ግብጽ ሰላም ሁኚ

The Love Forum (love, relationship) (የኔ ቆንጆ እንተዋወቅ :-)

ግብጽ ሰላም ሁኚ

Postby ሾተል » Fri Jul 05, 2013 3:22 pm

እንደ ሁሌው የአለምን ሁኔታ አትኩሬ እንደምቃኘው ሰሞኑን የአለምን ቀልብ ከሳቡት አነጋጋሪ ክስተቶች አንዱ ለአሜሪካ ስለላ ድርጅት በኮንትራት ተቀጥሮ ይሰራ ስለነበረው ስለ ስኖውደንና የግብጽ ሁኔታ ነበር ::አሜሪካኖች የተሳሳተ ወሬ ፈጥረው በማሰራጨት የቦሊቪያውን ፕሬዚደንት ኢቮ ሞራሌስን ከሞስኮ ወደ አገሩ ሊሄድ ነዳጅ አየር ላይ አልቆበት አንዱ አውሮፓ አገር ወርዶ ሊቀዳ ሲል አሜሪካንን ፈርተው እነ ስፔን ,ጣልያን ,ፈረንሳይ ወዘተዎች እንኩዋን ነዳጅ ልትቀዳ በኛ አየር ስፔስ ማለፍም አይፈቀድልህም ብታልፍ ውርድ ከራስኽ ብለው ያልፈቀዱለትን ምክንያት ሲደረድሩ እሱም የአሜሪካንን ሚስጥር የዘከዘከውን የድሮውን የአሜሪካ ሰላይ ጭነኻል ብለው ቁም ስቅል ሲያበሉት የኛው የኦስትርያ መንግስት በመጥለፍም እንዲሁም ፍላጎቱን ለማሟላት ና ውረድ ብለው ፕሬዚደንት ሞራሌስን አውርደው ከ 10 ሰአት በላይ አየር ጣብያችን ላይ አቆይተው ነገር ግን በጥሩ ሁኔታ ተንከባክበው ፕሬዚደንታችን ዶክተር ሀይንስ ፊሸር (የሾተል ጉዋደኛ ) ፕሬዚደንት ሞላሬስን ኤርፖርት ድረስ ሄደው አጫውተውና የሚፈልገውና አስፈላጊ እንክብካቤ እንዳይጎልበት ለሚመለከታቸው ክፍሎች አስጠንንቀው ሲያበቁ ፕሬዚደንቱ ስሜቱን እንደፈለገ እንዲገልጽ ከትንሽ እስከ ትልቅ ሜድያዎች ድረስ ለጋዜጠኞች እድሉን ክፍት አድርገው ሁሉም ነገር በጊዜው ተጠናቆ ሲያበቃ የቦሊቭያውን ፕሬዚደንት ነዳጅ ሞልተን መሸኘታችን ቀልብ ሳቢ ዜና ሆኖ ሳለ ሁላችንም ወደዛ ተጠቃለን ስንከታተል በተጉዋዳኝ ደግሞ ሰሞኑን የተጀመረው የግብጽ አመጽ ሀይሉን እያጠናከረ ደጋፊዎቹን እያበዛ ወሰኑን እያሰፋ ቆየና ወታደሩ ጉልበት ነበረውና በህዝብ ድምጽ የተመረጠውን መሪ በሀይል ሸልቶ በልቶት ስልጣኑን ለጊዜውም ይሁን ለረጅም ጊዜ የታወቀ ነገር ባይኖርም ተቆጣጥሮ ወይ ጉድ አሰኘን ::

ይኽ በእንዲህ እንዳለ ከዚች ሁለት ቀን ጀምሮ የተለያዩ ሜድያዎችን ስንከታተል በዛውም እስቲ የኛዎቹ ስለግብጽ አመጽና አዲስ ክስተት ምን ይላሉ ብለን ስንከታተል በጣም በጣም የሚያሳዝንና የሚገርም ነገር ማንበብ ,ማዳመጥ ብንጀምር ያ አስተዛዝቦን ነጻ ስሜታችንን እድሜ ለዋርክዬ ዘላለም ያኑርልንና ልንገልጽ ይኼው መጻፍ ጀመርን ::

ነገሩ ወዲህ ግድም ነው ::ግብጽ ማንም እንደሚያውቀው በግልጽ የማትታይ ነገር ግን ተደብቃ እንደ ስናይፐር አድብቶ ተኩሳ የምታቆስለንና ስታቆስለን ወይም ስታስቆስለን የነበረችና ያለች አገር ነች ::ለህልውናዋና ለኤግሲስታንሷ ስትል እኛን ማዳከም እንዳለባት ስለምታውቅ ከጥንት ጀምሮ ታሪክ እንደነገረንም አሁንም ታሪክ እየነገረን እንዳለው ጠላቶቻችንን በመርዳት እንዳናድግ ,በሰላም እንዳንኖር የቻለችውን ሁሉ እያደረገች በእኛ መናቆር ,በእኛ ደም መፍሰስ ህልውናዋን አብግሬድ እያደረገች እስካሁን ድረስ መድረሷ ማንም የሚያውቀው ጉዳይ ስለሆነ ይቀራል ብለን የማንጠረጥረው ጉዳይ ነው ::የሷ ህልውናና የመኖር አንዱና ዋናው ጉዳይ አባይ ሲሆን አባይ ከሌለ ግብጽም መኖርዋ አጠራጣሪ ስለሆነ ለአባይ መኖር የአባይን ባለቤት ሰላም መንሳትና አባይ ያለ አንዳችም የውሀ ጠብታ ቅናሶ እንደፈለገ ባገሯ እንዲንሿለልና እንዲንፏለል በዛ የተነሳ እንጀራዋንና ዳቦዋን ለመጋገር የአባይን ባለቤት ሰላም መንሳት ድህነት ውስጥ መዶልና አቅም ማሳጣት የግድ ማድረግ ያለባት የመኖር ወይም የሞት ሽረት ስለሆነ ያንን ስታደርግ እንደነበረችው አሁንም እያደረገች እንዳለች የሚታወቅ ነው :: ::

ይኽ ታሪክ ለጊዜው እንደ ድሀ ልብስ አጥር ላይ ይንጠልጠልና ግብጾች ባለፈው መንግስታቸው በሙባረክ ሲሰቃዩ ስለነበር ያ ቢመራቸው አደባባይ ወጥተው በሰላማዊ ተቃውሞ ደማቸው እየፈሰሰ ህይወታቸው እየጠፋ ያንን ፍጹም የሙባረክን አንባገነን መንግስት ጥለው ይሻለኛል ብለው ሌላ ቢመርጡና የተመረጠው የሙርሲ መንግስት ለራሱ ሀይማኖታዊ አብዮት ብቻ አድልቶ ያ ባደባባይ የፈሰሰውን ደም ረስቶ ወይም ሰላማዊ አብዮተኞችን ዘንግቶ ለራሱ ምቾት አድልቶ ግዛቱን አስፍቶ ግብጽን በሸርያ ህግ ለማስተዳደር መንገዱን ሲዘረጋ አሁንም ሆ ብለው በመውጣት ሙርሲንም ሲቅሙትና ደም ድጋሚ መፍሰስ ሲጀምር የኛዎቹ ወላ አብዮተኞች እንበላቸው ታዛቢዎች በሰው ደም መፍሰስ ወይም በግብጻውያን ደም መፍሰስና ህይወት መጥፋት አልፎም ሰላም ማጣት ደስታቸውን በጮቤ ረጋጣ ሲያስነኩት ብሰማና ባነብ ውስጤ አዘነና የሀሳቤን የህሊናዬን ልጽፍ ተገደድኩ ::

ግብጽ ስውሯ ጠላታችን ነች ::ታድያ ስለሆነች የሰላማዊያን የግብጽ ደም መፍሰስ አለበት ?ቢፈስ ደግሞ መደሰት አለብን ?

ግብጽ ሰላማችን እንዳይጸና ጠላቶቻችንን ትረዳለች ::ያንን ግብጽ ስላደረገች የንጹሀን ግብጻውያን ነፍስ መንገድ ላይ መጥፋት አለበት ?ቢጠፋ እኛ እልልልል ብለን መደሰት አለብን ?

ግብጽ ለራሷ ህልውና ስትል አባይን እንዳንገድብ የምትችለውን ነገር ሁሉ ታደርጋለች አድርጋለችም ::እንዴውም ቅርብ ጊዜ እንደሰማነው ኢትዮዽያ አንዲት ጠብታ ውሀ ከግብጽ ብታነሳ በደም እንተካዋለን ብላ ፎክራለች ::ታድያ ያንን ስላለች እኛ በግብጽ ህዝብ ስቃይና ሰላም ማጣት እንዲሁም አደባባይ ወጥቶ በዛው መቅረት መደሰትና ለእኛ ብቻ የተለየ አምላክ ያለን ይመስል እሰይ የኢትዮዽያ አምላክ ስለፈረደ ሰላሟን አጣች ብለን ጮቤ መርገጥ አለብን ?

በእኛ በክብርነታችን የለብንም ብለን እናስባለን ::

ግን የኛዎቹ የጨዋ ልጆችም ሆኑ ከብቶች አስተሳሰብና የሰሞኑ ደስታ ወይ ጉድ ሳያውቁት ሳዶ ማቾ ወይም ሳዲስት ሆነው አርፈውታል ብዬ ከልቤ እንድታዘባቸው ሆኛለሁ ::አዎ በሰው ስቃይ የሚደሰት ሳዲስት ነው ::ሰይጣናዊ ደስታ ነው ::ፌቲሽነት ነው ::ደደብነት ,ባለጌነት ,አለማሰብነት ,ሰይጣናዊነት ,አልረብቶነት ,ወዘተ ነው ::

የሰው ልጅ በሌላው ስቃይ አንዱ መደሰት አለበት ብዬ አላምንም ::

ባይሆን ግብጽ እኛ አባይን ስለገነባን መጥታ ትውጋንና የዛኔ እራሳችንን ለመከላከል ደም መፍሰስና ማፍሰስ ካለብን ያንን ብናደርግ እራስን ለመከላከል የሚደረግ ደም ማፍሰስና መፍሰስ ስለሆነ ያ የሚቀደስና የህልውና ጉዳይ ስለሆነ ያንን ማድረግ ያስከብራል እንጂ አያሳፍርም ::ግን ጦርነት ሳይሰብቁብን በራሳቸው የውስጥ ችግር የግብጻውያን ደም ስለፈሰሰ እኛ ደስ የሚለን ምን አይነት ልብ ቢኖረን ነው ?በተቃውሞ ምክንያት ምን የመሳሰሉ ምኑንም የማያውቁ ህጻናት እኮ እየተቀጩ ነው ::አባይ ምን ይሁን አባይ ከሱፐር ማርኬት የሚገዛ ውሀ ይሁን ? ወይም በተፈጥሮ የሚፈስ ወንዝ ምኑንም የማያውቁ ምስኪን ህጻናቶች እኮ ደማቸው ምንገድ ላይ እየፈሰሰ ነው ::በአባይ የተነሳ ደም መፍሰስ የለበትም ብለው የሚያምኑ አመዛዛኝ ግብስታውያን ለነጻነታቸው ሲሉ አደባባይ ስለወጡ ደማቸው ከንቱ ሆኖ ሲያበቃ ይቺን አለም ተሰናብተዋል እኮ ?

ታድያ የእኛ ደስታ የእፍርታም ደስታ እንጂ ምን ሊፈይድልን ነው ልባችንን በሰይጣን አሰርረን ስናበቃ ግብጽ ተበጣበጠች እልልልልልል ......ግብጽ ኢትዮዽያ ላይ ስለፎከረች የኢትዮዽያ አምላክ ግብጽን ቀጣ እያልን የቢሆን አለም እስክታችንን የምንመታው ምነው ግብጽ ግብጽን የሚጠብቅ አምላክ ስለለላትና የእኛ አምላክ የግብጽም አምላክ ስላልሆነ ስለተበቀላት ነው ?

ቆይ ስንት አምላክ አለ ?አምላክ ጣኦት ሆነ እንዴ ?በድሮ ድንጋይ ዘመን ሰዎች አንዴ የበሬ ምስል አንዴ የበግ አንዴ የምን ምስል እየሰሩ አምላካችን ነው እያሉ ያመልኩ ነበር አሉ ::እና ኢትዮዽያም የአባይን ምስል የመሰለ አምላክ አባይ ከእኛ እየወሰደ ለግብጽና ለሱዳን ከሚወስደው አፈር ተፈጭቶና ተቦክቶ የተሰራ ጣኦታዊ አምላክ ሰርተን ስናበቃ ነው የኢትዮዽያ አምላክ የምንለው ወይስ በጽሀፍ ቅዱስ የምናምነው እግዚአብሄር አንድ አምላክ ሙስሊሞችም አላህ ዋህድ ቡድሂስቶችም ቡዳህ አንድ አምላክ ወዘተ ብዙ አምላክ ሆኖ ነው ?

መቼም ኢትዮዽያዊያን ግማሽ ለግማሽ ሙስሊምና ክርስቲያን ስንሆን ሁለታችንም አምላክ የምንለው ግብጽም የምታምነው አረብ አገርም የሚያምኑት አሜሪካም የምታምነው ኮቲዲቩዋርም የሚያምኑት ወዘተ አንድ አምላክ መሰለኝ ::

ግን ለራስ ሲቆርሱ አያሳንሱ ሆነና እንዲሁም እኛ ኢትዮዽያዊያን የበታችነት ስሜት አጎልቶ ስለወረረን ሁሉንም ጥሩ ነገር ወደ እራሳችን ለማጠቃለል ስለምንፈልግ አምላክን ለያየንና ከአምላኮች ሁሉ የኢትዮዽያ አምላክ አንደኛ .....በሰው ዘርነትም ከአለም ሁሉ አንደኛ ....ከቅዱስ አገሮችም በአለም ላይ ቅዱሳውያን ቢኖር አንደኛ ....ከሸሌና ሸሌ በጂ ተባጂም ሌላው እርኩስ ሲሆን ከቤቲ ሌላ በአለም ቅዱስ ሸሌ የኛ ሸሌዎችና ከስተመሮቻቸው አንደኛ ወዘተ እያልን እራሳችንን ስንክብ ሌላው ግን መፈጠራችንን ሲረሳ አሁንም እራሳችንን ስንክብ ሌሎቹ ደግሞ ሲንቁን ይኼው ኢትዮዽያዊነት በሌሎቹ ፊት እፍረት ሆኖብን ሲያበቃ በባዶ መቆነናችን በራሳችን ጊዜ እየከፈልን በመላው አረብ አገር እየሄድን ዘመናዊ ለምኖ ባርያ አድርጉን ባርያዎችና ገረዶች ሆነን አረፍነው ::ከተሰዳጅ በአለም ውስጥ ደረጃ ቢደለደል ከፍተኛውን ቦታ የያዝን ለማኝ ስደተኞች ሆነን አረፍነው ::

እና ወገኖቼ ሳዲስት አንሁን ::ግብጽን የኢትዮዽያ አምላክ አይደለም የቀጣት ::ቅጣትም አልተቀጣችም ::የውስጥ ችግር ስለነበረባት ያንን ችግር ለማጥራትና ዘላለማዊ ሰላምን ለማምጣት በየአደባባዩ ተቃውሞዋን በማሰማት የማያስፈልጉዋትን እንመራሻለን ብለው የሚጫወቱባትን ነው ለማስወገድ በደፈረሰው ጉሽ ጠላ ውስጥ የጠራውን ለመቅዳት ደፋ ቀና እያለች ደሟን እየዘራች የምትገኘው ::ያ የሷ የፈሰሰው ደም ለእኛ ጣኦት መስዋእትነት የምናቀርበው ነው ?እውነት ይሁን እንጃ እንጂ ንጉስ ሀይለስላሴ ለሚያመልኩት ለቢሾፍቱው ሰይጣጣን ቅንድቡ የሞላ የበሁር ልጅ ይገብሩ ነበር ይባላል ::ያ አፈታሪክ ሊሆን ይችላል ::እንግዲህ ምን አልባት ያ ታሪክ አፈታሪክ ከነበረ ያንን አፈታሪክ ወደ እውነተኛ ታሪክ ለመቀየር ነው የግብጽን ደም ለቢሾፍቱው ሆራ ወንዝ ግብር ልንሰጥ እልልልልል የምንለው ?

ያሳፍራል ...!

ሙስሊም ነን ክርስትያን ነን እንላለን ግን ክርስትናና ሙስሊም ምን እንደሆነ የማናውቅ ማፈርያዎች ነን ::ክርስትያን ስለሆንኩ መጽሀፉ የሚለውን በጥቂቱ ስለማውቅ አትግደል የሰውን ደም አታፍስስ እኔ ቀናተኛ አምላክ ነኝ እንጂ አዳይ ተበቃይ አምላክ አይደለሁም ይላል ::እንግዲኽ መጽሀፉ ወዲህ ተግባሩ ወድያ ካልሆነ ለኢትዮዽያ ብሎ ግብጽን የሚቀጣ አዳይ አምላክን ከየት አመጣነው ?

እና ብቻ በጣም ሁላችንንም ታዘብኩ ::በሀሳባችንና ባላስፈለገው ደስታችን ከልቤ አፈርኩ ::ልቦናን በሁላችን ውስጥ እንዲሰጠንም አምርሬ ጸለይኩ ::

አምላክ ሆይ ግብጽ አባይን ገደባችሁ ብላ ጦር ቀስራ የምትመጣ ከሆነ የግድ ለድፍረቷ የሚገባትን እንድንሰጥ ጉልበትን ስጠን ነገር ግን ግብጽ ለነጻነቷ ስትል እያደረገችው ያለችውን ሰላማዊ ትግል ባርክ ::በዚህ ለሰላም እየተደረገ ባለው ሰላማዊ ውግያ ባረኮትን ትሰጣት ዘንድ እጸልያለሁ ::ግብጽን ሰላም አድርግልን ::የንጹሀን የግብጽን ደም እንዳይፈስ ጋሻ ጃግሬ ሁናቸው ::

የኤርትራን የሱማሌን ህዝብም ባርክ ::ሰላማቸውን አውርድ ::ነገር ግን ገፍተኽ ህልውናችንን ሊያዛቡ ከመጡ እንመክታቸው ዘንዳ ሀይልና ጉልበትን ስጠን ::አሜን !!!

የግርጌ ማስታወሻ :

ዛሬ ጧት እዚህ ያሉ የተወሰኑ ወጣት አበሻ እህቶቻችንን ዳንዩብ ወንዝ ጀርባ ወስደን የሰውነት ማጠንከርያ ስፖርት አሰርተን ስናበቃ በጣም ወሳኝ ቀጠሮ ነበረንና ወደዛ ልንሄድ ቢረፍድብን በሳይክላችን መሄዱን ተውንና ዋን ወይ መጉዋጉዋዣ ትኬት እረስተንና ተቻኩለን ስለነበር ሳንገዛ የከተማ አውቶቢስ ውስጥ ጥልቅ ብለን ብንገባ ልክ ሁለት ስቴሽን እንደሄድን ሁለት ጠብደል ጠብደል ህዝቡን ተመሳስለው ቁጭ ያሉ ትኬት ኮንትሮሎች ኮንትሮል ብለው ህዝቡ ትኬት ገዝቶ እንደሚጉዋጉዋዝ ለማረጋገጥ ኮንትሮል ሲያደርጉ ሾተል በክብርነታችን ሆነን ቀልባችን ድንግጥ ቢል ይግረምህ ብሎ አንደኛው የትኬት ኮንትሮል እኔ አጠገብ ሆኖ እኔንም ጠይቆ ወደሌሎቹ እየጠየቀ እያለ አንዱ ፈረንጅ ትኬት አልገዛም ነበርና ለእሱ መቶ 10 ኦይሮ ቅጣት አከናንቦት ሲያበቃ እኔን እያየኝ እንዳይጠይቀኝ ምን ሀይል እንዳሰረው እኔንጃ ብቻ እያየኝ ዝም ቢል እንዴ ይኼንን ሰውዬ ምን አደነዘዘው ብዬ እኔም ከሱ ጋር ተፋጥጬ ከጠየቀኝ መታወቅያዬን እሰጣለሁ ብዬ ሬዲ አድርጌ ስጠብቅ የመጨረሻው መውረጃ ስቴሽን ደረስንና ዝም ሲለኝ ቀስ ብዬ ውልቅ ብዬ ወጣሁ ::ሆነስት ባለመሆኔ ባፍርም እንዲሁም ህሊናዬ ባደረኩት ነገር ቆንጠጥ ቢያደርገኝም ከወጣሁ በሁዋላ ይቅርታ አልያዝኩም ነገር ግን ስለማርከኝ ወይም እንዳትጠይቀኝ ደንዝዘኽ ተፋጠኸኝ ስታበቃ ስለለቀቅከኝ አመስግኜኻለሁ ልበለው ወይስ ልሂድ ብዬ እየተሙዋገትኩ ከራሰ ጋር እንዳለሁ የምሄድበት ቦታ ረፍዶ ስለነበር ሌላ ባቡር ልይዝ እሩጫዬን ጀመርኩ ::

ምን አልባት የረፈደብኝ ጥሩ ነገር ለእህቶቼ ስለሰራሁና ለአንድ ሰአት አንድን ሰው ለማሰልጠን ብዙ ይሮዎች ሊከፈለኝ ሲገባ ለዛውም ብዙ የሆኑ ልጆችን በነጻ ጊዜዬንና ትእግስቴን ሰውቼ ስላደረኩ አምላክ ከቀጪዎች ጠብቆኝ ይሆን ?

ብቻ ግርም እንዳለኝ ቀጠሮዬ ጋር ደርቼ በሰላም ተመለስኩ እላችሁዋለሁ ::መቼም የሌባ ወይም አጭበርባሪ አምላክ የለምና አምላክ ሳጭበረብር ደገፈኝ ብዬ አልዘባነንም ::ግን ጥሩ ነገር ማድረጌ በራሱ ጊዜ ከቀጪ አድኖኝ ይሆን ?

መቶ 10 ይሮ ለጥፋቴ ብዙ ሆኖ ሳይሆን ሰሞኑን ለነገ የአገሬ ተስፋዎች ለማስተምራቸው ልጆች እልካለሁ ካልኩት በዛ ያለ ገንዘብ ውስት ነበር ቀንሼ እከፍል የነበረው ማለቴ ብቀጣ ::

በሉ መልካም ዋሉ

ከአንድ ሰአት በሁዋላ ለወደፊቱ እንጀራዬ የሚሆን ቦታ ለኢንተርቪው ስለምሄድ የምትወዱኝ ካላችሁ ይቅናህ ብላችሁ ጸልዩልኝ ::እዛ ሰርቼ የማገኘው ገንዘብ ወደ ኢትዮዽያ እየገሰገሰ ስለሚሄድና ኢትዮዽያዊያንን እንዲሁም ኢትዮዽያን በልማቱ በኩል የመርዳት አስተዋጽኦ ስለሚኖረው ::ለራሴ ከቦቆሎ ገንፎዬ ከለት እንጀራዬ ውጭ በዚች አለም የምፈልገው አንዳችም ምቾት አይኖርም ::ግን ለሌሎች ህይወት ምቾት ሲል ደግሞ ደጋግሞ ይስጠኝ ::አምላክ ሆይ ለራሱ ብቻ የሚኖር ስግብግብ አድርገኽ ስላልፈጠርከኝ ከልቤ አመሰግንኻለሁ ::አሜን !

መልክቱ ያልገባችሁ ቅኔው ያልተፈታላችሁ ርሰ አንቀጹ የከበዳችሁ ካላችሁ ደጋግማችሁ አንብቡ ::


ሾተል ነን ..............አንድ የሆንከው የአለም አንድ አምላክ አለማችንን ጠብቅ ::አሜን !!!!!
እሰይ ተመስጌን አምላኬ ለካስ በክብርነቴ እራሴን ሆኜ እኔነቴን ፈልጌ አግኝቼዋለሁ !?
ሾተል
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 9644
Joined: Thu Jan 13, 2005 9:42 pm
Location: Vienna-Austria

Return to Warka Intimate - ዋርካ ፍቅር

Who is online

Users browsing this forum: No registered users and 2 guests