ይህን ያውቁ ኖሯል ?

Topics related to cultures, arts, languages, arts such as humor, music, traditional literary genres of poems, ግጥም ፣ ቅኔ ፣ ተረትና ምሳሌ)

Postby ሙዝ1 » Tue Dec 25, 2012 2:44 pm

ዋዉ! ዋዉ በድጋሚ .... ቋንቋ አጠቃቀምህን በጣም ወድጀዋለሁ:: አተራረክህንም እንዲሁ::

በተረፈ ሶሻል ክሪቲክሱ ብዙም አልተዋጠለኝም ትንሽ ተጋኗል::

ልመንህ ታደሰ ...
ልክ ነህ አዲስ አበባ ጎዳና ላይ ነዉ:: የሆነ ቀን ... ከእስጢፋኖስ ወደ ኡራኤል በሚወስደዉ ጎዳና ላይ ነን:: ዮርዳኖስ ሆቴል ጋ ያለዉ የትራፊክ መብራት አስቁሞናል:: ከወዳጆቼ ጋ ነበርኩ:: ሁላችንም የአንድ ትዉልድ ሰዎች ነን:: እሁድ ከሰዐት በሗላን ከቲቪ ፊት ለፊት ተኮልኩለን በጉጉት ከምንጠብቃቸዉ ሰዎች አንዱ ... .. ምናልባት ግንባር ቀደሙ ልመንህ .... ከሶስቱ እረድፍ የመኪና ሰልፍ በመካከለኛዉ እየተሳደበ እየመጣ ነዉ:: ማመን አልቻልንም:: አብዛኛዉ ሰዉ ወደ መኪናዉ ሲደርስ የመኪና መስታዉት ይዘጋል:: በጣም ተበሳጨን:: እኛ ጋ ደረሰ:: እየመጣ ነዉ:: ሰፍ ብለን በስስት እያየነዉ ነዉ:: ሰላም አልነዉ:: የመኪና መብራት እይንዳይለቅ እየጸለይን ነዉ:: ቆም ብሎ አየን:: ሲጠጋን ጓደኛዬ ... በኪሱ የያዘዉን ብር ሙሉ ሳይሰስት ... ሳይቆጥር .... ሊሰጠዉ እጁን ዘረጋ .... የልመንህ መልስ ፈገግታን በተላበሰ ፊት ... በጉጉት እጁን ዘርግቶ አይደለም ብሩን የተቀበለን:: ብሩን አለመቀበሉ ብቻ ሳይሆን መልሱን አስደንጋጭ ነበር:: የደሀ ልጅ ከሚል ቃል ጋ የምራቅ ትፋት ነዉ የወረወረልን:: ኦ ... ደነገጥን .... ሰዉ ወዶ አይደለም መስታዉት እየዘጋበት ያለ ለማለት ባልደፍርም:: ልመንህ ግን ከሁላችን በላይ ነዉ::ለልመንህ የሚያስፈልገዉ ብር በቀጥታ አይደለም:: ምርኩዝ ነዉ:: ይዟቸዉ የሚሄዳቸዉን ስዕሎች ብንገዛዉ ይመርጣል .... ብር በጥሬዉ ከምንሰጠዉ:: ትክክለኛዉ ፍላጎቱ ያ ነዉ::የመዳኑም መስመር ይህ ብቻ ይመስለኛል:: ለዛም ነዉ ይህ ሰዉ ትልቅ ነዉና ታላቅ እንዲሆን ትንሽዬ ምርኩዝ የሚያስፈልገዉ:: ምርኩዙን ካላቀበልነዉ ወድቋል:: መጻዒዉም መሰባበር ነዉ::
አይን ሁሉን ቢያይም አጠገቡ ያለዉን ቅንድብ አይቶ አያዉቅም ...
ሙዝ1
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 3128
Joined: Wed Feb 22, 2006 9:25 am

Postby ምናል » Tue Dec 25, 2012 3:39 pm

betame enamasgnalen N.M ya houlgeza anbabehe nege.
evry monday adamtehalue.
ምናል
አዲስ
አዲስ
 
Posts: 14
Joined: Tue Jan 02, 2007 3:13 am
Location: usa

Postby ማህቡብ » Tue Jan 01, 2013 6:35 am

ዘመን በርቆ ዘመን ሲብት ቀሪው ታሪክ ነው::

ሐምሌ ላይ የደቡብ ኮሪያዉ ድምፃዊ ያዜማት ሙዚቃ ከኮሪያ ልሳነ-ምድር ታልፋለች ብሎ ያኔ የገመተ ጥቂት ነበር።ባመቱ ማብቂያ ግን የዓለም ወጣት እንደ ብሔራዊ መዝሙሩ እያዜመ አዲሱን ዓመት ሊቀበል ዳንኪራ ይረግጥበታል።አፍቃኒስታኖች፣ ፓኪስታኖች ሙታቸዉን ቀብረዉ፣ መሞቻ፣ መቀበሪያ፣ መሸሸጊያቸዉን ለአስራ-አንደኛ ዓመት ያሰላሰሉበት፣ኢራቆች እልቂት ጥፋትን የየዕለት ኑሯቸዉ አካል ያደረጉበት ዘጠነኛ ዓመት፣ ሶሪያዎች በዕልቂት ፍጅት ጥፋት ከቀዳሚዎቻቸዉ ለመቅደም የተጣደፉበት፣ ሊቢያ፣ የመን እና ናይጄሪያ ሶማሌዎችን ቀድመዉ፣ ቀዳሚዎችን የተከተሉበት ሁለተኛ ዓመት አበቃ።ግብፆች እየመረጡ፣ አደባባይን ሙጥኝ እንዳሉ፣ እስራኤል-ፍልስጤሞች እንደተገዳደሉ፣ አሜሪካኖች፣ ሩሲያዎች ቻይኖች እንደየፖለቲካቸዉ ወግ መሪዎቻቸዉን መርጠዉ ወይም ተመርጦላቸዉ፣ ዘንድሮን አምና ሊሉት ሠዓታት ቀራቸዉ።ከአዉሮጳ በመለስ ባለዉ ዓለም የተከናወኑ አበይት ክንዉኖችን ላፍታ ቃኝተን-እኛም ሁለት ሺሕ አስራ-ሁለትን እንሸኘዉ።

ሚያዚያ ሁለት ሺሕ ሰወስት ፕሬዝዳንት ጆርጅ ቡሽ እንደ ፊት አዉራሪ፣ ጠቅላይ ሚንስትር ቶኒ ብሌር እንደ አጋፋሪ፣ ኢራቅ ላይ የለኮሱትን እቶን ግመት የአረቦች ሕዝባዊ አብዮት፣ የሶሪያ አዲስ ጥፋት ሊጋርዱት መሞከራቸዉ አልቀረም።

ሶሪያ

እስከ ነገ-ዘንድሮ የምንለዉ ዓመትም እንደ ስምንት ቀዳሚዎቹ ሁሉ ያቺ ጥንታዊቱ ሐብታም ሐገር የቦምብ ማሳ፣ የሞት-እልቂት አዝመራ፣ የአስከሬን መከመሪነቷን ያረጋገጠዉ ገና በመባቻዉ ነበር።

የመርከብ ሽርሽር የሚያዘዉትረዉ ሐገር ጎብኚ ኮስታ ኮንኮርዲያ የተባለችዉ መርከብ ኢጣሊያ ባሕር ላይ በመላተሟ የሞቱ የቆሰሉ ተንሸራሻሪዎችን ቁጥር ከሚቆጥሩለት መገናኛ ዜዴዎች አይን-ጆሮዉን እንደለገተ፣ከወደ አሜሪካ በተለይ ለሙዚቃ አፍቃሪዎች መርዶ ተሰማ።

ኤታ ጀምስ።ድንቅ ድምፃዊት ነበረች።አረፈች።ሰባ አራት ዓመቷ ነበር።ጥር አስራ-ሰወስት።

በኮስታ ኮንኮሪያ አደጋ የሞቱት ሰዎች ቁጥር-አንድ ሁለት ሲባል፥ ሙታኑን ቀብሮ፣ ቁስለኞቹን ቆጥሮ እንዳለቀሰ፣ እየሞተ-የሚለቀስለት ኢራቃዊ ባስራ ላይ ተረኛ ሟች ቆስለኞችን አስቆጠረ።

አንድ አጥፍቶ ጠፊ ባፈነዳዉ ቦምብ ሐምሳ ሰወስት ሰዎች ተገደሉ።መቶ ሰላሳ ቆሰለ።

የአዉሮጳ ሕብረት፥ የኑክሌር ቦምብ ለመስራት ታሴራለች ከሚላን ኢራን ነዳጅ ዘይት ላለመግዛት ወሰነ።ጥር ሃያ-ሰወስት።ጥር ሃያ አምስት ካኑ የተባለችዉን የሰሜናዊ ናጄሪያን ግዛትን በተከታታይ ያሸበረዉ ቦምብ አንድ መቶ ሰማንያ አምስት ሰዉ ገደለ።አደጋዉን የጣለዉ ቦኩ ሐራም የተሰኘዉ ቡድን ነዉ ተብሎ ይታመናል።


ናጄሪያዊዉ አክራሪ ድርጅት የደረጀበት፣ ናጄሪያን በነ-ኢራቅ፥ በእነ-አፍቃኒስታን የጥፋት ጎዳና ለማጓዝ የፈለገበት ምክንያት አሳማኝ መረጃ ሳይገኝለት ጥር-አበቃ።ሁለት ሺሕ አስራ አንድን በሰልፍ፣ ምርጫ፣ ሸኝቶ ዘንድሮን በሰልፍ ምርጫ ለተቀበለዉ ግብፃዊ የካቲት የባተዉ ከመጥፎ ምልኪ ጋር ነበር።

የካቲት አንድ፣የሁለት እግር ኳስ ቡድናትን ግጥሚያ ለመመልከት ፖርት ሰኢድ ስታዲዮም የገባዉ የየቡድናቱ ደጋፊ ጎራ ለይቶ ይከታከት ገባ።ግብ ከሚቆጠር፣ ኳስ ከሚለቀምበት ሜዳ ሰባ-ዘጠኝ አስከሬን ተለቀመ።ቁስለኛዉ አንድ ሺሕ።

ሁለት የአዉስትሬሊያ ግዛቶችን ያጥለቀለቀዉ ጎርፍ አምስት ሰዉ ገድሎ በአስር ሺሕ የሚቆጠሩትን መግቢያ መዉጪያ አሳጥቶ ሲያስጨንቅ፣ ማዕከላዊ ፊሊፒንስን የመታዉ የመሬት መንቀጥቀጥ አርባ-ስምንት ሰዉ ገደለ።በሺ የሚቆጠር አፈናቀለ።የካቲት ስድስት ነበር።

የካቲት አስራ-አንድ።ዩናይትድ ስቴትስ ሌላ መርዶ።ድምፃዊትና የፊልም ተዋኝ ዊትኒ ሁዊስተን ሞተች።

ተስረቅራቂ ድምፅ፥ አማላይ ዉበት አፈር ሆነ።አርባ ዘጠኝ አመቷ ነበር።አካዶ በተባለዉ የሜክሲኮ ከተማ በሚገኝ ወሕኒ ቤት የታሰሩ የሁለት ተፃራሪ የአደንዛዥ ዕፅ አዘዋዋሪ ቡድናት አባላት ተጋጭተዉ አርባ-አራት እስረኞች የመገደላቸዉ ዜና ማዕከላዊ አሜሪካኖችን ጉድ-አሰኝቶ ሳያበቃ-የሁንዱራስ ወሕኒ ቤትን ያጋየ እሳት የሰወስት መቶ ስልሳ እስረኞች ሕይወት የመብላቱ አሳዛኝ ጉድ የሜክሲኮዉን ጉድ ዋጠዉ።
ብራሂሚና አሰድ በሕዝባዊ አመፅ ከስልጣን የተወገዱትን የየመንን ፕሬዝዳት ዓሊ አብደላ ሳሌሕን የተኩት ምክትል ፕሬዝዳት አብድ ራቡሕ መንሱር አል-ሐዲ ለፕሬዝዳንትነት ምርጫ ብቻቸዉን ተወዳድሩ-አሸነፉም።የየመን አል-ቃኢዳ ለአዲሱ የሐሪቱ ፕሬዝዳንት ያስተላለፈዉ የእንኳን ደስ አለዎት መልዕክት ነበር።ቦምብ።


የካቲት ሃያ-አምስት።ሙካላ በተባለችዉ ከተማ የፈነዳዉ ቦምብ ሃያ-ስድስት ሰዉ ገደለ።ለቦምብ-ማ ማን እንደ ኢራቅ።አስራ-ሁለት የኢራቅ ከተሞች ባንድ ቀን፣ በተመሳሳይ ሰዓት እኩል ተሸበሩ።የሞተ፧ ስልሳ። የቆሰለ ሁለት መቶ።የካቲት ሃያ-ሰወስት።


መጋቢት ሁለት፣ኢንዲያና እና ኬንታኪ የተባሉትን የዩናይትድ ስቴትስ ግዛቶች የመታዉ ሐይለኛ ማዕበል ሃያ-ሰባት ሰዉ ገደለ።ኮንጎ ሪፐብሊክ ርዕሠ-ከተማ ብራዛቪል ዉስጥ የጦር መሳሪያ ማከማቻ መጋዘን የደረሰ ተከታታይ ፍንዳታ ሁለት መቶ ሐምሳ ሰዉ ገደለ።

ኮንጎዎች የከሰለ-አስከሬናቸዉን ሲለቅሙ ሩሲያዎች ፕሬዝዳንታቸዉን መረጡ።መጋቢት አራት።ከሺ ዘጠኝ መቶ ዘጠና ዘጠኝ ጀምረዉ ሲሆንላቸዉ በፕሬዝዳንትነት፥ ሳይሆንላቸዉ በጠቅላይ ሚንስትርነት ከዓለም የምድር ገፅ አንድ-ሰባተኛዉን የምትይዘዉን ሰፊ፣የተፈጥሮ ሐብታም፣የጦር መሳሪያ ጉልበታም ሐገርን የመሩት ቭላድሚር ፑቲን እንደገና በፕሬዝዳትነት ተመረጡ።

የፑቲንን ዳግም መመረጥን፣ የምርጫዉ ሥርዓት፣ የድምፅ አሰጣጡን ሒደትና ዉጤት ተቃዋሚዎች በአደባባይ ሰልፍ ተቃዉመዉታል።


ምዕራባዉያን መንግሥታት ፈራተባ ባለ መግለጫ ተችተዉታል።ፑቲኒንን ግን አንዱም የሚያስጨንቅ አልሆነም።ግንቦት ሰባት፥- ክሬምሊንን እንደ ፕሬዝዳት ዳግም ተቆጣጠሩት።


እንደገና ኢራቅ፣ እንደ ገና ግድያ።ሐዲታ በተባለች ከተማ የሰፈሩ ፀጥታ አስከባሪዎችን የፖሊስ መለዮ ለብሶ የተቀየጠ አንድ ታጣቂ ሃያ-ሰባት ወታደሮችን ረሸነ።መጋቢት አምስት።እዚሕም እዚያም አራት-አምስት ሰዎች ከመገደላቸዉ ባለፍ የከፋ ግድያ-ጥፋት ሳይደርባት ጥርና የካቲትን ያለፈችዉ አፍቃኒስታን መጋቢት ላይ ደም-ጠጥቶ ደም ለሚጠማዉ ቆሌዋ አስራ-ስድስት ሰላማዊ ዜጎችዋን ገበረች።

ባግዳድ

ገዳዮች የአፍቃኒስታንን ሕዝብ «ከአሸባሪዎች ነፃ ለማዉጣት» የዘመቱት የአሜሪካ ወታደሮች ናቸዉ። መጋቢት አስራ-አንድ።በአምስተኛዉ ቀን የቱርክ ወታደሮች የሚያበሩት የኔቶ ሔሊኮብተር ካቡል አጠገብ መኖሪያ ቤቶች ላይ ተፈጥፍጦ አስር-ሰዎች ገደለ።ለአፍቃኒስታን ሁለት ሺሕ አስራ-ሁለት እንደ አስር ቀዳሚዎቹ ሁሉ አስከሬን እንዳስቆጠረ-ተጠናቀቀ።

የፕሬዝዳንት በሽር አል-አሰድን አገዛዝን በሰላማዊ ሕዝባዊ አብዮት ለመቃወም አምና መጋቢት የጀመሪያዉን የአደባባይ ሰልፍ ካደረገዉ የሆምስ ሕዝብ፥ ትግል የጀመረበትን የመጀመሪያ ዓመት ለመዘከር የታደለዉን ሥንትነት ማወቅ ሲበዛ ከባድ ነዉ።


ሕዝባዊዉ፣ ሰላማዊዉ ትግል ብልጭ ከማለቱ በጠመንጃ ዉጊያ በመዳፈኑ ጥፋት ቀድመዉ ከጠፉት አካባቢዎችና ሕዝብ አንዱ ግን በርግጥ ሰላማዊዉ ትግል ቀደሞ የተጀመረባትና የጀመሩት ሆምስና ሆምሶች ናቸዉ።


ሆምሶች የጀመሩት ትግል መጋቢት ላይ ዓመት ሲደፍን ከሶሪያዎች ዓልፎ፣ ዓለምን ለሁለት ገምሶ ዲፕሎማሲያዊ ድርድርን ከዉጊያ፣ ሽብርን-ከሽምገላ፣ ሰላም የማስከበር ዘመቻን ተፋላሚዎችን ከማሰልጠን-ማስታጠቅ ጋር በቀየጠ ተቃርኖ የሚያፋትገዉ የሶሪያ ምስቅልቅል፥ ከሃያ ሺሕ በላይ ሕዝብ መግደሉ፣ አስር ሺዎች ማቁሰሉ፣ መቶ ሺሕዎች ማፈናቀል-ማሰደዱ ይዘገብ ነበር።

እልቂት ፍጅት ጥፋቱ፣ የዉጪዉ ሽኩቻዉም ከመጋቢት በሕዋላ እስካሁን በተቆጠሩት ምናልባትም በሚቀጥሉትም-የመቀጠሉ አሳዛኝ ምልክት የታየዉም ሆምስ ነበር።መጋቢት አስራ-ሁለት።የሶሪያ መንግሥት ጦር አርባ አምስት የሆምስ ነዋሪዎች መግደሉን ተቃዋሚዎች አስታወቁ።የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ልዩ መልዕክተኛ ላሕዳር ብራሒሚ ባለፈዉ ቅዳሜም ሰላማዊ መፍትሔ አሉ።
አገረ ገዢ ራምኒ «ብቸኛዉ አማራጭ በእዉነት ገሐነብ ወይም ፖለቲካዊ ሒደት ከሆነ፥ እኛ ሁላችንም ለፖለቲካዊ ሒደት ያለ ዕረፍት መጣር ይገባናል።በጣም ከባድ ነዉ።በጣም የተወሳሰበ ነዉ።ግን ሌላ ምርጫ የለም።»

ቱርክን፣ አረቦችንና አዉሮጶችን አስከትላ አማፂያኑን የምትረዳዉ ዩናይትድ ስቴትስ ግን ሌላ ምርጫ አላት።በሽር አል-አሰድ መወገድ አለባቸዉ የሚል።ወደ በሽር አል-አሰድ የምታዘነብለዉ ሩሲያ ኢራንን በተዘዋዋሪ ከሩቁ አስከትላ፣ ቻይናን ከጎንዋ አቁማ የአሜሪካኖቹን ጎራ ትሞግታለች።

የደማስቆ ገዢዎችና አማፂያኑ ግን ይዋጋሉ።ሶሪያ ትጠፋለች።ሕዝባ ያልቃል።አማፂያኑ ባለፈዉ ቅዳሜ ብቻ ሁለት መቶ የመንግሥት ምርኮኛ ወታደሮችን ጨምሮ ሰወስት መቶ ሰዉ መግደላቸዉ ተዘግቧል።የተባበሩት መንግስታት ድርጅት እንደሚለዉ እስካሁን ከአርባ ሺሕ በላይ ሕዝብ አልቋል።፣ ከሁለት መቶ ሺሕ በላይ ቆስሏል።ከግማሽ ሚሊዮን በላይ ተሰዷል።አራት ሚሊዮን ተፈናቅሏል።

የጠፋዉ ሐብት ንብረት በአስር ቢሊዮን ይገመታል።የጥንታዊቱ ሐገር በገንዘብ የማይተመኑ ቅርሶች ወድመዋል።እና----እንደገና ኢራቅ-እንደገና ሞት።አስር የኢራቅ ከተሞችን ባሸበረ የቦምብ ጥቃት ሐምሳ ሰዎች ተገደሉ።ሁለት መቶ አርባ ቆሰሉ።መጋቢት ሃያ ነበር።


የጓቲማላ ፍርድ ቤት በሺሕ ዘጠኝ መቶ ሰማንያ ሁለት በተፈፀመ ጭፍጨፋ ተሳትፈዋል ያላቸዉን አምስት የቀድሞ የሐገሪቱ ሚሊሺያ ጦር ባልደረቦችን የሰባት ሺሕ ሰባት መቶ አስር ዓመታት እስራት ፈረደባቸዉ።ቀልድ ይመስላል።ግን እዉነት ነዉ።


መጋቢት ሃያ-ሁለት።የማሊ የጦር መኮንኖች የፕሬዝዳት አማዱ ቶማኒ ቶሬን መንግሥት ከሥልጣን አስወገዱ።እስልምና ሐይማኖትንና የቱዋሬግ ጎሳ ጥያቄን የተላበሰዉ ዉጊያ ጦርነት ታሪካዊቱ የሳሕል በረሐ ሐገርን ማጥፋቱም ተባባሰ።የምስራቅ አፍሪቃ ሐገራት ሶማሊያ ላይ እንዳደረጉት ሁሉ የምዕራብ አፍሪቃ መንግሥታት ወደ ማሊ ጦር ለማዝመት ይዘጋጁ ገቡ።የቀድሞዉ
ሶማሊያ ፕሬዝዳት ግን ይሕን ሳያዩ አረፉ ተገላገሉ።

ኦባማ-ከድል በኋላ

ኮሎኔል አብዱላሒ ዩሱፍ አሕመድ።ዚያድ ባሬ ሲደሰቱ እየሾሙ፥ እየሸለሟቸዉ፥ ሲከፉ እያሰሯቸዉ፥ ኮሎኔል መንግሥቱ ደስ ሲላቸዉ እያቀረቡ፥ እየረዱ-እየደገፏቸዉ፥ ሲቆጡ እያሰሯቸዉ፥ ጠቅላይ ሚንስትር መለስ ዜናዊ ሲፈልጓቸዉ እያሸሙ፥ ሳይፈልጓቸዉ እያሻሯቸዉ ነዉ-የኖሩት።የኢትዮጵያንም የሶማሊያንም አብያተ-መንግሥታት፥ ወሕኒ ቤቶችንም እኩል ያዉቋቸዉ ነበር።

ሰባ ስምት አመታቸዉ ነበር።ቀኑ-መጋቢት ሃያ-ሰወስት።የአብዱላሒ ዘመድ-ወዳጆች ሐዘን (ታእዚያ) እንደተቀመጡ የሞቃዲሾ ቲአትር በቦምብ ጋየ።የሶማሊያ ኦሎምፒክ ኮሚቴ ፕሬዝዳትን፥የሐገሪቱን የእግር ኳስ ፌደሬሽን መሪን ጨምሮ አስር-ሰዉ ተገደለ።ሚያዚም አራት አለ።

ሚያዚያ ሰባት፥ የቦምብ፥ ጥይት፥ ጥፋት ያልተለያት ፓኪስታን ተፈጥሮም-ጨከነባት።አንድ መቶ ሰላሳ ወታደሮችዋ በበቦረዶ ናዳ ተቀበሩ።በሁለተኛዉ ሳምንት ኢስላማባድ አጠገብ የመንገደኞች አዉሮፕላን ተፈጥፍጦ አንድ መቶ ሃያ-ሰባት ሰዎች ሞቱ።

የዓለም ወዝ አደሮች-ዓመታዊ ቀናቸዉን ሲያከብሩ፥ ለወትሮዉ በዓሉን ከማንም በላይ የሚያከብሩት የሞስኮና የቤጂንግ መሪዎች እንደ ካፒታሊስቱ ፈሊጥ የአስራ-አምስት ቢሊዮን ዶላር የንግድ ዉል ተፈራረሙ።

ግንቦት ሰባት ዓለም የቭላድሚር ፑቲንን በዓለ-ሲመት ከሞስኮ ሲከታተል፥ አፍቃኒስታን የሠፈረዉ የኔቶ የጦር አዉሮፕላን በጣለዉ ቦምብ አስራ-አራት ሠላማዊ ሰዎች ገደለ።ስድስት አቆሰለ።

ግንቦት አስራ-ሁለት።የጥንታዉያኑ የማያ ነገድ አዋቂዎች የቀመሩት የዘመን መቁጠሪያ ታሕሳስ ሃያ-አንድ፥ ሁለት ሺሕ አስራ ሁለት የአሮጌዉ ዘመን ማብቂያ፥ የአዲስ ዘመን መጀመሪያ እንጂ የዓለም ፍፃሜ እንዳልሆነ የሚያረጋግጥ መረጃ ተገኘ።

ታሕሳስ ሃያ-አንድ ምፅዓት፥ ቂያማ ወይም ፍፃሜ ነዉ በማለታቸዉ ጥሩ ገበያ ያገኙበት ወገኖች ግን አልተቀበሉትም። ፊልም፥ ሟርታቸዉን እንደቸበቸቡ ወሩ በወር ተተክቶ ታሕሳስ-ሃያ አንድ መጥቶ ሔደ።ዓለም እንደነበረች ነች።

ግንቦት አስራ-ሰባት።


ዶና ሰመር።አሜሪካዊቷ ድምፃዊት ሞተች።ስልሳ-አራት አመቷ ነበር።

ኢራቅ፥ የመን፥ ናጄሪያ በአጥፍቶ ጠፊ ቦምብ፥ ፓኪስታን በደፈጣ ተዋጊዎች ጥቃት፥ አፍቃኒስታን በኔቶ ጦር ድንደባም፥ በቦምብ፥ ሶሪያ በአማፂያንና በመንግሥት ጦር ዉጊያ በመቶ የሚቆጠሩ ዜጎቻቸዉን ቀብረዉን፥ ሌሎችን ወደ ሚቀብሩበት ሌላ ወር ተሻገሩ።ሰኔ።ናጄሪያ።የአዉሮፕላን አደጋ መቶ ሐምሳ ሁለት ሰዉ ገደለ።

ባግዳድ፥አዲስ ወር፥ አዲስ ፍንዳታ፥ አሮጌ-እልቂት።ኢራቅ ለሰኔ ቆሌ ወሩ መግቢያ ላይ የሃያ-ስድስት፥ አጋማሹ ላይ የዘጠና ሰወስት፥ ማብቂያዉ ላይ የስላሳ-ሁለት፥ ዜጎቿን፥ሕይወት፥ የስድስት መቶ ሰዎቿን አካል ገበረች።አፍቃኒስታንም እንዲያዉ ነዉ።በተከታታይ የቦምብ ጥቃት አምስት የዉጪ ሐገር ሰዎችን ጨምሮ አርባ-አንድ ተገደሉባት።መቶዎች ቆሰሉ።ናጄሪያ ደግሞ በጥይት፥-ሃያ ሰወስት ሰዉ ተገደለ።

የቀድሞዉ የሊቢያ መሪ የኮሎኔል ሙዓመር ቃዛፊ ደጋፊና ተቃዋሚ ጎሳ ታጣቂዎች ከቃዛፊ መገደል በሕዋላ ከፍተኛ ዉጊያ ያደረጉበት ወር ነበር።ሰኔ ሃያ-ብቻ አንድ መቶ አምስት ሰዎች ተገደሉ።ለግብፆች ግን ወሩ የዓመት ከመንፈቅ ትግላቸዉ ሁለተኛ ድል የታየበት ነበር።

በግብፅ የረጅም ጊዜ ታሪክ ፖለቲከኞች ለመሪነት ተወዳድረዉ ሕዝብ በድምፁ የሚፈልገዉን መረጠ።ሰኔ ሃያ-አራት።

የቀድሞዉ የሙስሊም ወንድማማቾች ፓርቲ አባል ዶክተር መሐመድ ሙርሲ በሚመሩት መንግሥት ሁሉም ግብፃዊ እንደሚወከል ቃል ገብተዉ ነበር።ግብፅ-ግርግር ቃል-ተስፋዉ ግን ዳር አልዘለቀም።ወይም ተቀባይ አላገኘም።ፕሬዝዳት ሙርሲ በሙባረክ ዘመን የተሸሙ ጠቅላይ አቃቤ ሕግን በአምባሳደርነት መሾማቸዉ፥ የሕገ-መንግሥታዊ ፍርድ ቤት ዳኞችን ሥልጠን መቀነሳቸዉን፥ ከሁሉም በላይ ባለፈዉ ሳምንት የፀደቀዉን ሕገ-መንግሥት ረቂቅን በመቃወምና በመደገፍ ሰበብ-የግብፅ ሕዝብ ካደባባይ ሰልፍ ሳይለይ-ድምፁን እንደሰጠ አመቱ ተጠቃለለ።

ሰኔ-ሰላሳ።የዩናይትድ ስቴትስ ምሥራቃዊ የባሕር ጠረፍ ግዛቶችን የመታዉ አዉሎ ንፋስ-አስራ አምስት ሰዉ ገደለ።ማዕበሉ በተለይ የኤሌክትሪክ መስመሮችን በመበጣጠሱ፥ በሚሊዮን የሚቆጠሩ የኦሐዮ፥ የቨርጂኒያ፥ የሜሪላንድ እና የዲስትሪክት ኦቭ ኮሎምቢያ አካባቢዎች በቀን ጨለማ ተዋጡ።

ጥንት የብሪታንያ ቅኝ ገዢዎች በአሸባሪነት የወነጀሏቸዉ፥ኋላ አሜሪካኖች የሚያደንቁ የሚደግፏቸዉ፥ እስራኤሎች እንደመሪ የሚያከብሯቸዉ፥ ፍልስጤሞች እንደ ጨካኝ የሚጠሏቸዉ፥ ከ1970ዎቹ ወዲሕ የካይሮ ገዢዎች እንደ ሰላም አርበኛ የሚያመወድሷቸዉ አንድ እስራኤላዊ ፖለቲከኛ ነበሩ።ይትሳቅ ሻሚር የሚባሉ።ድሮ እንግሊዞች ኢትዮጵያ ወይም ኤርትራ አስረዋቸዉ የነበሩ፥ ኋላ በኢትዮጵያዉያን አይሁዶች ዘንድ አጥብቀዉ የሚወደዱ ቁመተ አጭር፥ ደፋር ፖለቲከኛ መሪም ነበሩ።ብዙ እንዳወዛገቡ ብዙ ነረዋል።ዘጠና ሰባት አመት።ሰኔ-ሰላሳ ግን ሞቱ።

ሐምሌ ግም ከማለቱ ሕንድ፥ ባንግላዴሽ፥ ጃፓና፥ ቻይናን ያጥለቀለቀዉ ጎርፍ ብዙ መቶዎቹን ገድሎ፥ ብዙ ሺዎችን አፈናቅሎ-ሲጋመስ፥ ሩሲያንም በዉሐ እጁ አረጣጠባት።እና መቶ አርባ ሰዉ ገደለባት።የእስራኤል ሐገር ጎብኚዎችን አሳፍሮ ቡልገርስ ከተሰኘዉ የቡልጋሪያ አዉሮፕላን ማረፊያ ወደ ከተማ ይጓዝ የነበረ አዉቶቡስ በቦምብ ጋይቶ ስድስት እስራኤላዉን ተገደሉ።ሰላሳ ቆሰሉ። ሐምሌ-አስራ-ስምት።

ሰሜን ኮሪያ ለቀድሞ ገዢዋ ሞት ያጠለቀችዉን የሐዘን ማቅ-ለአዲሱ መሪዋ ሹመት ፌስታ አዉልቃ ቦረቀች።የሟቹ ታላቅ መሪ የኪም ጆንግ ኢል ልጅ፥ ኪም ጆንግ ኡን በማርሻል ማዕረግ የሐገሪቱ ላዕላይ መሪነትን ሥልጣን በይፋ ተረከቡ።የሃያ-ስምንት ዓመት ወጣት ናቸዉ።ሐምሌ አስራ-ስምት።

ፒዮንግ-ዮንግ በሹመት ሽልማት በተንበሸበሸች በሳምንቱ ገሚስ ሐገሪቱን ያጥለቀቀለዉ ጎርፍ ሰማንያ-ስምት ሰዉ ገደለ።ስድስት ሺሕ አፈናቀለ።

ግብፅ-ምርጫ

ከኢራቅ፥ ከአፍቃኒስታን፥ ከፓኪስታን፥ ከሶሪያ፥ ከየመን፥ ከናጄሪያ፥ ከማሊ፥ ከሊቢያ የእልቂት ፍጅት፥ ከሕንድ-እስከ ፊሊፒንስ፥ ከቻይና እስከ ኮሪያ፥ ከጃፓን እስከ ኢንዶኔዥያ፥ ከኔፓል እስከ ቬትናም ከደረሰዉ የተፈጥሮ መቅሰፍት፥ ከአሜሪካኖች የምርጫ ዘመቻ-ፋታ ዓለም ገለል ቀለል፥ ዘና የሚበልበት ድግስ አገኘ።ሐምሌ ሐያ-ሰባት።የበጋ የኦሎምፒክ ዉድድሮች በይፋ ተጀመረ።

«እንኳን ወደ ለንደን በደሕና መጣችሁ።»

አሉ የአዘጋጆቹ መሪ።

«የለንደን ዉድድሮች መጀመሩን አዉጃለሁ።»

ዳግማዊት ንግሥት ኤሊዛቤት።

ዉድድሩ ነሐሴ-አስራ ሁለት ተዘጋ።ኢትዮጵያዉያን በመሪያቸዉ፥ በርዕሠ ሊቃነጳጳሳታቸዉ ሞት ሐዘን ላይ ናቸዉ።ሰኔ ሃያ-አምስት።አሜሪካኖች ጨረቀን ለመጀመሪያ ጊዜ በረገጠዉ እዉቅ ጠፈረተኛቸዉ ሞት ኢትዮጵያዉያንን መሠለ።ሰኔ ሃያ-አምስት።ኒል አርምስትሮግ ሞቱ።ሰባ-ሁለት ዓመታቸዉ ነበር።

አሜሪካ የሚኖር አንድ ግብፃዊ የሙስሊሞችን ነብይ የሚያንቋሽሽ ፊልም ማሳራጨቱ ያስቆጣዉ ሙስሊም የዓለም ርዕሠ-ከተሞችን በቁጣ እንዳተከተከ ነሐሴ-ተራዉን ለመስከረም ለቀቀ።መስከረም አስራ አንድ።አሜሪካኖች በሁለት ሺሕ አስንድ፥ ኒዮርክና ዋሽንግተን ላይ በአሸባሪዎች የተገደሉባቸዉን ዜጎቻቸዉን ሲዘክሩ፥ በመላዉ ዓለም የሚገኙ የአሜሪካ ኤምባሲዎች የተለያዩ ጥቃቶች ዒላማ ሆነዉ፥ ወይም ከጥቃቱ ለማምለጥ ተከርችመዉ ዋሉ።

የቤንጋዚ-ሊቢያዉ ጥቃት ግን ለአሜሪካ ፖለቲከኞች ታላቅ ዉርደት ለፕሬዝዳት ባራክ ኦባማ መስተዳድር ደግሞ ሐያል ፈተና ነበር።የኤምባሲዉን ቅጥር ግቢ ያጋዩት ታጣቂዎች የአሜሪካዉን አምባሳደር ጄ. ክርስቶፈር ስቴቫንስን ጨምሮ አራት ዲፕሎማቶችን ገደሉ።

ሕይወት ግን ቀጠለች።የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ጠቅላላ ጉባኤም ተጀመረ።ሶማሌዎች አዲስ መሪ ሥለተመረጠላቸዉ በደስታ-ዓመቱን አጋምሰዉ መስከረምን ሲያሰሉ፥ በምሥራቅ አፍሪቃ ጦር የሚደገፈዉ የመንግስታቸዉ ጦር ሐምሳ የአሽባብ ደፈጣ ተዋጊዎችን መግደሉን አበሰረ-ወይም አረዳቸዉ።

ፓኪስታን፥-ካራቺና ላሆር የሚገኙ ሁለት ፋብሪካዎችን ያጋየዉ ቃጠሎ ሰወስት መቶ አርባ ሰዎችን ገደለ።የፋብሪካ ቃጠሎ ብዙ የባንግላዴሽ ዜጎችንም ገድላል። ከካቡል፥ ከባግዳድ፥ ከደማስቆ፥ከሌጎስ፥ ከሰነዓ ከሽብር-ጦርነት፥ ከሞት-ስደት ሌላ ሌላ ነገር ሳይሰማ መስከረም አበቃ።አባስ-ተመድ ጉባኤ ጃፓንና የቻይና በአንዲት ደሴት ይገባኛል ሰበብ የገጠሙት ዉዝግብ እንደናረ የባተዉ ጥቅምት የዩናይትድ ስቴትስ ተቀናቃኝ ፖለቲከኞች የምርጫ ዘመቻ ይጋጋምበት ያዘ።ናጄሪያ የሃያ-የኮሌጅ ተማሪዎቿ ሕይወት ለታጣቂዎች የደም ጥማት ገብራ-የተቀበለችዉን ጥቅምት-የተሰናበተችዉ በቦምብ ፍንዳታ፥ በታጣቂዎችና በፀጥታ አስከባሪዎች ግጭት ከመቶ በላይ ዜጎችዋ ተገድለዉባት ነዉ።

ከጥቅምት፥-ሃያ አራት እስከ እስከ ሰላሳ የካረቢክ ሐገራትን፥ በሐማስን፥ ዩናይትድ ስቴትስንና ካናዳን የመታዉ ዉሽንፍር አዘል ማዕበል ሁለት መቶ ዘጠኝ ሰዉ ገደሎ፥ ብዙ ሺዎችን አፈናቅሎ፥ ሃያ ቢሊዮን ዶላር የተገመተ ንብረት አዉድሞ ወሩ ሲያበቃ-ገርገብ አለ።

የተፈጥሮዉ መቅሰፍት ረገብ ሲል፥ የአሜሪካ ተፎካካሪ ፖለቲከኞች የምርጫ-ዘመቻ ሙግት ፉክክር ግን ጋመ።

አገረ ገዢ ሚት ሮምኒ።

ፕሬዝዳት ባራክ ኦባማ።የአሜሪካ ሕዝብ ሕዳር ስድስት ድምፅ ሰጠ።ፕሬዝዳት ባራክ ኦባማ አሸነፉ።

የአረብ ሕዝባዊ አብዮትን ሒደት ዉጤት፥ የሶሪያዉን ጦርነት በቅርብ ርቀት ሲከታተሉ የቆዩት የእስራኤልና የፍልስጤም ፖለቲከኞች ደም ላስለመዱት ምድር ደም ሳያፈሱበት ዓመቱን ሊሰናበቱ አልፈለጉም።ሕዳር አስራ-አራት። እስራኤል ጓዳ ሠራሽ ሮኬቶች ተኮሱብኝ ያለቻቸዉን የሐማስ ደፈጣ ተዋጊዎችን ለማጥፋት ጋዛ ሠርጥ ላይ ዘመተች።

በሳምንቱ ተኩስ አቁም ተባለ።የእስራኤሉ የዓለም ምርጥ ጦር ጓዳ ሰራሽ ሮኬት ከታጠቀዉ ከሐማስ ሚሊሺያ ጋር ባደረገዉ ዉጊያ አሸናፊ ተሸናፊዉ አለየም።አንድ መቶ ስልሳ ፍልስጤሞች መገደላቸዉ፥ አንድ ሺሕ ያሕል መቁሰላቸዉ ግን እዉነት ነዉ።እስራኤሎች አራት ተገድሎባቸዋል። ሁለት መቶ አስራ-ዘጠኝ ቆስሎባቸዋል።

ለፍልስጤሞቹ ፕሬዝዳት ለማሕሙድ አባስ ግን ሕዳር የዲፕሎማሲ ድል የተመዘገበበት ወር ነበር።ሕዳር ሐያ ዘጠኝ-ኒዮርክ።የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ጠቅላላ ጉባኤ።በአብላጫ ድምፅ ፍልስጤምን ሐገር ያልሆነች የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት አባል አደረጋት።ፍልስጤሞች የጋዛ ሐዘን-እንባቸዉን በኒዮኩ ዉሳኔ ፌስታ ተለቃለቁት።

ጋዛ ስትንድ


ታሕሳስ። ዓመቱ ሊጠናቀቅ ዕለታት ሲቀሩት ብዙ ጋዜጠኝችንና የመገናኛ ዘዴ ባለሙያዎችን በማስገደል አቻ የሌለዉ ዓመት መሆኑ ተመሠከረ።በባለሙያ ጋዜጠኞች ግድያ ሶማሊያ አንደኛ ናት።አስራ-ስምት ጋዜጠኞች ተገድለዉባታል።በኢንተርኔት ዘጋቢዎች፥ በመገናኛ ዘዴዎች በድጋፍ ሰጪ ሠራተኞች ሞት ግን አንደኝነቱን ሶሪያ ያለተቀናቃኝ ይዛዋለች።በድምሩ ስልሳ አምስት።ፓኪስታን አስር ጋዜጠኞች ተገድለዉባት-ሰወስተኛ ወጥታለች።

ዓመቱ የጊኒ ቢሳዉ፥ የማላዊ፥ የጋና፥ የኢትዮጵያ፥ መሪዎች ሞተዉበታል።የቬንዙዌላዉ ፕሬዝዳት ሁጎ ሻቬዝ ለዳግም መሪነት ተመርጠዉበት ግን በተቃራኒዉ አሁን ባመቱ ማብቂያ ታማዉ እያጣጠሩበት።

ሐምሌ ላይ የደቡብ ኮሪያዉ ድምፃዊ ያዜማት ሙዚቃ ከኮሪያ ልሳነ-ምድር ታልፋለች ብሎ ያኔ የገመተ ጥቂት ነበር።ባመቱ ማብቂያ ግን የዓለም ወጣት እንደ ብሔራዊ መዝሙሩ እያዜመ አዲሱን ዓመት ሊቀበል ዳንኪራ ይረግጥበታል።


ዘመን ለምትለዉጡ መልካም አዲስ ዓመት።
SELAM + FIKR MINGIZEAM LENANTE YIHUN
ማህቡብ
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 264
Joined: Thu Aug 18, 2005 3:17 pm

Postby ጌታ » Wed Jan 02, 2013 7:10 pm

አቤት አቀራረብ!!! ለዛው ይዘቱ ልዩ ነው ማህቡባችን!! ጥፍጥ ብሎኝ አወራረድኩት........
ኢትዮጵያ እጆቿን ወደ እግዚአብሄር ትዘረጋለች!!!
ጌታ
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 3029
Joined: Sun Apr 17, 2005 5:35 pm
Location: ዶሮ ተራ

Postby ማህቡብ » Tue Jan 15, 2013 2:52 pm

ሰላም ጤና ይስጥልኝ :) ጌትሽ ሙዝ እና ሾተል ሁላችሁንም አመሰግናለሁ::

ዘመን በርቆ ዘመን ሲጠልቅ ቀሪው ታሪክ ነው::

የፈረንሳይ ጦር ዘመቻ፤ማሊና ሶማሊያባጭር ቃል-ፈረንዮች ሶማሊያ ላይ ተሸነፉ።ከዓለም አቀፉ አሸባሪ ድርጅት ከአል-ቃኢዳ ጋር ያበረዉ፥ በአፍሪቃዉያን ጦር ዉጊያ የተዳከመዉ አሸባብ ባንፃሩ ታላቅ «ድል» አስመዘገበ።---ፕሬዝዳት ኦላንድ መፅናኛ ማሊ አለችላቸዉ

ለፕሬዝዳንት ኒኮላ ሳርኮዚ ሊቢያ የዋሽንግተን ለንደን፣ አቻዎቻዉን ያሳበሩባት፣የሪያድና የቀጠር ታማኞቻቸዉን ያስከተሉባት፣ ከሌሎች የተቋደሷት የጋራቸዉ ነበረች።ኮትዲቫር ግን በአቻ-ተከታዮቻቸዉ ፍቃድ፣ የብቻቸዉ።ለፕሬዝዳንት ፍራንሷ ኦሎንድ ሶማሊያ ወይም ሶሪያ ከሌሎቹ የሚቃመሷት የጋራቸዉ ነች።ማሊን ግን፣ሌሎችን የሚያስከትሉባት የብቻቸዉ አደረጓት።ኦሎንድ ሶማሊያ ላይ ቢያንስ ላሁኑ ከሸፈባቸዉ።ማሊ ላይ የሚወቁት፣ ሳርኮዚና ተሻራኪዎቻቸዉ የቃዛፊን ጥፋት-ከነሕይወታቸዉ ሲያጠፉ ሊቢያላይ የዘሩት ጥፋት-ምርት መሆኑ ነዉ ግራዉ።ለአንባገነኖች እብሪት፥ ለአክራሪዎች እብደት፣ ለምዕራቦች ፡ጥቅም ሚሊዮኖች መጥፋት፣መሰቃየታቸዉ ደግሞ ያሳዝናል።የአስተምሕሮቱ እንዴትነት ያጠያይቃል።ላፍታ አብረን እንጠይቅ።


DGSE በሚል የፈረንሳይኛ ምሕፃረ-ቃል የሚጠራዉ የፈረንሳይ የሥለላ ድርጅት ልዩ ጦር ባልደረባ ዴኒ አሌክስና ጓደኛዉ ሶማሊያ የገቡበት ዕለት፥ መንገድ፥ ሶማሊያ ዉስጥ የሠሩት ያኔም-አሁንም ድብቅ ነዉ።ዓላማቸዉ ግን ብዙ ያልተብራራ-ግን በግልፅ የሚታወቅ ነዉ።ሥለላ።


የሶማሊያዉ አክራሪ ደፈጣ ተዋጊ ቡድን አሸባብ ሐምሌ-ሁለት ሺሕ ዘጠኝ (ዘመኑ በሙሉ እንደ ጎርጎሮሳዉያኑ አቆጣጠር ነዉ) ከማረካቸዉ ወዲሕ የአጋቾቹ አሸባሪነት፥ ኢሰባአዊነት፥ የታጋቾቹ መሰቃየት፥ ከታጋቾቹ አንዱ የማምለጡ ጀግንነት በየመገናኛ ዘዴዉ ሲፈጭ-ሲቦካ፥ ታጋቾቹን ለማስለቀቅ የሚደረገዉ ድርድር፥ የተወሰደና የሚወሰደዉ እርምጃ በሚስጥር እንደተያዘ ታጋቾቹን ያዘመቱት ፕሬዝዳት ሳርኮዚ በፕሬዝዳት ኦላንድ ተከቱ።

ታጋቹ ዴኒ አሌክስ

ኦሎንድ ሳርኮዚ እንዳዘመቱት አሸባብ እጅ የወደቀዉን ሠላይ ለማስለቀቅ ካለፈዉ አርብ ሌሊት የተሻለ ቀን አላገኙም ነበር።ማሊ ያዘመቱት ጦር የቀድሞ የሐገራቸዉን ቅኝ ተገዢ ሐገር ሰሜናዊ ግዛት የሚቆጣጠሩትን አማፂያንን በጄት-የመደብደቡ ዜና ሳይቀዘቅዝ፥በዩናይትድ ስቴትስ የጦር ጄቶች የታጀቡት የፈረንሳይ የጦር ሔሊኮብተሮች ሶማሊያን የአየር ክልል እየገመሱ ከሚሹት ደረሱ።

«የከባድ ተኩስ ድምፅ ከእንቅልፋችን ቀሰቀሰን» አሉ አንድ የቡሎ ማረር ከተማ ነዋሪ።«ከሌሊቱ ስምንት ሰዓት ነበር» አከሉ።ከተማይቱ ላፍታ ተንቀረቀበች።በዩናይትድ ስቴትስ ጦር የታገዘዉ የፈረንሳይ ልዩ ኮማንዶ ጦር አስራ-ሰባት የአሸባብ ተዋጊዎችን መግደሉ ተነግሯል።ታጋቾን ግን አላስለቀቀም።ምናልባትም አስገድሎት ይሆናል።የአንድ ባልደረባዉን አስከሬን ይዞ፥ ሌላ ቁስለኛዉን ለማዉጣት እንኳ ጊዜ-አጥቶ ወደመጣበት እብስ አለ።

መከላከያ ሚንስትር ኢቭ ለ ድርዮ ምክንያት አላጡም።

«አፀፋዉ ጥቃት ከጠበቅነዉ በላይ ጠንካራ ነበር።በተለይ ከባድ መሳሪዎቹን ከግምት አላስገባናቸዉም ነበር።ዴኒ አሌክስ ለሰወስት ዓመት ከመንፈቅ ሰብአዊነት በጎደለዉ ሁኔታ እንደታገተ ነዉ።እሱን ለማስለቀቅ ያደረግነዉ ድርድርም መና ነዉ የቀረዉ።እዚያ እንደታሰረ እርግጠኞች ነበርን።(አካባቢዉን) ያጠቃነዉም እሱን የማስለቀቅ ግዴታ ሥለነበርብን ነዉ።»የፈረንሳይ ተዋጊ ጄት ማሊ ባጭር ቃል-ፈረንዮች ሶማሊያ ላይ ተሸነፉ።ከዓለም አቀፉ አሸባሪ ድርጅት ከአል-ቃኢዳ ጋር ያበረዉ፥ በአፍሪቃዉያን ጦር ዉጊያ የተዳከመዉ አሸባብ ባንፃሩ ታላቅ «ድል» አስመዘገበ።የአሸባብ ባለሥልጣናት እንደሚሉት ፕሬዝዳት ሳርኮዚ ያዘመቱት ሰላይ ወታደር ዴኒ አሌክስ አልሞተም።የፈረንሳይ ባለሥልጣናት ግን ሞቷል ባይ ናቸዉ።

አሌክስ ኖረም-ሞተ ለፕሬዝዳት ኦላንድ መፅናኛ ማሊ አለችላቸዉ።የማሊዉ ዉጥንቅጥም ልክ እንደ ሱማሊያዉ ሁሉ ሳርኮዚ ከሊቢያ ምሥቅልቅል ያስተረፉት ነዉ።መሠረቱ ግን፥ የአዉሮጳ በተለይ የፈረንሳይ ቅኝ ቀዢዎች ሰሜን እና ሰሜን ምሥራቅ አፍሪቃን ከረገጡበት ጊዜ ጀምሮ የሚታይ ሩቅ፥ ታሪኩም ረጅም ነዉ።

ለፕሬዝዳንት ኦላንድና ለተባባሪዎቻቸዉ ግን ረጅሙ ታሪክ አሰልቺ፥ ትክክለኛዉ ምክንያትም ዋጋቢስ ነዉ።ሰሜናዊ ማሊን የሚቆጣጠሩ ሐይላትም ከማሊ አልፈዉ ፈረንሳይን የሚያሰጉ አሸባሪዎች ናቸዉ።


«ከአሸባሪዎች ጋር የሚደረገዉ ዉጊያ ፈረንሳይ ዉስጥም ሁሉንም አይነት የጥንቃቄ እርምጃ እንዲወሰድ የሚያስገድድ ነዉ።የመንግሥት ሕንፃዎች በሙሉ እና የመገናኛ አዉታሮች ልዩ ጥበቃ እንዲደረግላቸዉ ጠቅላይ ሚንስትሩን ጠይቄያለሁ»

የበርበር ነገድ አባል የሆነዉ የቱአሬግ ጎሳ ለፈረንሳይ ቅኝ ገዢዎች አሜን ብሎ የገበረበት ዘመን የለም።አግ መሐመድ ዋዉ ቴጉይዳ ካሴን የመሩት የቱአሬግ ተዋጊ ሐይል በ1880 በፈረንሳይ ቅኝ ገዢዎችና በአካባቢዉ ተባባሪዎቻቸዉ ላይ የከፈተዉን ጥቃት ለመደፍለቅ የፈረንሳይ ጦርና ተባባሪዎቹ ድፍን አስር ዓመት መዋጋት ግድ ነበረበት።

የቱአሬግ ነገድ በብዛት የሠፈረባቸዉ ማሊና ኒጀር እንደ ብዙዎቹ ቅኝ ተገዢ የአፍሪቃ ሐገራት ሁሉ በፈረንሳዮች ፍቃድና ይሁንታ የየራሳቸዉን ባንዲራ ቢሰቅሉም የፓሪሶችን ጥቅም፥ፍላጎትና ትዕዛዝ ከማስፈፅም አለማለፋቸዉ፥ ነፃነቱ ለቱአሬጎች «ያዉ በገሌ» አይነት ቅሬታና ኋላም ቁጣን ነዉ የቀሰቀሰዉ።

በዚሕም ሰበብ ከ1962 ጀምሮ የባማኮና የንያሚ ገዢዎችን አጋዛዝ በመቃወም በተደጋጋሚ አምፀዋል። አመፃቸዉ በፈረንሳይ በሚታገዙት ገዢዎች በተደፈለቀ ቁጥር መሸሺጊያቸዉ ደቡብ ምሥራቅ አልጄሪያ፥ ደቡብ ምዕራብ ሊቢያ እና ሰሜናዊ ቡርኪናፋሶ ነዉ።

ፕሬዝዳንት ኦላንድ

የሊቢያዉ ገዢ ኮሎኔል ሙዓመር ቃዛፊ ትሪፖሊ ላይ ከተጠናከሩ በሕዋላ ደግሞ ሊቢያ ለቱአሬግ ተወላጆች መሸሸጊያ ብቻ ሳትሆን የጥሩ ገቢ ምንጭ፥ ጥራ ሥራ-ማግኚያ፥ ጥሩ መኖሪያ፥ በወታደርነት መሠልጠኛ፥ መቀጠሪያም ሐገር እንደሆነች ከቃዛፊ ዉድቀት ቀጥለለች።

በፕሬዝዳት ሳርኮዚ አስተባባሪነት፥ በፕሬዝዳት ባራክ ኦባማ እና በጠቅላይ ሚንስትር ዴቪድ ካሜሩን ድጋፍ ሰጪነት ሊቢያ የዘመተዉ የምዕራባዉን ጦር ኮሎኔል ሙዓመር ቃዛፊን ከረጅም ዘመን አጋዛዛቸዉ ጋር ሲያጠፋ የጋዛፊ ጦር ባልደረባ የነበሩት የቱአሬግ ተወላጆች ከነ-ሙሉ ትጥቃቸዉ ወደ ሰሜን ማሊ ገቡ።እና አዲስ አመፅ።

የመግሪብ አል-ቃኢዳ ከሚባለዉ አሸባሪ ቡድን የተገነጠሉ ሐይላት፥እና የሌሎች አሸባሪ ድርጅት አባላት ሰሜናዊ ማሊ ዉስጥ መመሸጋቸዉ አያጠያቅም።የሰሜን ማሊን አብዛኛ ግዛት ከመንግሥት ጦር የማረኩት፥ የሚቆጣጠሩት ግን አንሳር ዲን እና MNLA በሚል ምሕፃረ-ቃል የሚጠሩት ሐይላት ናቸዉ።ሁለቱም ቡድኖች በሊቢያ ጦር ዉስጥ እስከ ኮሎኔልነት ማዕረግ በደረሱ የጦር መኮንኖች የሚመሩ፥ በቅጡ የታጠቁ ሐይላት ናቸዉ።

ቃዛፊንና ሥርዓታቸዉን እስከ መግደል ብቻ ባለመዉ በሊቢያ አማፂያንና በምዕራባዉን ደጋፊያቸዉ ጦርና በቃዛፊ ታማኞች መካካል በተደረገዉ ዉጊያ በሺ የሚቆጠሩ ሊቢያዉያንን ተገድለዋል።በቢሊን የሚቆጠር ሐብት ንብረት ወድሟል።ቱአሬጎችን ጨምሮ በብዙ ሺሕ የሚቆጠሩ አፍሪቃዉያን ተበትነዋል።መቶዎችን ለባሕር ሲሳይ ዳርጓል።

ዘመቻዉ በራሷ በሊቢያና በአካባቢዉ ሐገራት የወደፊት ፖለቲካ ላይ የሚያሳድረዉ አሉታዊ ተፅዕኖ ከቁብ ስላልገባ የሰሜን ማሊ ሕዝብ ሁለተኛዉ ገፈት ቀማሽ ሆኗል።ሰሜናዊ ማሊን የሚያብጠዉ ጦርነት በሺሕ የሚቆጠር ሕዝብ ተገድሏል።የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት እንደገመተዉ ከግማሽ ሚሊዮን በላይ ሕዝብ አድም ተሰዶ፥ አለያም ተፈናቅሎ የዉጪ እርዳታ ጥገኛ ነዉ።

እንደ ፓሪሶች ሁሉ፥ ፓሪሶች ጦር ያዘመቱባቸዉ የማሊ አማፂያን አሁንም ለሌላ ጥፋት ይፎክራሉ።የአንሳር ዲን ተዋጊዎች «ለፈረንሳዮች የምናስተላልፈዉ መልዕክት፥ ጉዳዩ አሁንም በእጃችሁ ነዉ።የጠላትነት እርምጃችሁን አቁሙ።ይሕን ካላደረጋችሁ ግን የልጆቻችሁን መቃብር እየማሳችሁ፥ ወደ ገሐነብ እየሰደዳችኋቸዉ ነዉ።»

የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የፀጥታዉ ጥበቃ ምክር ቤት ባለፈዉ ሐሙስ በሙሉ ድምፅ ያፀደቀዉ ዉሳኔ ቁጥር 2085 ከወታደራዊ ዘመቻዉ በፊት በአማፂያንና በማሊ ጊዚያዊ መንግሥት መካካል የሚደረገዉ ድርድር እንዲቀጥል ይደነግጋል።

የአንሳር ዲን እና የMNLA ቡድናት ተወካዮች ከመንግሥት ጋር ለመደራደር ላለፈዉ ሐሙስ ቀጠሮ ነበራቸዉ።ዋጋዱጉ-ቡርኪናፋሶ ዉስጥ ይደረጋል የተባለዉ ድርድር በግልፅ ባልተነገረ ምክንያት ወደ ጥር አጋማሽ መዛወሩ በተሰማ ማግስት ግን ሰሜናዊ ማሊ በፈረንሳይ ጄቶች ትጋይ ገባች።


የጀርመኑ ዉጪ ጉዳይ ሚንስትር ጊዶ ቬስተርቬለ «ፖለቲካዊ ሒደት» ያሉትን የማሊን ተቀናቃኞችን የማደራደሩን ጥረትና መንግሥታቸዉ እንደሚረዳ አስታዉቀዋል።

«የጀርመን ተዋጊ ወታደሮች በዉጊያዉ ይሳተፋሉ ማለት ለክርክር የሚቀርብ ጉዳይ አይደለም።ይሁንና የፖለቲካዊዉን ሒደት ለማገዝ ዝግጁ ነን።»

ቬስተርቬለ «ፖለቲካዊ ሒደት» ያሉትም ሆነ፥ የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ድርድር እንዲቀድም መወሠሰኑ ወይም፥ተፋላሚዎችን ለማደራደር ሌላ ቀጠሮ መያዙ ጦርነቱ ከተጀመረ በኋላ ከእንግዲሕ የሚፈይደዉ መኖሩ ሲበዛ አጠራጣሪ ነዉ።

ሰወስት ሺሕ ጦር ለማዝመት ከተዘጋጁት ከምዕራብ አፍሪቃ የምጣኔ ሐብት ማሕበረሰብ አባል ሐገራት መካከልም ናይጄሪያና ሴኔጋል በሺሕ የሚቆጠሩ ወታደሮች አዝምተዋል።ፕሬዝዳት ሳርኮዚ ሎራ ባግቦን አሳስረዉ የኮትዲቯርን የመሪነት ሥልጣን ያስረከቧቸዉ አላሳኔ ዋተራም የሐገራቸዉ ጦር እንዲዘምት አዘዋል።

የማሊ ስደተኞች-ቡርኪናፋሶ

በወርቅ ማዕድን ከአፍሪቃ የሰወስተኝነቱን ደረጃ የያዘችዉ፥ በጥጥ፥ በማንጎ ምርቷ የታወቀችዉ ሰፊ፥ ደሐ፥ በረሐማ፥ ወደብ አልባዊቱ ሐገር የተደገሰላት ጦርነት ወዴት እንደሚያመራት ከግምት በላይ መናገር ላሁኑ በርግጥ ስሕተት ነዉ።በጣልቃ ገብ ጦሩ ዘመቻ፥ በዉጊያ ፉከራዉ መሐል የሚነገረዉ ድርድር እና ፖለቲካዊ ሒደት፥ ከአስራ-አንድ አመት ጦርነት በሕዋላ ከአፍቃኒስታን ታሊባኖች ጋር የሚደረገዉ አይነት ማለት ከሆነ ግን አስራ-አንድ ዓመት መጠበቅ ይኖርብናል።
SELAM + FIKR MINGIZEAM LENANTE YIHUN
ማህቡብ
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 264
Joined: Thu Aug 18, 2005 3:17 pm

Postby ማህቡብ » Tue Mar 05, 2013 2:57 pm

ዘመን በርቆ ዘመን ሲጠልቅ ቀሪው ታሪክ ነው ::

ከ1962 ጀምሮ ፈረንሳይ የጋቦን፥ የቻድ፥ የካሜሩን፥ የቡርኪና ፋሶ፥ የዛኢር፥ የኒዠር፥ የቱኒዚያ፥ የማዕከላዊ አፍሪቃ ሪፐብሊክ፥ የሩዋንዳ፥ የጅቡቲ እና የሌሎችም የቀድሞ ቅኝ ተገዢዎቿን አምባገነኖች ወይም አማፂዎችን በመደገፍ አፍሪቃ ዉስጥ ከሐምሳ ጊዜ በላይ ተዋግታለች።
ሠሜን ማሊ የሸመቁ ሙስሊም አማፂያንን የሚወጋዉ የፈረንሳይ ጦር፥ ድል፣ በድል እየተረማመደ ቅዳሜ፥ የግዛቲቱን ትልቅ ከተማ ጋዮ ተቆጣጠሮ ታሪካዊቷን ቱንቢክቱን ለመያዝ ከደጃፏ ደርሷል። በአዉሮጳ እና በአሜሪካ ሐያላን የፖለቲካ፣ የፕሮፓጋ፣ የሥንቅ-ትጥቅ ድጋፍ የተጠናከረዉ፣ በአፍሪቃዉን ወታደሮች የሚታገዘዉ የፈረንሳይ ጦር የበረሐማ-ግን ሥልታዊ፣ የደሐ ግን የማዕድን ሐብታሚቱን ሐገር ሙሉ ግዛት ከፓሪሶች እቅፍ የሚዶልበት ጊዜ ሩቅ አይደለም።ከዚያስ?-እንጂ ጥያቄዉ።ጥያቄዉ የወታደራዊ ጣልቃ ገብነትን ዓላማ፣ ሒደት ዉጤትን፣ የሚያጣቅስ-ሌላ ጥያቄ ማስከተሉ-እንጂ አነጋጋሪዉ።ላፍታ እንጠይቅ-እንነጋገር።
ለፈረንሳዊዉ የአፍሪቃ የፖለቲካ ጉዳይ አጥኚ ለፕሮፌሰር ሮናልድ ማርሻል ያቺን ጥያቄ-የወረወርኩት የዛሬ አሥራ-አምስት ቀን በዚሁ ዝግጅት ያልኩትን ለማስረገጥ ነበር።ለፕሬዝዳንት ኒኮላይ ሳርኮዝ ሊቢያ ከሌሎች የሚጋሯት አይቮሪኮስት ወይም ኮትዲቯር ግን በሌሎች፣ ፍቃድና ይሁንታ የብቻቸዉ ያደረጓት ነበረች።ፕሬዝዳንት ፍሯንሷ ኦሎንድ ደግሞ ከሌሎች የሚጋርዋት ሶሪያ ትሆን-ይሆናል።ማሊ ግን በሌሎች ድጋፍ፣ ፍቃድና ይሁንታ በርግጥ የብቻቸዉ ሆነች።
«ሙሉ በሙሉ እንደዚያ አይደለም።» መለሱ ፈረንሳዊዉ የፖለቲካ ሊቅ---ምክንያቱም እያሉ ቀጠሉም
አማፂያኑ


«ምክንያቱም አይቪሪኮስትን የጀመሩት ሺራክ ናቸዉ።---ሳርኮዚ ጨረሱት---በማሊ ግን ልክ ነዉ ኦላንድ ሰም እያገኙ ነዉ።»
እነሱ-ይቀያየራሉ።የወታደራዊ ጣልቃ ገብነት ዓላማ-መርሕን ግን ይወራረሳሉ፥ አንዱ የጀመረዉን ሌላዉ ካለበት ዘመን-ወግ ፈሊጥ ጋር እያጣጠመ ስም-እየሰጠ-ስም አግኝቶ ይቀጥላል-ወይም ይፈፅመዋል።
በሺሕ-ሥልሳ ስድስት (ዘመኑ በሙሉ እንደ ጎርጎሮሳዉያኑ አቆጣጠር ነዉ) ፈረንሳይና ብሪታንያ ሐስቲንግስ ላይ የገጠሙት ጦርነት በፈረንሳዮች ድል አድራጊነት መጠናቀቁ ለአሸናፊዎቹ ታላቅ ኩራት ማጎናፀፉ፣ ተሸናፊዎቹን ከፍተኛ ሐፍረት ማከናነቡ አላጠያየቅም።
የኩራት ሐፍረቱ ተቃርኖ ድል አድራጊዎች አዉሮጳን ከዚያም አልፈዉ ድፍን ዓለምን መግዛት አለብን ከሚል እብሪት፣ ድል-ተደራጊዎችን እንዴት እንሸነፋለን ከሚል-የበቀል ቁጭት ዶሎ ለሌላ ጦርነት ከመዘጋጀት ባለፍ ለአዉሮጳም-አዉሮጳ ለመራችዉ ዓለምም ሠላም የተከረዉ የለም።
እብሪት ብቀላዉ ሁለተኛዉ የዓለም ጦርነት እስከተፈፀመበት ጊዜ ድረስ አዉሮጳን ካንዱ ጦርነት ሳታገግም ከሌላ ጦርነት እየማገደ፣ ሌላዉ ዓለምን እያነደደ ዘመናት አስቆጥሯል። ወደ ዘጠኝ መቶ ዓመት ባስቆጠረዉ ዘመን የብሪታንያዉ ማሰራጫ ጣቢያ ቢቢሲ እንደዘገበዉ አዉሮጳ ሐምሳ-ሰወስት ትላልቅ ጦርነቶችን አስተናግዳለች።
ቲምቡክቱ ከሐምሳ ሰወስቱ፥ በአርባ-ዘጠኙ ትላልቅ ጦርነት፣ ወይም አንድ መቶ ሰማንያ አምስት ሥፍራ በተደረጉ ዉጊያዎች ፈረንሳይ በቀጥታ ተካፍላለች።ከአንድ መቶ ሰማንያ-አምስቱ ዉጊያ አንድ-መቶ ሰላሳ ሁለቱን የፈረንሳይ ጦር አሸንፏል።አርባ-ሰወስት ጊዜ ተሸንፏል።በተቀሩት አስሩ-በኳስ ግጥሚያ ቋንቋ-«አቻ ወጥቷል።»
ፈረንሳይና ጀርመን ባለፈዉ ሳምንት ለሐምሳኛ ዓመት ያከበሩት የወዳጅነት ስምምነት፣(በቀድሞዋ ይጎዝላቪያዉ አንዴ ከተከሰተዉ በስተቀር) አዉሮጳና አዉሮጳዉያን የመሠረቱት ሰሜን አሜሪካ-ጦርነትንና ከጦርነት የሚዶሉ እብሪት፣ብቀላዎችን እርግፍ አድርገዉ የመተዋችዉ፣ አለመግባባቶችን በዉይይት እየፈቱ ትብራቸዉን የማጠናከራቸዉ የቅርብ ጉሉሕ ምስክር ነዉ።
የጦርነት መጥፎ ዉጤት ለማወቅ በጦርነት መሐል ማለፍ አያስፈልግም።የጀርመኗ መራሒተ-መንግሥት የሰብአዊ መብት ጉዳይ አማካሪ ጉተር ኑከ እንደሚሉት ደግሞ ለፍጡራን ሕልዉና የሚጨነቅ ከጦርነት ጨርሶ አይገባም።

«ሁለንተናዊ የሠብአዊ መብት ፅንሰ ሐሰብን ከልቡ የተቀበለ ምንጊዜም ጦርነት አያደርግም። ምክንያቱም ጦርነት በተደረገ ቁጥር ሕይወት ሥለሚጠፋ፥ ከፍተኛ የሰብአዊ መብት ጥሰት ሥለሚፈፀም።ያም ሆኖ ፖሊስ ያስፈልጋል። አንዳዴ የሐይል እርምጃ ይወሰዳል።»
ፕሬዝዳንት ሻርልስ ዶጎልና መራሔ መንግሥት ኮንራድ አደናወር ዛሬ ለአዉሮጳ ሠላም፥ አድነት፥ የጋራ ብልፅግና መሠረት የጣለዉን ሥምምነት በ1963 መፈራረማቸዉ ከአስከፊዉ ጦርነት የመማራቸዉ፥ ኑከ እንዳሉት የሰብአዊ መብትን ሁለንተናዊ ፅንሠ-ሐሳብ ገቢር ለማድረግ የመወሰናቸዉ አብነት ነበር።
ይሁንና ስምምነቱ ከመፈረሙ በፊትና በሚፈረምበትም መሐል ፥ከኮሪያ እስከ ቬትናም ከአልጄሪያ እስከ ጋቦን፥ ከኩባ እስከ ምሥራቅ ጀርመን የነበረዉ ጦርነት፥ ግጭትና ፍጥጫ የሁለተኛዉ የዓለም ጦርነት ተዋጊዎች ለራሳቸዉ ሠላም፥ ሰብአዊነት፥ ትብብር፥ ብልፅግናን ለማስረፅ ከመወሰን መጣራቸዉ እኩል እንደገና ኑከ እንዳሉት ሌላዉን ዓለም እንደ ፖሊስ ለመቆጣጠር መፈለግ-ማቀዳቸዉን-ጠቋሚ፥ በጦርነት የኖረዉ ዓለምም በጦርነት የመቀጠሉ ምልክት ነበር።
የፈረንሳይና የጀርመን የወዳጅነት ስምምነት የብር ኢዮቢሊዮ በዓል ሲከበር የፈረንሳይ ጦር ሰሜናዊ ማሊን ከሚያተራምሰዉ ጦርነት መግባቱ ደግሞ ከአሁለተኛዉ የዓለም ጦርነት ማግሥት አዉሮጳና ሰሜን አሜሪካን ላይ ሠላም ሲሰርፅ ሌላዉ ጋ የቀጠለዉ ጦርነት ዛሬም ያለማባራቱ አብነት አይሆንም ማለት አይቻልም።
የፈረንሳይ ጦር ማሊ ላይ የሚወጋቸዉ አማፂያን አሸባሪዎች አለያም ጂሐዲስት መሆናቸዉን ያልመሰከረ-የለም።ካለም የሚሰማዉ የለም።አሸባሪዎች ደግሞ መጥፋት አለባቸዉ።እና ፕሬፌሰር ማርሻል እንደሚሉት የፈረንሳይ ጦር ዘመቻ ተገቢ ነዉ።

«ሁኔታዉ ምንድ ነዉ ጂሐዲስቶች ራሳቸዉ ሲቫሬ፥ ኮና እና ምብቲ ላይ ጥቃት ከፍተዋል።ይሕ አፀፋ ያስፈልገዋል።የማሊም ሆነ የኢኮዋስ ጦር ለጥቃቱ አፀፋ ለመስጠት አልቻሉም።ሥለዚሕ የፈረንሳዮች አርፈዉ ቢቀመጡ ኖሩ ምን-ይሆን ነበር።»
ጥያቄዉን ዛሬ መመለስ በርግጥ ይከብዳል።እንዲያዉ ለግምቱ ያሕል፥- ምናልባት እንደ ፈረንሳዮች ኮት-ከራቫት የሚያጠልቁት የባማኮ ገዢዎች እንደ ቱአሬጎች ወይም እንደ አረቦች ጀላቢያ ባጠለቁ፥ በጠመጠሙ፥ ጢማም ገዢዎች ይቀየሩ ነበር።ምናልባት የባማኮ ገዢዎችና የቱአሬግ አማፂያን ይታረቁ ይሆናል።ምናልባት ማሊ ኢራቅን፥ አፍቃኒስታንን ሊቢያን ትቀላቀል-ይሆናል።ምናልባት---ሌም ሰበብ መስጠት ይቻላል።
እርግጡ ግን-የፈረንሳይ ጦር ማሊ-ለመዝመት፥ መዋጋቱ የተሰጠዉ ምክንያት የጂሐዲስቶችን አደጋ ማስወገድ የሚል መሆኑ ነዉ።የፈረንሳይ ቅኝ ገዢ ጦር በ1954 ዲየን ቢየን ፉ ላይ እስከተሸነፈበት ጊዜ ድረስ እንዲሕ እንዳሁኑ በአሜሪካና በምዕራብ አዉሮጶች ርዳታ ቬትናሞቹን ለመዉጋቱ የተሰጠዉ ሰበብ ምክንያት «ኮሚንስቶችን ማስወገድ» የሚል ነበር።
ዩናይትድ ስቴትስ እዚያዉ ቬትናም፥ ከቬትናም በፊት ደግሞ የኢትዮጵያን ጨምሮ የገሚስ ዓለምን ጦር አስከትላ ኮሪያ ለመዝመት-መዋጋትዋ የተሰጠዉ ምክንያትም «የኮሚንስቶችን ሥጋት ማስወገድ» የሚል ነበር።እንደ እዉነቱ ከሆነ ኮሚንስቶች ይወገዱ የነበረዉ የፈረንሳይ ጦር በ1962 ተሸንፎ እስከ ወጣበት አልጄሪያዎችን ሲወጋ፥ ሰሜን አፍሪቃዊቱን አረባዊት ሐገር በማጥፋቱ፥ ወይም የሕዝብ ነፃነትን በመደፍለቁ ከመከሰስ-መወቀሱ ይልቅ «ሸፍቶችን ለማጥፋት» በመፋለሙ ሲደነቅ-ሲወደስ ነበር።
ከ1962 ጀምሮ ፈረንሳይ የጋቦን፥ የቻድ፥ የካሜሩን፥ የቡርኪና ፋሶ፥ የዛኢር፥ የኒዠር፥ የቱኒዚያ፥ የማዕከላዊ አፍሪቃ ሪፐብሊክ፥ የሩዋንዳ፥ የጅቡቲ እና የሌሎችም የቀድሞ ቅኝ ተገዢዎቿን አምባገነኖች ወይም አማፂዎችን በመደገፍ አፍሪቃ ዉስጥ ከሐምሳ ጊዜ በላይ ተዋግታለች።ለየጣልቃ ገብ ዘመቻ-ዉጊያዋ ከየዘመኑ ወግ ጋር የሚጣጠም ሰበብ ምክንያት ሰጥታለች።በወዳጆችዋ ተደግፋለች።
ሺራክ ጀምረዉት ሳርኮዚ ለጨረሱት ለኮትዲቯሩ ዘመቻ የተሰጠዉ ሰበብ ምክንያት አምባገነን መሪን አስወግዶ በሕዝብ የተመረጡትን
የአፍሪቃ መሪዎች-አዲስ አበባ ሥልጣን ማስያዝ ነበር።ለሊቢያዉ ድብደባ አማላይ ሰበብ ምክንያት ተበጅቶለታል።ለማሊዉ ዉጊያም «አሸባሪዎችን ማጥፋት» የሚል ቀልብ-ጆሮን ሳቢ ምክንያት መስጠቱ አልገደደም።ጥያቄዉ አምና እና ሐቻምና ማሊ ላይ የማይታወቁት አሸባሪዎች በመንፈቅ እድሜ ከየት መጡ ነዉ።
የሩሲያዉ ዉጪ ጉዳይ ሚንስትር ሰርጌይ ላቭሮቭ ከሊቢያ የሚል አጭር መልስ አላቸዉ።ላቫሮቭ ባለፈዉ ሳምንት እንዳሉት አልጄሪያ ዉስጥ በርካታ ሰዎችን አግተዉ የነበሩት አሸባሪዎች በሊቢያዉ ጦርነት ምዕራባዉያን ሐገራት ከጎናቸዉ አሰለፋዋቸዉ የነበሩት ሐይላት ናቸዉ።ሰሜን ማሊ የሸመቁት ደግሞ የቃዛፊ ጦር ባልደረቦች።
ፕሮፌሰር ማርሻልም ተቀራራቢ መልስ አላቸዉ።

«በርካታ ቱአሬጎች፥ ቱአሬጎች ብቻ ሳይሆኑ ሌሎችም፥ ግን ያዉ ባብዛኛዉ ቱአሬጎች ከሊቢያ ከባድ ዘመናይ ጦር መሳሪያና ጥይት ታጥቀዉ ማሊ ገብተዋል።ብዙዎቹ የማሊ ጦርን መቀላቀል ፈልገዉ ነበር።ጦሩ ግን ቀድሞ ፈረሰ።እነሱም አልተደራጁም ነበር።በዚሕ መልኩ ሲታይ የሊቢያዉ ቀዉስ አሁን ሠሜን ማሊለ ለምናያቸዉ አማፂያን እግረኛ ጦር አበርክቷል።»
የሊቢያዉ ጦርነት የረጅም ጊዜ፥ አካባቢያዊ መዘዝ ባለመጤኑ ዛሬ ማሊ በጦርነት ትነዳለች።ሕዝቧ ያልቃል፥ ይሰደዳል፥ ይፈናቀላልም።ከማሊዉ ዉጊያ ቀጥሎ የሚሆነዉን የሚያዉቅ የለም።የፈረንሳይ ጦር የሚወጓቸዉ አማፂያን ግን ባብዛኛዉ ወደ ሊቢያ እየተመለሱ ነዉ።
ከሁለተኛዉ የዓለም ጦርነት ማግሥት ጀምሮ የዋሽግተን፥ የሞስኮ፥ የፓሪስ፥ የለንደን ሐያላን በየፊናቸዉ በቀጥታ ወይም በተዘዋዋሪ በሚመሩት ወታደራዊ ፖለቲካዊ ጣልቃ-ገብነት በየዘመኑ የነበረ ጥቅማቸዉን ማስከበር ችለዋል።
ኮኮሪያ እስከ ቬትናም፥ ከመካከለኛዉ ምሥራቅ እስከ አፍሪቃ፥ ከኩባ እስከ አፍቃኒስታን፥ ከሶማሊያ እስከ ኮትዲቯር፥ ከኢራቅ እስከ ሊቢያ ጣልቃ በተገባ ቁጥር ጊዚያዊ ጥቅምን ከማስከበር ባለፍ ጣልቃ-የሚገባበትን ትክክለኛ ምክንያት፥ የዉጊያዉን ዉጤት፥ የረጅም ጊዜ ተፅዕኖዉን ለማጤን አለመፈለጋቸዉ ግን ዓለምን በተለይ አፍሪቃና እስያን ከጦርነት አዉድ ሆነዉ እንዲቀሩ አስገድዷቸዋል።
ከቀዝቃዛዉ ጦርነት ፍፃሜ በተለይም ከአሜሪካ መራሹ የአፍቃኒስታን ዘመቻ ማግሥት እንዳዲስ በተያዘዉ ሥልት መሠረት ከዳርፉር እስከ ሶማሊያ፥ ከኢትዮጵያ እስከ ኤርትራ፥ ከኮንጎ ዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ እስከ ላይቤሪያ፥ አሁን ደግሞ እስከ ማሊ በተለጠጠዉ ወታደራዊ ጣልቃ ገብነት የአፍሪቃ ሐገራት ተሳትፎ ጨምሯል።የአፍሪቃ መሪዎች ለአፍሪቃዉያን ችግር አፍሪቃዊ መፍትሔ ማለታቸዉ አልቀረም።
ጋዎ-ሰሜን ማሊ አዉሮፕላን ማረፊያ የአፍሪቃ መሪዎች የየራሳቸዉን ሕዝብ በብረት ጡጫ-እየቀጠቀጡ የሌዉ አፍሪቃዊ ችግር ያስጨንቀናል ማለታቸዉ ከማሳዘን፥ ማስተዛዘቡ አልፎ-ብዙዎችን ያስፈግጋል።
እንዲያም ሆኖ አፍሪቃዉያን በራሳቸዉ የጋራ ስምምነት፥ ለሕዝባቸዉ ሠላምና ደሕንነት ጦር ያዘመቱ፥ ያዋጉ፥ ሠላም ያስከበሩበት ጊዜ የለም። ካለም ከቁጥር የሚገባ አይደለም።የማሊዉ ዘመቻ ሲነገር፥ ሲታቀድ፥ የምዕራብ አፍሪቃ የኢኮኖሚ ማሕበረሰብ (ኢኮዋስ) አባል ሐገራት ጦር የሚያዘምቱት የድርድሩ አማራጭ ካልተሳካ ብቻ ነዉ ተብሎ ነበር።ድርድሩ በቀጠሮ እንደተንጠለጠለ ፈረንሳዮች አፍሪቃዉያኑን ቀድሞ ከአፍሪቃዊቱ ማሊ ገቡ።
ሮናልድ ማርሻል ፈረሳዮች ምክንያት-ያሉትን ምክንያት ይናገራሉ።

«ባለፉት ወራት የሆነዉ ችግሩን በድርድር ለመፍታት አልጀሪያ የተለያዩ ሙከራዎችን አድርጋለች።ብዙ ጊዜ ግን ለድርድር አልጀሪያ የሚሔዱት የአማፂያኑ መልዕክተኞች ከንቅናቄያቸዉ ተጨባጭ አቋም ይልቅ የአልጀሪያን ፍላጎት ማንፀባረቁን ነዉ-የወደዱት።ይሕ አንዱ ነዉ።ሁለተኛዉ ለመደራደር ከፈለጉ የመፍቲ ከተማን ለምን አጠቁ።ይሕ ጥቃት አልጄሪያዎች የፈረንሳይ የጦር አዉሮፕላኖች በአየር ክልላቸዉ እንዲበር በመፍቀድ የፈረንሳይን ወታደራዊ ጣልቃ ገብነት ደግፈዋል።»
የአፍሪቃ ሕብረትና ኢኮዋስን የወከሉት አደራዳሪ ግን አልጄሪያ ሳትሆን የኮትዲቯሩ ፕሬዝዳት ብሌስ ኮፓወሬ ነበሩ።ኮምፓወሬም ሆኑ ሌሎቹ የአፍሪቃ መሪዎች የድርድሩ ሒደት ባልተፈለገ አቅጣጫ መሔዱ፥ አስከፊዉ ጦርነት መጋሙ፥ በፈረንሳይ መቀደማቸዉ አላስጨነቃቸዉም።ፈረንሳይን ለማመስገን ግን እየተሸቀዳደሙ ነዉ።
እስከ ትናንት ድረስ የአፍሪቃ ሕብረትን የሊቀመንበርነት ሥልጣን ይዘዉ የነበሩት የቤኒኑ ፕሬዝዳት ቶማስ ያዬ ቦኒን በጣም ያሳሰባቸዉ ደግሞ የፈረንሳይ ጦርን የሚያግዘዉ የኢኮዋስ ጦር ፈጥኖ አለመዝመቱ ነዉ።ፈጠነም-ዘገየ የአፍሪቃ ሕብረት፥ የተባበሩት መንግሥታት ድርጅትም እንዲዘምት የወሰኑት የኢኮዋስ አባል ሐገራት ጦርን ነበር።ቀድሞ የዘመተዉ ግን የፈረንሳይ ጦር ነዉ።የፈረንሳይ ጦርን ቀድሞ የተከተለዉ ደግሞ የኢኮዋስ አባል ያልሆነችዉ ግን የቀድሞ የፈረንሳይ ቅኝ ተገዢ የቻድ ጦር ነዉ።
ፈረንሳይ-ማሊ
ለምስቅልቅሉ ጦርነት መስቅልቅል መፍትሔ።አሸባሪን የማጥፋት፥ ማሊን የማረጋጋቱ ዘመቻ-እንዲሕ ቀጥሏል።የአፍሪቃ ሠላም፥ የዓለም ፀጥታ፥ የሕዝብ ደሕንነት፥ መብት ነፃነትም-እንዲሁ።ከዚያስ? ትናንት ተጠይቆ-ነበር።ዛሬም ይጠየቃል።ነገም።
SELAM + FIKR MINGIZEAM LENANTE YIHUN
ማህቡብ
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 264
Joined: Thu Aug 18, 2005 3:17 pm

Postby ማህቡብ » Mon Mar 11, 2013 6:56 am

አስተያየታቸውን የሰጡ የፖለቲካ ተንታኞች ፣ ያመጹት የኤርትራ ወታደሮች እርምጃ በኤርትራ መንግሥት ውስጥ ውጥረቱ የመባባሱና የአገዛዙ የመዳከም ምልክት መሆኑን ተናግረዋል
ትናንት ባመጹ ወታደሮች ተቋርጦ ነበር የተባለው የኤርትራ መንግሥት ቴሌቪዥን ስርጭት መቀጠሉ ተዘገበ ። በፈረንሳይ ዜና አገልግሎት ዘገባ መሰረት የኤርትራ መንግሥትም በዋና ከተማይቱ አስመራ ሁሉም ነገር ሠላማዊ መሆኑን አስታውቋል ። ይሁንና በጉዳዩ ላይ ለዶቼቬለ አስተያየታቸውን የሰጡ የፖለቲካ ተንታኞች ፣ ያመጹት የኤርትራ ወታደሮች እርምጃ በኤርትራ መንግሥት ውስጥ ውጥረቱ የመባባሱና የአገዛዙ የመዳከም ምልክት መሆኑን ተናግረዋል ።
የኤርትራ ፕሬዝዳንት የአቶ ኢሳያስ አፈወርቂ ቃል አቀባይ አቶ የማነ ገብረ መስቀል እንደ ትናንት ሁሉ ዛሬም አስመራ ሰላማዊ ናት ማለታቸውን የፈረንሳይ ዜና አገልግሎት ዘግቧል ። አንድ የተቃዋሚ ድረ ገፅን የጠቀሰው AFP ወደ 100 ይጠጋሉ ያላቸው ትናንት የኤርትራ ማስታወቂያ ሚኒስቴርን የተቆጣጠሩ ያመፁ ወታደሮች አዛዥ እጃቸውን ለመስጠት መስማማታቸውን ዘግቧል ።

የዘገባው እውነትነት ግን በሌላ ምንጭ አልተረጋገጠም ። አንዳንድ ምንጮችም የወታደሮቹን እርምጃ ከመፈንቅለ መንግሥት ጋር አስተካክለውታል ። በብሪታኒያው የጥናት ተቋም ቻተምሃውስ የአፍሪቃ ቀንድ ጉዳዮች አጥኚ አህመድ ሶልሜን ግን ከኤርትራ ትክክለኛ መረጃ ማግኘት በማይቻልበት ሁኔታ የተፈፀመውን ለማወቅ አዳጋች መሆኑን ነው ለዶቼቬለ የተናገሩት ።
« መፈንቅለ መንግሥት ወይም በወታደሩ ውስጥ አመፅ ነበር ለማለት አስቸጋሪ ነው ። በአሁኑ ጊዜ የትናንቱ እርምጃ ውጤት ምን እንደሆነ ለማወቅ መጠበቅ አለብን ። ስለዚህ በአሁኑ ጊዜ ሁኔታው ምን እንደሆነ አናውቅም ። ሆኖም የሆነ አይነት አመፅ እየተካሄደ ነው ። »
በአንዳንድ ዘገባዎች እንደተጠቆመው ወታደሮቹ ህገ መንግሥቱ እንዲከበርና የፖለቲካ እሥረኞች እንዲፈቱ የሚጠይቀው መግለጫቸው ትናንት በኤርትራ ቴሌቪዥን እንዲነበብ አድርገዋል ። የአፍሪቃ የሰላምና ፀጥታ ጉዳዮች አማካሪና የፖለቲካ ተንታኝ ዶክተር ማሃሪ ታደለ ማሩ የወታደሮቹ እርምጃ ለመንግሥት የማስጠንቀቂያ ደውል ነው ይላሉ ።
የኤርትራው ፕሬዝዳንት አቶ ኢሳያስ አፈወርቂ ሥልጣን ከያዙ ወዲህ ይህን መሰሉ የአመፅ እንቅስቃሴ መካሄዱ ሲነገር የአሁኑ የመጀመሪያው ነው ። ይህ ወዴት ሊያመራ ይችላል ? ምንስ ያመለክታል ተብለው የተጠየቁት የቻተም ሃውሱ ተንታኝ አህመድ ሶልመን ሲመልሱ

« ይህ በአጭር ጊዜ ውስጥ ለውጥ ማምጣት አለማምጣቱ ወደፊት የሚታይ ይሆናል ። እኔ ግን ለውጥ ማምጣቱን እጠራጠራለሁ ። ኢሳያስ ሁኔታዎችን መቆጣጠር የሚችሉ ይመስለኛል ። ሆኖም በርግጥ ይህ እርምጃ በቅርቡ የማስታወቂያ ሚኒስትር አቶ አሊ አብዶ ከድተው መኮብለላቸው ከተዘገበ በኋላ የተወሰደ 2 ተኛ እርምጃ ነው ። ስለዚህ በራሱ በአስመራ መንግሥት ውስጥ ውጥረቱ እየተጠናከረ የመምጣቱ ምልክቶች አሉ ። »
የፖለቲካ ተንታኝ ዶክተር መሃሪም ተመሳሳይ አስተያየት ነው ያላቸው ።
ትናንት በኤርትራ ማስታወቂያ ሚኒስቴር ውስጥ ያመፁ ወታደሮች ወሰዱ የተባለው እርምጃ የቻተም ሃውሱ ተንታኝ አህመድ ስልሜን እንዳሉት የህዝቡ ብሶት መገለጫ ተደርጎ ሊወሰድ ይችላል ።
« የተደማመረ ነገር እንዳለ ይታያል የሰብአዊ መብት ይዞታው ወጣት ኤርትራውያን በግዳጅ ለውትድርና መመልመላቸውና በአነስተኛ ክፍያም ለረዥም ጊዜ እንዲያገለግሉ በመደረጉ በርካታ ወጣት ዜጎች ህይወታቸውን ለማትረፍ ወደ ሌሎች የአካባቢው ሃገራት እየተሰደዱ ነው ። ስለዚህ ባለፉት 24 ሰአታት የተከናወኑት ድርጊቶች ለተፈፀሙት ሁኔታዎች እንደ ምሬት መግለጫ ሆነው ነው የሚታዩ ይመስለኛል ። ይህ እንደሚሆንም የሚጠበቅ ነው ። ሆኖም በኛ ግምት ይህ የአገዛዙ መዳከም ምልክት ነው ። »
SELAM + FIKR MINGIZEAM LENANTE YIHUN
ማህቡብ
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 264
Joined: Thu Aug 18, 2005 3:17 pm

Re: ይህን ያውቁ ኖሯል ?

Postby ማህቡብ » Mon Mar 11, 2013 7:41 am

ማህቡብ wrote:ውድ ተሳታፊዎች :- የዘዎትር ሠላምታየን በማስቀደም.... በዚህ አምድ ላይ የታሪክ መዝገብ አገላብጣችሁ ያገኛችሁትን በመጻፍ ለሌላው ያሳውቁ ::

***እንደ አውሮፓዊያን አቆጣጠር በ 1196 ንጉስ ቢያባው የያኔ ሴሎን ያሁንዋ ስሪላንካን ለመምራት ዘውድ በደፉ ከሁለት ሰአታት በሁዋላ አንድ ሰው ገደላቸው, በታሪክ ላይም ንጉስ ቢያባው አገራቸውን ለሁለት ሰአት በመምራት ይታወቃሉ ::

*** ለረጅም ጊዜ በትረ ስልጣን ይዘው የቆዩ የአለም መሪ የግብጹ ፋሮ/ንጉስ ሄፔ ሁለተኛው ናቸው እኒህ የግብጽ ፋሮ 2310 አመተ አለም ከክርስቶስ ልደት በፊት በ6 አመታቸው ዘውድ ጭነው ለ94 አመታት ግብጽን
ገዝተዋል ::

***የወረቀትን ገንዘብ ለመጀመሪይ ጊዜ በጥቅም ያዋለቸ አገር ማን እንደሆነች ታውቃላችሁ ? የወረቀትን ገንዘብ በጥቅም ላይ ያዋለችው የመጀመሪያ አገር ቻይና ናት ጊዜው ከክርስቶስ ልደት በፊት 910 አመተ አለም ::


ከአክብሮት ጋር
SELAM + FIKR MINGIZEAM LENANTE YIHUN
ማህቡብ
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 264
Joined: Thu Aug 18, 2005 3:17 pm

Postby ማህቡብ » Tue Mar 19, 2013 2:44 pm

ዘመን በርቆ ዘመን ሲጠልቅ ቀሪው ታሪክ ነው ::


«---አዲሲቱ ኢራቅን እንድትገነቡ እንረዳችኋለን።በነፃይቱ ኢራቅ በጎረቤቶቻችሁ ላይ የሚፈፀም ወረራ አይኖርም።ተቃዋሚዎች አይገደሉም።የማሰቃያ ጉሮኖዎች፥ የመድፈሪያ ክፍሎች አይኖሩም።የአምባገነኑ ዘመን እያበቃ ነዉ።የነፃነታችሁ ቀን
ተቃርቧል።» ቡሽ

መጋቢት 18 2003 (ዘመኑ በሙሉ እንደ ጎርጎሮሳዉያኑ አቆጣጠር ነዉ) የባግዳድ አደባባዮች።
ዋሽንግተን፥-ፕሬዝዳት ጆርጅ ደብሊዉ ቡሽ።«ሳዳም ሁሴንን እና ወንድ ልጆቹ በሃያ-አራት ሠዓታት ዉስጥ ኢራቅን ለቀዉ መዉጣት አለባቸዉ።»ዛሬ አስረኛ ዓመቱ።በሳልስቱ ባግዳድ ትነድ፥ ኢራቅ ትጋይ፥ ትወድም ገባች።የወረራዉ አስረኛ ዓመት መነሻ፥ የኢራቅ የዛሬ እዉነት ማጣቃሻ፥ የወረራዉ ዉጤት የአስተምሕሮት መድረሻችን ነዉ።ላፍታ አብራችሁኝ ቆዩ።

«ዛሬ ብዙ ኢራቃዉያን የንግግሬን ትርጉም በራዲዮ ይሰሙኛል።ለነሱ መልዕክት አለኝ።ወታደራዊ ዘመቻዉን ከጀመርን (ጥቃቱ) የሚያነጣጥረዉ ሐገራችሁን በሚገዛዉ ሕገ-ወጥ ግለሰብ ላይ ነዉ።በናንተ ላይ አይደለም።ተጣማሪ ሐይላችን ሥልጣን ሲይዝ የምትፈልጉትን ምግብና መድሐኒት እናቀርብላችኃለን።»

መጀመሪያ ግን ያዉ ቦምብ ሚሳዬል መላክ አለበት።መጋቢት አስራ-ዘጠኝ ለሃያ-አጥቢያ።ተላከ። ባግዳድ።

የአሜሪካዉ አልበቃም።የብሪታንያም ታከለበት።የያኔዉ የብሪታንያ ጠቅላይ ሚንስትር ቶኒ ብሌር።

«ዛሬ ማታ የብሪታንያ ሴትና ወንድ ወታደሮች የአየር፥ የምድርና የባሕር ዉጊያ ጀምረዋል። ተልዕኳቸዉ ሳዳም ሁሴንን ከስልጣን ማስወገድና ኢራቅን የአዉዳሚ የጦር መሳሪያ ትጥቅ ማስፈታት ነዉ።»
የወረራዉ ገሚስ ዉጤት


አዉዳሚ ጦር መሳሪያ-አደገኛ ነዉ።ቶኒ ብሌር ያኔ ብለዉት እንደነበረዉ ደግሞ አደጋዉ በጣም አስጊ ነዉ።ሳዳም ሁሴን በአርባ-አምስት ደቂቃ ዉስጥ ሊተኩስት ተዘጋጅተዋል።በአርባ-አምስት ደቂቃ።

«ኢራቅ ኬሚካዊና ባዮሎጂካዊ ጦር መሳሪያ እንዳላት መረጃዉ ያረጋግጣል።ሳዳም እነዚሕን መሳሪያዎች ማምረት መቀጠላቸዉን፥ መሳሪያዎቹን ለመተኮስ ወታደራዊ እቅድ እንዳላቸዉ እና እቅዱ በአርባ አምስት ደቂቃ ዉስጥ ገቢር እንደሚሆን (መረጃዉ) ያጠቃልላል።»

አርባ አምስት ደቂቃ።ሌሎችም ሰጉ፥ ፈሩ።እና ጦር አዘመቱ፥ በጥቅሉ ከመቶ ሰባ ሺሕ በላይ የዉጪ ጦር።ደካማይቱን፥ግን የነዳጅ ዘይት ሐብታሚቲን ኢራቅን ሌት ተቀን ከምድር፥ ካየር፥ ከባሕር ይወቅጣት ያዘ።

«ለኢራቆች የሽብር መዋቅሩን እንበጣጥሰላችኋለን።አዲሲቱ ኢራቅን እንድትገነቡ እንረዳችኋለን።በነፃይቱ ኢራቅ በጎረቤቶቻችሁ ላይ የሚፈፀም ወረራ አይኖርም።ተቃዋሚዎች አይገደሉም።የማሰቃያ ጉሮኖዎች፥ የመድፈሪያ ክፍሎች አይኖሩም።የአምባገነኑ ዘመን እያበቃ ነዉ።የነፃነታችሁ ቀን ተቃርቧል።»

ሳዳም አስወግዶ፥ በአርባ አምስት ደቂቃ የሚተኮሰዉን የኢራቅን የአዉዳሚ ጦር መሳሪያ ማርኮ፥ ለኢራቆች ሠላም፥ ዲሞክራሲ፥ ነፃነት፥ ብልፅግና ለማስፈን የዘመተዉ ጦር፥ በተከታታይ ጦርነት የላሸቀዉን፥ አስራ-ሁለት ዓመት በፀና ማዕቀብ የደቀቀዉን የኢራቅ ጠላቱን ለመፈረካከስ ሰወስት ሳምንት አልፈጀበትም።

ሚያዚያ ዘጠኝ አሜሪካ መራሹ ጦር ባግዳድን ተቆጣጠረ።የሳዳም ሁሴይን ሐዉልትም፥ የአሜሪካኖችን ባንዲራ ለብሶ፥ ባሜሪካኖች ታንክ ተጎትቶ፥ አሜሪካኖችን ባሰለፉት ሕዝብ ጭብጨባ፥ ፉጨት ታጅቦ ተገነደሰ።

በቡሽ ቋንቋ የሽብር መዋቅሩ ይበጣጠስ ያዘ።የአምባገነኑ ሥርዓት አበቃ።ኢራቆችም ነፃ ወጡ። ከእንግዲሕ አዲሲቱ ኢራቅ ነች።የመካከለኛዉ ምሥራቅ የሰላም፥ ዲሞክራሲ፥ የብልፅግና የፍትሕ አብነት የምትሆነዋ አዲሲቱ ኢራቅ-አሉ አሳቸዉ።ምን ገዷቸዉ።

«አምባገነኑ ሲወገድ እነሱ (ኢራቆች) ለመካከለኛዉ ምሥራቅ የሥላምና የሉዓላዊነት ምሳሌ የምትሆን ነፃ ሐገር መመስረት ይችላሉ።ዩናይትድ ስቴትስና ሌሎች ሐገራትም በዚያ አካባቢ ሠላምና ነፃነትን ለማሥረፅ አበክረዉ ይሠራሉ።»

የሳዳም ሁሴይን ሁለት ወንድ ልጆች ለአካለ መጠን ካልደረሰ የልጅ ልጃቸዉ ጋር ጭዳ ከሆኑ ዘጠኝ ዓመት አልፎታል።እንደ ጀግና ጦር ሜዳ ሊወድቁ ሲፎክሩ ኖረዉ እንደ አይጥ ከጉርጓድ የተመዘዙት ሳዳም ሁሴይን ራሳቸዉ ባደባባይ ከተንጠለጠሉ ስድስት ዓመት አለፈ::

የጥንታዊ ሥልጣኔ መገኛይቱ፥ የነዳጅ ሐብታሚቱ፥ የመካከለኛዉ ምሥራቅ የዘመናይ ትምሕርት የእዉቀት ምሳሌይቱ ኢራቅም ለመካከለኛዉ ምሥራቅ አይደለም ለመላዉ ዓለም ምሳሌ ሆናለች።የሠላም ግን አይደለም፥ የሽብር እንጂ።የብልፅግናም አይደለም፥ የእልቂት ፍጅት፥ የጥፋት ዉድመት፥ የሥቃይ-እንግልት፥ የሥደት ምሳሌ እንጂ።

ከወራራዉ ጀምሮ ዕለት በዕለት በሚያሽብራት ቦምብ ሚሳዬል አርባ ሺሕ ያሕል ታጣቂዎች፥ አንድ መቶ አርባ ሺሕ ሰላማዊ ሰዎች አልቀዉባታል።አራት ሚሊዮን ያክል አድም ተሰዶ፥ አለያም ተፈናቅሎ ምፅዋት ለማኝ ነዉ።አካሉ የጎደለ፥ ያበደ፥ የቆሰለዉን፥ ቤቱ ይቁጠረዉ። ከአቡ ግራይብ ወይሕኒ ቤት እስከ ፋሉጃ መንደሮች በአሜሪካኖችና በተባባሪዎቻቸዉ ጦር ግፍ የተዋለበት፥ የተደፈረ፥ የተገረፈዉን የቆጠረዉ ካለ ዘመድ-ወዳጁ ብቻ ነዉ።

የሐያሊቱ ሐገር ሐያል ጦር ጠቅላይ አዛዥ ጆርጅ ደብሊዉ ቡሽ ዛሬ ከዚያ ትልቅ ሥልጣናቸዉ ላይ የሉም።በአርባ አምስት ደቂቃ ዉስጥ ይተኮሳል የተባለዉ የኢራቅ ጅምላ ጨራሽ ፥አዉዳሚ ጦር መሳሪያም ያኔም አልነበረም።ኋላም አልተገኘም።«አለ» ብለዉ የዋሹት፥ «ሳዳም ሁሴን ሊተኩሱት ነዉ» እያሉ ዓለምን ያስፈራሩት ሐይላት ኋላ ሐቁ ሲፈጋ መዋሸታቸዉን ማመን ግድ ነበራባቸዉ የ።

«ሳዳም ባዮሎጂያዊና ኬሚካዊ ጦር መሳሪያ አላቸዉ፥ እያመረቱም ነዉ የሚለዉ መረጃ ሐሰት ነዉ።ይሕን አምናለሁ።ተቀብያለሁም።»

ጠቅላይ ሚንስትር ቶኒ ብሌር።እና እንደ ብልሕ ወጣት ፖለቲከኛ ተደንቀዉ፥ ተወደዉ፥ የያዙትን ሥልጣን በኢራቅ ሰበብ እንደ ዉሸታም መሪ ተወቅሰዉ፥ ተተችተዉ ሥልጣናቸዉን በግድ መልቀቅ፥ መርማሪ ኮሚቴ ፊት ጥፋታቸዉን መናዘዝ ነበረባቸዉ።የፍትሕ ነፃነት፥ የዲሞክራ አብነቱ ዓለም ግን አንዳቸዉንም በፍርድ ቤት ተጠያቂ ግን አላደረገም።

ወረራዉ፥ ዉሸቱ፥ ዉሸቱን ማመኑ አንዱም ለኢራቅ አልፈየደም።ለአሜሪካ፥ ለብሪታንያ፥ ተከታዮቻቸዉም አልጠቀመም።አሜሪካና ተባባሪዎችዋ አራት ሺሕ ስምንት መቶ አምስት ወታደሮቻቸዉ ተገድለዉባቸዋል።አራት ሺሕ አምስት መቶ ያሕሉ አሜሪካዉያን ናቸዉ።ከሐምሳ አንድ ሺሕ በላይ ቆስሏል።ከአንድ ሺሕ አምስት መቶ በላይ የኮንትራት ሠራተኞች ተገድለዋል።አርባ አራት ሺሕ ቆስለዋል።

አሜሪካና ተባባሪዎችዋ ወደ አንድ ትሪሊዮን ዶለር የሚቆጠር ገንዘብ ከስክሰዋል።ከብራዚል እስከ ፊሊፒንስ ያሉ ሐገራት የዜጎቻቸዉን፥ ከተባበሩት መንግሥታት ድርጅት እስከ ዓለም ቀይ መስቀል ማሕበሩ ያሉ ድርጅቶች የእዉቅ ባለሥልጣን፥ የተራ ሠራተኞቻቸዉን ሕይወት መገበር ግድ ነበረባቸዉ። ወረራዉ ለዓለም ሠላምም የተከረዉ የለም።ምዕራቡ ዓለም በምጣኔ ሐብት ድቀት፥ በገንዘብ ኪሳራ፥ግራ ቀኝ የሚላጋዉም፥ የተቀረዉም ዓለም በኪራ የሚዳክረዉ ከወረራዉ በሕዋላ ነዉ።

የቀድሞዋ የዩናይትድ ስቴት ዉጪ ጉዳይ ሚንስትር ወይዘሮ ሒላሪ ክሊንተን ሥልጣናቸዉን ሊለቁ ዕለታት ሲቀራቸዉ ባራት ዓመት ዘመነ-ሥልጣናቸዉ የሠሩት ነገር «የተበላሸዉን የአሜሪካ በጎ ሥም ዝና ወደነበረበት ለመመለስ መጣር» ነበር አሉ።

የፖለቲካ አዋቂ ዳንኤል ሐሚልተን እንደሚሉት የኦባማ መስተዳር በጥቅሉ፥ የክሊንተን በተናጥል ያደረጉት ጥረት በከፊልም ቢሆን ተሳክቷል።

«እንደሚመስለኝ ሒላሪ ክሊንተን ከፕሬዝዳት ኦባማ ጋር ሆነዉ፥ በቡሽ ዘመን የጠፋዉን አሜሪካ በዓለም የነበራትን መልካም ገፅታ ለማሻሻል ሞክረዋል።በአንዳዶች አይን ፕሬዝዳት ኦባማ መጥፎዉን ገፅታ አሻሽለዉታል።የክሊንተንም አስተዋፅኦ ቀላል አይደለም።»

ቶኒ ብሌየር


ፕሬዝዳት ጆርጅ ደብሊዉ ቡሽና ጠቅላይ ሚንስትር ቶኒ ብሌር ኢራቅን የወረሩት፥ የተባበሩት መንግሥታት ድርጅትን ደንብና ሕግ ጥሰዉ፥ የወዳጆቻቸዉን ምክር አጣጥለዉ፥ የመረጣቸዉን ሕዝብ ሳይቀር የአብዛኛዉን ዓለም ሕዝብ ተቃዉሞና ተማፅኖ ደፍልቀዉ ነዉ።እብሪት ማን አሕሎኝነታቸዉ ከሳዳም ሁሴን ሕይወት፥ ሥልጣን እኩል የሚሊዮን ኢራቃዉያንን፥ የብዙ ሺሕ አሜሪካዉያንን በመቶ የብዙ መቶ ብሪታንያዉያንን ሕይወት፥ አካል፥ ሐብት በማጥፋት አልቆመም።ዩናይትድ ስቴትስ ከሁለተኛዉ የዓለም ጦርነት ወዲሕ የነበራትን ተወዳጅነት፥ ክብር፥ ሥም ዝናም አጉድፎታል።የዓለም ሠላምንም አናግቶታል።አስር ዓመቱ።ከእንግዲሕስ?
SELAM + FIKR MINGIZEAM LENANTE YIHUN
ማህቡብ
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 264
Joined: Thu Aug 18, 2005 3:17 pm

Previous

Return to Warka Culture and Literature - ዋርካ ባህልና ሥነ ጽሑፍ

Who is online

Users browsing this forum: No registered users and 3 guests