ሰላም ድዩ ጁሀር
እውነቱን ለመናገር እኔ እንኳን አንተ የምትጽፋቸውን በቁምነገር አንብቤያቸው አላውቅም ... አይ ሆፕ ቅር እንደማይልህ ... ምክንያቱም አንተም ታውቀዋለህ ... በቁምነገር እንደማትጽፋቸው ... ቅቅቅ
እዚህ ጋ ስላልነሳኸው ነገር ... ስለኔና ስለባለቤቴ በተመለከተ ወደ ጎን ትቼ (አስፈላጊ ሆኖ ሲገኝ ወደፊት ልንተርከው እንደምንችል እየጠቆምኩኝ) ... ከርታታውን በሚመለከት ስለጻፍከው መልስ ልስጥህ::
አንደኛ በጣም ያሳቀኝ ነጥብ ... እንደ ከርታታው ፋስት ... ስትል ... የምሬን ነው የምልህ ... ቅቅቅቅ ... በጣም ነው የሳቅኩት:: ... አሁን ጸሀይ ጋር ... አንሶላ ለመጋፈፍ ቢበቁ ... አወጣችው ነው የሚባል አወጣት ... ቅቅቅ ... ፋስት ትላለህ እንዴ ደግሞ ... አንዲት ባለትዳር ሴት ... ባሏን ከጎን አስቀምጣ ... በጠጅ የጠበሰችውንና በራሷ ግፊት ለቀጠሮ የበቃን ሰው ... ፋስት ማለት ምን ማለት ነው ... :lol: :lol: የናንተ ፋስትነት እንደዞብል ... የአራዳ ዘመን አራዳነት ነው እንዴ? ... ፍሬንድ ዘመኑ 'ኮ ተለውጧል ... ጨዋታውም እንዲሁ ተለውጧል::
ስማ ልንገርህ ... ገና ሀይስኩል ሳለሁ ነው ... አንዱ የፒያሳ "ጎዳና ተዳዳሪ" ... አራዳነት አውቆና ቀድሞ መገኘት እንደሆነ ያስተማረኝ ... በኢቲቪ መቶ ሀያ ፕሮግራም በኩል ... የምሬን ነው:: ... ለድሮ ሰዎች ... ሰክሮ መንደፋደፍ ... ከሸሌ ጋር ውቤ በርሀ ላይ መጋፋት ... በጠለፋና በምናምን አስገድዶ መድፈር ... ወዘተ ... የአራዳነት መገለጫው ነበር ... ቅቅቅ ... ኋላም HIV + ሆኖ መገኘትም እንደ አራዳነት የሚታይበት ዘመን ነበር ... ቅቅቅ አሁን ወንድሜ ... አራዳነት ስሙም ራሱ ይደብራል ... የገባው ነቄ ምናምን ... ሲባል እንጂ አራዳ ሲባል ... የዞብል አይነት የዘኬ ሊቃውንትን ነው የሚያስታውሰን ... ቅቅቅ
እና ምን ለማለት ነው ... ከርታታው ራሱንም ለመግለጽ እንደሞከረው ... ትንሽ "አራዳነት" ካለበት ... ሂ ኒድስ ቱ ዱ ዘ ራይት ቲንግ ... :!: ... ባለትዳርን ማማገጥ ... አራዳነት አይደለም:: ... በተለይ ደግሞ ... እሷ ጠባሽ ... እሷ ቆስቋሽ ሆኖ ... ካወጣችው ... ቅቅቅ ... ይቅር በቃ .. አልጨርሰው
ምን ይላሉ መሰለህ ደግሞ ... ውሀ መጠጫ ብርጭቆህን ለመስበር ምንም ጉልበትም ሆነ ጥበብ አያስፈልግህም ... ከእጅህ ለቀቅ ማድረግ ብቻ ነው:: ... ልስራው ብትል ግን ... ቀናትን ምናልባትም ሳምንት ይፈጅብሃል ... ያውም መስራቱን የምትችልበት ከሆነ ነው:: ... ፊዚስቶች እንደዚህ አይነት ሁኔታ ሲገልጹ ... ኢንትሮፒ ምናምን የሚል ነገር ጠቅሰው ... ኬኦስን መፍጠር ቀላል ሲሆን ... ኦርደርን ማምጣት ግን በጣም ከባድ ነው:: ... የተሰበረውን ብርጭቆ ወደ ነበረበት ለመመለስ (ኦርደር ለማምጣት)... ብዙ ጉልበት ጥበብ ምናምን ይጠይቃል:: ... ጤነኛውን ብርጭቆ ለመስበር (ኬኦስ ለመፍጠር) ግን ... ምንም የሚከብድ አይደለም:: ... ትዳርን አክብሮ የትዳርን ኦርደር መፍጠር መቻል ... ለአንድ ማህበረሰብ ከባድ ራስ ምታት ነው:: ... ትዳርን መበተን ግን ... በጣም ቀላል ነገር ነው:: ... በህይወትህ አንድ ትዳር ብቻ ነው ስኬታማ ማድረግ የምትችለው:: ... ትዳር ለመበተን ግን በቀን ምናልባትም ከአስር በላይ ሊሳካልህ ይችላል:: ... ሶ አውቆና ነቅቶ መገኘት ስንል ... ለትዳርና ለቤተሰብ ሀላፊነት የሚሰማህ ዜጋ መሆንን ይጠይቃል:: ... እያንዳንዱ ትዳሩን ቢያከብር ... ልጆቹን በስነምግባር እያነጸ ቢያሳድግ ... አሁን የምታያቸውን የግለሰብ, የማህበረሰብ, የአገር ወዘት ችግሮች በብዙ ሺ እጥፍ በቀነሱ:: ...
ፍቅር ነው ምናምን ስላልከው ነገር ... እኔ የተረዳሁት መፈላለግ እንዳላቸው እንጂ ፍቅር አይመስለኝም:: ... ከጽሁፉም እንደምታየው ... ፍቅር የያዘው ሰው እንዳልሆነ ነው:-
በእህትነት ቢሆን ደስ የሚለኝ ይመስለኛል :: በሮማንሱም ቢሆን አይከፋኝም ::
ፍቅር ቢሆን ምን ማድረግ አለበት ሌላ ጉዳይ ነው ... እኔ ይህ ይሁን ይህ አይሁን ማለት አልችልም:: ... አሁን ባለው ሁኔታ ግን ... መራቅ ነው ያለበት:: ... ወይም ደግሞ የሷ ፍላጎት ምንም ይሁን ምን እሱ ወደ እህትነት መቀየር ያለበት ይመስለኛል:: ... አት ሊስት እኔ ብሆን የማደርገውን ነው እንግዲህ እያወራሁ ያለሁት::
ጁሀር2012 wrote:ባክህ አታስቦካው አንተ እንደዚህ አይነት ቻንስ ስላላጋጠመህ የተበሳጨህ ይመስላል ወይንም ሚስትህን አንዱ እንደ ከርታታው አይነት ፋስት ሰው ነጭቶብሀል ማለት ነው. :lol: አይዞን ቀልድ ነው ! ግን ስማ ፍቅር ማለት ረቂቅ የሆነ በ2 ኦፖዚት ጾታዎች መካከል የትም ቦታና በማንኛውም አጋጣሚ ሊያጋጥም የሚችል ታላቅና ረቂቅ ጸጋ እንደሆነ ማወቅ አለብህ. ስለዚህ በጋብቻ, በኑሮ ሁኔታ, በዘር እንዲያውም ባጠቃላይ በኮመን ሴንስ ሁላ ልንገልጸው የማንችል ከላይ የተሰጠ ጸጋ ነው. ልጁ እስከወደዳት ድረስና እስዋም እስከወደደችው ድረስ ባልዋን ሁላ ፈታ እሱን ማግባት መብትዋ ነው. ሰው አብሮ የሚኖረው ፍቅር እስካለው እና በመፈቃቀድ ላይ ብቻ የተሞረከዘ እንደሆነ ነው. ሰውን ልጅ በጋብቻ ምክንያት ብቻ ፍቅርን ኢምፖዝድ ማድረግ እንደማይቻል ግልጽ ነው. ነገሩ ለባልየው ምን ያህል ከባድና ስሜትን የሚነካ ነገር እንደሆነ ግልጽ ነው ነገር ግን አንዳንድ ግዜ የውነታውን አለም መጋፈጥ የግድ የሚልበት ጊዜ አለ.