ጂኒ (ጅን)... ጋኔን አጋንንት ምንድን ነው?

Topics related to cultures, arts, languages, arts such as humor, music, traditional literary genres of poems, ግጥም ፣ ቅኔ ፣ ተረትና ምሳሌ)

ጂኒ (ጅን)... ጋኔን አጋንንት ምንድን ነው?

Postby ጋንች. » Mon Jul 15, 2013 7:05 pm

ጂኒ (ጅን)... ጋኔን አጋንንት ምንድን ነው?
በደረጀ ይመሩ

ጂኒዎች (ጅኖች) በተለያዩ በርካታ መጠሪያዎች በዓለም ዙሪያ ይታወቃሉ፡፡ ጂኒ፣ ጅን፣ ጋኔን፣ አጋንንት ሰይጣን ዲያብሎስ፣ ኢብሊስ፣ ማራ፣ አብዶን፣ ብኤል ዜቡል፣ ሴዱ፣ ላማሱ፣ ሊሊቱ፣ ኢቲሙ፣ ዳናቫስ፣ ዳኤይተስ፣ ስሪም፣ ሳቲር፣ ዴሚዩን (ዴሞን) ወዘተ... እየተባሉ ይጠራሉ፡፡ በሁሉም የእምነት መጽሐፍትና ባህሎች ውስጥ እየተከበሩም ሆነ እየተናቁ እንደሚገኙ ከጥንት ጥንት ጀምሮ ከሰው ጋር አብረው እንደሚኖሩ የሚጠቁሙና የሚያረጋግጡ ብዙ የሰነድ ማስረጃዎች አሉ፡፡

ጂኒዎች (ጋኔን/አጋንንት) በሰው መደበኛ አይን የማይታዩ ፍጡራን ናቸው፡፡ ከሰው አይን ተሰውረው (ተደብቀው) በየወንዛወንዙ በቀትርና በጨለማ፣ በፍርስራሽና በቆሻሻ ስፍራዎች ይገኛሉ፡፡ በአገራችንም ከ11-12 ሰዓት ድረስ ባለው የማታ ክፍለ ጊዜ (ሚስቲያብ፣ መግሪብ) ጂኒዎች ስለሚለቀቁ ሴቶች ልጆቻቸውን ወደቤት እንዲሰበስቡ በራቸውን እንዲዘጉ፣ ቡሃቃና ሌማታቸውን እንዲከድኑ የሚመከሩበት ባህል አለ፡፡ ከጂኒዎች (ከጅኖች) መካከል አብዛኞቹ በፈጣሪ (አሏህ) የሚያምኑና ለጌታ ተገዢዎች መሆናቸው በብዙ ሰነዶች ተገልጿል፡፡ በአንዳንድ የእምነት አስተምህሮት መሰረት በፈጣሪ አምላክ (አሏህ) የሚያምኑና ለእሱ የማይገዙ ጅኖች ‹‹ሰይጣን Satan›› ይባላሉ፡፡ የተረገሙ ፍጡራን ናቸው፡፡ ሙስሊሞች ‹‹አአዙ ቢሏሂ ሚነ ሸይጧን ረጂም›› ሲሉ ከተረገመው ሰይጣን በፈጣሪ (በአሏህ) እጠበቃለሁ ማለታቸው ነው፡፡ ከእርጉሙ ሰይጣን ጌታ ይጠብቀኝ እንደማለት ነው፡፡

ጂኒዎች (ጅኖች) አይታዩም፡፡ ጂኒ (ጅን) የተባሉትም በዚሁ ባለመታየት (በስውርነት) ባህርያቸው ነው፡፡ ስለጂን (ጂኒ) ጠሊቅ ምርምር ያደረጉ የእውቀት ባለቤቶች እንደሚያምኑት ከሆነ ጅን (ጂኒ) የሚለው ቃል የመጣው ከአረብኛ ነው፡፡ ‹‹ጀነ›› ከሚለውና ትርጉሙ የማይታይ የተሰወረ ድንቅ ማለት ከሆነው የአረብኛ ስርወ ቃል ነው ይላሉ፡፡

ቀደምት ታሪኮችን ስንቃኝ ለምሳሌ በጥንታዊቷ ሜስፓታሚያና በቢሎናውያን ባህሎች መሰረት ሁለት አይነት ጅኖች (አጋንንት) አሉ፡፡ አንደኛው አይነት ‹‹ላባርቱ-Labartu›› የሚባሉ የጂኒ ዘሮችን (ጎሳዎችን) የሚመለከት ነው፡፡ እነዚህ ሰው ያልሆኑና በአደገኛ ስፍራዎች በአብዛኛው በበረሃና በመቃብር በተራራ በሸለቆ በረግረግ... አካባቢዎች የሚኖሩ ከዚያ እየመጡ ሰውን የሚተናኮሉ በተለይ ህፃናትን የሚጠናወቱ ጅኖች (አጋንንት) በሁለቱም ፆታዎች ይገኛሉ፡፡ ወንድ ጂኒ (ጋኔን) አለ፡፡ ሴት ጂኒ (ጋኔን) አለች፡፡ በአንድ በኩል መጥፎ የሆነና በሌላ በኩል ደግሞ እንደጠባቂ መንፈስ (አውሊያ) የሚያገለግሉ አጋንንት መኖራቸውም በጥንታዊና ዕድሜ ጠገብ የጥናት ድርሳናት ውስጥ ሰፍሯል፡፡

በጂኒዎች (አጋንነት) ትንታኔ መሰረት እጅግ በጣም ውብ የሆኑ የጠይም ቆንጆዎች ጎላ ያለው ጡታቸው ማራኪ ወገብ ዳሌና መቀመጫቸው ማንኛውንም ወንድ ለማንበርከክ የማይሳነው ተፈጥሮ ያላቸው ሴት ጋኔኖች (ጅኖች) አሉ፡፡ በሰላም ወደተኛው አንድ (ሰው) ሌሊት በእንቅልፍ ልቡ እየመጡ ወደር በሌለው ወሲባዊ ጡዘት የስሜቱ ጣሪያ ላይ አድርሰው ተራክቦ (ወሲብ) እየፈፀሙ ሰውዬው በሌላ ጊዜ ከሚያመነጨው የዘር ፈሳሽ (ስፐርም) በብዙ እጥፍ የሆነ ፈሳሽን አስረጭተው ይሄዳሉ፡፡ ሰውዬው ከእንቅልፉ ሲነቃ የብልቱ አካባቢ በሚያጣብቅና ብዛት ባለው ወንዴ ፈሳሽ ረጥቦ ያገኛል፡፡ የሆነውን ነገር ሲያስታውሰው ከፍተኛ ደስታ ይሰማዋል፡ ፡ ሁሌም መጥታ በተዋሰበችኝ (በተገናኘችኝ) እያለ በጊዜ ይተኛል፡፡ ይህቺ ጂኒ (ጋኔን) ‹‹ሊሊቱ Lilitu›› ትባላለች፡ ፡ ከሊሊቱ ጋር የእንቅልፍ ልብ ወሲብ የደጋገመ ሰው ከሌሎች መደበኛ ሴቶች (ሰዎች) ጋር ወሲባዊ ግንኙነት የመፈፀም ፍላጎቱ በእጅጉ ይቀንሳል፡፡ እንደ እሷ (እንደ ሊሊቱ) የማይሆንለት እየመሰለው እንደ ከንቱ ድካም ስለሚቆጥረው ከሚስቱ ጋር ጭምር የባልነት (የወንድነት) ሚናውን ለመጫወት ዳተኛ ይሆናል፡፡ ከሚስቱ ጋር በሚገናኝበት ጊዜም የዛችን ጂኒ (የሌሊቱን) ወሲባዊ አኳሀን በሀሳቡ እያመጣ እሷን (ሊሊቱን) እንደተገናኘ በምናቡ እየሳለ ካልሆነ በቀርም እንደ ወንድ መጠን ኃላፊነቱን በብቃት ለመወጣት ያዳግተዋል፡፡ በተመሳሳይ ሁኔታ ሌሊት እየመጡ ሴቶችን የሚገናኙና የልጃገረዶችን ክብረ ንፅህና (ድንግል) የሚገስሱ ወንድ ጂኒዎች (ጋኔን) አሉ፡፡ እነዚህ በአንደኛው የጂኒ ቡድን ከሚጠቀሱት ጥቂቶቹ ናቸው፡፡

ሁለተኞቹ የጂኒ (የአጋንንት) አይነት ደግሞ ‹‹ኢቲሙ Etimu›› ይባላሉ፡፡ እነዚህ ጂኒዎች ያለ ዕድሜያቸው በተለያዩ ተፈጥሯዊ ባልሆነ ምክንያት የሞቱ ሰዎች የሙት መንፈስ ሆነው ለበቀል የሚመጡ ናቸው፡፡ ባልታሰበ ጊዜና ሁኔታ እየመጡ በሚያደርሱት የበቀል ጥቃት ለከፍተኛ አደጋና ለበሽታ የሚዳርጉ ስለመሆናቸው በሜስፓተሚያ የእምነትና የባህል ታሪኮች ውስጥ አለ፡፡

በህንዶች እምነት ውስጥም ሁለት አይነት ጂኒዎች (አጋንንት) አሉ፡፡ የሰው የሙት መንፈስ ያልሆኑት ጂኒዎች ‹‹ዳናቫስ Danavas, ዳኤይታስ፣ Daeitas፣ ራካሳስ Racasas›› በመባል ይታወቃሉ፡ ፡ የሰው የሙት መንፈስ ሆነው ለበቀል የሚመጡትና አደጋና በሽታ በማድረስ የሚታወቁት ጂኒዎች ደግሞ ‹‹ቡታስ Bhutas›› ይባላሉ፡፡

በእንግሊዝኛው Demon (ዴሞን) የሚባለው የአጋንንት መጠሪያ የመጣው ዲሚዩን (Demeon) ከሚለው የጽርእ (የግሪክ) ቃል ነው፡፡ በጥንታዊ ግሪካውያን እምነትና ባህል መሰረት ጨለማን ተገን አድርገው የሚንቀሳቀሱ አራት (4) አይነት ጅኖች (አጋንንት) አሉ፡፡ አንደኛውና በጣም ጥሩ የሆነውን ካልነኩት የማይነካውን ካልደረሱበት የማይደርሰውን እንዲያውም ካቀረቡትና ከተለማመኑት ከገበሩለትና ከሰገዱለት ሀብት (ገንዘብ) ይሰጣል ብለው የሚያምኑበትን ጋኔን ዲሚዩን (Demeon) ይሉታል፡፡ ያለ አግባብ በሴት የተነሳ ወይም በገንዘብ፣ በስልጣን፣ በቅናት፣ በምቀኝነት የተነሳ እንዲሞቱ የተደረጉ (የተገደሉ) ሰዎች የሙት መንፈስ ሆነው መጥተው አስለፍልፈው፣ አሰቃይተው፣ ሽባ (ስንኩል) አድርገው፣ በበሽታ መትተው የሚበቀሉ የአጋንንት ሠራዊት ደግሞ ‹‹አላስተር Alastor›› ይሏቸዋል፡፡

በአይሁድና በክርስትና እምነቶችና ባህሎች ውስጥ ‹‹ጅን፣ ጋኔን፣ አጋንንት...›› የሚሉ መጠሪያዎች በበርካታ ቅዱሳን መጽሐፍት ውስጥ ተጠቅሰው ይገኛሉ፡ ፡ ለምሳሌ በትንቢተ ኢሳያስ (34፡14) ላይ፡-

‹‹... አጋንንትም እርስ በርሳቸው ይጠራራሉ፤ ጅንም በዚያ ትኖራለች፡፡ ለእርስዋም ማረፊያ ታገኛለች... The satyr shall cry to his fellows... the Night Nag...›› ተብሎ ተፅፏል፡፡

በጥንቱ መጽሐፍ ውስጥ የአጋንንት መጠሪያ ‹‹ሴሪም Serim›› ነበር፡፡ በስተኋላ ጊዜ በተሻሻለው መጽሐፍ ውስጥ ግን ‹‹ሳቲር satyr›› ተብሏል፡፡ ዞሮ ዞሮ ያው አጋንንት ነው፡፡

በወንጌል ውስጥም ስለ ጅን (ጋኔን አጋንንት...) የሚያወሱ በርካታ ጥቅሶች አሉ፡፡ ጥቂት ምሳሌዎችን እነሆ፡-

‹‹...ዮሐንስ ሳይበላና ሳይጠጣ መጣ፣ እነርሱም ጋኔን አለበት አሉ›› (ማቴዎ 11፡18)››

‹‹ጋኔን ያደረበትን እውር ዲዳም ወደ እርሱ (ወደ ኢየሱስ) አመጡ፡፡ እውሩም ዲዳውም እስኪያይና እስኪሰማ ድረስ ፈወሰው፤ እነርሱም በአጋንንት አለቃ በብኤል ዜቡል ካልሆነ በቀር አጋንንትን አያዋጣም አሉ፡፡ ኢየሱስም እርስ በርሷ የተከፋፈለች መንግስት ትወድቃለች ሰይጣንም በሰይጣን አይወጣም...›› (ማቴ 12፡ከ22)

‹‹...ኢየሱስ ጋኔኑን (Demon) ካወጣ በኋላ ዲዳው ተናገረ›› (ማቴ 9፡33-34)

‹‹...ሴትዮዋን ልጄን ጋኔን ክፉኛ ይዞታል አለች›› (ማቴ 15፡22)

‹‹...ኢየሱስ ከብላቴናው ጋኔኑን ገስፆ አስወጣው›› (ማቴ 17፡18)

‹‹...የታመሙትን አጋንንት ያደረባቸውንም ሁሉ ወደ እርሱ አመጡ፤ ብዙዎችን አጋንንት አወጣ፤ አጋንንትም ክርስቶስ መሆኑን አውቀው ነበረና ሊናገሩ አልፈቀደላቸውም›› (ማርቆስ 1፡23)

‹‹...አህዛብ የሚሰዉት ለአጋንንት እንጂ ለእግዚአብሔር እንዳልሆነ... ከአጋንንት ጋር ማህበርተኛ እንዳትሆኑ... የጌታን ጽዋና የአጋንንትን ጽዋ ልትጠጡ አትችሉም›› (1ኛ ቆሮንቶስ 10፡20-1)

‹‹...አይሁድ ኢየሱስ ሳምራዊ እንደሆንክ፣ ጋኔንም እንዳለብህ በማለታችን እኛ መልካም አንል የለምን? አሉት እርሱም እኔስ ጋኔን የለብኝም አላቸው›› (ዮሐ 8፡48)

‹‹...ታላቂቱ ባቢሎን ወደቀች የአጋንንትም ማደሪያ ሆነች የርኩስ መናፍስት ሁሉ መጠጊያ ሆነች...›› (ዮሐንስ 18፡02)

በጣም ብዙ ቦታ ተጠቅሷል፡፡ ጅን (አጋንንት) የሚለው ቃል ወደ 40 ጊዜ ገደማ ተጽፎ ይገኛል፡፡

በእስልምና አስተምህሮት ውስጥ ጅን (ጂኒ) መኖር የተረጋገጠ ነው፡፡ በቁርአኑ ውስጥ በብዛት ተጠቅሷል፡፡ ነቢዩ (ሰ.ዐ.ወ) ከአሏህ የተላኩት ለሁለቱም አለማት (ለሰውና ለጅኖች) መሆኑም ተጽፏል፡፡ ጅኖች ለፈጣሪ (አሏህ) ተገዢ መሆናቸውና እንደሰው የሚሰሙና የሚናገሩ መሆናቸውም አለ፡፡ ቁርአን ሲነበብ ሰምተው መደነቃቸው ተገልጿል፡፡ ‹‹ኢና ሰሚዕና ቁርአነን አጀባ›› ጅኖች በመጽሐፉ ውስጥ የራሳቸው ምዕራፍ አላቸው፡ ፡ ሱረተል ጅን ይባላል፡፡ ጅኖች እንደሰው ሴቶችን የሚደፍሩ መሆናቸውን በማወቅ ለፈጣሪ የታዘዙ ፃድቃን ሰዎች ገነት ሲገቡ የሚያጋጥሟቸው ሴቶች ከዚህ በፊት ሰውም ሆነ ጅን ያልደፈራቸው (ያልተራከባቸው) ንፁህ ውብ ሴቶች መሆናቸውም ይነበባል፡፡ ‹‹ለም የጥሚሱሁነ ኢንሳኑ ቀብለሁም ወላ ጃን›› (ረህማን (55)፣ 74)

ነብዩ ሙሐመድ (ሰ.ዐ.ወ) ጅን (ጂኒ) ያደረባቸውን በርካታ ልክፍተኞችና በሽተኞች ከቁርአን ውስጥ ያሉትን የአሏህ መልዕክቶች (አያዎች) በመቅራት መፈወሳቸው በታመኑት ስድስቱ ሃዲስ ዘጋቢዎች (ሷሂህ ሲታእ) ተዘግቧል፡፡ እውነትነቱም አንዳች አያጠራጥርም፡፡

በአጠቃላይ ሲታይ ጅን (ጋኔን/አጋንንት) የተጠናወታቸውን ሰዎች ማስለቀቅ የሚቻልበት ዘዴ አለ፡፡ አጋንንት ሰው እንዲተናኮሉ የማድረጊያ ጥበብም አለ፡፡ አጋንንት እየጠሩ (እየጎተቱ) ሜርኩሪ አምጣ... ሉባን ዘከር አጭስ... በግ ይታረድ... እያሉ ገንዘብ እንዲወርድ የሚያደርጉ (ያስተውሪድ) ሰዎችም አሉ፡፡ ይህ ግን ከፈጣሪ አምላክ የሚያቆራርጥ ሰይጣናዊ ዘዴ በመሆኑ በትክክለኛ የእምነት ተከታዮች ዘንድ የተወገዘ ነው፡፡ ፈጣሪ ቀድሞ በወሰነው (በቀደረው) መንገድ ብቻ መጓዝ ይበቃል፡፡ ‹‹የፈለገው ይምጣ... በልቼ ልሙት... ወዘተ›› ብሎ አጋንንት መጎተትና ማዘዝ ቢያስፈልግ እንኳ ጉዳዩ ከፍተኛ እውቀትና ጥንቃቄን የሚጠይቅ ነው፡፡ ዘው ብሎ የሚገቡበት ነገር አይደለም፡፡

አጋንንትን መጎተት (መጥራት) የሚፈልግ ሰው የመመለሻውን ዘዴም ማወቅ አለበት፡፡ ያለዚያ ጎትቶ ያመጣው አጋንንት (ሰይጣን) እንደኳስ ተጫውቶበት ሊሄድ ይችላል፡፡

አንድ ጓደኛዬ ወሎ ውስጥ በእንጀራ አባቱ ላይ የደረሰውን ታሪክ ነግሮኝ በሳቅ አፍርሶኛል፡፡ ላጫውታችሁ፡፡ እናቱ ሌላ ባል ነበራቸው፡፡ የእሱ አባት ማለት ነው፡፡ የአጋንንት መጥሪያና ማዘዣ መጽሐፍ ነበራቸው፡፡ እሳቸው ሲሞቱ ያ መጽሐፍ እናቱ ሳጥን ውስጥ ነበር፡፡ በኋላ እናትየው አንድ አስተማሪ ሰውዬ አግብተው ሲኖሩ ያን መጽሐፍ ድንገት ሲያመጡ አስተማሪ ሆዬ ያይና ‹‹ምንድነው እሱ? እስቲ ወዲህ በይው›› ይላቸዋል፡፡ ‹‹ተው አንቱ ሰውዬ መጥፎ መጽሐፍ ነው ይቅርብዎት›› ይላሉ እናትየዋ፡፡ ባልየው ነጥቆ ይቀበልና ያየዋል፡፡ የአጋንንት መጥሪያ (መጎተቻ) ንባቦችን ያገኛል፡፡ ጫቱን ገዝቶ መጣና ጀመረው፡፡ ሞከረ ሞከረና ተሳካለት፡፡ የተጠሩት ሁለት ፈርጣማ ጅኖች (አጋንንት) ከች አሉ፡፡ እንደሚከተለው ተነጋገሩ፡፡

አጋንንት፡- በጠራኸን መሰረት መጥተናል ምን እንታዘዝ?

ሰውዬው፡- በጣም ጥሩ እኔ የምፈልገው ገንዘብ ነው

አጋንንት፡- በብር ነው? በዶላር?

ሰውየው፡- በዶላር ይሻለኛል

አጋንንት፡- ምን ያህል ዶላር ይበቃሃል?

ሰውየው፡- በሁለት ኩርቱ ፌስታል (በትልቁ) አድርጋችሁ በባለመቶ ዶላር ኖት ካመጣችሁልኝ ለጊዜው ይበቃኛል፡፡ ሌላ ጊዜ ደግሞ እጠራችኋለሁ፡፡

አጋንንት፡- ታዛዥ ነን እናመጣለን አሁን አሰናብተን

ሰውየው፡- በቃ ሂዱ! አላቸው፤ (እሱ መጥሪያውን እንጂ መመለሻውን አላነበብም (አላወቀም))

አጋንንት፡- ማሰናበት’ኮ እንዲህ አይደለም

ሰውየው፡- ታዲያ እንዴት ነው?

አጋንንት፡- ምስ (ምሳችንን) ስጠን እንጂ?

ሰውየው፡- ዶላሩን ይዛችሁ ስትመጡ እሰጣችኋለሁ፡፡

አጋንንት፡- አሁን የመሰናበቻ የምታቀምሰን ነገር የለም?

ሰውየው፡- ለጊዜው የለም

አጋንንት፡- የአረቄ ጥንፋፊ፣ ትንሽ ስጋ አተላ እንኳ ቢሆን የለህም?

ሰውየው፡- ወይ ስጋ? ሁሉንም ስትመጡ አቀርባለሁ፤ አሁን ሂዱ፤ ይሄኔ አጋንንቱ በቋንቋቸው ተነጋገሩና ስማ አሉት፤ አንተ ሁለት ኩርቱ በትልቁ ፌስታል ሙሉ ዶላር እንድናመጣልህ የጠራኸን ለእኛ የምታቀምሰን ምናምኒት እንኳ ሳታዘጋጅልን ነው እንዴ? የማነህ አራዳ ጃል? ብለው ሁለቱ አጋንንት እንደ ዌስሊ ስናይፕስ በጫማ ጥፊና በጡጫ ሲነርቱት ወገቡን ሰብረው ጣሉት፡፡ አስተማሪ ተብየው በምን ጉልበትና ዘዴው ይቻለው? በኋላ እናትየዋ ጉድጉዱን ሰምተው ከኩሽና ብቅ ሲሉ ባልየው ወገቡ ተሰብሮ ወድቋል፡፡ የሚያጫጭሱትን አጫጭሰው የሚያደርጉትን አደራርገው የባላቸው ነብስ መልስ አለችላቸው፡፡ ታዲያ ምን ያደርጋል ባልየው በአጋንንት ጡንቻ የተሰበረ ወገባቸው ሊድን አልቻለም፡፡ ይኸው እስከ ዛሬ ድረስ እንደከዘራ ጎብጠው መሬት መሬት እያዩ ይሄዳሉ፡፡ ቀና ማለት እንኳ አይችሉም፡፡ አያድርስ አይደለም? ቀልድ እንዳይመስላችሁ፡፡ እውነተኛ ታሪክ ነው፡፡ ይቅርባችሁ፡ ፡ ለትልቁም ለትንሹም አጋንንት ጎታች ዘንድ ‹‹አዋቂ ናቸው›› እያላችሁ አትመላለሱ፡፡ ገላችሁን አታርክሱ፤ በፈጣሪ ዘንድም አትወቀሱ፡፡ ልባችሁን ወደ አንድ ፈጣሪ (አሏህ) ብቻ መልሱ፡፡ እሱ አሏህ ይጠብቃችኋል፡፡ ወደ ቀጥተኛው መንገድም (ሲራጠን ሙልተቂም) ተመለሱ፡፡
ጋንች.
ጀማሪ ኮትኳች
ጀማሪ ኮትኳች
 
Posts: 96
Joined: Fri Dec 16, 2011 6:25 pm

Postby ክቡራን » Mon Jul 15, 2013 8:21 pm

ጋንቾ አሪፍ ጽሁፍ ነው ያስነበበከን:: እኔማ ማስታወሻ ሁሉ ይዣለሁ:: :D ከሞላ ጎደል በጽሁፉ ትክክለኛነት እስማማለሁ:: ልጅ ሆኔ ይመሰለኛል አንድ ጂኒ ካልጋዬ ላይ አንስቶ አፍኖ አሸከርክሮ አሽከርክሮ ብጮህ ዖ ዖ ብል እንኴን (አፍኖ ሊገድለኝም ነበር መሰለኝ) ...ከዛ አልጋዬ ላይ ወረውሮኝ ሄዷል:: ባየር ላይ አንሳፎኛል ምን አለፋህ በጠረባ ሰው ሲመታህ ጭንቅላትህ መሬት እንደሚነካ እነዚህ ጂኒዎች መሬት የሚነኩ አይመስሉኝም ብድግ ያደርጉህና ባየር ላይ በጠረባ ይሉሀል..ያኔ አየር ላይ መንሳፈፍ ትጀምራለህ :: :D ወንድሜ ያልጠራኌቸው የቅዱሳን ስም የሉም:: እንደዚህ አይነት ነገር ግን ከዛ በኌላ አላጋጠመኝም :: ይሄ ታቡ ሳይሆን እውነት ነው:: በዚህ ጉዳይ ላይ መወያየት ይቻላል:: ክፉ መነፈሶች አሉ ደግ መንፈሶችም አሉ:: ግን ሁሉም ነገር ካንሲስተሮችህ ጋር ይያዛል:: ጥሩ ና መልካም የሚያደርጉ አንሲስተሮች ካሉህ ሁሌም በጥሩ መንፈስ ትከበባለህ...አንሲስተሮች መጥፎ ከሆኑ ግን አንተም መጥፎ የምትሆንበትም ምክንያት አለ:: መፍቴሄው ላንሲስተሮቻችን መጽለይ አለበን:: የነሱ መሳያ ( Messiah ) እኛ ነን:: እነሱ ወደ ምድር ተመልሰው መመጣት አይችሉም:: የኛ ጸሎትና መልካም ማድረግ እነሱን ይረዳቸዋል:: ወደሚቀጥለውም ሪያልም እንዲያልፉም ያግዛቸዋል:: ለዚህ ነው በስማቸው በኦርቶዶክስ እምነት ዝክር, አርባ , የሙት አመት እየተባለ በስማቸው መልካም ነገር የሚደርግላቸው. ስፕሪትዩአል ዎርልድ ዝም ብለህ የምትተኛበት አይደለም....ሂደት ነው ፕሮሰስ ነው:: ግን ሂደቱ ፈጣን አይደለም እንደ ጂኦሎጂ ታይም ነው...!! .በነገርህ ላይ የምትላቸው ጂኒዎች እዚህ ዋርካ ላይ በብዛት አሉ:: ዋርካ ፖሎቲካና, ዋርካ ጄኔራል ከለጠፍከው ጂኒዎቹ እንማን እንደሆኑ ባለኝ መገለጽና እውቀት ክላሲፋይ አድርጌ እነግርሀለሁ:: :D
ክቡራን
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 8282
Joined: Tue Mar 04, 2008 4:24 pm

Re: ጂኒ (ጅን)... ጋኔን አጋንንት ምንድን ነው?

Postby ደጉ » Sun Aug 04, 2013 9:48 am

ጋንች. wrote:....በጂኒዎች (አጋንነት) ትንታኔ መሰረት እጅግ በጣም ውብ የሆኑ የጠይም ቆንጆዎች ጎላ ያለው ጡታቸው ማራኪ ወገብ ዳሌና መቀመጫቸው ማንኛውንም ወንድ ለማንበርከክ የማይሳነው ተፈጥሮ ያላቸው ሴት ጋኔኖች (ጅኖች) አሉ፡፡ በሰላም ወደተኛው አንድ (ሰው) ሌሊት በእንቅልፍ ልቡ እየመጡ ወደር በሌለው ወሲባዊ ጡዘት የስሜቱ ጣሪያ ላይ አድርሰው ተራክቦ (ወሲብ) እየፈፀሙ ሰውዬው በሌላ ጊዜ ከሚያመነጨው የዘር ፈሳሽ (ስፐርም) በብዙ እጥፍ የሆነ ፈሳሽን አስረጭተው ይሄዳሉ፡፡ ሰውዬው ከእንቅልፉ ሲነቃ የብልቱ አካባቢ በሚያጣብቅና ብዛት ባለው ወንዴ ፈሳሽ ረጥቦ ያገኛል፡፡ የሆነውን ነገር ሲያስታውሰው ከፍተኛ ደስታ ይሰማዋል፡ ፡ ሁሌም መጥታ በተዋሰበችኝ (በተገናኘችኝ) እያለ በጊዜ ይተኛል፡፡ ይህቺ ጂኒ (ጋኔን) ‹‹ሊሊቱ Lilitu›› ትባላለች፡ ፡ ከሊሊቱ ጋር የእንቅልፍ ልብ ወሲብ የደጋገመ ሰው ከሌሎች መደበኛ ሴቶች (ሰዎች) ጋር ወሲባዊ ግንኙነት የመፈፀም ፍላጎቱ በእጅጉ ይቀንሳል፡፡ እንደ እሷ (እንደ ሊሊቱ) የማይሆንለት እየመሰለው እንደ ከንቱ ድካም ስለሚቆጥረው ከሚስቱ ጋር ጭምር የባልነት (የወንድነት) ሚናውን ለመጫወት ዳተኛ ይሆናል፡፡ ከሚስቱ ጋር በሚገናኝበት ጊዜም የዛችን ጂኒ (የሌሊቱን) ወሲባዊ አኳሀን በሀሳቡ እያመጣ እሷን (ሊሊቱን) እንደተገናኘ በምናቡ እየሳለ ካልሆነ በቀርም እንደ ወንድ መጠን ኃላፊነቱን በብቃት ለመወጣት ያዳግተዋል፡፡...

.....ለካ ድሮ ድሮ እኔ ጋ ትመጣ የነበረችው አንዱዋ የነዚሀ አይነትዋ ቆንጆ ነበረች ..አስተምሪው ተብላ የተላከች ይመስለኝ ነበር....እናትዋንና ሌላ ቦይ ፍሬንድ አግኝንታ ነው ማለት ከኔ ጋ ድራሽዋ የጠፋው....:( ;)
...ግን እንዴት ነው ወንዱ የልጃገረዶቹን ህግ መውሰድ እሚችለው..?;) በዚህ አይነት እንትናዬ የሌላት ለዛ ነው ማለት ነው...;)
"STUPID IS AS STUPID DOES " :D
ደጉ
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 4458
Joined: Mon Dec 15, 2003 10:39 am
Location: afghanistan

Postby ደጉ » Sun Aug 04, 2013 1:02 pm

ክቡራን wrote:ጋንቾ አሪፍ ጽሁፍ ነው ያስነበበከን:: እኔማ ማስታወሻ ሁሉ ይዣለሁ:: :D ከሞላ ጎደል በጽሁፉ ትክክለኛነት እስማማለሁ:: ልጅ ሆኔ ይመሰለኛል አንድ ጂኒ ካልጋዬ ላይ አንስቶ አፍኖ አሸከርክሮ አሽከርክሮ ብጮህ ዖ ዖ ብል እንኴን (አፍኖ ሊገድለኝም ነበር መሰለኝ) ...ከዛ አልጋዬ ላይ ወረውሮኝ ሄዷል:: ባየር ላይ አንሳፎኛል ምን አለፋህ በጠረባ ሰው ሲመታህ ጭንቅላትህ መሬት እንደሚነካ እነዚህ ጂኒዎች መሬት የሚነኩ አይመስሉኝም ብድግ ያደርጉህና ባየር ላይ በጠረባ ይሉሀል..ያኔ አየር ላይ መንሳፈፍ ትጀምራለህ :: :D ወንድሜ ያልጠራኌቸው የቅዱሳን ስም የሉም:: እንደዚህ አይነት ነገር ግን ከዛ በኌላ አላጋጠመኝም :: ይሄ ታቡ ሳይሆን እውነት ነው:: በዚህ ጉዳይ ላይ መወያየት ይቻላል:: ክፉ መነፈሶች አሉ ደግ መንፈሶችም አሉ:: ግን ሁሉም ነገር ካንሲስተሮችህ ጋር ይያዛል:: ጥሩ ና መልካም የሚያደርጉ አንሲስተሮች ካሉህ ሁሌም በጥሩ መንፈስ ትከበባለህ...አንሲስተሮች መጥፎ ከሆኑ ግን አንተም መጥፎ የምትሆንበትም ምክንያት አለ:: መፍቴሄው ላንሲስተሮቻችን መጽለይ አለበን:: የነሱ መሳያ ( Messiah ) እኛ ነን:: እነሱ ወደ ምድር ተመልሰው መመጣት አይችሉም:: የኛ ጸሎትና መልካም ማድረግ እነሱን ይረዳቸዋል:: ወደሚቀጥለውም ሪያልም እንዲያልፉም ያግዛቸዋል:: ለዚህ ነው በስማቸው በኦርቶዶክስ እምነት ዝክር, አርባ , የሙት አመት እየተባለ በስማቸው መልካም ነገር የሚደርግላቸው. ስፕሪትዩአል ዎርልድ ዝም ብለህ የምትተኛበት አይደለም....ሂደት ነው ፕሮሰስ ነው:: ግን ሂደቱ ፈጣን አይደለም እንደ ጂኦሎጂ ታይም ነው...!! .በነገርህ ላይ የምትላቸው ጂኒዎች እዚህ ዋርካ ላይ በብዛት አሉ:: ዋርካ ፖሎቲካና, ዋርካ ጄኔራል ከለጠፍከው ጂኒዎቹ እንማን እንደሆኑ ባለኝ መገለጽና እውቀት ክላሲፋይ አድርጌ እነግርሀለሁ:: :D

....አሁንም አለቀቁህም እኮ ....ምንም ክላሲፋይ ማድረግ አያስፈልግህም ....እዚህ ከ ርእስ ርእስ እንደ ውሻ እሚያሩዋሩጡህ እነሱ ናቸው .. :lol: አንድ አራት አምስት ትሆናላችሁ በግምት .. :D
"STUPID IS AS STUPID DOES " :D
ደጉ
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 4458
Joined: Mon Dec 15, 2003 10:39 am
Location: afghanistan


Return to Warka Culture and Literature - ዋርካ ባህልና ሥነ ጽሑፍ

Who is online

Users browsing this forum: No registered users and 3 guests