በመጀመሪያ ይቺን ቪዱ ከልሟትና ወደ ጉድዬ ልግባ
http://www.amharictube.com/musicvideo.php?vid=05d8be5d3
እኔ በበኩሌ የዚህችን ሴት የ26 ዓመት ጉዞ አንድም ቀን አስቤው አላውቅም። እንዴት እዛ ቦታ እንደደረሰችም አላውቅም። የማውቀው ነበር ቢኖር ያየሁትን የስድስት ደቂቃ ሴክስና ስለሷ የተፃፉትን ጥቂት ነገሮች አንብቤ ነው። ሁሉንም ያወቅኩት ሰሞኑን ነው።
እነዚህን ማወቄ ግን አገር አዋረደች እያልኩ ለመደስኮር ብቁ አያደርገኝም። አገራችሁን እስከዛሬ በክብር የምታዩና ልጅቱ አዋረደችን የምትሉ ሰዎች አይናችሁን ገልጣችሁ የአገር ውርደት ማለት ምን ማለት እንደሆነ እንድታዩ ይሁን። ወጣ በሉና ዓለም በቲቪ ሳይሆን በአይኑ እያያቸው ያሉትን ውርደቶቻችንን ተመልከቱ።
ሌላው ደግሞ ወንዱ ከኢትዮጵያ ሴቷ ከሴራሊዮን ቢሆን ኖሮ እይታችን እንዴት ይሆን ነበር? ልጅቱ ኬኒያዊ ብትሆን ኖሮስ? ኬንያ ተዋረደች ይባልና ከነበራት ክብር ላይ ወርዳ ትፈጠፈጥ ነበር ማለት ነው? ልጅቱ ተሳስታስ ቢሆን? ሰው የፈለገውን የማድረግም የመሳሳትም መብት አለው። የቲቪ ዝግጅቱ ላይ ልጅቱ ኢትዮጵያን ወከለችም፣ አይን አውጣ ሆነችም፣ አይን አፋር ሆነችም ልክ እንደኛው ሰው ናት። ስሜት ያላት፣ የምትወድ፣ የምትጠላ፣ የምትረሳ ወዘተ። መቼስ ኢትዮጵያን ለመጉዳት ብላ እንዲህ አታደርግም ብታደርግም ኢትዮጵያ በዚህ አትጎዳም።
ያየነው የአምስት ደቂቃ ተንቀሳቃሽ ምስል እኛ ከምናውቀውና ካደረግነው በጣም ይለያል። ተለየም አልተለየም፣ አደረገችም አላደረገችም ጉድ አንድ ሰሞን ነው። ተሳሳተች ብለን ወሬውን ማራገባችን ለክፉው ማንነታችን ደስታ ይሰጠው ይሆናል እንጂ ለማን ይጠቅማል? እኔን የገረመኝ ይህ ሁሉ ወንድ መንኩሶ ያዙኝ ልቀቁኝ ማለቱና ከዚህ ሁሉ የወንዶች ጫጫታ ውስጥ አንድ የሴት ድምፅ መጥፋቱ ነው።
በበኩሌ በልጅቱ ስህተት አልተዋረድኩም፣ የኔ ቤተሰቦችና ጎረቤቶችም አልተዋረዱም። ምክንያቱም ልጅቱ የነበረችበትን ሁኔታ የሚያውቅ ስለሌለ ለመፍረድ አንቸኩልም።