ፍቅር ምንድነው..?

The Love Forum (love, relationship) (የኔ ቆንጆ እንተዋወቅ :-)

Re: ፍቅር ምንድነው..?

Postby ለማ12 » Mon Nov 26, 2012 10:02 am

ክቡ ሰላም ነው ?


አልሰሜን ግባ በለው አሉ
ማነን ማን ይዳረው ? አንተ እኔን ወይስ እኔ አንተን??


በነገራችን ላይ ጽሁፎቼ መነሻና መድረሻ አላቸው ተከታተላቸው: ዝም ብለው የሚጠቀጠቁ አይደሉም:
ቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅክቡራን wrote:ወይ ወንድሜን ለማ ...ፍቅር እንደ ሴት ስካር አይነት ነው አልክ... :D ለዚህ ነው ለካ አንዳድንዴ ጠጅ ጠግቦ ሞቅ ያለው ጽሁፍ የምትጽፈው..? :D አይዞህ !! አሁን ደርሽልሀለሁ...ትንሽ ቀን ነው..ሴትየዋ መጥተው መልስ ሰጥተዋል...አንተም በርታ በል ርዳኝ...ህይ ሀው አር ዩ በል...ዝም ብለህ ጭራና እግር የሌለው ተረት ብቻውን ካላማችን አያደርሰንም....እንደውም በቅርቡ I love you more than I can say..በሚል ርዕስ አንድ ቤት እንድትከፍት ሀሳብ እሰጣለሁ:: ሴትየዋ ረቀቅ ያለ እንጊሊዝኛ ከጀመሩ አለሁ..እንራዳለን.. :D አይዞን ለማዬ ዘንድሮ አንተን ካልዳርኩማ እኔ ክቡራን አይደለሁም.. :D !!
ለማ12 wrote:ክ ቡ ሰላም ነው?

ፍቅር ምንድን ነው አልክ?
ዝም ብሎ የሚአስለቅስ እንዲያው በደፈናው እንደ ሴት ስካር አይነት
የሴት ስካር ታውቃለሕ ??ክቡራን wrote:አሁን ሳስበው የቡዙዎቻችን ችግር ይሄ ይመሰለኛል...:: እረ አንደውም ያለም የራሷ ችግር ይሄ ሳይሆን አይቀርም:: ፍቅር ማለት ምን ማለት ነው..?? አንድ ሰው ከተቃራኒ ጾታ ጋር ፍቅር እንደያዘው በምን ማወቅ ይቻላል..? በውነት ያፈቅረነው ወይም ያፈቀርናት ልጅ አፈቅርኩህ ( ሽ) የምነለው ራሳችን ስለምንወድ እንጂ እሱን ወይም እሷን እንደምነለው ወደናት ይሆን..? በፍቅር ውስጥ ራስን መወድድ ካለ ፍቅር አለ ማለት ይቻላል? ስሜትንና ፍቅርን እንዴት መለየት ይቻላል? እስኪ ልምዳቹሁንና ገጠመኛችሁን እንወያይ...የፍቅር ታሪካቹህንም ማውጋት ይቻላል.. :wink: ይሄን ውይይት እኔ ክቡራን ሆስት አደርጋለሁ:: መልካም የፍቅር ውይይት:: :D
ለማ12
ውሃ አጠጪ
ውሃ አጠጪ
 
Posts: 1144
Joined: Sat Jun 16, 2012 9:46 am

Postby recho » Mon Nov 26, 2012 5:27 pm

ክቡ .. ክብነት .. ክቡዋለም .. ክባችን :lol: :lol:
አንተ ልጅ ግን ከምርን አንድ ነገር ሁሌ የሚገርመኝ ራስህን ለሚተኩሱብህ አዘጋጅተህ የምትቀመጥበት ምክኛት ብቻ ነው ቅቅቅ
ጠያቂው ቢያስቸግረኝ
ስለፍቅርሽ ሁኔታ
አልወዳትም አልኩዋቸው
እንዲያገኙ ደስታ ዲም ዲርሪም ዲርንንን ቅቅቅ ይችን ዘፈን ለኔ እንደመረጥክልኝ ገብቶኛል .. አይዞህ አትፈር እንዴ ፍቅር ባንተ አልተጀመረ .. አሁን እጅጽፈቴን ፕሪንት አርገህ ከአልጋህ ፊትለፊት እንደለጠፍከውና እሱን ካላየህ እንቅልፍ እንደማይወስድህ የማያውቅ ዋርካዊ አለ ? ሰሞኑን ጠፍተሀል ደግሞ .. ሰው ያስባል ይጨነቃል በል .. ለምዬ ከእጅህ ላይ ሙጭልፍ አርጎብህ ሲሄድ ዝም ብለህ ትረታለህ ? አየየየየየየ :lol: :lol: :lol: :lol: :lol:


ክቡራን wrote:አንዱ የፌስ ቡክ ጠረንገሎ ይሄን ቤት የከፈትከው ፍቅርን አጣጥመህ ስላማታውቅ ነው አለኝ...ፍቅር ቢገባህ ኖሮ ፍቅር ምንድነው ብለህም ባልጠየክ ነበር አለኝ ቀጠለና ...እስኪ ይሁና... :D : የምስጋናን ቀን ከዘመድ ከወዳጅ ከጔደኛ ( ከፍቅር ወይም ከትዳር ) ባጠቃላይ ሰብሰብ ብላቹ ለምታከክብሩ (እኔም ከዘመዴ ጋር ኩክ አድርገን እንግዶቻችን እየጠበቅን ባገኘኌት ደቂቃ ነው እቺን የምጽፍላቹ) ለሁላችሁም ሀፒ ታንክስ ጊቪንግ ደይ እየተመኘሁ...ለቤቷ ተስማሚ ናት ያልኩትን ሙዚቃ ስመርጥ በታላቅ ደስታ ነው:: በፍቅራችን መኅል ...ሚኒልክ ወስናቸው ነው...እቺን ጠቅ:: ለማ ጠቅጥቅ.. እንግዲ እንዳንተ የተመቸው ማን አለ....?? :D
"ሰነፍ በልቡ። አምላክ የለም ይላል በሥራቸው ረከሱ ጐስቈሉ በጎ ነገርን የሚሠራ የለም " መዝሙረ ዳዊት ምእራፍ 14:1
recho
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 3171
Joined: Mon Sep 20, 2004 12:28 pm
Location: Earth

Postby ቁምቢ » Mon Nov 26, 2012 9:23 pm

ፍቅር የብዙ ስሜቶች ድብልቅ ነው እነሱም

ደስታ-ፈልገህ ካገኝ?ው

ሀዘን-የምትወዳት ስትከዳህ

ቅናት- ባላጋራ ሲመጣብህ

ጥላቻ- ሲያልቅ-----

ፍቅር ህይወት በአንድ ቃል ማለት ነው:: ፍቅር ከሌለ ህይወት የለህም ካለ ፍቅር የሚኖር ማንም ሰው የለም:: እግዚአብሄር ፍቅር ነው:: ስንሞት አሉ የድሮ ሰዎች ሲናገሩ ክፉ ሰዎች ከሆንን የእግዚአብሄር ፍቅር ከኛ ይለያል ብቸኝነቱ የከፋና እጅግ ከባድ ይሆናል...በዚ ላይ የገሀነም እሳት ሲጨመርበት......ጨርቅህን ጥለህ ነው ይምታብደው--- የፍቅርን ሀያልነት ከዚህ መገንዘብ ትችላለህ------ለመሆኑ አፍቅረህ ነው ተፈቅረህ ትርጉም ፍለጋ የምትባዝነው :?:
የሰው ልጅ
መውደድ ሲችል መጥላቱ
መምከር ሲችል ማማቱ
መስራት ሲችል መቅናቱ
ማስታረቅ ሲችል ማጣላቱ
ያሳዝናል የሰው ፍጥረት በሕይወቱ፥፥
ቁምቢ
ጀማሪ ኮትኳች
ጀማሪ ኮትኳች
 
Posts: 83
Joined: Mon Nov 26, 2012 3:55 am

Postby ክቡራን » Mon Nov 26, 2012 10:21 pm

ቁምቢ ፍቅር ተነተነውና እንዲህ ል ጠየቀኝ...:
ለመሆኑ አፍቅረህ ነው ተፈቅረህ ትርጉም ፍለጋ የምትባዝነው
_________________
አሪፍ ጥያቄ ናት.. :D ሁለቱንም ሆኘ ነው..:: :D ትንትናህ ግሩም ነው ተመችቶኛል..!
ፍቅር ማጣት እኮ ግን በራሱ ገኅነም ነው...የእጊዚአብሄርን ፕርዘንስ ስታጣ እዛ ጋ ሲኦል ይጀምራል:: ሌላ እሳት ለምን ይጨመራል...? እስኪ አስፋፋውና ሂድበት ይሄን ሀሳብ...


ሪቾ ..ሬቾ....የኔ ከረፈፍ ...የሚኒልክ ዘፈን ለኔ ነው የተመረጠው እያልሽ አስረኛ ፎቅ ላይ ተቀምጠሽ ሸልዪ...እሺ...የኔ ባለ ቴክስ ኮፍያ.. :D እኛ ፈርስት ፍሎር ላይ ስራችንን እየሰራን ነው...ይሄን ዝግጅት ደሞ አዳምጭውና ለኔ የተመረጠ ሙዚቃ ነው በይ እሺ... ጠቅ አድርጊው ማታ ማታ ቢፎር ዩ ጎ ቱ ቤድ.. :D
እቺን ጠቅ..
ክቡራን
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 8282
Joined: Tue Mar 04, 2008 4:24 pm

Postby ሓየት11 » Mon Nov 26, 2012 11:37 pm

ክቡራን wrote:
እቺን ጠቅ..
[/color]

ስሚ እንጂ ክቡ ... ሪች ጠቅልላ ገባች እንዴ? ... የሷን ድምጽ ነው የምሰማው ያንተን ... ቅቅቅ ... አይ ክብነሽ ... እንደው በዛች ሰላላ ድምጽህ ... መደጋገም ታበዛለህ ... ቅዱስ ጎርጊስ ድግምት ይደግምብህና :lol:
ሓየት11
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 2945
Joined: Sun Apr 06, 2008 7:34 pm
Location: ላን'ሊይ

Postby ክቡራን » Mon Nov 26, 2012 11:49 pm

ችግሩ እኮ ያለው አንተ ጋ ነው ጺላው...ያንተው ኅኅኅኅ ህ..ክ..ታ.. አይነት ድምጽ ስለሆነ ሁሌም ያንን ስለምትሰማ የሌላው ሰው ድምጽ ሁሌም ላነተ የቀጠነ ቡና ይሆንብሀል...ለዛ ነው...ሰው ያጋዘን ድምጽ ይዞ ይፈጠራል...?? !! ማስፈራሪያ!! :lol:
ክቡራን
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 8282
Joined: Tue Mar 04, 2008 4:24 pm

Postby ሓየት11 » Tue Nov 27, 2012 12:00 am

አሄሄ ህደግ ሞ አታ ... የኛ ድምጽ ... ልክ እንደ ስቴሪዮ ጠዳ ያለ ... ፋይን ቲዩን የተደረገ ... የሪቾን ልብ ደብል የሚያስመታ ... አይነት ነው ... እስቲ ሪቾነት ብቅ ትበልና ቃሏን ትስጥ ... እንግዲህ ያንተንም የኔንም ሰምታለች ... የለማንም ሳትሰማ አትቀርም ... የማን ድምጽ የልብ ምንቷን ያፈጥናል ... ትናገር ...

ይልቅ ... ሰላላነቱን ምንም አታደርገውምና ... መደጋገሙን ተው ... ሾካካ ነገር ያስመስልሃል ... ቅቅቅ ... አቡዬን :lol:


ክቡራን wrote:ችግሩ እኮ ያለው አንተ ጋ ነው ጺላው...ያንተው ኅኅኅኅ ህ..ክ..ታ.. አይነት ድምጽ ስለሆነ ሁሌም ያንን ስለምትሰማ የሌላው ሰው ድምጽ ሁሌም ላነተ የቀጠነ ቡና ይሆንብሀል...ለዛ ነው...ሰው ያጋዘን ድምጽ ይዞ ይፈጠራል...?? !! ማስፈራሪያ!! :lol:
ሓየት11
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 2945
Joined: Sun Apr 06, 2008 7:34 pm
Location: ላን'ሊይ

Postby ክቡራን » Tue Nov 27, 2012 12:10 am

የኛ ድምጽ ... ልክ እንደ ስቴሪዮ ጠዳ ያለ ... ፋይን ቲዩን የተደረገ ... የሪቾን ልብ ደብል የሚያስመታ ... አይነት ነው ... እስቲ ሪቾነት ብቅ ትበልና ቃሏን ትስጥ...

ቅቅቅቅ ኦኬ...ችግሩ የት እንዳለ አሁን ገባኝ ..ለካ አንተም ልብህ ይመኛል... :lol: :lol: ለማ አንተ የጠላ ቤት ተረት ታወራለህ እዚህ አገርህ ተወሯል ...ና ቶሎ !! ይሄን እባብ ሳላውቀው ጭንቅላቱ ላይ ስቆም ፍላጎቱን መናዝዝ ጀምረ...ቅቅቅቅ :lol: ወይ ሀዩ ጺላው ..ለካ አድፍጠሽ ነበር...እኔ መቼ አውቄ!! ...ኢት ኢስ ጉድ ቱ ኖ..! በቅርብ ቀን ላንተም የምትቀበርበት ጉድጔድ ይፈጠረልሀል...ወይለየከ አነ!! :lol: :lol:
ክቡራን
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 8282
Joined: Tue Mar 04, 2008 4:24 pm

Postby ቁምቢ » Tue Nov 27, 2012 4:12 am

ክቡራን wrote:ቁምቢ ፍቅር ተነተነውና እንዲህ ል ጠየቀኝ...:
ለመሆኑ አፍቅረህ ነው ተፈቅረህ ትርጉም ፍለጋ የምትባዝነው
_________________
አሪፍ ጥያቄ ናት.. :D ሁለቱንም ሆኘ ነው..:: :D ትንትናህ ግሩም ነው ተመችቶኛል..!
ፍቅር ማጣት እኮ ግን በራሱ ገኅነም ነው...የእጊዚአብሄርን ፕርዘንስ ስታጣ እዛ ጋ ሲኦል ይጀምራል:: ሌላ እሳት ለምን ይጨመራል...? እስኪ አስፋፋውና ሂድበት ይሄን ሀሳብ...


ሪቾ ..ሬቾ....የኔ ከረፈፍ ...የሚኒልክ ዘፈን ለኔ ነው የተመረጠው እያልሽ አስረኛ ፎቅ ላይ ተቀምጠሽ ሸልዪ...እሺ...የኔ ባለ ቴክስ ኮፍያ.. :D እኛ ፈርስት ፍሎር ላይ ስራችንን እየሰራን ነው...ይሄን ዝግጅት ደሞ አዳምጭውና ለኔ የተመረጠ ሙዚቃ ነው በይ እሺ... ጠቅ አድርጊው ማታ ማታ ቢፎር ዩ ጎ ቱ ቤድ.. :D
እቺን ጠቅ..


ወይ ፍቅር አለ መሀሙድ......ፍቅር ማጣት ትንሽ ይከብድ ይሆናል ይሁን እንጂ የፍቅረኛ ፍቅር ስላጣህ አትሞትም ወገን ዘመድ ምንም የሌለው የመንገድ አዳሪ ምናልባት አብሮት የሚዞር አንድ ውሻ አያጣም እሱም እኮ ፍቅር ነው....ሞጭሟጫ አይኖቹን እያቅለሰለሰ ጭራውን ከግራ ወደ ቀኝ እያማታ ሲተሻሸው ሰውየው በፍቅር አይን እያየ ያሻሸዋል............በአለም ላይ ፍቅር የሌለበት ቦታ የለም......

ግን ፍቅርን ሲሰጡት መቀበል የማይችል እንከፍ ደግሞ ሞልቷል..........አንድ ታሪክ ላጫውትህ..........ድሮ ከአንድ የሰፈሬ ልጅ ጋር በጓደኝነት ጀምረን ከዛ ቅልጥ ያለ ፍቅር ውስጥ ገባን....ታዲይ ሲበዛ ወረተኛ ነኝ......ለግዜው በቃ አስረሽ ምችው አልኩና ልጅቷ በንፁ ልቧ ስትወደኝ መኩራት አመጣው.......አንዳንድ ፍሬንዶች ደግሞ አንተና እሷኮ አትሄዱም.....ከዚች የተሻለች ስንት ቺክ መያዝ ስትችል ይቺን ይዘን ለምን ትጃጃላለህ.....ምናምን እያሉ....ልቤን አሳበጡት....ሞከረች ሞከረች ሲያቅታት አልቅሳ ተለያየን............ከምንም አልቆጠርኳትም ያኔ.......የመጨረሻ ቀን አገሬን ለቅቄ ልወጣ የሆነ ቦታ ላይ አይቻት እንዳላየ አለፍኳት.......ነገሩን ስለሰማች በአይኗ ሸኝችኝ......ስደት ክፉ ብዙ ነገር አሳየኝ....ማግኝት ማጣት...መውደድ መጥላት.......እኔም ታዲያ በተራዬ አሜሪካ ከመጣው በxላ አንዲት ቆንጆ ወድጄ ፍዳዬን ፈተፈትኩኝ...........ልጅቷ እንደኔ አይነት መጤና ያልተቋቋመ ሰው እንደማትፈልግና ለወደፊት ኑሮዋ የሚበጃትን እንደምትፈልግ ጠቆመችኝ..........ብለምን ባስለምን ጆሮ ዳባ ልበስ ብላ አንዱን ባለ ብር አገባች........ለካ ልብ ሲሰበር እንደዚ ነው.......ለካ ወዶ ማጣት ይሄን ይመስላል.............ያቺን አገር ቤት ያስቀየምኳት ልጅ ባይኔ ላይ አሁንም አሁንም ድቅን ትላለች..........ስራ ጀምሬ ኑሮ ተስተካክሎ ሁለት አመታት አለፉ..........አሁንም ግን ልቤ እሷን ከማሰብ አልባዘነም.........አንድ ቀን ታዲያ የመጣው ይምጣ ብዬ የሞባይሏን ስልክ ፈልጌ ደወልኩላት......ሀሎ! ሄሎ! ማን ልበል!.........ትንፋሽ አጥሮኝ ትንሽ ዝም አልኩና ማንነቴን ነገርኳት..........ዝም ብላ ትንሽ ቆይታ.........እንዴት ደወልክ አለችኝ......በቃ ያሁሉ ኩራት የለ ያ ሁሉ ጥጋብ የለ......የልቤን ነገርኳት አለምን ዞርኩኝ አንቺን የመሰለች የደጎችና የየዋሆች ንግስት ግን ላገኝ አልቻልኩም አልኳት.........አሁንም በዝምታ ተዋጠችና ይቅርታዬን እንደምትቀበል ነግራኝ አሁን ግን የምትወደው ጓደኛ እንዳላትና.......በመጨው ጥር ሊጋቡ ማሰባቸውን አረዳችኝ..........እኔም በተራዬ አልቅሸ......ተሰናበትኳት.......

አሁን ታዲያ ፍቅር ክቡርና ሰማያዊ መሆኑን ተረዳው......የፍቅርም ጡር እንዳለው በከባዱ ተማርኩኝ.....አሁን አግብታ የአንድ ልጅ እናት ሆናለች አውርተን አናውቅም ግን በማላውቀው ባሏ ስቀና እኖራለው...........ፍቅር ይሄን ይመስላል ዛሬ የማገኛቸውን ቀበጦች ሁሉ እንደሷ ቢሆንሉኝ እየተመኝው በምኞት ብቻ ቀረው......
የሰው ልጅ
መውደድ ሲችል መጥላቱ
መምከር ሲችል ማማቱ
መስራት ሲችል መቅናቱ
ማስታረቅ ሲችል ማጣላቱ
ያሳዝናል የሰው ፍጥረት በሕይወቱ፥፥
ቁምቢ
ጀማሪ ኮትኳች
ጀማሪ ኮትኳች
 
Posts: 83
Joined: Mon Nov 26, 2012 3:55 am

Postby ክቡራን » Tue Nov 27, 2012 7:11 am

ሂር ካምስ ሳም ዋን አይ ካን ቻት.. :D ቁምቤው ምስጋናየ በድጋሚ ይደርስህ...ባይገርምህ ተመሳሳይ ገጠመኝ አለን....እኔም የራሴን ገጠመኝ ጽፌ ልልክ ስል ኮምፒውተሬ ፍርዚ አደረገ...ሪስታርት ለማድረግ ብሞክርም አልተሳካም በኌላ ሻት ዳውን አደርኩት የጻፍኩትም አብሮ ሄደ:: በሌላ ጊዜ መልሽ .ትዝታዎቼን እጽፋለሁ:: አንተም በዚህ ርእስ ላይ የመሰለህን ቀጥል:: ካክብሮት ጋር::
ክቡራን
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 8282
Joined: Tue Mar 04, 2008 4:24 pm

Postby ክቡራን » Tue Nov 27, 2012 8:08 pm

ላይቭ ፕሮግራም በሤሉላር ፎኔ እየሰማሁ ነብር..tune in Radio ስልክዎ ላይ ካለ መኪናዎንም እየነዱ የሸገር FM ን በቀጥታ ማግኘት ይችላሉ... ባንድ ድንጋይ 4 ወፍ ይላሉ ይሄ ነው..እናማ ጉዞዬን እያስነካሁ ደግሞም እየሰማሁ ..ደግሞም እያስነካሁ... :D በነገራችን ላይ እቺ ቃል ( አስነካው ) በደንብ የገባችኝ ትናንት ነው:: አንዲት የላሊበላ ልጅ ናት...ላሊበላ ውስጥ የቱሪዝም ጋይድ ቢዝነስ ትሰራ ነበር ..አሁን እዚህ አለች:: ትናንት እራት በላንና ወደ ቤቷ ሳደርሳት ቀይ መብራት ይዞን እንደቆምን አረንጔዴ መብራቱን ሳላየው ዝም ብዬ ሳቆም...""አስነካው እንጂ አንተ ! "" አለችኝ
"" ...ምኑን ነው የማስነካው..?? :"" D ሳቄ መጣብኝ..
""አስነካው እንጂ መኪናውን ነዋ.!""
አስነካው== ንዳው.... ማለት ነው...በወሎ ዜማ በላሊበላ ቅላጸ. :D አስነካሁታ ታዲያ....እኔም. :D

እቺን እዚህ ላይ ላቁምና አንዳድ ሴቶች ሲፈቀሩ ብቻቸውን መሆን ይፈልጋሉ...መፈቀራቸውን ሌላ ሰው እንዲያወቅባቸው ስለማይፈልጉ ነው ይላል አዘጋጁ.. .በዚህ ጉዳይ ወጣት ሴቶች ተጠይቀው ሲመልሱ እንዳሉት ፍቅር ሲይዛቸው ብቻቸውን መሆን ይመርጣሉ...ከሰው መቀላቀል አይፈልጉም... ለምን ይሆን..?? ..የፍቅር ህይወታቸውን እንዳይደፈርስባቸው ይሆን..? ውጭው ስለሚያስፈራቸው ይሆን ..ውስጣቸውን ብቻ መስማትና ማዳመጥ ስለሚፈልጉ ይሆን..?? ወይም ፍቅር ከፈጠረላቸው ውስጣዊ ትኩሳት... ያገኙትን ደስታ ከሌላው ጋር መሽማት ስለማይፈልጉ ይሆን..? እስኪ ቁምቢው ይሄን ጉዳይ አስፋፈተህ ሂድበት.. :D ሌሎቻቹም መሳተፍ የምትችሉ መሆኑን እገልጻለሁ:: :D
ክቡራን
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 8282
Joined: Tue Mar 04, 2008 4:24 pm

Postby ክቡራን » Wed Nov 28, 2012 3:50 am

አለምዬ ሶራ ... ሶራ ..ሶራ..
እናት አለም ሶራ ...
ሶራ ...ሶራ ...
ቅዱስ ላሊበላ ሶራ ነው ምንጣፉ..
ቅዱስ ገ/ማርያም ሶራ ነው ምንጣፉ..
የግሩ መረገጫ ወርቅ ነው ክፈፉ...
ሸለለለለለለለለለለለለለለ...
ውይይይይይ...አቤት አቤት....
ሸብ ሸብ ,...ቸብ ቸብ....
እቺን ጠቅ ጠቃጠቅ .
ቤቱን ሞቅ ሞቃሞቅ...
ደመቅመቅ...
ጊርጊራ ..ጊርጊራ ጊርጊራ....
ያዝ እንጊዲ... :D


.
ክቡራን
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 8282
Joined: Tue Mar 04, 2008 4:24 pm

Postby ቁምቢ » Wed Nov 28, 2012 1:00 pm

ክቡራን ሰላምታ አድርሰናል......... ሴቶች በተለይ ሲያፈቅሩ ብቻቸውን ይሆናሉ ላልከው እኔ በበኩሌ እንደ ሰው የሚለያይ ይመስለኛል............ ብቻቸውን ከሆኑም ምናልባት ስሜታቸውን የሚረዳላቸው ሰው ካለማግኝት ይመስለኛል........ጓደኛ ግን ካላቸው እንዲሁ ካንተ ከተለዩ በxላ ሲንሾካሾኩ ነው የሚውሉት..........ይገርምሃል ግን ጓደኛ የሌላት ሴት ስታፈቅር እንደ ጉንፋን አድርጎ ሁሉ ሊያስተኛት ይችላል.........የሆዳቸውን የሚያዋዩት ጓደኛ የሌላቸው ሴቶች ብዙ ግዜ ወንዶች እንዳሏቸው ነው የሚያደርጉት.........ያሳዝኑሀል........ጓደኛ ካላት ስታማክራት አይ ይሄማ አይሆንም እንደዚህ ካለሽ እንደዚ በይው እየተባባሉ ይማከሩብሀል.........ምናልባት በፍቅር ታውራ ያላየችውን ያንተን ጉድለት ብዙ ግዜ ጓደኞቿ ናቸው የሚያዩት.........ወንዱም ጓደኛ የሌላት ብቸኛ መሆኗን ካወቀ የልብ ልብ ይሰማዋል.........ነይ እንጨፍር ብሎ የሚወስዳትና አዲስ ሰው የሚያስተዋውቃት ጓደኛ እንደሌላት ስለሚያውቅ የትም የምትሄድ አይመስለውም..........አየህ በፍቅር ውስጥ ትንሽዬ ስፔስ ያስፈልጋል.........አንተም ወደ ጓደኞችህ እሷም ወደ ጓደኖቿ መሄድ ይኖርባችxል........ካልሆነ መሰለቻቸት ይመጣል......ጨዋታም ያልቅና ጭቅጭቅ ብቻ ይሆናል ማለት ነው.......................ይገርምሀል ብዙ ሰዎች በላይፌ ሴት የማተራምስና ደስተኛ አድርገው ያዩኛል እኔ ግን ከስንት አንዴ ክለብ ወጥቼ ጠልፌ ከምመጣቸውና በወርና በሁለት ወር እየጠፉ ከሚመጡ ቺኮች በስተቀር የማውቀው የለም.............በፍቅር ከቺክ ጋር ስትኖር ግን,...........ዋናው እምነት ነው ልታምናት ይገባል...........ልታከብራት ይገባል...........ለራሷ ግዜ ልትሰጣትም ይገባል.........ብዙ ሴቶች ሌላ ወንድ ጋር የሚሄዱት አንተ ጋር የሌለ ነገር ሌላ ቦታ ስለሚያገኙ ነው.........

ወደ ዋናው ቁም ነገር ስንመጣ........የሴቶች ሲያፈቅሩ የብቸኝነታቸው ምንጭ ምን እንደሆነ ምናልባት ሴቶች እራሳቸው ቢናገሩት ጥሩ ነው........በወንድ በኩል ግን ስታፈቅር እሷ እንጂ ማንም ስለማያስደስትህ ከሷ ስትለይ እቤት ቁጭ ብለህ ሙዚቃ እየሰማህ እንዲያው ከሜዳ ፈገግ ያሰኝሀል.........ይገርማል ሰውን እብድ የሚያሰኝው የእብድን ስራ ሲሰራ መታየቱ እንጂ የእብድን ስራ መስራቱ አይደለም አይደል ያሉት ሀዲስ አልማየው በፍቅር እስከመቃብር ላይ..........አንዳንዴ ፍቅር የያዘውን ሰው ትክ ብለህ ብታየው እኮ ያበደ ሁሉ ይመስልሀል.............ቀኝ ቀኙን
የሰው ልጅ
መውደድ ሲችል መጥላቱ
መምከር ሲችል ማማቱ
መስራት ሲችል መቅናቱ
ማስታረቅ ሲችል ማጣላቱ
ያሳዝናል የሰው ፍጥረት በሕይወቱ፥፥
ቁምቢ
ጀማሪ ኮትኳች
ጀማሪ ኮትኳች
 
Posts: 83
Joined: Mon Nov 26, 2012 3:55 am

Postby ገልብጤ » Wed Nov 28, 2012 2:54 pm

»ዋሌቴና ሽንኩርት አንድ ናቸው ሲከፈቱ ያስለቅሱኛል


ጋሽ ቁምቢ ..ይቺ ነገር ትብራራልኝ ...ዋሌትዎ ባዶ በመሆኗ ነው የምታስለቅስዎ :!:
ያልበሰለ ፖለቲከኛ ስለቀጣዩ ምርጫ ሲያስብ
የበሰለ ፖለቲከኛ ስለቀጣዩ ትውልድ ያስባል
James freeman clarke
ገልብጤ
ዋና ውሃ አጠጪ
ዋና ውሃ አጠጪ
 
Posts: 1708
Joined: Sat Jun 26, 2010 11:24 pm

Postby ቁምቢ » Wed Nov 28, 2012 10:32 pm

ገልብጤ wrote:
»ዋሌቴና ሽንኩርት አንድ ናቸው ሲከፈቱ ያስለቅሱኛል


ጋሽ ቁምቢ ..ይቺ ነገር ትብራራልኝ ...ዋሌትዎ ባዶ በመሆኗ ነው የምታስለቅስዎ :!:


አቶ ገልብጤ ሰላም ብለናል...................ባጠቃላይ ሀሳቡ ዋሌቴን የምከፍተው ገንዘብ ለማውጣት ስለሆነ......ገንዘብ ማውጣት ደግሞ ሰልስት እንደተጠራ ሰው ያስለቅሰኛል ለማለት ነው............ምናባቴ ላድርግ ብለህ ነው.......በዚህ በሰለጠነው አለም በሰአት እየከፈሉ በደቂቃ ይቀበሉሃል.............በዛ ላይ አገር ቤት ትበጭቃለህ........ አሁን አሁን በየሁለት ወሩ ነው የምበጭቀው..........ኑሮ ግን ተወዷል ምናምን ይላሉ..........
የሰው ልጅ
መውደድ ሲችል መጥላቱ
መምከር ሲችል ማማቱ
መስራት ሲችል መቅናቱ
ማስታረቅ ሲችል ማጣላቱ
ያሳዝናል የሰው ፍጥረት በሕይወቱ፥፥
ቁምቢ
ጀማሪ ኮትኳች
ጀማሪ ኮትኳች
 
Posts: 83
Joined: Mon Nov 26, 2012 3:55 am

PreviousNext

Return to Warka Intimate - ዋርካ ፍቅር

Who is online

Users browsing this forum: Google Adsense [Bot] and 13 guests