ዳግማዊ አፄ ምኒሊክ(፲፰፻፴፮‐፲፱፻፮)(፲፰፻፹፩—፲፱፻፮)

Current political, socio-economic and human rights issues.

Moderators: ዘበኛ ፩, ዘበኛ ፫, ዘበኛ ፪, ዘበኛ ፬

ዳግማዊ አፄ ምኒሊክ(፲፰፻፴፮‐፲፱፻፮)(፲፰፻፹፩—፲፱፻፮)

Postby ዘርዐይ ደረስ » Thu Oct 06, 2011 7:03 pm

ሰላም ለሁላችሁም እያልኩ:-

ትላንት ስለ አፄ ምኒሊክ አንድ ፅሑፍ ፖስት አድርጌ ዛሬ ተጨማሪ ለመፃፍ ሳስብ ለካ የፃፍኩበት ቤት ተሰርዟል::ልፋቴ ቢያሳዝነኝም ለወደፊቱ በየትኛው ርእስ ሥር መፃፍ እንዳለብኝ ትምህርት ሰጥቶኛል::

ያም ሆነ ይህ ስለ እኚህ የኢትዮጵያ ኩራት የምንወያይበት ክፍል መክፈቱ የተሻለ ስለመሠለኝ አስተያየት መስጠት የምትፈልጉ በሥነ ሥርዓት እንድታደርጉት ምክርም ማሳሰቢያም አቀርባለሁ::

ለመጀመር ያህል ትላንት የፃፍኩትን እሳቸው ለኢትዮጵያና ለሕዝቧ ባበረከቱት አስተዋፅዖ እጀምራለሁ::

1)በዘመናቸው በዓለም ላይ ከሚታወቁት የሳይንስና ቴክኖሎጂ ውጤቶች መካከል ለኢትዮጵያ ይጠቅማል ያሉትን ወደ አገራችን በማስገባታቸው::

2)ለዘመናት ከትውልድ ወደ ትውልድ ሲተላለፉ የኖሩትን ኋላ ቀር አስተሳሰቦችና ልማዶች በተቻለ መጠን እንዲወገዱ በማድረጋቸው::

3)በወቅቱ የነበረውን የኃይማኖት ጭቅጭቅና ግጭት እንደ አፄ ቴዎድሮስና አፄ ዮሐንስ 4ኛ በኃይል ሳይሆን የተለያዩ ዘዴዎችን በመጠቀም ለመፍታት መሞከራቸው::

4) ኢትዮጵያን አንድ ለማድረግ በሚጥሩበት ወቅት የሚገጥማቸውን ተቃውሞ ግድ ካልሆነ በቀር ኃይል አለመጠቀማቸው::

5)የተለያዩትን የኢትዮጵያ ነገሥታትና የጎሳ መሪዎች በሚያስገብሩበት ወቅት ብዙ ጊዜ የአካባቢውን ሰዎች መሾማቸው::

6)ባለሥልጣኖቻቸውን ሲሾሙ ከዘር ሐረጋቸው ይልቅ በችሎታቸውና ለአገራቸው ባላቸው አመለካከት እንዲሆን ማድረጋቸው::

7)በመጀመርያ ደረጃ ሊጠቀስ የሚገባው ደግሞ መላው አፍሪካና ባብዛኛው እስያ በቅኝ አገዛዝ በሚሰቃይበት ወቅት የተለያዩትንና በአግባቡ የማይተዋወቁትን የኢትዮጵያ ነገዶች በማስማማትና በማግባባት የቅኝ ገዢዎችን ወረራ በመመከትና ለኢትዮጵያውያን ብቻ ሳይሆን ለመላው የዓለም ነፃነት ፈላጊ ሕዝቦች መኩርያ የሆነውን የአድዋ ድል ለማስገኘትመቻላቸው:.

8)ከዘመኑ ኃያላን አገሮች ጋር እንደ በታች ሳይሆን እንደ አንድ ሉዓላዊ አገር መሪ በተለያዩ ጉዳዮች ላይ መደራደር መቻላቸው::

9)በአርቆ አስተዋይነታቸው ማሸነፍ የማይችሉትን ጠላት በዲፕሎማሲ በመጠቀም የተገኘውን ድል ማስጠበቅ መቻላቸው::

10) ብዙዎቹ ባለስልጣኖቻቸው ሐማሴኖችና ትግሬዎች ከጣሊያን ጋር አብረዋልና(ያኔ ባንዳ የሚለው ቃል አይታወቅም) መካከላችን ያሉት የትግራይ ሹሞች ይቀጡ ባሉበት ወቅት ከጠላት ጋር ያበረውን ብቻ እንጂ ሌሎቹን አልቀጣም ብለው ሩህሩህነታቸውንና አርቆ አስተዋይነታቸውን ማሳየታቸው::

ይቀጥላል
Last edited by ዘርዐይ ደረስ on Fri Mar 02, 2018 10:34 pm, edited 1 time in total.
''ፍምን እፍ ብትላት ትነዳለች ትፍም ብትልባት ትጠፋለች ሁለቱም ሁሉ ከአንድ አፍ ይወጣሉ ::''መጽሐፈ ሲራክ 28:12
ዘርዐይ ደረስ
ውሃ አጠጪ
ውሃ አጠጪ
 
Posts: 1089
Joined: Sat Oct 23, 2004 3:52 am
Location: ethiopia

Postby ዘርዐይ ደረስ » Sun Jul 29, 2012 2:05 pm

ሰላም ለሁላችሁ እያልኩ:-

ይህን ከ10 ወራት በፊት የከፈትኩትን ርእስ ወደፊት ያመጣሁበት ምክንያት ሰሞኑን እዚህ ዋርካ ላይና በተለይም በፓል ቶክ በአፄው ላይ የሥም ማጥፋት ዘመቻ ስለሚካሄድ ነው::በተጨማሪም ስለ ንጉሡ የሚጻፉትን አንዳንድ የተሳሳቱ መረጃዎች ለማስተካከል እንድንችል ነው::ለምሳሌም:-

ስሙ ይናገር እንደጻፈው:-

ሌላው ሁለቱም በኤርትራ ላይ ያላቸው አቋም አንድ ነው ምንሊክም ኤርትራን አይፈልጋትም መለስም ያሳየን ያንን ነው ሁለቱም አኗኗራቸው እንደሚመሳሰል አሟሟታቸውም ቢመሳሰል ምን ይደንቃል

በእርግጥ አጼ ምኒሊክ የዘመኑ ጎጠኞች እንደሚሉት ኤርትራንና ህዝቡን ሳይፈልጉ ቀርተው ነው ለጣልያን አሳልፈው የሰጡት?የምናወራው ከ 120 ዓመታት በፊት ስለነበረ ክስተት ነው::በዚያን ወቅት የአውሮፓ ቅኝ ገዢዎች መላውን አፍሪካ ተቆጣጥረው ዓይናቸውን ኢትዮጵያ ላይ የጣሉበት ሁኔታ ነበር::በስምምነታቸውም መሠረት ኢትዮጵያን ለጣልያን ትተውለት ነበር::ሁላችንም እንድምናውቀው ሙከራው በአድዋ ድል ከሽፏል::በርግጥ ከዚያ በኋላ ምኒሊክ ከጣልያን ጋር ሥምምነት አድርገዋል::ብዙዎች የታሪክ ጸሐፊዎች እንደሚስማሙበት ይህ ዲፕሎማሲያዊ መንገድ አስፈላጊ ነበር::ምክንያቱም ከአድዋ ድል በኋላ ጦርነቱን ቀጥለው ቢሆን ኖሮ የተገኘውን ድል እስከማጣት ይደረስ ነበር::በተጨማሪም ዳግማዊ ምኒሊክ ኢትዮጵያን አንድ ሲያደርጉ ጣልያን ኤርትራን ተቆጣጥሮ ነበር::

ስሙ ይናገር እንደጻፈው:-

ምኒልክ በምንም መልኩ ለእኛ ለኦሮሞዎች ማፈሪያ ነው ቆማጣ ተቆምጦ መሞቱን ታውቅ ነበር ወይስ ዛሬ ልንገርህ ?

አጼ ምኒሊክ ካረጁ በኋላ ለምጽ ጀማምሯቸው ነበር እንጂ ቁምጥና አልያዛቸውም::ለህዝብ መታየት ያቆሙትም እግራቸው ሽባ ሆኖ መንቀሳቀስ ስላልቻሉ ነበር::

ቆቁ እንደጻፈው:-

ምኒሊክ በምንም በምንም የቀዳማዊ ምኒሊክ የትውልድ ሐረግ ውስጥ ይደለም

ዳግማዊ ምኒሊክ ባባታቸው በሸዋው ንጉሥ ኃይለ መለኮት በኩል የሰለሞናዊው ሥርወ መንግሥት ዝርያ አላቸው::
''ፍምን እፍ ብትላት ትነዳለች ትፍም ብትልባት ትጠፋለች ሁለቱም ሁሉ ከአንድ አፍ ይወጣሉ ::''መጽሐፈ ሲራክ 28:12
ዘርዐይ ደረስ
ውሃ አጠጪ
ውሃ አጠጪ
 
Posts: 1089
Joined: Sat Oct 23, 2004 3:52 am
Location: ethiopia

..

Postby ቁራ10 » Sun Jul 29, 2012 3:33 pm

: ኤርትራና ትግራይ እንደ ተቀናቃኝ በማየት ሁለቱንም ለጣልያን ለመስጥት የ ውጫሌ ትሪቲ የፈረሙትስ
: ራስ አሉላ ከ አድዋ በሀላ ኤርትራን ነጳ እናውጣ ሲሉ አሻፈረኝ ያሉ ባንዳ መሆናቸውንስ (ትግርኛ ተናጋሪዎችን ለማዳከም)
: ከ ትውልድ ወደ ትውልድ የ ተሻገረ እሳት ቀብረው መሄዳቸውንስ (e.g Eritrean caase)
: ከ ደርቡሽ ጋር አብረው ዮሀንስን ማስገደላቸውንስ
: ጅቡቲን ለ ፈረንሳይ መሸጣቸውንስ
: የ syphills በሽታ introduce ያደረጉ ዘማዊ መሪ መሆናቸውንስ
ለመሆኑ እንደ ሚኒሊክ ባንዳ አለ እንዴ!

ሌላም ሌላም እመለሳለሁ!
ya
ቁራ10
አዲስ
አዲስ
 
Posts: 31
Joined: Sun Jul 15, 2012 12:53 pm
Location: asmara

Re: ዳግማዊ አፄ ምኒሊክ(1836-1906)(1881-1906)

Postby ስሙ ይናገር » Sun Jul 29, 2012 4:40 pm

የጻፍኩትርን ዋርካ በላብኝ ዋርካ በላብኝ
በአጭሩ ለትንታኔህ መልስ ለመመለስ ያክል ነው
ሳይረዝም ግን አልቀረም
በተራቁጥር 1 ላይ ላሰፈርከው
መለስ በእርሱ ዘመን የድህረ ገጽ ቴክኖሎጂ ወደ ሀገራችን ስለገባ ደጋፊው ብትሆን ምን ብለህ እንደምትጽፍ ሳስብ ድንቁርናህ ያሳዝነኛል:: አንድ የሀገር መሪ መድረግ የሚገባውን ወቅቱ ያዘዘውን ነገር ያደርጋል ይህ ደግሞ የመሪው ብርታትና ጥንካሬ ሳይሆን ዘመኑ የሚፈልገውን ነገር ማድረጉ ነው

በተ/ቁ 2 ላይ ላልከው
ምናልባት የሰመኑን ኃላቀርነት ካልሆነ እስከዛሬ በሰለጠኑ ማህበረሰቦች (ህእገሮች) እንኳን መተግበር ተስኗቸው የሚታገሉትን የህዝብ አስተዳደር የኦሮሞ ሕዝብ ከጥንት ሲተዳደርበት የኖረው ለመሆኑ መቼም የታሪክ መዛግብትን ማገላበት ተገቢ ይመስለኛል:: በምኒልክ ዘመን የነበረው የባሪያ ንግድ ተወዳዳሪ የማይገኝለት እንደነበር በቅርቡ እንኳን የቢቢሲ ዘገባ ታያለህ:: ታድያ የትኛውን ኃላ-ቀርነት እንዳስወገደ አይገባኝም

በተ/ቁ 3 ላልከው
እስከዛሬ ድረስ ከነበሩት መንግስታት ካልበለጠ በስተቀር ባልተናነሰ መልኩ የሐይማኖት እኩልነት ያልታየበት ዘመን እንደነበረ በማስረጃ ላቅርብልህ
የመጀመሪያው የኦሮሞ ፕሮቴስታንት አማኝ ኦኒስሞስ ነሲብ (አባ ገመቺስ , ሂካ አዋጂ ) በባርነት ተሽጦ ከሔደበት ሀገር ወንጌል ተምሮ ሲመለስ አላስገባም ብለው በገዛ ሀገሩ እንዳይገባ የተከለከለ ሰው ነበር ከዛም መጽሐፍ ቅዱስን በኦሮሚኛ ቋንቋ ተርጉሞ ለወገኖቹ በነጮች አማካይነት ሲልክ በቁጥር ከመቶ ሺህ ኮፒ በላይ ወጥቶ በእሳት እንዲቃጠል የተደረገው የሐይማኖት እኩልነት እንዲሰፍን ከሆነ እራስህን እያታለልክ ነው ማለት ነው ይህ የምልህ ሰው የሞተው በእስር ቤት ውስጥ ነው ምንም ወንጀል አልሰራም ወንጀሉ ለእምነቱ ብቁ ሆኖ ህዝቡን ወንጌል ማስተማሩ ነበር::
የእስልምናውን አታንሳ ምን ያክል ይገፉ እንደነበረ ቤት ይቁጠረው ስለዚህ በዚህም አልተሳካልህም

በተ/ቁ 4 ላነሳሔው
ምኒልክ ደቡቡን ሲቆጣጠር ወዶ የተገዛለት አልነበረም እንዲያውም የጨለንቆው የሀርማ ሙራው የወሎው የአርሲው የባሌው የጦናው ልጆቻቸው ይፋረዱሀል ወንዱ በህይወት እንዳለ ብሊቱ ሴቷ በሴትነቷ ክብር ሲገባት በሰልፍ ጢቷን ለቆራጭ ስትሰጥ
በአጠቃላይ ምኒልክ ማለት የሴይጣን ቁራጭ ካልሆነ ምን ሊሆን ይችላል? እውነቴን ነው የምልህ ሴይጣን ለመኖሩ ትልቁ ምልክት ከዛሬ 100 አመት ገደማ የኖረው ምኒልክ ማስረጃ ነው::

በተ/ቁ 5 ላይ ላቀረብከው
አሁን እነ ኩምሳ ሞረዳና አባጅፋርን ምሳሌ ልትሰጠኝ እንደምትዘጋጅ አውቃለው ግን እነ ራስ ተሰማ ናደው ምዕራቡን ሁሉ ሲገዙ ተወላጅ ሆኖ ነው ወይስ ከአማራ ያውም ከመንዝ ተሹመው ነው አየህ በእያንዳንዱ የክልል ሰው ስር የተሰገሰገው አማራ ቁጥር የለውም እንዲያውም ከመለስ ሀር የሚያመሳስላቸው አንዱ በብሔር በሔረሰቦች የሚጫወቱት የቁማር አይነት ነው
ከላይ እነ ሐብተጊዮርጊስ ዲነግዴን እነ ጎበና የሚያሽከረክሩት እኮ እነ ጎራው ናቸው ስለዚህ እዚህም ላይ ከወያኔ አይሻልም ሁለቱም አንድ ናቸው

በተ/ቁ 6 ይህም ቅጥ ያጣ አስተያየት ነው
ሰው የሚሾመው በፖለቲካ ወገንተኝነቱ እንጂ በችሎታው ሆኖ አያውቅም ይህም በሰለጠነው አለም እንኳ ሌቤር ሲገዛ የሚሾመው የሌበር ፓርቲ የሆነ ሰው ነው ወያኔም ያደረገው ያንን ነው ምኒልክም ያደረገው ያንን ነው በእርግጥ ምኒልክ ችሎታ ካላቸው የሌላ ህዝቦች ስር ሁለት ወይም ሶስት የመንዝ ሰው ታኮ ያስቀምጥ ነበር ልክ እንደ ወያኔ ይህ ታዲያ ዲሞክራቲክ ካሰኘው የዲሞክራሲ ጽንሰ ሀሳብ አልገባህም ማለት ነው

በተ/ቁ 7
ይህም የተሳሳተ ነው አንድ ያልሆነ ህዝብ አንድ ለማድረግ ጣረ ማለ ካልሆነ ሌላ ትርፍ የለውም ደግሞ በአውሮፓዊያኑ መታለፉ ጀግንነታችን ቢቻ አይደለም ዋናው አውሮፒያዊያኑ ወደ አፍሪካ የተሰማሩበትን አላማ ሲያከናውን ስላገኙት ከድካም አዳናቸው የአውሮፒያዊያኑ የረጅም ጊዜ ስራ በአፍሪካ ውስጥ ፈንጅ መትከል ነው ያውም አንድ ያልሆነውን ህዝብ በአንድ ሰብስበው timing bomb መትከል ነው ያንን ደግሞ ተክሎላቸዋል ስለዚህ በአፍሪካ ውስጥ ስራቸውን የሰራላቸውን ሰው ለምን ብለው ይወሩታል እንጂ እንግሊዝ ወይም ፈረንሳይ ሊወሩ ቢፈልጉ አንድ ቀን አይፈጅባቸውም በአዱዋና በማይጨው እንግሊዝና ፈረንሳይ ለኢትዮጵያ ጦር ማቀበላቸው ለዛ ይመስለኛል::

በተ/ቁ 8 እና 9
አንድ ተረት ሰምቼ ነበር የፈርንሳዩን ንጉስ መጥተህ የባቡር መንገድ የማትሰራልኝ ከሆነ ጦሬን አሰልፌ መጥቼ እወጋሀለው አሉት ያኔም ፈርንሳዩ ፈርቶ መሀንዲሶችን ላከና አሰራላቸው ቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅ በዚህ ተረት ኖራችኃል በእርግጥ ለምኒልክ የማደንቅለት ነገር የሚስቱን ምክር ይሰማል ቅቅቅቅቅቅቅ ደግሞም በምኒልክ ዘንድ ተኮልኩለው የሚቀመጡ ፈርንጅ አማካሪዎች ነበሩት ወቅቱም ቢሆን ያንን እንዲያደርግ ይመክረዋል እንጂ የተለየ ችሎታና እየታ ስለነበረው አይደለም ገባህ

ተ/ቁ 10 ይህም ተረት ነው እርሱስ ቢሆን ቴውድሮስንና ዮሐንስን ያስገደለው በስልጣን ሹኩቻ አይደልም እንዴ?

የላይ ያስቀመጥከውን እንድመልስልህ ያደረገኝ ሁለት ምክንያቶች ናቸው
1. ስሙ ይናገር እንዲህ አለ ስላልከኝና
2. ይብቃን ውሸት ለማለት ያክል ነው ስንዋሽ ብዙ ዘመን አለፈ አሁንስ አይበቃም ወይ
ስሜና ያነሳህበት ሁለቱም ኤርትራን አይፈልጉም ባልኩት ላይ ነው አንድ ሰው ሲደግፍም ሲቃወምም ምክንያታዊ መሆን አለበት እኔ ያቀረብኩት መከራከሪያ አሳማኝ ካልሆነ ሀሳብህን አቅርብ ካልሆነ መለስም በስዬ የሚመራው የኢትዮጵያ ጦር ኤርትራን ለመውረር 50 ኪሎሜትር ቀርቶት የመመለሻ ፊሽካ የነፋው አጋርነቱን ለመግለጽ ነው ምኒልክም አዱዋ ላይ ድል (የተመታውን) ??? የኢጣሊያን ጦር እስከ ኤርትራ እንዝለቅና ድል እያድርገው ሲሉ የተወው ወዶ አይደለም ስልታዊ ይሁን እንጂ በዚህም በዛም መሰሪ ተግባር ነበረው
በዚህ አጋጣሚ ስለምኒልክ የአውሮፓዊያን ተንኮል አንድ ነገር ልበልህ
ኢትዮጵያ ቦርደር ላይ ያሉትን ሀገሮች አንዴ በአይነ ሂሊናህ ቃኛቸው በኦሮሞ በኩል የኢትዮ ቦረናንና የኬኒያ ቦረናን በሱማሌ በኩል ኦጋዴንና የሱማሊያን ግዛት በዕራብ በኩል ጋምቤላን ኑኤርንና አኙአክንና የደቡብ ሱዳኖችን በሰሜን በኩል አንድ ቋንቋ ተናጋሪ የሆኑትን ትግራይንና ኤርትራን ለምን ቆራርጦ አስቀረ?????? ይህ ትልቅ የፖለቲካና የታሪክ ፍልስፍናን ይጠይቃል እስቲ ተመራመርበት:: የእኔው ምርምር ግን ከአውሮፓዊያን ጋር ተቀምጦ የተደራደረበት ጉዳይ ይኖራል ብዬ አስባለሁ ለዚህ ትውልድ የተቀመጠ የቤት ስራ
God is Great
ስሙ ይናገር
ውሃ አጠጪ
ውሃ አጠጪ
 
Posts: 1150
Joined: Fri Mar 14, 2008 4:46 pm

Re: ዳግማዊ አፄ ምኒሊክ(1836-1906)(1881-1906)

Postby ግዛቸው » Sun Jul 29, 2012 5:09 pm

ዘራዐይ ደርስ

ጥሩ እርስ ነው የከፈትከው::
እኔ በዚህ ክፍል ከተለያዮ መጽፋፍት የማገኛቸውን ለመጻፍ እሞክራለሁ::

በርታ!!

በአድዋ ጦርነት ወቅት አጼ-ሚንሊክና እቴገ ጸሀይቱ በርካታ የጣሊያ ወታደሮች እና ኢትዮፕያውያን በውቂያው ሞተው በመጨረሻ የአጼ ሚኒሊክ ጦር አሸንፎ ሲጨፍር እንዲህ ነበር ያሉት::

Emperor Menelik returned to Adowa from Amba Abba Gerima. Once the Emperor had returned to Adowa, the command was given to halt the fighting. No more of the enemy were to be killed from that point, only taken prisoner. Baratieri barely escaped with his life, General Arimondi and Dabormida met their deaths, and General Albertone was captured. Fires were set to smoke out soldiers hiding in the tall grasses. Soldiers began to sing victory songs and praises of Menelik and the great leaders of the battle, and women began to ulultate. Immediately, the Emperor called a halt to the celebration stating "It is Christians who have slaughtered each other today, there is no reason to celebrate." Both he and his Empress had their red umbrellas folded, and ordered black umbrellas opened in their stead, and a torrential rain began to fall. The Empress wept as she was told the names of some of the many who had died on the Ethiopian side, and the court and the army were plunged into mourning even as they savored a great victory. Between 4 and 8 thousand Ethiopians lay dead, and 6 thousand Italian troops (both European and Eritrean) were also dead. Italians were being captured by the hundreds as were their Eritrean "askari" colonial troops.ዘርዐይ ደረስ wrote:ሰላም ለሁላችሁም እያልኩ:-

ትላንት ስለ አፄ ምኒሊክ አንድ ፅሑፍ ፖስት አድርጌ ዛሬ ተጨማሪ ለመፃፍ ሳስብ ለካ የፃፍኩበት ቤት ተሰርዟል::ልፋቴ ቢያሳዝነኝም ለወደፊቱ በየትኛው ርእስ ሥር መፃፍ እንዳለብኝ ትምህርት ሰጥቶኛል::

ያም ሆነ ይህ ስለ እኚህ የኢትዮጵያ ኩራት የምንወያይበት ክፍል መክፈቱ የተሻለ ስለመሠለኝ አስተያየት መስጠት የምትፈልጉ በሥነ ሥርዓት እንድታደርጉት ምክርም ማሳሰቢያም አቀርባለሁ::

ለመጀመር ያህል ትላንት የፃፍኩትን እሳቸው ለኢትዮጵያና ለሕዝቧ ባበረከቱት አስተዋፅዖ እጀምራለሁ::

1)በዘመናቸው በዓለም ላይ ከሚታወቁት የሳይንስና ቴክኖሎጂ ውጤቶች መካከል ለኢትዮጵያ ይጠቅማል ያሉትን ወደ አገራችን በማስገባታቸው::

2)ለዘመናት ከትውልድ ወደ ትውልድ ሲተላለፉ የኖሩትን ኋላ ቀር አስተሳሰቦችና ልማዶች በተቻለ መጠን እንዲወገዱ በማድረጋቸው::

3)በወቅቱ የነበረውን የኃይማኖት ጭቅጭቅና ግጭት እንደ አፄ ቴዎድሮስና አፄ ዮሐንስ 4ኛ በኃይል ሳይሆን የተለያዩ ዘዴዎችን በመጠቀም ለመፍታት መሞከራቸው::

4) ኢትዮጵያን አንድ ለማድረግ በሚጥሩበት ወቅት የሚገጥማቸውን ተቃውሞ ግድ ካልሆነ በቀር ኃይል አለመጠቀማቸው::

5)የተለያዩትን የኢትዮጵያ ነገሥታትና የጎሳ መሪዎች በሚያስገብሩበት ወቅት ብዙ ጊዜ የአካባቢውን ሰዎች መሾማቸው::

6)ባለሥልጣኖቻቸውን ሲሾሙ ከዘር ሐረጋቸው ይልቅ በችሎታቸውና ለአገራቸው ባላቸው አመለካከት እንዲሆን ማድረጋቸው::

7)በመጀመርያ ደረጃ ሊጠቀስ የሚገባው ደግሞ መላው አፍሪካና ባብዛኛው እስያ በቅኝ አገዛዝ በሚሰቃይበት ወቅት የተለያዩትንና በአግባቡ የማይተዋወቁትን የኢትዮጵያ ነገዶች በማስማማትና በማግባባት የቅኝ ገዢዎችን ወረራ በመመከትና ለኢትዮጵያውያን ብቻ ሳይሆን ለመላው የዓለም ነፃነት ፈላጊ ሕዝቦች መኩርያ የሆነውን የአድዋ ድል ለማስገኘትመቻላቸው:.

8)ከዘመኑ ኃያላን አገሮች ጋር እንደ በታች ሳይሆን እንደ አንድ ሉዓላዊ አገር መሪ በተለያዩ ጉዳዮች ላይ መደራደር መቻላቸው::

9)በአርቆ አስተዋይነታቸው ማሸነፍ የማይችሉትን ጠላት በዲፕሎማሲ በመጠቀም የተገኘውን ድል ማስጠበቅ መቻላቸው::

10) ብዙዎቹ ባለስልጣኖቻቸው ሐማሴኖችና ትግሬዎች ከጣሊያን ጋር አብረዋልና(ያኔ ባንዳ የሚለው ቃል አይታወቅም) መካከላችን ያሉት የትግራይ ሹሞች ይቀጡ ባሉበት ወቅት ከጠላት ጋር ያበረውን ብቻ እንጂ ሌሎቹን አልቀጣም ብለው ሩህሩህነታቸውንና አርቆ አስተዋይነታቸውን ማሳየታቸው::

ይቀጥላል
Visit My Blog
----===-----
ኢትዮ-ፈን ብሎግ |||
“Freedom is not free.”
ግዛቸው
ዋና ውሃ አጠጪ
ዋና ውሃ አጠጪ
 
Posts: 1530
Joined: Fri Jul 16, 2004 11:18 am

Re: ዳግማዊ አፄ ምኒሊክ(1836-1906)(1881-1906)

Postby ዘርዐይ ደረስ » Mon Jul 30, 2012 10:27 pm

ስሙ ይናገር እንደጻፈው:-

በአጭሩ ለትንታኔህ መልስ ለመመለስ ያክል ነው
ሳይረዝም ግን አልቀረም
በተራቁጥር 1 ላይ ላሰፈርከው
መለስ በእርሱ ዘመን የድህረ ገጽ ቴክኖሎጂ ወደ ሀገራችን ስለገባ ደጋፊው ብትሆን ምን ብለህ እንደምትጽፍ ሳስብ ድንቁርናህ ያሳዝነኛል:: አንድ የሀገር መሪ መድረግ የሚገባውን ወቅቱ ያዘዘውን ነገር ያደርጋል ይህ ደግሞ የመሪው ብርታትና ጥንካሬ ሳይሆን ዘመኑ የሚፈልገውን ነገር ማድረጉ ነው

ኃይለሥላሴ ደርግና ወያኔ/ኢህአዴግ ቴክኖሎጂን ቢያስፋፉ አይገርምም::በአፄ ምኒሊክ ዘመን ግን ህዝቡ ዘመናዊ ቴክኖሎጂን የሠይጣን ሥራ አድርጎ ይቆጥር ስለነበር አፄው በዘመናቸው የነበረውን ኅብረተሰብ አመለካከት ባብዛኛው በመቀየር ሥር ነቀል ለውጥ በማድረጋቸው ነው ይደነቃሉ ያልኩት::

በተ/ቁ 2 ላይ ላልከው
ምናልባት የሰመኑን ኃላቀርነት ካልሆነ እስከዛሬ በሰለጠኑ ማህበረሰቦች (ህእገሮች) እንኳን መተግበር ተስኗቸው የሚታገሉትን የህዝብ አስተዳደር የኦሮሞ ሕዝብ ከጥንት ሲተዳደርበት የኖረው ለመሆኑ መቼም የታሪክ መዛግብትን ማገላበት ተገቢ ይመስለኛል:: በምኒልክ ዘመን የነበረው የባሪያ ንግድ ተወዳዳሪ የማይገኝለት እንደነበር በቅርቡ እንኳን የቢቢሲ ዘገባ ታያለህ:: ታድያ የትኛውን ኃላ-ቀርነት እንዳስወገደ አይገባኝም

በነገራችን ላይ ካነሳኸው አልቀር ምኒሊክ የባርያ ንግድ እንዲሻሻል በሂደትም እንዲቀር የገባር ሥርዓትም እንዲሻሻል ከሳቸው በፊት ባልተለመደ ሁኔታ ከፍተኛ አስተዋጽኦ አድርገዋል::የሴቶችን መብት በሚመለከትና የህግ የበላይነትን በማስከበርም የማይናቅ ድርሻ አላቸው::ኋላ ቀር ባህልን በማስወገድ ረገድ አገሪቱ በምኒሊክ ጊዜ ያደረገችውን ጥረት የምናወዳድረው አሁን ካለንበት ጊዜ ጋር ሳይሆን ከሳቸው በፊት ከነበሩት ነገሥታት ጋር ነው::የኦሮሞ ጎሣዎችና ሌሎችም በኢትዮጵያዊነት ጥላ ሥር የተዋሃዱ ህዝቦች ከዚያ በፊት ይተዳደሩበት ስለነበረው ሥርዓት በቂ ዕውቀት ስለሌለኝ ከአጼው ሥርዓት ጋር ለማወዳደር አስተያየት ከመስጠት ተቆጥቤአለሁ::

በተ/ቁ 3 ላልከው
እስከዛሬ ድረስ ከነበሩት መንግስታት ካልበለጠ በስተቀር ባልተናነሰ መልኩ የሐይማኖት እኩልነት ያልታየበት ዘመን እንደነበረ በማስረጃ ላቅርብልህ
የመጀመሪያው የኦሮሞ ፕሮቴስታንት አማኝ ኦኒስሞስ ነሲብ (አባ ገመቺስ , ሂካ አዋጂ ) በባርነት ተሽጦ ከሔደበት ሀገር ወንጌል ተምሮ ሲመለስ አላስገባም ብለው በገዛ ሀገሩ እንዳይገባ የተከለከለ ሰው ነበር ከዛም መጽሐፍ ቅዱስን በኦሮሚኛ ቋንቋ ተርጉሞ ለወገኖቹ በነጮች አማካይነት ሲልክ በቁጥር ከመቶ ሺህ ኮፒ በላይ ወጥቶ በእሳት እንዲቃጠል የተደረገው የሐይማኖት እኩልነት እንዲሰፍን ከሆነ እራስህን እያታለልክ ነው ማለት ነው ይህ የምልህ ሰው የሞተው በእስር ቤት ውስጥ ነው ምንም ወንጀል አልሰራም ወንጀሉ ለእምነቱ ብቁ ሆኖ ህዝቡን ወንጌል ማስተማሩ ነበር::
የእስልምናውን አታንሳ ምን ያክል ይገፉ እንደነበረ ቤት ይቁጠረው ስለዚህ በዚህም አልተሳካልህም

እዚህ ላይ መዘንጋት የሌለብን ነገር ቢኖር አጼ ምኒሊክ ሥልጣነ መንግሥቱን የተረከቡት ከአፄ ዮሐንስ ነው::ሁላችንም እንደምናውቀው አፄ ዮሐንስ ኢትዮጵያ ውስጥ አንድ ሐይማኖት ብቻ(ተዋሕዶ ኦርቶዶክስ) ለማስፈን ቆርጠው ተነስተው የእስልምና ሃይማኖት ተከታዮች ክርስትናን እንዲቀበሉ አስገደድዋል:.እንቢ ያሉትም ተሰደዋል ህይወታቸውን ያጡትም ጥቂት አልነበሩም::በነገራችን ላይ ከተዋሕዶ ውጭ የነበሩትም ኦርቶዶክሶች (ቅባትና ፀጋ ይባሉ የነበሩት) እንዲሁም የፕሮቴስታንት እምነት ተከታዮች ከፍተኛ ችግር ደርሶባቸዋል::በአፄ ምኒሊክ ዘመን ግን የሃይማኖት ነፃነትን በሚመለከት ጉልህ መሻሻሎች ተደርገዋል::ሃይማኖትን በሚመለከት የአፄ ዮሐንስና የአፄ ምኒሊክ ዘመን ሳይምታታብህ አልቀረም::በእርግጥ የተዋሕዶ ኦርቶዶክስ ሃይማኖት የንጉሡ ሃይማኖት ከመሆኑም በላይ በአገሪቱ የበላይነት ነበረው ::እስልምናና ሌሎችም እምነቶች ግን አንፃራዊ ነፃነት ነበራቸው እንዲያውም የንጉሡ አማካሪ እስከመሆን የደረሱ እንደ ከንቲባ ገብሩ ደስታ ያሉ የፕሮቴስታንት ተከታዮች ነበሩ::አንተ ስለ አነሳሃቸው አናሲሞስ ነሲብ ሰምቼአለሁ:.እንዲያውም ስለ ቁቤ በተነሳው ርእስ ላይ መረጃ ለማግኘት ጉግል ሳደርግ ታሪካቸውን አንብቤአለሁ::አንተ እንዳልከው የመጀመርያው ኦሮሞ የፕሮቴስታንት እምነት ተከታይ እንደነበሩ እርግጠኛ ባልሆንም መፅሐፍ ቅዱስን በኦሮምኛ ተርጉመዋል::ስደትናአ ችግር የገተማቸው ግን የፕሮቴስታንት ሃይማኖትን ለማስፋፋት ባደረጉት ጥረት ተ ነበር::ያም ሆኖ ግን አንተ አምርረህ የምትጠላቸው ምኒሊክ አናሲሞስን ለመርዳት ጥረት ማድረጋቸውንና ክሱ በድጋሚ ታይቶ ያለፈውን ይቅር ብለዋቸው ለወደፊቱ እንዳይሰብኩ አስጠንቅቀው እንደለቀቋቸው ለማንበብ ችያለሁ::ተቃጠሉ ስላልካቸው መጽሐፍ ቅዱስ ግን ያየሁት ነገር የለም::

ከታች ኮት ያደረግኩትን ሙሉ ታሪክ ለማንበብ

http://www.dacb.org/stories/ethiopia/on ... nesib.html

On July 13, 1906, he was tried on several false charges. Only Alequa Tegenye witnessed in his favor. Abune Mateos, the archbishop, joined the accusers in calling down the judgment of heaven on Onesimus who was sentenced to lose all his property and was imprisoned laden with heavy chains. The same punishment was to be meted out to all his followers in Wellega, including the governor of Leqa and Wellega. As a result, in order to avoid suffering this punishment and to save face with the local clergy, the governor was forced to carry out the archbishop's orders and to excommunicate Onesimus and denounce his teaching.

However, the emperor refused to confirm the archbishop's verdict and ordered Alequa Istifanos, minister of church affairs (later Afe Nigus--the King's spokesman--and minister of justice) to examine the case. Istifanos, who was known for his fair outlook when it came to harsh judgments, listened to the parties for several hours and concluded that Onesimus was not guilty of any crime. The only charge that could be brought against him was that he did not believe in the mediating role of the Virgin Mary and the saints. Menelik therefore decided that Onesimus should stop preaching and teaching. However, the emperor sent him to the minister of commerce to see if he had the skills to work there. He was examined for his knowledge of languages, mathematics, and crafts. But since Onesimus did not possess technical skills, he was instead sent back to Naqamte to live on farming and trade.

በተ/ቁ 4 ላነሳሔው
ምኒልክ ደቡቡን ሲቆጣጠር ወዶ የተገዛለት አልነበረም እንዲያውም የጨለንቆው የሀርማ ሙራው የወሎው የአርሲው የባሌው የጦናው ልጆቻቸው ይፋረዱሀል ወንዱ በህይወት እንዳለ ብሊቱ ሴቷ በሴትነቷ ክብር ሲገባት በሰልፍ ጢቷን ለቆራጭ ስትሰጥ
በአጠቃላይ ምኒልክ ማለት የሴይጣን ቁራጭ ካልሆነ ምን ሊሆን ይችላል? እውነቴን ነው የምልህ ሴይጣን ለመኖሩ ትልቁ ምልክት ከዛሬ 100 አመት ገደማ የኖረው ምኒልክ ማስረጃ ነው::

እነ ራስ ጎበና ዳጨው ሀብተጊዮርጊስ ዺነግዼ ገበየሁ ባልቻ አባ ነፍሶ ወዘተ ና ተከታዮቻቸው የንጉሡን ጦር ተቀላቅለው ለኢትዮጵያ አንድነት የታገሉና ለአድዋ ድል ከፍተኛ አስተዋፆ ያደረጉ ናቸው:.እነዚህና ሌሎች በታሪክ ሥማቸው ስለተጠቀሰ ነው እንጂ በ መቶ ሺህ የሚቆጠሩ(ምናልባትም በሚሊዮን) የሚቆጠሩ ከኦሮሞ ጎሣዎችና ከደቡብ እንዲሁም ምዕራብና ምሥራቅ ለኢትዮጵያ አንድነትና ለአገሪቱ ሉዓላዊነት ታግለዋል ህይወታቸውንም ሰጥተዋል::በርግጥ በፊትም እንደጠቀስኩት አልገብር ያለውን በሃይል አስገብረዋል ኦነግ ወያኔና ሻዕቢያ እንደሚሉት ያለ ግፍ መሠራቱን ግን በታሪክ መጻሕፍት ላይ አላነበብኩም::

በተ/ቁ
5 ላይ ላቀረብከው
አሁን እነ ኩምሳ ሞረዳና አባጅፋርን ምሳሌ ልትሰጠኝ እንደምትዘጋጅ አውቃለው ግን እነ ራስ ተሰማ ናደው ምዕራቡን ሁሉ ሲገዙ ተወላጅ ሆኖ ነው ወይስ ከአማራ ያውም ከመንዝ ተሹመው ነው አየህ በእያንዳንዱ የክልል ሰው ስር የተሰገሰገው አማራ ቁጥር የለውም እንዲያውም ከመለስ ሀር የሚያመሳስላቸው አንዱ በብሔር በሔረሰቦች የሚጫወቱት የቁማር አይነት ነው
ከላይ እነ ሐብተጊዮርጊስ ዲነግዴን እነ ጎበና የሚያሽከረክሩት እኮ እነ ጎራው ናቸው ስለዚህ እዚህም ላይ ከወያኔ አይሻልም ሁለቱም አንድ ናቸው

በነግራችን ላይ ራስ ተሰማ ናደው መንዜ ሳይሆኑ አዲስጌ ከሚባለው ጎሣ(ጉራጌ ይመሥለኛል) ናቸው::እነ እስከማውቀው ግን ራስ ጎበና የምኒልክ አጎት የሆኑትን ንጉሥ ወልደ ጊዮርጊስ ሳቀሩ የሚያዙ ነበሩ::ፊታውራሪ ሃብተ ጊዮርጊስም ቢሆኑ የጦር ሚኒስትር ነበሩ::ለሎቹም እንደዚሁ:.በእርግጥ የማያምኗቸውንና እገብራለሁ ብለው የካዱትን ገዢዎች ግዛታቸውን ነጥቀዋቸዋል::

በተ/ቁ 6 ይህም ቅጥ ያጣ አስተያየት ነው
ሰው የሚሾመው በፖለቲካ ወገንተኝነቱ እንጂ በችሎታው ሆኖ አያውቅም ይህም በሰለጠነው አለም እንኳ ሌቤር ሲገዛ የሚሾመው የሌበር ፓርቲ የሆነ ሰው ነው ወያኔም ያደረገው ያንን ነው ምኒልክም ያደረገው ያንን ነው በእርግጥ ምኒልክ ችሎታ ካላቸው የሌላ ህዝቦች ስር ሁለት ወይም ሶስት የመንዝ ሰው ታኮ ያስቀምጥ ነበር ልክ እንደ ወያኔ ይህ ታዲያ ዲሞክራቲክ ካሰኘው የዲሞክራሲ ጽንሰ ሀሳብ አልገባህም ማለት ነው

አንተ እንዳልከው ቢሆንማ ስንት መኳንንት እያሉ ከላይ የጠቀስኳቸውን እንዲሁም ለሎችን ለከፍተኛ ሥልጣን ባላበቋቸው ነበር::እንደ ከንቲባ ገብሩና አለቃ ታዬ ያሉትንም የፕሮቴስታንት እምነት ተከታዮችን የጳጳሱንና የካህናቱን ተቃውሞ ችላ ብለው ወደ ቤተ መንግሥት ባላስጠጓቸው ነበር::

በተ/ቁ 7
ይህም የተሳሳተ ነው አንድ ያልሆነ ህዝብ አንድ ለማድረግ ጣረ ማለ ካልሆነ ሌላ ትርፍ የለውም ደግሞ በአውሮፓዊያኑ መታለፉ ጀግንነታችን ቢቻ አይደለም ዋናው አውሮፒያዊያኑ ወደ አፍሪካ የተሰማሩበትን አላማ ሲያከናውን ስላገኙት ከድካም አዳናቸው የአውሮፒያዊያኑ የረጅም ጊዜ ስራ በአፍሪካ ውስጥ ፈንጅ መትከል ነው ያውም አንድ ያልሆነውን ህዝብ በአንድ ሰብስበው timing bomb መትከል ነው ያንን ደግሞ ተክሎላቸዋል ስለዚህ በአፍሪካ ውስጥ ስራቸውን የሰራላቸውን ሰው ለምን ብለው ይወሩታል እንጂ እንግሊዝ ወይም ፈረንሳይ ሊወሩ ቢፈልጉ አንድ ቀን አይፈጅባቸውም በአዱዋና በማይጨው እንግሊዝና ፈረንሳይ ለኢትዮጵያ ጦር ማቀበላቸው ለዛ ይመስለኛል::

እንዲህ ዓይነት አመለካከት ከ አንድ ኢትዮጵያዊ አልጠብቅም ነበር::ኢትዮጵያ በኮሎኒ ያልተያዘችው በፈረንሣይና በእንግሊዝ መልካም ፈቃድ ነው እያልከኝ ነው?ይህንንስ እነሱም የሚሉ አይመስለኝም::

በተ/ቁ 8 እና 9
አንድ ተረት ሰምቼ ነበር የፈርንሳዩን ንጉስ መጥተህ የባቡር መንገድ የማትሰራልኝ ከሆነ ጦሬን አሰልፌ መጥቼ እወጋሀለው አሉት ያኔም ፈርንሳዩ ፈርቶ መሀንዲሶችን ላከና አሰራላቸው ቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅ በዚህ ተረት ኖራችኃል በእርግጥ ለምኒልክ የማደንቅለት ነገር የሚስቱን ምክር ይሰማል ቅቅቅቅቅቅቅ ደግሞም በምኒልክ ዘንድ ተኮልኩለው የሚቀመጡ ፈርንጅ አማካሪዎች ነበሩት ወቅቱም ቢሆን ያንን እንዲያደርግ ይመክረዋል እንጂ የተለየ ችሎታና እየታ ስለነበረው አይደለም ገባህ

ፈረንሣይ የባቡር ሐዲድ የሠራችው ጂቡቲ ለ99 ዓመት በኮንትራት ስለተሠጣት እንደሆነ ማንም የሚያውቀው ነው::ያንተን ተረት ከየት እንዳገኘኸው አላውቅም::በተረፈ እንኳን ያኔና የአሁኑ ዘመን መሪዎችም ቢሆኑ በአማካሪዎች እየተረዱ ነው የሚሠሩት::የአፄው አስደንቂ ችሎታ ግን የዚያን ዘመን ለአገራቸው የሚጠቅሙትን የውስጥና የውጭ አማካሪዎች ማሰባሰብና ማቀናጀት መቻላቸው ነው::

ተ/ቁ 10 ይህም ተረት ነው እርሱስ ቢሆን ቴውድሮስንና ዮሐንስን ያስገደለው በስልጣን ሹኩቻ አይደልም እንዴ?

አሁንስ እየገረምከኝ መጥተሃል::ተዎድሮስ ሲሞቱ አፄ ምኒሊክ ዕድሜያቸው ስንት ነበር? ሥልጣናቸውስ ምን ነበር?አጼ ዮሐንስንስ ከማህዲስቶች ጋር ተመካክረው ነው ያስገደሏቸው?

የላይ ያስቀመጥከውን እንድመልስልህ ያደረገኝ ሁለት ምክንያቶች ናቸው
1. ስሙ ይናገር እንዲህ አለ ስላልከኝና
2. ይብቃን ውሸት ለማለት ያክል ነው ስንዋሽ ብዙ ዘመን አለፈ አሁንስ አይበቃም ወይ

በዚህ ጉዳይ እኔም እስማማለሁ::

ስሜና ያነሳህበት ሁለቱም ኤርትራን አይፈልጉም ባልኩት ላይ ነው አንድ ሰው ሲደግፍም ሲቃወምም ምክንያታዊ መሆን አለበት እኔ ያቀረብኩት መከራከሪያ አሳማኝ ካልሆነ ሀሳብህን አቅርብ ካልሆነ መለስም በስዬ የሚመራው የኢትዮጵያ ጦር ኤርትራን ለመውረር 50 ኪሎሜትር ቀርቶት የመመለሻ ፊሽካ የነፋው አጋርነቱን ለመግለጽ ነው ምኒልክም አዱዋ ላይ ድል (የተመታውን) ??? የኢጣሊያን ጦር እስከ ኤርትራ እንዝለቅና ድል እያድርገው ሲሉ የተወው ወዶ አይደለም ስልታዊ ይሁን እንጂ በዚህም በዛም መሰሪ ተግባር ነበረው

በዚህ ጉዳይ ላይ በፊት ያልኩትን ነው የምደግመው::አትሠ ምኒሊክ ንጉሠ ነገሥት ሲባሉ ኤርትራ በጣሊያን እጅ ነበረች::ስለሆነም በጊዜው የነበረውን የኃይል አሰላለፍ በመረዳት አንድ ያደረጓትን ኢትዮጵያ ሉዓላዊነት ለመጠበቅ ኢትዮጵያን ከከበቧት ቅኝ ገዢዎች ጋር መደራደሩ ብቸኛ አማራጭ ስለነበር ዲፕሎማሲያዊውን መንገድ መርጠዋል::ፈረንሣይና እንግሊዝ ስምምነቱን ቢያከብሩም ጣልያን ግን የውጫሌውን ውል በተንኮል ስላፈረሰችና ጦርነት ስለከፈተች የነበረው አማራጭ ተዋግቶ ሉዓላዊነትን ማስከበር ስለነበር የአጸፋ እርምጃ ለመውሰድና ኢትዮጵያውያን ብቻ ሳይሆን መላው የጥቁር ሕዝብ መኩርያ የሆነውን የዓድዋን ድል ተቀዳጅተዋል::ከድሉ በኋላ ጦርነቱን ቀጥለው ቢሆን ኖሮ ግን ታዋቂው ታሪክ ፀሐፊ ጳውሎስ ኞኞ እንዳለው ''የአፄ ምኒሊክ ሠራዊት ተዳክሞ ስለነበር ወሬ ነጋሪ እንኳ ላይመለስ ይችል ነበር::''

በዚህ አጋጣሚ ስለምኒልክ የአውሮፓዊያን ተንኮል አንድ ነገር ልበልህ
ኢትዮጵያ ቦርደር ላይ ያሉትን ሀገሮች አንዴ በአይነ ሂሊናህ ቃኛቸው በኦሮሞ በኩል የኢትዮ ቦረናንና የኬኒያ ቦረናን በሱማሌ በኩል ኦጋዴንና የሱማሊያን ግዛት በዕራብ በኩል ጋምቤላን ኑኤርንና አኙአክንና የደቡብ ሱዳኖችን በሰሜን በኩል አንድ ቋንቋ ተናጋሪ የሆኑትን ትግራይንና ኤርትራን ለምን ቆራርጦ አስቀረ?????? ይህ ትልቅ የፖለቲካና የታሪክ ፍልስፍናን ይጠይቃል እስቲ ተመራመርበት:: የእኔው ምርምር ግን ከአውሮፓዊያን ጋር ተቀምጦ የተደራደረበት ጉዳይ ይኖራል ብዬ አስባለሁ ለዚህ ትውልድ የተቀመጠ የቤት ስራ

ይህንን ክስተት የማየው አንተ ባየህበት መልኩ አይደለም::ምክንያቱም ምኒሊክ ኢትዮጵያን አንድ በማድረግ ግዛታቸውን ሲያስፋፉ ኮሎኒያሊስቶቹ የያዟቸው ግዛቶች ጋር ሲደርሱ መቆም ነበረባቸው :::ገፍቼ ሊሂድ ቢሉ ኖሮ ይደርስ የነበረውን ጥፋት መገመት ይቻላል::በዚህም ምክንያት ነው አንዳንድ ጎሣዎች በተለያዩ አገሮች እንዲኖሩ የተገደዱት::

ቁራ:-ለስሙ ይናገር በሰጠሁት መልስ ላይ ያንተንም ትያቄዎች ለማካተት ሞክሬአለሁ ::በሽታ ግን እንዴት Introduce እንደሚደረግ አልገባኝም!ግዛቸው:-ለሰጠኸኝ ሞራል እያመሰገንኩ እንዳልከው ተሳትፎህን እንደምትቀጥል ተስፋ አደርጋለሁ
''ፍምን እፍ ብትላት ትነዳለች ትፍም ብትልባት ትጠፋለች ሁለቱም ሁሉ ከአንድ አፍ ይወጣሉ ::''መጽሐፈ ሲራክ 28:12
ዘርዐይ ደረስ
ውሃ አጠጪ
ውሃ አጠጪ
 
Posts: 1089
Joined: Sat Oct 23, 2004 3:52 am
Location: ethiopia

Postby ዘርዐይ ደረስ » Tue Apr 09, 2013 4:02 pm

የአጼ ምኒሊክ የዘር ሐረግ:-

ምኒሊክ--ኃይለመለኮት--ሣሕለሥላሴ--ወሰንሰገድ--አስፋወሰን--አምኃኢየሱስ--አብዬ--ስብስትያኖስ(ስብስቴ)--ነጋሢ--ወ/ሮ ሰንበልት--ሥግው ቃል--ያዕቆብ--ልብነድንግል
''ፍምን እፍ ብትላት ትነዳለች ትፍም ብትልባት ትጠፋለች ሁለቱም ሁሉ ከአንድ አፍ ይወጣሉ ::''መጽሐፈ ሲራክ 28:12
ዘርዐይ ደረስ
ውሃ አጠጪ
ውሃ አጠጪ
 
Posts: 1089
Joined: Sat Oct 23, 2004 3:52 am
Location: ethiopia

Re: ..

Postby ቢተወደድ » Tue Apr 09, 2013 4:52 pm

ምነው የዚችኛዋ ጥያቄ መልስ ዘገየች? ነገሩን ሚዛናዊ ለማድረግ ሁሉንም አቅጣጫ መመልከቱ ባልከፋም ነበር::

አንድ ቦታ ላይ እንደ አጼ ቴዲና አጼ ዮኒ በጉልበት ሳይሆን የሚል ነገር አንብቤያለሁ::

ሰውየው; አጼ ሚኒሊክ የደቡብ ሕዝቦች አልገዛም ሲሊ የእንስቶችን ጡት ሳይቀር አይደለም እንዴ እየቆረጡና እየገደሉ የግዛት አድማሳቸውን ያሰፉት?

ቁራ10 wrote:: ኤርትራና ትግራይ እንደ ተቀናቃኝ በማየት ሁለቱንም ለጣልያን ለመስጥት የ ውጫሌ ትሪቲ የፈረሙትስ
: ራስ አሉላ ከ አድዋ በሀላ ኤርትራን ነጳ እናውጣ ሲሉ አሻፈረኝ ያሉ ባንዳ መሆናቸውንስ (ትግርኛ ተናጋሪዎችን ለማዳከም)
: ከ ትውልድ ወደ ትውልድ የ ተሻገረ እሳት ቀብረው መሄዳቸውንስ (e.g Eritrean caase)
: ከ ደርቡሽ ጋር አብረው ዮሀንስን ማስገደላቸውንስ
: ጅቡቲን ለ ፈረንሳይ መሸጣቸውንስ
: የ syphills በሽታ introduce ያደረጉ ዘማዊ መሪ መሆናቸውንስ
ለመሆኑ እንደ ሚኒሊክ ባንዳ አለ እንዴ!

ሌላም ሌላም እመለሳለሁ!
When we do it right No-one remembers,
When we do it wrong No-one forgets.
ቢተወደድ
ዋና ውሃ አጠጪ
ዋና ውሃ አጠጪ
 
Posts: 1965
Joined: Tue Jul 21, 2009 3:21 pm
Location: Dabra Za`Yet

Postby ­ » Tue Apr 09, 2013 4:57 pm

ዘርአይ ደረስ
ሚኒሊክን ምንም ንፁህ ሰው አድርገህ ለማቅረብ ብትሞክር ስልጣን ላይ ስለነበረ ባለስልጣን ሁሉ ወንጀለኛ ነው» ይሄ ሰውዬ እንደ መለስ ዜናዊ ሁሉ እጁ በደም የታጠበ ነው አማራ ስለሆነ አይደለም መለስም ትግሬ ስለሆነ አይደለም■ ሁለቱም ባለስልጣኖችና የስልጣን ጥም ያለባቸው ግለሰቦች ናቸው■ በስልጣን ለመቆየት ሲሊ አስፈላጊ መስሎ ከታያቸው የራሳቸውን ህዝቦች ክማረድ አይመለሱም■ይሄንን ነገር ለመረዳት ከህዝብ ጋር መቆም አለብህ ከባለስልጣንና ከፊውዳሉ ወገን ከሆንክ ግን የማወራው በፍፁም አይገባህም■

■■■■መለስ ታላቁ መሪ እየተባለ በሚሞካሽበት ዘመን ላይ ነን አዋ እውነት ነው መለስ ጥሩ መሪ ነው ለህዝቡ ለሚመራው ለተዋጋለት ህዝብ ግሩም መሪ ነው■■■■ ለኔ ግን አይደለም ሆኖም አያውቅም ሚኒሊክም ለተወሰነ ሰው ጥሩ ነው ለኔ አባቶች ግን ጥሩ ሰው አልነበረም ስለዚህ ያንተን ጌታ በግድ ውደደው አትበለኝ■ላንተ ጮማ ሲያጎርስ ለሌላው ጡት ሲቆርጥና ሲጨፈጭፍ የነበረ አረመኔ ነው■ ስለ ሂትለርም ብናወራ በእርግጠኝነት ብዙ ስራ ሰርቷል ችግሩ ግን ለጀርመኖች ታላቅ መሪ የነበረ ቢሆንም ለይሁዳዊያን ግን ይሄንን ብትነግራቸው ሊጣሉህ ሁሉ ይችላሉ■በልዩነታችን እንኑር ያንተ ሂሮ ለኔ ዜሮ እንደሆነ መረዳት አለብህ■ለዚህም ነው ወያኔዎች መለስ እኮ ጥሩ ነው መለስ እኮ ነብይ ነው ሲሉን አልቀየማቸውም ምክንያቱን በእውነት መለስ ጥሩ ሰው ነበር ለህዝቡ■ ስለዚህ ውሸታቸውን እንዳይመስልህ ሲያሞግሱት they really believe that የኔን መጎዳት ግን እኔና ወገኖቼ እንጂ ማንም አያውቅም የዛሬ መቶ አመት ታዲያ የትግሬው ልጅ መለስን እንደ ሀይለሥላሤ ሲያመልከው የኔ ልጅ ግን የኔን ቁስል ነው የሚናገረው■ ሁለቱም ግን ትክክል ናቸው■
­
አዲስ
አዲስ
 
Posts: 32
Joined: Fri Jul 20, 2012 12:22 am

Re: ..

Postby ዘርዐይ ደረስ » Sat Apr 13, 2013 12:25 pm

ሰላም ቢትወደድ:-

ምነው የዚችኛዋ ጥያቄ መልስ ዘገየች? ነገሩን ሚዛናዊ ለማድረግ ሁሉንም አቅጣጫ መመልከቱ ባልከፋም ነበር::

የየትኛዋ ጥያቄ መልስ ነው የዘገየው?ግልጽ ብታደርገው::ማንኛውንም ነገር ሚዛናዊ በሆነ መልኩና ከተለያዩ አቅጣጫዎች ማየቱ እንዳልከው አስፈላጊ ነው::ሆኖም ግን ይህን ርእስ በከፈትኩበት ወቅት ግንቦት 7ና የተገነጠለው ኦነግ አብረው ለመስራት የተስማሙበት ሰሞን ነበር::ስለዚህም በተለይ ፓልቶክ ላይ በአንድ በኩል በሚኒሊክ ላይ ከፍተኛ የጥላቻ ፕሮፓጋንዳ ሲካሄድ የአጸፋ መልስ ግን መስጠት የሚቻልበት አጋጣሚ አልነበረም ማለት ይቻላል.::በኢትዮጵያዊነት እናምናለን የሚሉ አንዳንድ የፓልቶክ ሩሞች እንኳ ስለ ምኒሊክ መልካም ጎን የሚናገረውን ሁሉ ያዋክቡት ነበር::እንግዲህ ለጊዚያዊ የፖለቲካ ጥቅም ሲባል የምኒልክን አኩሪ ታሪክ መስዋዕት አድርጎ ማቅረብ አስፈላጎ መስሎ ታይቶ ይሆናል::እናም ሚዛናዊ የታሪክ ግምገማ እናድርግ ከተባለ ተቃራኒውም ወገን ዝግጁ መሆን አለበት እላለሁ::የአጼ ምኒሊክ ሠራዊት ሠርቷል የሚባለውን ግፍ ስናነሳ የአንዳንድ የኦሮሞ ባላባቶችና የደቡብ ገዢዎች የሠሩትንም መጠቃቀስ የሚያስፈልግ ይመስለኛል::

አንድ ቦታ ላይ እንደ አጼ ቴዲና አጼ ዮኒ በጉልበት ሳይሆን የሚል ነገር አንብቤያለሁ::

ይህን ያልኩት ሃይማኖትን በሚመልከቱ ጉዳይዮች ላይ ነው::

ውየው; አጼ ሚኒሊክ የደቡብ ሕዝቦች አልገዛም ሲሊ የእንስቶችን ጡት ሳይቀር አይደለም እንዴ እየቆረጡና እየገደሉ የግዛት አድማሳቸውን ያሰፉት?

እኔ በበኩሌ መደበኛ ትምህርት የጀመርኩትም ሆነ የጨረስኩት በደርግ ዘመን ስለሆነ አንተ የምትላቸው ታሪኮች የመጡት በህወሓት/ኢህአዴግ ዘመን ነውና አንተ በአዲሱ ሥርዓተ ትምህርት 'የታነጽክ' ልትሆን ትችላለህ ብዬ እገምታለሁ::በተጨማሪም የቤተሰብና የአካባቢ ተጽዕኖም ይኖራል::የምናነባቸው የታሪክ መጻሕፍትም ላለንና ለሚኖረን አስተሳሰብ ወሳኝ ናቸው::በድጋሚ ላሳስብ የምፈልገው ነገር ቢኖር ሚኒሊክን ማወዳደር ያለብን ከሳቸው በፊትና በሳቸው ጊዜ ከነበሩት መሪዎች ጋርና በወቅቱ በዓለም ላይ ከነበረው ተጨባጭ ሁኔታ አንጻር መሆን ያለበት ይመስለኛል::
''ፍምን እፍ ብትላት ትነዳለች ትፍም ብትልባት ትጠፋለች ሁለቱም ሁሉ ከአንድ አፍ ይወጣሉ ::''መጽሐፈ ሲራክ 28:12
ዘርዐይ ደረስ
ውሃ አጠጪ
ውሃ አጠጪ
 
Posts: 1089
Joined: Sat Oct 23, 2004 3:52 am
Location: ethiopia

Postby ዘርዐይ ደረስ » Sat Apr 13, 2013 1:22 pm

ሰላም ነጥቡ: :lol:

ዘርአይ ደረስ
ሚኒሊክን ምንም ንፁህ ሰው አድርገህ ለማቅረብ ብትሞክር ስልጣን ላይ ስለነበረ ባለስልጣን ሁሉ ወንጀለኛ ነው»

ከላይ ለቢትወደድ መልስ ስሰጥ እናዳልኩት የምኒሊክ ጠላቶች ሚዛናዊ መሆን እስካልቻሉ ድረስ ይህን ዓይነት ውይይት የሚያካሂድ ወገናዊነት ማሳየቱ የማይቀር ነው::በታሪክ ላይ እንደራደር ከተባለ አንዱ አቋሙን አለቅም ብሎ ሌላው compromise እንዲያደርግ መጠበቅ አግባብ አይመስለኝም::

ይሄ ሰውዬ እንደ መለስ ዜናዊ ሁሉ እጁ በደም የታጠበ ነው አማራ ስለሆነ አይደለም መለስም ትግሬ ስለሆነ አይደለም■ ሁለቱም ባለስልጣኖችና የስልጣን ጥም ያለባቸው ግለሰቦች ናቸው■ በስልጣን ለመቆየት ሲሊ አስፈላጊ መስሎ ከታያቸው የራሳቸውን ህዝቦች ክማረድ አይመለሱም■

መለስ ዜናዊ ለመከፋፈል አጼ ምኒልክ ደግሞ አንድ ለማድረግ ባደረጉት ትግል የበርካታ ኢትዮጵያውያን ህይወት መጥፋቱ የሚካድ አይደለም::

ይሄንን ነገር ለመረዳት ከህዝብ ጋር መቆም አለብህ ከባለስልጣንና ከፊውዳሉ ወገን ከሆንክ ግን የማወራው በፍፁም አይገባህም■

ከየትኛው ሕዝብ ጎን ነው የምቆመው?በምኒሊክ ጉዳይ ላይ እኮ 'ሕዝቡ' አንድ አቋም የለውም::አንተ እንደምትለውም የምኒሊክ ደጋፊ ሁሉ 'ከባለሥልጣንና' 'ከፊውዳሉ' ወገን አይደለም::የሚቃወማቸው ሁሉም 'ግፍ የደረሰበትና' 'የተጨቆነው' የሚባለው የኅብረተሰብ ክፍል ብቻ አይደለም::

■■■■መለስ ታላቁ መሪ እየተባለ በሚሞካሽበት ዘመን ላይ ነን አዋ እውነት ነው መለስ ጥሩ መሪ ነው ለህዝቡ ለሚመራው ለተዋጋለት ህዝብ ግሩም መሪ ነው■■■■ ለኔ ግን አይደለም ሆኖም አያውቅም

መለስ እኮ በኛው ዘመን የነበረ ስለሆነ ስለሱ የማናውቀው ነገር ጥቂት ነው::ስለዚህ ለመደገፍም ሆነ ለመቃወም በቂ መረጃ አለን::

ሚኒሊክም ለተወሰነ ሰው ጥሩ ነው ለኔ አባቶች ግን ጥሩ ሰው አልነበረም ስለዚህ ያንተን ጌታ በግድ ውደደው አትበለኝ■ላንተ ጮማ ሲያጎርስ ለሌላው ጡት ሲቆርጥና ሲጨፈጭፍ የነበረ አረመኔ ነው■

አጼ ምኒሊክን በሚመለከት ያሉን መረጃዎች የተዛቡ ይመስለኛል::የጊዜው ርቀትና የዓለም ሁኔታ መቀየሩ ለዚህ ብዥታ ከሚጠቀሱ ምክንያቶች አንዳንዶቹ ናቸው::በነገራችን ላይ የአጼ ምኒሊክ ዘመን በከፊል ለሁሉም ሕዝብ የጦርነት የመከራና የችግር ጊዜ ለመሆኑ ታሪክ የሚያወሳው ነው::እሳቸውን ተከትለው የመጡት ነገሥታት ግን አንጻራዊ ሰላምና ብልጽግና ባለበት ተጨባጭ ሁኔታ የህዝቡን ኑሮ ብዙም አላሻሻሉትም::

ስለ ሂትለርም ብናወራ በእርግጠኝነት ብዙ ስራ ሰርቷል ችግሩ ግን ለጀርመኖች ታላቅ መሪ የነበረ ቢሆንም ለይሁዳዊያን ግን ይሄንን ብትነግራቸው ሊጣሉህ ሁሉ ይችላሉ■በልዩነታችን እንኑር ያንተ ሂሮ ለኔ ዜሮ እንደሆነ መረዳት አለብህ■

ከምኒሊክ ተቃዋሚዎች ጋር ለመደራደር አስቸጋሪ የሚሆነው ምኒልክን በሰው ልጅ ታሪክ ውስጥ በጨካኝነታቸው ወደር ከማይገኝላቸው ከሂትለር ግራዚያኒና ከመሳሰሉት ጋር ለማወዳደር ስለሚሞክሩ ነው::

ለዚህም ነው ወያኔዎች መለስ እኮ ጥሩ ነው መለስ እኮ ነብይ ነው ሲሉን አልቀየማቸውም ምክንያቱን በእውነት መለስ ጥሩ ሰው ነበር ለህዝቡ■ ስለዚህ ውሸታቸውን እንዳይመስልህ ሲያሞግሱት they really believe that የኔን መጎዳት ግን እኔና ወገኖቼ እንጂ ማንም አያውቅም የዛሬ መቶ አመት ታዲያ የትግሬው ልጅ መለስን እንደ ሀይለሥላሤ ሲያመልከው የኔ ልጅ ግን የኔን ቁስል ነው የሚናገረው■ ሁለቱም ግን ትክክል ናቸው■

መለስ ለሕዝቡ ጥሩ ነበር ስትል ለየትኛው ሕዝብ ማለትህ እንደሆነ ግልጽ ብታደርግልኝ?
''ፍምን እፍ ብትላት ትነዳለች ትፍም ብትልባት ትጠፋለች ሁለቱም ሁሉ ከአንድ አፍ ይወጣሉ ::''መጽሐፈ ሲራክ 28:12
ዘርዐይ ደረስ
ውሃ አጠጪ
ውሃ አጠጪ
 
Posts: 1089
Joined: Sat Oct 23, 2004 3:52 am
Location: ethiopia

Postby ኮኮቴ » Sat Apr 13, 2013 2:22 pm

ሰላም ወንድሜ ዘርዐይ ደረስ

ወያኔ ኢህአዴግ ወደ ስልጣን ከመጣ ጀመሮ በከፍተኛ ደረጃ የጥላቻ ፕሮፓጋንዳ ኢላማ ከሆኑት መሪዎች መካከል እምዬ ሚኒሊክ ዋነኛው ናቸው:: አልፎ ተርፎም በእርሳቸው ስም በሚጠራው ቤተ መንግስት ውስጥ ስልጣን ላይ ተቀምጦ የነበረው መለስ እንኮአን ሳይቀር ንጉሱ ለሀገራችን ያበረከቱትን መልካም ተግባራት እያኮሰሰ ሲናገር ተሰማ::

ሰሞኑን ደግሞ የዋርካዎቹ ጉዶች 'ሚኒሊክ እያለ የግራዚያኒ ስም ለምን ይወገዛል' የሚል ሀሳብ በድፍረት ይዘው ብቅ አሉ:: ታዲያ እንዲህ አሳፋሪ ነገሮች በሚታዩበት ግዜ አንተ ከረጅም ግዜ በፊት ከፍተሀት የነበረችዋ የመወያያ ርእስ ነፍስ ዘርታ ሰዎችን ግራ እና ቀኝ ስታወያይ በማየቴ ደስ ብሎኛል::

ሁላችንም እንደምናውቀው አንዳንዶቹ አውቆ አጥፊዎች ... ሰሞኑን ከሚሰሙት አሳሳቢ ጉዳዮች የሰዉን ሀሳብ ለመስረቅ ሲሉ አሳፋሪ ርእስ ያላቸው ቤቶች ሲከፍቱ ማየት የተለመደ ሆኗል:: እነዚህ አውቆ አጥፊዎች ምናልባት በእጃቸው ጸረ-ሚኒሊክ ጽሁፍ የሚጽፉት የቴዲ አፍሮን "ጥቁር ሰው" ሙዚቃ እየሰሙ ሊሆን ይችላል :lol:

ለማንኛውም በስተመጨረሻው ለነ ሌንጮ ለታ ማስተዋልን የሰጠ አምላክ እነዚህንም አውቆ አጥፊዎች ያስባቸው እላለሁ::

መልካም የእረፍት ቀን

ኮኮቴ

ዘርዐይ ደረስ wrote:ሰላም ነጥቡ: :lol:

ዘርአይ ደረስ
ሚኒሊክን ምንም ንፁህ ሰው አድርገህ ለማቅረብ ብትሞክር ስልጣን ላይ ስለነበረ ባለስልጣን ሁሉ ወንጀለኛ ነው»

ከላይ ለቢትወደድ መልስ ስሰጥ እናዳልኩት የምኒሊክ ጠላቶች ሚዛናዊ መሆን እስካልቻሉ ድረስ ይህን ዓይነት ውይይት የሚያካሂድ ወገናዊነት ማሳየቱ የማይቀር ነው::በታሪክ ላይ እንደራደር ከተባለ አንዱ አቋሙን አለቅም ብሎ ሌላው compromise እንዲያደርግ መጠበቅ አግባብ አይመስለኝም::

ይሄ ሰውዬ እንደ መለስ ዜናዊ ሁሉ እጁ በደም የታጠበ ነው አማራ ስለሆነ አይደለም መለስም ትግሬ ስለሆነ አይደለም■ ሁለቱም ባለስልጣኖችና የስልጣን ጥም ያለባቸው ግለሰቦች ናቸው■ በስልጣን ለመቆየት ሲሊ አስፈላጊ መስሎ ከታያቸው የራሳቸውን ህዝቦች ክማረድ አይመለሱም■

መለስ ዜናዊ ለመከፋፈል አጼ ምኒልክ ደግሞ አንድ ለማድረግ ባደረጉት ትግል የበርካታ ኢትዮጵያውያን ህይወት መጥፋቱ የሚካድ አይደለም::

ይሄንን ነገር ለመረዳት ከህዝብ ጋር መቆም አለብህ ከባለስልጣንና ከፊውዳሉ ወገን ከሆንክ ግን የማወራው በፍፁም አይገባህም■

ከየትኛው ሕዝብ ጎን ነው የምቆመው?በምኒሊክ ጉዳይ ላይ እኮ 'ሕዝቡ' አንድ አቋም የለውም::አንተ እንደምትለውም የምኒሊክ ደጋፊ ሁሉ 'ከባለሥልጣንና' 'ከፊውዳሉ' ወገን አይደለም::የሚቃወማቸው ሁሉም 'ግፍ የደረሰበትና' 'የተጨቆነው' የሚባለው የኅብረተሰብ ክፍል ብቻ አይደለም::

■■■■መለስ ታላቁ መሪ እየተባለ በሚሞካሽበት ዘመን ላይ ነን አዋ እውነት ነው መለስ ጥሩ መሪ ነው ለህዝቡ ለሚመራው ለተዋጋለት ህዝብ ግሩም መሪ ነው■■■■ ለኔ ግን አይደለም ሆኖም አያውቅም

መለስ እኮ በኛው ዘመን የነበረ ስለሆነ ስለሱ የማናውቀው ነገር ጥቂት ነው::ስለዚህ ለመደገፍም ሆነ ለመቃወም በቂ መረጃ አለን::

ሚኒሊክም ለተወሰነ ሰው ጥሩ ነው ለኔ አባቶች ግን ጥሩ ሰው አልነበረም ስለዚህ ያንተን ጌታ በግድ ውደደው አትበለኝ■ላንተ ጮማ ሲያጎርስ ለሌላው ጡት ሲቆርጥና ሲጨፈጭፍ የነበረ አረመኔ ነው■

አጼ ምኒሊክን በሚመለከት ያሉን መረጃዎች የተዛቡ ይመስለኛል::የጊዜው ርቀትና የዓለም ሁኔታ መቀየሩ ለዚህ ብዥታ ከሚጠቀሱ ምክንያቶች አንዳንዶቹ ናቸው::በነገራችን ላይ የአጼ ምኒሊክ ዘመን በከፊል ለሁሉም ሕዝብ የጦርነት የመከራና የችግር ጊዜ ለመሆኑ ታሪክ የሚያወሳው ነው::እሳቸውን ተከትለው የመጡት ነገሥታት ግን አንጻራዊ ሰላምና ብልጽግና ባለበት ተጨባጭ ሁኔታ የህዝቡን ኑሮ ብዙም አላሻሻሉትም::

ስለ ሂትለርም ብናወራ በእርግጠኝነት ብዙ ስራ ሰርቷል ችግሩ ግን ለጀርመኖች ታላቅ መሪ የነበረ ቢሆንም ለይሁዳዊያን ግን ይሄንን ብትነግራቸው ሊጣሉህ ሁሉ ይችላሉ■በልዩነታችን እንኑር ያንተ ሂሮ ለኔ ዜሮ እንደሆነ መረዳት አለብህ■

ከምኒሊክ ተቃዋሚዎች ጋር ለመደራደር አስቸጋሪ የሚሆነው ምኒልክን በሰው ልጅ ታሪክ ውስጥ በጨካኝነታቸው ወደር ከማይገኝላቸው ከሂትለር ግራዚያኒና ከመሳሰሉት ጋር ለማወዳደር ስለሚሞክሩ ነው::

ለዚህም ነው ወያኔዎች መለስ እኮ ጥሩ ነው መለስ እኮ ነብይ ነው ሲሉን አልቀየማቸውም ምክንያቱን በእውነት መለስ ጥሩ ሰው ነበር ለህዝቡ■ ስለዚህ ውሸታቸውን እንዳይመስልህ ሲያሞግሱት they really believe that የኔን መጎዳት ግን እኔና ወገኖቼ እንጂ ማንም አያውቅም የዛሬ መቶ አመት ታዲያ የትግሬው ልጅ መለስን እንደ ሀይለሥላሤ ሲያመልከው የኔ ልጅ ግን የኔን ቁስል ነው የሚናገረው■ ሁለቱም ግን ትክክል ናቸው■

መለስ ለሕዝቡ ጥሩ ነበር ስትል ለየትኛው ሕዝብ ማለትህ እንደሆነ ግልጽ ብታደርግልኝ?
o-o-o-o-o-o-o-o-o-o-o-o
".... Indeed, we Ethiopians are a beautiful multi-lingual and multi-cultural people who in a flower vase called Ethiopia decorate the great continent of Africa", Professor Ephraim Isaac
ኮኮቴ
ውሃ አጠጪ
ውሃ አጠጪ
 
Posts: 1289
Joined: Wed Nov 04, 2009 2:07 am

Postby ዘርዐይ ደረስ » Wed Apr 17, 2013 6:16 pm

ሰላም ወንድማችን(የነ ተድላ እህት :lol:) ኮኮቴ:-

ወያኔ ኢህአዴግ ወደ ስልጣን ከመጣ ጀመሮ በከፍተኛ ደረጃ የጥላቻ ፕሮፓጋንዳ ኢላማ ከሆኑት መሪዎች መካከል እምዬ ሚኒሊክ ዋነኛው ናቸው::

መች በፕሮፓጋንዳ ብቻ አቆሙ?ወኔያቸው ገና ባልከዳቸው ኢትዮጵያውያን ባይከሽፍ ኖሮ ሐውልታቸውን ለማፍረስ ተምክሮ ነበር እኮ!ከዚያም አልፎ በበደኖ በወተር በአሰቦት ገዳም በአርባ ጉጉና በሌሎችም ቦታዎች የጅምላ ጭፍጨ(genocide) ሰለባ የሆኑት ወገኖች እኮ ራሳቸው የሰሩት በደል ኖሮ ሳይሆን ካለፉት ነገሥታት(በተለይም አፄ ምኒሊክ) ጋር የተያያዘ ነው::

አልፎ ተርፎም በእርሳቸው ስም በሚጠራው ቤተ መንግስት ውስጥ ስልጣን ላይ ተቀምጦ የነበረው መለስ እንኮአን ሳይቀር ንጉሱ ለሀገራችን ያበረከቱትን መልካም ተግባራት እያኮሰሰ ሲናገር ተሰማ::

ከዓለምም ሆነ ከአገራችን ታሪክ እንደምንረዳው ትንንሽ ሰዎች ራሳቸውን በሥራቸው አጉልተው ማሳየት ስለሚሳናቸው የታላላቆቹን መሪዎች ግዙፍ ስብዕና በማንኳሰስ ጎልተው ለመታየት ቢሞክሩና ለጊዜውም ቢሆን የጥቂት አጨብጫቢዎቻቸውን ቀልብ ለመሳብ ቢችሉም ይህ 'ዝናቸው' ዘላቂነት የለውም::

ሰሞኑን ደግሞ የዋርካዎቹ ጉዶች 'ሚኒሊክ እያለ የግራዚያኒ ስም ለምን ይወገዛል' የሚል ሀሳብ በድፍረት ይዘው ብቅ አሉ:: ታዲያ እንዲህ አሳፋሪ ነገሮች በሚታዩበት ግዜ አንተ ከረጅም ግዜ በፊት ከፍተሀት የነበረችዋ የመወያያ ርእስ ነፍስ ዘርታ ሰዎችን ግራ እና ቀኝ ስታወያይ በማየቴ ደስ ብሎኛል::

አዎ ሰዎቹ ካፈርኩ አይመልሰኝ ያሉ ይመስላል::እኔም ይህን ርእስ ከተደበቀበት ያመጣሁት በእነሱ ምክንያት ነበር:: በጅምላ ከመወንጀልና ከመሳደብ ውጭ ነጥብ በነጥብ መከራከር የሚችሉ ዓይነት አይመስሉም::

ሁላችንም እንደምናውቀው አንዳንዶቹ አውቆ አጥፊዎች ... ሰሞኑን ከሚሰሙት አሳሳቢ ጉዳዮች የሰዉን ሀሳብ ለመስረቅ ሲሉ አሳፋሪ ርእስ ያላቸው ቤቶች ሲከፍቱ ማየት የተለመደ ሆኗል:: እነዚህ አውቆ አጥፊዎች ምናልባት በእጃቸው ጸረ-ሚኒሊክ ጽሁፍ የሚጽፉት የቴዲ አፍሮን "ጥቁር ሰው" ሙዚቃ እየሰሙ ሊሆን ይችላል :lol:

ትክክል ነው ብዙ ጊዜ ያለፈውን ታሪክ የሚያነሱት ከአንገብጋቢው ወቅታዊ ጉዳይ ለማዘናጋት ነው::እንዳልከው 'ጥቁር ሰውን' እየሰሙ ይሆናል :lol: ቢሆንም ግን ለሙዚቃው ሲሉ እንጂ መልዕክቱ ቢገባቸው የሚደግሙት አይመስለኝም::

ለማንኛውም በስተመጨረሻው ለነ ሌንጮ ለታ ማስተዋልን የሰጠ አምላክ እነዚህንም አውቆ አጥፊዎች ያስባቸው እላለሁ::

ኮኮቴ:-የነ ሌንጮ ጉዳይ እንኳ ግልፅ አልሆነልኝም::በተለይ የዶ/ር ዲማ ነገዎን ቃለ ምልልስ ከሰማሁ በኋላ የድርጅቱ ዓላማ ግራ አጋብቶኛል::ስለ ድርጅቱ የምታውቀው ተስፋ የሚጣልበት ነገር ካለ በሌላ ርእስ ብታጫውተን ጥሩ ነው::
''ፍምን እፍ ብትላት ትነዳለች ትፍም ብትልባት ትጠፋለች ሁለቱም ሁሉ ከአንድ አፍ ይወጣሉ ::''መጽሐፈ ሲራክ 28:12
ዘርዐይ ደረስ
ውሃ አጠጪ
ውሃ አጠጪ
 
Posts: 1089
Joined: Sat Oct 23, 2004 3:52 am
Location: ethiopia

Postby ኮኮቴ » Wed Apr 17, 2013 9:36 pm

ሰላም ወንድማችን ዘርዓይ ደረስ

እነ ሌንጮ አቆአማቸውን ግዜ ወስደው ... ሳያምታቱ ሳያደናብሩ ጥርት አድርገው እንደሚያስረዱ ተስፋ አደርጋለሁ::

ባለፈው ቅዳሜ ዶ/ር በያን ከአበበ በለው ጋር በአደረግው ቃለ ምልልስ ላይ 'ጊዜያችንን ያለፈ ታሪክ እያነሳን በመወቃቀስ ማጥፋት የለብንም ... አሁን ማሰብ ያለብን ስለወደፊቷ ኢትዮጵያ ነው' ሲል ሰምቸው በዚህ አባባሉ ተደስቼ ነው ... 'ለእነ ሌልጮ ለታ ማስተዋልን የሰጠ ...' ያልኩት::

ያው ወራጅ ውሀ እና የኢትዮጵያ ፖለቲካ እያደር ስለሆነ የሚጠራው .... ታግሰን ማየት ነው: የሚሆነውን ነገር :)

መልካም ግዜ ለሁላችንም

ኮኮቴ

ዘርዐይ ደረስ wrote:ሰላም ወንድማችን(የነ ተድላ እህት :lol:) ኮኮቴ:-ለማንኛውም በስተመጨረሻው ለነ ሌንጮ ለታ ማስተዋልን የሰጠ አምላክ እነዚህንም አውቆ አጥፊዎች ያስባቸው እላለሁ::

ኮኮቴ:-የነ ሌንጮ ጉዳይ እንኳ ግልፅ አልሆነልኝም::በተለይ የዶ/ር ዲማ ነገዎን ቃለ ምልልስ ከሰማሁ በኋላ የድርጅቱ ዓላማ ግራ አጋብቶኛል::ስለ ድርጅቱ የምታውቀው ተስፋ የሚጣልበት ነገር ካለ በሌላ ርእስ ብታጫውተን ጥሩ ነው::
o-o-o-o-o-o-o-o-o-o-o-o
".... Indeed, we Ethiopians are a beautiful multi-lingual and multi-cultural people who in a flower vase called Ethiopia decorate the great continent of Africa", Professor Ephraim Isaac
ኮኮቴ
ውሃ አጠጪ
ውሃ አጠጪ
 
Posts: 1289
Joined: Wed Nov 04, 2009 2:07 am

Re: ዳግማዊ አፄ ምኒሊክ(1836-1906)(1881-1906)

Postby ዘርዐይ ደረስ » Wed May 10, 2017 2:47 pm

ይህንን ርእስ እንዳስታውስ ያደረገኝ ከ10 ዓመታት በፊት አቶ አሰፋ ጫቦ ስለ አጼ ምኒልክ የጻፉት ነው::እንደ እሳቸው አባባል አጼ ምኒልክ በምንም ዓይነት የኦሮሞና የደቡብ ህዝቦች ጀግና ሊሆኑ አይችሉም::በወቅቱ አንድ ጸሐፊ የአቶ አሰፋ አድናቂ እንደነበርና በዚህ አባባላቸው ግን እንደተበሳጨ ካሳወቀ በኋላ አጼ ምኒልክ በኢትዮጵያ ምድር ላይ ባይነሱ ኖሮ የነአሰፋ እናቶች ዕጣ ፈንታ ባርነት እንደሚሆን ተናግሮ እንደነበር አስትውሳለሁ::አቶ አሰፋም በዚህ አባባሉ ተበሳጭተው ስለ ባርነት ጽንሰ ሃሳብ መልስ ሰጥተዋል::በነገራችን ላይ አቶ አሰፋ ፕሮፌሰር አስራት ወልደየስንም ጀግና ከተባሉ የአማራ እንጂ የኢትዮጵያ ሊሆኑ እንደማይችሉ ገልጸው ነበር::የፕሮፌሰር አስራትን ወደ ጎን ትቼ አንድ ከኔ በላይ ኢትዮጵያን የሚወድ ያለ አይመስለኝም የሚል ሰው እንዴት ለአጼ ምኒልክ ያን የመሰል አመለካከት ሊኖረው ይችላል?ብዬ ተገረምኩ::
''ፍምን እፍ ብትላት ትነዳለች ትፍም ብትልባት ትጠፋለች ሁለቱም ሁሉ ከአንድ አፍ ይወጣሉ ::''መጽሐፈ ሲራክ 28:12
ዘርዐይ ደረስ
ውሃ አጠጪ
ውሃ አጠጪ
 
Posts: 1089
Joined: Sat Oct 23, 2004 3:52 am
Location: ethiopia

Next

Return to Warka Politics - ዋርካ ፖለቲካ

Who is online

Users browsing this forum: No registered users and 2 guests