ኢትዮጵያ በለንደን ኦሎምፒክ

ስፖርት - Sport related topics

Postby ገልብጤ » Mon Aug 06, 2012 11:23 pm

ዳግማዊ ዋለልኝ wrote:የተከበሩ ጓድ ውቃው

ዉቃው wrote:ጓድ ቀደምት
አቶ ብርሃነ ኪዳነማርያም ይህደጎ ከዋልታ ኢንፎርሜሽን ማዕከል የኦሎምፒክ ኮሚቲ ፕሬዚደንት : ወ/ሪት ዳግማዊት ግርማይ ብርሀነ በዋና ጸሀፊነት የሚመሩት አካል የሚያመጣውን ውጤት በተሰፋ ብንጥብቅስ ::

ኮሚቴውን አቶ ብርሀነ እና ወ/ት ዳግማዊት ባይመሩት ኖሮ የኦሎምፒኩን ውጤት በተስፋ አይጠብቁም ነበር :?: 8)

ጌዩ ውስጥ ለውስጥ ያሉት እዚህ ላይ ተመልሶልሀል
ያልበሰለ ፖለቲከኛ ስለቀጣዩ ምርጫ ሲያስብ
የበሰለ ፖለቲከኛ ስለቀጣዩ ትውልድ ያስባል
James freeman clarke
ገልብጤ
ዋና ውሃ አጠጪ
ዋና ውሃ አጠጪ
 
Posts: 1680
Joined: Sat Jun 26, 2010 11:24 pm

Postby ዳግማዊ ዋለልኝ » Mon Aug 06, 2012 11:36 pm

ከብቱ

አትፍራ.....ዙሪያውን ከምትዞር ዲየዲየቡ ጭንቅላትህን ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ አሰራውና ሀሳብህን ግለፅ......አይዞህ አልስቅብህም :lol: :lol: :lol:

1. በገነት ቦታ ጥሩነሽ እንድትወዳደር ያደረጉት አቶ ብርሀነ ናቸው እያልክ ነው :?:

2. ጥሩነሽ በገነት ምትክ መወዳደሯን አትደግፍም ማለት ነው :?:

መልስ እስቲ ዲየዲየቡ....ዛሬ እንኳን በራስህ ተማመን :lol: :lol: :lol:

ገልብጤ wrote:
ዳግማዊ ዋለልኝ wrote:የተከበሩ ጓድ ውቃው

ዉቃው wrote:ጓድ ቀደምት
አቶ ብርሃነ ኪዳነማርያም ይህደጎ ከዋልታ ኢንፎርሜሽን ማዕከል የኦሎምፒክ ኮሚቲ ፕሬዚደንት : ወ/ሪት ዳግማዊት ግርማይ ብርሀነ በዋና ጸሀፊነት የሚመሩት አካል የሚያመጣውን ውጤት በተሰፋ ብንጥብቅስ ::

ኮሚቴውን አቶ ብርሀነ እና ወ/ት ዳግማዊት ባይመሩት ኖሮ የኦሎምፒኩን ውጤት በተስፋ አይጠብቁም ነበር :?: 8)

ጌዩ ውስጥ ለውስጥ ያሉት እዚህ ላይ ተመልሶልሀል
"እቺ ለቅሶ ከፍየል በላይ ነች"
ዳግማዊ ዋለልኝ
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 3193
Joined: Wed Oct 20, 2010 12:09 am

Postby ቀደምት » Tue Aug 07, 2012 5:21 pm

ዳግማዊ ዋለልኝ wrote:.....ይበልጥ ደግሞ ጥሩነሽ በገነት ቦታ እንድትሮጥ መደረጉም ያሳዝናል....አስቀድሞ በወጣው መስፈርት መሰረት መሮጥ የነበረባት ገነት ያለው ነበረች.....ገና ለገና ለሜዳልያ ጉጉት ተብሎ መርህን መጣስና ለታዳጊዎች እድል አለመስጠት በጣም ስህተት ነው :!: የሚገርመው ደግሞ ተተኪ ታዳጊዎችን መኮትኮት ያስፈልጋል እያሉ የሚያላዝኑ ሁሉ አሁን ጥሩነሽ መሮጥ አለባት እያሉ መጮሀቸው ነው :wink:

ዳግማዊ በበኩሌ ጥሩነሽ እንድትሮጥ የደገፍኩት በቀደም ባሳየችን ኮንዲሽኗ የማሸነፍ ዕድል እንዳላት በመገመት ነው:: ገነት የበለጠ የማሸነፍ ዕድል ካላት ምናልባት ትክክል ልትሆን ትችላለህ:: እኔ የሷን ብቃት አላውቅም: ጥሩነሽ እንድትወዳደር ቢደረግ ጥሩ ነው ያልኩትም ከገነት ጋር በማዎዳደር አልነበረም:: ያልገባህ ነገር ግን የውድድሩ ዓላማ ማሸነፍ የመሆኑ ነገር ይመስለኛል:: ስፖርት ስለሆነ የማሸነፍ ብቃት ያለውን የተሻለ አትሌት እንዲወዳደር የማድረግ ነው:: ነገር ግን እንደ ፖለቲካው የጎሳ ተዋጽኦ: የታዳጊ ወይም የሌላ ነገር ተዋጽኦ አይደለም:: ያ የሚያስፈልገው ለሁሉም እድል ይሰጥ በሚለው መርሕ በምልመላውና በዝግጅቱ ወቅት ነው:: ተመልምለው ከተገኙት አትሌቶች ውስጥ ግን መወዳደር ያለበት የተሻለ ብቃት ያለው/ያላት አትሌት ነው/ናት:: የሜዳሊያ ጉጉት ያልከውም ትንሽ ፈገግ የሚያስብል ነው:: ዋናው ነጥብ ሜዳሊያ ማግኘቱ መሆኑን ዘነጋህ መሰለኝ:: ሌላው ሁለተኛና ሦስተኛ ጉዳይ ነው::

ከዚህ በተጨማሪ ጥሩነሽና ገነት ሁለቱም እኩል የማሸነፍ እኩል ችሎታ ያላቸው መሆኑ ከታዎቀም አሁንም እድሉ ይበልጥ ለጥሩነሽ ቢሰጥ እደግፋለሁ:: ምክንያቱም ድጋሜ ካሸነፈች ለራሷም ሆነ ለአገሯ ብዙ ጊዜ በታሪክ ሊቆይና ሊጠቀስ የሚችል ልዩ ክብር ስለሚሆን ነው:: ገነት ከጥሩነሽ የተሻለ የማሸነፍ ብቃት እንዳላት እርግጠኛ ከሆኑ ግን ገነት ብትመወዳደር ተገቢ ይመስለኛል:: የሆኖ ሆኖ ውሳኔው ቴክኒካል ጉዳይ ስለሆነ በቦታው ያሉት ባለሙያዎች አመዛዝነው የሚወስኑት ጉዳይ ነው:: በትክክል በአትሌቲክስ ስፖርት ሙያ ላይ በተመሠረተ ውሳኔ መመራት አለበት ብየ አምናልሁ::

.
ቀደምት
ዋና ኮትኳች
ዋና ኮትኳች
 
Posts: 761
Joined: Mon Feb 20, 2006 3:22 pm

Postby ቀደምት » Tue Aug 07, 2012 10:15 pm

ሰላም የስፖርት አፍቃሪዎች

የ800ሜትር ተወዳዳሪው መሃመድ አማን የሜዳሊያ ተስፋው ጠንከር ብሏል:: ለፍጻሜው ያለፈው ከምድቡ በመምራት ነው:: በዚህ ርቀት ወርቅ ያገኛል የተባለው ኬንያዊ ዴቪድ በሌላው ምድብ በመምራት በጥሩ ሰዓት ለፍጻሜው አልፏል:: ኬንያዊዩን ከዚህ ቀደም ያሸነፈ ብቸኛ አትሌት ኢትዮጵያዊዩ ነው ተብሏል:: መሀመድ ምንም አይነት ከለር ሜዳሊያ ቢያየግኝ ለኢትዮጵያ አትሌቶች ጥሩ ምሣሌ ይሆናል:: ምክንያቱም እንደረዥም ርቀቱ በአጭር ርቀትም ማሸነፍ እንደምንችል ማረጋገጫ ነው:: መልካም እድል::

ዛሬ 1500ሜ ፍጻሜ የተካፈለው መኮንን ገብረመድኅን 30 ሜትር እስኪቀረው ድረስ ሁለተኛ ቆይቶ 6ኛ መጨረሱ የሚያሳዝን ነው:: አሯሯጡ የቴክኒክ ስህተት የነበረበት መሆኑ ግልጽ ነው::

.
ቀደምት
ዋና ኮትኳች
ዋና ኮትኳች
 
Posts: 761
Joined: Mon Feb 20, 2006 3:22 pm

Postby ዳግማዊ ዋለልኝ » Wed Aug 08, 2012 8:59 am

ሠላም ቀደምት

መጀመሪያ ከላይ "እያላዘኑ" ብዬ የጠቀስኩት አንተን አይደለም........ሀሳቡን የምትጋራ ብትሆንም አንተን ግን እንዳላልኩኝ እወቅልኝ

ወደዋናው ሀሳብ ስንመጣ የኦሎምፒክ ተሳትፎ ዓላማው ሜዳልያ ማግኘት መሆኑንማ ማንም የሚያጣው አይመስለኝም......ለዚህም ተብሎ ሜዳልያ ለማግኘት ብቃት ያላቸውን ለመምረጥ በየምድቡ በአመቱ ባስመዘገቡት ምርጥ ሰዓት የሚለው መስፈርት ፍትሐዊና በየምድቡ ማን ሜዳልያ ሊያስገኝ ይችላል ለሚለው ምክንያታዊ መመዘኛ የሆነው.........ጥሩነሽ እጅግ ድንቅና ምናልባትም የምንጊዜም ኮከብ የርቀት ራጭ ብትሆንም በዚህ ዓመት ግን በ5000 ሜትር ያስመዘገበችው ሰዓት ከገነት ያለው እንደሚበልጥ ማስረጃ ላገኝ አልቻልኩም.....በ2012 ከገነት የበለጠ ሰዓት አስመዝግባ ከሆነ እሰየው

ሁለተኛ ነጥብ ደግሞ ድንቋ አትሌት ጥሩነሽ አሁንም ቢሆን በ5000ሜትር ውድድሩ ሜዳልያ ልታመጣ ትችላለች.....ዋናው ዓላማ ግን አንደኛ የምርጫው መስፈርት ተጥሷል...ሁለተኛ ደግሞ የገነት ያለው ሞራልና መነሳሳት ተጎድቷል....ይህ ጉዳይ የገነት ብቻ አይደለም.....ታዳጊ አትሌቶቻችንን በስፋት በማናይበት በአሁኑ ጊዜ ገነት እንዳትወዳደር ማድረግ የመጪዎቹንም ተስፋና ምኞት ላይ ከፍተኛ ተፅእኖ አለው.......ጀግናዋ ጥሩነሽ ከአሁኑ በኦሊምፒክ ሶስት ወርቅ በማግኘት ታሪክ ሰርታለች.....ለ5000 ሜትሩ ውድድርም መሰረት ደፋር እና ገለቴ ቡርቃ አስቀድመው ተመርጠዋል...ስለዚህ ለ20 ዓመቷ ታዳጊ ለገነት ያለው እድል መሰጠት ነበረበት ብዬ አምናለሁ

አስቀድሜ እንዳልኩት ግን የአትሌቲክስ ቴክኒካል ኮሚቲው ወይም አንተ ብቻ ሳትሆን በሚገርም ሁኔታ ሁሉም ሰው በሚያስብል አይነት የጥሩነሽ መወዳደር አስደስቶታል.....እንግዲያው ስህተተኛው እኔ ነኝ ማለት ነው :lol: "ይሁና" አሉ መቶ አለቃ ገብሩ በከዘራቸው መሬቱን እየቆረቆሩ :wink:

ቀደምት wrote:
ዳግማዊ ዋለልኝ wrote:.....ይበልጥ ደግሞ ጥሩነሽ በገነት ቦታ እንድትሮጥ መደረጉም ያሳዝናል....አስቀድሞ በወጣው መስፈርት መሰረት መሮጥ የነበረባት ገነት ያለው ነበረች.....ገና ለገና ለሜዳልያ ጉጉት ተብሎ መርህን መጣስና ለታዳጊዎች እድል አለመስጠት በጣም ስህተት ነው :!: የሚገርመው ደግሞ ተተኪ ታዳጊዎችን መኮትኮት ያስፈልጋል እያሉ የሚያላዝኑ ሁሉ አሁን ጥሩነሽ መሮጥ አለባት እያሉ መጮሀቸው ነው :wink:

ዳግማዊ በበኩሌ ጥሩነሽ እንድትሮጥ የደገፍኩት በቀደም ባሳየችን ኮንዲሽኗ የማሸነፍ ዕድል እንዳላት በመገመት ነው:: ገነት የበለጠ የማሸነፍ ዕድል ካላት ምናልባት ትክክል ልትሆን ትችላለህ:: እኔ የሷን ብቃት አላውቅም: ጥሩነሽ እንድትወዳደር ቢደረግ ጥሩ ነው ያልኩትም ከገነት ጋር በማዎዳደር አልነበረም:: ያልገባህ ነገር ግን የውድድሩ ዓላማ ማሸነፍ የመሆኑ ነገር ይመስለኛል:: ስፖርት ስለሆነ የማሸነፍ ብቃት ያለውን የተሻለ አትሌት እንዲወዳደር የማድረግ ነው:: ነገር ግን እንደ ፖለቲካው የጎሳ ተዋጽኦ: የታዳጊ ወይም የሌላ ነገር ተዋጽኦ አይደለም:: ያ የሚያስፈልገው ለሁሉም እድል ይሰጥ በሚለው መርሕ በምልመላውና በዝግጅቱ ወቅት ነው:: ተመልምለው ከተገኙት አትሌቶች ውስጥ ግን መወዳደር ያለበት የተሻለ ብቃት ያለው/ያላት አትሌት ነው/ናት:: የሜዳሊያ ጉጉት ያልከውም ትንሽ ፈገግ የሚያስብል ነው:: ዋናው ነጥብ ሜዳሊያ ማግኘቱ መሆኑን ዘነጋህ መሰለኝ:: ሌላው ሁለተኛና ሦስተኛ ጉዳይ ነው::

ከዚህ በተጨማሪ ጥሩነሽና ገነት ሁለቱም እኩል የማሸነፍ እኩል ችሎታ ያላቸው መሆኑ ከታዎቀም አሁንም እድሉ ይበልጥ ለጥሩነሽ ቢሰጥ እደግፋለሁ:: ምክንያቱም ድጋሜ ካሸነፈች ለራሷም ሆነ ለአገሯ ብዙ ጊዜ በታሪክ ሊቆይና ሊጠቀስ የሚችል ልዩ ክብር ስለሚሆን ነው:: ገነት ከጥሩነሽ የተሻለ የማሸነፍ ብቃት እንዳላት እርግጠኛ ከሆኑ ግን ገነት ብትመወዳደር ተገቢ ይመስለኛል:: የሆኖ ሆኖ ውሳኔው ቴክኒካል ጉዳይ ስለሆነ በቦታው ያሉት ባለሙያዎች አመዛዝነው የሚወስኑት ጉዳይ ነው:: በትክክል በአትሌቲክስ ስፖርት ሙያ ላይ በተመሠረተ ውሳኔ መመራት አለበት ብየ አምናልሁ::

.
"እቺ ለቅሶ ከፍየል በላይ ነች"
ዳግማዊ ዋለልኝ
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 3193
Joined: Wed Oct 20, 2010 12:09 am

Postby ቀደምት » Sat Aug 11, 2012 10:05 pm

በሴቶቹ5ሺ መሠረት ደፋር አስደሳች ውጤት በማምጣቷ ክብራችንን አስጠብቃለች:: ጥሩነሽ ያለመችው ድጋሜ ድል ስላልተሳካላት ብዙም ደስተኛ ሆና ባትታይም ነሀሱ ጥሩ ውጤት ስለሆነ ልትኮራ ይገባታል::

በወንዶችም በ5ሺ ደጀን የብር ሜዳሊያ ባለቤት ስላደረገን እንኳን ደስ ያለን!! ነገር ግን በኔ ግምት የቴክኒክ ስህተት ባይፈጽም ኖሮ ወርቁ የሱ ይሆን ነበር:: በመጨረሻው ዙር ይዞት የነበረውን ቦታ መጠበቅና ከሞፋራ ጋር መሄድ ሲገባው ፍጥነቱን ሳይገደድ በመቀነስና ቦታውን በመልቀቅ አስቸጋሪ መስመር ውስጥ ሊታሸግ በቃ:: ከዚያም ለመውጣት በሚሞክርበት ጊዜ እንዲያውም ተደናቅፎ ሁሉ ነበር:: ከአንዴም ሁለቴ መስመር ለማግኘት ትንሽ ተቸግሮ በመጨረሻ ግን ዘግይቶም ቢሆን ፍጥነቱን በመጨመር ሁለተኛ መሆኑ አስደሳች ነው:: ነገር ግን አንደኛና ሦስተኛ ከፈጸሙት አትሌቶች ጋር ሲተያይ በአንጻራዊነት ገና በደህና ትንፋሽና ፍጥነት ላይ እያለ ነው ውድድሩ ማለቂያ ላይ የደረሰው:: ስለሆነም ቴክኒካሊ ባይሳሳት ኖሮ አሸናፊ ሊሆን ይችል ነበር ብየ ትንሽ አስቆጭቶኛል:: ባመጣው ውጤት ግን ሊመሰገን የሚገባው: ለወደፊቱም ተስፋ ያለው አትሌት ነው::

ባጠቃላይ የረዥም ርቀት ሩጫ ሁሌ በዋስትና ይዘነው የምንቆየው ነገር አለመሆኑን የሚያሳይ ነውና የተሻለ ትኩረትና ዝግጅት ማድረግ ካልቻልን እንደብዙዎቹ አገሮች ያለምንም አይነት ውጤት ወደቤት መመለስ ይመጣል::

.
ቀደምት
ዋና ኮትኳች
ዋና ኮትኳች
 
Posts: 761
Joined: Mon Feb 20, 2006 3:22 pm

Postby ዳግማዊ ዋለልኝ » Sun Aug 12, 2012 7:11 am

የ2012 የለንደን ኦሊምፒክ የመጨረሻ ውድድር በሆነው የወንዶች ማራቶን ላይ ለሚወዳደሩት ኢትዮጵያውያን አየለ አብሽሮ....ጌቱ ፈለቀና....ዲኖ ስፍር መልካም ውጤት :!: እናቸንፋለን :D

እንዲሁም በለንደን ኦሊምፒክ ሀገር አልባ ስለሆነ በኦሊምፒክ ባንዲራ ስር ኢንዲፔንደንት ኦሊምፒክ አትሊት ሆኖ ለሚሮጠው ደቡብ ሱዳናዊው ጉኦር ሜርያል መልካም ዕድል :!:
"እቺ ለቅሶ ከፍየል በላይ ነች"
ዳግማዊ ዋለልኝ
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 3193
Joined: Wed Oct 20, 2010 12:09 am

Postby ቀደምት » Sun Aug 12, 2012 4:35 pm

በዚህ ኦሎምፒክ የኢትዮጵያ ወንድ አትሌቶች አንድም ወርቅ ለማግኘት አልቻሉም:: የአትሌቶቹ ዝግጅት በአመራር በኩል ችግሮች እንደነበረበት ቀደም ባሉት ወራት ፍንጭ አግኝተን ነበር:: ይኸውና በውጤቱ እንደታየው ጥያቄዎች መነሳታቸው አይቀርም:: ኃይሌ ገብረሥላሴም አንስቶታል::

እኔ የማይገባኝ አንድ ነገር ጥቂት አሰልጣኞች ስፖርቱን ርስት-ጉልት አድርገውት በጡረታ ወይም በሽምግልና ተዳክመው እስኪለቁ አድራጊ ፈጣሪ ሆነው መኖራቸው ነው:: በስፖርት ስልጠና በርግጥ ልምድ ያላቸው ሰዎች ብዙ ጊዜ አስፈላጊ ናቸው:: ነገር ግን ያሳዩት የመሻሻል ግራፍ በመታየት በየወቅቱ አዲስ ኃይልና አዲስ አስተሳሰብ ካልተጨመረበት በስተቀር በዘመናዊ ቴክኖሎጂና በብዙ ካፒታል ከሚፎካከሩት አገሮች ጋር ለመወዳደር ብቃት ሊኖረን አይችልም:: በአትሌቲክስ ስፖርት comparative advantage ያለን አገር ሆነን ሳለ ዝግጅቱን ካላወቅንበት አርኪ ውጤት ለማምጣት አንችልም::

ለምሳሌ እንደ ይልማ በርታ አይነቱን አሰልጣኝ ተመልከቱ:: ከ30 ዓመት በላይ አለ:: ሰውየው ዶ/ር ነው :: ነገር ግን እስካሁን በመስኩ አንድም የምርምር መጽሐፍ መጻፉን አልሰማንም:: እንደዚህ ረዥም ልምድ አላቸው የሚባሉ ሰዎች ካስፈለገ በስፖርት ሚንስትር መስሪያቤት አካባቢ ሆነው ሌላ አገልግሎት ቢሰጡ የተሻለ ይመስለኛል:: በቀጥታ አሰልጣኝነትን ይዘው ከሚቀጥሉ:: በትምሕርት ያገኙትንና በልምድ ያካበቱትን እውቀት አካተው ለትምሕርት ቤቶች የሚያገለግል የስፖርት ካሪክለሞችን ቢያዘጋጁ ተገቢ ነው:: ሳይንሱ በየጊዜው እያደገ ስለሚሄድ ብቃት ያላቸው: የተሻለ አሰራር ለመዘርጋት ሃሳብ የሚያመነጩ ትጉህ ሰዎች ያስፈልጋሉ::

ይልማ በርታ ወደለንደን ሊመጣ ሲል ጠቅላይ ሚኒስትር መለስን ለስፖርት ባላቸው ፍቅር ባደረጉት ድጋፍ...ምናምን እያለ ሲያሞካሽ ነበር:: መንግሥት ትኩረት ሰጥቶ በገንዘብም ሆነ በፖሊሲ ደረጃ ለስፖርቱ ድጋፍ ቢሰጥ ኖሮ (ያለን የኢኮኖሚ ድክመትም እንደተጠበቀ) አስገራሚ ውጤት ለማምጣት ይቻላል:: እነዚህ የቆዩት ሰዎች የእድሜልክ ቅጥር እንዲሆንላቸው ከፖለቲካ ሰዎች ጋር እየተሻሹ ለማዝገም የሚፈልጉ እንጂ በነሱ ስር ተተኪ የሚሆኑ ብቁ አሰልጣኞች እንዲኮተኮቱ የሚሹ አይመስለኝም::

በለንደን ኦሎምፒክ ያገኘነው ውጠት የሚያስደስተን ቢሆንም ከዚህም በላይ ልናገኝ እንችል ስለነበር የተከሰቱ የድክመት ምንጮችን መመርመርና ለሚቀጥለው በተሻለ ለመዘጋጀት መነሳት ያስፈልጋል:: ለማንኛውም ከፍተኛ ተጋድሎ አድርገው ሜዳሊያ ያስገኙልን አትሌቶችንና ሌሎችም የቻሉትን ያህል ጥረት ያደረጉትን ወኪሎቻችንን ከልብ ልናመሰግናቸው ይገባል::

.
ቀደምት
ዋና ኮትኳች
ዋና ኮትኳች
 
Posts: 761
Joined: Mon Feb 20, 2006 3:22 pm

Previous

Return to Warka Sports - ዋርካ ስፖርት

Who is online

Users browsing this forum: No registered users and 1 guest