ሞትስ ሞቷል ይሁዳ:ጥርጥር የለኝ አልሰጋ:
ተለይቷል ከዚህ ዓለም በአካል ሥጋ:
መንፈሱ እንጅ ያልሞተዉ የሚኖረዉ ከኛጋ::
መልከ-ብዙ ይሁዳዎች: ገጸ-ብዙ ፈርጅ ያላቸዉ:
ለዓለም መናጥ ሰበብ-አስባብ በየፊናዉ:
መንፈሱ ነው የይሁዳ እኛ ከእርሱ የወረስነው::
ሩሙን ለማሞቅ ያክል እንጅ መቼም ያንቺን ግጥም ችሎታ ለመገዳደር እንዳይደል ይታወቅልኝ:: ቅቅቅ
እቴጌይት wrote:አልሞተም ይሁዳ
የክህደቱ- ግዝፈት መጠን- ብርሀነ ውስጡን -አክስሎ
የበደሉ -ጸጸት ሸክም - ሕሊናውን አቁስሎ
መኖር ታክቶት - በጸለመ -እሱነቱ
መስሎኝ ነበር -አኮ ይሁዳ- የታነቀ- በኅጢአቱ
ግና ዛሬ- የዘመን ጉድ- ጉድ አሳየ
ከአንበብነው- ከመጣፉ- የተለየ
ትውፊት ንግርት- ትንቢቱ ሁሉ- ተለዋውጦ
ሀዲስ ብሉይ- ኦሪት ራዕይ- ተገላብጦ
የከሃዲው- መታነቁ -ሞቱ ቀርቶ
ማቅ መልብሱ -ምልጃው ጠፍቶ
በአደባባይ- እንደጻዲቅ- መድረክ ወጥቶ
ክህደት ግብሩን -ገድሉን ሲያውጅ- አፉን ሞልቶ
እውነት ታስሮ- ለስቅላት- ፍርድ ሲነዳ
ብዙ አሳየን- ገና አልሞተም -የኛ ይሁዳ!