by ShyBoy » Sat Jan 19, 2013 7:04 pm
ዘጌው ከባድ ሰው: እንዴት ነህሳ? አንተም የአሜሪካን ፉትቦል ታያለህ እንዴ? እኔ ድሮ ድሮ በጣም ነበር የሚደብረኝ.......ህጉን እና ስትራቴጂውን ሳላውቅ:: አሁን አሁን ከሶከር በበለጠ እየሳበኝ መቷል:: ቻርጀርስ በጣም የምወደው ክለብ ነበር: ከአምና ጀምሮ ሾቀ እንጅ:: ሁለተኛ ቡድኔ ሬቨንስ ለክፉ አይሰጡም:: ከማልወዳቸው ቡድኖች አንዱ የሆነውን ፓትሪየትስ አሽንፈው ለሱፐር ቦውል እንደሚደርሱ ተስፋ አለኝ........አምና በማይረባ ስህተት ወደቁ እንጅ ማሸነፍ ይችሉ ነበር::
ምንም እንኳን ከባድ ቢሆንም: ሬቨንስ ከ 49ነርስ ደርሰው ሬይ ልዊስ የመጨልሻ ጨዋታውን በድል ያጠናቅቃል ብየ ተስፋ አደርጋለሁ (እንደ ዚዙ አይነት አጋጣሚ እንዳይደርስበት እንጅ)::
ድል ለ ሬቨንስ!