እንጨዋወት!

Topics related to cultures, arts, languages, arts such as humor, music, traditional literary genres of poems, ግጥም ፣ ቅኔ ፣ ተረትና ምሳሌ)

እንጨዋወት!

Postby መላጣ » Wed Jan 02, 2013 7:10 pm

ይህ ቤት ሁሉን አቀፍ የመዝናኛ የመሳቂያና የመፍለቅለቂያ እንዲሆን ታስቦ ሲከፈት ሳቂዎችና አሳቂዎች ወደ ቤቱ ጎራ በማለት ያላችሁን ግጥምም ሆነ ዘፈና ዘፈን ጣል በማድረግ የቤቱ ተጋሪ እንድትሆኑልኝ ከልብ በመጠየቅ የሳቀና ያሳቀ ከድሜው በሴኮንድም ቢሆን ከፍ ይላል የሚል ጥንት የኔታ የነገሩኝን በማስታወስ ነው:: ለዛሬው በዚህ ሙዚቃ ቤቱን ላሙቅና በቅርቡ እስክመለስ ሰላም እላለሁ::
http://www.diretube.com/mesfin-bekele/e ... 9bb2d.html
መላጣ
ዋና ኮትኳች
ዋና ኮትኳች
 
Posts: 606
Joined: Fri Feb 27, 2004 10:30 am

Postby መላጣ » Thu Jan 03, 2013 11:52 am

ባንድ ወቅት ወጣቱ ባር ይገባና እንዳጋጣሚ ካንዲት አሮጊት ጎን በመጠጋት አብረው መጠጣት ይጀምራሉ:: ወሬ እየቀጠለ ጨዋታ ይደራና አሮጊቷ 59 ዓመቷን እንደምታከብር እቤት ወጣትና ቆንጆ ልጅ እንዳለቻት ታበስረዋለች:: መጠጥ በመጠጥ ላይ እየተጨመረ ሲመጣ ወጣቱ አሮጊቷን በተመለከታት ቁጥር አማረችው ቆንጆ ሆና ታየችው ወደዳትም:: ከዚያም አሮጊት ለመሆኑ ከዚህ በፊት እናትና ልጅን አርገህ ታውቃለህ ወይ? ስትለው ወጣት ደንገጥ ብሎ ምን ማለትሽ ነው አልገባኝም ትነግሪኝ ሲላት ተወው ለማንኛው ታክሲ ይጠሩና ይዛው ወደ ቤቷ እንደደረሱ በሩን ከፈት አርጋ ""እማዬ እንደነቃሽ ነው""? ብላ ስትጣራ ወጣትሆይ በድንጋጤ ክው ብሎ ወደመጣበት ፈረጠጠ ይባላል:: ጉጉ መስሎት ወጣት የተገኘ :(

http://www.youtube.com/watch?v=y6sSxgbd75g
መላጣ
ዋና ኮትኳች
ዋና ኮትኳች
 
Posts: 606
Joined: Fri Feb 27, 2004 10:30 am

Postby ጌታ » Thu Jan 03, 2013 3:19 pm

ሰሞኑን ቲቪ ላይ የሰማሁትን ቀልድ ላካፍላቹ - ከሩሲያንኛ ወዳማርኛ ስተረጉመው ካልገባቹ ያለመሳቅ መብታቹ የተጠበቀ ነው::

ሰውየው አንዲት በግ አቅፎ እየሄደ አንዲት ኪካ ወደሱ አቅጣጫ ትመጣለች:: 'ድሮ የምቀመጭላት አሳማ ይቺውና' ብሎ ሲናገር ሴትዮዋ 'የያዝከው እኮ በግ እንጂ አሳማ አይደለም' ስትለው 'አንቺን ማናናገረሽ ከበጓ ጋር ነው የማወራው' አላት :lol: :lol: :lol:
ኢትዮጵያ እጆቿን ወደ እግዚአብሄር ትዘረጋለች!!!
ጌታ
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 3029
Joined: Sun Apr 17, 2005 5:35 pm
Location: ዶሮ ተራ

Postby እንሰት » Thu Jan 03, 2013 3:27 pm

ሩስኪዎች ዋዛ? ልዩ ናቸው በተለይ ቀልድ ፈጠራቸው ላይ:: እስኪ በነካ እጅህ ደገምገም አርገን


ጌታ wrote:ሰሞኑን ቲቪ ላይ የሰማሁትን ቀልድ ላካፍላቹ - ከሩሲያንኛ ወዳማርኛ ስተረጉመው ካልገባቹ ያለመሳቅ መብታቹ የተጠበቀ ነው::

ሰውየው አንዲት በግ አቅፎ እየሄደ አንዲት ኪካ ወደሱ አቅጣጫ ትመጣለች:: 'ድሮ የምቀመጭላት አሳማ ይቺውና' ብሎ ሲናገር ሴትዮዋ 'የያዝከው እኮ በግ እንጂ አሳማ አይደለም' ስትለው 'አንቺን ማናናገረሽ ከበጓ ጋር ነው የማወራው' አላት :lol: :lol: :lol:
እንሰት
ውሃ አጠጪ
ውሃ አጠጪ
 
Posts: 1213
Joined: Sun Jan 30, 2005 1:14 am
Location: united states

Postby ስራ ፈት » Fri Jan 04, 2013 6:22 pm

አሪፍ ነው ሳቅ የደስታ ምንጭ ነው አይደለ የሚባለው::

አንዷ ወመቴ ተኳኩላ ፌስ ቡክ ላይ እራሷን ገጭ አድርጋለች:: አንድ ቀን ከአንዱ ጋር ቻት ሲያደርጉ የት ነው ያለሽው ይላታል:: አሜሪካ ነኝ ትለዋለችና ብዙ ይጨዋወታሉ ሸበላው ጠበስኩኝ ብሎ በደስታ ሰክሯል::

ቀኖች አለፉ ወራቶች ተቆጠሩ አንድ ቀን ቆሎ ተራ የሚባል ሰፈር ይሄዳል (ካሜሪካን ግቢ ትንሽ ወረድ ብሎ ሱማሌ ተራ አካባቢ ነው):: አንድ የሆነ ከረንቦላ ቤት ሲገባ ይቺሁ አሜሪካ ነኝ ያለችው ወመቴ ከረንቡላዋን ስትከካ እጅ ከፈንጅ ይይዛታል::

አንቺ አሜሪካ ነኝ አላልሽኝም ነበር እንዴ :?: ብሎ ሸበላው ሲያፈጥባት እሷም 'አንተ ምን ልትሰራ ቬጋስ መጣህ' አለችው ይባላል
ስራ ፈት
ጀማሪ ኮትኳች
ጀማሪ ኮትኳች
 
Posts: 65
Joined: Mon Jan 17, 2005 8:37 pm

Postby መራራ » Mon Jan 07, 2013 10:50 am

:lol: :lol: :lol: :lol: :lol: :lol: ምን ልትሰራ ቬጋስ መጣህ? :lol: :lol: :lol: :lol:

ስራ ፈት wrote:አሪፍ ነው ሳቅ የደስታ ምንጭ ነው አይደለ የሚባለው::

አንዷ ወመቴ ተኳኩላ ፌስ ቡክ ላይ እራሷን ገጭ አድርጋለች:: አንድ ቀን ከአንዱ ጋር ቻት ሲያደርጉ የት ነው ያለሽው ይላታል:: አሜሪካ ነኝ ትለዋለችና ብዙ ይጨዋወታሉ ሸበላው ጠበስኩኝ ብሎ በደስታ ሰክሯል::

ቀኖች አለፉ ወራቶች ተቆጠሩ አንድ ቀን ቆሎ ተራ የሚባል ሰፈር ይሄዳል (ካሜሪካን ግቢ ትንሽ ወረድ ብሎ ሱማሌ ተራ አካባቢ ነው):: አንድ የሆነ ከረንቦላ ቤት ሲገባ ይቺሁ አሜሪካ ነኝ ያለችው ወመቴ ከረንቡላዋን ስትከካ እጅ ከፈንጅ ይይዛታል::

አንቺ አሜሪካ ነኝ አላልሽኝም ነበር እንዴ :?: ብሎ ሸበላው ሲያፈጥባት እሷም 'አንተ ምን ልትሰራ ቬጋስ መጣህ' አለችው ይባላል
መራራ
ዋና ኮትኳች
ዋና ኮትኳች
 
Posts: 753
Joined: Sat Sep 25, 2004 9:58 am
Location: united states

Postby መላጣ » Mon Jan 07, 2013 6:13 pm

ቬጋስ ያስቃል ጨመር ጨመርመር ነው ይለማምድብህ ወንድሜ :) :)

አንዲት ኮረዳ ቴክሳስ በርሀውን እያቋረጠች በመኪናዋ ስትበር ድንገት መኃል ላይ ነዳጅ ያልቅባትና ትቆማለች::
እንዳጋጣሚ አንድ ኢንድያን በፈረሱ እየጋለበ ወደ ኮረዳዋ በመጠጋት ወደ አቅራቢያው ቤንዚን ስቴሽን አፈናጡዋት እንዲያደርሳት ሲጠይቃት ተደስታ እሺ በማለት ከኃላው በመፈናጠጥ ወገቡ ላይ ተጠምጥማ መጋለብ ይጀምራል:: 5 ደቂቃ ያህል እንደተጓዙ ኢንዲያኑ እሪ እያለ እየጮኸ እንደማይደረስ የለ ላብ በላብ ሆኖ ስቴሽኑጋ አውርዷት በብስጭት እየጮኸ ሲጋልብ የተመለከተው የስቴሽኑ ሰራተኛ ለመሆኑ ምን ብታደርጊው ነው እንዲህ የጮኸው? ብሎ ኮረዳዋን ሲጠይቃት "እኔ ምንም አላደረኩትም ከኃላው ተፈናጥጬ ወገቡ ላይ በመጠምጠም እንዳልወድቅ በመፍራት የኮርቻውን መያዢያ ከማነቅ በቀር" ሲላት ስሚ እንጂ እንዲያኖች እኮ! ሲጋልቡ ኮርቻ እይጠቀሙም አላት ለካስ አጅሪት አንቶኒዎንን ልትነቅል ማለት ነበር: :lol:

መልካም የገና በዓልን እመኛለሁ::
http://www.youtube.com/watch?v=oFG7AnNjEYc
መላጣ
ዋና ኮትኳች
ዋና ኮትኳች
 
Posts: 606
Joined: Fri Feb 27, 2004 10:30 am

Postby መላጣ » Tue Jan 15, 2013 3:47 pm

አግኝቶ ከማጣት አጥቶ ማግኘት በጣም የተሻለ ነው::

አንድ በጣም ከበርቴ የነበረ ሰው ንብረቱን ሁሉ ያጣና በጣም ይቸገራል:: ቢጥር ቢለፋ ኑሮ አልሳካልህ ስላለው ከዚህ ዓለም መጥፋትን እንደምርጫ አርጎ በመውሰድ በአራት ነገር እራሱን ለመግደና ሊሰናበት ወሰነ::

አንደኛው ምርጫ የንቅልፍ መድኅኒት ኪኒኒ ከመጠን በላይ በመዋጥ: ሁለተኛው ምርጫው ደግሞ በገመድ መታነቅ ሦስተኛው በሽጉጥ ጭንቅላቱን አፍርሶ ለመሞት አራተኛውና የመጨረሻው በሐር ውስጥ ሰምጦ ለመሞት ናቸው:: እንዳስበውም አንድ ብልቃጥ ሙሉ የንቅልፍ መከላከያ ኪኒኖችን ይውጥና ገመድ በማዘጋጀት ወደ አንድ ትልቅ ድልድይ አካባቢ በመሄድ ገመዱን አንገቱ ያገባና ይንጠለጠላል: ወድያውኑ ከኪሱ ሽጉጡን አንስቶ ግንባሩን ለመምታት ሲተኩስ ይስትና ገመዱን ሲበጥሰው ከታች ያለው ባህር ውስጥ ይወድቃል: ለካስ ከድልድዩ ስር ያለው በሐር መሳይ ጉድ ከየአካባቢው የተጠራቀመ የሰገራ ፍሳሽ ቆሻሻ ስለነበረ ከመጠን በላይ ስለተጋተው ያቅለሸልሸዋል በማስታወክም ውጦት የነበረው ኪኒኒ በጠቅላላ ይወጣል: እንዳጋጣሚም በስፍራው የነበሩ ሰዎች ጎትተው በማውጣት ህይወቱን ሊያተርፉት ቻሉ ይባላል::

ይህ አባባል የሚያሳየው የሰው ልጅ ሟች ቢሆንም ቅሉ እሞታለሁ ስላለ ብቻ ወዲያውኑ ሟች አለመሆኑን ነው ምክንያቱም ከፈጣሪው የተቆረጠለትና የተቋጨለት ቀን ስላለ ያቺን ቀን ይጠብቃል እሷንም አያልፍም እንደማለት ነው::
መላጣ
ዋና ኮትኳች
ዋና ኮትኳች
 
Posts: 606
Joined: Fri Feb 27, 2004 10:30 am

Postby መላጣ » Thu Jan 17, 2013 11:35 am

አንዳንድ ሰዎች ሥራዬ ብለው የሚዋሹ አሉ አንዳንዶች ደግሞ ለማሳቅ ሲሉ የሆነና ያልሆነውን እየቀባጠሩ የሚዋሹ አሉ::

ያኔ ጥንት በመንደራችን በአስቂኝ ውሸታምነቱ የታወቀ ወጣት ነበር:: ይህ ወጣት ሊሴ ገብረማርያም የፈረንሣይ ተማሪ ሲሆን በተለይ ከትምህርት ቤት ሲወጣ የሚይዛቸው መጽሐፍቶች በጣም ወፋፍር ከመሆናቸውም በላይ ቁጥራቸው ከሦስት አራት የሚበልጡ ነበር:: የመንደር ልጆች ተሰብስበን ለምን ይህን ሁሉ መጽሐፍ ትሸከማለህ አይከብድህም ወይ? ስንለው የምማረው የትምህርት ዓይነት ብዙ ስለሆነ እንዲያውም የተቀሩትን ሁለት ሦስት አባቴ በመኪና ቤት ይዞልኝ ሄዷል ይላል:: ከዚያም ለጠቅ አርገን ለምን ካባትህ ጋር በመኪና ቤት አልሄድክም ስንለው? አንዲት ጥቁር አሜሪካዊት ገርል ፍሬንዴ አባቷ አምባሳደር ስለነበሩ ሥራ ጨርሰው ዛሬ ወደ አገራቸው ስለተመለሱ እሷን ለመሸኘት ቦሌ ኤርፖት ሄጄ ነው:: በጣም የምወዳት ነበር እዩ አይኔ አብጦ አትመለከቱም ያይሮፕላኑን መስኮት ዝቅ አርጋ "አይ ላቭ ዩ ነቨር ፎርጌት ዩ" ስትለኝ ያነባሁት እንባ ነው እያለ ይጠፍገን ነበር:: አስቡት ያይሮፕላን መስኮት ያውም ዝቅ አርጋ ካልዋሹ አይቀር እንዲህ ነው:: እኛ በዚያን ጊዜ ልጁን እንደመዝናኛችን እንቆጥረው ነበር:: ይቀጥላል...
መላጣ
ዋና ኮትኳች
ዋና ኮትኳች
 
Posts: 606
Joined: Fri Feb 27, 2004 10:30 am

Postby መላጣ » Fri Jan 18, 2013 2:35 pm

ወጣቱን ምክንያቱ ምን እንደሆነ ሳናውቀው "ፖምፒዱ" የሚል ቅጽል ስም ሰተነው ነበር:: የሰፈር ልጆች ሲደብረን ፖምፒዱ መጥቶ በጠፈገን እያልን እንመኝ ነበር::

የቀልድ እውሸት ያስቃል ክፋት የለውም ግን ትልቅ ሆኖ በውነቱ መዋሸት ያስጠላል:: በተለይ ደግሞ ስልጣንን መከታ አድርጎ መቀለድ አስነዋሪ ከመሆኑም በላይ ጎጂነት አለው::


ካንዱ ጓዋደኛዬ ጋር ይህን አርስት በተመለከተ ስንጨዋወት የቀድሞው ጠቅላይ ምኒስትራችን እውሸታም ናቸው እየተባለ ይወራል ለመሆኑ እውሸታም መሆናቸው እንዴት ይታወቃል? ብሎ ይጠይቀኛል:: ሳያውቅ ሳይሆን እያፌዘ መሆኑን ስለተረዳሁት "እሳቸውማ እውሸታቸው ከንፈራቸው በተንቀሳቀሰ ቁጥር" ብዬ ስመልስለት ሆዱን እስከሚያመው ድረስ ሳቀ:: እንድትስቅ ፈልገህ ነው አይደል? አልኩት አዎ አሁንም መሳቅ እፈልጋለሁ ለመሆኑ ያሁኑና ያለፈው ጠቅላይ ምኒስትራችን የሚለዩበት መንገድ አለ ወይ? ብሎ ነገረኛው ጓዴ ጠየቀኝ:: የሚለዩበት ሁኔታ ያኛው መላጣ ይሄኛው ባለጎፈሬ እንዲሁም ያኛው "እውነት ለምን እምነቴ" ይሄኛው "እምነት እውሸት እምነቴ! ከሚመስል በቀር ኮፒ መስለው ይታያሉ:: አሁንም ሳቀ ግን የምነት ጉዳይ ሲነሳ ፊቱ ሲለውጥ ታየኝ አሳሳቁ እንደመጀመሪያው ሳይሆን የተነካ ነገር ይመስል የፊቱ ስሮች እንደጅማት ሲወጠሩ ተመለከትኩ ሁኔታው ስላላማረኝ ብዙ ማውራት ባልፈልግም ቅሉ:: ይቀጥላል!
መላጣ
ዋና ኮትኳች
ዋና ኮትኳች
 
Posts: 606
Joined: Fri Feb 27, 2004 10:30 am

Postby መላጣ » Tue Mar 19, 2013 11:27 am

እምነት የምትለዋ ቋንቋ እንደተሰማች ሰውነቱ የተለዋወጠው ጓዴ የቁና ያህል ተንፍሶ "አሁንማ ተመስገን እንበል አምላክ ፊቱን ወደ ኢትዮጵያ አገራችን መልሷል ክርስቲያን መሪያችን አድርጎ ሾሞልናል" ብሎ እንድተናገረ ትኩር ብዬ ስመለከተው ለብዙ ጊዜ የማውቅው ጓዴ መስሎ አልታይ አለኝ::

በዚህ ጉዳይ ከሱ ጋር መነጋገሩ የሚፈይደው ቁም ነገር አለመኖሩን በመረዳት ግን ቀደም ሲል ስለ ጓዴ ይወራ የነበረውን ሀሜት አውጥቼ በማውረድ ሳብላላው ለካስ እውነት ኖሯል የሚል ግምት አሳደርኩ::

ጉዳዩ እንዲህ ነው (እንዲታወቅልኝ የምፈልገው የሰው ልጅ እምነት ኅይማኖቱን አከብራለሁ) ግን በሀሰት ላይ ተንተርሶ የሌላውን ኅይማኖት የሚነካ እቃወማለሁ:: ጓዴ ፈጣሪ ፊቱን ወደ አገራችን መልሶ ክሪስቲያን መሪ አድርጎልናል ሲል ምን ማለቱ ነው??? ይቀጥላል

ዓይምሮን ዘና እናርግ:---
http://www.youtube.com/watch?feature=fv ... NXNKs&NR=1
መላጣ
ዋና ኮትኳች
ዋና ኮትኳች
 
Posts: 606
Joined: Fri Feb 27, 2004 10:30 am

Postby መላጣ » Tue Mar 19, 2013 4:17 pm

ምናልባት ጓዴ የተገለፀለት የግዚአብሔር ፊቱን ማዞር ላገር ለኔ ግልጽ ያልሆነልኝ የመሪው እምነት ማንነት ይሆን እንዴ? ብዬም ጥርጥር ውስጥ ገባሁ:: ጓዴን ሳውቀው በተገናኘን ወቅት ወግ ስንጀምር ማወራረጃ የቢራ ጠርሙስ አንቀን እየተንጎራደድን ሞቅ ሞቅሞቅ ሲል ደግሞ ውስኪውን ስንጨልፍ ተወዳዳሪንት በሚያሳጣ መልኩ ሲሆን እንዴት ብዬ የሱን ኅይማኖት ልወቅ::

ቀስ በቀስ ለካስ የሚወራበትና የሚታማበት እውነተኛነቱ እየቀረበ መጣ:: ይህ ሰው አንተንና አንተን የመሰሉ ሲያገኝ እናንተን መስሎ ይቀርባል ግን በሌላው መንገድ ደግሞ ካማኞች ጋር ከጴንጤዎች ጋር ይጸልያል እንዲያውም ምስክርነት ሰጥቷል የሰጠውም የምስክርነት ቃል እጅግ በጣም የሚያሳዝንና የሚያዋርድ ታሪክ ባህልንና ኅይማኖትን የሚነካ የትውልድ ብልሹነትን የሚያመለክት ነው አሉ::

ምስክርነቱም እንዲህ ነው አሉ:- እየሱስ የተመሰገነ ይሁን አሜን! እኔ ዛሬ እፊታችሁ ቆሜ ይህን የምስክርነት ቃል እንድሰጥ ለመረጠኝ እየሱስ ምስጋና ይግባው አሜን! ኢትዮጵያ እያለሁ የደርግ በትር አስቃይቶ ህይወቴን ሊያጠፋት በተቃረበ ወቅት ለሊቱ ላይ በንቅልፍ ሰመመን እያለሁ የመስኮቴ በር ሲንኳኳ ተነስቼ ስከፍት ፊቱ በብርሀን የተሞላ አንድ አዛውንት ልጄ የጭንቅና የመከራህ ጊዜ ልትወገድ ነው አሁኑኑ የታቀደልህና የታሰበልህ ቦታ ስላለ ተከተለኝ ብሎ እጄን ይዞ ወደ ማላውቅበት አገር ይዞኝ ሄደ: በዚህን ወቅት አዳማጩ ሕዝብ በአሜንና በጭበጨባ አዳራሹ ይሞላል:: ለጠቅ አርጎም በደረስኩበት የጎረቤት አገር ያለምንም ችግር በዓለም አቀፉ የጥገኞች ማስተባበሪያ ውስጥ ታቅፌ ካለሁበት እድል አግኝቼ ይኸው ዛሬ ከናንተ ፊት እገኛለሁ:: ጭሆት ሆነ እልልታ የየሱስ ስም እየተደጋገመ 30ና 50 ጊዜ ተጠራ:: አሳሳቹ ጓዴ ለጠቅ አርጎም አባትና እናቴ አምስት ወንድም እህቶቼን እንዲሁም እኔን ጨምሮ ስምንት ነን ከነዚህ ሁሉ እየሱስን የማውቅና ክርስቲያን እኔ ብቻ ነኝ እነሱ አያውቁትም ሲል የመዝሙሩ የእልልታው የአሜኑ የዳንኪራው ኧረ! ምኑ ዓለም አለቀልሽ ነበር ትዕይንቱ:: ይቀጥላል:---

ላሳሳቹ ጓዴ የሚመጥን መዝሙር :lol:
http://www.youtube.com/watch?v=j6ou_oGdHx4
መላጣ
ዋና ኮትኳች
ዋና ኮትኳች
 
Posts: 606
Joined: Fri Feb 27, 2004 10:30 am

Postby መላጣ » Wed Mar 20, 2013 10:45 am

ምናልባት አሳሳቹ ጓዴ ከናት አባቱ ቀድሞ የተገኘው እሱ ሆኖ መስሎት ይሆን እንዴ ከቤተሰብ እኔ ብቻ ነኝ ጌታን የተቀበልኩና ክርስቲያን ነኝ ማለቱ? ያሳዝናል እያወቀ በ 40 ዓመቱ እንዲህ መቅለሉ::

ከናቱ መሐፀን እንደወጣ አባትና እናት በ 40ኛ ቀኑ በወግ ማዕረግ በኦርቶዶክስ እምነታቸው በመመራት ቤተክርስቲያን በመውሰድ አስጠምቀው ክርስትና አስነስተውታል:: ታዲያ የሱ ብቻ ክርስቲያንነት ከየት የመጣ ነው? እናት አባቱንስ የምን ዓይነት ኅይማኖት ተከታይ ሊያረጋቸው ነው ከቤታችን ውስጥ እኔ ብቻ ነኝ ክርስቲያን ያለው? አሳዛኝና አጓጉል ትውልድ ማለት ይህ ነው::

ኢትዮጵያችን በኅይማኖት ተከባብራ የኖረች አገር ስትሆን ክርስትናም ወደ አገራችን የገባው በ 4 ክፍለ ዘመን እንደሆነ ይነገራል:: በዚያው በተጠቀሰው ዘመን ብዙም ሳይቆይ ማለት ነው መጽሐፍ ቅዱስ በቀድሞው የኢትዮጵያ ቋንቋ ወደ ግዕዝ የተረጎመው:: ከዚያ በ 14 ኛው ክፍለ ዘመን ተሻሽሎ ተፃፈ:: የመጀመሪያውና ሙሉ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ ደግሞ በ 1832-1833 ዓ.ም እንደተተሮገመ ታሪክ ይነግራል:: ታዲያ ይህን የመሰለና ጠንካራ እምነት ይዘው ለልጅ ልጆቻቸው ያሳለፉትንና የሚያሳልፉትን እናት አባቶችን ኅይማኖት ለማሳጣት የተነሳው አጓጉሉ ጓዴ ወደ እሱነቱ እንዲመለስ ጥሪ አቀርባለሁ::

እንዲሁም በውነትነት ላይ የተረጋገጠ የእውሸት እምነት ተሸክመህ ፈጣሪ ፊቱን ወደኛ መለሰ መሪያችን ብለህ አትመጻደቅ:: ምክንያቱም የእግዚአብሔር ፍቅር የተሞላበት ፍቅርን ይጋብዛል እንጂ ህብረተሰብን አይጎዳም:: ህዝቡ እየተፈናቀለ እየተራበ ያላግባብ እየታሰረና እየተገደለ እየተሰወረ እየተሰደደ እያለ ወንበር ላይ ቁጭ ያለው አማኙ መሪህ ከሞቱት በላይ ካሉት በታች የተጎለተ ግንብ ነው እልኃለሁ::
እስቲ ለማንኛውም የክርትና አመጣጣችንና የኦርቶዶክስ እምነታችንን በመጠኑ የሚያሳይ ክሊፕ ላሳይህና ከላይ እንዳልኩህ ወዳንተነትህ ቢመልስህ:: መልካም ቀን!
http://www.youtube.com/watch?v=NJfbtupc ... 17&index=1
መላጣ
ዋና ኮትኳች
ዋና ኮትኳች
 
Posts: 606
Joined: Fri Feb 27, 2004 10:30 am

Postby መላጣ » Fri Apr 19, 2013 11:22 am

ሰውዬው አልጋ ላይ ጋደም ብሎ መጽሐፍ እያነበበ እያለ ሚስት ከጎኑ መጥታ ጉንጩን ሳም አድርጋ እሷም አረፍ ትላለች:: ከዚያም ባልየው ቀስ ብሎ እጁን ወደ ታፋዋ በመስደድ ብልቷን ማሸት ሲጀምር ፍቅርዬ ማረግ ትፈልጋለህ እንዴ? ስትለው አይ አልፈልግም የመጽሐፉን ገጽ ለመግለጥ እንዲያመቸኝ ጣቴን ለማርጠብ ፈልጌ ነው አላትና አረፈው:: አቤት አቤት ጉድ ነው አይደል???
http://www.diretube.com/yegna/abet-ft-h ... b810b.html
መላጣ
ዋና ኮትኳች
ዋና ኮትኳች
 
Posts: 606
Joined: Fri Feb 27, 2004 10:30 am

Postby መላጣ » Tue Apr 30, 2013 12:01 pm

መቀሌ ውስጥ ነው ሁለት የወያኔ ካድሬዎች በልማት ተወጥረው አንደኛው ጉርጓድ ሲቆፍር አንደኛው ጉርጓዱን ሲደፍን ቀኑን ሙሉ ላብ በላብ ተጨማልቀው የተመለከተ አንድ ያካባቢው ሰው ወደ ካድሬዎቹ ጠጋ ብሎ ለመሆኑ ምን እያረጋችሁ ነው? ብሎ ሲጠይቃቸው አይ አባባ ሦስት ነበርን ችግኙን የሚተክለው ዛሬ ታሞ ስለቀረ ነው ብለውት እርፍ:- ይቺ ናት ልማት ሃ ሃ ሃ.. :lol:
http://www.youtube.com/watch?v=JTtIi4IAZrk
መላጣ
ዋና ኮትኳች
ዋና ኮትኳች
 
Posts: 606
Joined: Fri Feb 27, 2004 10:30 am

Next

Return to Warka Culture and Literature - ዋርካ ባህልና ሥነ ጽሑፍ

Who is online

Users browsing this forum: No registered users and 4 guests