የክርስቶስ ወንጌል ዘማሪ ተስፋዬ ጋቢሶ

Issues and Articles of General Interests including topics related to religion

የክርስቶስ ወንጌል ዘማሪ ተስፋዬ ጋቢሶ

Postby ዲጎኔ » Sat Jul 06, 2013 7:07 pm

http://www.youtube.com/watch?v=hLxqygKtz_c&1

ዘመን የማይሽራቸው የጌታችንና መድሀኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስን የወንጌል መልክቶች ዘማሪ ፓስተር ተስፋዬ ጋቢሶ ዛሬም ይዘምራል::በቤተክርስቲያን ህንጻ ምረቃ ኦግስት 8 -11 በግራንድ ራፒድስ ሚቺጋን ያገለግላል::
ዲጎኔ
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 4752
Joined: Fri Aug 19, 2005 2:03 am
Location: united states

Postby ክቡራን » Sat Jul 06, 2013 9:52 pm

በውነቱ የወንድም ተስፋዬ ጋቢሶ መዝሙሮች መንፈስ ያረሰርሳሉ:: መንፈሳዊ ጥልቀት አላቸው:: በነ ደረጀ ከበደ ና በነ ወንድም ተስፋዬ ጊዜ የተነሱ አገልጋዮች መንፈስ ውስጣቸውን ነክቶ ያስነሳቸው እንጂ እንደ አሁኑ ዘመን ወሮ በሎች ከደጃች ውቤ ሰፈር አምልጠው የገቡ አልነበሩም:: ያሁን ጊዜ መዝሙር እኮ የጨበሬ ተዝካር ነው...ትንሽ ገፋ ሲል ""እንብላው!!"" ነው :: እኔማ ዘማሪዎች ሳይሆኑ የሚናገሩ ጅቦች ፊቴ ላይ እየታያኝ ተቸግሬአለሁ:: ባለፈው አንዱ አርበ ሰፊ ዘማሪ ""እጊዚአብሄር በጆርጂያ መንገድ ላይ ማርሴዲስ ትነዳለህ "" ብሎ ተናግሮኛል ሲል ሰምቼ ለሱ ተሸማቀኩ:: የእጊዚአብሄር ቤት እሱን በመሰሉ ቀንዳም ቃልቾች ተሞልቶ አረፈው:: "" የቤትህ ቅናት በላኝ! "" ይላል ቃሉ:: ማን ይሆን ያን ቃል እንዲያስፈጸም እጊዚአብሄር በዚህ ዘመን እንዲወጣ ያዘዘው..?? አቤት አቤት ያ አገልጋይ የመጣ ቀን!! ወዮ ለነሱ!! ቄስ ጉዲና የሚባሉ የአትላንታ ፓስተርም ነገራቸው ሁሉ ""እንብላው"" ነው:: እኔማ ኦሮምኛና እንጊሊዝኛ እየተናገሩ ሰው የሚዘርፉ ጅብ ይመስሉኛል:: አዑዑዑዑዑ!! አንድ ሰሞን የማስታረቅ ራዕይ ጌታ ሰጥቶኛል እያሉ አብያተ ክርቲያንትን ከማቀራርብ ይልቅ የባሰ በቴስታ አገጫጫቸው:: "" ብኩራታችሁን ለእጊአጊዚአሄር ስጡ ""ይላሉ አዲስ ፈለጣ ናት!! የሚፈለጥ ከተገኘ!! :lol: በጎን ግን ለኔ ስጡኝ ነው መልክቱ!! ..ምን አጥቶ ነው እኔ ለእግዚአብሄር የምሰጠው..?? ""ሳታመካኝ ብላኝ "" አለች ጥንቸል እኮ ናት!! የእምነት ሰው ባምላኩ ጽንቶ ይቆማል እንጂ የባንክ አካውንት ከፍቶ አስራት አምጣ አይልም:: ባለፈው እንኴን ከሞር ሀውስ የተመረቀውን ልጅ ሲያትል ስትሄድ የማይክሮሶፍት ከሚከፍልህ ካምፓኒ ቼኩን እንድትልክ ሲሉት ሰምቼ ለሳቸው አፈርኩ:: እሱ ሲያትል እየኖረ ለሳችው የሚልክበት ምክንያቱ ምንድነው?? ምን አይነት የቀን ጅብ ናቸው እባካቹ..?? :D እስኪ አንዱን ትምህርታቸውን እኔም ልጋብዛቹ::
እቺን ጠቅ::
ክቡራን
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 8070
Joined: Tue Mar 04, 2008 4:24 pm


Return to Warka General

Who is online

Users browsing this forum: No registered users and 1 guest