ለአለም ዋንጫ ለማለፍ እድሉን ያሰፋው ቡድናችን

ስፖርት - Sport related topics

ለአለም ዋንጫ ለማለፍ እድሉን ያሰፋው ቡድናችን

Postby nebsie » Wed May 01, 2013 4:02 am

አንድ እርምጃ ተራምደናል ወደፊት... እጅግ በጣም አስደሳች ነው;;; ሆኖም ግን..ከዚህ በኋላ ያሉት ጨዋታዎች ወሳኝ ናቸው;;;; የሚቀጥለው ጨዋታ ቦትስዋና ላይ ነው መሰለኝ;; ያፍዝ ያደንግዝ እና ቆጭቆጬ በአዋዜ እንዲሁም በለጬ አበረው ከቡድኑ ጋር መጛዝ አለበት;;; ሻሜታም ወይም በጥንት አጠራሩ ቦርዴ;;;ዙር በጎኔ ወይም በሶ ጭነው መሄድ አለባቸው;;; የቆጭቆጬውና የአዋዜው ጥቅም እንደሚከተለው ይሆናል;; ጋባሮኒ ቦትስዋና እንደሄዱ ሆቴላቸው እንዳረፉ የቦትስዋና ተጫዋጮችን ሆቴላቸው ጋብዘው የባህል ምግባችንን እናሳያቹ ብለው ይሄንን የጨሰ የበግ ቀይ ወጥ የዶሮ ቀይ ወጥ ቅቅል እንዲሁም ክትፎ እስኪበቃቸው ማብላት ጥብስ በአዋዜ በቆጭቆጫ አብልቶ ያው የጨዋታው ቀን ግማሹ ጋዝ በጋዝ ይሆናል ሆዱ...አለበለዚያም ስለሚያማቸው አይሰለፉም አብዛኞቹ ስለዚህ እኛ እንጠቀማለን;;;በጠፋ ቢጠፋ 10-0 አንሸነፍም ቅቅቅቅቅቅቅቅ አስተያየት ጨምሩ እስኪ
nebsie
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 260
Joined: Wed Sep 17, 2003 10:51 am

Postby nebsie » Sun Jun 09, 2013 12:21 am

በእውነቱ የዛሬው ውጤት አስደስቶናል;; አሁን ገና ያቀረብነው ምክር ቢጤ ጆሮ አግኝቶ ዘዴውን ተጠቅመው ይሄንን የመሰለ ውጤት ከሀገር ውጪ አስመዝግበዋል;; የሰጠነውን ምክር ሙሉ ለሙሉ ተጠቅመው ሳይሆን ነገር ግን ከምክሩ ላይ አንዳንድ ሀሳብ በመውሰድ ለዚህ ደረጃ በቅተዋል;; እንደሰማነው ከሆነ ቦትስዋናዎቹ የእራት ግብዣውን እምቢ ብለዋል;; ያፍዝ ያደንግዝ ይዘው ከቡድኑ ጋር ለመሄድ ያሰቡትም ሰዎች ቪዛ እንደተከለከሉ ተነግሮናል;; የተከለከሉበት ምክንያትም የቦትስዋና መንግስት ማንነታቸውን ደርሶበት ያፍዝ ያደንግዙ ተጫዋቾችን ብቻ ሳይሆን ስታድየም ውስጥ የገባውን ህዝባቸውንም ጭምር አፍዝዞ ቤታቸው እንክዋን እንዳይሄዱ ፈዘው ስታድየሙ ውስጥ እንዳያድሩ ህዝቡን ከዚህ ለመጠበቅ መሆኑ ተነግሮናል (ምንጭ ታምራት ገለታ ከቃሊቲ ሸቤ ቤት). ለማንኛውም ባመጡት ውጤት ኮርተናል;; የሚቀጥለው ጨዋታ አዲስ አበባ ላይ ከሳውዝ አፍሪካ ጋር ሲለሚሆን የማሸነፍ እድላቸው የሰፋ ይሆናል;;ያኔ እንክዋን ያፍዝ ያደንግዝ ምናምኑ አይሰራም;; በንጹህ ጨዋታና በከባድ የደጋፊ ማበረታታት ወደፊት እንደሚሄዱ እንጠብቃለን;; መልካም እድን ለጎበዞቹ ተጫዋቾቻችን;; በሰው ሀገር ላይ በጭዋታ በልጦ 2-1 ማሸነፍ ቀላል አይደለም;;
nebsie
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 260
Joined: Wed Sep 17, 2003 10:51 am

Postby nebsie » Fri Jun 14, 2013 3:38 am

:D :D :D :D :D :D የሳውዝ አፍሪካው ተጫዋች ዛሬ መግለጫ እንደሰጠው በእርግጠኛነት ኢትዮጵያን በሜዳቸው ላይ አሸንፈናቸው እንመጣለን ነው ያለው;; እንደተጫዋቹ አባባል ሳውዝ አፍሪካ ልምድ ባላቸው ተጨዋቾች የተሞላች ስለሆነች በበቀደሙ 3-0 ያሸናፊነታቸውን ክስተት እንደ ሞራል እና እንደ ጉራ ተጠቅሞ በርግጠኝነት እናሸንፋለን ብሏል;; ማን ያውቃል:; በራሱ ሀገር ውስጥ መጫወት አድቫንቴጅ ያለው ቢሆንም ነገር ግን በአንድ በኩል ተጫዋቾቻችን ላይ ፕሬዠር ያሳድራል ተጽኖ ያሳድራል;; ለማንኛውም የኢትዮጵያ አምላክ የነ ይድነቃቸው ተሰማ አምላክ ይስማቸውና ሳውዝ አፍሪካንም ሆነ የሚቀጥለውን የማጣሪያ ጨዋታ አሸንፈው ለመጀመሪያ ጊዜ ኢትዮጵያን ለአለም ዋንጫ ተሰላፊ እንዲያደርጎአት ጸሎታችን ነው;; በአለም ላይ በእግር ካስ ጨዋታ ላይ ሀገራችንን ተጠርታ እንድናይ ያድርገን;; ከተሸነፉም ደግሞ ምንም አይደል;;እዚህ መድረሳቸው እራሱ ፉትቦላችን ተኝቶ ከነበረበት እንቅልፍ አንቅተውታል እና ሊደነቁ ይገባል;; ድጋፋቹ እና ጸሎታቹ አይለያቸው ቪቫ ዋልያ ቪቫ ኢትዮጵያ; ዛሬ ዛሬ ነው ዛሬ..... ዛሬ ዛሬ ነው ዛሬ;;;;የርግብ አሞራ;;;አያያ ሳውዝ አፍሪካን ነመኛታ;;;;; አያያ ሳውዛፍሪካን ነመኛታ;;; ነመኛታ ነመኛታ;;;;;
nebsie
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 260
Joined: Wed Sep 17, 2003 10:51 am

Postby nebsie » Thu Jun 20, 2013 3:39 am

ወይ መቃጠልልልልልል ወይ መቃጠልልልልል ወይ መቃጠልልልል ወይ ፌዴሬሽን አይ አመራር ምን ይሻላል ግን; እንዴት ያለ ሀላፊነት የጎደለው ስራ ነው;;; እንዲህ ማድረግ ይቻላል ወይ እንዴ? ወረቀት የፈረምኩበት ጠፋ; ምናምን እያሉ በክዋስ አፍቃሪው ላይ መቀለድ ይቻላል እንዴ? ምን አይነት ሗላ ቀር አሰራር ነው? መቼ ነው የሚያልፍልን?? እንዴ ፉትቦል ፌዴሬሽናችን ኮምፕዩተር የለውም ማለት ነው? ስካን አድርጎ ሴቭ ማድረግ እንክዋን አቃታቸው ማለት ነው?? በዚህ አለም በሰለጠነበት ዘመን እንደው በፈጣሪ ወረቀት ፈርሜ ጠፋ ብሎ ማለፍ ይቻላል እንዴ? ምን አይነት ቀልደኛ ሀገር ነው? ሶስት ነጥብ ተቀንሶብን ሳለ ሌላም ሳውዝ አፍሪካ ጥያቄ አቅርባለች ሶስት ነጥብ ይገባኛል ብላ ምክንያቱም ይኽው ልጅ ከነሱ ጋር ተሰልፎ ተጫውቷል;; ደንቡን ተላልፏል ስለዚህ ይገባኛል ብላ ጥያቄ እየጠየቀች ነው ሳውዝ አፍሪካ? ክርክሩን ካሸነፉ ኢትዮጵያ ስድስት ነጥብ ትነጠቃለች አለቀ ነገሩ;;; የማይረቡ ;; ወራዳ ፌዴሬሽን!!! እንደውም ሰዎቹን አባሮ ፌዴሬሽን ህንጻውን ማከራየት ነው የሚያስፈልገው;; አንጀቴ ተቃጠለ??
nebsie
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 260
Joined: Wed Sep 17, 2003 10:51 am


Return to Warka Sports - ዋርካ ስፖርት

Who is online

Users browsing this forum: No registered users and 1 guest