የአእምሮ በሽታ ( ፐርሰናሊቲ ዲሶርደር)

Issues and Articles of General Interests including topics related to religion

Postby ፀዋር » Mon Mar 19, 2012 9:54 pm

ሠላም ሙጢነት

መጽሀፉን ናና አብጠልጥልልን የሚል ግፊት ሳታበዙብኝ በፊት በቀናነት ከአጉል ልማድ ህዝባችንን ነጻ ማውጣት ይገባችኋል ስለ በነበረበት ጊዜ ደቂ እስጢፋን እንደአብነት ጠቅሼ ነበር:: የመርሳት ችግር ይኖራል እንጂ እንዲህ ዋናው መጽሀፍ ላይ ከመድረሳችን በፊት እኮ ትችቴ እነ ተክልዬ ላይ ያነጣጠረ ነበር:: ከዛም በፊት ሀይማኖተ አበው ምናምን የምትሉት ባይብልን የተካው ድርሰታችሁ ላይ ነበር የማነጣጥረው:: መመሪያችን ባይብል ነው ካላችሁ በባይብል ተመሩና ህዝቡን ከባዕድ አምልኮ አላቅቁት እያልኩ ነበር:: ጊዜውን ንዋዩን ጉልበቱን በባዶ ተስፋ ለመናፍስት አሳልፎ ሰጥቶ የጨቋኞች መጫወቻ አታድርጉት የሚል ነበር የመጀመሪያው ምክር አዘል ትችቴ:: እናንተ ግን "---- ነህ" የሚል አጭር መልስ ነበር የሰጣችሁኝ :lol: አሁን እንዲህ ዋልድባ ተነጠቅኩ ብለህ እየየ ልትል :lol: ገና በቁምህ ታርደህ ታልቃታለህ :roll: መብትህን ከማስከበር ይልቅ ለተክልዬ እየተሳልክ ለሳምሪ እየዘከርክ ፀሎትህን አድርስ:: ማን ያውቃል ለናንተ ሲባል የምጻትን ቀን ሊያፋጥኑት ይችላሉ::

በል የሚቀጥለውን ሊንክ ተመልከተው:: ደቂ እስጢፋን ለምን ያኔ እንደጠቀስኳቸው ሊገባህ ይችል ይሆናልና
http://www.cyberethiopia.com/warka4/vie ... c&start=15
እናመሰግንሃለ� wrote:ወይኔ...! ሰበር ዜና...! ጸዋር ለክርስትና ሃይማኖት የተሰዉት ደቂቀ እስጢፋኖሳውያንን ሲያንቆለጳጵስ ተያዘ:: :lol: :lol: :lol:

ጸዋር እንደከተበው...

ለአላማ ኖሮ ከመሞት በላይ የበለጠ ነገር ምን አለ ? የህይወት ሙላት ሞት ነው ! ደቂ እስጢፋ እውነትን ስላስተማሩ ብቻ በቁማቸው ተቃጥለዋል :: የዚህን ቤ /ክ /ያን ታሪክ ትንሽ ብታውቅ እንዴት ልትንገበገብ እንደምትችል አትጠይቀኝ ::


ከዚህ ውጪ ምን ላነብብ እመኝ ይሆን! :lol: :lol: :lol:

የሚገርመው እኮ እነዚሁ ደቅ እስጢፋ ከቤተክህነት ፖለቲከኞች አልፈው ግብጥ አገር ያሉ መሐመዳውያን አገረ-ገዢዎችን ያርበደበዱና ለነርሱም ያላጎበደዱ ጀግኖች መሆናቸው ነው:: (እህየው! ሀዲስ ሊናደድ ነው! :lol: )

ጸዋር እስከዛሬ ኤቴዪስትም ዴዪስትም ስትባል ነበረ:: አሁን ሳስበው እርሱም ይበዛብሃል:: ዝም ብለህ እንደለማኝ ፍርፋሪ ከተለያየ ኮርነር የተለቃቀመ ጸረ-ተዋሕዶ ፕሮፓጋንዳ ጋርቤጅ ነህ:: ለምን ኦርቶዶክስ ተዋሕዶን መቃወም እንደፈለግህ ራሱ ለራስህም አልገባህም:: ላይህ ላይ ያለው ጥብርኤል እንደጉድ ነው የሚጋልብህ ጃል! :lol: :lol:

እስቲ አሁን መጽሐፍ ቅዱስን እግዚአብሔር አልጻፈውም ብሎ የሚከራከር ሰው...እንደገና መልሶ በመጽሐፍ ቅዱስ ሊትራል አተረጓጎም ላይ ያላቸው እምነት ከቤተክህነትና ቤተመንግሥት ስታተስኮ በልጦ እስከመስዋዕትነት ያደረሳቸውን ደቅ እስጢፋኖስን ያንቆለጳጵሳል? :lol: :lol:

ገብቶሽ ሳለ 'ምታደርቂኝ አሉ አብዬ! እንደዛሬ ስቄም አላውቅ!!
ፀዋር
ዋና ኮትኳች
ዋና ኮትኳች
 
Posts: 507
Joined: Tue Feb 16, 2010 12:40 pm

Postby ሱልጣን » Tue Mar 20, 2012 3:26 pm

ቆቁ wrote:ሀዲስ ወዳጄከተበላሹ ሰዎች ጋር መነታረክ ያበላሻል
ካበዱ ሰዎች ጋር መጨቃጨቅ ያሳብዳል


ወይ ቆቁ :idea:
ይመችህ ብያለሁ...


ያንኛውን እብድ ስታክም ሌላው እብድ ብቅ ይላል

የልቡን ሲነግሩት የኮረኮሩትን ያክል :lol: ይላል ያገሬ ሰው!!

[/quote]
HONESTY~TRUSTWORTHINESS~SINCERITY
''Whoever is carless with in small matters....
Cannot be trusted in important affairs''
ሱልጣን
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 261
Joined: Wed Sep 03, 2003 11:38 am

Postby ቆቁ » Wed Mar 28, 2012 7:27 pm

ሱልጣን ወዳጀ
እስቲ ወደ ዜናው ብቅ በል

ናርዚስቲክ ፐሮስናሊቲ ዲሶርደርን ከዋርካ አልፈን እስቲ ወደ በየሐይማኖታችን ውስጥ ጠለቅ ብለህ እንመርምረው እስቲ

በል ሱልጣን አንተም በእምነትህ
እኔም በእምነቴ የዚህን በሽታ ሁኔታ እንመርምር

እንደ ጸዋር ያለው እምነት የሌለውንም እንደዚሁ በጋራ እንመርምር

በፖለቲካው ውስጥም እንደዚሁ እንመርምር

ይህ የናርዚስቲክ ፐሮስናሊቲ ዲሶርደር ነው ሐገራችንን እያናወጠ የሚገኘው::

ሳይካትሪስቱ ቆቁ
ቆቁ
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 4025
Joined: Sun Sep 21, 2003 9:57 am
Location: united states

Postby ፀዋር » Thu Mar 29, 2012 10:44 pm

ሠላም ለነገረኛው እንዲህውም ለዘላባጁ ወዳጄ ቆቁ

እስኪ እምነት ያላችሁ ሰዎች እንድትወያዩበት ዕድሉን ልስጣችሁና ከዳር ቆሜ ት/ት ልውሰድ

http://youtu.be/me1joZHo0Zo

ምን ተሰማህ? እንዴት ነው ትላለህ? ትክክል ነው?

እንደዚህ አይነት እምነት ይዞ ሰው ከሚኖር በነጻነት በባዶ መኖር አይሻልም???

እስኪ ተወያዩና አስተምሩን :lol:


ሠላም

ቆቁ wrote:ሱልጣን ወዳጀ
እስቲ ወደ ዜናው ብቅ በል

ናርዚስቲክ ፐሮስናሊቲ ዲሶርደርን ከዋርካ አልፈን እስቲ ወደ በየሐይማኖታችን ውስጥ ጠለቅ ብለህ እንመርምረው እስቲ

በል ሱልጣን አንተም በእምነትህ
እኔም በእምነቴ የዚህን በሽታ ሁኔታ እንመርምር

እንደ ጸዋር ያለው እምነት የሌለውንም እንደዚሁ በጋራ እንመርምር

በፖለቲካው ውስጥም እንደዚሁ እንመርምር

ይህ የናርዚስቲክ ፐሮስናሊቲ ዲሶርደር ነው ሐገራችንን እያናወጠ የሚገኘው::

ሳይካትሪስቱ ቆቁ
ፀዋር
ዋና ኮትኳች
ዋና ኮትኳች
 
Posts: 507
Joined: Tue Feb 16, 2010 12:40 pm

Postby ቆቁ 2 » Mon Apr 02, 2012 7:32 am

ፀዋር wrote:ሠላም ለነገረኛው እንዲህውም ለዘላባጁ ወዳጄ ቆቁ

እስኪ እምነት ያላችሁ ሰዎች እንድትወያዩበት ዕድሉን ልስጣችሁና ከዳር ቆሜ ት/ት ልውሰድ

http://youtu.be/me1joZHo0Zo

ምን ተሰማህ? እንዴት ነው ትላለህ? ትክክል ነው?

እንደዚህ አይነት እምነት ይዞ ሰው ከሚኖር በነጻነት በባዶ መኖር አይሻልም???

እስኪ ተወያዩና አስተምሩን :lol:


ሠላም

ቆቁ wrote:ሱልጣን ወዳጀ
እስቲ ወደ ዜናው ብቅ በል

ናርዚስቲክ ፐሮስናሊቲ ዲሶርደርን ከዋርካ አልፈን እስቲ ወደ በየሐይማኖታችን ውስጥ ጠለቅ ብለህ እንመርምረው እስቲ

በል ሱልጣን አንተም በእምነትህ
እኔም በእምነቴ የዚህን በሽታ ሁኔታ እንመርምር

እንደ ጸዋር ያለው እምነት የሌለውንም እንደዚሁ በጋራ እንመርምር

በፖለቲካው ውስጥም እንደዚሁ እንመርምር

ይህ የናርዚስቲክ ፐሮስናሊቲ ዲሶርደር ነው ሐገራችንን እያናወጠ የሚገኘው::

ሳይካትሪስቱ ቆቁ


ተረጋጉ

ጠቢቡ ቆቁ
ቆቁ 2
አዲስ
አዲስ
 
Posts: 48
Joined: Sat Dec 22, 2007 3:17 pm

Postby ቆቁ » Tue Jun 05, 2012 5:59 pm

ጸዋር ወዳጄ

አንድ ጊዜ የት ነበት ያየሁህ
አስተሳሰባችን አንድ ሆኖ ያየሁብህ ቦታ ጠፋብኝ : አንድ ቦታ ላይ ተገናኝተን ነበር

ይህ የናርዚስቲክ ፐርሶናሊቲ ዲሶርደር
በሐይማኖት ( በእስልምናውና በክርስትናው እምነት )
በፖለቲካው
በቢዝነሱ

ዓለም ጎልቶ የሚታይ ነው::

ገንዘብ ለማግኘት
ታዋቂ ለመሆን
እዚህም እዛም አለሁ ማለት

ይህ ሁላ የኑሮን ትግል ለማሸነፍ የሚደረግ ትግል ሳይሆን
የኑሮሎጂካል ዲሶርደር ነው::

አንተ ትክክል ነህ እኔ ግን ትክክል አይደለሁም
እኔ ትክክል ነኝ አንተ ግን ትክክል አይደለህም
አንተ ትክክል አይደለህም እኔም ትክክል አይደለሁም

ከሚሉት ሶስት ፐርሶናሊቲ ካራክተር ይጀምራል
እያንዳንዱን በሚቀጥለው

ቆቁ ጠቢቡ እንዴነህ ? የት ጠፋህ ?

ሳይካትሪስቱ ቆቁ
ቆቁ
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 4025
Joined: Sun Sep 21, 2003 9:57 am
Location: united states

Postby ቆቁ » Wed Jun 20, 2012 4:50 pm

ቁ'ጥር 1 :
አንተ ትክክል ነህ እኔ ትክክል አይደለሁም

ይህ :ባህርይ: ራስን: ማወቅ: ነው:: ወይም: ራስን: ዝቅ: አድርጎ: መመልከትም :ይሆናል::

ይህ :ሁኔታ :ሙሉ: በሙሉ: የሆነ: ወይም: ላላ: ያለ: ጥገኝነትን: የሚያስከትል: ባህርይ: ነው::

ጥገኝነት: ያለ :የኖረና: የሚኖር: የተፈጥሮ: ባህርይ: ነው::

በልጅነታችን: በፍቅር: ወይም: በጉብዝና: አንድን: ሰው: እንወዳለን:: ይህ :የውዴታ: ባህርያችን: እስከ: መጨረሻው: ወይም :ከጉዋደኛችን: በሆነ: አጋጣሚ: እስከተለያየን :ድረስ: የሚቀጥል: ባህርይ: ነው::

አንድ: ግለሰብ: በሌላ: ግለሰብ: ትክክለኝነት: ካመነ: እና: ትክክለኛነቱን: ከተቀበለ : ይህ :ግለሰብ: ሁል: ጊዜ: ትክክል: ነው: በማለት: ያምነዋል::

በትንሹም: በትልቁም: ወደዚህ: ትክክለኛ: ነው :ብሎ :ወደ: ሚያምነው: ግለሰብ: ቀረቤታ: ይኖረዋል::

ይህ: ግንኙነት: በልጅነታችን: ያደረግነው: ግንኙነት: ነው:: የልጅነት: ጉዳደኛችን :በጉልበት: ወይም በእውቀት: ጠንካራ: ከሆነ: እሱን: ደጀን: አድርገን: እንኮራለን::

የምንፈልገውን: ነገር: ከዚህ :መከታችን: እንጠይቃለን:
አድርጉ :የሚለንን: እናደርጋለን::

ምክንያቱም: በችግር: ጊዜ :መከታችን: ነው: ብለን: ስለምናምን::

ይህ: ግንኙነት: በሁለቱም: ጎራ: መተማመንን: ስለሚፈጥር: ሰላማዊ: የሆነ: ግንኙነት: ይመስላል ::
ለምሳሌ
ሰባኪዎችን: እና :ፖለቲከኞችን: መውሰድ: ይቻላል::
አንድ: ሰው: በአንድ: የሐይማኖት ሰው ሰበካ: ከተማረከ: ለዚህ :ግለሰብ: በዚህ: የሰበካ ትምህርቱ: ጥገኛ :ይሆናል: ማለት: ነው:: በዚህ: ግለሰብ: ሰበካ: ምርቃና: ውስጥ: ይዘፈቃል: ማለት: ይሆናል::

በፖለቲካውም :ዓለም: እንደዚሁ: ፖለቲከኛው: በሚቀደው: ቀደዳ: ከተማረከ: ይህ: ፖለቲከኛ :በሚቀደው: ቀደዳ:ሁላ: ሲመረቅን: ይታያል::

ሳይካትሪስቱ ቆቁ
ቆቁ
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 4025
Joined: Sun Sep 21, 2003 9:57 am
Location: united states

Postby ቆቁ » Wed Oct 03, 2012 8:03 pm


እኔ: ትክክል: ነኝ: አንተ: ግን :ትክክል: አይደለህም::
ይህ: የሰው: ልጅ: ጠባይ: ከቁጥር :አንድ :የሚለይበት: ጉዳይ: የለም: ተመሳሳይ: ጉዳይ: ነው::

ትክክል: የሆነው: ግለሰብ: ትክክል: ያልሆነው: ግለሰብ: በማሳመን: ሁኔታውን: ሊያስገነዝበው: ይችላል::

አንድ: ተማሪ: እንበል: የሆነ: የካልኩሌሽን: ስህተት: ይሰራ:ል እንበል :: ሌላው: ጉዋደኛው: ይህ: የሰራኸው: ካልኩሌሽን: ትክክል: አይደለም: ነገር: ግን: ትክክል: የሚሆነው: እንደዚህ :እንደዚህ :አድርገህ: ብትሰራው :ነው: ብሎ: ማስረዳቱ: ትክክለኛ :የሰው: ልጆች :ማለትም: ኖርማል: የሆነው :የሰው: ልጆች: ባህርይ: ነው::

ከነዚህ: ከቁጥር 1:እና: ከቁጥር 2: የምንገነዘበው: ነገር: ቢኖር: በዚህ: በዋርካ: መድረክ: የፖለቲካ: እና: የሐይማኖት: ውይይት :አንድም :የመተማመን :እና: የመተሳሰብ: ውይይት: አለመደረጉን: ነው::ከዚህ: በመነሳት: የሚቀጥለውን: ቁጥር 3 :እንመለከታለን:
እኔ: ትክክል: አይደለሁም: አንተም: ትክክል: አይደለህም ::
ይህ :ሁኔታ: ነው: ናርዚስቲክ: ፐርሶናሊቲ: ዲሶርደር: የሚባለው::

ሳይካትሪስቱ ቆቁ

ጥሉበት
የሚቀጥል
ቆቁ
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 4025
Joined: Sun Sep 21, 2003 9:57 am
Location: united states

Postby ቆቁ » Sat Oct 06, 2012 4:46 pm

ለዋርካ :ታዳሚ :

ከአትላንቲክ: እና :ከፓስፊክ: ውቅያኖስ: የጠለቀ :ነገር: ውስጥ: ስለምንገባ :

በመጀመሪያ: ጥናታዊ: ጥያቄ :እንዳቀርብ: እገደዳለሁ::


ወደ: ቀድሞው: ምሳሌ: ልመለስ :
A- ላይብራሪ: ውስጥ :ቁጭ: ብሎ : ካልኩለስ: ይቀምራል::

B- ደግሞ: በሌላ :አቅጣጫ: ተቀምጦ :ያንኑ :ካልኩለስ: ይቀምራል::


ሁለቱም: ሲቀምሩ: አንድ: ውጤት: ላይ :ይደርሳሉ::


B-: Aን :እንዴት: አድርጎ : ካልኩለሱን: እንደቀመረ: ይጠይቀዋል ::

A-: ቅመራውንና: የቅመራውን: ውጤት: ለB :ያስረዳዋል::

በድንገት: B- :ትክክል: አይደለህም: ይላል::

A-: ምኑ : ላይ: ነው :ስህተቴ :ይለዋል ::

B-: እንዳንተ: አይደለም: የሚሰራው: እንደኔ :ነው: ይለዋል::

A-: እስቲ: ልየው: የሰራኽውን: ብሎ :ይጠይቀዋል ::

B-: እንዳንተ: አይደለም :የሚሰራው: አልኩህ :እኮ !

A-: አሳየኝ: እኮ: ነው :የምልህ :ይለዋል: መልሶ:

B- ስነግርህ: አትሰማም: እንዴ ?

ከተባባሉ: በሁዋላ :ይለያያሉ::

ጥናታዊ :ጥያቄዬ: የሚከተለው: ይሆናል::

A-: እንዴት: የሚሆን: ይመስላችሁዋል :?: :?: :?:

B-: እንዴት- የሚሆን -ይመስላችሁዋል :?: :?: :?:

ሳይካትሪስቱ ቆቁ
ቆቁ
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 4025
Joined: Sun Sep 21, 2003 9:57 am
Location: united states

Postby ቆቁ » Wed Nov 07, 2012 6:43 pm

B = በቀለ
A= አበበ

ከላይ እንደቀረበው በቀለና አበበ ባልታወቀ መንገድ የሆነ "የዞረ ድምር" ላይ ይገኛሉ ማለት ነው::

አበበ ራሱን መጠራጠር ይጀምራል:: እያገላበጠ የቀመረውን ካልኩለስ ወዲያ እና ወዲህ በመቀማመር እንደገና ትክክል ለማድረግ ይለፋል

በመጨረሻም ምናባቱ ትክክል ነኝ በማለት ወይም ስህተት ሰርቼ ይሆን በማለት ስራውን ለአስተማሪው በመጠራጠር ያቀርባል::

በቀለ የተናገረውን ነገር ጨርሶ ረስቶታል ወይም አበበ በትክክል በመስራቱ አጭሶታል::

እንደገና ወደ መሰረታዊ ትንተናችን ስንመጣ

ለምን በቀለ በአበበ ሊቀና ቻለ የሚለው ጥያቄ ላይ እንደርሳለን

ለመሆኑ ቅናት ምንድነው የሚለው ጥያቄ ላይ ስንደርስ
ቅናት የሰው ልጆች የተፈጥሮ ባህርይ ነው ወይስ የሳይኮሎጂካል ችግር ወደ ሚለው አንኩዋር ጥያቄ እናመራለን::

ለመሆኑ ቅናት ምድነው ?

ሳይካትሪስቱ ቆቁ
ቆቁ
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 4025
Joined: Sun Sep 21, 2003 9:57 am
Location: united states

Postby ቆቁ » Thu Dec 20, 2012 6:53 pm

ቅናት: ምንድነው ?

አንድ: ግለሰብ :በሌላ :ግለሰብ :ሊቀና: ይችላል::
የተፈጥሮ: ሕግ: ነው: ነገር :ግን :ራሱን: አስተካክሎ: ሊቀመጥ: ይችላል:: " እድል ": ነው: በማለት: ያልፈዋል::

ቅናት: ይህ: ብቻ :አይደለም: ሌላ: የቅናት: መንፈስም: አለ:: አንድ: ሰው: በሐብት: ቢበልጥህ :ልትቀና: ትችላለህ:: አንድ: ሰው: በትምህርት: ቢበልጥህ: ልትቀና: ትችላለህ::

መንፈሳዊ: ቅናት: አለ::
ናርዚስቲክ: ቅናት: አለ ::

መንፈሳዊ: ቅናት:
ለዓላማ: ያነሳሳል:: በትምህርት: ከተበለጠ :አንድ: ግለሰብ: ራሱን: ለማሻሻል: ታጥቆ: እንዲነሳ: ያደርጋል::

በሩጫ: ከተሸነፈ :ትሬኒንጉን: የበለጠ: በመደጋገም: ቨሩጫ: ለማሸነፍ: ያነሳሳል::

እነዚህ: ከብዙ: ምሳሌዎች: ጥቂቶቹ: ናቸው ::

ሌላው: ደግሞ: ከላይ: እንደተጠቀሰው: ሁሉም :የማይሆን: ከሆነ: "" የእድል ጉዳይ "" :ነው: ወይም :የሱ: " የአንድዬ :ጉዳይ" :ነው: በማለት: በዝምታ: መቀመጥም: አለ::

ናርዚስቲክ: ቅናት: ማለት: ምን: ማለት: ይሆን ?
ይህ :ቅናት :ዲስትራክቲቭ: የሆነ: በሌላ: ሰው: ከመቅናት: አልፎ: ከራስ: ጋር: በቅናት: እርር :ማለት: ነው::

እንዴት ?
ወደፊት እንመለከተዋለን : ሐሳብ: ያለው: መቀጠል: ይችላል::


ሳይካትሪስቱ: ቆቁ
ቆቁ
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 4025
Joined: Sun Sep 21, 2003 9:57 am
Location: united states

Postby ቆቁ » Tue Aug 13, 2013 9:48 pm

ወደ ዋናው ዓላማ ስንመጥ

እኔ ትክክል አይደለሁም እናንተም ትክክል አይደላችሁም የሚለው ይህ ፐርሶናሊቲ ዲሶርደር ያለበት ግለሰብ እንዴት አድርጎ ሌላ የሌላ ግለሰብን ጊዜና ሕይወት ያባክናል ብለን መጠየቅ እንገደዳለን

እኔ ትክክል አይደለሁም ለማለት እንዴት ይችላል አንድ ግለሰብ

ይህ ግለሰብ በጠዋቱ በልጅነቱ የናትና የአባት ፍቅር የተነፈገው በሚያደርገው እንቅስቃሴ ሁላ ተው : እረፍ : አትንካ : ዝም በል እየተባለ ያደገ የቤተ ሰብ ማለትም የእናትና የአባት ፍቅር የማያውቅ ግለሰብ ነው::

ይህ ግለሰብ የሰራው ስራ ሁላ ትክክል አይመስለውም ስለማይመስለው "" እኔ ትክክል አይደለሁም "" ወደ ሚለው ዋናው የፐሰናሊቲ ዲሶርደር ዓላማ ይመጣል

እኔ ትክክል አይደለሁም ብሎ አያቆምም እናንተም ትክክል አይደላችሁም በማለት አዲስ ሕይወት ኣዲስ ኣለም ለመፍጠር ይፍጨረጭራል

አዲስ አለም አዲስ ሕይወት ???

ምንድነው ይህ አዲስ ዓለም እና አዲስ ሕይወት ለዚህ ፐርሶናልቲቲ ዲሶርደር ለተጠናወተው ግለሳብ ?

ወደፊት እንመጣበታለን

ፈላስፋው ቆቁ
ቆቁ
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 4025
Joined: Sun Sep 21, 2003 9:57 am
Location: united states

Postby ቆቁ » Wed Aug 14, 2013 8:32 pm

እኔ ትክክል አይደለሁም እናንተም ትክክል አይደላችሁም የሚለው በኢትዮጵያ ሁኔታ እንዴት ይገለጻል?

በፈረንጁ ዓለም ይህንን ሁኔታ ለመግለጽ ብዙ አያዳግትም::

እኔ ትክክል አይደለሁም እናንተም ትክክል አይደላችሁም በሚለው ዓላማ የፈረንጁ ዜጋ በተፈለገው ዓይነት መስዋእት በመክፈል የወጣለት ፕሮፌሰር : የወጣለት ባለሙያ : የወጣለት መካኒክ : የወጣለት አስተማሪ የወጣለት ዘፋኝ እንደ ማይክል ጃክሰን እና ዊትኒ ሁስተን

አለባበሱ እንከን የማይወጣለት: አነጋገሩ የማይታረም : የጸጉሩ አበጥጣጠር ከዓለም አንደኛ
አስተሳሰቡ ከፕሮፌሰር የበለጠ እንደው በሁሉም በዓለም አንደኛ ለመሆኑ የሚሞክር ግለሰብ ነው::

በዚህ ዓይነት ፐርሶናሊቲ ዲሶርደር የምንገታገቱ የምናውቃቸው ስመ ጥር ግለሰቦች በፈረንጁ ዓለም በሽ ናቸው

በኛስ ሐገርስ ይህ ዓይነት ፐርሶናሊቲ ዲሶርደር እንዴት ይገለጻል

""እኔ ትክክል አይደለሁም እናንተም ትክክል አይደላችሁም""

ሳይካትሪስቱ ቆቁ
ቆቁ
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 4025
Joined: Sun Sep 21, 2003 9:57 am
Location: united states

Postby ቆቁ » Thu Aug 22, 2013 9:37 pm

ፐርሶናሊቲ ዲሶርደር እንዴት በኢትዮጵያ ሐገራችን ይገለጻል

የቤተ ሰብ ፍቅር የተነፈገው/ጋት ቤተ ሰቡን ጥሎ መጥፋት: ወደ ከተማ መኮብለል ወይም ወደ ወታደርነት: ወይም ወደ ወዛደርነት ዓለም በመኮብለል ኑሮውን ድቅድቅ ወደ አለ ጨለማ ይመራል::

መውጫ መግቢያ አይኖረውም


ሌላው የቤተሰብ ጥላቻን አምቆ እንደምንም ብሎ ወደ ትምህርቱ ዓለም ወይም በንግድ መልክ የተሳካለት ከሞላ ጎደል ወደፈረንጁ ዓይነት ፐርሶናሊቲ ዲሶርደር ያመራል::

ለምሳሌ በፖለቲካው ዓለም ውስጥ የተዘፈቁት ልሂቅ የሚባሉትን ብንመረምር ከፈረንጁ ዓለም ያልተለየ ፐርሶናሊቲ ዲሶርደር ይታይባቸዋል

እኔ ትክክል አይደለሁም አንተም ትክክል አይደለህም
ወይም
እኔ ትክክል አይደለሁም እናንተ ትክክል አይደላችሁም የሚለው መሰረታዊ የፐርሶናሊቲ ዲሶርደር ጸባይ በግልጽ የሚታየው በነዚህ የሐገራችን የፖለቲካ ሰዎች ዘንድ ይሆናል

በዲያስፖራ ያለ ፖለቲከኛ በሐገራችን ያለ ፖለቲከኛ ሁላ በዚህ የፐርሶናሊቲ ዲሶርደር ላይ የሚገለጽ ባህርይ አላቸው ቢባል ስህተት አይሆንም

ለዚህም ምሳሌ በእስልምና እና በክርስትና እምነት መካከል በዚህ በዋርካ መድረክ ያለ ክርክር

በዋርካ ፖለቲካ የሚጻፈው ቱቱ ቡቱቱ

በየዌብ ሳይቱ የሚጻፈው ቀደዳ እና ዝባዝንኬ

ጥሩ ምሳሌዎች ናቸው

እያንዳንዱ ቱቱ ቡቱቱ እና ቀደዳ ወይም ዝባዝንኬ ያለምንም ደጋፊ ወይም ከሁለቱ በማይበልጡ ደጋፊዎች ብቻ የሚጻፍ ግላዊ ጽሁፍ ነው :: ይህ ግላዊ ጽሁፍ የግለሰቡን ፐርሶናሊቲ ዲሶርደር የሚያንጸባርቅ ጽሁፍ ነው


የፐርሶናሊቲ ዲሶርደር ያለበት ግለሰብ ለብቻው ይኖራል ማለት አይደለም :: ፐርሶናሊቲ ዲሶርደር ያለበት ግለሰብ ሰውን እንደ በግ መንጋ እየነዳ የሚያስኬድ ባሀርይም አለበት


ፐርሶናሊቲ ዲሶርደር ማለት አማኑኤል መግባት ማለት አይደለም አማኑኤል የገባ ለይቶለታል ነገር ግን ፐርሶናሊቲ ዲሶርደር ያለበት ግለሰብ ጥገኛ ያደረገውን ግለሰብም ሆነ ግሩፕ በራሱ ላይ ጊዜና ወቅት እስኪተረማመስበትና የመጨረሻው ወሳኝ መውደቂያው ላይ እስኪደርስ ድረስ ሌሎችን ማተረማመስ ነውየቤተ ሰብ ፍቅር ማለት ምን ማለት ነው ?


ሳይካትሪስቱ ቆቁ
ቆቁ
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 4025
Joined: Sun Sep 21, 2003 9:57 am
Location: united states

Postby ቆቁ » Thu Sep 26, 2013 7:51 pm

አስተዳደጋችን የሚያጠያይቅ ነው
በአጭሩ

1. የሐብታም ልጆች ከሆንን በቤተ ሰራተኛ ቅዘናችን እየተጠረገ ገላችን እየታጠበ ይሆናል ያደግነው
ከዛም አልፎ ከእናታችን ወይም ከአባታችን ጋር ያለን ግንኙነት እንደ የቤት ሰራተኛችን ያህል የጠነከረ ግንኙነት ያለው አይደለም ::

2. በድህነት ያደግን ከሆነ ደግሞ የእናታችን ፍቅር እጅግ የጠነከረ ነው ያለ እናታችን የምናውቀው ነገር የለም

3. የታደልን ከአባታችንም ከእናታችንም የጠነከረ ግንኙነት ያለን መልካም ፍቅር ይዘን ያደግንም እንኖራለን


እዚህ ላይ ነጥቡ ምን ያህል ፍቅር ነው ወላጆቻችን ለኛ ለልጆቻቸው የሰጡት የሚለው ጥያቄ ነው ለዚህ ለፐርሶናሊቲ ዲሶርደር ትንተና የሚዳርገን

ከሁሉም የበላይ ለመሆን
ከሁሉም በላይ ተወዳጅ ለመሆን
ከሁሉም በላይ በትምህርትም በገንዘብም ለመብለጥ ትግል
እኔ ብቻ ነኝ አዋቂው : እኔ ለእኔ አንተም ለእኔ በሚል መመሪያ መኖር ማለት የእአምሮ ዲሶርደር ነው

ከላይ በተመለክተነው የቤተ ሰብ ፍቅር ላይ ተመርኩዘን ፐርሶናሊቲስ ዲሶርደር ምን እንደሆነ እንመለከታለን


ሳይካትሪስቱ ቆቁ
ቆቁ
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 4025
Joined: Sun Sep 21, 2003 9:57 am
Location: united states

PreviousNext

Return to Warka General

Who is online

Users browsing this forum: No registered users and 3 guests