የቄስ ዘመድኩን ክርስትና ግራ የገባው እምነት

Issues and Articles of General Interests including topics related to religion

የቄስ ዘመድኩን ክርስትና ግራ የገባው እምነት

Postby መርፊው » Mon Apr 15, 2013 6:30 pm

መጽሐፍ ‹ቅዱስ› በመባል የሚታወቀው የክርስትያኖች የእምነት መጽሐፍ ሁለት ዋናዋና ክፍሎች አሉት፡፡ ብሉይ ኪዳንና አዲስ ኪዳን፡፡ በክርስትያኖች ዘንድ ብሉይ ኪዳን በነብያት አማካይነት ለእስራኤላውያን የተሰጠ መጽሐፍ እንደሆነ ሲገመት፣ አዲስ ኪዳን በሐዋሪያት አማካይነት በመንፈስ ቅዱስ መሪነት የተጻፈ እንደሆነ ተደርጎ በዘልማድ ይታመናል፡፡በእርግጥ ይህን የዘልማድ እምነት የሚያፈራርሱ የክርስትያን ምሁራን ጥናቶች ይፋ መሆን ከጀመሩ ውለው አድረዋል፡፡

ብሉይ ኪዳን 39 ያህል መጽሐፍትን በውስጡ ያካተተ ሲሆን አዲስ ኪዳን 27 መጽሐፍትን ይዟል፡፡ ድምራቸው 66 መሆኑ ነው፡፡ ካቶሊኮች 7 መጽሐፍትን በማከል የመጽሐፍቱን ብዛት ወደ 73 ከፍ ያደርጉታል፡፡ ኦርቶዶክሶች ደግሞ ሌሎች 8 ትርፍ (አዋልድ) መጽሐፍትን በመጨመር ወደ 81 ያሳድጉታል፡፡ ቁጥሩ በዚህ ብቻ የሚገደብ አይደለም፡፡ በተለይም በሃገራችን መጽሐፈ ዚቅ፣ እንደ ሰኔ ጉልጉታና መጽሐፈ ባልቴት የመሳሰሉ በኢትዮጵያን ደራሲያን የተጻፉ መጽሐፍትም ቅዱሳን ተሰኝተው የዚሁ መጽሐፍ አካል የሚሆኑበትን ሁኔታ የሚያመለክቱ ፍንጮች እየታዩ ነው፡፡ ይህ ሁኔታ ያሰጋቸው የኦርቶዶክስ ቄስ አለማየሁ ሞገስ እንዲህ ሲሉ ምሬታቸውን ገልጸዋል፡-

‹ዛሬ ዓለም ሁሉ በቀድሞው ዘመን ባለመግባባት የተነጣጠሉ አብያተ ክርስትያናት ሁሉ በሐይማኖት ካልሆነ በስርዓት የተለያዩት ሁሉ ለመገናኘት በሚጥሩበት ጊዜ በሁለት ባህሪ ምክንያት ያልነበረ እያወራችሁ ልዩነትን በልበ ንጹሐን የምትተክሉ፣ ሰማንያ አሐዱ መጽሐፍትን ገድላገድሉን ሁሉ ጨምራችሁ ከ83፡ 89 ያገባችሁ፣ ቃለ እግዚአብሔርን ከናንተ ሐሳብ ጋር ካልተስማማ ስትደልዙና ስትሰርዙ የማታፍሩ ሰዎች ምናችሁ ክርስትያን ናችሁ ተብሎ ይመሰከርላችኋል?› (1)

እንዲህ ሲሉም አክለዋል፡-

‹ከቀድሞ ጀምሮ በፈትሐ ነገስቱ የታዘዘው የ81 መጽሐፍት ቁጥር ይህ ሲሆን፣ አሁን ግን በግእዝ የተጻፉ አዋልድና ሊቃውንት ለምን ይቀራሉ ብለው ነው መሰለኝ በ1980 በሲኖዶሱ ፍቃድ በኢትዮጵያ መጽሐፍ ቅዱስ ማሕበር አሳታሚነት የታተመው መጽሐፍ ‹ቅዱስ› 93 ደርሷል፡፡ በዚሁ እትም ላይም ሌላም አሻሽለን እንጨምራለን ብለው ቃል ስለገቡ፣ እነ ሰይፈ መለኮት፣ እነ ሰኔ ጎልጎታ፣ እነ አጋኖርን፣ እነ ውዳሴ አምላክ ወዘተ የመሳሰሉትም ቢሆን እንደሚጨመሩ ባለሙሉ ተስፋ ነኝ፡፡ መጽሐፈ ባልቴትስ ቢሆን ከልፋፈ ጽድቅ ጋራ በገዛ ሐገሩ ቢጨመር ምን አለበት?› (2)

ኘሮቴስታንት፣ ካቶሊክና ኦርቶዶክስ የክርስትና አንጃዎች እያንዳንዳቸው፡- «ትክክለኛው መጽሐፍ ቅዱስ የኔ ነው፡፡ ሌሎች ጨምረዋል ወይም ቀንሰዋል» በማለት ይከራከራሉ፡፡ ለምሳሌ በኘሮቴስታንቶች እምነት ካቶሊኮችና ኦርቶዶክሶች ከአምላክ ቃል ሊታከሉ የማይገባቸውን መጽሐፍት ከመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ በማካተት የመጨመር ግድፈት ፈጽመዋል፡፡ በካቶሊኮች እምነት ኘሮቴስታንቶች ከአምላክ ቃል የተወሰነውን ክፍል የቀነሱ ሲሆን ኦርቶዶክሶች ደግሞ መጨመር የማይገባቸውን የርሱ ቃል ያልሆኑ መጽሐፍ ጨምረዋል፡፡ በኦርቶዶክሶች እምነት ካቶሊኮችም ሆኑ ኘሮቴስታንቶች የአምላክን ቃል ቀንሰዋል፡፡ የሚገርመው ግን ሁሉም አንጃዎች ‹መጽሐፍ ቅዱስ አልተጨመረም አልተቀነሰም› በማለት ሽንጣቸውን ገትረው ይሟገታሉ፡፡ ... ይቀጥላል

መርፊው ዘ_ነገደ የሁዳ
Last edited by መርፊው on Wed Jun 05, 2013 8:40 pm, edited 2 times in total.
መርፊው
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 260
Joined: Sat Oct 15, 2011 4:22 pm

Postby መርፊው » Fri Apr 19, 2013 8:26 pm

የዮሃንስ ወንጌል ማን ጻፈው?:- :-

ወንጌላዊውን ዮሃንስ በተመለከተ ምሁራን
ወንጌልን የጻፈው ዮሃንስ የ እየሱስ ደቀመዝሙር የነበረው ዮሃንስ አይደለም
ይላሉ ።

ተንታኞች እንደሚናገሩት የዮሃንስ ወንጌል ይዘት እና የቃላት አጠቃቀሙ
ሲታይ በእየሱስ ሃዋርያው ዮሃንስ የተጻፈ ሊሆን አይችልም ።

የሆነ ሰው ጽፎት
የበለጠ ተአማኒነት ለማሰጠት ከሃዋርያው ዮሃንስ ጋር አያይዞታል ። ወንጌሉ የተጻፈው በ 97 ዓ .ክ አካባቢ ማለትም ከ እየሱስ
መሰወር ስልሳ አራት(64) አመታት ቡሃላ
መሆኑን ምሁራን ያረጋግጣሉ።

ኢየሱስ ሲሰወር ዮሃንስ እድሜው ሃያ(20) አመት ብቻ ነበር ።

ቢባል ወንጌሉ በተጻፈበት ጊዜ
እድሜው በትንሹ ሰማንያ አራት አመት
ነው ።

ታድያ ሃዋርያው ዮሃንስ ወንጌሉን ለመጻፍ
እድሜው 84 አመት እስኪሆን ድረስ
መቆየት ለምን አስፈለገው ?

ስራውን ለመጀመር 64 አመት ሙሉ ምን
አስጠበቀው ፧

ይህ የዩሃንስ ወንጌል
በሃዋርያው ዮሃንስ አልተጻፈም የሚለውን
ማጠቃለያ ያረጋግጣል ።
መርፊው
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 260
Joined: Sat Oct 15, 2011 4:22 pm

Postby መርፊው » Sun Apr 21, 2013 12:52 am

ኢየሱስ ከሰራቸው ሀጥያቶች ውስጥ ነጥረው የወጡትን እንመለከታለን(ለዚህ ፅሁፍ ሁለቱን ብቻ ለማየት እንገደዳለን)!

1. ስድብ
<<ስድብ? ይህ ነው ታድያ ትልቁ ወንጀል?›› የሚል ጥያቄ መነሳቱ አይቀርም፤ አግባብም ነው፡፡ አዎን! በመጽሃፍ ቅዱስ መሰረት ስድብ እጅግ በጣም ከባድ ከሚባሉት ወንጀሎች ውስጥ ይካተታል!
‹‹ ለቀደሙት አትግደል እንደተባለ ሰምታችኋል፤ የገደለም ሁሉ ፍርድ ይገባዋል፡፡ እኔ ግን እላችኋለሁ፤ በወንድሙ ላይ የሚቆጣ ሁሉ ፍርድ ይገባዋል፤ ወንድሙንም ጨርቅ ለባሽ የሚለው ሁሉ የሸንጎ ፍርድ ይገባዋል፤ ደንቆሮ የሚለውም ሁሉ የገሃነም እሳት ፍርድ ይገባዋል…››(ማቴ 5፤21-23)

ሆኖም ኢየሱስ በማቴዎስ ወንጌል ብቻ በደርዘን ለሚቆጠሩ ግዜያት ይህንን ህግ በጠራራ ፀሀይ መተላለፉ ተዘግቧል፡፡ ለአብነት ያክል የተወሰኑት እንመልከት፡፡

ሀ. ትውልዱን በሙሉ(እሱና ብጽእቱን እናቱን ጨምሮ) በመዝለፍ
‹‹ ክፉና አመንዝራ ትውልድ..›› (ማቴ 12፤38…)
‹‹ እናንተ የማታምን ጠማማ ትውልድ..›› (ሉቃ 9፤41)
ለ. ጻፎችንና ፈሪሳውያንን በመነጠል
‹‹እናንተ ግብዞች..›› (ማቴ 23፤13 23፤16 23፤23 23፤25 23፤27 23፤29...)
‹‹እናንተ ደንቆሮዎችና ዕውሮች…›› (ማቴ 23፤17 23፤19)
‹‹ እናንተ እባቦች፤ የእፉኝ ልጆች..›› (ማቴ 23፤33)
ሐ. ግለሰቦችን በመነጠል
‹‹ አንተ እውር ፈሪሳዊ.. ›› (ማቴ 23፤26)
‹‹ ጴጥሮስን፡- ወደ ኋላዬ ሂድ አንተ ሰይጣን፤ የሰውን እንጂ የእግዚአብሄርን አታስብምና እንቅፋት ሆነህብኛል..›› (ማቴ 16፤23)

ከላይ በሰፈሩት ጥቅሶች መሰረት፤ ኢየሱስ ከባድ ወንጀል መፈፀሙን እንረዳለን፤ ያውም ገሀነም ሊያስገባ የሚያስችል፡፡ ታድያ ይህ ድግስ ተደግሶ፤ እንዴት ኢየሱስን ከሃጥያት ነፃ ነው ልንል እንችላለን? መልሱን ለአንባቢያን እተዋለሁ፡፡ ነገር ግን ክርስትያን ወንድሞች ይህንን እንቆቅልሽ (puzzle) ለመፍታት የተለያዩ ማምለጫዎችን ለማቅረብ ሞክረዋል፤ እስኪ አንድ በአንድ እንመልከታቸው፡፡

A. ስድብ የተከለከለው ‹‹ለሃይማኖት ወንድም›› እንጂ ለሌላውማ ምን ችግር አለው፡

የማቴዎስ ወንጌል ላይ ‹‹ ለቀደሙት አትግደል እንደተባለ ሰምታችኋል፤ የገደለም ሁሉ ፍርድ ይገባዋል፡፡ እኔ ግን እላችኋለሁ፤ በወንድሙ ላይ የሚቆጣ ሁሉ ፍርድ ይገባዋል፤ ወንድሙንም ጨርቅ ለባሽ የሚለው ሁሉ የሸንጎ ፍርድ ይገባዋል፤ ደንቆሮ የሚለውም ሁሉ የገሃነም እሳት ፍርድ ይገባዋል…›› የሚለውን ጥቅስ እናያለን፡፡ ኢየሱስ በዚህ ጥቅስ መሰረት መግደልንም፤ መሳደብንም በማያሻማ ቋንቋ ከልክሏል፡፡ የሃይማኖት ወንድምን ብቻ ነው የከለከለው የምንል ከሆነ፤ ሌሎች ፈርጀ ብዙ ህግጋት መናዱ አይቀሬ ነው የሚሆነው፡፡ ‹‹በመጀመርያ ደረጃ አትግደል የተባለው ማንን ነው?›› ለሚለው ጥያቄ መልስ ሊበጅለት የግድ ነው፡፡ ‹‹ለቀደሙት አትግደል›› የተባለው የኦሪት ህግ ማንን ነው የሚመለከተው? ለአማኞት ብቻ ነው ብለን መልስ በመስጠት ለጊዜው ለማምለጥ እንችል ይሆናል፤ ነገር ግን ሌላ መዘዝ ይዞብን ከተፍ ይላል፡፡ ይህ ህግ በአዲስ ኪዳን መቀጠሉን ከላይ በጠቀስነው አንቀፅ ላይ ተመልክተናል፡፡ በመሆኑም እንደ ክርስትና እምነት መሰረት ‹‹አትግደል›› የሚለው ህግ ለአማኞች ብቻ የተገደበ ነው እንድንል ያስገድደናል፡፡ ከዚህም አልፎ ተርፎ በየመንገዱ የምታገኘውን የሌላ እምነት ተከታይ መስደብም ይፈቀዳል እንደማለት ነው፡፡

ስለዚህ ለክርስትያን ወንድሞቻችን ሁለት ምርጫ ቀርቧል ማለት ነው፡፡ አንደኛው፤ አማኝ ያልሆነን መግደልም ሆነ መስደብ ይቻላል፤ በመሆኑም ኢየሱስ በመሳደቡ ወንጀል አልሰራም፡፡ ሁለተኛው ደግሞ የሌላ እምነት ተከታይን መግደልም ሆነ መስደብ አይፈቀድም፤ ነገር ግን ኢየሱስ ይህንን ህግ ጥሷል፡፡ ምርጫውን እንተውላቸዋለን፡፡ ደግሞም ለሃይማኖት ወንድም ነው ለማለት በቂ መረጃ ማቅረብ ግዴታ ነው፡፡ ሌላውም ወሳኝ ነጥብ ኢየሱስ ሁሉንም ሰው መስደቡን ማሰተዋል ልብ ይሏል፤ትውልዱን በሙሉ፣ አማኙንም ኢ-አማኙንም፡፡ (ማቴ 12፤38…) (ማቴ 16፤23)

B. ኢየሱስ እየተሳደበ ሳይሆን፤ እነርሱ የሆኑትን ነው እየነገራቸው ያለው፡፡ ያልሆኑትን ነገር ፈጥሮ አልተናገረም፡፡

ይሄ ብዙ የማያራምድ ምላሽ ነው፡፡በዋናነት መመለስ ያለብን ጥያቄ ‹‹ስድብ ምን ማለት ነው›› የሚለውን ይሆናል፡፡ ለምሳሌ ያክል አንድ መላጣን ‹‹አንተ መላጣ(ቢሊጮ)›› ብንለው ስድብ አይደለምን? ብዙ የማይገባውንም ሰው ‹‹አንተ ደንቆሮ›› ብንለውስ? ይህ ስድብ ካልሆነ የስድብ ትርጉም ተለወጠ ቢሉን ይቀላቸዋል፡፡ ሌላው ደግሞ ‹‹እናንተ ግብዞች፤ እባቦች›› እያለ ኢየሱስ ሲዘልፋቸው፤ መቼም እንስሳውን እባብ እንዳልሆነ ማስተዋል ይቻላል፡፡ ባህሪያችሁ ከእባብ ይመሳሰላል፤ መርዘኞች ናችሁ እንደማለቱ ነው፡፡ ታድያ ይሄን ስድብ እንበለው ምክር?

ሌላው ነጥብ ኢየሱስ ጴጥሮስን የተናገረው ንግግር ነው፡፡‹‹ ..ወደ ኋላዬ ሂድ አንተ ሰይጣን፤ የሰውን እንጂ የእግዚአብሄርን አታስብምና እንቅፋት ሆነህብኛል..››(ማቴ 16፤23) ሰይጣን??? ታላቁን ደቀመዝሙር ሰይጣን እያለው መቼም ይህንንም እንደማናስተባብለው ምኞቴ ነው፡፡ ነገር ግን ምኞቴ ምኞት ሆኖ ቀረና ማስተባበሉን ተያይዘውታል፡፡ ‹‹ኢየሱስ እኮ ጴጥሮስን ሳይሆን እንዲህ ያለው በውስጡ መጥፎ የሚያናግረውን ሰይጣንን ነው..›› ጉድ በሉ!!! መጥፎ ሲሰራ ያየነውን ሰው በሙሉ ‹‹አንተ ሰይጣን›› እያልን መዝለፍ ይቻላል እያሉን ነው፡፡ ከዛም ‹‹ለምን ተሳደባችሁ›› ብንባል ውስጡ ያለውን ሰይጣን እንጂ ሰውዬውን አይደለም ማለት ያቻላልም እያሉን ነው፡፡ ‹‹ጉድ ሳይሰማ…!›› እኔን መውጫ ይጥፋኝ እንጂ ሌላ ምን እንላለን!!

C. ይሳደባ፤ መብቱ ነው፡፡ እሱ ከህግ በላይ ነው፤ እርሱን በህግ መነፅር አንዳኘውም!

ስለ ሃቅ ከተነጋገርን፤ ይህ መልስ ከሁሉም የተሻለ እና ቅንነት የተላበሰ (honest) ምላሽ ነው! ሊጨበጨብላቸው ይገባል! ብራቮ! ይሄ ሁላ ከሚያሽከረክሩን መጀመርያውኑ እንዲህ ቢሉን የተሻለ ነበር፤ ስራችንንም ያቀልልን ነበር፡፡ መልሳቸው ‹‹ኢየሱስ ሃጢያተኛ ቢሆንም እንኳን፤ ከህግ በላይ በመሆኑ እንደ ስህተት አይቆጠርበትም›› የሚል መልዕክት ያዘለ ነው፡፡ እኛም ጥያቄ እናቅርብ፡፡ ታድያ ኢየሱስ ሃጢያት ያልነካው ነው ስትሉን ምን ማለታችሁ ነው? አግባብ የሆነስ ድንፋታ ነውን? በአንድ በኩል ነው፤ በሌላ በኩል አይደለም እያሉ መሄድስ ይቻላልን? በፍፁም! ስለሆነም ኢየሱስ ከሃጢያት ንፁህ ነው የሚለው ቀረርቶ ወንዝ ስለማያሻግር ሊቆም ይገባዋል ብለን እንመክራለን!

አንዳንዶችም ኢየሱስን ንፁህ ለማለት የጲላጦስን ‹‹ከሀጢያት አንድ እንኳን አላየሁበትም›› የሚለውን የምስክርነት ቃል በመውሰድ እንደመረጃነት ሲጠቀሙበት ይታያል፡፡ የምስክር ሰጪውን ማንነት ፤ የተናገረበትን ሙሉ አውድ እንዲሁም ሌሎች መረጃዎችን በማቅረብ ዕራቆቱን ማስቀረት ይቻላል! እንዲሁም ከላይ የዘረዘርኳቸው ማብራርያዎች ላይ ተመርኩዘን ብንመለከተው፤ ግጭት ፈጥሯል ማለትንም ያስይዛል፡፡ ‹‹ሃጢያት›› የሚለው አገባብ ከሌሎች መፅሃፍ ቅዱሳዊ አስተምህሮቶች አንጻርም የሚገመገም ይሆናል!
መርፊው
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 260
Joined: Sat Oct 15, 2011 4:22 pm

Postby መርፊው » Mon Apr 22, 2013 7:25 pm

አስደንጋጩ ታሪክ

ግጭት ያውም ጣሪያ የነካ ፣ ተቃርኖ እንደ አቧራ እዚም እዚያም የተበተነበት ፣ አለመስማማት የበረከተበት …. ሁሉም የዝሆን ጆሮ ይስጠኝ ብሎ ሰምቶ እንዳለሰማ የሆነበት "በመንፈስ ቅዱስ" ሽፋን የራሱን እምነት የሚነዛበትም የሚያንሰራፋበት ወቅት 2 ክ/ዘመን፡፡
አንድ ስል የምነግርህ እውነታ ቢኖር በዛን ወቅት(2 ክ/ዘመን) የነበሩ ክርስትያኖች በአመለካከትም በ እምነትም ከዛሬዎቹ ከእናንተ አንፃር ሲታዩ የሰማይ ያህል ይርቃሉ፡፡ ምናልባት መንፈስ ቅዱስ ረድቶህ በዛን ወቅት የነበረውን አንዱን ክርስትያን ከሙታን ብትቀሰቅሰው እና ስለ እምነትህ ብትሰብከው "መናፍቅ" ወይም "ሙናፊቅ" የሚል "ታርጋ " ወይም ቻባ ራስጌህ ላይ ባሰረፈ ነበር ፡፡ ይህን ስልህ ግር ሊልህ ይችላል፡፡ እስኪ እንዴት? እኮ እንዴት ? የሚልም ጥያቄ ትጠይቅ ይሆናል ፡፡

ግና እንደ አንተ አይነት አጥብቆ ጠያቂ ተረጋጋ እያልኩ ወደ መሰረታዊው ምላሽ ላምራ

1. የመጀመሪያዎቹ ክርስትያኖች (Jewish Christians):- በክርስትናው ታሪክ ቀደምት የተባላቸው ክርስትያኖች መካከል እነዚህ የአይሁድ ክርስትያኖች የመጀመሪያዎቹ ናቸው ፡፡ እንዳልኩህ አሁን ካሉ ክርስትያኖች እነዚህ ክርስትያኖች በእምነትም በ አመለካከትም ይለያሉ፡፡ ይህን ፅሁፍ ያነበበ ሰው ሁሉ ይጠይቃል፡፡ እነዚህ ክርስትያኖች ከዛሬዎቹ ከተለዩ በምን? እምነታቸው እንዲሁም አመለካከታቸው ምን ይሆን? ሲልም ያውጠነጥናል ፡፡ ይህ እንግዲህ ጭንቅላት ወዶ ሳይሆን ተገዶ ሚጠይቀው መሰረታዊ ጥያቄ ነው፡፡

ለዚህም መሰረታዊ ጥያቄ ምላሽ አለኝ ሲል አንድ ይለናል እውቁ አለም ያጨበጨበለት የመፅሀፍ ቅዱስ ሊቅ የ ብሩስ መተዝገር ተማሪ Proffeser Bart D.Ehrman እኔም እድሉን ለመስኩ ጠበብት ለቀቅ ላርግ፡፡ ምን ነበር ያልከው?

“Jewish Christian’s adoptionist ፡- a form of religion embresed by group of second century. jewish Christian known to be in palastain ….. Thise belevers maintaind that Jesus was a remarkable man, more righteous in the Jewish law ….. For even though Jesus was choosen by God. He was not himself divine. he was a righteous man but nothing more than a man"(51)

ይህ ነበር አንዱ ጥንታዊው ክርስትና !!! እነዚህ ክርስትያንኖች እየሱስ አምላክ ነው ሲል የተናገረውን ሁሉ በክህደት ይፈርጁታል፡፡ ጳውሎስን ራሱ የእየሱስን አስተምሮ ለመቀየር የሞከረ ክህደት የፈፀመ ሰው ሲሉ አውግዘውታል ፡፡ በነዚህ ክርስትያኖች ጳውሎስ መናፍቅ የሚል የ እምባሻ ስም አግኝቷል(52) ይህን እውነት እና ታሪካዊ ሀቅ እነሱ ዛሬ ላይ መተው ባይነግሩንም ምሁራን እየደረሱበት ያለ እውነታ መሆኑ ነው፡፡(53) በነዚህ ክርስትያኖች መሰረት አንተ ክርስትያን አደለህም፡፡ አንተ ሌላውን መናፍቅ ስትል የምታጣጥለውን ያህል እነሱም አንተን መናፍቅ ሲሉ ሁለተኛው ክ/ዘመን ላይ ሆነው 21 ክ/ፍ ዘመን ላይ ያለሀውን አንተን እንዲሁም 36000 ውንም የክርስትያን አንጃ በሙሉ ያጣጥላሉ፡፡ የሆነ ሆኖ እነዚህ ክርስትያኖች እየሱስ አምላክ አደለም ካሉ ሳናነሳ ማናልፈው መሰረታዊ እና ወሳኝ ጥያቄ አለ፡፡ ይህ መሰረታዊ አስተምሮዋቸው እንደ ድንገት ከባዶ መሬት አልበቀለም ወይም እንደ መና ከሰማይ አልወረደም፡፡ አስተምሮው ምንጭ አለው ፡፡ ይህን ያህል- ያውም በአይሁድ ክርስትያኖች ዘንድ ተቀባይነት ያገኝ ዘንድ ሚና የተጫወተው ምንጩ ምንድ ነው? ብዬ ጥያቄውን ላንተው በመተው ወደ ሁለተኛዎቹ የክርስትና ጎራ ላምራ ነው ሚባለው ልለፍ?

2. ማርኪዮናይት ክርስትያኖች (Marcionite Christians) ፡- ሹፍ! እነዚህ ክርስትያኖች ከሁለተኛው ክ/ዘመን አጋማሽ እስከ ሁለተኛው ክ/ዘመን መጨረሻ የነበሩ ሌሎች የክርስትና እምነት አንጃዎች ናቸው፡፡ የእነዚህ አንጃዎች አብዛኛዎቹ ሚገኙት በአሁኗ ቱርክ አካባቢ ሲሆን Marcionite የሚል ራስ ጌ ያገኙት ከተቃዋሚዎቻቸው ከ አይሁድ ክርስትያኖች መሆኑ ነው፡፡ ምክንያቱም ይህን ክርስትና በመጠንሰስ ጠንስሶም በማስፋፋት ወሳኝ ሚናውን የተጫወተው Marcion የተባለው ወንጌላዊ በመሆኑ ነው፡፡ ይህ ወንጌላዊ እራሱ በሰጠው ቃል መሰረት ትክክለኛው የክርስትና አስተምሮ የጳውሎስ አስተምሮ መሆኑን ሲሆን ሌላው አስተምሮ ግን መሰረተ ቢስ እንደሆነ አውጇል ፡፡ እንዳውም የጳውሎስን አስተምሮ በመደገፍ የአይሁዶች ህግ እንደተሻረና ዋጋ ቢስ እንደሆነ ሰብኳል(ልክ እንደ ጳውሎስ)፡፡ የሆነ ሆኖ የዚህ እምነት ጠንሳሽ ዋና አስተምሮው የክርስትና አምላክ እና የአይሁድ አምላክ የተለያዩ መሆናቸውን ነው፡፡ የ ክርስትናው አምላክ እዝነትን ሰባኪ ብሎ ገልፆ ሲያበቃ የ አይሁዱን አምላክ ደግሞ ርህራሄ የሌለው ሲል ያጣጥለዋል፡፡ በዚህ አስተምሮ ቀኖና(54) መሰረት እየሱስ የመጣው የሰውን ልጅ ከ አይሁዶች አምላክ ለመታደግ እና ለማዳን ነው፡፡(55) በተረፈ እየሱስ አምላክ እንጂ ሰው አይደለም የሚለው ዋና አቂዳቸው ነው ፡፡ ለማን? ለነዚሁ ክርስትያኖች፡፡ እውነት እውነት እልሃለው እነዚህም ክርስትያኖች መሆናቸው ነው፡፡ እንቀጥል……..
3. ጊኖስቲክ (56) ክርስትያን (Gnostic Christians):- ይህ ቡድንን የተምታታበት ቡድን ብለው ማጋነን አድርገህ አትውሰድብኝ!!! ፡፡ ይህን ስልህ ለምን መሰለህ በዚህ ቡድን ውስጥ እራሱ ስምምነት ሚባል ነገር ወፍ የለም!!! ያውም በእየሱስ ማንነት ላይ፡፡ አንዳንዱ ጊኖስቲክ ከ አይሁድ ክርስትያኖች ጋር ተስማምቶ ሲያበቃ እየሱስ ፍፁም ሰው እንጂ አምላክ አደለም ሲል በአደባባይ ይሰብካል፡፡ ሌላው ጊኖስቲክ ደግሞ 360 በመዞር እየሱስ ፍፁም አምላክ እንጂ ሰው አይደለም ሲል እየተቀባበለ በ የአህጉሩ ያስተጋባል፡፡ የሆነ ሆኖ እነዚህን ፊርቃ ወይም ቡድኖችን ሚያስማማቸው አንድ እውነት አለ እሱም መዳን ሚቻለው ፅሁፍ በማንበብ ሳይሆን ትርጉሙን በማወቅ ነው የሚለው ፅንሰ ሀሳብ ሲሆን ትርጉም ለማወቅ በሚያደርጉት ጥረት በመካከላቸው ሚኖረው የልዩነት አድማስ እየሰፋ እንደሚሄድ ደግሞ ለማወቅ እንግዲህ ነብይ መሆን አያስፈልግም፡፡ አብዛኛው ጊኖስቲኮች መሰረታቸውን ካደረጉባቸው ወንጌሎች መካከል አንዱ ዛሬ ዮሐንስ ተብሎ የሚታወቀው ወንጌላይ እና ሌሎች እንዲወድሙ በተደረጉ ወንጌሎች ላይ ሲሆን አንዳንዶቹ ዛሬ በአርኬዮሎጂስቶች ቁፋሮ ተገኝተዋል ለምሳሌ የቶማስ ወንጌል፣ የማርያም ወንጌል፣ የፊሊፕ ወንጌል እንዲሁም እውነተኛው ወንጌል በመባል የሚታወቁት ናቸው(57)፡፡ የሆነ ሆኖ እዚህ ጋር ጥያቄ ማንሳቴ አይቀርም እነዚህ ወንጌሎች ያሁኑ አዲስ ኪዳንህ ውስጥ አሉ ከሌሉ ለምን ? ምላሹን ምታገኘው ቀጣዩን የክርስትያን አንጃ ምንነት ስታውቅ ስለሆነ ንባብህን ቀጥል………
4. ፕሮቶ ኦርቶዶክስ ክርስትያኖች (proto- Ortodox Christians):- ይህን የክርስትና እምነት ምሁራን መጤ ይሉታል ምክንያቱ ዘግይቶ የመጣ በመሆኑ ነው፡፡ ፕሮቶ ምትለዋ ቃል ይህን ነው ምታመለክተው ፡፡ ይህ የክርስትያን አንጃ አስተምሮቱን ይዞ ብቅ ሲል ከለይ በተጠቀሱት የክርስትና አንጃዎች መናፍቅ የሚል ስያሜ የተሰጠው ሲሆን ምክን ያቱንም ሲነግሩን ሆን ብሎ በፍላጎት ከ እውነት ያፈነገጠ ስለሆነ ነው ይሉናል ፡፡ ለዚህም ነው ኦርቶዶክስ የሚል ስያሜ ያገኘው( ኦርቶዶክሲ የሚለው የግሪክ ቃል ቀጥተኛ ትርኩሙ ንፍቅና ማለት ሲሆን) ስያሜውንም ያገኘው በዚህ ምክንያት ነው፡፡ ሆን ብሎ ከእውነት በማፈንገጡ፡፡(58) ይህ አንጃ ነው እንግዲህ በጊዜው በእየሱስ ደቀመዝሙር ተፅፈዋል ተብለው በቀድሞ ክርስትያኖች ተአማኒነት የተጣለባቸውን መፅሀፎች ውድቅ ያደረገው ለምሳሌ የጴጥሮስ ወንጌል፣ የቶማስ ወንጌል፣ የፊሊፕ ወንጌል ወዘተረፈ….. ለምን ውድቅ አደረገ? መልሱ ግልፅ እና ግልፅ ነው፡፡ ከ አስተምሮቱ ጋር ስለማይሄድ፡፡ አልፎ ተርፎ በእነዚህ አንጃዎች ነው አዲስ ኪዳን 27 መፅሀፍት እንዲይዙ ውሳኔ የተሰጠባቸው (የአሌክሳንደሪያው ዋና ቄስ አትናትዮስ) ፡፡ እነሆ ይህ አንጃ ተቀባይነት ያገኝ ዘንድ ቀድሞ የማይታወቅ አዲስ ፅንሰ ሀሳብ ይዞ ብቅ አለ እሱም እየሱስ ፍፁም ሰውም ፍፁም አምላክ ነው የሚለውን ሀሳብ እና አስተምህሮ፡፡ በ ኒቅያውም ጉባኤ በጭብጨባ አስፀደቀ…… ዛሬ 36000 ውም ክርስትያን እያመነበት ያለው ፅሁፍ በዚህ አንጃ አማካኝነት ፀድቆ የተላለፈውን ብቻ እና ብቻ ነው፡፡ ዛሬም ላይ ሆነህ በእየሱስ ደቀመዝሙሮች ነው የተፃፉት የምትለን ወንጌሎች እንግዲ በ ዚህ አንጃ እንጂ የተሰየመው አንድም እነዚህ ወንጌሎች ማን እንደፃፋቸው አይናገሩም ሁለትም በእየሱስ ደቀ መዝሙር እንዳልተፃፉ ጥናቶች ደምድመዋል ፡፡(59) ይህ አንጃ በጊዜው ተቀባይነት የነበራቸው እና በእየሱስ ደቀ መዛሙርት ተፃፉ ተብለው ሲታመንባቸው የነበሩትን ፅሁፎች የሻውን ደብቆ የሻውን ቢያወድምም ይህ ከሆነ 1600 አመት በኋላ በቁፋሮ አርኬዮሎጂስቶች የተደበቁ አንዳንድ ፅሁፎችን ናግሀማዲ ግብፅ ላይ ሊያገኛቸው ችለዋል በዚህም ምክንያት ናግሀማዲ ቴክስት ተብለው ይታወቃሉ፡፡
5. ማጠቃለያ ፡- ካላይ ያነበብከው ፅሁፍ በእጅጉ አጠር ባለ መልኩ የቀረበ ነው፡፡ ዛሬ የምታገኘው አዲስ ኪዳን እንግዲህ ከዚህ ዝግመተ ለውጥ ውስጥ የተረፈ መሆኑን ለነጥብ መጠራጠር የለብህም ፡፡ ማን? እንዴት ? ለምን አላማ? የት? ተፃፈ የሚለው ጥያቄ ጥርጣሬ የታከለበት እንጂ ተገቢ ምላሽ አልተገኘለትም፡፡ የእየሱስ አስተምሮ እንዳልተጠበቀ እና ይህ እጅህ ላይ የቀረው አዲስ ኪዳን ውስጥ እራሱ ከባድ ችግር እንዳለበት በዚሁ ርእስ ቀጣይ ክፍሎች እንደምመለስበት ቃል እየገባሁ
መርፊው
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 260
Joined: Sat Oct 15, 2011 4:22 pm

Postby መርፊው » Sun Apr 28, 2013 2:46 pm

‹እየሱስ ሰው ነው፤ ፍጡር ግን አይደለም››???
ከጥቂት ወራቶች በፊት በፌስቡክ መስኮት ከአንድ የክርስትና እምነት ተከታይ ጋር ስለ እየሱስ አምላክነት ጉዳይ በመወያየት ላይ ነበርን… በመሃልም ስለ ይሆዋ ምስክሮች መነሳት ተጀመረ… ‹‹እናንተን ከነሱ ምንድነው የሚለያችሁ›› ብዬ ጥያቄ አቀረብኩለት.. እሱም በመቀጠል.. ‹‹ ስንቱን ቆጥሬ ልጨርስልህ.. ጉዳቸው መች ተቆጥሮ ያልቃል›› ሲለኝ… እኔም ዋናው ልዩነት ምን እንደሆነ እንዲነግረኝ ጠየቁት.. ‹‹ኢየሱስን እኮ ፍጡር ነው ይሉታል.. ስላሴንም ከቶውኑ አይቀበሉም..››ብሎ መለሰልኝ.. እኔም በማስከተል… እናነተስ ይሄን መች ካዳችሁ ስለው.. ‹‹ቂቂቂ ወይ መሃይምነትህ.. እያለ መሳለቁን ተያያዘው››.. እኔም… ‹እየሱስ ሰው ነው፤ ፍጡር ግን አይደለም›ትሉት የለ .. ታድያ ይህ እኮ ማለት.. ፍፁም ፍጡር፤ ፍፁም ፋጣሪ ነው እያላቹት ነው.. እናነተስ መች ካዳቹት ፍጡርነቱ.. ጥላችን አኮ ፈጣሪ ነው በሚለው ላይ ነው.. አርዮስን እኮ ትተቹታላችሁ እንጂ እናነተም እኮ የኢየሱስን ፍጡርነት 100 በ 100 ተቀብላቹታል..›› ስለው.. ‹‹ሰው ነው እንጂ ፍጡር ነው እንልም›› የሚል ቀጭን መልስ ሰጠኝ.. እኔም.. ‹‹.. እንደዛ ከሆነ አሁን ላለንበት 21ኛ መቶ ክፍለ ዘመን አዲስ ቀኖና ማፅደቅ ይጠበቅባችኋል… በኒቅያ ጉባዔ ላይ የእየሱስን አምላክነት እንዳወጃችሁት.. ዛሬም ዳግማዊ ኒቅያ ጉባዔ ጠርታችሁ.. ‹እየሱስ ሰው ነው፤ ፍጡር ግን አይደለም› ብላችሁ ከምስጢረ ስላሴ፣ ስጋዌ፣ ቁርባን.. ተርታ በማስቀመጥ.. አዋጅ አውጡ.. በመቀጠልም ህዝቡን አስተምሩ.. ያኔ ውጤቱን በጋራ እናየዋለን…›› የሚል መልስ ሰጥቸው ውይይታችን ተቋጨ፡፡
ሰውነቱን ተቀብላችሁ ፍጡር አይደለም ማለት… ልክ አምላክነቱን ተቀብሎ ፈጣሪ አይደለም የሚለውን ያስይዛል.. ስለዚህ አንዴውኑ ‹‹እየሱስ ፍፁም ሰው ነው፤ ፍጹምም አምላክ ነው›› ግን ፍጡርም ፈጣሪም መሆኑን አያሳይም ብላችሁን እርፍ በሉዋ!!
መርፊው
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 260
Joined: Sat Oct 15, 2011 4:22 pm

Postby መርፊው » Wed May 01, 2013 10:11 pm

እንደ ክርስትና መለያየት ሁሉ የመፅሀፍ ቅዱስ ፅሁፍ እንደሚለያይ ለማወቅ እንግዲህ ነብይ መሆን አሊያም ማስጠንቆል አያስፈልግህም፡፡ መፅሀፍ ቅዱስህ ይለያያል ይህም አለም ያወቀው ፀሀይ የሞቀው ሀቅ መሆኑን አንተም እራስህ ምስክር ልትሆን እንደምትችል እጠረጥራለሁ፡፡ ለምን መሰለህ የተለያዩ የ ቤተ ክርስትያን ክፍሎችን በየደረጃው እየወረድን ስንመለከትናቸው የመፅሀፍ ቅዱስን መለያያት ያለ ቁፋሮ እንረዳለን ተመልከት፡-
- Protestant church
- Roman catholic church
- Anglican church
- Greek orthodox church
- Ethiopic Church
- Syriac church
ሹፋ! በ እነዚህ አንጃዎች ዘንድ በሚገኙት መፅሀፍ ቅዱሶች ውስጥ እንኳ በ አይነት እንዲሁም በሚቀበሉት መፅሀፍ መጠን የጀነት እና የጀሀነም አይነተ መራራቅ አለ፡፡ ይህን ደግሞ እራሱን በቻለ ርእስ እመለስበታለሁ፡፡

ወደ ተነሳሁበት ርእስ ስመልስህ ክርስትያኖች በፌደራሉ ቋንቋ አዲስ ኪዳን ወይም በ ኢንተርናሽናሉ ቋንቋ New Testament ስትል በምታምንበት መፅሀፍ ላይ ምሁራን #ከ አፉ እስከ ጫፉ; ጥናት አደረጉ፡፡ አድረገው ሲያበቁ እንዲህ ሲሉ እውነቱን ነግረውናል

#IT IS safe to say there is not one sentence in new testament in which manuscript tradition wholly Uniform;(1)

ይህን ያሉት ያንተው ምሁራን መሆናቸው ነው ፡፡ ከፍለክ ኢንተርፕሬተር ባይብል ዲክሽነሪይ ውስጥ ታገኘዋለህ፡፡ ….. እናም በ እጃቹህ ላይ የሚገኙ 5000 ጥንታዊ ፅሁፎች ሲሆኑ አንዱም ከ አንዱ ጋር በ አንድ አረፍተነገር አይስማማም ብላችሁን አበቃችሁ ከዛም እንዲህ ስትሉ ሀሳባችሁን አጠናከራችሁ

#The original copies of the NT books have, of course, long since disappeared. This fact should not cause surprise. In the first place, they were written on papyrus, a very fragile and perishable material. In the second place, and probably of even more importance, the original copies of the NT books were not looked upon as scripture by those of the early Christian communities;(2)

ኦርጂናሉ የ አዲስ ኪዳን ፅሁፍ ላይገኝ ህልም እልም , ሲል ጠፍቷል ይህ የሆነበት ምክንያት አንድም ፓፒረስ ላይ በመፃፉ ሲሆን ሁለትም በጊዜው በነበሩ ክርስትያኖች መለኮታዊ(የአምላክ ቃል) መፅሃፍ ተደርጎ ባለመታየቱ ነው ብላችሁናል ፡፡ ይህ በ እንዲህ ሳለ አዲስ ኪዳን መለኮታዊ ነው ስትሉ አሁንም ድረስ ትሟገታላችሁ!!!

አሉ የተባሉት 5000 ጥንታዊ የ አዲስ ኪዳን ፅሁፎች በ አንድ አ/ነገር እርስ በእርስ ጥል ላይ ካሉ( ካልተስማሙ) ሲደመር የቱ ትክክል እንደሆነ ሊለይ የሚችለው ዳኛው መፅሀፍ(ኦርጂናሉ) ቻው!! ሲላችሁ እስከ ትንሳኤ ድረስ ከተለያችሁ ይህ ፅሁፍ(አዲስ ኪዳን) ተአማኒ ይሆን ዘንድ አስረጅ ማስረጃ ፈልጋችሁም አፈላልጋችሁም ካጣቹህ ወይም ራሱን ከሰወረባችሁ #መለኮታዊ;በሚል ብሂል ለምን ትወተውቱናላችሁ? አልፎ ተርፎ ጥንታዊ ክርስትያኖች መለኮታዊነቱን ያላፀደቁትን መፅሀፍ በምን መስፈርት ነው ዛሬ ላይ መለኮታዊ ስትሉ ቀንም ማታም አንድ ምትሉን?
ጥንታውያን የ ቤተክርስትያን አባቶች በዚህ ጉዳይ ላይ በ አይነቱ የተለያየ መፅሀፎች ሲኖራቸው እንደወረደ በዚህ መልኩ ይቀርባል፡፡
Church Tradition & Apostolic Fathers
Clement Of Rome
Ignatius Of Antioch
The Didache
Papias Of Heirapolis
Barnabas
Polycarp Of Smyrna
Hermas Of Rome
The So-Called Second Epistle Of Clement
ተመልከት ከላይ የጠቀስኩልህ የ ቸርች አባቶች ሲሆኑ በነፍስ ወከፍ የየራሳቸው ፅሁፍን ፅፈዋል እነዚህንም ፅሁፎች አጥንቶ ሲያበቃ ብሩስ መተዝገር ፡

#For early Jewish Christians the Bible consisted of the Old Testament and some Jewish apocryphal literature. Along with this written authority went traditions, chiefly oral, of sayings attributed to Jesus. On the other hand, authors who belonged to the 'Hellenistic Wing' of the Church refer more frequently to writings that later came to be included in the New Testament. At the same time, however, they very rarely regarded such documents as 'Scripture'.
Furthermore, there was as yet no conception of the duty of exact quotation from books that were not yet in the full sense canonical. Consequently, it is sometimes exceedingly difficult to ascertain which New Testament books were known to early Christian writers; our evidence does not become clear until the end of second century.;(3)
ትሻልን ፈትቼ ትብስን አገባሁ ሆነ ኮ ነገሩ
በ አውራው(እየሱስ) ጊዜ የተገኘ ፅሁፍ አለመኖሩን ሳስብ ሲደመር ከሁለተኛ ክፍለ ዘመን መጨረሻ ጀምሮ በተሰበሰቡት ፅኁፎች መሀል የሚገኘውን የገዘፈ ልዩነት ሳስተውል ሁሌም በ አግራሞት እደመማለው፡፡ በጣም ሚገርመው ደግሞ ምን መሰለህ ከ 2ተኛው ክ/ዘመን መጨረሻ ጀምሮ የተገኙ ጥንታዊ ፅሁፎች መካከል ያለው ልዩነት ለየቅል በመሆኑ ምሁራን ይቁጠሩት በለው እንጂ ቆጥረህ አትዘልቀውም፡፡ ሲደመር ጥንታዊ ክርስትያኖች መለኮታዊነታቸውን ያላፀደቋቸውን እነዚህ #የልዩነት ጎርፍ ያጥለቀለቃቸውን; በምን መስፈርት መለኮታዊ ናቸው ሲሉ የዳቦ ስም እንዳሸከሟቸው ምክንያቱን በ አይኔም በቴሌስኮፐም ብፈልግም እውነቴን ነው ምልህ ፈልጌ ላገኘው አልቻልኩም፡፡ በዛ ላይ ኦርጅናሉ ፅሁፍ ወፍ!!!! የለም
አቦ!! ምን ነበር ያልከው ዴቪድ ኖኤል ፍሬድ ማን?
#Since - like virtually all ancient literature - no autographs are extant for the NT, its most likely original text must be reconstructed from these imperfect, often widely divergent, later copies.;(4)
ከ እንግዲህ ነው መጥፋት !!!
የናንተው ምሁራን ተ አማኒነት ከሌላቸው እርስ በርሳቸው እንኳ ፍፁም ከማይስማሙ imperfect ጥንታዊ ፅኁፎች ኦርጂናል የሆነውን ፅሁፍ እናገኘዋለን ስትሉ ስሰማ ቀልድ ነበር የመሰለኝ….
እውነት እውነት እልሀለው ለቀልድ አይደለም ይህን ሚሉን የምራቸውን ነው ፡፡ እንዴት? እኮ እንዴት ? ሲል ለሚጠይቅ አጥብቆ ጠያቂ ምሰጠው ምላሽ #በድምፅ ብልጫ; የሚል ይሆናል በኔው አማርኛ
- ኦርጅናሉ ላይገኝ ጠፍቷል
- በአይነታቸው በ አንድ አ/ነገር ማይስማሙ ጥንታዊ ኢምፐርፌክት ፅሁፎች ተሰባሰቡ
- ሊቃውንትም መረመሯቸው
- በራሳቸው በስፈርት እና በድምፅ ብልጫ ይህ ይሁን ኦርጅናል ንባቡ ሲሉ አፀደቁ፡፡ ጉድ በል ያገሬ ልጅ !!!1
እናስ? እናማ ሚሽነሪዎች ለ ኦርጅናሉ የቀረበ ፅሁፍ አለን ሲሉ እንደ ፓሮት መደጋገሙን ተያያዙት አንድም ኦርጅናሉ ሳይኖራቸው ሁለትም መረጃን ሳይፈትሹ፡፡ ይሁን ብቻ እያልን እንቀጥል…..
ይህ አዲስ ኪዳን ፅ ሁፍ ላይ ከጊዜ ወደ ጊዜ በሰው እጅ # እየተደፈረ; መጣ ገልባጭ ነን ባዮች ሲፈልጉ ፅሁፉን በመጠምዘዝ ፣ ሲሻቸው በመደለዝ እና መከለስ ተያያዙት ፡፡ ይህም በራሳቸው መስፈርት በሆኑ ነው #የመረቀነው; አንድ መስፈርት ሲኖረው # ያልመረቀነው; ሌላ መስፈርትን ያስቀምጣል ፡፡ በዚህ መሀል መረጃ እንደ ሰማይ የራቀው ምስኪን ማህበረሰብ አሜን ሲል ውይም አሚን ሲል ዝም .ርጭ..ጭጭ…. ይህን ኩዳይ የምንለው አለን ይሉናል ኩርት አላንድ እና በርናንድ አላንድ እንድሉን እስቲ እንስጣቸው
#They also felt themselves free to make corrections in the text, improving it by their own standard of correctness, whether grammatically, stylistically, or more substantively. This was all the more true of the early period, when the text had not been attained canonical status, especially in the earliest period when Christians considered themselves to be filled with the Spirit. As a consequence the text of the early period was many-faceted, and each manuscript had its own peculiar character;(5)…… ይቀጥላል

REFERENCE BOOK
1. George Arthur Buttrick (Ed.), The Interpreter's Dictionary Of The Bible, Volume 4, 1962 (1996 Print), Abingdon Press, Nashville, pp. 594-595 (Under "Text, NT")
2. Op.Cit,, p. 599 (Under "Text, NT").
3. Bruce M Metzger, The Canon Of The New Testament: Its Origin, Significance & Development, 1997, Clarendon Press, Oxford, pp. 72-73.
4. David Noel Freedman (Ed.), The Anchor Bible Dictionary On CD-ROM, 1997, New York: Doubleday (CD-ROM Edition by Logos Research Systems), (Under "Textual Criticism, NT").
5. Kurt Aland & Barbara Aland, The Text Of The New Testament, 1995, William B Eerdmans Publishing Company, Grand Rapids, Michigan, p. 69
መርፊው
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 260
Joined: Sat Oct 15, 2011 4:22 pm

Postby መርፊው » Tue Jun 04, 2013 5:02 pm

በመጽሐፍ ‹‹ቅዱስ›› ውስጥ በነብያት ዙሪያ የተሰነዘሩ አስጸያፊ ሐሰቶች*^*^*

*** በኦሪት ዘፍጥረት 19:31-35 ) ውስጥ ሉጥን በተመለከተ አስጸያፊ መልእክቶች ሰፍረዋል፡፡ ሉጥ አስካሪ መጠጥ ጠጥተው መስከራቸው፣ ከዚያም ከሴት ልጃቸው ጋር መዘሞታቸው፣ እርሷም ማርገዟና ዝሪያቸው በርሷ በኩል መቀጠሉ ተጠቅሷል፡፡ እስኪ አስቡት! አላህ የሶዶምን ከተማ የገለበጠውና ሕዝቡን ያጠፋው የሶዶም ሕዝብ የኒህን ንጹህ ነብይ ቃል ባለመስማቱ፣ በርሳቸው እና በትምርታቸው በመሳለቁ ነበር፡፡ ወደ ንጽህና ያደረጉትን ጥሪ ባለመቀበሉ በጅምላ ቀጣው፡፡ የኢብራሂም የወንድም ልጅ የሆኑትን የሉጥን ንጽህና ለመመስከር ከጠፉ ከተሞች ቅሪቶች ውጭ ሌላ ምስክር ባይኖር እንኳ በቂ ምስክር አይደለምን? እንዲህ ዓይነት አስጸያፊ መልእክቶችን የያዘን መጽሐፍ መለኮታዊ ብለን ልንቀበለው እንችላለን?

*** ኦሪት ዘፍጥረት ምእራፍ 38 ላይ የየእቁብ ልጅ የሁዛ -ምን አልባትም ነብይ ሊሆን ይችላል- ከልጁ ሚስት ጋር ዝሙት መፈጸሙ ተጠቅሷል፡፡ የበኑ ኢስራኤል ነብያት ዝርያ ለምሳሌ (ዳውድና ሱለይማን) የተገኙት ከዚህ የዝሙት የዘር ግንድ መሆኑም ተጠቅሷል፡፡
ይህ ዘገባ ሐሰት መሆኑ ጥርጥር የለውም፡፡ ምንም ዓይነት መሠረት የሌለው ቅጥፈት ነው፡፡ የአላህ መልእክተኛ (ሶ.ዐ.ወ) እንደሚሉት፡- ‹‹ከአደም አንስቶ የርሳቸው የዘር ግንድ በጋብቻ ላይ ብቻ የተመሰረተ እና የተገኘ ነው፡፡›› (ደላኢሉ ኑቡዋ በይሐቂ 1/173-175)

በሌላ ሐዲስ እንዲህ ብለዋል፡- ‹‹ነብያት የአንድ አባት ልጆች ናቸው፡፡›› (ቡኻሪና ሙስሊም)

የአላህ መልእክተኛ (ሶ.ዐ.ወ) አያት ቅድመ አያት ውስጥ አንድም የዝሙት ልጅ ከሌለ ይህ ባህሪ በሌሎች ነብያትም ላይ የሚሰራ ነው፡፡ እርሳቸው የኢብራሂም የልጅ ልጅ አይደሉምን? የሁዛም እንደዚሁ የኢብራሂም የልጅ ልጅ ነው፡፡ በነብያት ቤት ውስጥ ዝሙት ሊከሰት አይችልም፡፡

*** በመጽሐፈ ነገስት ምእራፍ 11፣ውስጥ ሱለይማን በእድሚያቸው መጨረሻ ላይ እንደካዱና ጣኦት ማምለክ እንደጀመሩ ይገልጻል፡፡ በዚህም ሆነ በመጭው ዓለም ታላቅ ደረጃ ለግሶ አላህ የመረጠው ነብይ ክህደት ይፍጽማል ተብሎ እንዴት ይታሰባል? ሱለይማን አላህን በጽኑ አምላኪና አመስጋኝ ነብይ እንደሆኑ በቁርአን ተጠቅሷል፡፡ ለነብይ ተገቢው ባህሪ ይህ አመስጋኝነት ነው፡፡

ቁርአን ዒሳን፡- ‹‹አላህ ወደ መርየም ያኖረው መንፈሱና ቃሉ›› ሲል ይገልጻቸዋል፡፡ (አል ኒሣእ 171)

ኢብራሂም የአላህ ምርጥ ወዳጅ፣(አልኒሣእ 125)

ሙሳ አላህ ያናገራቸው፣ ( አልኒሣእ 114) መሆናቸውንም ተናግሯል፡፡

የዳውድን ቤተሰብም፡- ‹‹የዳውድ ቤተሰቦች ሆይ፣ አመስጋኞች ስትሆኑ ስሩ›› ሲል አናግሯቸዋል፡፡ (ሰበእ 13) አላህ ነብያቱን የሚገልጽባቸው ባህሪያት እነዚህ ናቸው፡፡

*** ብሉይ ኪዳን ስለ ነቢዩላህ ዳውድ ሲተርክ አርያ የተባለውን ሰው ሚስት እንደተመኙና ሆነ ብለው እርሱን በማስገደል ሚስቱን እንደቀሙት ይተርካል፡፡ ሳሙኤል 2ኛ 11፡2-4)

ይህ እኩይ ባህሪ ለነቢይ ቀርቶ ለተራ ሰው፣ በእውን ቀርቶ በሕልም እንኳ የሚያስጸይፍ ነው፡፡ አላህ ዳውድን በተመለከተ ‹‹ምን ያምር አገልጋይ፡፡ እርሱ ወደ አምላኩ ተመላሽ ነው፡፡›› ብሏል፡፡ (ሱረቱ ሷድ 30)

*^*^* የነብያትን ስም እንዲህ የሚያጠፋና የሚያረክስ መጽሐፍ እንዴት ከአላህ የተገኘ ሊሆን ይችላል? ይህ ታሪክ ይከሰታል ብሎ ማሰብ የነብይነትን ደረጃ አለማወቅ ነው፡፡ ነቢ ዳውድ አላህን አዘውትረው የሚያመልኩና አልቃሽ ነብይ ነበሩ፡፡ ከርሳቸው ጋር የተቀመጡ ሁሉ የርሳቸው ለቅሶ ተጋብቶበት ያለቅሳል፡፡ ወደ አላህ በንስሐ መመለስን ያበዛሉ፡፡ ፊታቸውን ከአምላካቸው ለቅጽበት እንኳ አላዞሩም፡፡
የሕይወታቸው ዋነኛ መርህ ዑቡዲያ ነበር፡፡ አላህን ዘወትር ማምለክ፡፡(ሷድ 17)

የአላህ መልእክተኛ (ሶ.ዐ.ወ) የነቢይ ዳውድን ኢባዳ ሲያወድሱ እንዲህ ብለዋል፡-
‹‹ከአላህ ዘንድ ይበልጥ ተወዳጁ ሶላት የዳውድ ሶላት ነው፡፡ ከላህ ዘንድ ይበልጥ ተወዳጁ ጾም የዳውድ ጾም ነው፡፡ የሌሊቱን ግማሽ ይተኙና ሲሶውን ይቆማሉ፡፡ 1/6ኛውንም ይተኛሉ፡፡ 1 ቀን ይጾማሉ፣ አንድ ቀን ያፈጥራሉ፡፡›› (ቡኻሪና ሙስሊም)

ነቢይ ዳውድ ንጉስ ነበሩ፡፡ የመንግስት ሃብት በአጠቃላይ በእርሳቸው እጅ ነው፡፡ ይህም ሆኖ ግን ያን ሃብትና ንብረት ለግላቸው ለመጠቀም፣ ሌላው ቀርቶ በርሱ አንዲት ቁራሽ ምግብ እንኳን ለመግዛት ፈቃደኛ አልነበሩም፡፡ ራሳቸውንና ቤተሰባቸውን የሚቀልቡት የእጅ ሙያቸውን ተጠቅመው በሚያገኙት የግል ገቢ ነበር፡፡ አንዲት ቁራሽ እንኳ ያለ አግባብ ለመውሰድ ባልፈቀዱት፣ የሕይወት መርሃቸው እና ልዩ ባህሪያቸው አላህን ማገልገል በሆኑት በዚህ ነብይ ላይ መጽሐፍ ቅዱስ ያንን አጸያፊ ቅጥፈት ይደርትባቸዋል፡፡ እጅግ ብጹእ እና ንጹህ ከመሆናቸው አኳያ ይህ ቅጥፈት በተግባር ቀርቶ በሐሳብ እንኳ ለቅጽበት ሊታወሳቸው ፈጽሞ የሚችል አይደለም፡፡

**** በብሉይ ኪዳን (ዘፍጥረት 32፡22-28) ውስጥ አእምሮ ሊቀበለው የማይችል ሌላም አስገራሚ ነገር እናገኛለን፡፡ እርሱም እስራኤል (ያእቁብ) ከአምላክ ጋር ታግለው ማሸነፋቸው ነው፡፡ እናም የምእራቡ አለም ቁሳዊ ፍልስፍና ወሰንን ሁሉ ጥሶ አምላክን የሰው ቅርጽ በማስያዝ ከነብዩ ጋር እንዲታገል አድርጎታል፡፡ ሐምዛ ከመስለማቸው በፊት ለነቢዩ ሙሐመድ (ሶ.ዐ.ወ) የተናገሩት ተከታዩ ቃል ለነዚህ ወገኖች ጥሩ ምላሽ ይዟል፡-

‹‹የወንድሜ ልጅ ሙሐመድ ወይ፣ ሌሊት በበረሃ በምዘዋወር ጊዜ አላህ በግንብ ውስጥ ተወስኖ ከመቀመጥ በላይ መሆኑን እረዳለሁ፡፡››
ስለዚህም ክርስትያኖችና አይሁዶች የአምላክ ቃል ነው ብለው የሚያስቡት መጽሐፍ በዘመነ መሐይምነት ወደነበሩት ሐምዛ የሕሊና ደረጃ እንኳ ከፍ ሊል አልቻለም፡፡ ታዲያ በእንዲህ አይነት ብክለቶች የተሞላውን ይህን መጽሐፍ የአምላክ ቃል ነው ብሎ እንዴት ማሰብ ይቻላል?

ይህ መጽሐፍ ስለ ነቢያት የሚናገረው ሊታመን ይችላልን? በፍጹም አይታመንም፡፡ መጽሐፍ ቅዱስ አላህንና ነቢያቱን አስመልክቶ በቅጥፈትና በጥመት የተሞላ ነው፡፡ ብሉይ ኪዳን የጥመት ምንጮች ናቸው፡፡

*^* ቁርአን በነብያት ዙሪያ ለተደረቱ ቅጥፈቶች ተገቢውን ምላሽ ይሰጣል፡፡ ምክንያቱም ነብያትን ሙሉ በሙሉ እንድንከተል ያዘናልና፡፡ በቁርአን ትምህርት መሠረት ነብያት ስብእናቸው የተሟላ፣ የቅን ጎዳና መሪዎች፣ በሁሉም ጉዳዮች ሊከተሏቸው እና ሊታዘዟቸው የሚገቡ ታላላቅ መምህራን ናቸው፡፡ ሁሉም ነብያት የአላህን ውዴታ የሚያየንጸባርቁልን መስታወቶች ናቸው፡፡ ከነዚህ መስታወቶች ላይ አንዲት እንኳ የአቧራ ቅንጣት አይገኝም፡፡ የተከበረው ቁርአን ይህንን እውነታ እጅግ ውብና ግልጽ በሆነ መልኩ አስቀምጦታል፡፡
ቁርአን ውስጥ የተጠቀሱ የአንዳንድ ነብያትን ድርጊቶች በስህተት በመረዳት ነብያት ሐጢአት ሊፈጽሙ እንደሚችሉ የሚያስቡ ወገኖችን እናገኛለን፡፡ የስህተታቸው ምንጭ መልእክቶችን በወጉ አለረዳት ሲሆን ጥቂት ቢያስተነትኑ የአስተሳሰባቸውን ግድፈት መረዳትና እንደብዙሐን ዓሊሞች ለነብያት ተገቢውን ክብር መስጠት በቻሉ ነበር፡፡

ምንጭ፡- ዘላለማዊ ብርሃን
በሙሐመድ ፈትሁላህ ጉለን
ትርጉም፡ በኡስታዝ ሐሰን ታጁ
መርፊው
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 260
Joined: Sat Oct 15, 2011 4:22 pm

Postby መርፊው » Wed Jun 05, 2013 8:30 pm

በኦርቶዶሱ ዘንድ እውቅናን ያተረፈው የቅድስት ስላሴ መንፈሳዊ ኮሌጅ የነገረ መለኮት ምሩቅ ሚሽነሪ መምህር ታሪኩ አበራ እንዲህ ሲል ፅፏል፡፡
#ዛሬም ከመፅፍ ቅዱስ ሀይለ ቃላትን እየመዘዙ በእየሱስ ክርስቶስ እየተሰናከሉ ያሉ ብዙዎች ናቸው፡፡ አንዳንዶቹ (ሙስሊሞችን ማለቱ ነው) ጥቅስ እየመረጡ ኢየሱስ ነብይ ነው ይላሉ አንዳንዶቹ ደግሞ ከመፅሀፍ ቅዱስ መረጃ አለን ኢየሱስ አምላክ ሳይሆን መልአክ ነው ይላሉ አንዳንዶቹ ደግሞ እየሱስ እንደማንኛውም ሰው ፍጡር ነው እያሉ ንግግራቸውን በጥቅስ ለማጀብ ሲሞክሩ እንመለከታቸዋለን ፡፡ በተለይ አሁን ባለንበት ዘመን ሙስሊም ወገኖቻችን ክርስቶስ ማ ነው? ብለው 303 ጥያቄዎችን ጠይቀዋል (1) ለእነዚህ ወገኖች መልስ ለመስጠት ይህን እየሱስ ማ ነው? የሚለውን መፅሀፍ በመንፈስ ቅዱስ እርዳታ ለንባብ ሳበቃ ብዙዎቹ በ ክርስቶስ ማንነት ላይ ለሚጠየቁ ጥያቄዎች የህሊና እረፍት የሚያገኙበትን መልስ እንደሚያገኙ በረዳኝ ጌታ በመተማመን ነው፡፡;(2)
መምህር ታሪኩ እኛ ሙስሊሞች ጥቅስ እየመዘዝን ወይም እየጠመዘዝን #አምላክ የሆነውን እየሱስ; አደለም! እምቢ!!! ብለን ከአምላክነቱ ለማውረድ አደገኛ ሙከራ እያደረግን እንደሆነ አሳውቆን ሲያበቃ ለዚህ ጥያቄያችን በመንፈስ ቅዱስ እርዳታ ምላሽ ለመስጠት እንደቻለ ደግሞ ጨመሮ ነግሮናል፡፡ እኛም ማላሹ አጥጋቢ ከሆነ ብለን መፅሀፉን አነበብን፡፡ አንብበንም ምላሽ ተብዬው ምላሽ ሊሆን አለመቻሉን ተረዳን መፅሀፉንም ከደነው ፀሀይም ጠለቀች፡፡ ይህም ምክንያት ሆኖን ዛሬም ድረስ ጥያቄያችንን ቀጠልንበት
የሆነ ሆኖ ክርስቶስ ማ ነው? ስንል አሁንም እጠይቃለን ፡፡ አዎ ክርስቶስ ማ ነው? በመንፈስ ቅዱስ እርዳታ ሚሽነሪዎች የሚከተሉትን ምላሽ ሰተውናል፡፡
ምን ነበር ያልከው መምህር ታሪኩ?
#......ወልድን ፍጡር ነው ማለት ከዚህ መፅሀፍ ቅዱስ እውነት ውጪ በጭፍን ግልቢያ መሄድ ነው……;(3)
መጋቤ ጥበብ ሰለሞንም በበኩሉ #መፅሀፍ ቅዱስ እየሱስ ክርስቶስ እርሱ አምላክ መሆኑን በተለያየ መልኩ ገልፆታል;(4)
አባ ሳሙኤልም ይጨምሩና #በሶስት አካላት እራሱን የገለፀው አንድ አምላክ …;(5) ሲሉ ስእላዊ ማስረጃ በመፅሀፋቸው ላይ ሲያቀርቡ ተመልክተናል ፡፡
መምህር ኪዳነ ማሪያም ጌታሁን ደግሞ # begotten not made; በግእዙ #ዘተወልደ ወአኮ ዘተገብረ; #እየሱስ ክርስቶስ ያልተፈጠረ ብቸኛ የእግዚአብሄር ልጅ ነው ; የሚለው የስነ መለኮት ፍልስፍና ምርምር እና ጥናት ወደ ሚስጥረ ስላሴ ይወስደናል;(6) ሲሉ ግእዙንም ኢንተርናሽናሉንም ቋንቋ አስከትለው አቋማቸውን አሳውቀውናል ፡፡ ሌሎችም ይህንኑ መለኮታዊ ፅንሰ ሀሳብ #ኮፒ ፔስት ; ሲያደርጉ አንድም በፌስ ቡክ ሁለትም በድህረገፆቻቸው ላይ ለንባብ አብቅተውታል፡፡
እናስ እናማ አሁንም እንጠይቃለን እየሱስ መለታዊ ነው ካላችሁ ማስረጃችሁን አምጡ አራት ነጥብ፡፡

1ጢሞ 3፡16 እየሱስ አምላክ መሆኑን ወይስ መፅሀፍ ቅዱስ መለኮታዊ አለመሆኑን ማስረጃው ለየቱ ነው?

ሆሴዕ 11፡9 # እኔ አምላክ እንጂ ሰው አይደለሁም; ብሎ አምላክ ተናግሮ ሳለ ሚሽነሪዎች 360 ዲግሪ በመዞር አምላክ ሰው ሆነ ይሉናል የሆነ ሆኖ አምላክ ሰው ለመሆኑ ማስረጃ እንዲያመጡ ሚሽነሪዎች ሲጠየቁ እንደ መረጃ ሲያርቡት የምናየው የመጀመሪያው አንቀፅ 1ጢሞ 3፡16 ነው(ዮሀ 1፡1 በሌላ ርእስ እመለስበተላለሁ) ፡፡ አንቀፁን ኪንግ ጀምስ ቅጂ በሚከተለው መልኩ ቢያቀርበው አይገርምም፡፡
#God was manifest in the flesh; በፌደራሉ ቋንቋ እንግዲህ #አምላክ በስጋ ታየ ; ተብሎ ይተረጎማል ፡፡ ይህ ነው እንግዲህ አምላክ ስጋ ለብሶ መጣ ብለው እንዲያምኑ በውድም በግድም ካስገደዳቸው አንቀፆች አንዱ የሆነው ፡፡ በመሆኑም የዛሬውን ርእስ በዚህ አንቀፅ ዙሪያ ላይ አንዲሆን ታስቧልም ተደርጓልም፡፡ ብቻ አንተ ነብብህን ቀጥል….
እግዚአብሄር በስጋ ተገለጠ ወይም በግሪኩ theos ephanerothe en sarki የሚለው አንቀፅ ንባብ የሚገኘው እንግዲህ ንጉስ ጀምስ ቅጂ በመባል በሚታወቀው በክርስትናው አለም ሰፊ ተቀባይነት ካላቸው መጽሀፍ ቅዱሶች አንዱ በሆነው የመፅሀፍ ቅዱስ አይነት ነው ፡፡ ሚሽነሪዎችም እስከ ቅርብ ጊዜ ድረስ ይህንን አንቀፅ በማቅረብ አምላክ ስጋ ለብሶ ምድር ላይ መምጣቱን ለመንገር ያላሰለሰ ሙከራ አድርገዋል ፡፡ በነገራችን ላይ እዚህ ላይ አንድን ነገር ማንሳት እፈልጋለው በመጀመሪያ አስተምሮቱ የ እየሱስ አለመሆኑ በቀዩ ሊሰመርበት ይገባል ፡፡ ሲቀጥል ደግሞ ይህ አንቀፅ የተገኘው በአስተምሮ ከእየሱስ ጋር በተቃርኖ ሚታወቀው ከ ጳውሎስ መልእክት ውስጥ መሆኑ ነው፡፡(7)
ተመልከት ይህ አንቀፅ incarnation of God ወይም አምላክ ሰው ለመሆኑ መረጃ ነው ሲሉ ደግመው ደጋግመው ሚሽነሪዎች ለምእተ አመታት ሰብከውበታል ፡፡ አንዱም ከሌላው እየተቀባበሉ እንደ ገደል ማሚቱ አስተጋብተውታል
Best, W. E. (1971). The Impeccable Christ. በተሰኘ መፅሀፉ እንዲህ ሲል ፅፏል # 1ጢሞጥዮስ 3፡16 ፈጣሪ ሰው ሆኖ መገለጡን ያበስራል;(8) ብሎናል ይህ እንግዲህ አንዱ ምሳሌ ነው፡፡
አሁን ባንተም ላይ የሚነሳ ጥያቄ አለ? አምላክ ሰው መሆኑ ከተገለፀ ፣ ይህ አስተምሮ በመፅሃፍ ቅዱስ ላይ መሰረት ካለው አንተ አምላክ ሰው ሆኖ አልተገለፀም ለማለት የደፈርገው ምን መረጃ ቢኖርህ ነው ልትለኝ ነው፡፡ እኔም መረጃዬ ጥናት እና ምርምር ነው አይልኩህ ወደ ቁምነገሩ ዘው ብዬ ልለፍ
1. እንዳልኩህ ይህ አንቀፅ የሚገኘው ኪንግ ጀምስ በተሰኘውን የመፅሀፍ ቅዱስ ቅጂ ሲሆን ይህም ቅጂ ሲፃፍ መሰረቱ ያደረገው በግሪኩ Textus Receptus ወይም Received Text በመባል የሚታወቀውን በ1516 Desiderius Erasmus በተባለ ምሁር የተዘጋጀውን ፅሁፍ ነው፡፡ እመነኝ ዛሬ ዛሬ ላይ ለ ኪንግ ጀምስ ቅጂ ምንጭ ሊሆን የቻለውን ይህን ፅሁፍ ምሁራን አጠኑት አጥንተውም ሲያበቁም የደረሱበት ማጠቃለያ እንደሚያሳየው ከሆነ ይህ ቴክሰስ ሪሴፐተስ በመባል የሚታወቀው ፅሁፍ ምንጩ ያደረገው ጥንታውያኑን የመፅሀፍ ቅዱስ ቅጂ አለመሆኑን ነው፡፡ ይልቁንም ይህ ፅሁፍ መሰረቱ ያደረገው በ 12 እና በ13 ክ/ዘመን ባሉ የባዛንተይን ቅጂዎች ላይ ነው ፡፡ በመሆኑም ምሁራን ስንት ትውልድ ካለፈ በኋላ በ 19 ክ/ዘመን መጨረሻ ተነሱና ቴክሰስ ሪሴፐተስ እንደመረጃ ሊቀርብ አይችልም አሉህ፡፡ ይልቁንም እውነታውን ከፈለክ በኢራስመስ ጊዜ የነበረትን ማንስክሪቶችን መቀበል አለብህ ሲሉ ደመደሙ፡፡ ይህን እንግዲህ እኔ አይደለሁም እያልኩህ ያለሁት እመነኝ ያንተው ምሁራን ናቸው ፡፡
Prof. Raymond Brown እንደሚልህ #“Scholarship at the end of the 19th century finally won the battle to replace the inferior Textus Receptus by new editions of the Greek NT based on the great uncial codices and other evidence made available since Erasmus’ time…”(9)
እነሆ ይህ በክርስትናው አለም ለምእተ አመታት ሲሰራበት የነበረውን ሲደመር ሲታመንበት የነበረውን ፅሁፍ ዛሬ ላይ የተነሱ ምሁራኖች ስህተት አዛሏል ሲሉ ተቃወሙት ማለትም የዚህ ቃል ካሴት ሲገለበጥ የሚሰጥህ ትርጉም ቴክሰስ ሪሴፐቶስ የሰው እጅ ገብቶበታል ወይም እስካሁን ሲታመንበት የነበረው መፅሀፍ ቅዱስ ተበርዟል የሚል ይሆናል ፡፡
ይህ ምክንያት ሆኖት ነው እንግዲህ Michael A. Barber እንዲህ ወደሚል ማጠቃለያ ያመራው
“The translators of the King James version of the 1611 used the Textus Receptus, the Received Text, for their translation. At that time this Greek text was so highly regarded that many considered it to be inspired of God. Its text read “God was manifest in the flesh.” However, the value of the Textus Receptus has since been discredited by scholars and superseded by the three major manuscripts (among others), all of them of great antiquity, and therefore nearer to the original writings of the inspired penmen: The Vatican manuscript No. 1209 of the 4th century, the Sinaitic manuscript also of the 4th century (discovered by Tischendorf at a monastery at the foot of Mount Sinai in 1844) and the Alexandrine manuscript of the early 5th century.” (10)
በ አጭሩ ይህ ባንተም በብዙሃኑ ለምእተ አመታት ሲታመንበት የነበረው የግሪኩ ቴ ክሶስ ሪሴፕቶስ ከ አገልግሎት መስጫ ክልል ውጪ ሆኗል ማለት ነው፡፡ ወይም ስለዚህ መፅሀፍ ምህራንን ምናልባት ከጠየካቸው ምታገኘው ምላሽ # ይቅርታ የሚጠቀሙበት መፅሀፍ ከአልገልግሎት መስጫ ክልል ውጪ ነው; የሚል ይሆናል ማለት ነው፡፡ ለምን? እኮ ለምን? ለምን መሰለህ ወዳጄ !
ይህ መፅሀፍ 1ጢሞ 3፡16 ጨምሮ የካተታቸው ፅሁፎች በጥንታዊነታቸው የሚታወቁት የ4 ክ/ዘ ፅሁፎች ኮዴክስ ሲናይቲከስ ኮዴክስ ቬቲካኑስ እንዲሁም የ5 ክ/ዘ ፅሁፍ ኮዴክስ አሌክሳንደሪያነስ ውስጥ ባለመኖሩ፡፡
2. ይህ theos ephanerothe en sarki በሚል ግሪከኛ ቃል ቴክሶስ ሪሴፐቶስ ውስጥ የሚገኘው ቃል ጥንታዊ ኮዴክሶች ውስጥ የለም ካልን ሌላ ጥያቄ መነሳቱ አይቀርም እሱም ok! ጥንታዊ ኮዴሶች ውስጥ የለም ካልክ አይቀር ያለው ቃል ታዲያ ምን ይሆን በል ንገረና? የሚል ይሆናል ፡፡ በሁለቱም የ4ክ/ዘ ፅሁፎች ወይም Codex Sinaiticus and Vaticanus ያለውን ቃል እንግዲህ እንዲህ አንብበው #hos ephanerothe en sarki ; ሹፍ! በኪንግ ጀምስ ቅጂ መፅሀፍ ቅዱስ ላይ ቲኦስ( theos) ወይም አምላክ የሚለው ቃል በነዚህ ፅሁፎች ላይ የለም ፡፡ ይልቁንም ሆስ “hos” የሚለው ግሪከኛ ቃል ነው ያለው ፡፡ ሆስ የሚለው ቃል ቲኦስ እንደሚለው noun ሳይሆን pronoun መሆኑ ነው፡፡ በነዚህ መካከል የለውን ልዩነት እንኳ ኢለመንተሪ ተማሪን ብትጠይቀው ሳይጨምር ሳይቀንስ ልዩነታቸውን ይነግርሀል፡፡ እናስ? እናም ይህም ጨምሮ ጨማምሮ የሚያሳይህ በመፅሀፍህ ላይ ለውጥ የተደረገ መሆኑን እንጂ ሌላ አይደለም፡፡ የሆነ ሆኖ ይህ ለውጥ እንዴት ሊከሰት ቻለ ብለህ ለመጠየቅ ትገደዳለህ ፡፡ ይህም በሁለቱ የግሪክ ቃላት መሃል ያለውን ልዩነት እንድንፈትሽ ያስገድደናል ማለት ነው፡፡ እንቀጥል……
3. ሆስ የሚለው ቃል በክሪክ ሲፃፍ OΣ (ኦሚክሮን እና ሲግማ) ተጣምረው የሚያመጡት ሲሆኑ ቲኦስ(θεός) የሚለው ደግሞ θΣ(ቴታ እና ሲግማ) ተጣምረው ሲጀምሩ የሚወልዱት nomina sacra መለኮታዊ ስም ነው፡፡ በግሪክ ቋንቋ መሰረት ደግሞ ኦሚክሮን ወደ ቴታ መለወጥ ከፈለክ የምታደርገው ነገር ቢኖር በኦሚክሮን መሃል ላይ የጎን መስመር መጨመር ነው፡፡ ወይም በተገላቢጦሹ ፡፡ ይህን ተያይዞ በመፅሀፍ ቅዱስ ቅጪዎች ላይ የተደረገው ለውጥ ሊቃውንትን ለሁለት ቢከፍል አይገርምም ብዙሀኑ ፈጣሪ ሰው ሆኖ እንደመጣ ለማፅደቅ ሲባል ሆን ተብሎ ለውጥ የተደረገበት ነው ሲሉ ፡፡ አንዳንዶቹ በዚህ ሀሳብ አይስማሙም በእይታ ስህተት የተከሰተነው ሲሉም ያክላሉ ከነዚህም አንዱ ተዋቂው የክርስትና ሊቅ ብሩስ መተዝገር አንዱ ነው ፡፡ ይህ ምሁር 1968 በታተመው The Text of the New Testament በተሰኘ መፅኀፉ ላይ ከእይታ የመነጨ ስህተት በሚል ስር 1ጢሞ 3፡16 ሚመድበውም በዚሁ መፅሀፍ ሁለተኛ እትሙ1975 ላይ ደግሞ ሆን ተብሎ ለውጥ ተደርጎበት ሊሆን እንደሚችል ሳይጠቅስ አላለፈም፡፡(11) የብሩስ መተዝገር ምርጥ ተማሪ የሆነው Prof. Bart Ehrman በ 1ጢሞ የሰፈረው አንቀፅ ቸርች ሆን ብላ የእየሱስ መለኮታዊነትን ለማፅደቅ ስትል ያደረገችው ለውጥ እንደሆነ ፅፏል፡፡(12)(13) የመፅኀፍ ቅዱሱ ሊቃውንት Keith Elliot እንዲሁም Ian Moire’s በ ኢህርማን ሀሳብ ይስማማሉ ምን ነበር ያላችሁት?
“Another reason for the deliberate change from ‘who’ to ‘God’ is that the church may have wished here to emphasize its belief in the divinity of Jesus… ;(14)
እነዚህ ሊቃውንት ሙስሊም መስለውህ እንዳትስት! በጭራሽ ያንተው ምሁራን ናቸው ይህን እያሉህ ያሉት፡፡ ይህም ለውጥ ሆን ተብሎ የስላሴ ፅንሰ ሀሳብ ለማፅደቅ ሆን ተብሎ መደረጉን ከላይ ከተጠቀሱት ምሁራን በተጨማሪ Sir Anthony Buzzard and Charles F. Hunting(15)፣ Michael Barbe(16) ወዘተረፈ ጠቅሰውታል
ኮዴክስ ሲናይቲከስ እና ቬቲካነስ ቁጥር 1209 ላይ የሰፈረው ግሪክ ቃል #hos ephanerothe en sarki ; የሚል ሲሆን # እሱ(እየሱስ) በስጋ ታየ የሚል ትርጓሜ ይኖረዋል ፡፡ እየሱስ በስጋ የመምጣቱ እና ለየመታየቱ ጉዳይ ላይ ሁሉም ይስማማል፡፡ ሙስሊሙንም ጨምሮ ….

ማጠቃለያ

ከላይ የተመለከትከው የ1 ጢሞ አንቀፅ የአምላክ ሰው መሆንን ያመለክት ዘንድ ሆን ተብሎ የተፈበረገ እንደሆነ አብዛኛው ሊቃውንት ነግረውናል ፡፡ ይንም ያደረጉበት ዋና አላማ አሁን የምታምንበትን የስላሴ አስተምሮ ለማፅደቅ መሆኑ ነው፡፡ ቸርች ሆን ብላ መፅሀፎቿ ላይ ምን አይነት ለውጥ እያደረገች እንዳለች ያንተው ምሁራን እየነገሩህ ነው፡፡ በመሆኑም 1ጢሞ የተደረጉ ጥናቶች ፈጣሪ ሰው አለመሆኑን በአንድ በኩል ሲነግርህ በበሌላ በኩል የመፅሀፍህን መበረዝ እና መከለስ ይነግርል፡፡ ከዚህ በዘለለ እየሱስ መለኮታዊ እንደሆነ ያሳያሉ ሲሉበሚሽነሪዎች ለሚቀርቡ የመፅሀፍ ቅዱስ አንቀፆች አስመልክቶ እራሳቸውን በቻሉ ርእሶች እንደምንመጣባቸው እያስታወስኩ በመጨረሻም ከላይ የቀረቡትን መረጃዎች አውቀህ ምንም ብረዛን እንዲሁም የሰውን እጅ ወዳላስተናገደው ቁርአን ና እያልኩ የዛሬውን ፅሁፍ እዚህ ጋር ለመደምደም እገደዳለሁ ያንተው ቃልአሚን፡፡
ምን ነበር ያልከው ሸይኹል ኢስላም ኢብኑ ተይሚያህ
#ህዝባችን የሀይማኖት መፅፎቻቸውን እንዳልጠበቁት አይሁዶች እና ክርስትያኖች አይደለም ፡፡ በምድር ላይ የሚገኙ የቁርአን ፅሁፎች ሁሉ ቢጠፉ እንኳ ቁርአን በህዝበ ሙስሊሙ ልቦና ውስጥ ተጠብቆ ይቆያል;(17)

References Sources
1. አህመዲን ጀበል ፣ ክርስቶስ ማ ነው 303 ጥያቄዎች
2. ታሪኩ አበራ ፣ እየሱስ ማ ነው 3ኛ እትም፣2003 መግቢያ ፅሁፍ
3. ታሪኩ አበራ ፣ እየሱስ ማ ነው 3ኛ እትም፣2003 ገፅ 7
4. በመጋቤ ጥበብ ሰለሞን፣ አንድ አምላክ ብቻ ለሙስሊም ጥያቄዎች አጠቃላይ ምላሽ፣2003 ገፅ 140
5. አባ ሳሙኤል፣ በ ኢትዮጵያ የሐይማኖት መቻቻል አለን ፣3ተኛ እትም፣ ገፅ136
6. መምህር ኪዳነ ማሪያም ጌታሁን ፣ክርስቶስ ከቁርአን ጋር ምን አገናኘው 1999 2ተኛ እትም ገፅ 78
7. ህግና ትእዛዝት በቀይ መስመር ላይ የሚለውን ፅሁፌን በዚሁ ፔጅ ላይ አንብብ
8. Best, W. E. (1971). The Impeccable Christ. U.S. : Lightning Source Inc. p. 23
9. Brown, R. E. (1997). An Introduction to the New Testament. U.S. : Yale University Press. p. 52
10. Barber, M. A. (2006). Should Christians Abandon the Doctrine of the Trinity?. Boca Raton, Florida: Universal Publishers. p. 47
11. Metzger, B. M. (1968). The Text of the New Testament : Its Transmission, Corruption, and Restoration, 2nd ed. Oxford: The Clarendon Press. p. 187 , A Textual Commentary on the Greek New Testament, 4th ed. London: United Bible Societies. pp. 573-574
12. Ehrman, B. D. (1993). The Orthodox Corruption of Scripture: The Effect of Early Christological Controversies on the Text of the New Testament. Madison Avenue, New York: Oxford University Press.,
13. Ehrman, B. D. (2005). Misquoting Jesus: The Story Behind Who Changed the Bible and Why. New York: HarperSanFrancisco. pp. 157-158
14. Elliot, K., & Moir, I. (1995). Manuscripts and the Text of the New Testament: An Introduction for English Readers. London: T&T Clark Ltd. p. 73
15. Buzzard, A., & Hunting, C. F. (1998). The Doctrine of the Trinity: Christianity’s Self-Inflicted Wound. Lanham, Maryland: International Scholars Publications. p. 303
16. Barber, M. A. Op. Cit. p. 48
17. ኢብኑ ተይሚያህ መጅሙእ አል ፈታዋ ቅፅ 17 ገፅ 436
መርፊው
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 260
Joined: Sat Oct 15, 2011 4:22 pm

Postby መርፊው » Thu Jun 06, 2013 8:07 pm

ተላኪውን (እየሱስ) እና ዕውነታው በራሱ አንደበት ባይብል
From :-Bahise Haqe
~~~~~~~~~~~~
1. ትምህርቱ ከራሱ እይደለም
‹ለዚህ ኢየሱስ መለሰ እንዲህም አላቸው፦ ትምህርቴስ ከላከኝ ነው እንጂ ከእኔ አይደለም፤› ዩሐ 7፡16 ላኪና ተላኪ?

2. ማንነቱ እራሱ ሲገልጽ ((ነቢይ))

‹ዳሩ ግን ነቢይ ከኢየሩሳሌም ውጭ ይጠፋ ዘንድ አይገባውምና ዛሬና ነገ ከነገ በስቲያም ልሄድ ያስፈልገኛል።› ሉቃስ 13፡33

‹ኢየሱስ ግን፦ ነቢይ ከገዛ አገሩና ከገዛ ቤቱ በቀር ሳይከበር አይቀርም አላቸው። ›ማቴ 13፡57

3. አምላክ አላው (ወደ አምላኬና ወደ አምላካችሁ)

‹ኢየሱስም፦ ገና ወደ አባቴ አላረግሁምና አትንኪኝ፤ ነገር ግን ወደ ወንድሞቼ ሄደሽ። እኔ ወደ አባቴና ወደ አባታችሁ ወደ አምላኬና ወደ አምላካችሁ ዓርጋለሁ ብለሽ ንገሪአቸው አላት።›› ዩሐ 20፡17

‹‹እውነተኛ አምላክ ብቻ የሆንህ አንተን የላክኸውንም ኢየሱስ ክርስቶስን ያውቁ ዘንድ ይህች የዘላለም ሕይወት ናት። የዮሐንስ ወንጌል 17፡3

4. ለዚህ አምላክ ይጸልይ ነበር

‹‹ጥቂትም ወደ ፊት እልፍ ብሎ በፊቱ ወደቀና ሲጸልይ።..› ማቴ 26፡39

5. የተላከው

‹‹እርሱም መልሶ፦ ከእስራኤል ቤት ለጠፉት በጎች በቀር አልተላክሁም አለ። ማቴ 15፡24

6. ሰው ነው

‹የእስራኤል ሰዎች ሆይ፥ ይህን ቃል ስሙ፤ ራሳችሁ እንደምታውቁ፥ የናዝሬቱ ኢየሱስ እግዚአብሔር በመካከላችሁ በእርሱ በኩል ባደረገው ተአምራትና በድንቆች በምልክቶችም ከእግዚአብሔር ዘንድ ለእናንተ የተገለጠ ሰው ነበረ፤› የሐዋሪያስራ 2፡22

7. ከራሱ ምንም ማድረግ አይችልም

‹እኔ ከራሴ አንዳች ላደርግ አይቻለኝም፤ እንደ ሰማሁ እፈርዳለሁ ፍርዴም ቅን ነው፥ የላከኝን ፈቃድ እንጂ ፈቃዴን አልሻምና።› ዩሐንስ ወንጌል 5፡30

‹ኢየሱስም እንዲህ አላቸው፦ የእኔስ መብል የላከኝን ፈቃድ አደርግ ዘንድ ሥራውንም እፈጽም ዘንድ ነው።›ዩሐ 4፡34

ታዲያ ለምን ይሆን የተላከ መልክተኛ(ረሱል) ነው ማለታችን መወገዙ ?

8. የመጀመሪያ ያስተማረው ትዕዛዝ
‹ኢየሱስም መልሶ እንዲህ አለው፦ ከትእዛዛቱ ሁሉ ፊተኛይቱ። እስራኤል ሆይ፥ ስማ፤ ጌታ አምላካችን አንድ ጌታ ነው፥ ማር 12፡29

-->አዎ የሱ የኛም የጋራ አምላክ ‹‹አምላካችን›› ማለቱ ለዚያ ነው

9. ዕውቀቱ ከአምላክ ጋር ይነጻጻር ይሆን ?
‹ስለዚያች ቀን ወይም ስለዚያች ሰዓት ግን የሰማይ መላእክትም ቢሆኑ ልጅም ቢሆን ከአባት በቀር የሚያውቅ የለም። › ማር 13፡32

10. ለማን መሰገድ አንዳለበት ሲያስተምር
‹ኢየሱስም መልሶ፦ ለጌታ ለአምላክህ ስገድ እርሱንም ብቻ አምልክ ተብሎ ተጽፎአል አለው። ›ሉቃስ 4፡8

11. እየሱስ እራሱን
* ዩሐ 7፡16፤ ዩሐ 16፡5፤ሉቃስ 10፡16፤ዩሐ 7፡29 .. .. ..ከ10 ያላነሱ ቦታዎች እንደ ሌሎች መልክተኛ(ረሱል) መሆኑን ይገልጻል፡፡

12. ወደፊትም ይችላል የሚል ካለ ወደፊት ያውቃል

‹..እኔ እሆን ዘንድ አባቴም እንዳስተማረኝ እነዚህን እናገር ዘንድ እንጂ ከራሴ አንዳች እንዳላደርግ በዚያን ጊዜ ታውቃላችሁ። ›ዩሐ8፡28

13. ጌታ ነው የሚለው ሁሉ ((የሚለኝ ሁሉ))

‹‹ጌታ ሆይ፥ ጌታ ሆይ፥ የሚለኝ ሁሉ መንግሥተ ሰማያት የሚገባ አይደለም።›› ማቴ 7፡21 ጀምሮ ተመልከቱ በጣም የሚገርማችሁ ይህን የተባሉት በስሙ ትንቢት የሚናገሩ፤አጋንንት የሚያወጡ … ወዘተ አሁን አንደምናየው እልል የሚባልላቸው እንጂ ተራ አማኞች አለመሆኑ ነው ልክ ነኝ ?

14. በተጨማሪም ከንቱነታቸው ሲገለጽ

*ይህ ሕዝብ በከንፈሩ ያከብረኛል፥ ልቡ ግን ከእኔ በጣም የራቀ ነው፤ የሰውም ሥርዓት የሆነ ትምህርት እያስተማሩ በከንቱ ያመልኩኛል ብሎ በእውነት ትንቢት ተናገረ።ማቴዎስ 15፡8-9

15. ቸር ሲባል፡-ቸር ማን መባል አንዳለበት ሲያስተምር

‹‹ኢየሱስም፦ ስለ ምን ቸር ትለኛለህ? ከአንዱ ከእግዚአብሔር በቀር ቸር ማንም የለም።›› ማቴ 10፡18 ሉቃስ 18፡19
16 . ወዘተ

…. የአምልኮ ስርዓቱ በዝርዝር በማየት እንሻአላህ ይቀጥላል

ሰላም ቅኑን መንገድ በተከተለ ላይ ይሁን አሚን
መርፊው
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 260
Joined: Sat Oct 15, 2011 4:22 pm


Return to Warka General

Who is online

Users browsing this forum: No registered users and 9 guests