የእንግሊዝ ፕሪምየርሊግ 2012/13

ስፖርት - Sport related topics

የእንግሊዝ ፕሪምየርሊግ 2012/13

Postby ቲኪ_ታካ » Thu Aug 23, 2012 7:47 am

የእግርኳስ አፍቃርያን ይህችን ገጽ ለፕሪምየርሊግ መወያያ ትሆነን ዘንድ ከፍቻታለሁ:: እየመጣቹ ሀሳቦችን እንድንለዋወጥ እጋብዛለሁ::

ዛሬ ቼልሲ ሬዲንግን 4-2 አሸንፎ በሁለት ጨዋታ ሙሉ 6 ነጥብ አፍኗል:: ሰኞ እለት ማንቼ በኤቨርተን ባልታሰበ ሁኔታ 1-0 ተሸንፏል:: ቫንፐርሲም ለ 20 ደቂቃ ገብቶ ውር ውር ቢልም ምንም ሊፈይድ አልቻለም:: አርሰናል በሜዳው ከ ሰንደርላንድ ጋር ያለግብ አቻ ተለያይቷል:: ማንሲቲም ተንደፋድፎ ሳውዝሀምፕተንን 3-2 ሲረታ ሊቨርፑል በ ዌስት ብሮም 3 ጎል ቅሞ በባዶ ተሸኝቷል::

ካሁኑ ሞቅ ደመቅ እያለ ነው ውድድሩ:: የቼልሲው ኤዲን ሀዛርድ የስካሁኑ ግሩም እንቅስቃሴው አይን ውስጥ እየገባ ነው::
ቲኪ_ታካ
አዲስ
አዲስ
 
Posts: 17
Joined: Tue Jun 05, 2012 4:58 pm

Postby ገልብጤ » Fri Aug 24, 2012 9:29 pm

ቲኪ-ታካ የሲዝኑ ምርጥ ቡድን ማን ይመስልሀል ..ሲዝኑ ገና ቢጀመርም ባንተ እይታ ማለቴ ነው
ያልበሰለ ፖለቲከኛ ስለቀጣዩ ምርጫ ሲያስብ
የበሰለ ፖለቲከኛ ስለቀጣዩ ትውልድ ያስባል
James freeman clarke
ገልብጤ
ዋና ውሃ አጠጪ
ዋና ውሃ አጠጪ
 
Posts: 1680
Joined: Sat Jun 26, 2010 11:24 pm

Postby ቲኪ_ታካ » Sat Aug 25, 2012 4:03 am

ገልብጤ እንደምነህ?
የሲቲውን ኮች ማንቺኒን ጨምሮ ብዙ ሰዎች ማንቸስተር ዩናይትድ ባለድል ይሆናል ሲሉ ይተነብያሉ:: በበኩሌ ብዙም አልቀበለውም:: ከሮይ ኪን ወዲህ ዩናይትድ ሚድፊልዱን አሳምኖ የሚቆጣጠር ተጭዋች የላቸውም:: አምናም ይህ ችግር ነበር ከምንም በላይ ካለዋንጫ እንዲጨርሱና በተለይ ከ ሲቲ ጋ ሲጫወቱ ያያ ቱሬ እንዲፈነጭባቸው የሆነው:: ባጠቃላይ የዩናይትድ ችግር የ አይደንቲቲ እና ያጨዋወት ፕሪንሲፕል ጉዳይ ነው:: በዚ ጉዳይ በሰፊው ለወደፊቱ እንጫወታለን::
ቼልሲ ከቶሬዝ ሌላ አንድ ሁነኛ አጥቂ ቢጨምሩ ለኔ ምርጡ ቡድን እነሱ ናቸው:: ሀዛርድ. ሁዋን ማታ እና ኦስካር ሲቀናጁ ለማንም የማይመለስ ቡድን ሆኖ ነው የሚቀርቡት:: ማን ሲቲም ገናና ተጭዋች ባይገዙም የዋዛ ቲም አይደለም:: ዳቪድ ሲልቫ ባለፈው ሲዝን አጋማሽ ጀምሮ በታም ቀዝቅዞዋል:: ደግነቱ ሳሚር ናስሪ ጥሩ ፎርም ላይ ያለ ይመስላል:: የቴቬዝ መረጋጋትም ለቡድኑ ጥሩ ይመስላል:: አርሰናልን ለጊዜው ብዙም የምለው ባይኖረኝም ነገር ግን ዌንገር አሁንም ኳስ ለሚያውቁ ግሩም ተጭዋቾች አይን እንዳለው ሳንቲ ካዞርላን ከ ማላጋ ሲያስፈርም አስመስክሯል:: ከአምናው የዘንድሮው ስብስቤ ይሻላ ስላለም እስኪ በተስፋ እንጠብቃ:: ቶተንሀምም በትኩረት ልንከታተለው የሚገባ ቡድን ነው:: ኒውካስልም ስብስቡ አሪፍ ነው:: በቀደም ዴምባ ባ ያገባው ጎል አስደናቂ ነው:: ከሀገሩ ሴኔጋል ልጅ ፓፒስ ሲሴ ጋር ተራ ጎል ላያገቡ የተማማሉ ይመስላል:: ሊቨርፑል በነገራችን ላይ አሰልጣኙ ብራንደን ሮጀርስ በጣም አሪፍ አይዲያ አይለው አሰልጣኝ ነው:: እንደባርሳ ኳስ ቁጥጥር ላይ ያተኮረ ፉትቦል ሊጫወት ይሞክራል:: ግን ችግሩ ወደተግባር ለመቀየር በተለይ ያሁኑ የሊቨርፑል ስብስብስ ላይ እጅግ ይከብደዋል:: ስለዚ ታይም ይፈልጋል:: አማን ስዋንሲ ቡድንን ሲያሰለጥን አጨዋወታቸው በጣም ማራኪ ነበር::


ገልብጤ አንተስ ምን አስተያየት አለህ?
ቲኪ_ታካ
አዲስ
አዲስ
 
Posts: 17
Joined: Tue Jun 05, 2012 4:58 pm

Postby ገልብጤ » Sun Aug 26, 2012 8:58 pm

ቲኪ -ታካ እንደምን አለህ የስፖርት ወዳጅ

እኔ እንኳን እንደሚመስለኝ የዝሂ ሲዝን ባለድሎች ማንዩትድ ወይ ከቸልሲ አያልፍም ባይ ነኝ ምክኒያቱም ሁለቱም ቡድን እንዳየሁት ከሆነ ምርጥ ተጫዋቾች ነው ያስፈረሙት ...ካግዋን ያዩታል ..ሀዛርድንስ ብትል ቫንፔርሲ ጥሩ ጥሩ ኳስ ከገኘ ወደጎል የሚቀይር ተጫዋች ነው ...ከላይ ስለማንቸስተርም ያልከው ልክ ነህ ማንዩትድ መሀል ክፍሉን ከሮይኪን በኍላ ሊያጠናክረው አልቻለም ምኪንያቱም እሱን እና ፖልስኮልስን የሚተካ ተጫዋች መግኘት በጣም ከባድ ነው
ያልበሰለ ፖለቲከኛ ስለቀጣዩ ምርጫ ሲያስብ
የበሰለ ፖለቲከኛ ስለቀጣዩ ትውልድ ያስባል
James freeman clarke
ገልብጤ
ዋና ውሃ አጠጪ
ዋና ውሃ አጠጪ
 
Posts: 1680
Joined: Sat Jun 26, 2010 11:24 pm

Postby ቲኪ_ታካ » Tue Aug 28, 2012 5:37 pm

ጥሩ ብለሀል ገልብጤ
የሳምንቱ ማለቅያ ጨዋታዎችን እንዴት አየካቸው? በኔ በኩል ሊቨርፑል ማንሲቲን ሁለቱንም ጎሎች ጊፍት ሰጥዋቸው ነው የሚያስብለኝ:: ;አሁኑ ሊቨርፑሎች ነፍስ እየዘሩም ይመስላል ያው ቆየት ብለን የቡድኑን እውነተኛ ሌቭል እንረዳለን:: ማንችስተር ዩናይትድ ከፉልሀም ጋ አይረገው ጨዋታ ደሀን ነበር ግን የከላካይ መስመር በረኛውን ጨምሮ አሳማኝ አይደሉም:: ቪዲች ለረጅም ግዜ ከጨዋታ ስለራቀ ወደቀድሞው ብቃት ለመመለስ ጥቂት ኮምፕቲቲቭ ጨዋታዎችን ያሻዋል:: በረኛው ዴቪድ ደሄየ ቀጥታ ወደጎል የሚሻሙ ኳሶችን ዶሚኔት አርጎ የማክሸፍ ነገር አልሆንልህ ብሎታል:: በቀላሉ የሚገፋና አካሉም ቀጭን ስለሆነ ለዚህ ችግር ደጋግሞ ሲጋለጥ ይታያል ግን ከዛ በስተቀር በሌላ ነገሮቹ እንከን የማይወጣለት በረኛ ነው:; ቫንፐርሲ አስደናቂ ጎል አግብቷል:: በይበልጥ ከተጫዋቾቹ ጋ ሲግባባ ብዙ ሊጠቅማቸው ይችላል:; ቼልሲ ከትልልቆቹ ቡድኖች ጥሩ አቋምና ጥንካሬ እንዳለው ከሶስት ጨዋታ 9 ሙሉ ነጥብ በመያዝ አስመስክሯል:: አጨዋወታቸውም ግልጽ በሆነ መልኩ ከአምናው ተቀይሯል:: በተለይ ወጣቱ የቤልጅየም ኢንተርናሽናል ኤዲን ሀዛርድ ኮንፊደንሱ ሙሉ የሆነ ግሩም ተጭዋች ነው:; ከራሱም አልፎ በዙርያው ያሉትን ተጭዋቾች ጥሩ ማድረግ የሚችል አጨዋወትን ነው የሚከተለው:: ፈጣን አብዶኛ እና ደፋር ልጅ ነው:: ስዋንሲ አሁንም ቢውቲፉል ፉትቦል እየተጫወቱ ይገኛሉ:: በቀደም ዌስትሀምን ሲያቸንፉ ልክ ባርሴሎናን ነበር የሚመስሉት:: ሰስክ ፋብሪጋስ እራሱ በትዊተር መልእክቱ የስዋንሲ አጨዋወት አድናቂ መሆኑን ጽፎዋል::
ቲኪ_ታካ
አዲስ
አዲስ
 
Posts: 17
Joined: Tue Jun 05, 2012 4:58 pm

Postby HD » Wed Sep 12, 2012 5:54 pm

አቦ ባካቹ አትፈላሰፉ ዋንጫው ከሊቨርፑል እጅ አይወጣም,
HD
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 114
Joined: Mon Jul 12, 2010 3:11 am


Return to Warka Sports - ዋርካ ስፖርት

Who is online

Users browsing this forum: No registered users and 1 guest