አብቹን ምን በላው....

The Love Forum (love, relationship) (የኔ ቆንጆ እንተዋወቅ :-)

አብቹን ምን በላው....

Postby ገልብጤ » Sun Mar 03, 2013 9:11 pm

አብቹ የ16 አመት ጉብል ነው፤ ግን ደግሞ የራስ ዳሽንን ያህል ግዙፍ ታሪክ ባለቤት፡፡ ግን ደግሞ ተንኮል፣ ግብዝነትና ቅናት በወለዱት ከንቱ አስተሳሰብ የሰናፍጭ ቅንጣት ያህል ቦታ ያልተሰጠው ምስኪን ጀግና! አብቹ በቼኮዝሎቫኪያዊው ጸሐፊ አዶልፍ ፓርለሳክ ብዕር በአጭሩ እንዲህ ይገለፃል፡፡
አብቹ የተወለደው በ1912 ዓ.ም ነው፤ ቦታው ደግሞ የዛሬው ሰሜን ሸዋ (ኦሮሚያ ክልል) ወረጃርሶ ወረዳ፡፡ አባቱ የወረጃርሶ ጦር መሪ ነበሩ፡፡ በጣሊያን ወረራ ዋዜማ ላይ በተፈጥሮ ህመም ሞቱና ዘመድ አዝማድ አልቅሶላቸው በወጉ ተቀበሩ፡፡
አባት ሲሞት ልጅ በአባቱ እግር ተተክቶ ኃላፊቱን መወጣት የቆየ ልማድ ነበረና የጃርሶን ጦር የአብቹ ሁለት ወንድሞች እንዲመሩት ይደረጋል፡፡ የሰላሌና የበጌምድርን ጦር በበላይነት የሚመሩት ራስ ካሳ ቢሆኑም የጃርሶ ጦር መሪዎች የሚታዘዙት ግን ለራስ ካሳ ልጅ ደጃዝማች አበራ ነበር፡፡ በ1928 ዓ.ም ፋሽስት ጣሊያን አገራችንን መውረሩ እንደተሰማ ዘገራቸውን በቁጣ ከነቀነቁ እውነተኛ ኢትዮጵያን መሃል የአብቹ ወንድሞች ተጠቃሽ ሆኑ፡፡ የሁለቱን አናብስት ወንድሞቹን ወኔ የተመለከተው የ16 አመቱ ጉብል (አብቹም) “ከወንድሞቼ ጋር ካልዘመትሁ ሞቼ እገኛለሁ” አለና ቤተሰቡን አስቸገረ፡፡ እንኳን ጥይትን ራሱ ሞት ጥርሱን አግጥጦ ቢመጣበትም ፈርቶ አንዲት ጋት መሬት እንኳ ወደኋላ ላያፈገፍግ በምኒሊክ ስም ማለ፡፡
የልጃቸውን ከብረት የፀና አቋም የተረዱት እናትም “የአብቹን ነገር አደራ!” ብለው ለደጃዝማች አበራ አስረከቡ፡፡ ደጃዝማች አበራ አውሮፓ ሄዶ ሲማር የነበረ ብልህና ወጣት መኮንን ነው፡፡ አብቹም አገሩ ላይ በወቅቱ ይሰጥ የነበረውን ዘመናዊ ትምህርት አጠናቅቆ ለከፍተኛ ትምህርት ወደ አውሮፓ ሊሄድ ሲሰናዳ አውሮፓዊ ጠላት መጣና ሩቅ የነበረ ህልሙ ተደናቀፈ፡፡
ስለዚህ አብቹ ያገሩን ጠላት ለመፋለም ከወንድሞቹ ጋር መዝመት አለበት፤ ዘመተ፡፡ ከወንድሞቹ ጋር ይዝመት እንጂ የደጃዝማች አበራና የእሱ ፍቅር ለጉድ ነው፡፡ አብቹ አዕምሮው ብሩህ ጉብል ነው፡፡ እድሜውና ድርጊቱ በፍፁም ሊገናኙ የሚችሉ አይመስሉም፡፡
ከሰላሌ የተንቀሳቀሰው ጦር የቻለ ስንቁን በፈረስ፣ በበቅሎና በአህያ ጭኖ፤ ያልቻለ ደግሞ በትከሻው ተሸክሞ ለሰባት ወራት በእግሩ ሲኳትን ከቆየ በኋላ ለጦርነት የተፈጠረ ከሚመስለው የትግራይ ተራራማ ግዛት አምባላጌ ደረሰ፡፡ የአንበሳው አሉላ አባነጋ የትውልድ ቦታ ከሆነው ቆላ ተምቤን በመውረድም አምባራዶም ከተባለ ቦታ ላይ ከወራሪው ኃይል ጋር የሞት ሽረት ትግል አካሄደ፡፡
በውጊያው ላይ እጅግ በርካታ የፋሽስት መንጋ አንገቶችን እንደ ጐመን የቀነጠሱ ጀግኖች የአገራቸውንና የወገናቸውን ቀጣይ ውርደት ሳያዩ በክብር ወደቁ፡፡ ከእነዚህ አንበሶች መሃል የአብቹ ወንድሞች ይገኙበታል፡፡ አንደኛው ወንድሙ ይማረክ ወይም ይሙት እርግጡ ያልታወቀ ሲሆን የሌላኛውን ወንድሙን አስከሬን ግን ከአንዲት ዋርካ ዛፍ ስር ቀብሮ እርሙን ተወጣ፡፡
ሆኖም ደጃዝማች አበራን ክፉኛ የፈተነ አጋጣሚ ተፈጠረ፡፡ አብቹ በአደራ የተሰጠው ጓደኛውም የአደራ ልጁም ነው፡፡ ይህ እንደ ነፍሱ የሚወደው የክፉ ቀን ባልደረባው ከወንድሙ መቃብር አጠገብ ካለች አንዲት ድንጋይ ላይ ቁጭ ብሎ ሌት ከቀን ይተክዝ ጀመር፡፡ እህል ውሃ ሳይቀምስ ለሁለት ቀናት በመቆየቱም ደጃዝማች አበራን እጅግ አሳሳቢ ሁኔታ ገጠመው፡፡
አብቹ “እህልም ሆነ ውሃ አልቀምስም” ብሎ ያስቸገረው ሞቱን አይቶ ለቀበረው ወንድሙ አዝኖ ሳይሆን ሞቱም ሆነ ህይወቱ ያልታወቀው ሌላኛው ወንድሙ ምን እንደነካው፣ የት እንደደረሰ ቁርጡን ሳያውቅ እህል ውሃ እንደማይቀምስ ለራሱ ስለማለ ነው፡፡ በዚህ ላይ የጃርሶ ጦር መሪ የለውም ወንድማማቾች በጋራ ይመሩት ነበር፤ እነሱም በአንዲት ጀንበር ጦርነት ተለዩት፡፡
ደጃዝማች አበራን ያስጨነቀውም የአብቹ እህል ውሃ ለመቅመስ “አሻፈረኝ” ማለትና የጃርሶ ጦር መሪ ማጣቱ ነው፡፡ እርግጥ መሪነቱን ለሌላ ሰው መስጠት ይቻላል፤ ግን አብቹ ቢቀየመውስ? መጀመሪያ ለብዙ ዘመናት አባቱ፤ ከዚያም “የማይጨው ዘመቻ” የሚባለው ግዳጅ ከተጀመረበት ጊዜ ጀምሮ ደግሞ ወንድሞቹ በጋራና በፍቅር ሲመሩት ነበር፡፡ ይህንን የቆየና ህዝቡ አምኖ አክብሮት የቆየውን ልማድ እንዴት መሻር ይቻላል? “አብቹ ይምራው” እንዳይባል ገና የ16 አመት ጉብል ነው፡፡ በ16 አመት ጉብል የሚመራ ጦርስ እንዴት ከሰለጠነ፣ ከተደራጀና በመሳሪያ ፍፁም የበላይነት ካለው የአውሮፓ ጦር ጋር ውጊያ ማካሄድ ይቻላል? የደጃዝማች አበራ ጭንቅላት በሃሳብ እንደ እንቧይ ሊፈርጥ ምንም አልቀረውም፡፡
የሚያደርገው ቢያጣ ሽማግሌዎችንና ሌሎች አማካሪዎቹን ሰብስቦ በጉዳዩ ላይ ሰፊ ጊዜ የፈጀ ውይይት ተካሄደ፡፡ መጨረሻ ላይ አንድ የጃርሶ ጦር አባል “እኔ አሳምነዋለሁ፤ እህል ውሃ እንዲቀምስም አደርጋለሁ” ብሎ ኃላፊነቱን ወሰደ፡፡ በምን ዘዴ እንዳሳመነው ባይታወቅም እውነትም አብቹ ሁለት ቀንና ሁለት ሌት ብቻውን ከተቀመጠበት ድንጋይ ላይ ተነስቶ ከጦሩ ጋር ተቀላቀለ፡፡ ግን እህል የሚቀምሰው ጥያቄው ከተመለሰለት ብቻ መሆኑን አስገነዘበ፡፡
ጥያቄውም “ሁለት መቶ ወጣቶች ይሰጡኝና ወንድሜን ከጣሊያን ምርኮ ነፃ ላውጣው” የሚል ነው፡፡ የጃርሶን ጦርም አጐቱ ቀኛማች ገለታ እና ቀኛዝማች ሼህ ሁሴን አባወርቁ እንዲመሩት ፈቀደ፡፡
ወጣቶችን ብቻ ከጐኑ ለማሰለፍ ያቀረበው ሃሳብ በቦታው የነበሩ አንዳንድ አዛውንቶችን ቢያስቀይምም ደጃዝማች አበራን ግን ከህሊና ምጥ ገላገለው፡፡ የጠየቀው እንደሚሟላለትም ቃል ገባለት፡፡
የደጃዝማቹን ፈቃድ ሲያገኝ የአብቹ ደስታ ወሰን አልነበረውም፡፡ እንዲያውም ያንን የልጅነት አዕምሮውን ክፉኛ የበጠበጠውን ሀዘኑን እርግፍ አርጐ ትቶ በሚገርም ደስታ ቀየረው፡፡ የቀሩትን ሦስት በሬዎች አርዶም ጦሩን ሲጋብዝ፣ ሲዘፍንና ሲያዘፍን አመሸ፡፡ ሊነጋጋ ሲል የተመረጡለትን 200 ያህል ወጣቶች አስከትሎ በሞቀ ቀረርቶና ፉከራ ወደ ጣሊያን ምሽግ ገሰገሰ፡፡ ከዚያን ቀን ጀምሮ “አብቹን አየሁ” የሚል ጠፋ፡፡
ከተወሰነ ጊዜ በኋላ የአብቹ ዝና በትግራይ ሰማይና ምድር ብቻ ሳይሆን በሮማ ከተማ ጭምር በመናኘቱ እጅግ በርካታ ወጣቶች አለቆቻቸውን፤ ማለትም ራስ ካሳን፣ ራስ ሥዩም መንገሻንና ደጃዝማች አበራን በመክዳት ከእሱ ጦር ጋር ይቀላቀሉ ጀመር፡፡
በአብቹ የሚመራው ጦር ጠላቱ ላይ ጥቃት የሚፈፅመው ጠላት ባላሰበው አሳቻ ስፍራና ሰዓት በመሆኑ ነፍሰ በላዎቹን ፋሽስቶች ብርክ ያስይዛቸው ጀመር፡፡ የአብቹን ጥቃት መቋቋም የተሳነው ፋሽስት፤ ሰላማዊውን ሰውና እንስሳትን ሳይቀር በአረመኔነት መጨፍጨፉን ስላጠነከረ ንጉሡና ራሶች አብቹ በቁጥጥር ሥር እንዲውል ወሰኑ፡፡ ግን አብቹን ማን ይይዘዋል? አብቹኮ በለጋነቱ የሚታወቀው ጉብል ሳይሆን ተዓምር ሊባል በሚችል ሁኔታ እሳተ ነበልባል ሆኗል፡፡
አብቹን አባብለውም ሆነ በሃይል ይዘው እንዲመጡ የሚላኩት ሰዎች ሁሉ የአብቹ አመራር እየማረካቸው በዚያው እየቀሩ ራሶችንና ደጃዝማቾችን አስቸገሩ፡፡ ከሁሉ የሚገርመው ኢትዮጵያን ለመውጋት ከጣሊያን ፋሽስቶች ጋር የመጣ አንድ ባታሊዮን ኤርትራዊ ጦር አዛዡን ጣሊያናዊ ገድሎ ከአብቹ ጦር ጋር መቀላቀሉ ነው፡፡ከጣሊያን በሚማርከው ትጥቅና ስንቅ የአብቹ ክንድ እየፈረጠመ፤ እግረ መንገዱንም በጣሊያኖችና አሽቃባጮቻቸው ላይ የሚፈፅመው ቅጣት እየጠነከረ በመሄዱ ጣሊያኖች በመርዝ ጋዝ ህዝቡን ያሰቃዩት ጀመር፡፡ በዚህ የተነሳ አብቹ በወገኖቹም በጠላቱም እጅግ ተሳዳጅ ሆነ፡፡
ንጉሡም ሆኑ ራሶች “ልጁን እሰሩት!” የሚል ቀጭን ትእዛዝ ለበታች ሹሞቻቸው በተደጋጋሚ ቢያስተላልፉም አብቹ የእሳት አሎሎ ሆነ፡፡ እንዲያውም ከትግራይ በጄኔራል ተስፋ ጽዮን፣ ከኤርትራ በጄኔራል ሃብቶም፣ ከጐጃም በጄኔራል ጋሹ፣ አንዲሁም ከሰላሌ በጄኔራል ወርቁ የሚመራ አንድ አንድ በድምሩ አራት ባታሊዮን ጦር ተቀላቀለውና በንጉሡም ሆነ በፋሽስት ጠላቶቹ ዘንድ ቁጥር አንድ ስጋት እየሆነ መጣ፡፡ “የልጁ ሠራዊት በዚህ በኩል አለፈ” ከተባለ ምድረ ፋሽስትና ባንዳ እንደ ቄጠማ እየራደ የሚይዝ የሚለቀውን ማጣት የየእለት ተግባሩ ሆነና አረፈው፡፡ የአብቹን እጅ በቀላሉ መያዝ አልሆንለት ያለው ደጃዝማች አበራ፤ አንድ ቀን የተሻለ ዘዴ ተጠቀመና ተሳካለት፡፡ እሱም “አበራ በጠና ታሟልና በነፍሱ ድረስ ብላችሁ ንገሩት፡፡ በእኔ የሚጨክን አንጀት የለውም” የሚል መልእክት በታማኝ ወዳጁ አማካይነት ለአብቹ እንዲደርሰው ማድረግ ነበር፡፡
መልእክቱ ሲደርሰው እውነትም አብቹ መዋል ማደር አልቻለም፡፡ ድንገት ከደጃዝማች አበራ ዋሻ ዘው ሲል ደጃዝማቹም ሆነ አብረውት የነበሩ መኳንንትና አሽከሮች ልክ መብረቅ የወረደባቸው ያህል ክው ብለው ቀሩ፡፡ ከጥቂት የመረጋጋት ጊዜ በኋላ ደጃዝማች አበራ በአይን ጥቅሻ ለአሽከሩ የሆነ ምልክት ሰጠው - “እሰሩት” የሚል ነው መልእክቱ፡፡
የደጃዝማቹ አሽከር ተጨማሪ አሽከሮችን ለመጥራት ከድንኳን በፍጥነት ቢወጣም በሌላ ሃይል እየተነዳ በምርኮኛ መልክ ሁለት እጁን ወደላይ ሰቅሎ ሲመለስ ጊዜ አልፈጀበትም፡፡ በዚህ ጊዜ “ኮሌኔል ኮኖቫሎቭ” የተባለ ሰው (ዋሻው ውስጥ ከነበሩት አንዱ) ደንግጦ “ምርኮኞች ሆንን ማለት ነው?” ብሎ አብቹን ሲጠይቀው አብቹ የተሟላ ህሊና ያለውን ሰው ቀርቶ የግራኞችን ባህር አንጀት ሳይቀር የሚያላውስ መልስ ይሰጣል፡፡ እንዲህ ሲልም ይጠይቃል፡-
“ደጃዝማች ገና ከሰላሌ ስንነሳ ታማኝነቴን በምኒሊክ ስም ቃል የገባሁት ላንተ እንጂ ለሽማግሌዎች (ራስ ሥዩምንና ራስ ካሣን ማለቱ ነው) ወይም ለንጉሡ አይደለም፡፡ እኔ ንጉሥ አይደለሁም፤ ተራ ወታደር እንጂ፡፡ እና እኔ ሁለት ሦስት ወር ደሴ ተጐልቼ (ቆላ ተምቤን፣ አምባራዶምና አቢአዲ አካባቢ ዘግናኝ ጦርነቶች ሲካሄዱ ንጉሡ ደሴ ሆነው “ተከላከሉ እንጂ አትዋጉ” ሲሉ ስለነበር ያንን በአሽሙር ለመግለጽ ፈልጐ ነው) ጣሊያኖች እጄን እስኪይዙኝ አልጠብቅም፡፡ ላንተ ግን አሁንም በምኒሊክ ስም፣ በምኒሊክ አምላክ በድጋሚ ቃሌን እሰጣለሁ፡፡ ላንተ እሞታለሁ፡፡ ተመለስ! ላልኸው ግን የት ነው የምመለሰው? ምንስ መመለሻ ቤት አለኝና? እዚህም እዚያም እሳት እየነደደ እንዴት ቁጭ ልበል? ሽማግሌዎቹ ጦር ሊሰዱብኝ አስበው ከሆነ ደግ፤ ምንም ችግር የለም፡፡ ግን እኔ ከእነሱ ጠብ እንደሌለኝና የሀገሬ ታማኝ ወታደር እንደሆንኩ አስረዳልኝ፡፡ ደጃዝማች ስማኝማ! ምንአልባት ካልተገናኘን እማማን ደስተኛ እንደነበርኩ ንገራት፡፡ በእሳተ ገሞራ መሃል ማለፍ ቢኖርብኝም ወደ ሰላሌ እመለሳለሁ” አለና የደጃዝማች አበራን ዋሻ ለቅቆ ወጣ፡፡ የት እንደሄደ ግን የሚታወቅ ነገር የለም፡፡
ብቻ ከሁለት ሺህ በላይ ወታደሮቹን በትግራይ በረሃዎች እያዟዟረ ጣሊያኖችንና ባንዳዎችን ድባቅ መምታቱን ቀጠለ፡፡ አቢአዲ አለ ሲባል አምባ አራዶም፤ አምባራዶም ታየ ሲባል መቀሌ፣ መቀሌ አለ ሲባል ማይጨው እየተወረወረ እንኳን ጠላቱን ወዳጆቹን እነደጃዝማች አበራንና ሁለቱን ራሶች፣ እንዲሁም ንጉሠ ነገሥቱን ግራ አጋባቸው፡፡
እንዲያውም አንዳንዴማ በሌለበት ቦታ ሁሉ “እዚህ አካባቢ አብቹ ታየ” ከተባለ ጣሊያን ጓዙን ሸክፎ መፈርጠጥ ይጀምራል፡፡ ግና ምን ያደርጋል፤ አብቹ ጦርነት ውስጥ የገባው ከጣሊያን ጋር ብቻ ሳይሆን ከገዛ ወገኖቹ ጭምር ነው፡፡ እሱ “ጣሊያንና ባንዳን ቀጥቼ ሀገሬን ከወረራ አድናለሁ” ሲል የንጉሡን ትእዛዝ ያለምንም ማቅማማት የሚፈፅሙት ራሶች ደግሞ “ምን ሲደረግ?” ባዮች ናቸው፡፡ ይህ ደግሞ ለአንድ የ16 አመት ጉብል የማይታሰብ ቢሆንም አብቹ ግን እንደ ብረት ጠንካራ በመሆን ሁሉንም የመከራ አይነቶች በፅናት መጋፈጡን ቀጠለ፡፡
በአስቸጋሪዎቹ የተምቤን ተራራዎች ጣሊያንን አይቀጡ ቅጣት ሲቀጣ ቆይቶ የወገን ጦር ወደማይጨው እንዲሰባሰብ በመታዘዙ ምንም እንኳ ከጦሩ እዝና ቁጥጥር ውጭ የሚንቀሳቀስ፣ በንጉሡና በራሶች ዘንድ ባለጌና ወሮበላ ተደርጐ የሚታይ ቢሆንም ለደጃዝማች አበራ የተለየ ፍቅር ስለነበረው ጀግኖቹን እየመራ ለወሳኝ ፍልሚያ ወደማይጨው ተጓዘ፡፡
ጉዞው ግን በቃል ሊገለፅ የማይችል መራራና ሌት ከቀን ከሞት ጋር በመጋፈጥ ሞትን ራሱን አሸንፎ ማለፍን የሚጠይቅ ነበር፡፡ የመጨረሻው የኢትዮጵያ ዕጣ ፈንታ የሚወሰነው ማይጨው ላይ በመሆኑም በራስ እምሩ ኃይለሥላሴ ከሚመራው ጦር በቀር የሶስቱ ራሶች (ራስ ሥዩም መንገሻ፣ ራስ ሙሉጌታ ይገዙና ራስ ካሣ ኃይሉ) ጦር አንድ ቦታ ላይ በመቀናጀት ጠላትን ቀጥቶ ዳግማዊ አድዋን በማይጨው ለመድገም ተወስኗል፡፡ ምንም እንኳ ራሶችና ደጃዝማቾች በእድሜም ሆነ በስልጣንና በጦር ብዛት የተራራ ያህል ቢበልጡትም አብቹ ለዚህ ወሳኝ ጦርነት አስፈላጊነቱ ጥርጥር የለውም፡፡ አብቹም ሆነ በእሱ የሚመሩት አንበሶች መንገድ ላይ የሚገጥማቸውን መሰናክል ሁሉ በከፍተኛ ወኔ እየተጋፈጡ ማይጨው ደረሱ፡፡
ከፊት ነፍሰበላው የጣሊያን ጦር ከኋላ ደግሞ መንጋ የባንዳ ግባሶ የጥይት በረዶ እያዘነበባቸው ከሰው የተፈጠሩና በሞት የሚረቱ ሳይመስሉ ግዳጃቸውን ተአምር በሚመስል ሁኔታ ተወጡ፡፡ ከጣሊያን ምሽግም እየዘለሉ ገቡና የተወለደበትን ቀን ያስቆጥሩት ጀመር፡፡ ግና ምን ይሆናል ከወገን በኩል ምንም አይነት አጋዥ ኃይል ማግኘት አልቻሉም፡፡ ስለሆነም ጄኔራል ተስፋ ጽዮንና ጄኔራል ጋሹ የተባሉትን ምርጥ አዛዦችንና በርካታ አባሎቻቸውን አጥተው ወደ ሰላሌ መመለስ ግድ ሆነባቸው፡፡
ሰላሌ ከመጡ በኋላ ከደጃዝማች አበራና ከሌሎች ወዶ ዘማች ፈረንጆች ጋር ተሰነባብተው ወደ ጃርሶ አመሩ፡፡ በተለይ አብቹ ከአንድ የጣሊያን ጀኔራል የማረከውን ሽጉጥ ለደጃዝማች አበራ፣ ሁለት ጐራዴዎችን ለሁለት ፈረንጆች በሽልማት መልክ ሰጥቶ በጥቁር ፈረሱ ላይ ወጣና ቁልቁል ወደ ጃርሶ ከነፈ፡፡ ግን የት ደርሶ ይሆን? የሳምንት ሰው ይበለን፤ እንመለስበታለን፡፡


ከአዲሳድማስ የተወሰደ
Last edited by ገልብጤ on Wed Mar 13, 2013 10:37 pm, edited 6 times in total.
ያልበሰለ ፖለቲከኛ ስለቀጣዩ ምርጫ ሲያስብ
የበሰለ ፖለቲከኛ ስለቀጣዩ ትውልድ ያስባል
James freeman clarke
ገልብጤ
ዋና ውሃ አጠጪ
ዋና ውሃ አጠጪ
 
Posts: 1746
Joined: Sat Jun 26, 2010 11:24 pm

Postby ገልብጤ » Wed Mar 13, 2013 10:26 pm(ካለፈው የቀጠለ) ባለፈው ሳምንት በዚሁ ርዕስ ስለ አብቹ ማንነት፣ የት ተወልዶ የት እንዳደገ፣ ገና የ16 ዓመት ጉብል ሳለ ስለፈፀመው ተዓምራዊ ጀብዱ፣ በንጉሡና በራሶች ዘንድ ስጋት ሆኖ ስለመታየቱ፣ የጣሊያኖችንም ሆን የባንዳዎችን ቅስም እየሰበረ ወደፊት ስለመገስገሱ፣ ከማይጨው ሽንፈት በኋላም የሚወደውን አለቃውንና ጓደኛውን ደጃዝማች አበራን እና ሁለት ወዶ ዘማች ፈረንጆችን (አንደኛው የአብቹን ታሪክ በመጠኑም ቢሆን የጻፈውን አዶልፍ ፓርለሳክ ነው) ተሰናብቶ በጥቁር ፈረሱ ላይ ሆኖ፣ ከሁለት የጦር ሜዳ ጀግኖቹ (ጀኔራል ወርቁና ጀኔራል ሃብቶም) ጋር ቁልቁል ወደ ዓባይ ሸለቆ ሽምጥ መጋለቡን ገልጬ ነበር በቀጠሮ የተለየኋችሁ፡፡ ቀጣዩን ክፍል እንዲህ አቅርቤዋለሁ፡፡ ከቅስም ሰባሪው የማይጨው ሽንፈት በኋላ፣ንጉሡና ምርጥ አሽከሮቻቸው ወደ አውሮፓ በባቡር ሲኮበልሉ መጀመሪያም የፋሽስቶችን አረር በደረቱ እየመከተ የሀገርን ክብር ለማስጠበቅ የተዋደቀው ምስኪን ድምር ህዝብ ግን የሚያሰባስበው አላገኘም፡፡

በመሆኑም በአግባቡ የተደራጀውንና በዘመናዊ ትጥቅ ጡንቻውን ያፈረጠመውን የጠላት ኃይል በተናጠል መመከት አልቻለም፡፡ የኋላ ኋላ ግን ምንም እንኳ ንጉሡ ሜዳ ላይ በትነውት ቢፈረጥጡም፣ ምንም እንኳ አቅሙ ደካማ መሆኑን አሳምሮ ቢያውቅም፤ አያት ቅድመ አያቶቹ በባዕድ ተገዝተው አያውቁምና “አሜን” ብሎ መገዛት የሞት ሞት ሆኖ ታየው፡፡ ስለሆነም በየአካባቢው የጐበዝ አለቆችን እየመረጡ ከጣሊያን ጋር ፊትለፊት መጋፈጡን በቁርጠኝነትና በፍጹም ጽናት ተያያዘው፡፡ አብቹም ለተመሳሳይ ዓላማ ጃርሶ ወረደ፡፡

ከዚያስ? ሃሳቡ ተሳክቶለት በለመደው የጀግንነት ወኔ ጣሊያንን ተፋለመ? ተፋልሞስ ለድል በቃ? ወይስ በጠላት አረር ከሆነ፣ ከማይታወቅ ቦታ ወድቆ የጆቢራ ራት ሆነ? ወይስ መንግስት ቂም ቋጥሮ ቆይቶ እንደነበላይ ዘለቀ በድብቅ ቀበረው? ለፈፀመው ጀብዱስ ከድል በኋላ መንግሥት ምን ወሮታ ከፈለው? በአብቹና መሰል አርበኞች ለዘውድ የበቁት ንጉሥ እንዴት ረሱት? በአስጨናቂዎቹ የጦርነት ወቅቶች “እሰሩት! ገንዙት!” ሲሉ የነበሩ ልዑላን ራሶች ከድል በኋላ እንዴት ስሙ እንኳ ትዝ አላለቸውም? አምባራዶምም ሆነ ማይጨውና መቀሌ አካባቢ በተካሄዱ ውጊያዎች ላይ በዘግናኝ ሁኔታ ያለቁት ምስኪን ዜጐች ቀድሞውንም በሥርዓት ስላልተመዘገቡና ስለማይታወቁ፣ ስማቸው በወርቅ ቀለም አለመጻፉ ላያስደንቅ ይችል ይሆናል፡፡

ሆኖም አገራቸውና ቤተሰባቸው እንዲሁም ታሪክ በነሲብ ሲያወሳቸው ይኖራል፡፡ ግን አብቹ እንዴት ይረሳል? በወዶ ዘማችነት ከራስ ካሳ ጦር ጋር ዘምቶ የነበረው ቸኮዝሎባኪያዊው አዶልፍ ፓርለሳክ እንኳ ከዚያ ሁሉ ሠራዊት መሃል እንደ አብቹ በህሊናው ታትሞበት የቀረ ምርጥ ጦረኛ ያለ አይመስልም፡፡ በዚያ አስከፊ ሰዓት እንዲህ ዓይነት ተዓምር የሠራ የ16 ዓመት ጉብል መኖሩን የነገረንም እሱ ብቻ ነው፡፡ ብዙ ሰዎች ስለማይጨው ጦርነት ጽፈዋል፡፡ ብዙ የመጻፋቸውን ያህል የንጉሡንና የራሶችን “እንከን አልባ” ታሪክ ሊነግሩን ደከሙ እንጂ እንዲህ እንደ አብቹ ያሉ ሳተናዎችን ታሪክ እየመዘዙ አላሳዩንም፡፡ ይልቁንም “ንጉሡ ወደ አውሮፓ የሄዱት ሸሽተው ሳይሆን የተባበሩትን መንግሥታት (ሌግ ኦፍ ኔሽን) እርዳታ ለማግኘት ነው” የሚል ስብከት ደጋግመው ይነግሩንና የትየለሌ ኢትዮጵያውያን በመርዝ ጋዝ እየተጠበሱ አምስት ዓመት ሙሉ ፍዳቸውን አይተው ያስመዘገቡትን ድል ለንጉሡ በገጸበረከትነት ያቀርባሉ፡፡ “ፀሐዩ ንጉሠ ነገሥት በድል አድራጊነት መጡ” እያሉም ድሉን በኪሳቸው ውስጥ ይዘው የመጡ በማስመሰል ከኬኩ ላይ ክሬሙን እንዲልሱ ያደርጓቸዋል፡፡ በመሠረቱ እንዲህ ዓይነቱ ዘገባ ስህተት ሳይሆን ክህደት ይመስለኛል፡፡ በጣሊያን የመርዝ ጋዝ በየበረሃው አካሉ እንደ ቅጠል ረግፎ የቀረው፣ በወንድሙ ሬሣ ላይ እየተራመደ የሀገሩን ጠላት አናዝዞ ለድል የበቃው አርበኛው የኢትዮጵያ ህዝብ እንጂ ንጉሡ አይደሉም፡፡ ንጉሡማ አውሮፓ ውስጥ ከቤተሰባቸውና ከምርጥ አሽከሮቻቸው ጋር የሞቀ ኑሮ እየኖሩ ነበር፡፡ ጦርነት ደግሞ በርቀት መቆጣጠሪያ ሊካሄድ የሚችል ቀላል ጨዋታ (ጌም) አይደለም፡፡ እንዴት አርጐ ነው ታዲያ ድል ከአውሮፓ ያውም ከእንግሊዝ ይዘውልን የሚመጡት? ቀድሞ ነገር ጣሊያን የወረረችንኮ የእንግሊዝን ሙሉ ድጋፍ አግኝታ ነው፡፡ ሁለተኛው የዓለም ጦርነት ወዳጅና ጠላትን ሳይለይ አውሮፓን ስላመሳቀለው፣ ጣሊያንም በምስራቅ አፍሪካ አካባቢ የእንግሊዝን ጥቅም የሚነካ ተግባር በመፈፀሟ ነው ፊት የተዟዟሩት፡፡ ያም ሆኖ ድሉ የተገኘው አብቹን በመሰሉ ቆፍጣና ጀግኖች መራራ ትግልና መስዋዕትነት እንጂ ከእንግሊዝ ወይም ከንጉሡ አይደለም፤ ሊሆንም አይችልም፡፡

ንጉሡ በእንግሊዞች አጃቢነት ገና መንገድ ላይ ሳሉኮ ኢትዮጵያውያን አርበኞች ጣሊያንን አርበድብደው መጋቢት 28 ቀን 1933 ዓ.ም አዲስ አበባ ላይ የደሙላትን፣ በርካታ ወገኖቻቸውን ጭዳ ያደረጉላትንና ምንጊዜም ተዋርዳ የማታውቀውን ሰንደቅ ዓላማቸውን አውለብልበዋል፡፡ ይህ ቀን በደርግ ዘመን በክብር ሲታሰብ እንደነበረ አስታውሳለሁ፡፡ ኢህአዴግ አዲስ አበባ ሲገባ ግን ቀኑን ወደሚያዝያ 27 ቀይሮታል፡፡ ቀኑ ደግሞ ንጉሡ አዲስ አበባ የገቡበት ነው፡፡ ግን ለምን? ትክክለኛው የድል ቀን አርበኞች የገቡበት ነው፡፡ ሚያዝያ 27 ማለት ንጉሡ ሳያስቡት ተገፍትረው ያጡትን ዙፋን መልሰው ያገኙበት እንጂ እንደ አጼ ቴዎድሮስ፣ እንደ አፄ ዮሐንስ ወይም እንደ አጼ ምኒሊክ ጦራቸውን መርተው፣ በጀግንነት ተዋግተው ለድል ያበቁበት ዕለት አይደለም፡፡ ይልቁንም ሚያዝያ 27 ቀን 1928 ዓ.ም ጣሊያን አዲስ አበባን የተቆጣጠረችበትና የኢትዮጵያን ሰንደቅ ዓላማ አዋርዳ የራስዋን ሰንደቅ ዓላማ በክብር ያውለበለበችበት ዕለት ነው፡፡

ስለዚህ የምናከብረው የማንን የድል ዕለት ለማስታወስ ይሆን? የጣሊያንን ወይስ…? ለነገሩ ይህኛው ሃሳብ በጠለፋ ገባ እንጂ የጽሑፌ ዓላማ ብሔራዊው አርበኛ አብቹ ከማይጨው የሽንፈት መልስ በኋላ የት እንደገባ መጠየቅና የላሊበላን ታሪክ ቀባሪዎች ለማወቅ መትጋት ነው፡፡ አምስት የፍዳ ዓመታት በገድል ከተፈፀሙ በኋላ ንጉሡ “በድል አድራጊነት” ሳይሆን በእንግሊዞች አጃቢነትና በጀግኖቻችን ድል አድራጊነት ወደ ሥልጣን ሲመለሱ በብዛት ይሾሙና ይሸልሙ የነበሩት ለዘውድ ያበቋቸውን የቁርጥ ቀን ጀግኖች ሳይሆን የወገኑን አንገት እንደ ጐመን ያስቀነጠሰ ባንዳንና ስደተኛውን ነበር፡፡ አንዳንዶችን እንዲያውም ማዕረጋቸውን ብቻ ሳይሆን ህይወታቸውንም በመሪር ግፍ ነጥቀዋቸዋል፡፡ ከህይወታቸውም ከማዕረጋቸውም በላይ ታሪካቸውን የተነጠቁት ደግሞ እጅግ የሚያሳዝኑ ናቸው፡፡ እንዴት ታሪክ ይገደላል? ስለአብቹም ሆነ አምባራዶም ላይ በተካሄደው ዘግናኝ ጦርነት ተዓምር ስለሰሩት ጀግኖች የነገሩን ቼኮዝሎባኪያዊው አዶልፍ ፓርለሳክና ኪውባዊው ኮሎኔል ዴል ባዬ ብቻ ናቸው፡፡ “ሐበሽስካ ኦዲየሳ” የተሰኘው የታሪክ መጽሐፍ ወደ አማርኛ እስከ ተመለሰበት 1989 ድረስ አብቹ የሚባል ጀግና ስለመፈጠሩም የሚያውቅ ሰው ያለ አይመስለኝም፡፡ እውነተኛ ጀግኖች በመብራት በሚታሰሱበት በዚያ ዘግናኝ ወቅት ተዓምር የሚመስል ጀብዱ እየፈፀመ ጣሊያንን ሲያርበደብድ የነበረ ጀግና፣ የመከራው ጊዜ ሲያልፍ ስሙ እንኳ ለምን ተረሳ? የሚገርም ጉዳይ ነው፡፡

የጃጀ የመከላከል ሃሳብ ለነበራቸው ጁጁዎች ባለመታዘዙ ሹመት ሽልማቱ ይቅርበት፤ ግዴለም፡፡ ግን እንዴት በስህተት እንኳ ስሙ አይነሳም? የሃገራችን ታሪክ ጸሐፊዎችስ (በተለይ ስለማይጨው ዘመቻ የጻፉና በግንባሩ የነበሩ) ለምን ንፉግ ሆኑ? አብቹኮ ህይወቱን አልነፈገንም፡፡ አብቹ ከጣሊያን ጋር ሲዋጋ በአንዱ የሃገሩ ሸለቆ ውስጥ ወድቆ ያገሩ አሞራ በልቶታል፤ ወይም “እሰሩት ገንዙት” ሲሉ የነበሩ ወግ ጠራቂ መኳንንት አስገድለውታል፤ ወይም ድምጹን አጥፍቶ ኖሮ በህመም ሞቷል፤ ወይም ዕድለኛ ከሆነ ዛሬ የዘጠና ሶስት ዓመት አዛውንት ሆኖ ትውልዱንም ዘመኑንም ይታዘባል፡፡ ለነገሩ ሰውን ገድሎም ሆነ በቁሙ መቅበር አዲስ ነገር አይደለም ግን ታሪክን እንዴት መቅበር ይቻላል? አብቹን የመሰለ ብሔራዊ አርበኛ ታሪክስ ከምን ዓይነት ጥልቅ ጉድጓድ ውስጥ ቢቀበር ነው ፍንጩ እንኳ የታጣው? ለነገሩ ታሪክን መቅበር የዳበረ ልምድ ያለን ይመስለኛል፡፡

እንኳን የአብቹን የአንድ ፍሬ ልጅ (ግን ወኔ ሙሉ ጀግና) ታሪክ የዓለም ማህበረሰብ “… ቅርሴ ነው” ብሎ በክብር የመዘገበው የላሊበላ ታሪክስ መች በቅጡ ይታወቃል? የሚታወቀው “ላሊበላ የሚባል የተቀደሰ ንጉሥ በእግዚአብሔር ትዕዛዝ ከድንጋይ ሠራው” የሚል ነው፤ በቃ፡፡ ግን መጀመሪያ እንዴት ሃሳቡን አፈለቀው? ወይም እኒያን አይነት ተዓምረኛ ቤተክርስቲያኖችን ለመሥራት ያነሳሳው ሰበብ ምን ነበር? የዚያ ዓይነት ድንጋይ በአካባቢው እንደሚገኝ በምን ተገነዘበ? የከርሰ ምድር መመርመሪያ ቴክኖሎጂ በወቅቱ ነበር? በእርግጥ በመጥረቢያ ነበር የሠራው? በመጥረቢያ ከሰራውስ ለምን ምልክቱ ቤተ ጊዮርጊስ ላይ አልታየም? ድንጋዩን እንደ እንጨት አለስልሶ የሚጠርብ መሳሪያስ ምን ዓይነት ነው? ድንጋዩ ሲጠረብ (በተለይ ማዕዘን አካባቢ) ለምን አንድ ቦታ ላይ እንኳ አይሸረፍም? እጅግ ብዙ ጥያቄዎች ሊነሱና ተገቢው መልስ ሊሰጥባቸው ይገባ ነበር፡፡ ትክክለኛውን መልስ መስጠት የሚቻለው ግን ትክክለኛ ታሪኩ ሲገኝ ነው፡፡ የዚያ ግዙፍ ተግባር ባለቤት (የላሊበላ) ታሪክ የት ተቀበረ? በምን ያህል ጥልቀት ተቀበረ? ማን ቀበረው? ለምን? እጅግ የሚገርም ጉዳይ ነው፡፡

ከእሱ በፊት የኖሩት የአክሱም ነገሥታት ዝርዝር ታሪክ ሲጻፍና ሲተነተን፤ ሌላው ቀርቶ በጦርነት ድል ያደረጓቸው ህዝቦች፣ የወጉት ሀገር፣ ያደሱት ዕልቂት መጠን፣ ወዘተ በሰፊው ሲነገርና ሲዘከር የላሊበላና ቤተሰቦቹ ትክክለኛ ታሪክ እንዴት ተዳፍኖ ቀረ? ለማን ጥቅም? ለምን ዓላማ? ይህ ዓይነት ቅጥራት የሚፈፀመው ምን አልባት “ከሰሎሞን ዘር የወጣን እኛ እንጂ የላሊበላ ዘር አይደለም” በሚሉ ግብዝ ጸሐፊዎች ሊሆን ይችላል፡፡ ግንኮ በዚያው ግብዝ ሥራቸውም ቢሆን የላሊበላን ዘር (በእናቱ በኩል ገረድ ቢያደርጉትም) አባታቸው ሰሎሞን መሆኑን ገልጸዋል፡፡ ታዲያ ያን የመሰለ ድንቅ ጥበብ ለዓለም ያስተማረውን ጀግና ታሪክ መቅበር ለምን አስፈለገ? ታሪክ መቅበር የጀመርነው በላሊበላ ሳይሆን ይቀራል? በላሊበላ ዘውድ ወራሾችና በ “ሰሎሞናዊው” ይኩኖአምላክ መሃል የከረረ፣ የመረረ ውጊያ ሳይካሄድ በአባ ተክለሃይማኖትና በአባ ኢየሱስ ሞዐ ፖለቲካዊ ጥበብ ሥልጣን ወደ ሸዋ መሻገሩን ብዙዎች ጽፈዋል፡፡ ለከፈሉት ፖለቲካዊ ውለታም ለአባ ተክለ ሃይማኖት የዕጩጌነት፣ ለአባ ኢየሱስ ሞዐ ደግሞ የዓቃቤ ሰዓትነት ክብር ከይኩኖአምላክ ተቸሮአቸዋል፡፡

በሽግግሩ ወቅትም ሆነ በኋላ ላሊበላ ላይ ብቻ ያተኮረ የውጭ ወራሪ አልተነሳም፡፡ ታዲያ ምን መዓት ወረደና ታሪኩን ቀበረው? ምን አልባት ወርቃማውን የላሊበላ ታሪክና ጥበብ ጥልቅ ጉድጓድ ውስጥ የቀበሩት ተንኮልን ማደሪያቸው ያደረጉ እበላ ባይ ደባትር ሊሆኑ ይችላሉ - የሚያፎደፉዱላቸው ነገሥታት ከላሊበላ የተሻለ ሳይሆን ጫፉ ጋ የሚደርስ ተግባር ማከናወን ስለማይችሉ፡፡ የጀግናውን አብቹን ታሪክ ጥልቅ ጉድጓድ ውስጥ የቀበሩትም የእነሱ የልጅ ልጆች ሊሆኑ ይችላሉ፡፡ እናም እባካችሁ የጀግናውን አብቹንም ሆነ የላሊበላን ምሉዕ ታሪክ ያያችሁ ና ወዲህ በሉኝ! ከታሪክ ቀባሪዎች ይሰውረን፡፡
ያልበሰለ ፖለቲከኛ ስለቀጣዩ ምርጫ ሲያስብ
የበሰለ ፖለቲከኛ ስለቀጣዩ ትውልድ ያስባል
James freeman clarke
ገልብጤ
ዋና ውሃ አጠጪ
ዋና ውሃ አጠጪ
 
Posts: 1746
Joined: Sat Jun 26, 2010 11:24 pm

Postby recho » Sat Mar 16, 2013 5:18 pm

እንደው በማሪያም ይሄንን ሁሉ ያነቡታል ብለህ ነው የጻፍከው? እንኩዋን አብቹ አባይ ራሱ ቢጠፋ አላነብልህም ሙት :lol: :lol: :lol: ይልቅ የአብቹን የበላው ነገር አሳሳቢ ከሆነ ጽሁፉን ራፕ አርግልን ... እኔ ስክሮል አርጌ መጨረስ ራሱ አቅቶኛል .. :lol: :lol:
"ሰነፍ በልቡ። አምላክ የለም ይላል በሥራቸው ረከሱ ጐስቈሉ በጎ ነገርን የሚሠራ የለም " መዝሙረ ዳዊት ምእራፍ 14:1
recho
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 3171
Joined: Mon Sep 20, 2004 12:28 pm
Location: Earth

Postby ገልብጤ » Sat Mar 16, 2013 6:43 pm

recho wrote:እንደው በማሪያም ይሄንን ሁሉ ያነቡታል ብለህ ነው የጻፍከው? እንኩዋን አብቹ አባይ ራሱ ቢጠፋ አላነብልህም ሙት :lol: :lol: :lol: ይልቅ የአብቹን የበላው ነገር አሳሳቢ ከሆነ ጽሁፉን ራፕ አርግልን ... እኔ ስክሮል አርጌ መጨረስ ራሱ አቅቶኛል .. :lol: :lol:

ሀሀሀሀ እንዴት ነው ደቤ ጨዋታ እኮ ጨምረሀል....ምን ላድርግ ብለህ ነው ..ይህ ሁሉ ብጽፈውማ ,,እነ ዲጉ ፕሮፌሰር ባደረጉኝ ነበር ..
እኔ የምለው ግን ታሪክ ሲጣፍ ማን ያነባዋል ብለህ ነው...ስለ እሙሙ ቢጣፍ ግን ባንዴ 1000 ሰው ባነበበው ነበር
ያልበሰለ ፖለቲከኛ ስለቀጣዩ ምርጫ ሲያስብ
የበሰለ ፖለቲከኛ ስለቀጣዩ ትውልድ ያስባል
James freeman clarke
ገልብጤ
ዋና ውሃ አጠጪ
ዋና ውሃ አጠጪ
 
Posts: 1746
Joined: Sat Jun 26, 2010 11:24 pm

Postby recho » Sat Mar 16, 2013 7:36 pm

ገልብጤ wrote:ሀሀሀሀ እንዴት ነው ደቤ ጨዋታ እኮ ጨምረሀል....ምን ላድርግ ብለህ ነው ..ይህ ሁሉ ብጽፈውማ ,,እነ ዲጉ ፕሮፌሰር ባደረጉኝ ነበር ..
እኔ የምለው ግን ታሪክ ሲጣፍ ማን ያነባዋል ብለህ ነው...ስለ እሙሙ ቢጣፍ ግን ባንዴ 1000 ሰው ባነበበው ነበር
ቅቅቅቅ ፕሮፌሰር :lol: :lol: ከምር ግን አንበህዋል? አረዛዘሙ .. ባይሆን በ ኤፒሶድ እና ሲሪስ ከፋፍልልን .. እንጂ ይሄንን ሁሉ ማን ያነባል ... አይናችንም እየደከመ ነው እንደምታውቀው :lol: :lol:
"ሰነፍ በልቡ። አምላክ የለም ይላል በሥራቸው ረከሱ ጐስቈሉ በጎ ነገርን የሚሠራ የለም " መዝሙረ ዳዊት ምእራፍ 14:1
recho
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 3171
Joined: Mon Sep 20, 2004 12:28 pm
Location: Earth

Postby ፓን ሪዚኮ » Tue May 28, 2013 12:55 pm

recho wrote:እንደው በማሪያም ይሄንን ሁሉ ያነቡታል ብለህ ነው የጻፍከው? እንኩዋን አብቹ አባይ ራሱ ቢጠፋ አላነብልህም ሙት :lol: :lol: :lol: ይልቅ የአብቹን የበላው ነገር አሳሳቢ ከሆነ ጽሁፉን ራፕ አርግልን ... እኔ ስክሮል አርጌ መጨረስ ራሱ አቅቶኛል .. :lol: :lol:
ስሚ የኔ አሮጊት ...ይሄን ያሮጊት አፍሺን ከፍተሽ አቢቹ ይጥፋ ትያለሽ ?
ስታሳዝኚ..
ፓኑ አባ ፈርዳ
Imageኢትዮጲያ ትቅደም
ፓን ሪዚኮ
አለቃ
አለቃ
 
Posts: 2044
Joined: Tue Aug 03, 2004 3:35 am
Location: ጎሃ ጽዮን

Postby ፓን ሪዚኮ » Tue May 28, 2013 1:44 pm

ገልብጣችን ....የአቢቹ ሙሉ ታሪክ በ "የኃበሻ ጀብዱ " ቁጥር 2 ላይ በሰፊው ይቀርባል .....ትንሽ በትግስት ጠብቅ::
ፓኑ አባ ፈርዳ
Imageኢትዮጲያ ትቅደም
ፓን ሪዚኮ
አለቃ
አለቃ
 
Posts: 2044
Joined: Tue Aug 03, 2004 3:35 am
Location: ጎሃ ጽዮን

Postby ሙዝ1 » Wed May 29, 2013 3:08 pm

ፓን ሪዚኮ wrote:ገልብጣችን ....የአቢቹ ሙሉ ታሪክ በ "የኃበሻ ጀብዱ " ቁጥር 2 ላይ በሰፊው ይቀርባል .....ትንሽ በትግስት ጠብቅ::
ፓኑ አባ ፈርዳ


በጉጉት አለቅን'ኮ ጌታዉ ... ቶሎ ቶሎ በል እንጂ :lol: ... ጠፍተሀል ደግሞ ... በሰላም ነዉ?
አይን ሁሉን ቢያይም አጠገቡ ያለዉን ቅንድብ አይቶ አያዉቅም ...
ሙዝ1
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 3128
Joined: Wed Feb 22, 2006 9:25 am

Postby ፓን ሪዚኮ » Wed May 29, 2013 3:33 pm

ሙዝ1 wrote:
ፓን ሪዚኮ wrote:ገልብጣችን ....የአቢቹ ሙሉ ታሪክ በ "የኃበሻ ጀብዱ " ቁጥር 2 ላይ በሰፊው ይቀርባል .....ትንሽ በትግስት ጠብቅ::
ፓኑ አባ ፈርዳ


በጉጉት አለቅን'ኮ ጌታዉ ... ቶሎ ቶሎ በል እንጂ :lol: ... ጠፍተሀል ደግሞ ... በሰላም ነዉ?
ሰላም ሙዝነት
ያው ዋርካ ቅጥ ሲያጣ ጠፋሁ እንጂ በህይወትስ መኖሩን አለሁ::የአቢቹን ታሪክ እያዘጋጀሁ እያለሁ ሌሎች መረጃዎች እጄ ስለገቡ ....የችኮላ ስራ እንዳይሆን ...ከቀረበ አልቀር ክብሩን ጠብቆ እንዲቀርብ በማሰብ ነው የዘገየሁት ::አይዞን እያለቀ ነው ! ዘመዶቻችንን ሰላም በልልን
ፓኑ አባ ፈርዳ
Imageኢትዮጲያ ትቅደም
ፓን ሪዚኮ
አለቃ
አለቃ
 
Posts: 2044
Joined: Tue Aug 03, 2004 3:35 am
Location: ጎሃ ጽዮን

Postby ሙዝ1 » Thu May 30, 2013 8:14 am

ፓን ሪዚኮ wrote:
ሙዝ1 wrote:
ፓን ሪዚኮ wrote:ገልብጣችን ....የአቢቹ ሙሉ ታሪክ በ "የኃበሻ ጀብዱ " ቁጥር 2 ላይ በሰፊው ይቀርባል .....ትንሽ በትግስት ጠብቅ::
ፓኑ አባ ፈርዳ


በጉጉት አለቅን'ኮ ጌታዉ ... ቶሎ ቶሎ በል እንጂ :lol: ... ጠፍተሀል ደግሞ ... በሰላም ነዉ?
ሰላም ሙዝነት
ያው ዋርካ ቅጥ ሲያጣ ጠፋሁ እንጂ በህይወትስ መኖሩን አለሁ::የአቢቹን ታሪክ እያዘጋጀሁ እያለሁ ሌሎች መረጃዎች እጄ ስለገቡ ....የችኮላ ስራ እንዳይሆን ...ከቀረበ አልቀር ክብሩን ጠብቆ እንዲቀርብ በማሰብ ነው የዘገየሁት ::አይዞን እያለቀ ነው ! ዘመዶቻችንን ሰላም በልልን
ፓኑ አባ ፈርዳ


ፓኑ ዚ ግሬት ...
እንደ ተጋባዥ ቸኩያለሁ ... ... አንተ ደግሞ እንደ ደጋሽ ተረጋግተህ የሚጥም ነገር ይዘህ መቅረብ አለብህ ... የነ ቶሎ ቶሎ ቤት እንዳይሆን ... ... .. በተረፈ ያለቀ መስሎኝ ለዘመዶቻችንም በዛ መልኩ ነበር የነገርኳቸዉ ... በጉጉት እየጠበቁ ነዉ .... ... ለሁሉም ሳገኛቸዉ ሰላምታህን አደርሳለሁ ...

መልካም ስራ
አይን ሁሉን ቢያይም አጠገቡ ያለዉን ቅንድብ አይቶ አያዉቅም ...
ሙዝ1
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 3128
Joined: Wed Feb 22, 2006 9:25 am

Postby ፓን ሪዚኮ » Thu Jun 06, 2013 9:05 am

ገልብጣችን ...አባ ፈርዳን ፈራXኢው እንዴ ? ድምጽሽ ጠፋኮ?አሮጊቷ /ራሄል/እንኳን ልማዷ ነው ...ሲፈጥራት ትፈራኛለች:: አይዞሽ አሮጊቴ ..ከሰሞኑ ጎርፍ ይበላኝና ትገላገያለሽ::
ፓኑ አባ ፈርዳ
Imageኢትዮጲያ ትቅደም
ፓን ሪዚኮ
አለቃ
አለቃ
 
Posts: 2044
Joined: Tue Aug 03, 2004 3:35 am
Location: ጎሃ ጽዮን

Postby ገልብጤ » Thu Jun 06, 2013 8:53 pm

አንፈራም ..ሞት እንኳን አንፈራም
ደህና ነገር የሚጣፍ ጠፋ እንጂ..አብቹንም ካንተው እየጠበቅን
ያልበሰለ ፖለቲከኛ ስለቀጣዩ ምርጫ ሲያስብ
የበሰለ ፖለቲከኛ ስለቀጣዩ ትውልድ ያስባል
James freeman clarke
ገልብጤ
ዋና ውሃ አጠጪ
ዋና ውሃ አጠጪ
 
Posts: 1746
Joined: Sat Jun 26, 2010 11:24 pm

Postby ዲያስፖራ » Sat Jul 06, 2013 8:39 am

:arrow:
Last edited by ዲያስፖራ on Sat Jul 06, 2013 9:05 am, edited 3 times in total.
ቀይ ባህር ድንበራችን ነው !!!!
I Love Ethiopia !!!
ዲያስፖራ
ዋና ኮትኳች
ዋና ኮትኳች
 
Posts: 781
Joined: Wed Apr 29, 2009 4:39 pm
Location: no

Postby ዳግማዊ ዋለልኝ » Sat Jul 06, 2013 8:55 am

ዲያስፖራ wrote:
ፓን ሪዚኮ wrote:ገልብጣችን ....የአቢቹ ሙሉ ታሪክ በ "የኃበሻ ጀብዱ " ቁጥር 2 ላይ በሰፊው ይቀርባል .....ትንሽ በትግስት ጠብቅ::
ፓኑ አባ ፈርዳ


የት ቦታ ነው አብቹ ይጥፋ ያለችው ? ግርም ይለኛል ይህን የኢትዮጵያ ታሪክ ልክ እንደ ግልህ ሀብት ለራስህ ለማረግ አትሞክር በመተጎርምህ ልትመስገን ይገባል እንደ እድል ሆኖ ኢትዮጵያ ያስተማረቻቸው ሰዎች ልህዝባቸው ክብር ሳይሰማቸው ሳይማር ባስተማራቸው ህዝብ ታርክ እራሳቸውን እንደ ጀገና ሲቀቡ ይታያሉ እንደ ደራሲነትህ ወይም እንደ ተርጋሚ ሀላፊነት ያለው ጻፍ ደጋፊም ሆነ ተቀዋሚ ተቺም ሆነ ገንቢ ኡሉ ሁሉንም በመልካም መቀበል አለብህ እኔ እንዳንበብኩት ሁሉ ሪቾ በድንብ አንበዋለች የፍለገችው የአቡን መጨረሻ ለማወቅ ካላት ጉጉት ይህን ሁሉ ማን ያነባል አሳጥረው ማለታ የአብቹ ጉጉት ያሳደረባት እንጂ ሳታነበው ቀርታ አይደለም ::ያውም ሆነ ይህ ታሪካችን የማወቅ መብታችን እንደሆነ እውቅ :: ምስጋና ለማሞ ውድነህ ምስጋና ለአቤጉበኛ መስጋና ታሪክን ጽፈውልን ላለፉት ሁሉ የዛሬው ትውልድ ግን መጻፍ መተርጎም ቢዝነስ አድርገውታል ::


'የተጫኔ ጆብሬ ጀብዱ ክፍል ሶስት' ተጀመረ ይሏል ይሄኔ ነው :lol: :lol: :lol: :lol: :lol:
"እቺ ለቅሶ ከፍየል በላይ ነች"
ዳግማዊ ዋለልኝ
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 3193
Joined: Wed Oct 20, 2010 12:09 am

Postby ዲያስፖራ » Sat Jul 06, 2013 9:09 am

ፓን ሪዚኮ wrote:
recho wrote:እንደው በማሪያም ይሄንን ሁሉ ያነቡታል ብለህ ነው የጻፍከው? እንኩዋን አብቹ አባይ ራሱ ቢጠፋ አላነብልህም ሙት :lol: :lol: :lol: ይልቅ የአብቹን የበላው ነገር አሳሳቢ ከሆነ ጽሁፉን ራፕ አርግልን ... እኔ ስክሮል አርጌ መጨረስ ራሱ አቅቶኛል .. :lol: :lol:
ስሚ የኔ አሮጊት ...ይሄን ያሮጊት አፍሺን ከፍተሽ አቢቹ ይጥፋ ትያለሽ ?
ስታሳዝኚ..
ፓኑ አባ ፈርዳ


የት ቦታ ነው አብቹ ይጥፋ ያለችው ? ግርም ይለኛል ይህን የኢትዮጵያ ታሪክ ልክ እንደ ግልህ ሀብት ለራስህ ለማረግ አትሞክር በመተጎርምህ ልትመስገን ይገባል እንደ እድል ሆኖ ኢትዮጵያ ያስተማረቻቸው ሰዎች ልህዝባቸው ክብር ሳይሰማቸው ሳይማር ባስተማራቸው ህዝብ ታርክ እራሳቸውን እንደ ጀገና ሲቀቡ ይታያሉ እንደ ደራሲነትህ ወይም እንደ ተርጋሚ ሀላፊነት ያለው ጻፍ ደጋፊም ሆነ ተቀዋሚ ተቺም ሆነ ገንቢ ኡሉ ሁሉንም በመልካም መቀበል አለብህ እኔ እንዳንበብኩት ሁሉ ሪቾ በድንብ አንበዋለች የፍለገችው የአቡን መጨረሻ ለማወቅ ካላት ጉጉት ይህን ሁሉ ማን ያነባል አሳጥረው ማለታ የአብቹ ጉጉት ያሳደረባት እንጂ ሳታነበው ቀርታ አይደለም ::ያውም ሆነ ይህ ታሪካችን የማወቅ መብታችን እንደሆነ እውቅ :: ምስጋና ለማሞ ውድነህ ምስጋና ለአቤጉበኛ መስጋና ታሪክን ጽፈውልን ላለፉት ሁሉ የዛሬው ትውልድ ግን መጻፍ መተርጎም ቢዝነስ አድርገውታል ::
_________________
ቀይ ባህር ድንበራችን ነው !!!!
I Love Ethiopia !!!
ዲያስፖራ
ዋና ኮትኳች
ዋና ኮትኳች
 
Posts: 781
Joined: Wed Apr 29, 2009 4:39 pm
Location: no

Next

Return to Warka Intimate - ዋርካ ፍቅር

Who is online

Users browsing this forum: No registered users and 4 guests