ሚስትዬዋ

The Love Forum (love, relationship) (የኔ ቆንጆ እንተዋወቅ :-)

Postby ኪኮ » Thu Aug 23, 2012 5:09 pm

የስታር ባክስ ሰራተኝች ምን ላምጣልህ ይላሉ ? ራስህ ሄደህ ታዛለህ እንጅ እንደሬስቶራንት አንተ ጋር መጥተው ምን እንታዘዘዝ ይላሉ ?


ካሸሯ ያለችበትን ባንኮኒ ተደግፎ ከቆመ...... አዎን ይላሉ.......What Can I get for you ? ብላ ልትለው ትችላለች ? ይህ ምኑ ነው የሚያስገርመው ???? ራስህ ሄደህ ተራ ጠብቀህ ተሰልፈህ ብታዝም ..... የምትፈልገውን ነገር ይህን እፈልጋለሁ ከማለትህ በፊት ........ወረፋው ሲደርስህ What Can I get for you ? የምትለዋን ጥያቄ መስማትህ አይቀሬ ነው
ኪኮ
ጀማሪ ኮትኳች
ጀማሪ ኮትኳች
 
Posts: 62
Joined: Fri Aug 05, 2005 9:33 am
Location: ethiopia

Postby ገደል » Thu Aug 23, 2012 5:31 pm

ሌላው ቢቀር መሀይምነትህን እንኩዋ የማታውቅ የለየልህ ---- ሹጣም ነህ:: እዚህ የምናወራ ለአንተ የሚከብድ ስለሆነ:: አፍህን ዝጋ ሹጥህን አታንጠባጥብን:: በከቻ አጋስስ
ገላጋይ-1 wrote:
ገደል wrote:ባንተ ቤት ተናግረህ ሞተሀል....ዝቃጭ ብጤ ነህ:: መጀመርያ ታሪኩን በደምብ አንብብ ከዚያ አስተያየት ስጥ::
ልጁ ያለው ቦታ ስላጣሁ ባንኮኒ ደገፍ ብዬ ቆምኩ ካለ በሁዋላ ከዚያ አስተናጋጅዋ ጠየቀቺኝ ነው:: የስታር ባክስ አስተናጋጆች ከባንኮኒው ወጥተው የተቀመጡን ሰዎች ምን ልታዘዝ አይሉም:: ግን ባንኮኒ ላይ የቆመን ሰው ይጠይቃሉ:: እንዴት ነው ለማዘዝ ባንኮኒው ጋ ስትሄድ ምን ልታዘዝ ብለውህ አያውቁም? አትዘባርቅ.....ልጁ ታሪኩን ይቀጥልበት::
ገላጋይ-1 wrote:
ከርታታው88 wrote: ስታርባክስ..... ወዲያው አስተናጋጁዋ ምን ላምጣልህ አለች:: ቆይ የምጠብቀው ሰው ስላለ ትንሽ ታገሺ ብያት ሄደች::


የስታር ባክስ ሰራተኝች ምን ላምጣልህ ይላሉ? ራስህ ሄደህ ታዛለህ እንጅ እንደሬስቶራንት አንተ ጋር መጥተው ምን እንታዘዘዝ ይላሉ?

ጽሁፍህን ጥሩ እየተከላተልኩት ነበር... ይህንን ሳይ ግን ደበረኝ...ገደል አፍ

ምን ላምጣልህ አለችኝ ነው ያለው .... አንተ ክፍት አፍ .... መቀመጫ አጥቶ ከሆነ እንኩዋን ምን ልርዳህ እንጅ 'ምን ላምጣልህ' አትለውም ...

..... ደግሞም ታሪኩ የማይመስል ነገር ነው .... እውነት ቢሆንም ብዙም የሚያስደስት አይደለም ... የሰው ሚስት ማማገጥ ... ያች ሸሌ ነገር ... ለይስሙላ ባል አላት .... but she is a prostitute ... ብዙ ሀበሾች አሉ የሱዋ አይነት married prostitutes ...

ገደል አፍ.... ሁለተኛ እንዳትመልስልኝ አንተ የኮንዶም ትራፊ ....
ገደል
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 489
Joined: Sat Jan 02, 2010 12:03 am

Postby ሳምራውው33 » Thu Aug 23, 2012 10:20 pm

እኔ የሚመስለኝ ግምት እንደሚከተለው ነው ::

ሴትየዋ እና ባልዋ ዘመናዊ ተብለው ከሚመደቡ ባልና ሚስቶች መካከል ናቸው :: ባልየው ሳያውቅ እንዳይመስልህ አንተ ጋር ስትመጣ ያውቃል ነገር ግን ከላይ እንዳልኩህ ነው ምንም ነገር እንደማታደርግ እስዋም እሱም ያውቃሉ ግፋ ቢል ጉንጭ ለጉንጭ መሳሳም ነው ስለዚህ ወዳኛለች የሚል ሀሳብ እንዳይኖርህ :: ነገር ግን እንደነገረችህ ወይ ለምታውቀው ሰው ወይንም ለቤተሰብዋ ልትድርህ አስባለች :!: :!: :!: ለትዳር ዝግጁ ነህ ወይ :?: ከሆነ ከሴትየዋ ጋር በየቀጠሮው ተመላለስ አለበለዚያ ግንኙንትህን አቁም ::
ሳምራውው33
ዋና ኮትኳች
ዋና ኮትኳች
 
Posts: 530
Joined: Thu Jun 21, 2007 12:23 am

Postby ጨላጣው » Tue Aug 28, 2012 7:46 pm

ከርታታው የት ጠፋህ.......ተከረቸምክ እንዴ?
kifu aynkan
ጨላጣው
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 434
Joined: Fri Mar 17, 2006 5:18 pm

Postby ሓየት11 » Tue Aug 28, 2012 8:31 pm

እዚህ ቤት የሚመላለሰው ቢበዛ ... ምንድነው ነገሩ ብዬ ገባሁ ... ገባሁና የሰው ተራነት አይቼ ቀረሁ:: ... ዝም ብዬ ግን አልወጣም ... የመሰለኝን ጣል አደርጋለሁ::


ከርታታው ... ትረካው እውነት ከሆነ ... በበኩሌ አሳፋሪ ነገር ነው:: ... ዩ ኖው ዋይ? ... በአንድ አጋጣሚ ያገኛሀትን ባላትዳር ሴት ... በእርስዋ ትውውቅ ... ወደዚህ መድረስህ የሚገርም ነገር ነው:: ... ሲጀመር ለእንደዚህ አይነት ቀጠሮ ፖሰቲቭ መልስ መስጠት አልነበረብህም:: ... ሌሎቹ እንደሚሉት ለሌላ (ዘመድ ምናምን) ልትዳር አስባ ከሆነ ... ወይም ... ወንድምነትህን ፈልጋው ከሆነ ... ወዘተ ... ብቻዋን ልትቀጥርህ አይገባም ነበር:: ... ሀሳቧ ያ ቢሆን ኖሮ ለምሳሌ ከባለቤቷ ጋር ቤቷ ወይም ውጪ ብትጋብዝህ ... የበለጠ ውጤታማ ይሆናልና:: ... ሆኖም የተለየ ፍላጎት ቢኖር ነው እንግዲህ ... ብቻዋን ከአንድም ሁለቴ ልታገኝህ የምትሞክረው:: ... ዘ ፖይንት ኢዝ ... ሴትዮዋ እንግዲህ ቤቷ ውስጥ ያለውን ጉድ አንተ አታውቅላትም:: ... ሺ መይ ዲዛየር ዩ ... መይ ቢ ፎር ፈን ... ኦር ... መይ ቢ ፎር ኤክስተንድድ ሪ/ሽፕ :: ... ነገር ግን ... አንተ በቤትዋ ውስጥ ያለባትን ነገር ሳታውቅና ... በተለይ ደግሞ ባለትዳር (ያውም በማንኛውም መስፈርት ካንተ የተሻለ ወንድ ባለቤት ) መሆኗን እያወቅ ... ብትገባበት .... አይ አም ቴሊንግ ዩ ዚስ ... ዩ ሀቭ ኖ ሪስፔክት ፎር ሜሬጅ :!: ... የሰውን ትዳር የማያከብር ሰው ... አይ ዳውት ... የራሱንም ለማክበሩ:: ... እሷም እንዲሁ ... ካንተ የተሻለ ለሚመስለው "ባሏ" ያልታመነች ... ነገ ላንተ ልትታመን አትችልም:: ... ሳስበው .... መፈላለግ እንጂ ፍቅር በማሀላችሁ የለም ...:: ... እናም ቢ ጀንትል! ... ለትዳሯ የበለጠ እንዳትታመን ... ሰበብ አትሁናት:: ... ለውጫዊ ውበቷ ብለህ ... ላንተም ነገ ሊጸጽትህ የሚችል ነገር ከመስራት ተቆጠብ:: ... ውስጡ ካላማረ ውበት ምንድነው? ...ጨላጣው wrote:ከርታታው የት ጠፋህ.......ተከረቸምክ እንዴ?
ሓየት11
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 2945
Joined: Sun Apr 06, 2008 7:34 pm
Location: ላን'ሊይ

Postby ጁሀር2012 » Fri Aug 31, 2012 2:53 am

ባክህ አታስቦካው አንተ እንደዚህ አይነት ቻንስ ስላላጋጠመህ የተበሳጨህ ይመስላል ወይንም ሚስትህን አንዱ እንደ ከርታታው አይነት ፋስት ሰው ነጭቶብሀል ማለት ነው. :lol: አይዞን ቀልድ ነው ! ግን ስማ ፍቅር ማለት ረቂቅ የሆነ በ2 ኦፖዚት ጾታዎች መካከል የትም ቦታና በማንኛውም አጋጣሚ ሊያጋጥም የሚችል ታላቅና ረቂቅ ጸጋ እንደሆነ ማወቅ አለብህ. ስለዚህ በጋብቻ, በኑሮ ሁኔታ, በዘር እንዲያውም ባጠቃላይ በኮመን ሴንስ ሁላ ልንገልጸው የማንችል ከላይ የተሰጠ ጸጋ ነው. ልጁ እስከወደዳት ድረስና እስዋም እስከወደደችው ድረስ ባልዋን ሁላ ፈታ እሱን ማግባት መብትዋ ነው. ሰው አብሮ የሚኖረው ፍቅር እስካለው እና በመፈቃቀድ ላይ ብቻ የተሞረከዘ እንደሆነ ነው. ሰውን ልጅ በጋብቻ ምክንያት ብቻ ፍቅርን ኢምፖዝድ ማድረግ እንደማይቻል ግልጽ ነው. ነገሩ ለባልየው ምን ያህል ከባድና ስሜትን የሚነካ ነገር እንደሆነ ግልጽ ነው ነገር ግን አንዳንድ ግዜ የውነታውን አለም መጋፈጥ የግድ የሚልበት ጊዜ አለ.
ጁሀር2012
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 113
Joined: Sun May 27, 2012 9:06 pm

Postby ሓየት11 » Fri Aug 31, 2012 3:00 pm

ሰላም ድዩ ጁሀር

እውነቱን ለመናገር እኔ እንኳን አንተ የምትጽፋቸውን በቁምነገር አንብቤያቸው አላውቅም ... አይ ሆፕ ቅር እንደማይልህ ... ምክንያቱም አንተም ታውቀዋለህ ... በቁምነገር እንደማትጽፋቸው ... ቅቅቅ

እዚህ ጋ ስላልነሳኸው ነገር ... ስለኔና ስለባለቤቴ በተመለከተ ወደ ጎን ትቼ (አስፈላጊ ሆኖ ሲገኝ ወደፊት ልንተርከው እንደምንችል እየጠቆምኩኝ) ... ከርታታውን በሚመለከት ስለጻፍከው መልስ ልስጥህ::

አንደኛ በጣም ያሳቀኝ ነጥብ ... እንደ ከርታታው ፋስት ... ስትል ... የምሬን ነው የምልህ ... ቅቅቅቅ ... በጣም ነው የሳቅኩት:: ... አሁን ጸሀይ ጋር ... አንሶላ ለመጋፈፍ ቢበቁ ... አወጣችው ነው የሚባል አወጣት ... ቅቅቅ ... ፋስት ትላለህ እንዴ ደግሞ ... አንዲት ባለትዳር ሴት ... ባሏን ከጎን አስቀምጣ ... በጠጅ የጠበሰችውንና በራሷ ግፊት ለቀጠሮ የበቃን ሰው ... ፋስት ማለት ምን ማለት ነው ... :lol: :lol: የናንተ ፋስትነት እንደዞብል ... የአራዳ ዘመን አራዳነት ነው እንዴ? ... ፍሬንድ ዘመኑ 'ኮ ተለውጧል ... ጨዋታውም እንዲሁ ተለውጧል::

ስማ ልንገርህ ... ገና ሀይስኩል ሳለሁ ነው ... አንዱ የፒያሳ "ጎዳና ተዳዳሪ" ... አራዳነት አውቆና ቀድሞ መገኘት እንደሆነ ያስተማረኝ ... በኢቲቪ መቶ ሀያ ፕሮግራም በኩል ... የምሬን ነው:: ... ለድሮ ሰዎች ... ሰክሮ መንደፋደፍ ... ከሸሌ ጋር ውቤ በርሀ ላይ መጋፋት ... በጠለፋና በምናምን አስገድዶ መድፈር ... ወዘተ ... የአራዳነት መገለጫው ነበር ... ቅቅቅ ... ኋላም HIV + ሆኖ መገኘትም እንደ አራዳነት የሚታይበት ዘመን ነበር ... ቅቅቅ አሁን ወንድሜ ... አራዳነት ስሙም ራሱ ይደብራል ... የገባው ነቄ ምናምን ... ሲባል እንጂ አራዳ ሲባል ... የዞብል አይነት የዘኬ ሊቃውንትን ነው የሚያስታውሰን ... ቅቅቅ

እና ምን ለማለት ነው ... ከርታታው ራሱንም ለመግለጽ እንደሞከረው ... ትንሽ "አራዳነት" ካለበት ... ሂ ኒድስ ቱ ዱ ዘ ራይት ቲንግ ... :!: ... ባለትዳርን ማማገጥ ... አራዳነት አይደለም:: ... በተለይ ደግሞ ... እሷ ጠባሽ ... እሷ ቆስቋሽ ሆኖ ... ካወጣችው ... ቅቅቅ ... ይቅር በቃ .. አልጨርሰው

ምን ይላሉ መሰለህ ደግሞ ... ውሀ መጠጫ ብርጭቆህን ለመስበር ምንም ጉልበትም ሆነ ጥበብ አያስፈልግህም ... ከእጅህ ለቀቅ ማድረግ ብቻ ነው:: ... ልስራው ብትል ግን ... ቀናትን ምናልባትም ሳምንት ይፈጅብሃል ... ያውም መስራቱን የምትችልበት ከሆነ ነው:: ... ፊዚስቶች እንደዚህ አይነት ሁኔታ ሲገልጹ ... ኢንትሮፒ ምናምን የሚል ነገር ጠቅሰው ... ኬኦስን መፍጠር ቀላል ሲሆን ... ኦርደርን ማምጣት ግን በጣም ከባድ ነው:: ... የተሰበረውን ብርጭቆ ወደ ነበረበት ለመመለስ (ኦርደር ለማምጣት)... ብዙ ጉልበት ጥበብ ምናምን ይጠይቃል:: ... ጤነኛውን ብርጭቆ ለመስበር (ኬኦስ ለመፍጠር) ግን ... ምንም የሚከብድ አይደለም:: ... ትዳርን አክብሮ የትዳርን ኦርደር መፍጠር መቻል ... ለአንድ ማህበረሰብ ከባድ ራስ ምታት ነው:: ... ትዳርን መበተን ግን ... በጣም ቀላል ነገር ነው:: ... በህይወትህ አንድ ትዳር ብቻ ነው ስኬታማ ማድረግ የምትችለው:: ... ትዳር ለመበተን ግን በቀን ምናልባትም ከአስር በላይ ሊሳካልህ ይችላል:: ... ሶ አውቆና ነቅቶ መገኘት ስንል ... ለትዳርና ለቤተሰብ ሀላፊነት የሚሰማህ ዜጋ መሆንን ይጠይቃል:: ... እያንዳንዱ ትዳሩን ቢያከብር ... ልጆቹን በስነምግባር እያነጸ ቢያሳድግ ... አሁን የምታያቸውን የግለሰብ, የማህበረሰብ, የአገር ወዘት ችግሮች በብዙ ሺ እጥፍ በቀነሱ:: ...

ፍቅር ነው ምናምን ስላልከው ነገር ... እኔ የተረዳሁት መፈላለግ እንዳላቸው እንጂ ፍቅር አይመስለኝም:: ... ከጽሁፉም እንደምታየው ... ፍቅር የያዘው ሰው እንዳልሆነ ነው:-
በእህትነት ቢሆን ደስ የሚለኝ ይመስለኛል :: በሮማንሱም ቢሆን አይከፋኝም ::


ፍቅር ቢሆን ምን ማድረግ አለበት ሌላ ጉዳይ ነው ... እኔ ይህ ይሁን ይህ አይሁን ማለት አልችልም:: ... አሁን ባለው ሁኔታ ግን ... መራቅ ነው ያለበት:: ... ወይም ደግሞ የሷ ፍላጎት ምንም ይሁን ምን እሱ ወደ እህትነት መቀየር ያለበት ይመስለኛል:: ... አት ሊስት እኔ ብሆን የማደርገውን ነው እንግዲህ እያወራሁ ያለሁት::ጁሀር2012 wrote:ባክህ አታስቦካው አንተ እንደዚህ አይነት ቻንስ ስላላጋጠመህ የተበሳጨህ ይመስላል ወይንም ሚስትህን አንዱ እንደ ከርታታው አይነት ፋስት ሰው ነጭቶብሀል ማለት ነው. :lol: አይዞን ቀልድ ነው ! ግን ስማ ፍቅር ማለት ረቂቅ የሆነ በ2 ኦፖዚት ጾታዎች መካከል የትም ቦታና በማንኛውም አጋጣሚ ሊያጋጥም የሚችል ታላቅና ረቂቅ ጸጋ እንደሆነ ማወቅ አለብህ. ስለዚህ በጋብቻ, በኑሮ ሁኔታ, በዘር እንዲያውም ባጠቃላይ በኮመን ሴንስ ሁላ ልንገልጸው የማንችል ከላይ የተሰጠ ጸጋ ነው. ልጁ እስከወደዳት ድረስና እስዋም እስከወደደችው ድረስ ባልዋን ሁላ ፈታ እሱን ማግባት መብትዋ ነው. ሰው አብሮ የሚኖረው ፍቅር እስካለው እና በመፈቃቀድ ላይ ብቻ የተሞረከዘ እንደሆነ ነው. ሰውን ልጅ በጋብቻ ምክንያት ብቻ ፍቅርን ኢምፖዝድ ማድረግ እንደማይቻል ግልጽ ነው. ነገሩ ለባልየው ምን ያህል ከባድና ስሜትን የሚነካ ነገር እንደሆነ ግልጽ ነው ነገር ግን አንዳንድ ግዜ የውነታውን አለም መጋፈጥ የግድ የሚልበት ጊዜ አለ.
ሓየት11
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 2945
Joined: Sun Apr 06, 2008 7:34 pm
Location: ላን'ሊይ

Postby ቂቅ » Fri Aug 31, 2012 6:41 pm

የዋሆች ከርታታው ልብ-ወለድ እየተለማመደ እንደሆነ ግልጽ ነው :wink: ዋርካ ሳይበር በዲያስፖራው ዘንድ በደንብ ይታወቃል ሰትዮዋም ባልዋም ይህን ታሪክ ሊያነበው እንደሚችል መገመት አያቅተውምም ነበር እውነተና ገጠመኝ ቢሆን:. ያውም ገና ያጋጣሚውን መጨረሻ ሳያውቅ አይጽፈውም ነበር:: እኔ የጓደኛየን ገርል ፍሬንድ ውስልትና ታሪኬን የቆጠብኳት ወድጄ ነው እንዴ :wink: አሁን ከርታታው ልብወለድዋን እንዴት እንደሚጨርሳት ጠፍቶበት ጠፋ :lol:
ቂቅ
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 144
Joined: Wed Aug 08, 2012 4:41 pm
Location: Saturn

Postby ሓየት11 » Fri Aug 31, 2012 7:25 pm

እኔኮ ሰለ ሚቀጥለው ቀጠሮ ምን ላድርግ ምናምን ቢል የምር መስሎኝ ነው ... ባይሆንም ግን ... መጥፎ መልዕክት መተላለፍ የለበትም:: ... ነገርዬው ፊክሽን ከሆነ ... የኔን ጽሁፍ ... ለፊክሽን የተሰጠ ትችት አድርገህ ውሰደው::

የኢትዮጵያ ድርሰት , ልበወለዱም ብትል ግጥሙ, ጽልመትን ተንኮልን ክፋትን ብልግናን ባጠቃላይ ስነ.ምግባር የጎደለው ኔጌቲቭ ነገር ይበዛበታል ... ያንን መመከት አስፈላጊ ነው ብዬ አምናለሁ::

ቂቅ wrote:የዋሆች ከርታታው ልብ-ወለድ እየተለማመደ እንደሆነ ግልጽ ነው :wink: ዋርካ ሳይበር በዲያስፖራው ዘንድ በደንብ ይታወቃል ሰትዮዋም ባልዋም ይህን ታሪክ ሊያነበው እንደሚችል መገመት አያቅተውምም ነበር እውነተና ገጠመኝ ቢሆን:. ያውም ገና ያጋጣሚውን መጨረሻ ሳያውቅ አይጽፈውም ነበር:: እኔ የጓደኛየን ገርል ፍሬንድ ውስልትና ታሪኬን የቆጠብኳት ወድጄ ነው እንዴ :wink: አሁን ከርታታው ልብወለድዋን እንዴት እንደሚጨርሳት ጠፍቶበት ጠፋ :lol:
ሓየት11
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 2945
Joined: Sun Apr 06, 2008 7:34 pm
Location: ላን'ሊይ

Postby ጁሀር2012 » Fri Aug 31, 2012 8:10 pm

በመጀመርያ ደረጃ ጽሁፌን ለማንበብ ባለመፈለግህ አልከፋም ምክንያቱም እንዳልከው ጁሀር2012 የሚለው ኒክ የሚታወቀው በብልግና ስለሆነ ያው ኒክ ኔም ቀይሬ ከች እስካላልኩ ድረስ ስለምጽፈው ጽሁፍ በቁም ነገር ቦታ እንደማይሰጠው አቃለው. በቃ አሪፍ አዲስ ኒክ ኔም እያፈላለኩ ስለሆነ እስቲ ታገሱኝ. :lol: ወደ ከርታታው ጉዳይ ስገባ ከላይ በጻፍከው ፖይንቶች ሁሉ እስማማለው. በእድሜ ይሁን በኤክስፒርያንስ ብዛት ባላቅም በጣም በሳልና ግሩም አስተያየት ነው.
ጁሀር2012
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 113
Joined: Sun May 27, 2012 9:06 pm

Postby ቂቅ » Sat Sep 01, 2012 1:43 am

ልክ ነህ ያንተው አሁን ገባኝ 'ታሪኩ እውነት ከሆነ' ብለህ ነው የመከርከው:: ከርታታው ግን ልብ ወለዱን ለመጨረስ ማጣፊያው አጥሮት እየተንከራተተ ያለበት ሁኔታ ላይ ያለ ይመስላል :(

ሓየት11 wrote:እኔኮ ሰለ ሚቀጥለው ቀጠሮ ምን ላድርግ ምናምን ቢል የምር መስሎኝ ነው ... ባይሆንም ግን ... መጥፎ መልዕክት መተላለፍ የለበትም:: ... ነገርዬው ፊክሽን ከሆነ ... የኔን ጽሁፍ ... ለፊክሽን የተሰጠ ትችት አድርገህ ውሰደው::

የኢትዮጵያ ድርሰት , ልበወለዱም ብትል ግጥሙ, ጽልመትን ተንኮልን ክፋትን ብልግናን ባጠቃላይ ስነ.ምግባር የጎደለው ኔጌቲቭ ነገር ይበዛበታል ... ያንን መመከት አስፈላጊ ነው ብዬ አምናለሁ::

ቂቅ wrote:የዋሆች ከርታታው ልብ-ወለድ እየተለማመደ እንደሆነ ግልጽ ነው :wink: ዋርካ ሳይበር በዲያስፖራው ዘንድ በደንብ ይታወቃል ሰትዮዋም ባልዋም ይህን ታሪክ ሊያነበው እንደሚችል መገመት አያቅተውምም ነበር እውነተና ገጠመኝ ቢሆን:. ያውም ገና ያጋጣሚውን መጨረሻ ሳያውቅ አይጽፈውም ነበር:: እኔ የጓደኛየን ገርል ፍሬንድ ውስልትና ታሪኬን የቆጠብኳት ወድጄ ነው እንዴ :wink: አሁን ከርታታው ልብወለድዋን እንዴት እንደሚጨርሳት ጠፍቶበት ጠፋ :lol:
ቂቅ
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 144
Joined: Wed Aug 08, 2012 4:41 pm
Location: Saturn

Postby ከርታታው88 » Wed Dec 05, 2012 9:57 pm

ዋርካዎች.....ጠፋሁ አይደል? ምን ላድርግ መወጣጠር በዛ:: በጠፋሁበት ሳምንታት ከሚስትዬዋ ጋር ለበርካታ ጊዜ ተገናኝተናል:: በዝርዝ ልሄድበት ባልችልም ከጊዜ አንጻር አለፍ አለፍ እያልኩ ዋና ዋናውን አጫውታችሁዋለሁ:: ይህን የማደርግበት ምክንያት አለኝ::
በመጀምርያ አንድ አንዶቻችሁ እንዳላችሁት ድርጊቱ ልብወለድ እንዳልሆነ አረጋግጥላችሁዋለሁ:: ሁለተኛ ለእናንተ ለማጫወት ያነሳሳኝ የሚትዬዋም ሆነ የእኔ ስውርነት የተጠበቀ ይሆናል ብዬ ስላመንኩ ነው:: እንግዲህ ይህን ካልኩ ዘንድ ያለፉትን ሳምንታታ ድርጊቶች በሚቀጥለው ጽፉፌ ገረፍ ገረፍ አደርግላችሁዋለህ:: stay tuned
ከርታታው88
ዋና ኮትኳች
ዋና ኮትኳች
 
Posts: 530
Joined: Tue Jan 10, 2006 7:43 pm

Postby የቦግዪ » Wed Dec 05, 2012 10:14 pm

ታሪክ ጀምሮ መጥፋት ምን የሚሉት ነው?
Gotta live my life like there's one more move to make.
የቦግዪ
አዲስ
አዲስ
 
Posts: 40
Joined: Sun Oct 28, 2012 6:56 pm

Postby ከርታታው88 » Thu Dec 06, 2012 7:32 pm

እንደተለመደው ሲክ ሊቭ ጠይቄ ሀሙስ እለት ሙሉ ቀን ከሥራ ቀርቼ እቤት ጉድ ጉድ እያልኩ ነበር: ልክ 11:45 ጠዋት ሥልክ ሲጮህ:: ሥልኬ ኪቺን ጠረጴዛ ላይ ስለነበር ዘለል ብዬ አነሳሁት: ሚስትዬዋ ነበረች:: ሚስትዬዋ እያልኩ ከምጠራት ከአሁን በሁዋላ ጉዋደኛዬ ልበላት መሰልኝ:: "መንደራችሁ እንዴት አስቸጋሪ ነው እባክህ? እስቲ ምራኝ አፓርትመንትህ የቱ ጋ ነው::" አለች እኔም ሰላምታ አይቀድምም ብዬ ሳልጨርስ...."ለሰላምታው ብዙ ጊዜ አለን...አሁን አቅጣጫውን ነገረኝ" አለች እንደመቸኮል ብላ:: ቆይ የቱ ጋ ነው ያለሺው እኔ እመጣለሁ ብያት ነገርቺኝና እዚያ ድረስ ራመድ ራመድ ብዬ ሄድኩና ይዤያት አፓርትሜንቴ ገባን:: እንደገባቺም ቆም አለቺና...."እንዴት ጽድት ያለቺና የምታምር ቤት አለቺህ" ስትል እኔም በሆዴ አይ ትናንት ከትናት ወዲያ ባየሺው አልኩና አመሰግናለሁ በይ ቁጭ በይ አልኩዋት:: "እንዴ የረባ ሰላምታ አልተለዋወጥንም አልቺን ያንን የተለመደውን አደንዛዥ ሀግ ከጉንጭ መተሻሸት ጋር ስትሰጠኝ መላ ሰውነቴ ልክ ኮረንቲ እንደያዘው ሰው ተብረከረከ:: እኔ ከደሰብኝ ድንገተኛ መብረክረክ ለማገገም ስጣጣር እሱዋ አጠገቡዋ ካለው ሶፋ ላይ ቁጭ አለች:: እንደማገገም ስል ወደ ኪቺን አቀናሁና ሰሞኑን አንዲት ኢትዮጵያዊ ለምኜ የጋገረቺኝን ዳቦ ቆረስ ቆረስ አድርጌ በሳህን ይዤ ብቅ አልኩ:: ውይ የእኔ ጉድ መኪና ውስጥ እቃ ነበር ረስቼው አልቺና ስትነሳ ለምን እኔ አላመጣልሽም አልኩዋት:: አይ አብረን እንሂድ አለቺና ሄደን ይዛ የመጣቺውን አምባሽ የሚመስል ዳቦ እና አንድ ጠርሙስ ሜርሎት ሬድ ዋይን አውጥታ ሰጠቺኝ:: እኔም ያቺ ግድርድርነቴ አለች አይደል...እስቲ አሁን ምን አደከመሽ እኔ እኮ ሁሉንም አዘጋጅቼ ነበር ስላት ቀበል አድርጋ....አይ እንግዲህ..... እኔ አታዘጋጂም ብዬ አይደለም..ደስታዬን ለመግለጽ ያህል ነው...ደሞ ምን ቁምነገር አለው ብለህ እያለች እቤት ተመለሰን:: ቁልፉዋን እቦርሳዋ ውስጥ ጣል አደረግቺና እዚያው ሶፋ ላይ ቁጭ አለች:: እኔም የመጣልኝን ዳቦና ዋይን ላስቀምጥ ኪችን ገባሁ:: ከዚያም የሚጠጣ ነገር እያዘጋጀሁ እያለሁ ከመቀምጪዋ ተነስታ ...ምን እያደረክ ነው ቁጭ በልና እንጫወት ምግቡን ቀስ ብለን እናዘጋጀዋለን አለቺና አንድ ጠርሙስ ፔሪ ይዛ ወደ መቀመጫዋ እያመራች በል አንተም አንድ ነገር ያዝና ትንሽ ቁጭ ብለን እንጫወት አለች:: እኔም ፈጠን ብዬ እሺ አልኩና አንድ የሄኒከን ጣሳዬን ይዤ ሄዱኩና ከፊት ለፊቱዋ ባለው ሶፋ ላይ ጉብ አልኩ: የሚከተለውን ባለማወቅ:: "ቢራ በጠዋት....!!!" አለቺና ወዲያው ሰአቱዋን መልከት ብላ "እንዴ 12 አልፎዋልና" ብላ እንደ መገረም አለች::
ዛሬ እዚህ ላይ እናቁም::
ከርታታው88
ዋና ኮትኳች
ዋና ኮትኳች
 
Posts: 530
Joined: Tue Jan 10, 2006 7:43 pm

Postby ከርታታው88 » Wed Dec 19, 2012 9:31 pm

ጊዜ ጠፋ እባካችሁ
ከርታታው88
ዋና ኮትኳች
ዋና ኮትኳች
 
Posts: 530
Joined: Tue Jan 10, 2006 7:43 pm

PreviousNext

Return to Warka Intimate - ዋርካ ፍቅር

Who is online

Users browsing this forum: Google [Bot] and 6 guests