ፓ ፓ አፍሪካ

Topics related to cultures, arts, languages, arts such as humor, music, traditional literary genres of poems, ግጥም ፣ ቅኔ ፣ ተረትና ምሳሌ)

ፓ ፓ አፍሪካ

Postby ስራ ፈት » Thu Jul 19, 2012 5:45 am

ጤና በግብዳው ዘግኖ ዘግኖ ይስጣቹ ከላይ እስከ ታች ከትልቅ እስከ ትንሽ:: ዋርካ ላይ ብዙ ነገር አይቻለው::የአፍሪካ ሙዚቃ ግን አላየውምና ላካፍላችው ከቀያችው ከተምኩኝ:: የምታውቁት ካለ ጀባ እያላችሁን እናንተም ተሳተፉ:: ግን ግን የኛዎቹ ቺኮች እንደዚህ መወዛወዝን ቢማሩልን በወደድን ነበር:: በምኞት አይገኝ ዋንኬ ብቻ አለ ክብበው ገዳ:: በሉ ለዘፈን መጥቼ ነገር ውስጥ ገባው:: የኛ ያበሾች ነገር እኮ በቁንጥጫ ጀምረን በፈንጂ ነው የምንጨርሰው::

ለዛሬ እንሆ በረከት

http://youtu.be/CIdXdI92jkk

ትርጉም እንዳጠይቁኝ እንደ ጠጅ ቤት ደንበኛ ሙላ ሙላ ብቻ ነው የሚሰማኝ: :lol: :lol:
ስራ ፈት
ጀማሪ ኮትኳች
ጀማሪ ኮትኳች
 
Posts: 65
Joined: Mon Jan 17, 2005 8:37 pm

Postby ዘጌ_ዘጋንባው » Fri Jul 20, 2012 12:03 am

ስማ ምነው በዚችኛዋ ኒክህ ጠፋህብኝ?... ሰው ሚስቱን ይፈታል አንተ ደልቶክ ስራ ፈተካል...አይ ጥሩ ነው....

እና ልልህ የፈለኩት ግሩም ሩም ከፍተካል......

እኔ የምቀድሰው በናይጄያዊው የ አፍሮቢት ሙዚቃ ፈርቀዳጅና ማይስትሮ የሆነው ፌላ አኒኩላፖ ኩቲ ...ሁለት ስራዎችን በመለጠፍ ይሆናል:: እርግጥ ነው ዝነኛ ስራዎቹ ፖሊቲካሊ ቻርጅድ ነበሩ:: ግዜው 60ዎቹ ማብቅያና ሰባዎቹ የቬትናም ጦርነትን ተከትሎ ፕሮቴስት ሚይውዚክ አይነተኛው እርፍና ነበርና ፌላም በዛ ስታይል ያገሩን ኮረፕት ወታደራዊ-መንግስት በሙዚቃ ስራዎቹ ከመጎነታተል አላረፈም:: አፍሪካ ሽራይን የተባለው የሌጎስ ናይት ክለቡ አለማቀፋዊ ዝናው ከመናኘቱ የተነሳ ከአለም አራቱም ኮርነሮች አድናቂዎቹ እየተግተለተሉ ይታደሙ ነበር:: በቅርቡም ታዋቂዎቹ ጄይዚ እና ዊል ስሚዝ ባንክሮል ያረጉት በፌላ ኩቲ ሙዚቃዊ ህይወት ላይ ያጠነጠነ Fela! የተባለ ሚውዚካል ....ከ ኦርዲናሪ ስቴጅ ተነስቶ ወድያውኑ ብራድዌይ ላይ ለመታየት የበቃ ክሪቲካሊ አክሌይምድ ሾው እንደነበር የቅርብ ግዜ ትዝታችን ነው::

መቼም የሰው ልጅ ደካማ ነውና ኤክሰንትሪኩ ፌላ ያቺን ቀዳዳ አብዝቶ ይወድ ስለነበር በአፍላ እድሜው በ 58 አመቱ ይህችን አለም በ ኤይድስ በሽታ ሰበብ ለመሰናበት ግድ ብሎታል::

እስኪ ዞምቢ እና ሌዲ የተሰኙትን ስራዎቹን በርጋታ እንኮምኩም......

http://www.youtube.com/watch?v=O0psvbX1YB0


http://www.youtube.com/watch?v=TevLxi5V ... re=related

ለጠቅላላ እውቀት:- ፌላ እና የመጀመርያው ጥቁር የኖቤል ተሸላሚ .... ባለቅኔው.... ጸሀፌትያትር ዎሌ ሶይንካ የቅርብ ዘመድ.../ ከዝን ናቸው::

ስራ ፈት.... ሶሪ ቂጥ ዲስተርብ ማረግ ( መበጥበጥ) ያለበት ሙዚቃ ስላልጋበዝኩ :D
ዘጌ_ዘጋንባው
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 176
Joined: Wed Aug 18, 2010 5:45 am

Postby ዘጌ_ዘጋንባው » Fri Jul 20, 2012 5:54 am

አሊ ፋርካ ቱሬን ደሞ ልጋብዝ እስኪ:: ቱሬ የፈለቀው በሙዚቃ ከአፍሪካ ቁንጮ የሆነችዋና እንደ ኢሳ ባጋዮኮ, ሳሊፍ ኬይታ እና በቅርቡ ደሞ እንደ ሀቢብ ኮይቴ ያሉ ድንቅ ሙዚቀኖችን ካፈራቸው ሀገር ማሊ ነው:: ቱሬ በጊታር አጨዋወት ስልቱ አፍሪካዊው ጆን ሊ ሁከር ተብሎ አድናቆትን የተቸረው ምርጥ ሙዚቀኛ ነው:: ..... ቢ.ቢ. ኪንግን በሰማክበት ጆሮክ አሊ ፋርካ ቱሬን ስትሰማ ቋንቋው ይለያይ እንጂ ሪትሙ ጠንከር ያለ ትስስር ታይበታለክ:: እኔ እንደው ኦሮምኛ ቋንቋ የ ብሉዝ መሰረቱ ነው ብዬ ሁሉ ለመከራከር ይዳዳኛል .... :lol: ... ምክንያቱም ብሉዝ ካፍሪካ ከሆነ ማሊያን ሚይውዚክ ደሞ ቁርጥ እሱን ነው ...ከዛ ቀጥለክ በዛ ሎጂክ ስትወርድ ደሞ የማሊዎች ቋንቋ ሲናገሩት ባልሰማም ሲዘፍኑበት እንደኦሮምኛም ስለሚያረገው ..ያው ብሉዝም ኦሮሚፋ ነው ሶርሱ ብዬ አይኔን በልጥቼ እከራከራለዋ ( ማን ይሞታል አባ! ማጠጋጋት ነው እንጂ) .....

እና እልካለው አሁን የምጋብዘው ለስለስ ብሎ የሚሰረስረውን Au Di የተባለውን ዘፈን ይሆናል:: ይህ ዘፈን unfaithful የተሰኘ ሪቻርድ ጊር የሚተውንበት የበዴ ፊልም ሳውንድ ትራክም ሆኖ ማገልገሉ ብዙዎች አሊን እንዲያውቁት በሩን ከፍቶዋል..... ከ Ry Cooder ጋር ነው የተጫወተው.. አልበሙም talking timbuktu ሲሆን ከፈለክ አማዞን ላይ አለልክ ሸምተው:: ይህንን ዘፈን በሌላ ትሬድ ላይ በሌላ ኒክ መጋበዜ ትዝ ይለኛል ...ግን እንኳን ዘፈን ስምንተኛ ክፍልም ሁለቴ ነው የደገምኩት... ስለዚ ጣጣ የለውም አርፈክ ኮምኩም እልካለው...

http://www.youtube.com/watch?v=zLVdrgd8w_s

ጊታር ይናገራል ይልሀል!!

ለጠቅላላ እውቀት:- አሊ ፋርካ ቱሬ ልጆቹን ሙዚቀኛ እንዳይሆኑ ክፉኛ ይከላከል ነበር:: ግና ወንድ ልጁ Vieux Farka Toure በድብቅ ጊታርን ተምሮ የበቃ የነቃ ጊታሪስት ከመሆኑም በላይ አሁን በራሱ ግዜ ትልቅ አድናቆትና አክብሮት የሚቸረው ሙዚቀኛ ለመሆን በቅቷል::
ዘጌ_ዘጋንባው
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 176
Joined: Wed Aug 18, 2010 5:45 am

Postby ስራ ፈት » Sat Jul 21, 2012 9:33 am

ዘጌ ስራ በዝቶና የሆነ ነገር ጀምሬ ነው የጠፋውት እንጂ ወላሂ ይቺው ነች ስሜ:: በተረፈ ረመዳን ሲፈታ ከች ብዬ የሆነ መላ ያለው ጨዋታ አጫውትሻለው:: ይመችሽ::
ስራ ፈት
ጀማሪ ኮትኳች
ጀማሪ ኮትኳች
 
Posts: 65
Joined: Mon Jan 17, 2005 8:37 pm

Postby ዘጌ_ዘጋንባው » Tue Jul 24, 2012 12:54 am

እሺ..ስራ ፈት መልካም ረመዳን

እኔ ግን ዘፈን ከመጋበዝ አልቦዝንም እልካለው....


ለዛሬ በቅርብ አመታት ተወዳጅ ከሆነ አፍሪካዊ ዘፈኖች አንዱ የሆነው Gaou እጋብዛለሁ:: ዘፋኙ ማጂክ ሲስተም ሲሰኝ ... የዘፈኑ ስታይል Zonglou በመባል ሲታወቅ...... አጀማመሩም በ አይቮሪኮስት በ1990ዎቹ መጀመርያ የዩኒቨርስቲ ተማሪዎች የካምፓስ ኑሮን በተመለከተ መንግስት ላይ ያላቸውን ቅሬታ ሽሙጣዊ በሆነ ሁኔታ የሚገልጹበት የአዘፋፈን ዘይቤ ነው....

http://www.youtube.com/watch?v=plS_9hXh ... re=related

ኮምኩሙ::
ዘጌ_ዘጋንባው
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 176
Joined: Wed Aug 18, 2010 5:45 am

Postby ዘጌ_ዘጋንባው » Sun Jul 29, 2012 8:17 pm

በ ካሜሩናዊው ማኑ ዲባንጎ soul makossa ሳምንቱ ይዘጋለት መሰለኝ

ዲባንጎ ሀይለና ሳክስፎኒስት ነው.... የካሜሩንን ባህላዊ ሙዚቃ ከጃዝ ጋ በማቀናበር ለአለም ያስተዋወቀ የሙዚቃ ሰው ነው.....


ለጠቅላላ እውቀት:- ማይክል ጃክሰን ታዋቂው ትሪለር አልበም ውስጥ የተካተተው wanna be startin' somethin' .... እሚለው ዘፈን ውስጥ ደጋግሞ .....ማማሴ ማማሳ ማማኩሳ....ሲል ይደመጣል::ታድያ ይቺን ካለ ፍቃድ የወሰዳት መስመር ምንጯ የማኑ ዲባንጎ ዘፈን ሶል ማኮሳ እንደሆነች ደንቆሮም አይስተውም...በዚህ ሰበብም ማኑ ዲባንጎ ክስ መስርቶ በማሸነፍ ዳጎስ ያለ የካሳ ገንዘቡን አፍኖ ላጥ ብሏል::

ሶል ማኮሳ ያውላቹ እንግዲ..

http://www.youtube.com/watch?v=w2jYjUiulMQ

መልካም ነገ ሰኞ
ዘጌ_ዘጋንባው
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 176
Joined: Wed Aug 18, 2010 5:45 am

Postby ስራ ፈት » Fri Aug 24, 2012 9:02 am

ዘጌው አቤት መቼም ይሄ አሊ ፋርካ ቱሬ የሚባል ዘፋኝ እንደጉድ ይዘፍነዋል:: እኔማ አንዱን ዘፈን ሰባቴ እየደጋገምኩት በጊታር ችሎታው ተመስጨ አጃኢብ ስል ከረምኩኝ::

እንኩዋን አወኩት ብቻ:: ግን ምን አሰብኩኝ መሰለህ? ምን አለበት እኛም እንደዚህ በጊታር ችሎታው የተካነ አንድ ዘፋኝ ቢኖረን ብዬ ተመኝው::

ላፕቶፔ ከሰሞኑ ጤና ነስቷት ሰነበተ:: እንደ ብረምጣድ ቂጥ መጋሏ ሳያንሰኝ በጩኸት አገሩን ታሸብረዋለች:: ጭጭ ያልኳት እንደሆነ በገዛ ፍቃዷ ድርግም ትላለች::

በኌላ ምናባቱ ብዬ አራት መቶ ዶላር ፎጭ አድርጌ ምን የመሰለ ቶሺባ ገዛውና እንደ አሮጌ ጣሳ አውጥቼ ወረወርኳት(በርካሽ ለሆነ ኮምቲተር ለሚሰራ ሸጥኳት)

ስለዚህ ሰሞኑን ዋርካ ላይ በሽ ነኝ ማለት ነው:: እመለሳለው:: መልካም ቀን::
ስራ ፈት
ጀማሪ ኮትኳች
ጀማሪ ኮትኳች
 
Posts: 65
Joined: Mon Jan 17, 2005 8:37 pm

Postby ዘጌ_ዘጋንባው » Sat Aug 25, 2012 2:06 am

ሰራ ፈቱ.....ዌልካምባክ.... ረመዳን እንዴት ነበር? ....የ አሊ ፋርካ ቱሬን ሙዚቃ ኢንጆይ ስላረክ ደስ ብሎኛል...

ዛሬ ይገርምካል አፍሪካ መሆናችን ሳይረሳ አለ አይደል...ባገራችን ምርት እንኩራ የሚል መፈክር ይዤ ነው ከች ያልኩት....
ያው የሰው ስናደንቅ የኛንም እኮ መዘናጋት የለብንም በሚል...የሀገራችን የሙዚቃ ንጉስ ..ጥላሁን ገሰሰን .... የሂወቴ ሂወት የሚለውን ብጋብዝ ምን ይለኛል?

ጥላሁን ግን ዩኒክ ዘፋኝ ነበር....አንዳንዴ እኮ ዘፈኑ መፈክር አይነትም ነገር ነው...ቅቅቅቅቅ... ሜይ ቢ ትንፋሹን ረጅም ግዜ ስለሚይዘው ይሆናል...ግን ሰውዬው ጎበዝ ስለሆነ ያሳምረዋል....
ባይዘዌይ ይህን ዩትዩብ ክሊፕ ሳይ አንተ ታይሙ ቀላል ጭሮዋል እንዴ...ቅቅቅ...ፓንክ የተቆረጡ ሴቶች ምናምን አሉበት...አሙካ መሆን አለበት.... በ ቲና ተርነር ዘፈን የጨፈሩ ምናምን....
እስኪ እንኮምኩም ....ነቆራውን ትቼ.....
http://www.youtube.com/watch?v=vcfHecXL ... re=related


አንጠፋፋ
ዘጌ_ዘጋንባው
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 176
Joined: Wed Aug 18, 2010 5:45 am

Postby ጁሀር2012 » Sat Aug 25, 2012 9:24 am

ዘንጋባው እናትን ልብዳት ባለፈው ስሜ የሙስሊም ስለመሰለህ ብቻ የአረብ ሩዝ ምናምን እያልክ እንደናትን ---- የተላላጥክብኝ አሁን ደሞ ሙድ እንዳለው ሰው እስልምናን ሪስፔክት አርገህ ስለረመዳን ታወራለህ. ንፍጥም የሸርሙጣ ልጅ
ጁሀር2012
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 113
Joined: Sun May 27, 2012 9:06 pm

Postby ዘጌ_ዘጋንባው » Sat Aug 25, 2012 4:08 pm

ጁአራም... :lol: ... ዝም ብለሽ እንደአሽከር ትከታተይኛለሽ....ያለፈው ንግግረ ዚስ ማች ተጎድተሻል ለካ?..... በቃ ከተጎማዘዝክ ሩዙ በ ፓስታ ይቀየረልክ? ....ቅቅቅቅቅ.....ፓስታ ቀቃይ ልበልክ?... ሂድና አቦ...ደረቅ ፓስታ ሰባብረክ ቂጥክ ውስጥ ክተተው.... .... :lol: .... እና እልካለው ስድብ መፈብረክ ባትችል እንኳን ዴቨሎፕ ማረግ ተማር.... እኛን አይተሽን እንደሆነ..ኳስ በሰማይ ጀምረን ... ሳታስቢው በመሬት እናረጋጋለን..... የሆንክ ላባም ...ጢማም ልጃገረድ ነገር... :lol:

ነይና ደሞ እስኪ እንጫወት...አይ ጁአር....የለማኝ አር የሆንሽ ነገር....
ስማ ፓስታው እንዳይገነፍል ባይ ዘ ወይ :wink:
ዘጌ_ዘጋንባው
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 176
Joined: Wed Aug 18, 2010 5:45 am

Postby ስራ ፈት » Sat Aug 25, 2012 6:24 pm

ዘጌ ሰላም ነው ረመዳን ሰላም ነበረው:: በሀይለኛው ነበር ያሳለፍነው:: ክርስትያን ፍሬንዶቼ ሁሉ ከስራ ሲወጡ እቤት ከች እያሉ አብረን ነበር የምናመሸው:: ለሚቀጥለው በሰላም ያድርሰን ማለት ነው እንግዲህ::

የጥላሁን ሙዚቃ አሪፍ ነው:: ጥልሽ ነብሱን ይማረውና ስንቱን ቺክ በግዜው ለጥጧል:: ኢትዮጵያ ውስጥ ብዙ ታለንትድ የሆኑ ዘፋኞች እንዳሉ ሁሉ የሙዚቃ መሳሪያ የሚጫወቱ ግን በብዛት የሉም::

እስቲ የአቤን ልጋብዛችሁ http://www.youtube.com/watch?v=B9kq49SOBQw

ጁሀር ሰላም ብያለው:: ከዘጌው ጋር በየትኛዋ ቺክ ተጣልታችሁ ነው የምትነቋቆሩት? በሉ ነገር አብርዱና ጸዳ ያለ ሙዚቃ እያመጣችሁ አስደስቱን::

እስቲ አንድ ጥያቄ ልጠይቃችሁ:: ለመሆኑ ኢትዮጵያ ውስጥ ካሉ ዘፋኞች በጣም የምትጠሉትና ችሎታ የለውም ብላችሁ የምታስቡት ዘፋኝ ማን ነው :?:
ስራ ፈት
ጀማሪ ኮትኳች
ጀማሪ ኮትኳች
 
Posts: 65
Joined: Mon Jan 17, 2005 8:37 pm

Postby ጦምኔው » Sun Aug 26, 2012 12:35 am

ጥያቄ ለቤቱ ባለቤት:: አፍሪካ ቺክ አልነበረች እንዴ? "ማማ አፍሪካ" ስትባል እየሰማን ነው ያደግነው:: እንዴት ነው ሳንሰማ ወንድ ሆነች እንዴ? ወይስ "ፓ ፓ አፍሪካ ሌላ ትርጉም አለው?

ሙዚቃዎቻቹን ወድጄያቸዋለሁ:: ዘጌው የፌላ ብሮድዌይ እዚህ ዲሲ መጥቶ ሳይመቸኝ ቀርቶ ሳላየው አመለጠኝ:: ሙድ ያለው ዘፋኝ ነው:: እስኪ ኒው ዮርክ ተኪዶ ይከለምለታል:: ትንሽ ቀዌነት ባያጣውም በዘመኑ ግን ያንን ያህል ነጻ የሆነ አፍሪካ ውስጥ የተፈጠረ ጭንቅላት ሳያስገርመኝ አያልፍም::

ግብዣዎቻቹ ይቀጥሉ:::
ጦምኔው
ዋና ውሃ አጠጪ
ዋና ውሃ አጠጪ
 
Posts: 1529
Joined: Sun Jan 14, 2007 10:40 pm
Location: Right here

Postby ዘጌ_ዘጋንባው » Wed Sep 05, 2012 5:06 pm

ስራፈቱ..ታድያስ ፍረንዴ እንደት ሰነበትክ? ....... እኔ ያው ሌበር ዊኬንድን ያከበርኩት ከወትሮው በተለየ መልኩ ስጠገረርለት ነበር....ያው ታቅያለሽ ቀለም ካውንት ያላረገ ሰው..ሌበር ዴይ... ዱምዝዴይ...ሁሉም ዴይ እንሰራለን ነው ማጫውትክ....
ለዛሬ ኖርዝ አፍሪካ ጎራ ብንል ምን ይመስልካል? አልጄርያ ማለት ነው...
አልጄርያ ሲነሳ...ቼብ ካሊድ ...ቼብ ማሚ የሚባሉ አንጋፋ ዘፋኖች ይታወሱናል....በተለይ ካሊድ ዘፈኖቹ አገራችን ኢትዮጵያ ውስጥ ብዙ ተወዶለታል....ማርታ አሻጋሪ ወደአማርኛ እምቢ እምቢ ብላ የከረበተችው "didi" እና " አይሻ" smashing hits የሚባሉ አይነት ነበሩ.....

እና ይገርምካል በቀደም አድክም የሆነውን ዚ ዲክቴተር ሙቪ ስከልም...በጣም የሚመቸኝ ግን ዘፋኙ ማን እንደሆነ የማላውቀው ዘፈን ሳውንድታርክ ሆኖ ሰማሁትና... ይጣራ በሚል ኢንተርኔት በረበርኩልሻ.... በርብሬም አገኘሁት....

የዘፈኑ ስም "Goulou L'Mama" ሲሰኝ አቀንቃኙ ደሞ ጃላል ሀምዳዊ ይባላል... ቼብ ራያን የሚባለውን ፊቸር አርጎ ነው የሚዘፍነው.... እስኪ እንቍደሳ!

http://www.youtube.com/watch?v=DUIdM7zkcwI

ለጠቅላላ እውቀት:- በአልጄርያ ሙዚቃ ማህበረሰብ cheb የሚለው ታይትል ባንድ ወቅት ብቅ ብቅ ላሉ ዘመናዊ ዘፋኞች የተሰጠ ቅጥያ ሲሆን የአረብኛ ጥሬ ትርጉሙም "ወጣት' እንደማለት ነው...

መልካም ግዜ ....
ዘጌ_ዘጋንባው
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 176
Joined: Wed Aug 18, 2010 5:45 am


Return to Warka Culture and Literature - ዋርካ ባህልና ሥነ ጽሑፍ

Who is online

Users browsing this forum: Bing [Bot] and 1 guest