መጽሀፍ ቅዱስን እንመርምረው !!

Issues and Articles of General Interests including topics related to religion

መጽሀፍ ቅዱስን እንመርምረው !!

Postby መርፊው » Wed Apr 03, 2013 5:17 pm

እኔም አንድ ጥያቄ አለኝ መፅሀፍ ቅዱስ አዋቂዎች እንዲመልሱልኝ ምፈልገው
ኦሪት ዘፀአት
ምእራፍ 20 : 13
አትግደል
ከአስርቱ ትእዛዛት አንዱ ነው እንግዲህ
አንድ ገፅ ገለጥ ስታረጉ ደግሞ
ምእራፍ 21
ግደል ነው
ለመጥቀስ ያህል
12፤ ሰው ሰውን ቢመታ ቢሞትም፥ እርሱ ፈጽሞ ይገደል።
15፤ አባቱን ወይም እናቱን የሚመታ ፈጽሞ ይገደል።
16፤ ሰውን ሰርቆ ቢሸጥ፥ ወይም በእጁ ቢገኝ፥ እርሱ ፈጽሞ ይገደል።
17፤ አባቱን ወይም እናቱን የሚሰድብ ፈጽሞ ይገደል።
23፤ ጕዳት ግን ቢያገኛት ሕይወት በሕይወት፥
24፤ ዓይን በዓይን፥ ጥርስ በጥርስ፥ እጅ በእጅ፥
29፤ በሬው ግን አስቀድሞ ተዋጊ ቢሆን፥ ሰዎችም ለባለቤቱ ቢመሰክሩለት ባይጠብቀውም፥ ወንድንም ወይም ሴትን ቢገድል፥ በሬው ይወገር፥ ባለቤቱ ደግሞ ይገደል።
19፤ ከእንስሳ ጋር የሚረክስ ፈጽሞ ይገደል።
ኦሪት ዘጸአት 12 :12-13
12፤ እኔም በዚያች ሌሊት በግብፅ አገር አልፋለሁ፥ በግብፅም አገር ከሰው እስከ እንስሳ ድረስ በኵርን ሁሉ እገድላለሁ፤ በግብፅም አማልክት ሁሉ ላይ እፈርድባቸዋለሁ፤ እኔ እግዚአብሔር ነኝ።

ይህ የሰው ቃል ነው ወይስ የዲያቢሎስ :: መልስ ?


ኦሪት ዘዳግም ምእራፍ 23 ቁ 1-2

ምዕራፍ 23።
1፤ ቍላው የተቀጠቀጠ ብልቱም የተቈረጠ ወደ እግዚአብሔር ጉባኤ አይግባ።


2፤ ዲቃላ ወደ እግዚአብሔር ጉባኤ አይግባ፤ እስከ አሥር ትውልድ ድረስ ወደ እግዚአብሔር ጉባኤ አይግባ።

ይሄን ምን ትሉታላቹህ አንድ አካሉ አደጋ ስለደረሰበት ሰውየው አጠገቤ ድርሽ እንዳይል የሚል አምላክ ?!

Can Bible really be from God ????

You would know better

Please share this with all
.
.
FOLLOWING ARE SOME BIBLICAL VERSES:

Kill those who are not Christian or Jewish:

You must kill those who worship another god. Exodus 22:20

Kill any friends or family that worship a god that is different than your own. Deuteronomy 13:6-10

Kill all the inhabitants of any city where you find people that worship differently than you. Deuteronomy 13:12-16

Kill everyone who has religious views that are different than your own. Deuteronomy 17:2-7

Kill anyone who refuses to listen to a priest. Deuteronomy 17:12-13

Kill any false prophets. Deuteronomy 18:20

Any city that doesn’t receive the followers of Jesus will be destroyed in a manner even more savage than that of Sodom and Gomorrah. Mark 6:11

Jude reminds us that God destroys those who don’t believe in him. Jude 5

Ignorance is bliss. Christians should not practice free inquiry nor socialize with non Christians:

Don’t associate with non-Christians. Don’t receive them into your house or even exchange greeting with them. 2 John 1:10

Shun those who disagree with your religious views. Romans 16:17
መርፊው
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 260
Joined: Sat Oct 15, 2011 4:22 pm

Re: መጽሀፍ ቅዱስን እንመርምረው !!

Postby ጎነጠ » Thu Apr 04, 2013 11:00 pm

መርፊው wrote:እኔም አንድ ጥያቄ አለኝ መፅሀፍ ቅዱስ አዋቂዎች እንዲመልሱልኝ ምፈልገው
ኦሪት ዘፀአት
ምእራፍ 20 : 13
አትግደል
ከአስርቱ ትእዛዛት አንዱ ነው እንግዲህ
አንድ ገፅ ገለጥ ስታረጉ ደግሞ
ምእራፍ 21
ግደል ነው
ለመጥቀስ ያህል
12፤ ሰው ሰውን ቢመታ ቢሞትም፥ እርሱ ፈጽሞ ይገደል።
15፤ አባቱን ወይም እናቱን የሚመታ ፈጽሞ ይገደል።
16፤ ሰውን ሰርቆ ቢሸጥ፥ ወይም በእጁ ቢገኝ፥ እርሱ ፈጽሞ ይገደል።
17፤ አባቱን ወይም እናቱን የሚሰድብ ፈጽሞ ይገደል።
23፤ ጕዳት ግን ቢያገኛት ሕይወት በሕይወት፥
24፤ ዓይን በዓይን፥ ጥርስ በጥርስ፥ እጅ በእጅ፥
29፤ በሬው ግን አስቀድሞ ተዋጊ ቢሆን፥ ሰዎችም ለባለቤቱ ቢመሰክሩለት ባይጠብቀውም፥ ወንድንም ወይም ሴትን ቢገድል፥ በሬው ይወገር፥ ባለቤቱ ደግሞ ይገደል።
19፤ ከእንስሳ ጋር የሚረክስ ፈጽሞ ይገደል።
ኦሪት ዘጸአት 12 :12-13
12፤ እኔም በዚያች ሌሊት በግብፅ አገር አልፋለሁ፥ በግብፅም አገር ከሰው እስከ እንስሳ ድረስ በኵርን ሁሉ እገድላለሁ፤ በግብፅም አማልክት ሁሉ ላይ እፈርድባቸዋለሁ፤ እኔ እግዚአብሔር ነኝ።

ይህ የሰው ቃል ነው ወይስ የዲያቢሎስ :: መልስ ?


ኦሪት ዘዳግም ምእራፍ 23 ቁ 1-2

ምዕራፍ 23።
1፤ ቍላው የተቀጠቀጠ ብልቱም የተቈረጠ ወደ እግዚአብሔር ጉባኤ አይግባ።


2፤ ዲቃላ ወደ እግዚአብሔር ጉባኤ አይግባ፤ እስከ አሥር ትውልድ ድረስ ወደ እግዚአብሔር ጉባኤ አይግባ።

ይሄን ምን ትሉታላቹህ አንድ አካሉ አደጋ ስለደረሰበትሰውየው አጠገቤ ድርሽ እንዳይል የሚል አምላክ ?!

Can Bible really be from God ????

You would know better

Please share this with all
.
.
FOLLOWING ARE SOME BIBLICAL VERSES:

Kill those who are not Christian or Jewish:

You must kill those who worship another god. Exodus 22:20

Kill any friends or family that worship a god that is different than your own. Deuteronomy 13:6-10

Kill all the inhabitants of any city where you find people that worship differently than you. Deuteronomy 13:12-16

Kill everyone who has religious views that are different than your own. Deuteronomy 17:2-7

Kill anyone who refuses to listen to a priest. Deuteronomy 17:12-13

Kill any false prophets. Deuteronomy 18:20

Any city that doesn’t receive the followers of Jesus will be destroyed in a manner even more savage than that of Sodom and Gomorrah. Mark 6:11

Jude reminds us that God destroys those who don’t believe in him. Jude 5

Ignorance is bliss. Christians should not practice free inquiry nor socialize with non Christians:

Don’t associate with non-Christians. Don’t receive them into your house or even exchange greeting with them. 2 John 1:10

Shun those who disagree with your religious views. Romans 16:17

አይ መርፈው መች ይሆን ከጅል ስራ የምትወጣው መልስ ስጥ ተባልክ እንጅ ጥያቄ ገልብጥ ተባልክ እንዴ
ይኅውልህ ሙሄ አባትህ ከብሉኪዳን ያገኘውን ህግ ግልብጦ ጅብሪል ሰጠኝ እያለ ይቀባጥር ነበር ታዲያ ሙሄ የተሽወደው ዘመነ ፍዳና ዘመን ምህረትን አለማስተዋሉ ነው
ወንድሜ አሁንም ከዘመነ ፍዳ አልወጣም የምትል ከሆነ ምርጫው ያንተ ነው ያው ሙሄን የዋጠው ዲያብሎስ አንተንም ሳይደግምህ ነቅተህ ቁራንህን በደምብ አስተውለህ አንብ ከዚያም ምን ያህል በጨለማ እንዳለህ ታስተውላለህ ለቤተሰቦችህም ትተርፍስለህ
ለጥያቄወችህ መልስ ለማግኝት www.alfadytv.com
ግባና ገመናህን ሁሉ ታገኛለህ ቸር ሰንብት
I love ethiopia
ጎነጠ
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 103
Joined: Wed Aug 03, 2005 9:07 am
Location: ethiopia

Postby መርፊው » Fri Apr 05, 2013 4:48 pm

አያ ጎንጤ ጎንጣቸው በመጀመሪያ ደረጃ አንተ እዚህ የመጣሄው
ጥያቄ ጠይቀህ ለመማር ሳይሆን የሰውን ሀይማኖት ለመሳደብና
ለማንጓጠጥ ስለሆነ ላንተ መልስ የሚሰጥ ስራ ፈትየለም ምክንያቱም
አንተን የለከፈ ሰይጣን እየሱስህን የተፈታተነው ስይጣን መሆኑ
ን ደርሰንበታል በተጨማሪ ደግሞ የምናስተምርህ ነገር የሚከተለው ይሆናል አንተ የሰውን ሀይማኖት ከምትዘልፍና ባን
ተ ሰበብ ሀይማኖትህን ከምታዘልፍ ለምን የራስህን እምነት ጠበ
ቅ አድርገህ አትይዚም አንተ በግልህ ስለ ማታምንበት ሀይማኖት ምን አግብቶህ ትዘላብዳለህ የሌሎችን ሀይማኖት
ለሌሎች ተውላቸ :idea: :idea: :idea:

ደግሞ የገረመኝ የጥያቄውን መልስ አድበስብሰህ ማለፍህ ነው ?

ጥያቄው መመለስ ካቃትው አልውቅም ማለት በራሱ አዋቂነት
ነው ግን አንተ እየሱስህን የለከፈው ስይጣን ውስጥህ ስላለ
አይምሮህ በትክክል አይሰራም .: ልክፍታሙ እየሱስ እንኳን
እኔ የመጣሁት ህግ ልሽር ሳይሆን ህግ ላስተምር ነው እያለ
አንተ ግን አራምባና ቆቦ ትናገራለህ ::
መርፊው ዘ_ነገደ የሁዳ
መርፊው
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 260
Joined: Sat Oct 15, 2011 4:22 pm

Re: መጽሀፍ ቅዱስን እንመርምረው !!

Postby ነጻዋ » Sun Apr 07, 2013 3:34 am

ሰላም መርፌው
ጥያቄዎችህ ሞራላዊ እረፍት ለማግኘት የከመፈለግ መነጩ ከሆነ አጋርህ ነኝ:: በጥቅሉ እኔም እንዳንተው አዕምሮዬ አስተውሎት ሕሊናዬ መዝኖት ሊቀበላቸው የማይችላቸው በርካታ ትምህርቶች መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ በብዛት አይቻለሁኝ:: ፍጹም ሞራላዊ ነው ከሚባል ፈጣሪ በደካማው የዘመኑ ሰው ጭንቅላት እንኳን ሲታሰብ የሚዘገንን ትምህርት ሊመነጭ ይችላል ብሎ እንዴት ማሰብ እንደሚቻል በጣም ግራ ይገባኛል:: እንዳልከው አንድ ሰው አካሉ ስለጎደለ አይጠጋኝ የሚል ፈጣሪ....አንድ ፍጥሩ ያለእርሱ ፍቃድና ምርጫ ከጋብቻ ውጪ ስለተወለደ ብቻ አይጠጋኝ የሚል ፈጣሪ....ነጻ ፍቃድ ሰጥቻለሁኝ እያለ ግን እኔን የማያምኑት ይገደሉ የሚል ፈጣሪ (ለዛውም ነፍስ የማያውቁ እና ምርጫ የሌላቸውን ሕጻናትን ጨመሮ)...አይሁድን ብቻ ለይቶ የተቀረውን የሰው ዘር እንደ እቃ ለባርነት እንዲሸጥና እንዲለወጥ የሚፈቅድ ፈጣሪ....አንዱ በሰራው ሀይጢያት ዘር ማንዘር ትውልዱ የእዳ ወራሽ እንዲሆን የሚፈቅድ ፈጣሪ....ሴቶች ምንም ቢያውቁና ቢልቁ.. በአደባባይ ትንፍሽ እንዳይሉ የሚከለክል ፈጣሪ...ወዘተ..ባጭሩ በብልዩም ሆነ በአዲስ ተዘርዝሮ የማያልቅ ማንም በነጻ አዕምሮ ከመዘነው ሞራላዊና ፍትሀዊ ነው ብሎ ሊቀበለው የማይችለው ትምህርቶችን አያለሁኝ::

የሚገርምህ ግን ታዲያ እነዚህን ጥያቄ ስታነሳ ስብዕናህን መንካት, መዝለፍና መስደብ እንጂ ነጥብ በነጥብ የሚመልስልህ በምናባዊዋ ዋርካ አይደለም ከእምነት መሪዎችም ማግኘት ከባድ ነው (የግል ተመክሮዬ እስካሁን ያሳየኝ ይሄንን ነው::)!! የማይሰድቡህ ካገኘህ ትንሽ መንገድ ይሄዱ እና ከዛ ወይ ከጥያቄህ ውጪ አዕምሯቸው ውስጥ ያለውን እንደመፈክር ይደግሙልሀል ወይ አንተ የጠየከውን ሳይመልሱ ሌላ ትክክል ነገር ፈልገው ያመጡልሀል!! ስለጳውሎስ ስትጠይቅ ወንጌልን አንብብ ይሉሀል:: አንዴ የመጻህፍ ቅዱስ ጸሀፊዎች በፈጣሪ መንፈስ ተመርተው የእርሱን ፍቃዳ ነው ያስተማሩት ይሉህና.... የማያፈናፍን ኢሞራላዊ ትምህርት ሲያጋጥማቸው... አይ ይሄ የፈጣሪ ፍቃድ ሳይሆን እነ ሙሴ ለዘመኑ ህዝብ የጻፉት ትዕዛዝ ነው ይሉሀል!! አንዴ የፈጣሪ ፍቃድ ዘላለማዊ እና ሁሌም የማይቀየር ነው ይሉሁና... ከዛ ደግሞ አይ ይሄ ትምህርት በብልዩ ቀርቷል ይሉሀል:: አንዴ ኮንትኬስቱን አልተረዳህም ይሉሁና ምንም በማያወላዳ መልኩ ስታስቀምጥላቸው ደግሞ 'ይሄ የፈጣሪ ፍቃድ ነው..በቃ ሴት ትለጎም..ባሪያም ይገዛ...ቆራጣውም ከጉባዬ ይራቅ" ይሉሀል!..እንደዚህም ቢሆን የምመክርህ አዕምሮህ ሁሌ ሀሳብህን ሊያስቀይር ለሚችል መልስ ክፍት ይሁን ብዬ ነው:: በነጻነት የማሰብ ጸጋ እንዳይለይህ እመኛለሁኝ!
ነጻዋ
ጀማሪ ኮትኳች
ጀማሪ ኮትኳች
 
Posts: 52
Joined: Sat Nov 20, 2010 4:35 am

Postby ears » Sun Apr 07, 2013 10:41 pm

ነጻዋ መርፌው ከክርስቲያኖች ጦር ተማዟል የሱ አላማ እንኳን ክርስትናን ለመጎሸም ነው እንጂ ለማወቅ ሲባል በቅንነት የቀረበ ጥያቄ አይደለም ::

እንዳንቺ አልዋጥልህ ያሉኝ የመጽሀፍቅዱስ ጥቅሶች

1. "እኔ ቀናተኛ አምላክ ነኝ" .......ቅናት ለሰውልጅ ሀጢአት ሆኖ እንዴት አምላክ ይቀናል ?

2. ላለው ይሰጠዋል ከሌለው ይወሰድበታል...............እንዴት የድሆች አምላክ ከድሀ ወስዶ ላለው ይሰጣል ?


እነዚህ ሁለቱ አልዋጥ ብለውኛል
ears
አዲስ
አዲስ
 
Posts: 11
Joined: Sun Apr 07, 2013 10:10 pm

Postby ጎነጠ » Mon Apr 08, 2013 1:59 pm

ለመርፌው ,ነፃውears ያላመነ ያልተጠመቀ አይድንም የሚለውንስ አይታችሁት ይሆን
" ይህንን በመጀመሪያ እወቁ በመጽሀፍ ያለው ትንቢት ሁሉ በገዛ እራሱ ሊተረጉም አልተፈቀደም ትንቢት ከቶ ከሰው ፈቃድ አልመጣምና ዳሩ ግን ዳሩ ቅዱሳን ሰወች ከእግዚአብሄር ተልከው በመንፈስ ቅዱስ ተቃኝተው ተናገሩ "
ይላል ታዲያ ታዲያ እናንተ እንዲህ የሚል አምላክ እንዲህ አይነት አምላክ እያላችሁ. የምትተረጉሙት በየትኛው መንፈስ ተመርታችሁ ይህን ትርጉም ልትሰጡ ቻላችሁ
ነገሩ የትርጉማችሁ ትርጉም ይመሰክራል ከቀድሞው አባታችሁ ከዲብሎስ መሆኑን
[/img]
I love ethiopia
ጎነጠ
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 103
Joined: Wed Aug 03, 2005 9:07 am
Location: ethiopia

Postby ነጻዋ » Mon Apr 08, 2013 4:29 pm

ሠላም ears
መርፌው የሚባለው ሰውዬ ከዚህ በፊት የጻፋቸውን አላየኍቸውም ነበር:: በጣም አስጸያፊ የሆኑ ነገሮችን ስለእየሱስ የጻፈውን አንድ ጽሑፍ አሁን በአጋጣሚ አይቼ ዓላማው አንተ እንዳልከው ሞራላዊ እውነትን ፍለጋ እንዳልሆነ ተገንዝቤያለሁኝ:: ለእርማቱ አመሰግናለሁኝ::

ሠላም ጎነጠ
ማመን ሲባል እኮ ብዙ አይነት ማመኖች አሉ:: በማስተዋል ያልሆነ ማመን ደግሞ በጭፍን ወደ መነዳት ያመራል:: በማመን ስም ባርነትን ግዞትን ዲስክሪሚኔሽንን ጭምር ተቀበዪ ስትለኝ እምነትህን ባከብርልህም ለእኔ ግን ሕሊናዬ ሊቀበልልኝ አይችልም:: ስለዚህ እነዚህ ኢሞራልዊ ትምህርቶችን እንዴት መቀበል ይቻላል ለሚለው ጥያቄ ወይ መልስ ማምጣት ግድ ይላል::
ነጻዋ
ጀማሪ ኮትኳች
ጀማሪ ኮትኳች
 
Posts: 52
Joined: Sat Nov 20, 2010 4:35 am

Postby መርፊው » Mon Apr 08, 2013 4:48 pm

ears እኔ ከማንም ጦር አልተማዘዝኩም ተማዝዤም አላው

ቅም እኔ እዚህ ያለሁት አንዳንድ የራሳቸውን ሀይማኖት ጠንቅቀው ሳያውቁ የሰውን እምነት ለሚተነኩሱ ተልካሻ ፍጡራን ትምህርት ልሰጥ ነው ::እንዴት አንተ የሰው እምነት እየሰደብክ ትምህርት ሰጣለህ ብለህ ከጠየከኝ
መልሴ አንድና አንድ ነው እሱም የስውን ህይማኖትና እምነት የሚያንጓጥ የሱም ሀይማኖት እንደሚነካ ማወቅ
አለበት አለበለዚያ በስነስረአትና በመከባበር መማማር ሲቻል የኔ እምነት ከሌላ እምነት በላጭ ነው በሚል ጥንፈኝነት በመነሳሳት የባጥ የቆጡን እየለቀለቁ ቢውሉ ትርፉ እራስ ማስገመትና ወደ ዝቅጠት መውረድ ይሆናል ::
መርፊው ዘ _ ነገደ የሁዳ ከእየሩሳሌም

ears wrote:ነጻዋ መርፌው ከክርስቲያኖች ጦር ተማዟል የሱ አላማ እንኳን ክርስትናን ለመጎሸም ነው እንጂ ለማወቅ ሲባል በቅንነት የቀረበ ጥያቄ አይደለም ::

እንዳንቺ አልዋጥልህ ያሉኝ የመጽሀፍቅዱስ ጥቅሶች

1. "እኔ ቀናተኛ አምላክ ነኝ" .......ቅናት ለሰውልጅ ሀጢአት ሆኖ እንዴት አምላክ ይቀናል ?

2. ላለው ይሰጠዋል ከሌለው ይወሰድበታል...............እንዴት የድሆች አምላክ ከድሀ ወስዶ ላለው ይሰጣል ?


እነዚህ ሁለቱ አልዋጥ ብለውኛል
መርፊው
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 260
Joined: Sat Oct 15, 2011 4:22 pm

Postby መርፊው » Sun Apr 21, 2013 1:01 am

ኢየሱስ ከሰራቸው ሀጥያቶች ውስጥ ነጥረው የወጡትን እንመለከታለን(ለዚህ ፅሁፍ ሁለቱን ብቻ ለማየት እንገደዳለን)!

1. ስድብ
<<ስድብ? ይህ ነው ታድያ ትልቁ ወንጀል?›› የሚል ጥያቄ መነሳቱ አይቀርም፤ አግባብም ነው፡፡ አዎን! በመጽሃፍ ቅዱስ መሰረት ስድብ እጅግ በጣም ከባድ ከሚባሉት ወንጀሎች ውስጥ ይካተታል!
‹‹ ለቀደሙት አትግደል እንደተባለ ሰምታችኋል፤ የገደለም ሁሉ ፍርድ ይገባዋል፡፡ እኔ ግን እላችኋለሁ፤ በወንድሙ ላይ የሚቆጣ ሁሉ ፍርድ ይገባዋል፤ ወንድሙንም ጨርቅ ለባሽ የሚለው ሁሉ የሸንጎ ፍርድ ይገባዋል፤ ደንቆሮ የሚለውም ሁሉ የገሃነም እሳት ፍርድ ይገባዋል…››(ማቴ 5፤21-23)

ሆኖም ኢየሱስ በማቴዎስ ወንጌል ብቻ በደርዘን ለሚቆጠሩ ግዜያት ይህንን ህግ በጠራራ ፀሀይ መተላለፉ ተዘግቧል፡፡ ለአብነት ያክል የተወሰኑት እንመልከት፡፡

ሀ. ትውልዱን በሙሉ(እሱና ብጽእቱን እናቱን ጨምሮ) በመዝለፍ
‹‹ ክፉና አመንዝራ ትውልድ..›› (ማቴ 12፤38…)
‹‹ እናንተ የማታምን ጠማማ ትውልድ..›› (ሉቃ 9፤41)
ለ. ጻፎችንና ፈሪሳውያንን በመነጠል
‹‹እናንተ ግብዞች..›› (ማቴ 23፤13 23፤16 23፤23 23፤25 23፤27 23፤29...)
‹‹እናንተ ደንቆሮዎችና ዕውሮች…›› (ማቴ 23፤17 23፤19)
‹‹ እናንተ እባቦች፤ የእፉኝ ልጆች..›› (ማቴ 23፤33)
ሐ. ግለሰቦችን በመነጠል
‹‹ አንተ እውር ፈሪሳዊ.. ›› (ማቴ 23፤26)
‹‹ ጴጥሮስን፡- ወደ ኋላዬ ሂድ አንተ ሰይጣን፤ የሰውን እንጂ የእግዚአብሄርን አታስብምና እንቅፋት ሆነህብኛል..›› (ማቴ 16፤23)

ከላይ በሰፈሩት ጥቅሶች መሰረት፤ ኢየሱስ ከባድ ወንጀል መፈፀሙን እንረዳለን፤ ያውም ገሀነም ሊያስገባ የሚያስችል፡፡ ታድያ ይህ ድግስ ተደግሶ፤ እንዴት ኢየሱስን ከሃጥያት ነፃ ነው ልንል እንችላለን? መልሱን ለአንባቢያን እተዋለሁ፡፡ ነገር ግን ክርስትያን ወንድሞች ይህንን እንቆቅልሽ (puzzle) ለመፍታት የተለያዩ ማምለጫዎችን ለማቅረብ ሞክረዋል፤ እስኪ አንድ በአንድ እንመልከታቸው፡፡

A. ስድብ የተከለከለው ‹‹ለሃይማኖት ወንድም›› እንጂ ለሌላውማ ምን ችግር አለው፡

የማቴዎስ ወንጌል ላይ ‹‹ ለቀደሙት አትግደል እንደተባለ ሰምታችኋል፤ የገደለም ሁሉ ፍርድ ይገባዋል፡፡ እኔ ግን እላችኋለሁ፤ በወንድሙ ላይ የሚቆጣ ሁሉ ፍርድ ይገባዋል፤ ወንድሙንም ጨርቅ ለባሽ የሚለው ሁሉ የሸንጎ ፍርድ ይገባዋል፤ ደንቆሮ የሚለውም ሁሉ የገሃነም እሳት ፍርድ ይገባዋል…›› የሚለውን ጥቅስ እናያለን፡፡ ኢየሱስ በዚህ ጥቅስ መሰረት መግደልንም፤ መሳደብንም በማያሻማ ቋንቋ ከልክሏል፡፡ የሃይማኖት ወንድምን ብቻ ነው የከለከለው የምንል ከሆነ፤ ሌሎች ፈርጀ ብዙ ህግጋት መናዱ አይቀሬ ነው የሚሆነው፡፡ ‹‹በመጀመርያ ደረጃ አትግደል የተባለው ማንን ነው?›› ለሚለው ጥያቄ መልስ ሊበጅለት የግድ ነው፡፡ ‹‹ለቀደሙት አትግደል›› የተባለው የኦሪት ህግ ማንን ነው የሚመለከተው? ለአማኞት ብቻ ነው ብለን መልስ በመስጠት ለጊዜው ለማምለጥ እንችል ይሆናል፤ ነገር ግን ሌላ መዘዝ ይዞብን ከተፍ ይላል፡፡ ይህ ህግ በአዲስ ኪዳን መቀጠሉን ከላይ በጠቀስነው አንቀፅ ላይ ተመልክተናል፡፡ በመሆኑም እንደ ክርስትና እምነት መሰረት ‹‹አትግደል›› የሚለው ህግ ለአማኞች ብቻ የተገደበ ነው እንድንል ያስገድደናል፡፡ ከዚህም አልፎ ተርፎ በየመንገዱ የምታገኘውን የሌላ እምነት ተከታይ መስደብም ይፈቀዳል እንደማለት ነው፡፡

ስለዚህ ለክርስትያን ወንድሞቻችን ሁለት ምርጫ ቀርቧል ማለት ነው፡፡ አንደኛው፤ አማኝ ያልሆነን መግደልም ሆነ መስደብ ይቻላል፤ በመሆኑም ኢየሱስ በመሳደቡ ወንጀል አልሰራም፡፡ ሁለተኛው ደግሞ የሌላ እምነት ተከታይን መግደልም ሆነ መስደብ አይፈቀድም፤ ነገር ግን ኢየሱስ ይህንን ህግ ጥሷል፡፡ ምርጫውን እንተውላቸዋለን፡፡ ደግሞም ለሃይማኖት ወንድም ነው ለማለት በቂ መረጃ ማቅረብ ግዴታ ነው፡፡ ሌላውም ወሳኝ ነጥብ ኢየሱስ ሁሉንም ሰው መስደቡን ማሰተዋል ልብ ይሏል፤ትውልዱን በሙሉ፣ አማኙንም ኢ-አማኙንም፡፡ (ማቴ 12፤38…) (ማቴ 16፤23)

B. ኢየሱስ እየተሳደበ ሳይሆን፤ እነርሱ የሆኑትን ነው እየነገራቸው ያለው፡፡ ያልሆኑትን ነገር ፈጥሮ አልተናገረም፡፡

ይሄ ብዙ የማያራምድ ምላሽ ነው፡፡በዋናነት መመለስ ያለብን ጥያቄ ‹‹ስድብ ምን ማለት ነው›› የሚለውን ይሆናል፡፡ ለምሳሌ ያክል አንድ መላጣን ‹‹አንተ መላጣ(ቢሊጮ)›› ብንለው ስድብ አይደለምን? ብዙ የማይገባውንም ሰው ‹‹አንተ ደንቆሮ›› ብንለውስ? ይህ ስድብ ካልሆነ የስድብ ትርጉም ተለወጠ ቢሉን ይቀላቸዋል፡፡ ሌላው ደግሞ ‹‹እናንተ ግብዞች፤ እባቦች›› እያለ ኢየሱስ ሲዘልፋቸው፤ መቼም እንስሳውን እባብ እንዳልሆነ ማስተዋል ይቻላል፡፡ ባህሪያችሁ ከእባብ ይመሳሰላል፤ መርዘኞች ናችሁ እንደማለቱ ነው፡፡ ታድያ ይሄን ስድብ እንበለው ምክር?

ሌላው ነጥብ ኢየሱስ ጴጥሮስን የተናገረው ንግግር ነው፡፡‹‹ ..ወደ ኋላዬ ሂድ አንተ ሰይጣን፤ የሰውን እንጂ የእግዚአብሄርን አታስብምና እንቅፋት ሆነህብኛል..››(ማቴ 16፤23) ሰይጣን??? ታላቁን ደቀመዝሙር ሰይጣን እያለው መቼም ይህንንም እንደማናስተባብለው ምኞቴ ነው፡፡ ነገር ግን ምኞቴ ምኞት ሆኖ ቀረና ማስተባበሉን ተያይዘውታል፡፡ ‹‹ኢየሱስ እኮ ጴጥሮስን ሳይሆን እንዲህ ያለው በውስጡ መጥፎ የሚያናግረውን ሰይጣንን ነው..›› ጉድ በሉ!!! መጥፎ ሲሰራ ያየነውን ሰው በሙሉ ‹‹አንተ ሰይጣን›› እያልን መዝለፍ ይቻላል እያሉን ነው፡፡ ከዛም ‹‹ለምን ተሳደባችሁ›› ብንባል ውስጡ ያለውን ሰይጣን እንጂ ሰውዬውን አይደለም ማለት ያቻላልም እያሉን ነው፡፡ ‹‹ጉድ ሳይሰማ…!›› እኔን መውጫ ይጥፋኝ እንጂ ሌላ ምን እንላለን!!

C. ይሳደባ፤ መብቱ ነው፡፡ እሱ ከህግ በላይ ነው፤ እርሱን በህግ መነፅር አንዳኘውም!

ስለ ሃቅ ከተነጋገርን፤ ይህ መልስ ከሁሉም የተሻለ እና ቅንነት የተላበሰ (honest) ምላሽ ነው! ሊጨበጨብላቸው ይገባል! ብራቮ! ይሄ ሁላ ከሚያሽከረክሩን መጀመርያውኑ እንዲህ ቢሉን የተሻለ ነበር፤ ስራችንንም ያቀልልን ነበር፡፡ መልሳቸው ‹‹ኢየሱስ ሃጢያተኛ ቢሆንም እንኳን፤ ከህግ በላይ በመሆኑ እንደ ስህተት አይቆጠርበትም›› የሚል መልዕክት ያዘለ ነው፡፡ እኛም ጥያቄ እናቅርብ፡፡ ታድያ ኢየሱስ ሃጢያት ያልነካው ነው ስትሉን ምን ማለታችሁ ነው? አግባብ የሆነስ ድንፋታ ነውን? በአንድ በኩል ነው፤ በሌላ በኩል አይደለም እያሉ መሄድስ ይቻላልን? በፍፁም! ስለሆነም ኢየሱስ ከሃጢያት ንፁህ ነው የሚለው ቀረርቶ ወንዝ ስለማያሻግር ሊቆም ይገባዋል ብለን እንመክራለን!

አንዳንዶችም ኢየሱስን ንፁህ ለማለት የጲላጦስን ‹‹ከሀጢያት አንድ እንኳን አላየሁበትም›› የሚለውን የምስክርነት ቃል በመውሰድ እንደመረጃነት ሲጠቀሙበት ይታያል፡፡ የምስክር ሰጪውን ማንነት ፤ የተናገረበትን ሙሉ አውድ እንዲሁም ሌሎች መረጃዎችን በማቅረብ ዕራቆቱን ማስቀረት ይቻላል! እንዲሁም ከላይ የዘረዘርኳቸው ማብራርያዎች ላይ ተመርኩዘን ብንመለከተው፤ ግጭት ፈጥሯል ማለትንም ያስይዛል፡፡ ‹‹ሃጢያት›› የሚለው አገባብ ከሌሎች መፅሃፍ ቅዱሳዊ አስተምህሮቶች አንጻርም የሚገመገም ይሆናል!
መርፊው
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 260
Joined: Sat Oct 15, 2011 4:22 pm

Postby መርፊው » Sun Apr 21, 2013 8:57 am

የሴቶች መብት በክርስትና……አንዳንዶች የሴትና የወንድን እኩልነት ለላመቀበል ‹‹ሴት›› የሚለው ስያሜ በራሱ የድክመት ምልክት አድርገው ይወስዱታል፡፡ ድክመትና ፍርሃት ያለበትን ሰው ይህን የድክመት ምልክት ለመግለጽ ወንድ ቢሆን እንኳ ‹‹ሴት›› በማለት ሲገልጹ ይስታዋላል፡፡ መጽሐፍ ‹‹ቅዱስን›› ስንመለከት ይህኑኑ የሚደግፍ ይመስላል፡፡ በሚገባ ይደግፋል እንጂ! ይህንን ስል ከኪሴ አምጥቼ እንዳይመስላችሁ እራሱ መጽሐፍ ‹‹ቅዱስ›› በተለያዩ ምዕራፎች የተለያዩ ወገኖችን ድክመትና ፍርሃት በሴት መስሏቸዋል ለአብነት እነሆ፡-
‹‹በዚያ ቀን ግብጻውያን ‹‹እንደ ሴት ይሆናሉ›› የሰራዊት ጌታ እግዚአብሔር በእነርሱ ላይ ነሳው ክንዱ የተነሳ በፍርሃት ይንቀጠቀጣሉ፡፡››(ትንቢተ ኢሳያስ 19፡16)

በሌላ ቦታ ላይም እንዲህ የሚል እናነባለን፡-
‹‹ሰይፍ በፈረሰኞቹና በሰረገሎች ላይ በመካከሏ ባሉት ባዕዳን ወታደሮች ላይ መጣ ! ‹‹እነርሱም እንደሴቶች ይሆና›› ሰይፍ በሀብት በንብረት ላይ መጣ! ለለዝርፊያም ይሆናሉ፡፡››(ትንቢተ ኤርሚያስ 500፡37)

‹‹እነሆ ጭፍሮችሽ ‹‹ሁሉም ሴቶች›› ናቸው! የምድርህ በሮች ለጠላቶችህ ወለል ብለው ተከፍተዋል፤ መዝጊያዎቻቸውንም እሳት በልቶአቸዋል፡፡››(ትንቢተ ናሆም 3፡13)

‹‹የባቢሎን ጦረኞች መዋጋ ትተዋል፤ በምሽጋቸው ውስጥ ተቀምጠዋል፤ ኋይሎቻቸው ተሟጧል፤ ‹‹እንደ ሴት ሆነዋል››፡፡›› ( ትንቢተ ኤርሚያስ 51፡30)
የክርስታን ጸሐፊው መምህር ኪዳነ ማርያም ‹‹ሴት የሚለው የድክመት ምልክት ነውን?›› ለሚለው ንዑስ ክፍል እንዲህ ሲሉ የጻፉት ይገኝበታል፡- ‹‹አዎ የድክመት ምልክት ነው፡፡ ወንድና ሴት በተፈጥሮ እኩል ይሁኑ እንጂ በኃይልና በጉልበት እኩል አይደሉም ወንድ ከሴት ይበልጣል፡፡››(መምህር ኪዳነማርያም ጌታሁን ወርቁ ቢጠፋ ሚዛኑ ጠፋ ፤ ገጽ 67)
መርፊው
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 260
Joined: Sat Oct 15, 2011 4:22 pm

Postby መርፊው » Sun Apr 21, 2013 1:00 pm

የጠቢቡ ሰሎሞን ልቅ ጋብቻ!በመጽሀፍ ቅዱስ

መፅሃፍ ቅዱስ ከአንድ በላይ ስለማግባት(polygamous marriage) ምን አይነት ምልከታ እንዳለው እንመልከት፡፡ ርዕሱ ሰፊ ከመሆኑ አንፃር ለዛሬ ጠቢቡ ሰሎሞን እጅግ በርካታ ሚስቶች እንደነበሩት፤ እግዚአብሄርም ይህንን እንደተቀበለው በመጨረሻም እግዚአብሄር ሰሎሞንን ያወገዘው ከአንድ በላይ በማግባቱ ነው ወይስ የአህዛብ ሴቶችን ማግባቱ? ለሚለው ጥያቄ መረጃ ላይ በመመርኮዝ መልስ ይሰጥበታል(ኢንሻአላህ)፤ መልካም ንባብ ይሁንልዎ!
መፅሃፍ ቅዱስ ስለ ሰሎሞን ሚሰቶች ብዛት ሲገልፅ፡-
‹‹ለእርሱም ወይዛዘር የሆኑ ሰባት መቶ ሚሰቶች፤ ሶስት መቶም ቁባቶች ነበሩት…›› (2)
ይህን ጋብቻ ጊነስ ቡክ ኦፍ ሪከርድስ መመዝገብ አለበት እንደማትሉኝ ነው፡፡ ጠቢብ ተብሎ የሚወደሰው ሰሎሞን አንድ ከተማ የሚሞሉ ሴቶችን በሚስትነት እና በዕቁባትነት መያዙን መፅሀፉ ይነግረናል፡፡ ታድያ ክርስትያን ወንድሞች፤ ይህ ታላቅ ሰው ይህንን ያህል ሚሰቶችን ማግባቱ ከተፈቀደለት፤ ታድያ እንዴት ከአንድ በላይ ማግባትን ኢ-አምላካዊ ፍቃድ አድርጋችሁ ልትቆጥሩት ቻላችሁ? ለዚህ ጥያቄ ማምለጫ አንዳንዶች መጪውን ጥቅስ በመረጃነት በማቅረብ ‹‹እግዚአብሄር እኮ ሰሎሞንን ከአንድ በላይ ማግባቱን ተቃውሞታል›› ሊሉን ይወዳሉ፡፡
‹‹ሰሎሞንም በእግዚአብሄር ፊት ክፉን ነገር አደረገ፤ እንደ አባቱም እንደ ዳዊት እግዚአብሄርን በመከተል ፍፁም አልሆነም›› (3)
እኛም ጥያቄ እንጠይቃ! ሰሎሞን በእግዚአብሄር ፊት ያደረገው ክፉ ነገር ምንድነው? ከአንድ በላይ ማግባቱ ወይስ ጣዖታውያን አምላኪ የሆኑ አህዛቦችን ማግባቱ? መፅሀፍ ቅዱሰ ይናገር!
‹‹ ንጉሱም ሰሎሞን ከፈርዖን ልጅ ሌላ፤ በሞዓባውያንና በአሞናውያን በኤዶማውያንም በሲዶናውያንና በኬጢያውያን ሴቶች፤ በብዙ እንግዶች ሴቶች ፍቅር ተነደፈ፡፡ እግዚአብሄር የእስራዔልን ልጆች፤ አምላኮቻቸውን ትከተሉ ዘንድ ልባችሁን በእውነት ያዘነብላሉና ወደ እነርሱ አትግቡ፤ እነርሱም ወደ አንተ አይግቡ ካላቸው ከአህዛብ፤ ከእነዚህ ጋር በፍቅር ተጣበቀ..›› (4)
‹‹ሰሎሞንም ሲሸመግል ሚስቶቹ ሌሎችን አማልክት ይከተል ዘንድ ልቡን አዘነበሉት›› (5)
‹‹በዚያን ግዜ ሰሎሞን ለሞዓብ ርኩሰት ለካሞሽ፣ ለአሞንም ልጆች ርኩሰት ለሞሎክ በኢየሩሳሌም ፊተ ለፊት ባለው ተራራ ላይ መስገጃ ሰራ፡፡ ለአማልክቶቻቸው ዕጣን ለሚያጥኑ፤ መስዋዕትንም ለሚሰዉ ለእንግዶች ሚስቶች ሁሉ እንዲህ አደረገ..፡፡›› (6)
በኦሪት ህግ መሰረት እስራዔላውያን ወደ አህዛብ እንዳይገቡ ታዘው ነበር (ዘዳ 7፡3) ፡፡ ነገር ግን ሰሎሞን አሻፈረኝ አለ፡፡ በዚህም ምክንያት እግዚአብሄር ተቆጣበት፤ የሰራው ስራም ክፉ መሆኑ ታወጀ፡፡ ጥቅሶቹም ያስተላለፉት መልእክት ይህንኑ ነው፡፡ በየትኛውም አቅጣጫ ብንመለከት እነዚህ ጥቅሶች ከአንድ በላይ ማግባቱን መቃወምን አያስይዙም፤ በጭራሽ! እንደውም አህዛቦችን ማግባት ብቻ ነጥሎ በመቃወም ከአንድ በላይ ማግባቱን ሳይቃወም ማለፉ ለመፈቀዱ ሌላ መረጃ ነው፡፡ ሌላው ወሳኝ ነጥብ ዳዊትስ ቢሆንስ መች አንድ ሚስት ብቻ ነበረው?
‹‹ዳዊትም በኬብሮን ከመጣ በኋላ ሌሎቹን ቁባቶቹንን ሚሰቶቹን ከኢየሩሳሌም ወሰደ፣ ለዳዊትም ደግሞ ወንዶችና ሴቶች ልጆች ወለዱለት›› (7)
ዳዊት ‹‹እግዚአብሄርን በመከተል ፍፁም›› (8) ተብሎ የተቆለጳጰሰው ከአንድ በላይ ማግባቱ እየታወቀ መሆኑን ማስተዋል ልብ ይሏል! ዳዊት ተወደሰ፤ ሰሎሞን ተነቀፈ፡፡ ለምን? የኦሪትን ህግ በመጣሱ፤ አራት ነጥብ!
‹‹ (ከአህዛብ ጋር) አትጋባ፤ ሴት ልጅህን ለወንድ ልጁ አትስጥ፤ ሴት ልጁንም ለወንድ ልጅህ አትውሰድ›› (9)
‹‹በመፅሀፍ ቅዱስ አንድ ሺህ ሚሰቶችን ማግባት ተፈቅዷል፤ ታድያ የእናንተ ሃይማኖት ለምን ገደብ አበጀለት›› ብላችሁ እንደማታለቅሱ ተስፋ አደርጋለሁ፡፡
መርፊው
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 260
Joined: Sat Oct 15, 2011 4:22 pm

Postby መርፊው » Wed Apr 24, 2013 5:43 pm

የመፅሀፍ ቅዱስ ይዘትና ክፍሎች(ክፍል ሶስት)
ከሀ.ታ. መፅሃፍ የተወሰደ

በአመራረጥ ሂደት ላይ የታየ ማጭበርበር

በእርግጥ አጠቃላይ ሂደቱ በማጭበርበርና በሸፍጥ የተሞላ ነበር፡፡ ቶላንድ የተሰኘው ምእራባዊ ምሁር እንዲህ ሲል ጽፏል፡-
‹በቤተክርስትያን ውጥን ታሪክ ውስጥ ምን ያህል ማጭበርበርና ዝንፈት እንደተካሄደ የሚታወቅ ነው፡፡ መጽሐፍትን መበረዝና እውነትን ያላዘሉ መጽሐፍትን ማቅረብ ተስተውሏል፡፡ ይህ እኩይ ሥራ ቀሳውስት ጥሩም ይሁን መጥፎ የማንኛውም መጽሐፍት ጠባቂዎች በሆኑበት ወቅት ይበልጥ ተባብሶ ቀጥሏል፡፡ በሂደቱም የክርስትናን ታሪክ ከአፈ-ታሪክ፣ እውነትን ከሐሰት መለየት በማይቻልበት ደረጃ ላይ ተደርሷል፡፡› (1)

የታሪክ ተመራማሪው አዶልፍ ሐርናክ እንዲህ ሲሉ ጽፈዋል፡-
«በአራተኛው ክፍለ ዘመን የነበረው ወንጌል የግሪክ ፍልስፍናን ጭንብል ያጠለቀ ነበር፡፡ ጭንብሉን ከእውነተኛውና ወጥ ከሆነው (የእየሱስ) ትምህርት አንጥሮ ማውጣት የታሪክ ምሁራን ተልእኮ ነው፡፡» (2)
ይሁንና ይህን ማድረግ ምን ያህል አስቸጋሪና ፈታኝ ተግባር መሆኑን ሄርኖክ ሳይጠቅስ አላለፈም፡፡

የአዳዲስ መረጃዎች መገኘት

የእየሱስ ደቀመዝሙር የነበረው ሐዋርያው ባርናባስ አዘጋጀው የተባለው ወንጌል መገኘቱ፣ የሙት ባህር ጥቅሎች (The dead sea scrolls) እና ሌሎችም መረጃዎች የምእራባዊ ምሁራንን ቀልብ መሳባቸው አልቀረም፡፡ እናም ስለ እየሱስ ማንነትም ሆነ ስለ እውነተኛ ትምህርቱ አስደናቂ መረጃዎች መገኘት ቀጥለዋል፡፡ ከነዚህ መረጃዎች በመነሳት የታሪክ ምሁራን ስለ እየሱስ ማንነት የወንጌል ጸሐፍት ካቀረቧቸው የተለዩ መረጃዎችን እያገኙ ነው፡፡
The Guardian በሰኞ July 6,2009 እትሙ World’s Oldest bible goes online በሚል ርእስ ከየትኛውም መጽሐፍ ‹ቅዱስ› የቀደመ የተባለለትን ጥንታዊ መጽሐፍ ‹ቅዱስ› አስተዋውቆናል፡፡ እድሜው 1600 ዓመታት ሲሆን ይዘቱ አሁን በክርስትናያኖች እጅ ከሚገኙት መጽሐፍ ቅዱሶች በከፊል ይለያል፡፡

የሐሰት ትምህርቱ ይቀጥላል

7) ይህም ሆኖ ግን አብያተ ክርስትያናት በአፈታሪክ ላይ የተመሰረተ የሐሰት ትምህርታቸውን ከማስተማር ውጭ ሌላ አማራጭ እንደሌላቸው የታሪክ ተመራማሪው ጆሐነስ ሌህማን ይናገራሉ፡፡ ምክንያቱም እውነቱን ቢናገሩ የክርስትና ግብአተ መሬት ይሆናልና፡፡ የተመራማሪውን ቃል እነሆ፡-

‹የወንጌል ጸሐፍት ያቀረቡት ኢየሱስና የታሪክ ምሁራን የሚያምኑበት ኢየሱስ ማንነትና ገጽታ ገሃድ ቢወጣ ኢየሱስ በአሁኑ ወቅት በሰዎች የተደፋለትን የአምላክነት ዘውድ የሚቀበል ሆኖ አናገኘውም፡፡ ግና ይህ ኢን.ኤ. ዳህል እንዳሉት የሚያስከትለው ሃይማኖታዊ አደጋ ብቻ ሳይሆን የክርስትና እምነትን የመጨረሻ ውድቀት (ክስመት) ነው፡፡ ቢሆንም እኛ የሥነ-መለኮት ሊቃውንት የምንለው አናጣም- ከቶውንስ መፍትሔና መውጫ ቀዳዳ ያጣንበት ጊዜ ኖሮ ያውቃልን? ነገር ግን ዛሬ እየዋሸን እንዳለን ሁሉ ነገም እንዲሁ ሐሰት መናገራችን አይቀርም፡፡› (3)

ከላይ የሰፈሩ ኑዛዜዎችን የተናገሩት ለክርስትና ቀናኢ የሆኑ የአውሮፓ ምሁራን መሆናቸውን ልብ ይሏል፡፡


የወንጌላት መበረዝ

8) እጅግ አጠራጣሪና የተድበሰበሰ በሆነ መልኩ የተመረጡ ወንጌላት ባሉበት ሁኔታ ቢቀጥሉ መልካም ነበር፡፡ ግና ከዘመን ዘመን የሰው እጅ ሲገባባቸው፣ ሲበረዙና ሲከለሱ ኖረዋል፡፡ ምእራባዊ የታሪክ ምንጮች የሚሉትን እንስማ፡፡
In The Gosples on the other hand, the characteristic variation are Intentional, Such as the addition or Insertion of whole Passages, some of which must certainly have been supplied From an external source.
‹በአንጸሩ ወንጌላትን በተመለከተ ሆነ ተብሎ ወሳኝ ለውጦች ተደርገውባቸዋል፡፡ ለምሳሌ ሙሉ አረፍተ ነገር እና ሐሳብ መጨመር ይጠቀሳል፡፡ ከጭማሬዎቹ መሐል ከፊሎቹ ያለ ጥርጥር ከሌላ ምንጭ የተገኙ ናቸው፡፡› (4)... ይቀጥላል
መርፊው
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 260
Joined: Sat Oct 15, 2011 4:22 pm

Postby የጃማ ጦስኝ » Fri May 03, 2013 12:00 pm

መጽሐፍ ቅዱስን መመርመር ደስ ይላል:: እግዚአብሔር ይባርካችሁ:: መልካም ትንሳኤ
ይችንም የእግዚአብሔር ምስጋና በዛው አዳምጡልኝ::


http://youtu.be/WTMZyphw4YM
በቅንነት ፈራጅ ሕዝብ እንዳይጐዳ:
ማን ይሆን ትልቅ ሰው ሃቅን የተረዳ :?:

Image
http://www.cyberethiopia.com/warka5/vie ... hp?t=26693
የጃማ ጦስኝ
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 338
Joined: Sun Sep 02, 2007 12:02 am
Location: ጃማ

Postby መርፊው » Sun May 05, 2013 11:18 pm

በመጀመሪያዎቹ የክርስትና ሁለት ክፍለ ዘመናት የክርስትና እምነት ተከታይ ነን ባዮች እመነታቸውን ለማፅናት በማሰብ ብቻ መፅሀፍ ይፅፉ ነበር፡፡ በስማቸው መፅሀፉን ቢፅፉት አንድም ሚሰማቸው ስለማያገኙ ሁለትም ከባድ ውግዘት ስለሚገጥማቸው እንዲሁም በታሪክም የሰው መሳቂያ እና መሳለቂያ የመሆን አደገኛ እጣ ስለሚያደርሳቸው መፅሀፉን ፅፈው ሲያበቁ በእየሱስ ደቀ መዝሙር እንደተፃፈ አክለው ይፅፉና ተቀባይነት ይኖረው ዘንድ በየቦታው ያሰራጩ ነበር ፡፡ ይህም የሆነበት ዋና ምክንያት በጊዜው የተለያዩ የእየሱስ ታሪኮች እንዲሁም እየሱስ አስተማራቸው የተባሉ አስተምህሮቶች ብዙሀኑ አንዱ ካንዱ እየተቀበለ በማህበረሰቡ ዘንድ ሲያሽከረክራቸው ስለነበረና እያንዳንዱ የክርስትና አንጃ እምነቱን ተቀባይነት ይኖረው ዘንድ እልህ አስጨራሽ ፉክክር ላይ ስለነበረ ነው፡፡ እናም በጊዜው የነበሩ ሰዎች መፅሀፍ ፍብረካን እንደ አንድ ስራ በመያዝ መፅሀፍ መፈብረክ ስራቸው አድረው ያዙት፡፡ በእየሱስ ደቀ መዝሙር ተፃፈ ሲሉም የእምባሻ ስም በመስጠት በየቦታው ማስተጋባት እንዲሁም ማሰራጨት ጀመሩ፡፡ ይህ " እኔ ከማን አንሼ" በሚል ብሂል የተስፋፋው መፅሀፍ ፍብረካ--- የክርስትና ዋና አስተምሮ---- ላይ ከባድ ተፅኖ አደረሰ፡፡ ማንነታቸው በማይታወቁ ሰዎች የተፈበረኩ ፅሁፎች ከፊሉ ውድቅ ሲደረግ ከፊሉ መለኮታዊ እንደሆነ በጭብጨባ ፀደቀ ፡፡ የሆነ ሆኖ በአዲስ ኪዳን የሚገኙ ብዙ ፅሁፎች የተፈበረኩ መሆናቸውን ከ ከአንዳንድ ኢቫንጄሊስቶች በስተቀር ምሁራን በአንድ ድምፅ ይስማሙበታል፡፡፡ እውነት እውነት እልሀለው ማንነቱ በማይታወቅ ፀሀፊ የተፈበረኩትን ፅሁፎችን ነው እንግዲህ ዛሬ መለኮታዊ ነው ሲል ምታምንበት! ከምሁራን እና እድሚያቸውን እንደኔ ለዚህ መስክ ከሰዉ አንዳንድ ሰዎች በስተቀር ስለዚህ ጉዳይ ብዙሀኑ አያውቅም እንዲያውቅም አይፈለግም፡፡ ግን ለምን? አዎ ለምን ?
መርፊው
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 260
Joined: Sat Oct 15, 2011 4:22 pm

Postby መርፊው » Tue May 07, 2013 6:33 pm

ክርስቲያን ሰባኪዎች ሌትተቀን የሚነግሩን በዘመን አዲስ ኪዳን ሴቶች ነፃ እንደወጡ ነው፡፡ ግና በተጨባጭ ነፃ ወጥተዋልን ህይወታቸውስ ከዘመነ ብሉይ ተሻሽሏልን? በቀላሉ የሚከተሉት ጥቅሶች ይህን "ምኞት" ውድቅ ያደርጋሉ፡-

1፡-ነገር ግን የወንድ ሁሉ ራስ ክርስቶስ፥ የሴትም ራስ ወንድ፥ የክርስቶስም ራስ እግዚአብሔር እንደ ሆነ ልታውቁ እወዳለሁ። (1ኛ ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች 11፡3)

2፡-1ኛ ቆሮንጦስ 14፡34 ላይ እንዲህ ይላል«ሴቶች በማህበር ዝም ይበሉ ህግ ደግሞ እንደሚል እንዲገዙ እንጂ እንዲናገሩ አልተፈቀደላቸውምና፡፡ ለሴት በማህበር መካከል መናገር ነውር ነውና ምንም ሊማሩ ቢዱወዱ በቤታቸው ባሎቻቸውን ይጠይቁ፡፡»ይላል

3፡-ሴት ግን በዝግታ ትኑር እንጂ ልታስተምር ወይም በወንድ ላይ ልትሰለጥን አልፈቅድም። (1ኛ ወደ ጢሞቴዎስ 2፡12

4፡-ሚስትም ከባልዋ አትለያይ፥ ብትለያይ ግን ሳታገባ ትኑር ወይም ከባልዋ ትታረቅ፥፡፡(1ኛ ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች 7፡10-11)

5፡-ራስዋን ሳትሸፍን ግን የምትጸልይ ወይም ትንቢት የምትናገር ሴት ሁሉ ራስዋን ታዋርዳለች፤ እንደ ተላጨች ያህል አንድ ነውና። (1ኛ ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች 11፡5)

6፡-ሚስቶች ሆይ፥ ለጌታ እንደምትገዙ ለባሎቻችሁ ተገዙ፤ (ወደ ኤፌሶን ሰዎች 5፡22

7፡-ሚስቶች ሆይ፥ በጌታ እንደሚገባ ለባሎቻችሁ ተገዙ። (ወደ ቆላስይስ ሰዎች 3:18)

8፡-ሴት ግን በዝግታ ትኑር እንጂ ልታስተምር ወይም በወንድ ላይ ልትሰለጥን አልፈቅድም። አዳም ቀድሞ ተፈጥሮአልና፥ በኋላም ሔዋን ተፈጠረች። (1ኛ ወደ ጢሞቴዎ11፡12)

9፡-የተታለለም አዳም አይደለም፥ ሴቲቱ ግን ተታልላ በመተላለፍ ወደቀች፤
ነገር ግን በእምነትና በፍቅር በቅድስናም ራሳቸውን እየገዙ ቢኖሩ በመውለድ ትድናለች። (1ኛ ወደ ጢሞቴዎስ 2፡14-15)

10፡-ወንድ የእግዚአብሔር ምሳሌና ክብር ስለ ሆነ ራሱን መከናነብ አይገባውም፤ ሴት ግን የወንድ ክብር ናት። ሴት ከወንድ ናት እንጂ ወንድ ከሴት አይደለምና። ሴት ስለ ወንድ ተፈጠረች እንጂ ወንድ ስለ ሴት አልተፈጠረምና። ስለዚህ ሴት ከመላእክት የተነሣ በራስዋ ሥልጣን ሊኖራት ይገባል። (1ኛ ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች 11፡7-10)
መርፊው
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 260
Joined: Sat Oct 15, 2011 4:22 pm

Next

Return to Warka General

Who is online

Users browsing this forum: Google [Bot] and 0 guests