian scientists;
To promote contact among Ethiopian scientists, and between them and the world scientific community;
To enable women and other underprivileged and marginalized groups to participate in and benefit from scientific works and discoveries.
EAS has adopted a strategic plan (2011-2015) that forms the basis for its programs and activities for the coming five years. The core programs that EAS aims to achieve are the following:

Increasing and strengthening the visibility and relevance of EAS;
Providing consensus building platforms on critical national issues;
Promoting science, technology and innovation;
Recognizing excellence; and
Building institutional capacity and sustainability of EAS.
Implementation of the strategic plan requires inputs from all fields of sciences. EAS has, therefore, established five discipline based working groups, also referred to as Sectoral Working Groups, in the fields of Agriculture; Engineering and Technology; Health; Natural Sciences; and Social Sciences/ Humanities. The tasks of the working groups include:

Identification of critical national issues for consensus building amongst all stakeholders;
Identification of potential Fellows, Associate Fellows and Honorary Fellows for induction into the Academy as per regulations set in the Statute of the Academy;
Formulation of criteria for recognizing excellence in science;
Identification of potential areas of interest and subsequent collaboration with other academies in the region and beyond;
Identification of specific strategies for the promotion of science, technology and innovation.
እንሰት
ውሃ አጠጪ
ውሃ አጠጪ
 
Posts: 1213
Joined: Sun Jan 30, 2005 1:14 am
Location: united states

sharing

Postby ዋኖስ » Thu Dec 27, 2012 3:42 pm

Interesting!

Thank you for sharing!

damot

ዋኖስ
ዋና ውሃ አጠጪ
ዋና ውሃ አጠጪ
 
Posts: 1552
Joined: Tue Nov 16, 2004 2:39 pm
Location: Mars

ስብሀት ሲገመገም

Postby እንሰት » Thu Dec 27, 2012 3:58 pm

አሪፍ ድረ ገጽ
ሉላዊ ሴራ - የተሸሸጉ ታሪኮች
ሰው ዓለሙን ሁሉ ቢያተርፍ ነፍሱንም ቢያጎድል ምን ይጠቅመዋል ? ማቴ. 16፣26 (የሚስጥር ማህበራትን ሴራ የሚያጋልጥ በአማርኛ በአይነቱ የመጀመርያው ብሎግ the first blog in Amharic fully dedicated to exposing the secrete societies conspiracy.)ስብሃት፡ ሃዘንተኛው ባለቅኔ


ከዚች ድረ ገጽ ደግሞ ስለ ስብሀት እንዲህ ተብሎዋል::

በግደይ ገብረኪዳን

ይህ ለማከብረው ጓደኛዬና የምርምር አጋሬ ተክሉ አስኳሉ ፌስ ቡክ ላይ ስለ ስብሃት ገ/እግዚአብሔር በፃፈው ፅሁፍ ላይ የሰጠሁት አስተያየት ሲሆን እራሱን የቻለ መጣጥፍም ሊሆን ይቸላል በማለት ልለጥፈው ወስኛለው፡፡
5 March at 08:17
source: http://antiglobalconspiracy.blogspot.ca ... .html#more
ተክሉ የተሰማኝን እንድነግርህ እንደምትፈልግ በመገንዘብ ስሜቴን ላጋራህ እሻለው፡፡ ስብሃት ክፉ ነገር ነው የሰበከው ላልከው አልቃወምህም፡፡ ሆኖም ግን በዚህ አስመሳይና አድር ባይ ህብረተሰብ ባጥለቀለቀው አገር ውስጥ አቋም ይዞ የተገኘ በመሆኑ እጅግ ሊደነቅ የሚገባው ሰው መሆኑ ግን ሊረሳ አይገባውም፡፡ በከንቱ አድናቂው ነን የሚሉት የሰዶም መልእክተኛ መሆኑን ቢያጤኑ ኖሮ ቀልባቸው እንደሚገፈፍ እርግጠኛ ነኝ፡፡

ሆኖም ግን የስብሃት ስህተት እኮ መርዝ ብቻ አልነበረም፡- በስህተቱ ውስጥ ትክክለኛነት ነበረበት፤ ሴሰኝነትን የመረጠው ራስ ወዳድ መሰሪ ሁኖ ሳይሆን አቅሙ የፈቀደለት እውቀት እሱ ስለሆነበት ነው፡፡ እሱ ይቅርና በመፅሃፍ ቅዱስ ውስጥም እኮ ዝሙት የሰሩ ባእድ ያመለኩ የሰው የተመኙ ለስጋዊ ፈተና የወደቁ ወዘተ. ፃድቃናት የሉም እንዴ፡፡
ደሞም ስብሃትን እኮ እንደ ሃጥያት መጀመርያ አደረከው፡፡ ከሱ በፊት ይደረጉ የነበሩ፣ ባካባቢው ያያቸውን ክስተቶች ነው የፃፈው፡፡ ስብሃት ማጨስ የጀመረው በ40 ዓመቱ መሆኑን ሰምተሃል፡፡ ስብሃት የሰራው ስህተት ከራስ ወዳድነት ሳይሆን ከየዋህነት ነው፡፡ ለዚህም አይደል መፅሃፍ ቅዱስ ብዙ ግዜ በበጎ ምግባራቸው የመፃደቁትን የሚገስፀው፡፡ በስብሃት ሃጥያት ውስጥ ፅድቅ አለበት፡፡
ሁሉም ሰው እኮ ገበሬ፣ ሁሉም አዝማሪ፣ ሁሉም ባርያ፣ ሁሉም ጌታ መሆን አይችልም፡- እነ ዳኛቸውም እነ ስብሃትም በየግላቸው ነው መገምገም ያለባቸው እንጂ ያ ለምን እንዲህ አልሆነም አይባልም፡፡ ለምን ነብር ሳር አይበላም፣ ለምን በግ ስጋ አይበላም የሚሉትን ያህል ስህተት ይሆናል፡፡
ስብሃት ደሞ ከዶስቶየቭስኪ ጋር የሚያመሳስለው እኮ እራሱም እንደተናገረው፡- አንብቦት ከመልካም ገፀ-ባህርያቶቹ፣ ፍትወት ያናወዛቸው ስላሳመኑት ነው፡- ስብሃት እነ ዲሚትሪን ነው የመረጠው…፡፡
ደሞስ እንዴት ነው ስብሃትን ከተራ ፀሃፍያን ሊነፃፀር የሚችለው እነሱ እኮ የዝሙት ጀብዳቸውን መለፈፍ የወደዱ ቁሳውያን ራስ ወዳዶች ናቸው፣ ስብሃት እኮ ስለሰው ተፈጥሮ ባህርያት መመርመር የፈለገ የምሩ ፀሃፊ ነው፡፡
በውነቱ አንዳንድ እንደነ በውቀቱ ስዩም ያሉ ፀሃፍያን ሆን ብለው ፍትወት የመረጡ ራስ ወዳዶች ናቸው፣ በኢቲቪና በየዘፈን ክሊፑ የሚታዩት ግልፍጥ ሴቶች እኮ በነጋታው ነጠላ ለብሰው ቤተ ክርስቲያን ሊሳለሙ የሚሄዱ፤ ጴንጤ ከሆኑ ደሞ ከሳምንቱ መጨረሻ ቸርች ሊደንሱ የሚሄዱ እንጭጮች ናቸው፡፡ እንዲህ ባይሆኑም ታምሪያለሽ መባልና ብር መጥባት አመላቸው ከሆኑ ጋር ማነፃፀሩ ተገቢ አይደለም፡፡
ስብሃት ባለቅኔ ነበር፡፡ በርግጥ እያረጀ ሲመጣ እየቀለለ ሳይመጣ አልቀረም፡፡ አንበሳ እንኳ ሲያረጅ የዝንብ መጫወቻ ይሆናል አይደል የሚባለው፡፡ ግን መንፈሱ ቀና ነበረች፡፡ አንድ የኬርኬጋርድን ጥቅስ ላስታውስህ፡
“ባለቅኔ ምንድን ነው? ሃዘንተኛ የሆነ ሰው በልቡ ጥልቅ ስቃይ አምቆ የያዘ በከናፍርቱ ግን ቃላት ሲያልፉ ጥኡም ዘፈንን ይመስላሉ፡፡” ይላል፡፡ ይህን አይነት ሰው ከአንዲት ከርታታ ጋር ማነፃፀር አይገባም፡፡
ስብሃት በውስጡ ጥልቅ ስቃይ የሸሸገ ባለቅኔ ይመስለኛል፡፡ እናም ከዚህ ቀና መንፈሱ አንፃር እንገምግመው፡፡ እንጂ ወጣቱን አበላሸ ብለን አንፍረድበት፡፡ ወጣቱም እኮ የመምረጥ መብት አለው፡፡ ቀናነት የሌለው ወጣት ከስብሃት መጥፎ ነገር ብቻ ይታየዋል፡፡ በዚሁ ከቀጠልኩ መቋጫ አይኖረውም፣ ሰውየውን ግን በዚህ መልኩ እንረዳው፡፡


ተክሉ ዛሬ ኮምፒውተር በሚያስፈልገኝ ቀን አጥቼ ዋልኩኝ ሆኖም ግን እንደምንም የምለውን ለማለት ተሟሙቻለው፡፡ እርግጥ ነው ሰዎች በተለያየ መንገድ ተፅእኖ ይፈጥራሉ፣ የስብሃት ጎጂ ተፅእኖንም አልካድኩም፡፡ ማለት የፈለኩት ግንበዚህ ጎጂ ተፅእኖ በመፍጠሩ ምክንያት እንደ ስብሃት አይነቱ የስነ ፅሁፍሰው ሊወገዝ አይገባውም ምክንያቱም ስብሃት እንደ ኪንሰይ ሳይንቲስት ነኝ እንደማርክስ ...ፈላስፋ ነኝ (ሕብረተሰብ ቀራጭ) አልወጣውም፡፡ እሱ ባለ ቀኔ ነው፣ የሰው ባህርያት የሰው እጣፈንታ እና ተፈጥሮ ነው የሚመስጡት፡፡ የቅኔ መንፈስ ደሞ የምትረካው የግድ የተሰማውን ሲተነፍስ ነው፡፡ እንጂ እሱ ተከተሉኝ እኔ ነኝ ልክ አላለም፡፡ ሂወትን እንዲህ አየኋት፣ ገረመቺኝ ነው ያለው፡፡ ሌላ ሰው ማጥፋት ሲያምረው በሱ ማሳበብ ያሳብባል፡፡
እና ይህ የነብሱን ስቃይ ሲተነፍስ ወህኒ ስለማያስወርድ አቋም አልለውም ማለት አንችልም፡፡ መንግስት ብቻ አይደለም የሚፈራው እኮ፣ እሱ እማ ማንም ሂወት የመረረው ከመንግስት ጋር ሊሳፈጥ ይችላል፣ ስብሃት እኮ ከዘላለማዊው ሃያል ጋር ነው ሲሳፈጥ የኖረው፡፡ (መደገፌ ሳይሆንምን ያህል ጥንካሬ እንደሚጠይቅ ለማስታወስ ነው፡፡)
ዝሙት ፈፀመ ብለህ አትውቀሰው እኮ አላልኩም፡፡ ግን ያየውን ለምን ይፅፋል ማለት አይቻልም ነው ያልኩት፣ ባለ ቅኔ ነውና፡፡
እርግጥ ነው በሂወቱ መጨረሻ ሳይጃጃል አልቀረም፣ ሆኖም ግን እኔ የተከራከርኩለት ይህ ደራሲ ህሊና ያለው እና ለደረሰባቸው እውነቶች የቆመ ነው፡፡ ግዝያዊ ጥቅም መርጦ ሂወቱን በከንቱ በሹፈት ማሳለፍ የፈለገ ተራ ሰው አይደለም ለማለት ብዬ ነው፡፡
ሰቃይ በውስጡ ስለመያዙ መጀመርያውኑ ባለቅኔ የመሆኑ ሚስጥር ነው፡፡
በመጨረሻም ደግሜ የማስታውስህ ስብሃት አይነኬ ነው አትውቀሰው ለማለት ፈልጌ ሳይሆን እሱን የምናይበት መነፅር ይለያል ነው፡፡ የዘነጋሁት ካለ እጨምራለው ዛሬ ኮምፒትር ጉድ አርጎኛል፡፡
....
እንሰት
ውሃ አጠጪ
ውሃ አጠጪ
 
Posts: 1213
Joined: Sun Jan 30, 2005 1:14 am
Location: united states

Re: sharing

Postby እንሰት » Thu Dec 27, 2012 5:23 pm

ዋኖስ wrote:Interesting!

Thank you for sharing!

damotYou welcome Damot!
እንሰት
ውሃ አጠጪ
ውሃ አጠጪ
 
Posts: 1213
Joined: Sun Jan 30, 2005 1:14 am
Location: united states

"ሲጨልም" በእንዳለጌታ ከበደ

Postby እንሰት » Tue Aug 27, 2013 4:19 pm

"ሲጨልም" እንዳለጌታ ከበደ

ወደ ሰባዎቹ የሚጠጉ የሚመስሉ አንድ አረጋዊ “ልጄ” አሉት አስተናጋጁን፡፡ “የወሰድኩትን መድኃኒት ይዤብህ መጣሁ፣ እባክህን የሰጠኸኝን ወስደህ . . .”
አላስጨርሳቸውም፡፡ ግርግዳው ላይ ወደተለጠፈው ጽሑፍ አመለከታቸው፡፡ ‘የተሸጠ መድኃኒት አይመለስም አረጋዊው’ በለሰለሱ ቃላት መማፀን ያዙ፡፡
“ሰውዬ ዞር በል! ስራ ልስራበት! ለእንቶ ፈንቶ ጉዳይ የማባክነው ጊዜ የለኝም. . .” አለ ቁጣው እየተወለደ፡፡
“ዛሬ በዚህ ሰውዬ እንድጨቀጨቅ ተፈርዶብኛል ልበል?”
“እባክህን ልጄ አሳፋሪ ነገር ደርሶብኝ ነው ዘመድና ዕድር የለለኝ በመሆኑ እንጂ . . . ” አሉ ትሁት በሆነች ፈገግታ ሊያባብሉት እየሞከሩ፡፡
“ቅናሽ ዋጋ ብትከፍለኝም . . .”
“ይሄ ሰውዬ ነካ ያረገዋል ልበል?” አለና ሌሎች መድኃኒት ገዥዎችን ያስተናግድ ገባ፡፡ “ከያዙ አይለቁ”


“ድህነት ቢፈትነኝ ነው ልጄ” አለ¸ያደፈና የነተበ ነጠላቸውን እያሳዩት፡፡ ነጠላው ከሰውነታቸው በከፋ ሁኔታ ያረጀውን ኮታቸውን ደብቆላቸዋል፡፡
“አቅሜ የደከመ ባይሆን ኖሮ . . . ” ጫማ ካገኘ የከረመ እግራቸውን እያዩ፡፡ አንዲት ተስተናጋጅ “አልመልስም ካለ አልመልስም ነው፡፡ ለምንድነው የሚነዘንዙት?” አለች በሚነጫነጭ ድምጽ “ይሄኮ ፋርማሲ እንጂ አዛውንቶች የሚጦሩበት የድኩማን መርጃ ድርጅት አይደለም”
አነጋገሯን ያልወደደው የሚመስል ሌላኛው ጎልማሳ ደግሞ “መድኃኒቱን ሙሉ በሙሉ የገዙት ከዚሁ መደብር ነው?” የሚል ጥያቄ አመጣ፡፡
“አዎ ዶክተሩ ፅፎ በሰጠኝ መሠረት”
“ምን ያሕል ፈጀብዎት?”
“ሰባ ሁለት ብር ከሰማኒያ አምስት ሳንቲም፡፡ መድኃኒቱን ወስደው ግማሹን እንኳን ቢሰጡኝ ምን አለበት?” አሉ በሃዘኔታ፤ “የሁለታችንንም የጋብቻ ቀለበት አስይዤ ነው ከማምነው ሰው የተበደርኩት”
“መድኃኒቱን ለምን መመለስ ፈለጉ?” ዘንቢል ያንጠለጠሉ ያንዲት ምስኪን እናት ጥያቄ፡፡
በዚህ ጊዜ አስተናጋጁ ጣልቃ ገባ፡፡ “ባህላዊ ሕክምና ብትከታተል ኪስ እንደማታራቁት ገብቷቸው ይሆናላ! ወይ ፀበል ሊያጠምቋት! ወይ . . .”
“ኧይ ልጄ! ጉዳዩን ብታውቀው ኖሮ ያፌዝክበት ምላስህን ታፍርበት ነበር . . .” አሉ እንባ እየተናነቃቸው፡፡
“መድኃኒቱን ምን ላድርገው? ልዋጠው ወይስ ሽንት ቤት ልጨምረው?”
“ለባለቤቴ ነው የምገዛላት ብለው አልነበር? በጠና ታማብኛለች የእድሜዬ ጀምበር እየጠለቀ ባበት ሰዓት ለእህል ያላነሱና ለትምህርት ያልደረሱ ሦስት ልጆች በትናብኝ እንዳትሄድ ፀልይልኝ ብለውኝ አልነበር?”
“ማለቱንስ ብዬህ ነበር ልጄ! . . . ብዬ ነበር”
“እና ሩብ ሰዓት ያህል እንኳን ሳይቆዩ ሃሳብዎን አስሰርዞ የገዙትን መድኃኒት የሚያስመልስ ምን ተአምር ተፈጠረ?! ቅድም የማይመለከተኝን ነገር ሲዘላብዱልኝ ነበር እኮ” አረጋዊው አንገታቸውን ደፉ፡፡ “እኮ ምን ቢፈጠር ነው . . . ?”
“ቤቴ ሳልደርስ ነው አንተ ዘንድ የመጣሁት”
“ለምን?” የሌሎቹ ጥያቄ፡፡
“ሰፈርተኞቼ ደጄ ላይ ሲጯጯሁ አየሁ፡፡ ባቤቴን በህይወቷ ልደርስላት አልቻልኩም!” አሉ አረጋዊው ድምጻቸው እየሻከረ፡፡ እንባቸው እየወረደ፡፡ በመድኃኒት ሻጩ ፊት ላይ ፀፀት ድንጋጤ እየታየ ድፍን መቶ ብር አውጥቶ በሻካራ እጆቻቸው ላይ አኖረው፡፡ ሌሎቹም ኪሶቻቸውን ይፈታትሹ ጀምር፡፡
“ይባርካችሁ ልጆቼ! ከፈን መግዣ ስላልነበረኝ እንጂ . . . ” አንባ ተናነቃቸው፡፡
መንሰቅሰቃቸውን እየቀጠሉ ወጡ፡፡
ፀጥታ!

http://www.endalegetak.blogspot.ca/2013 ... .html#more

ኮፒ ፔስት እንሰት
እንሰት
ውሃ አጠጪ
ውሃ አጠጪ
 
Posts: 1213
Joined: Sun Jan 30, 2005 1:14 am
Location: united states

ማዕዶት በ ቆሎ ተማሪ

Postby እንሰት » Thu Aug 29, 2013 6:14 am

የዋርካው የቆሎ ትማሪ ማዕዶት የተሰኘ የግጥም መድበሉን አሳትሞዋል:: ዋርካውያንም ተመስግነዋል:: ከቅንጥብጣቢዎቼ ጋር እመለሳለሁ::
እንሰት
ውሃ አጠጪ
ውሃ አጠጪ
 
Posts: 1213
Joined: Sun Jan 30, 2005 1:14 am
Location: united states

PreviousNext

Return to Warka Culture and Literature - ዋርካ ባህልና ሥነ ጽሑፍ

Who is online

Users browsing this forum: No registered users and 1 guest