ይህ ስው ከዋርካ ነው?

The Love Forum (love, relationship) (የኔ ቆንጆ እንተዋወቅ :-)

Postby ፓፒዮ » Fri Nov 02, 2012 6:56 am

ሀሪከን2 wrote:የቦግዩ
ጠምደከዋል በሰላም ነው

አይገርምህም ገና አርስበታለሁ :lol: ሾትል እኮ ቀንድ የለውም እንጅ ጥቁር በሬ እኮ ነው

አንተ ግን ሾትል ስንቶችን የተከበሩ የዋርካ እድምተኞችን በዚህ እንደ ቂጡ በተቀደደ ክፍት አፉ እየዘለፈ ሲያባርር የት ነበርክ???


እውነቱን ለመናገር ስድቦቹና የፖለቲካ አመለካከቱ እንዲሁም ከሚገባው በላይ የተንዛዙ ጽሁፎቹ/መልሶቹ ባይመቸኝም የባለ ብዙ ታለንት ባለቤት መሆኑ የማይካድ ሀቅ ነው::

የሆነ ወቅት ላይ የሱን ታሪክ በተለይም ኬንያ እያለ ለማራቶን ሩጫ እንዴት እራሱን ትሬን እንደሚያደርግ አንብቤ ነሸጥ አርጎኝ(እሱ በዛ እድሜው ያን ያክል ወኔ ካለው እንዴት እኔ የሱን ግማሽ እድሜ ሄኜ እንዴ እሰንፋለሁ በሚል ወኔ,,,) ሩጫ ጀምሬ ነበር ግማሽ ማራቶንም ሮጬ እንደ ሀገሬ ልጆች ገንዘብ ባልሸለምም
የመኪና ቁልፍ መያዣ እንደተሸለምኩ ስናገር በኩራት ነው:: ኡራአ!!!!!!!!!! እንዲሁም የ እስፓርታ ሩጫ የሚባለውንም ሮጬ መጨረሴን ሳበስር እንዲሁ

ይሄን ሁሉ የለፈለፍኩት ሾተለን በዚህ አጋጣሚ ለማመስገን ነው
ፓፒዮ
አዲስ
አዲስ
 
Posts: 41
Joined: Tue Apr 17, 2012 8:28 pm
Location: agere mariyam

Postby ሾተል » Thu Nov 22, 2012 12:28 pm

ፓፒዮ


እውነቱን ለመናገር ስድቦቹና የፖለቲካ አመለካከቱ እንዲሁም ከሚገባው በላይ የተንዛዙ ጽሁፎቹ /መልሶቹ ባይመቸኝም የባለ ብዙ ታለንት ባለቤት መሆኑ የማይካድ ሀቅ ነው ::ፓፒዮ .....እውነቴን ነው የምለው ያንተን ጽሁፍ ይኼንን ያነበብኩት እንደለጠፍከው ወድያው ሲሆን በጣም ልትማርበት መልስ እመልስልሀለሁ ብዬ ሳበቃ የኑሮ ጉዳይ ሆኖ ምንም ጊዜ ባይኖረንም ሆነ ብዘናጋም አንድ ቀን እንደምጽፍልኽ አውቅ ስለነበር ጊዜው ይኼው ከች ስላለ ወደ ጽሁፉ ::

ሆነስትነት ከጽሁፍኽ ስላነበብኩ ደስ ብሎኛል ::አንድ ነገር ልንገርኽ አንባቢ አትመስለኝም እንጂ አንባቢ ከሆንክ ስለጽሁፍ መንዛዛት ወይም መርዘም ሳይሆን ኮምፕሌይን ማቅረብ የሚኖርብህ እዛ ውስጥ ስለተከማችሁት ሀሳቦች ነው ::ነፍሳቸውን ይማረውና የተከበሩ ደራሲ ሀዲስ አለማየሁ ፍቅር እስከመቃብርን ጽፈዋል ::መጽሀፉን ስታየው እንኩዋን ልታነበው ለጌጥ ለማስቀመጥም ቦታ ስለሚያጣብብ አንባቢ ካልሆንክ ጭራሽ መጽሀፉ ጋር ለመድረስም አትሞክርም ::ግና አንባቢ ሆነኽ ወይም ትግስት ኖሮህ መጽሀፉን ካነበብከው የማታገኘው ቁም ነገር የለም ::

ለምሳሌ ስምህን ስለወሰድከው ፓፒዮ መጽሀፍ እንሂድ ::መጽሀፉ አንድ ክፍለሀገር የሚያክል ግብዴ መጽሀፍ ነው ::መጽሀፉ የምርጦች ምርጥ ቢሆንም ስታየው ያስደነግጣል መጽሀፉ ትልቅ ከመሆኑ አንጻር ::በውስጡ የተንዛዙ ነገሮችም አሉበት ቢሆንም ማንበብ ከጀመርክ የማታስቀምጠው መጽሀፍ ነው ::

እኔ ለምሳሌ ትግስት ኖሮኝ ሹጉንን አንብቤያለሁ ::ስለጃፓኖች ታሪክ ነው ::ስንት ሺኽ ገጽ መሰለኽ ..... ታድያ የገኘሁት ቁም ነገርና ደስታ ይኼ ነው አይባልም..

እና እያልኩ ያለሁት የጽሁፉ መርዘምና መንዛዛት ሳይሆን አንባቢ ከሆንክ ውስጡ ምን አይነት ቅመማቅመሞች አሉት ?ጸሀፊው ምን ለመጻፍና ምን መልክት ለማስተላለፍ ፈልጎ ነው የጻፈው የሚሉትን ነገሮችን አንብበኽ ምንም ቁም ነገር ካላገኘኽበት ስለ ሀሳቡ አስተያየት ልትሰጥ ትችላለኽ እንጂ ገና ለገና ረጅም ጽሁፍ ተጻፈ ብለኽ ሳታነብ ሰልችቶኽ ከተውክ ባሉዋን ጎዳሁ ብላ እምሱዋን በእንጨት ስትበሳ አደረች እንደተባለው ሉዘር የምትሆነው አንተ ነኽ ::እና ምንም ነገር ይሁን አጠገብህ ካለ አንብብ....ከማንበብ ብዙ ነገር ይገኛል.....ለዛውም የምትጠላቸውን ጸሀፍት እያሳደድክ አንብ ከምትደግፋቸው ጸሀፍት ይልቅ....ለምን ብትል የምታደንቃቸው የሚጽፉት የምታደንቀውን ነገር ብቻ ስለሆነ....ግን ከማታደንቀው ጸሀፊ ደግሞ ያልገመትከው የምታደንቀውን ጽሁፍ ልታነብ ትችላለኽ....ጥሩውን ከመጥፎው ለማመሳከርስ ቢሆን ይነበባል እኮ::ከዛ የራስኽ አቁዋም ይኖርሀል....ያለዛ ባንድ ጎድ ብቻ ያዘነበልክ ሰው ትሆናለኽ....

ይሁን እንበልና እንዴው የሚጽፈው ጽሁፍ ተንዛዝቷል ያልከው ሾተል ያድርገውና አንድ ቀን የሚያስገርም መጽሀፍ ጽፎ ጉድ እየተባለ መጽሀፉ ቢነበብለት ወይኔ ለካስ ተሸውጃለሁ ብለኽ እዚህም ስጽፍ የነበረውን ጽሁፎች ስታነብ ልትከርም ነው ? ቅቅቅቅቅቅ.....ሁ ኖውስ

እዚህ ዋርካ ላይ በሰው ሰው እየሰሙ ስለ እኔ ባለጌነትና ተሳዳቢነት ወዘተ ሰምተው ሲያበቁ አናነበውም ብለው ወስነው ሳለ አንድ ቀን በስህተት የሆነ ጽሁፎቼንአንብበው የልባቸው የሚደርስ ጽሁፍ ሆኖ አግኝተውትና ተምረውበት ሲያበቁ ለካስ ሾተል እንደዚህ ያለ ጸሀፊ ነኽ መች አወቅን ቆይ እስቲ ፕሮፋይልህን ወደ ሁዋላ ተጎዘን ከዚህ በፊት የጻፍካቸውን ጽሁፎች እናንብ ብለው ከአንድም ብዙዎች ጽሁፋችንን አድንቀው .....ከእኛ መማራቸውን የመሰከሩልን ብዙዎች ናቸው ::አይዋሽ ነገር ሰዎቹም እዚህ ሾተልም እዚህ.....ምስክር መሆን ይችላሉ....ወይም አስፈላጊ ከሆነ ወደ ዋርካ ቀደምትም ሆነ የአሁን ጽሁፎች ወረድ ብሎና ፈለግለግ አድርጎ ማምጣት ይቻላል::

እና ጽሁፌ ረዘመ ወይም ተንዛዛ ብለኽ አትተወው ....ግድ የለኽም አንብበው .....ትማርበታለኽ ....ችግሩ የመረዳትና ያለመረዳት ነገር ስለሆነና አንዱ ቀድሞ የመሄድና አንዱ እዛው የመንጎአለል ነገር ሆኖ ይሆናል እንጂ እራስኽን አደነቅክ አትበለኝና ስድባ ስድብ የምጽፋቸውን ተዋቸውና ቁም ነገር የምጽፋቸውን ጽሁፎች አንባቸው ::ያስተምሩሀል ...ይቀይሩሀል .....ምንም መመሳሰል የሌለባቸው አንዱን ለመካብ አንዱን ለማውረድ ተብለው የተጻፉ ወይም የሚጻፉ ጽሁፎች አይደሉም ::ሰው ወስዶ ግሩፕ ውስጥ ስለከተተን ሾተል የዛ ግሩፕ አባል ነው ማለት አይደለም እንዴውም ሾተል ይኼ ግሩፕ ነው ብለኽ እራስህን አታሳምን ....እግዚአብሄርን ነው የምልኽ እኔ የእግዚአብሄርና የእኔ እንጂ የማንም አይደለሁም ....የቤተሰቦቼ እንኩዋን አይደለሁም ::በራሴ የህይወት ፕሪንሲፕል የምመራ ማንንም የማልከተል የራሴ የሆነ ህልምና ሙከራ ያለኝ ከማንም ጥቅም የማልፈልግና ለጥቅም ብዬ የማልኖር .......ሳይኖረኝም ለብዙ አመት ኖሬ የማቅና ኖሮኝም የማውቅ ......እዚህ አውሮፓ ሳይቀር ምንገድ ላይ ከማደር ያልተናነሰ ህይወት ጀምሮ አንቱ ተብሎ በጋዜጠኞች ታጅቦ ሆይ ሆይ እየተባለልን አሉ ከሚባሉ ትላልቅ ሰዎች ሽልማትን የተቀበልኩና እየተቀበልኩ የምገኝም ማለት ሁሉንም ያየሁና በሁሉም ኢንቫይሮሜንት ውስጥ መኖር የምችልና ምንም ነገር የማያስደንቀኝ አንድ ተራ ሰው ስሆን ማንም እኔን በጥቅም ሆነ በማስፈራራት ሊገዛኝ ሆነ ኮንትሮል ሊያደርገኝ የማይችል በራስ መተማመን እግዚአብሄር አድሎ የሰጠኝ አንድ ተራ ስደተኛ ስሆን በህይወቴ ውስጥ ምቾት ተመኝቼ የማላውቅ ነገር ግን እግዚአብሄር እየሰጠኝ እንዳለው አብዝቶ ቢሰጠኝ አሁንም ለሰዎች እንደምኖረው ለወደፊቱም ያለኝን ለሰዎች አከፋፍዬ የለት እንጀራዬን መግዣ ብቻ አስቀርቼ የምኖርና እንደዛ እየኖርኩ ያለሁ በቀን አንድ ጊዜ ብበላም ሶስት ጊዜ ብበላም ለእኔ ያው እንደሆነ ያወቅኩ ሰው ስሆን ሰው ስለመደበን ነን አይደለም ......እና እኔ የማንም እንዳልሆንኩና ፖለቲካ የምጠላና የማንም የፖለቲካ አጋፋሪ ሳልሆን የታየኝን መናገር የጀመርኩ ምንም ሆነ ምን አደጋም አመጣ አላመጣ እውነት የሆነውን ከታየኝ እውነት ነው ብዬ ባቅሜ ምንም ባላመጣ የምናገር ሰው መሆኔን አውቀኽ ልቦናህን ባላንስድ አድርገኽ ከሰው መማር የምትችል ሰው መሆንህን ስላወቅኩ ጽሁፎቼን አንብባቸው ::

ያልገቡህ ነገሮች ካሉ ጠይቀኝ ፈትፍቼ አስረዳኻለሁ ::የምጽፋቸው ጽሁፎች የተገለበጡ የተሰሙ ሳይሆኑ ከህይወት ልምድ በመነሳት ስለሆነ ሰከንድ ሀንድ ጸሀፊዎችን ለጊዜው ወድያ በላቸውና እራሱ ፈርስት ሀንዱ የጻፈውንና የሚጽፈውን አንብብ ::ማለቴ ምንም ጊዜ አንድ ባዮግራፊን እራሱ ባለታሪኩ የጻፈውና ሰው የጻፈለት አንድ አይደለም ::እራሱ አንድ ሰው ታሪኩን ከጻፈው የኖረበትንና በኖረበት ስሜት ስለሚጽፈው እውነተኛነቱ ሰው ከጻፈለት ቅይጥ የለበት ::

የምለውን ትረዳ ይሆናል .....ካልተረዳህ እዚህ ዋርካ ልይ ስጽፍ አንድን ሰው ታርጌት አድርጌ ስለማልጽፍ ጽሁፋችንን እየተከታተሉ የሚያነቡን ያነቡናል ...መውሰድ ያለባቸውን ከእኛ ይወስዳሉ ::

እኔ የፖለቲካ አመለካከት የለኝም ::እኔ ያለኝ አይናችሁን ጨፍኑና እናሞኛችሁ የሚሉትን አልቀበልም ነው ::ወያኔ እንደጥፋቱም ብዙ ልማቶችን ሰርቶ ሲያበቃ አልሰራም ቢሉኝ እንዴት ልመን ?ተቃዋሚ ነን ተብዬ ስለአንድነት ሰብከውን ሲያበቁ ረስተውት የትግራይን ህዝብ እናጥፋ እያሉ የስድብና ዛቻ ዘመቻ ሲያካሂዱበት እንዴት ህሊናዬ ይቀበል ?እድሜ ዘላለም ይበሰብሱ እንዳልነበር እነ አትሌት ሀይሌ ገብረስላሴንና ፕሮፌሰር ይሳቅ በአማላጅነት የታሰሩትን ቅንጅቶች አስፈትተው ሲያበቁ እነዚህ ታላቅ ያገር ሽማግሌዎች ጋር የስድብና ጥላቻ ዘመቻ ሲዘመትባቸውና በአለም አንገታችንን ቀና አድርገን እንድንሄድ አስተዋጽኦ ካደረጉልን በኦሎምፒክ ድል ያጎናጸፉን ከነ ጀግናው አበበ ቢቂላ ቀጥሎ እንደ ሀይሌ አይነቶችን የጀግናም ጀግኖች በአለም ከ 27 በላይ የአለም ክብረ ወሰን ሰብረው ስማችንን ከፍ አድርገው ከነባንዲራችን እንዲውለበለብ ያደረጉልንን ጀግኖች በርሊን ማራቶን ላይ ሊሳተፉ ሲሉ ምንገድ ላይ እንፍጃቸው ....ሪከርዳቸውን እንዳያሻሽሉ በባንዲራ ጠልፈን እንጣላቸው ሲሉ እንዴት ሾተል (አምባቸው አባተ ደጀኔ ) ይኸንን ነገር ተቀብሎ አብሮ ይራገብ ?.....እንዴትስ በገዛ ገንዘባችን የተገነባው ግልገል ግቤ 3 የተወሰነ ሜትር ግንባታው ቢፈርስ እንዴት እንደ ከብቶቹ ተቃዋሚ ነን ባዮች አብሬ እልልልልል ልበል ?

እረ እንዴት ?እንዴት የልማቱ ንጉሰ ነገር መለስ ዜናዊ ከኢትዮዽያ አልፎ ባፍሪካ ....ካፍሪካ አልፎ በአለም በሰራቸው ስራዎቹና ጭንቅላቱ ክብር ተሰጥቶትና ጭንቅላቱ ዳይናሚክ ነው ተብሎ እየሰማሁና እኔም በሰራቸው ከድህነት ሊያወጣን የሚችል ፕሮጀክቶቹ መደሰት ሲገባኝና በዚህ ታላቅ ሰው መኩራት ሲገባኝና ማድነቅ ሲገባን ስችል ደግሞ የጀመራቸውን የልማት ፖሊሲዎች ማገዝ ሲገባን ላውግዝ ?

ይኼው እንግዲኽ ላይመለስ መለስ ሞተ ::ታድያ እነዛ ያስገነባቸውን ድልድዮች ....መንገዶች ....ኮንዴሚኔም ቤቶች .....ሆስፒታሎች .....ትምህርት ቤቶች ....የገጠር ልማት ፕሮጄክቶቹን ወዘተ ይዞ ሄደ ?አልሄደም ....ኢህአዴግም ለዘላለም አይኖርም ........ግን ገንብቷቸው የሚያልፋቸው ልማቶች ለአሁኑ ትውልድም ሆነ ለመጪው ትውልድ ጥቅም ናቸው :: ያንን ነው በርቱ እያልን እያበረታታናቸው ያለነው::የሰራ ሰው ስህተት አይሰራም አይደለም::ብዙ የሚታዩና የማይታዩ ስህተቶች አሏቸው::ለልማት ተብሎ ከሚወጣው በጀት ግማሹ ግለሰቦች ኪስ እንደሚገባና የተጀመረን ልማት በሆዳምና ስግብግቦች የተነሳ ልማቱ እየቆመ ብዙው ጅምር ዳሜጅ እየሆነም ያየናቸው ነገሮች አሉ....በየምስራቤቶቹ ብዙ የጉቦ ትእይንቶች እንዳሉም የሚታዩ ነገሮች ናቸው::ያንን ደግሞ መንግስት እየተከታተለ አጥፊዎቹን ለፍርድ እያቀረበ ያየነውም ነገር አለ::ሁሉም ነገር ጅምር ስለሆነ የሚሻሻል ነገር ሲሆን እኛም ያቅማችንን አልሚዎቹን ካገዝን ያለንን እውቀት ካካፈልን ሁሉም ነገር በቀጥታ ይሆንና ሁሉም በጥቅም ፍቅር ሳይሆን በአገር ፍቅር አገርን ያለማል::ስለዚህ አስተዋጾ ለማድረግ እጃችንንና እውቀታችንን ለአገራችን እድገት እንስጥ.....

የሚደገፈውን እየደገፍን ከብቶቹ የሚቃወሙትን ምታድ የማያሰማ ጩኸትና መሰሪነት ብንቃወም ብንቃወም ፖለቲከኛ ናችሁ ብላችሁ እላይ ሰቅላችሁ አስደሰታችሁን ::ከወያኔ ጋር አንድም ጉዋደኝነት ሆነ ቻት እንኩዋን አድርገን ሳናውቅ ባልተዋጋነው ባልዋልነው ወያኔ ናችሁ ብላችሁ ለጀግኖቹ ጎራ ዱላችሁን አስደሰታችሁን ::ምናለ ህሊና ፈቅዶልን እነሱም እሺ ብለውን እነሱን በሆንን ?ግን እነሱም እሺ አይሉን እኛም ህሊናችን ለማንም እንድንሆን አይፈቅድልንም ::እነሱ ሰው አጥተው አንድ የዘመነ ካለብ ጊዘ ስደተኛን ና ስራልን ወይም ከእኛ ጋር ተሰለፍ ብለው ሲያስገቡኝ....ድንቄም አለች ወይዘሪት ባፈና.....ታድያ ወይ ነዶ አያስብልም ?

እስቲ መጣን

ሾተል ነን .....................እራሱ ከራሳችን
እሰይ ተመስጌን አምላኬ ለካስ በክብርነቴ እራሴን ሆኜ እኔነቴን ፈልጌ አግኝቼዋለሁ !?
ሾተል
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 9645
Joined: Thu Jan 13, 2005 9:42 pm
Location: Vienna-Austria

Postby ቱሉቦሎ » Thu Nov 22, 2012 2:07 pm

መቶ በመቶ እርግጠኛ ነኝ ፓፒዮ ከላይ በማንዛዛት የጻፍከውን አያነበውም :: እንደኔው ጨረፍ አድርጎ ነው የሚያልፈው

ሀሳብን በአጭሩ ለመግለጽ መቻል ራሱ አንድ ችሎታ ነው
የጸሀፊነት ወይም የተናጋሪነት አንዱ መስፈርት ነው ( ት/ቤት እያለን ስለዚህ ርዕስ በ500/1000... ወዘተ ቃላት ድርሰት ጻፍ የሚለውን አሳይንሜንት ያስታውሷል)

የአጻጻፍ ችሎታ የሌላቸው በስሜት ወይም አዋቂ ነኝ በሚል በተሳሳተ እምነት በመገፋት አሰሱን ገሰሱን ከእንጭጭ አንጎላቸው እንደፈሰሰ ያለገደብ በማንዛዛት ይለቀልቁታል ::
ቱሉቦሎ
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 195
Joined: Tue Sep 04, 2012 8:13 pm

Postby ሾተል » Thu Nov 22, 2012 4:42 pm

ቱሉቦሎ wrote:መቶ በመቶ እርግጠኛ ነኝ ፓፒዮ ከላይ በማንዛዛት የጻፍከውን አያነበውም :: እንደኔው ጨረፍ አድርጎ ነው የሚያልፈው

ሀሳብን በአጭሩ ለመግለጽ መቻል ራሱ አንድ ችሎታ ነው
የጸሀፊነት ወይም የተናጋሪነት አንዱ መስፈርት ነው ( ት/ቤት እያለን ስለዚህ ርዕስ በ500/1000... ወዘተ ቃላት ድርሰት ጻፍ የሚለውን አሳይንሜንት ያስታውሷል)

የአጻጻፍ ችሎታ የሌላቸው በስሜት ወይም አዋቂ ነኝ በሚል በተሳሳተ እምነት በመገፋት አሰሱን ገሰሱን ከእንጭጭ አንጎላቸው እንደፈሰሰ ያለገደብ በማንዛዛት ይለቀልቁታል ::


እንደናትህ ---- ሳታውቀው ሁለም ታለቀልቃለኽ እንጂ የሚፈለገው እንዳንተ ያለው ልፋጫም ከብት እንዲያነበኝ አይደል ?ይኼው እየተዝረከረክ መጥተኽ እራስኽ አነበብከን እኮ .....ሌላ ክብርነታችን ምን ይፈልጋል ?አንድም ሶስትም ካነበበኝ በቃኝ ......ብዙ ምን ይሰራል ....ማንበብህን አንተው አረጋገጥክ ....አንተማ የሚገርመው ከማንበብ አልፎ ልክ እኔ እየሆነ ነገር ጽፌ እንደለጠፍኩ ወድያው ኮፒ አድርገኽ ሀርድ ዲስክህን ማጣበብህን ባለፈው ሳታውቀው ተያዝክ እኮ ...

ባለፈው ፖለቲካ ሩም ለጠፍኩና የጽሁፍ ግድፈት ስለነበረው ለደቂቃ ሰርዤ ግድፈቴን አስተካክዬ እስክለጥፍ ድረስ በምኔው መጀመርያ የለጠፍኩትን ኮፒ አድርገኽ ማስቀመጥኽ እስካሁን ድረስ ግርም ሲለን ለካስ እንደዚህ የከብቶቼን አንጎልና ነርቭ ብቻ ሳይሆን እየተጫወትኩበት ያለሁት ጊዜያቸውንና ሀርድ ዲስካቸውንም እንዲሁም ኑሮዋቸውንና አላማቸውን ጭምር ነው ብዬ እንድገረም ሆንኩኝ ::

ከብቶ ቱለማ አንድ ነገር ልንገርኽ እዚህ የሆነ ነገር ከጻፍኩም ሆነ ከለጠፍኩ አምኜበት ስለሆነ አፍሬ የምሰርዘው ነገር አይኖርም .....ስለዚህ እኔን ያገኘኽ ያዝረከረክ መስሎህ አትልፋ ...ምን አልባት ሌሎች ላይ ይሰራል ....የምለው የምጽፈው የምናገረው የእምነቴን ስለሆነ ነገሮችን ረስቼ አልቀላቅልም .....እና እኔን ላያዋጣኽ መከታተሉን ተውና ሌላ ሰው ጋር ፎከስ አድርግ .....ለምን ብትል ከንቱ ጊዜህን ከማባከን ውጭ የምትፈጥረው ነገር ስለማይኖር በእኛ ላይ ማለት ነው ::

እኛ በፓልቶኩም በዚህም ጥሩነትን ክፋትን ብሽሽቅን ማናደድን ሰው ላይ ሙድ መያዝን ሁሉንም የተማርንና በዛ ውስጥ ለሙድ ቀን መግፊያ በትርፍ ጊዜ እየተጠቀምን ስለሆነ እውነቴን ነው የምልኽ ኢትዮላቭና ሳይበር ዋርካ ላይ በመሰድደብና በመበሻሸቅ እድሜውን ያጋመሰ ሰው ጋር ምንም ብሽሽቅ ባትሞክር ጥሩ ነው .....ምክሬ በብላሽ ነው ::እርስ በርሳችን ያልተማማርነው ነገር የለም ......ስለዚህ እኛ የኢትዮሎቭ አባላቶችን ማንም ሊያበሽቀን ቀርቶ ሊሞክረን የሚሞክር እራሱ የጅል ጅል ነው ::እኛ ግን ነርቭ በጥሰን ያልጋ ቁራኛ ሁሉ ልናደርግ እንችላለን ::

እስቲ እነ እኔውነኝ ሀዲዱ ወዘተ ሌሎቹም ክብርነታችን ጋር ጨዋታ ጀምረው ሲያበቁ አሁን የት አሉ ?አቫንስ ሰጠናቸውና ውር ውልፊት ውልፊጥ ቢሉ ልክ የመልስ ምት ስናስገባላቸውና የለበሱትን ልብስ ስንነግራቸው ወድያው በድንጋጤ ላጥ እንዳሉ ቀሩ ::አለማችን ትንሽ ነች ::

ለዛ መሰለን ከትንቢተ ዳንኤል ጋር ባጋጣሚ ተጋጭተን ስናበቃ አለም የሁላችን መዳፍ ውስጥ እንዳለች አውቀንና የምንተዋወቅ ዘመዳሞች ሆነን ተገኝተን ወድያው ይቅር ተባብለን ዝምድናችንን ያጠናከርነው ::

አታውቀኝም ካልክ ፍቃዱን ስጠኝና የዛሬውን ብቻ አይደለም የዛሬ ሳምንት ምን እንደበላህና ምን እንደለበስክ የት እንደምትውል መልክና ቁመናህን ሳይቀር ልነግርኽ እችላለሁ ::እንዳትረሳ ስማችንን ፍታው ....ሾተል ስንሆን ዝም ብለን ሳይሆን ሾተልም ስለሆንን ጭምር ሲሆን እንደ ንፋስ የትም ቦታ እንገኛለን :: ዩ ጋት ሚ ራይት ?

ለማንኛውም ይመችኽ .....

ተጫወት


ግን ሮንግ የሆነ ቦታ ሆነ እንጂ ጨዋታኽ ...

አንተማ ከትንቢተ ዳኔል ጋር ልታጣላ ማንቋለጥኽ ነበር ...ግን ሳይሳካልኽ አፍረኽ ዱቅ አልክ እንጂ ::

ያላወቅከው መሰደብ ካለበት ማንም ይሰደባል ...እራሴም መሰደብ ካለብን ድብን አድርጌ እሰድበዋለሁ ::መከበር ባለበት ሰአት ደግሞ ሰው ይከበራል ::

አሁንስ ተረዳኸኝ ?

ግን ያጣቢ ልጅ አለቅላቂ አትሁን ....እራስኽን ሁን ::ይረዳኻል ...እንደቀልድ ማለቅለቅ ጀምረኽ በዛው ከሄድክ የገሀዱ አለምህን ሊጎዳውና ከሰው ልትገለል ሁሉ ትችላለህና ለምታደርጋቸው ቀልዳቀልዶች ጥንቃቄ አድርግ ....ሳታስበው ወደ እውነት ተቀይሮ የሆነ ጊዜ ዘልቆ ወጥቶ ሊያዋርድው ይችላልና ::

ቻው

ሾተል ነን ,......ምክራችን በብላሽ
_________________
እሰይ ተመስጌን አምላኬ ለካስ በክብርነቴ እራሴን ሆኜ እኔነቴን ፈልጌ አግኝቼዋለሁ !?
ሾተል
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 9645
Joined: Thu Jan 13, 2005 9:42 pm
Location: Vienna-Austria

Postby ቱሉቦሎ » Thu Nov 22, 2012 6:05 pm

እስኪ አንብቤ መልስ እንድሰጥህ ከላይ እንደበሬ አንጀት ያዝረከረከውን ሀተታ በአጭሩ ጻፈው :: ከላይ እንዳለው ገና ሳየው ነው ቋቅ ሊለኝ የዳዳኝ

ታዲያ አትሞጣሞጥና ባፍህ አትቅዘን : ስድብ ወይም ተሳዳቢ ያስጠላኛል
ቱሉቦሎ
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 195
Joined: Tue Sep 04, 2012 8:13 pm

Postby ትንቢተ ዳንኤል » Thu Nov 22, 2012 7:23 pm

ሾተል እንደጻፈው
አንተማ ከትንቢተ ዳኔል ጋር ልታጣላ ማንቋለጥኽ ነበር ...ግን ሳይሳካልኽ አፍረኽ ዱቅ አልክ እንጂ ::


ጥላቻን ለሚዘሩ: ፍቅርን ለማያዉቁ: አክብሮት ለራቃቸው: ፈጣሪያቸውን ለማያከብሩ : ፍርቻና ጭንቀት የሞላበት ሕይዎትን የሚገፉ: ሌላውን ሲያጋጩ የነሱ ሰላም የሚመለስላቸው የሚመስላቸው ህልመኞች: ራሳቸውን ፈልገው ማኝት ሲያቅታቸው የሌላውን እንደጭራ እየተከተሉ ሰላማቸውን ለማደፍረስ የሚፍጨረጨሩትን አስተሳሰቦች ከመሰረታቸው ለማጥፋት በተጠራው ጉባኤ ላይ ተሳትፈን ስለነበር: በተማርነው መሰረት የጥላቻ አስተሳሰቦችን ወደየመጡበት እንኩዋን እንዳይመለሱ መንገዱን እንደ እየተገደበ እንዳለው የአባይ ግድብ ገድበንባቸው: መውጫው ጠፍቶባቸው እየዳክሩ ባለበት ሰአት እኛ ከወንድማችን ተስማምተን ወደፊትም ከፈጣሪ ጋር በሰፊው ልንወዳጅ እቅድን አድርገን ጥላቻን አንገቱን በማስደፋት ሂደቱ ዉስጥ ተሳታፊ እንድንሆን የፈቀደ ፈጣሪ ይባረክ::

ፈጣሪ አለማትን ይባርክ
ትንቢተ ዳንኤል
አዲስ
አዲስ
 
Posts: 17
Joined: Fri Nov 02, 2012 1:44 pm

Previous

Return to Warka Intimate - ዋርካ ፍቅር

Who is online

Users browsing this forum: No registered users and 5 guests