ቂቅ wrote:.....ሪቾ :lol: :lol: ሁለት አመት ሙሉ አንዴ ወደ ፊት አንዴ ወደኍላ አንዴ ራቁቱን እያስደረገች በዌብ ካም ወላይትኛ ስታስጨፍረው ኑራ ዛሬ ፓስወርድክን ስትለው ግራ ይገባዋል እንዴ እንዴ .....
:D ቂቅ በዚህች የፓል ህይወት ውስጥ ትንሽ ተቀጥተህ ያለፍክ ለመሆኑ አጻጻፍህ ይመስክራል....;) አንተም መቼም ዋርካ የቆየህ ለመሆኑ ባያጠያይቅም ...የዋርካውን እንተውና እስኪ ስለ ፓል ጥሩም ሆነ መጥፎ ልምድ ያካበትከውን ንገረን..መቼም የፍቅር ትሬድ ላይ ስለ ፍቅር እናውራ...ግድቡን ደግሞ ግድብ እሚወራበት ቦታ እናወራዋለን ...ፎረም ላይ በአፍ ገንብተን ምናልባት ቶሎ ብንጨርሰው... :D
....ግን አንድ ነገር የዋርካ የቆየ ባህል ሆኖ ሰው ምክር ሲጠይቅ በቅን ከመምከር ይልቅ በስድብ እምንጀምረው...በቅን የመለሳችሁትን አይመለከትም.....ስለ ጉዳዩ ለመናገር እማንችል ከሆነ እና ህሳቡም እውቀቱም ከሌለን ሰው እሚለውን ማንበብ... የሳይበር ላይ ፍቅር በአሁን ሰአት በየትኛውም የአለም ህብረተሰብ ውስጥ ይተቀሙበታል....እንደ ፓል ቶክ ሁሉ ፌስ ቡክ ቲዊተር ...እዚህም ብዙ ሳንርቅ ሳይበር ኢትዮጵያ...Ethio love አሁን ይኑር አይኑር አላውቅም...እነዚህ ሁሉ ብዙ እማይተዋወቁ ሰዎችን እሚያገናኙ ናቸው....ፓል ቶክ እርግጥ የከፋ ጎን እንዳለሁ ሁሉ የትወሰነ ጥሩ ጎንም አለው...ሳያ ቁዋርጥ 24 ሰአት እሚገባ ሰው ወይም በማንኛውም ጊዜ ስትገቡ እምታገኙት ሰው ካለ....የ አእምሮ ጤነኛ ነው ብላችሁ ካሰባችሁ ተሳስታችሁዋል...የዛኑ ያክል በተለያየ ምክንያት እዛ ላይ እማይጠፉ ሴቶች ደግሞ ብዙ ጊዜ ጤነኛ ሆነው እሚያጠቡ ወይ ከልጅ ጋ እሚውሉ እናቶች የሆኑም አሉ....ከዛ ወጣ ብሎ ደግሞ በጣም ጥቂት ባይሆኑም በስራ ላይ ያሉ...የራሳቸውን ስራ እሚሰሩ ጊዜ ሲያገኙ ለጨዋታ እና ቀኑን ሙሉ ሲያወሩ እሚውሉ ሩሞችን እንደ ሬድዮ እሚያዳምጡም አሉ....የሰዎቹም ክላስ እንደ ሩሞቹ ይለያያል....እንደ SINGLE ROOM. Etio Love ROOM, Free YOUR MIND, Sex Extra Vag, etc አይነት ሩሞች አዘውታሪ ከሆንክ ክልልህን (ምድብህን) እራስህ ታውቀዋለህ.. :D እነዚህ ሩሞች ደንበኛ ከሆንክ ከላይ የጠቀስከው አይነት ካም አስከፍተውህ ያንጎራድዱህና ...ከዛ ኒክህን ከ እነ ካም ኤግዚቢት ድምጽህን ጨምረው ሩም ውስጥ ያሰሙልህል..ከዛ በቃ ተማረህ ኒክህን ትቀይርና እዛው ትሆናለህ ወይ ወደ ዋርካ ትመጣና ብሶትህን በተለያየ መልኩ ታወጣዋለህ.. :D
...ፖለቲካ ሩም ደግሞ ስትገባ ምንም የፖለቲካ እውቀት ከሌለው አንስቶ በማርክስና ኤንግልስ በቀበሌ እስካጠናው ድረስ እውቀት ያለው ይኖራል....ከዛም አልፎ ምናልባት ሩስያ ውስጥ ፖለቲካ የተማረም ላይጠፋ ይችላል...ሌላው ግን በገዛ ፈቃዱ ፖለቲካ ውስጥ ገብቶ እሚዳክር ነው.. :lol: እዛ ላይ እነ ማን ይውላሉ....? ከ እኔ ይልቅ ወያኔ አለቆችህን እና ጉዋደኞችህን ብትጠይቅ መልስ ታገኛለህ... :D
.....ወደ ምእራፍ ችግር ስንመጣ ...መተማመን ካለ ይላል ቅዱስ መጽህፉ ሁለት ሆናችሁ ተራራ መግፋት ትችላላችሁ...ሁለት አመት ሊያቆያችሁ የቻለ የራሳችሁ ምክንያት ሊኖር ይችላል....የስራ ጉዳይ ወይ የአገር መራራቅ ወዘተ...እንደ እኔ እንደ እኔ ግን እስክትገናኙ ግንኙነታችሁ ጥሩ ባላንስ የጠበቀ ይሁን ...ከተገናኛችሁ በሁዋላና የሁለታችሁ ኬምስትሪ ፊት ካደረገ ..አይደለም ፓስ ወርድህን ነፍስህን ዋርካ ላይ ነፍሴን ልስጥ ወይ ብለህ ሳትመጣ እዛው መስጠት ትችላለህ.. :D
....በልብ መታመን ከሁሉም ይበልጣል ...ልጅትዋ እምነት አታብህ ከሆነ ለመታመን ሞክር እንደ አገላለጽህ ልጅትዋ በጣም እምውትወድህ ትመስላለች ለዛም ነው ልቡዋ እምነት እንዲኖረው እና ሰላም እንድታገኝ ወጪ ገቢህን መቆጣጠር የፈለገችው...ያ ትክክል እንዳልሆነ ታውቀዋለች ...ምናልባትም ምን ያህል ለ እሱዋ ኦፕን መሆንህን ለማወቅም ይሆናል....እሺ ብትላት ላትቀበልህም ትችላለች ...ሴቶች ወንድን ብዙ ጊዜ መፈተን ይወዳሉ....;) እኛ ደገሞ ሁሌ ፈተናቸውን አናልፍም እንወድቃለን....ወይ እኛም ፈተና እናውጣ መሰለኝ...;)
ሰላም እንሁን :)