by ዋናው » Fri Aug 23, 2013 1:11 am
እና ዋርካ ውስጥ አስር ዓመት ሞላን ማለት ነው... ጊዜ ግን እንዴት ቀልቃላ ነው አሁን እስቲ ምን አስሮጠው ... ሊደፋ...?
ሠላም ብያለሁ ለሁሉም ዋርካ ሎግ ኢን ማድረግ በስንት ጊዜ እሺ ብላኝ የብርቅ ሁሉ ነው ምፅፈው ይሄን ግሮሰሪ ለውቃውና ለ አባፈረዳ በአደራ እንዲያስተዳድሩ ብሰጣቸው ውቃው የአብዮት መቀልበሻ ፓኑ ደግሞ የጥቁር ፈረሱ ፋንድያ ማራገፊያ አደረጉት... ምን ላድርግ እሺ ለምስክርነት ሚበቁ ዋርካዊያን ሁሉ ዓለም በቃኝ ብለው ምንኩስናና ምናኔን መርጠው ትዝታቸው ብቻ ቀርቶ የውሃ ሽታ ሆነው ቀርተዋል...
የዛሬ ምንትስ ዓመት ወይም ወራት ነው መሰለኝ አንድ የሆነ ቤት ገብቼ ስለ ድሮ ቀደምት ዋርካዊያን እያነሳው በቁጭት ሳወራ አንዱ በንዴት አቦ ሼባዎች እየመጣችሁ ዋርካ ድሮ ቀረ ምናምን እያላችሁ አትነጅሱን ዋርካ ዛሬም አለች ይሄው እኛም እየኖርንባት ነው ብሎ ብሶቱን ፃፈ...
ድብልቅ ያለው ዕውነት ማለት ይሄ ነው ከምር... ሁሉም በዘመኑ ያሻዉን እያደረገ ይኖራል በዘመን ግስጋሴ ንፅፅርን እያመጡ የኖሩበትን ዘመን አውድሶ የቆሙበት መውቀሱ ቂልነት ነው ... ሁሌም 'ማምነው አንድ ነገር አለ ትላንትና ደብዛዛ ነው ነገም ጭላምጭል ነው ዛሬ ግን ስላለንበት ደማቅ ነው::
አሁን 'ስቲ የኔ ባዶ ቤት ገብቶ እንደዚህ ባቻ ማውራት ምን ይሉታል...?
እኔ 'ምለው ግን (ያ ልጅ እንዳይሰማኝ) ... የድሮ ዋርካዊያን አላችሁ...?
ጥበብ ከእኔ የበለጠ ጠንካራ ናት እኔ እንደምፈልገው ሳይሆን እሷ እንደፈለገችው ታደርገኛለች::