ፉገራ...ትረባ...ጭውውት...ነቆራ...ዘዘገደው

The Love Forum (love, relationship) (የኔ ቆንጆ እንተዋወቅ :-)

ፉገራ...ትረባ...ጭውውት...ነቆራ...ዘዘገደው

Postby ዘጌ_ዘጋንባው » Thu Sep 13, 2012 3:23 am

እንደምን አመሻቹ...ያው እኔ ጋ ምሽት ስለሆነ ሁላቹንም በደምሳሳው እንደምናመሻሻቹ ስል ሆድ እንደማይብሳቹ በማሰብ ነው.....
በነገራችን ላይ አዲስ አርስት ስለከፈትኩ ሶሪ....ምክንያቱም አዲስ ሩም እንደአተት እያጣደፉ መክፈት እስታይሉ አልፎበታል ብለው እነትና ሲያወሩ በቀደም ተንጠራርቼ በቀዳዳ ስለሰማሁ...አዲስ ሩም ስከፍት በታላቅ ደስታ ይሆናል!!

እንግዲ ከላይ አብረን የዘመርነው አዝማቹ ሲሆን ሁለተኛው ቨርሴ ደሞ እንደሚከተለው ይሆናል....

እንኳን አደረሳቹ እንኳን አደረሳቹ እስኪ እልል እልል እስኪ እልል በሉ ሁላቹ.... እያልኩ እንኳን ለ 2005 አ.ም. በፒስ አደረሳቹ....!! ስሙማ..እልል ምናምን ስል..በቀደም የሆነ ቪድዮ አያቹልኝ... ማለቴ የሆኑ ነጠላ የዘቀዘቁና ወደ ኢምባሲ ለቅሶ ሊደርሱ የሚካለቡ ሴትዮ ሚድል ፊንገራቸውን ለተቃዋሚዎች ጊቭ ያረጉበትን ነው የምላቹ.... እሳቸው ያሮጊት ቀላል ቢሆኑም..ግን እኔና እሳቸው ብቻ ለብቻ ጎል አፋፍ ብንገናኝ አለቃቸውም :lol: ማለቴ...ያው ባጃር ምናምን ሳይሆን..ስቲል እኮ ለብ ያለች ደም ፊታቸው ላይ ስትራወጥ ስላየሁ ዩ ኖው... አለ አይደል....

እና ሳወራቹ..... እዛ ቪድዮ ላይ አንዱ በሀሎ ሀሎ የሚቃወመው ፊቱ የማይታይ ወንድ....ዋይ ዋይ ወያኔ ሞተ... ዋይ ዋይ መለስ ሞተ ብሎ...በጠራራ ጸሀይ ...እልልልልልልልልልል...ሲል ልክ ሳሙና የታሸ ሹራብ በጥርሱ እንዳኘከ ሰው መላ ሰውነቴን ስቅጥጥጥጥ..አይለኝም?..... አህዛብ ምን ነካው? ዳያስፖራ ነው ዲያስፖራን ሙድ የሚያስይዙበት እኮ..እንደዚ ያሉ እልልታና ኡኡታው የተቀየጠባቸው እንደኔ ያሉ ታክሲ ዘዋሪዎች ናቸው... :lol: ....

ታክሲ ዘዋሪ ስል የሆነ ጭውቴ ላጫውታቹማ.....
እኔ ባለሁበት ከተማ ያሉ አበሻ ታክሲ አሽከርካሪዎች...ሚስት ሀርድ ሆኖባቸዋል ከምር.... ማለት...የሚስት ሀይለኛ ትሬድ ዴፊሲት ላይ ናቸው....ቅቅቅቅ.... በዲሲ እና አትላንታ ደረቅ ወደቦች.... ወይዘሮ ሚስትን እንደጉድ ኢምፖርት ያረጉታል.. ባይለኛ ኪሳራ!! በ ቀይዋን ያየ ...በቺም የኔ ያቺም የኔ...ቅፈላ...ችኮቹ የመጡበት ፕሌን ሞተሩ ሳይበርድ....በፊለፊት ተርሚናል ስራውን መስዋእት አርጎ ቲፕ አስመልጦ ምናምን ቴትራ ሳይክል በመሰለች ታክሲው ሲጠብቃት..እነሱ በጓሮ በር እየተሸበለሉ..ስንቱ ገዝቶ ለመገጣጠም 3 ሳምንት የፈጀበት ኢክያ ግብዳ አልጋ ላይ ብቻውን በንዴት አጋድመው ጉድ አርገውታል.....( የኢኪያ እቃዎች ግን ለምንድነው እንደዚ ለመገጣጠም ከፍተኛ I.Q የሚጠይቁት?.... ስዊድኖች መሬ ናቸው ግን ያጎሳቁሉናል) እናላቹ እሚገርመው...የታክሲ ነጂ ሞራል እና...ኢፍል ታወር....የተገነቡት ካንድ ማቴርያል ነው መሰለኝ ንቅንቅ የለም ስልህ..... ወድያው ባዲስ መልክ ተደራጅተው ከች ሲል ትታዘባለክ...
አንዱ .... አንዷ ተቄ ብላበት ምናምን በሳምንቱ....እዛው ታክሲ ተራ ጀለሱ ታክሲ ውስጥ ለሁለት ዱቅ ብለው...በዋላ መመልከቻ መስታወት እያዩ...እዚም እዛም የተዘሩ ሽበቶቻቸውን በጥፍር መቁረጫ እየቀነደቡ ሲነቅሉ አየሁና...አቤት አምላኬ ምን አይነት አስደማሚ ፒፕል ጋር ነው የምታኖረን ብዬ ..ጋድን አደነኩት! እላቹዋለው.... ለሌላ ራውንድ ሲዘጋጅ እኮ ነው.... ወይ ደረቅ ወደብ :lol:


በቀጣይ ትዝብት...በሌላ ነቆራ... እስክንመለስና እስክንገናኝ....


ላሁኑ መብራት ጠፍቷል
ዘጌ_ዘጋንባው
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 176
Joined: Wed Aug 18, 2010 5:45 am

Postby ዘጌ_ዘጋንባው » Sat Sep 15, 2012 10:03 pm

ሰላም ቅዳሜያውያን...
ኢትስ ኦኬ አይሰማኝም እሺ...አስተያየት ባትጽፉም ማንበባቹን የሚቆጥር ቆጣሪ ስላለ አምላክ ይመስገን....እላለሁ

ናይስ ቀን ነው ዛሬ...ዌዘሩ እዚ...
ህጻናቶች ከአፓርትመንቴ መስኮት ባቻገር ካለው አረንጓዴ መስክ ላይ ሲጫወቱና ሲንጫጩ እያየሁ መንፈሴን እያለመለምኩ ነው.... ለቅጽበትም የልጅ መውለድን ጸጋ አሰብኩትና..ተመኘሁት... ግን ከማን ልውለድ? ወይንም ላስወልድ? ....

ለክፉም ለደጉም... GAGNAM STYLE ብያለሁ... ዳንሱንም እየተለማመድኩ ነው...

http://www.youtube.com/watch?v=9bZkp7q19f0


ዚስ ዘፈን ማካሪናን አስታውሶኛል....
ዘጌ_ዘጋንባው
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 176
Joined: Wed Aug 18, 2010 5:45 am

Postby ማህሌትወ » Tue Sep 25, 2012 10:40 am

:) :) :) ጻፍ እናነባለን:: ኮሜንት አትጠብቅ::
ማህሌትወ
ጀማሪ ኮትኳች
ጀማሪ ኮትኳች
 
Posts: 77
Joined: Wed Aug 29, 2007 3:21 am

Postby ያባቱልጅ » Mon Oct 01, 2012 6:02 pm

ዘጌ_ዘጋንባው wrote:ሰላም ቅዳሜያውያን...
ኢትስ ኦኬ አይሰማኝም እሺ...አስተያየት ባትጽፉም ማንበባቹን የሚቆጥር ቆጣሪ ስላለ አምላክ ይመስገን....እላለሁ

ናይስ ቀን ነው ዛሬ...ዌዘሩ እዚ...
ህጻናቶች ከአፓርትመንቴ መስኮት ባቻገር ካለው አረንጓዴ መስክ ላይ ሲጫወቱና ሲንጫጩ እያየሁ መንፈሴን እያለመለምኩ ነው.... ለቅጽበትም የልጅ መውለድን ጸጋ አሰብኩትና..ተመኘሁት... ግን ከማን ልውለድ? ወይንም ላስወልድ? ....

ለክፉም ለደጉም... GAGNAM STYLE ብያለሁ... ዳንሱንም እየተለማመድኩ ነው...

http://www.youtube.com/watch?v=9bZkp7q19f0


ዚስ ዘፈን ማካሪናን አስታውሶኛል....ዘጌው

ጨዋታሽ እኮ ለዛ አለው ቅቅቅቅቅቅ ሳላነበሽ አላልፍም አንዳንዶቹ የምትጫወቻቸው ግራ ጎን ስታየው ቢጫ ቢያሰጠኝም ቅቅቅቅ
ግዴለም እስካሁን ያይሁትን ቢጫዎች እሱዋም አታስታውሳቸውም
ኑሮ ታዲያ እንዴት እንዴት እያረገህ ነው???

እስቲ ብቅ በል
ያባቱልጅ
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 363
Joined: Tue Oct 31, 2006 6:29 pm

Postby ዘጌ_ዘጋንባው » Tue Oct 02, 2012 4:37 am

ማህሌት..እሺ ሲስ.... አንቺ ብቻ በጥብቅ አንቢልኝ... :P

..ያቡካ ልጅጅጅጅ....እንዴ ምንድነው ነገሩ እንደዚ ጥፍቶ ማለት?...አገር ቤት መለስ ቀለስ እንደምታበዢ ባቅም...የዚን ያህል ግን ፕሊስ አትዘንጊን....
የቢጫ ማስጠንቀቅያ ካርዱ ነገር...ቂቂቂቂቂ...ነው ያስባለኝ.... አይ ኖው እንኳን ያንተ ጨዋ ግራ ጎን ይቅርና..የምጽፈው ነገር እኔኑ ራሴ አንዳንዴ መልሼ ሳነበው...ምን ነክቶኝ ነው ግን...ሁሉ እላለው....
አብሽር...ቢጫው ምንም አይደለም...ከህዋላ አደገኛ ታክል ብቻ እንዳትገባባት...እሱ እንደሊቨርፑሉ ተጭዋች ትሪስ ጨዋታ ነው የሚያስቀጣክ....


እኔማ....ያው ባክሽ...ጸጉሬ ከመሸሹና ስቶማኬ ከመወጣጠሩ በቀር እንዳለው አለሁልክ
መላጣዬማ.. ሰፍቶ... ብርቅርቅታ ምናምን ሆኖልሽ...የሆነ የግሪን-ቴክ ካምፓኒ እንደ ሶላር ፓናል እንጠቀምበት ብለውኝ.... ሀሳብ በሀሳብ አርገውኛል...... ሀሳቡ ደሞ ሲበዛ ታቅያለሽ....ጭንቄዬ ወርክ ሲያደርግ ምናምን...ለጉዴ ይግላል..... እናልሽ...ገርልፍረንዴ አንድ ፓንት አይደል ያላት?.... እሱን አጥባ የጋለ መላጣዬ ላይ ነው የምታሰጣው....በ 30 ደቂቃ ሙክክ አርጎ ያደርቅላታል.... :D

ከሰሞኑ ደሞ ስለስቶማኬ ነገር አጫውታቹዋለው,....

መንፌው ባለሶላሩ....
ዘጌ_ዘጋንባው
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 176
Joined: Wed Aug 18, 2010 5:45 am

Postby ገልብጤ » Tue Oct 02, 2012 9:43 pm

...ገርልፍረንዴ አንድ ፓንት አይደል ያላት ?.... እሱን አጥባ የጋለ መላጣዬ ላይ ነው የምታሰጣው ....በ 30 ደቂቃ ሙክክ አርጎ ያደርቅላታል

ምስኪን ምን አይነት ፓንት ይሆን ቶንግ ፓንት ይሆን አልበላም አልጠጣም ብላ ነው አይደል ባንድ ፓንት እንደ ታቱ ተጣብቃ የምትኖረው ...መንፌክሱ ያ ባለኪሱን ፓንት ታውቂዋለሽ እሱ ሳያዋጣት አይቀርም ያምስት አመት በጀት እኮ ነው
ያልበሰለ ፖለቲከኛ ስለቀጣዩ ምርጫ ሲያስብ
የበሰለ ፖለቲከኛ ስለቀጣዩ ትውልድ ያስባል
James freeman clarke
ገልብጤ
ዋና ውሃ አጠጪ
ዋና ውሃ አጠጪ
 
Posts: 1680
Joined: Sat Jun 26, 2010 11:24 pm

Postby ዘጌ_ዘጋንባው » Mon Oct 08, 2012 5:36 pm

ገልቤው
ኦፍኮርስ ጀምስ ባለኪሱንም ባለሰአቱንም አቃቸዋለው....
ባለኪሱ ከባለሰአቱ በዋላ የመጣ ስታይል ነበር.... ጀምስ ባለሰአቱ ብቻውን ወደ 5 ኪሎ ይመዝናል..እንደሶደሬ ምናምን ስትዋኝበትና ውሀ ሲያዝል ደሞ 15 ይገባል... እና እልካለው እሱን ለብሼ ክብደቱ ወደታች እየጎተተኝ ስላደኩ ለዛ ነው ስሜ...ዘነዘናው የተባለው....እልካለው

መልካም ሰኞ
ዘጌ_ዘጋንባው
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 176
Joined: Wed Aug 18, 2010 5:45 am

Postby ማማዬ » Wed Apr 03, 2013 5:49 pm

ዘጌ በጣም ተመችቶኛል ጨዋታህ !!!
"A journey of a thousand miles begins with a single step"
ማማዬ
አዲስ
አዲስ
 
Posts: 11
Joined: Wed Apr 03, 2013 12:17 pm
Location: Emamaye gare

Re:

Postby ገልብጤ » Wed Aug 31, 2016 11:19 am

ዘጌ_ዘጋንባው wrote:ሰላም ቅዳሜያውያን...
ኢትስ ኦኬ አይሰማኝም እሺ...አስተያየት ባትጽፉም ማንበባቹን የሚቆጥር ቆጣሪ ስላለ አምላክ ይመስገን....እላለሁ

ናይስ ቀን ነው ዛሬ...ዌዘሩ እዚ...
ህጻናቶች ከአፓርትመንቴ መስኮት ባቻገር ካለው አረንጓዴ መስክ ላይ ሲጫወቱና ሲንጫጩ እያየሁ መንፈሴን እያለመለምኩ ነው.... ለቅጽበትም የልጅ መውለድን ጸጋ አሰብኩትና..ተመኘሁት... ግን ከማን ልውለድ? ወይንም ላስወልድ? ....

ለክፉም ለደጉም... GAGNAM STYLE ብያለሁ... ዳንሱንም እየተለማመድኩ ነው...

http://www.youtube.com/watch?v=9bZkp7q19f0


ዚስ ዘፈን ማካሪናን አስታውሶኛል....

የዘጌው ህልም ተሳክቶ ይሆን ወልዶ ከብዶ ገብስማ ጠጉሩን በቀለም ስውቦ
ያልበሰለ ፖለቲከኛ ስለቀጣዩ ምርጫ ሲያስብ
የበሰለ ፖለቲከኛ ስለቀጣዩ ትውልድ ያስባል
James freeman clarke
ገልብጤ
ዋና ውሃ አጠጪ
ዋና ውሃ አጠጪ
 
Posts: 1680
Joined: Sat Jun 26, 2010 11:24 pm


Return to Warka Intimate - ዋርካ ፍቅር

Who is online

Users browsing this forum: No registered users and 3 guests