እድገት በህብረት.....ታሪካዊ ቅብጥርጥር

Topics related to cultures, arts, languages, arts such as humor, music, traditional literary genres of poems, ግጥም ፣ ቅኔ ፣ ተረትና ምሳሌ)

እድገት በህብረት.....ታሪካዊ ቅብጥርጥር

Postby ዳግማዊ ዋለልኝ » Sat Jul 27, 2013 11:00 am

እድገት በህብረት......ታሪካዊ ቅብጥርጥር

አሁንም ድረስ ጆሮዬ ላይ ያንቃጭላል

ፋኖ ተሰማራ
እንደሆ ቺ ሚኒህ
እንደቼ ጉ ቬራ

በወቅቱ የጀነራል ዊንጌት የአስራ ሁለተኛ ክፍል ተማሪ ነበርኩኝ:: ደስ የሚል ጊዜ...አስደሳች...ወቅት:: ወደኋላ መለስ ብዬ ውልደቴና ዕድገቴን ስመለከትም; ማርና ወተት ከምታፈሰው ኢትዮጵያ; ከባላባት ዘሮች የተወለድኩኝ; ህይወት ገና ከማህፀን በሐር ሻሽ የተቀበለችኝ ዕድለኛ.........

በጊዜው እንደማንኛውም ኢትዮጵያዊ በቄስ ትምህርት አልፌ መደበኛ አስኳላ ገብቼ; ጥሩ ውጤት እያመጣሁ ገስግሼ እነሆ የሁለተኛ ደረጃ ትምህርትን ልጨርስና ሀገሬን ላገለግል ጫፍ የደረስኩኝ ከእኔ በላይ ሊቅ የሌለ; መሀይሙ የሀገሬ ገበሬ አይኑን አንጋጦ; እጁን ዘርግቶ ከድንቁርና ነፃ እንዳወጣው የሚማፀነኝና ተስፋ የተጣለብኝ ትኩስ የለውጥ ሀይል እኔና እኔ ብቻ ነኝ........በእኔ ቤት :!:

ዕድገት በህብረትም ታወጀ.......ህልሜ እውን ሆነ

ፋኖ ተሰማራ
እንደሆ ቺ ሚኒህ
እንደቼ ጉ ቬራ

ደሜ በውስጤ ሲራወጥ ይሰማኛል......ለክብርና ለኩራት መታጨት ምንኛ ደስ ይላል........ኦ......ኢትዮጵያ....እኔ ባልኖር ምን አባትሽ ይውጥሽ ነበር :?: ......በመማሬ ኮራሁኝ; በማወቄ ተንጠባረርኩኝ......አበጀሁ :!:

ምስኪኗ የፍቅር ጓደኛዬ ገነት....እኔ እንደምጠራት ደግሞ ገኒ......እሷ ብቻ ቅር አላት........ገኒዬ የሀገር ፍቅር አይገባትም.....በያኔው ሳቄ ሳቅሁባት...ሀሀሀሀሀሀ...."ገኒዬ አልገባሽም...እኔ የምማረው; የምለፋው እኮ ለትልቅ ግብ; ለጭሰኛው ነፃነት ነው......የምለው የሚገባሽም አይመስለኝም" አልኳት.....ከት ብዬ እየሳቅሁኝ.......ዛሬ ላይ ሆኜ ሳየው ለካ ያልገባኝ እኔው ነበርኩኝ

____________________________________________________

የእድገት በህብረት ዘመቻ ምደባዬ አርሲ ኢተያ እንደሆነ አወቅኩኝ......ቦታውን ስሰማውን ለመጀመሪያ ጊዜ ነበር.....ግን የወጣትነትና የአብዮታዊነት ስሜቴ ተደበላልቆ ልዩ የደስታ ስሜት ፈጠረብኝ.......የትም ሆነ የትም እሔድና ይህን ያልተማረ ገበሬ አነቃዋለሁ......የቡርዧ; የኢምፔሪያሊዝምን ርዕዮተ-ዓለም አሳውቄ; ይህን ጭቁን ህዝብ አነቃዋለሁ የሚል ቃል ለራሴ ገባሁ......አወይ የዋህነቴ

አመሻሹ ላይ ወደገኒዬ ቤት አቀናሁና የጋሽ ሙሰማ ሱቅን ተደግፌ የጋሽ ሙሰማ ልጅ ሲራጅን ገኒን እንዲጠራት ላኩት........ቀዝቃዛ ምሽት......ሆኖም መርፌ የሚያስለቅም ሙሉ ጨረቃ ፍንትው ብላ የወጣችበት.........ገኒ የምሔድበትን ቦታና መሔዴ ቁርጥ መሆኑን ስነግራት ምን ትል ይሆን :?:..........ልቤ ራደ.......አዘነ........ከንፈሬ መንቀጥቀጥ ጀመረ.........ወዲያው ግን የሀገሬ ገበሬ ትውስ ሲለኝ ድፍረት አገኘሁ......አይ ድፍረት......ያኔ ምኑን አውቄው..........

ፋኖ ተሰማራ
እንደሆ ቺ ሚኒህ
እንደቼ ጉ ቬራ........

ይቀጥላል
"እቺ ለቅሶ ከፍየል በላይ ነች"
ዳግማዊ ዋለልኝ
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 3193
Joined: Wed Oct 20, 2010 12:09 am

Postby ገልብጤ » Sat Jul 27, 2013 4:32 pm

አሪፍ ቀደዳ ነው :wink:
ለምን እንደ ጎሳ PLAY BOY MEGAZINE ላይ አታወጣውም ታዲያ
ያልበሰለ ፖለቲከኛ ስለቀጣዩ ምርጫ ሲያስብ
የበሰለ ፖለቲከኛ ስለቀጣዩ ትውልድ ያስባል
James freeman clarke
ገልብጤ
ዋና ውሃ አጠጪ
ዋና ውሃ አጠጪ
 
Posts: 1695
Joined: Sat Jun 26, 2010 11:24 pm

Postby ዳግማዊ ዋለልኝ » Mon Sep 02, 2013 10:22 am

ገኒዬም ትክክል ነበረች.........እኔም ብዘገየም ግና ትክክለኛውን የህዝብ መስመርና ህወሀትን ተቀላቅዬ በአንድ ላይ ኢህአዴግን መሰረትን :!: ከእኔ የቀለም እውቀት በላይ የሀያሉን ገበሬ ጥበብና ሀያልነት መሰከርኩኝ!!

የትጥቅ ትግልም; የልማትም; የጥበብም ባለቤት የሆነው ኢትዮጵያው ኦሮሞ; አማራ; ትግራይ;አፋር; ወላይታ; አኝዋክ: ሐረሪ; ጉራጌ; ሽናሻ; ሲዳማ; ጋሞ: አገው; ስልጤ; ሶማሊ; ጉሙዝ; ወዘተ ጠቅላላው አርሶ አደርና አርብቶ አደር መሆኑን አወቅሁ.....ነፃ ወጥቼ...ነፃ አወጣሁኝ....እጅግም ደስ አለኝ :!: :!:

http://www.youtube.com/watch?v=pD-8ZUKgAnw

አበቃሁ :D ሙሉ ፅሁፌን አሳትሜ በነፃ ሳድለው ያንብቡት :D
"እቺ ለቅሶ ከፍየል በላይ ነች"
ዳግማዊ ዋለልኝ
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 3193
Joined: Wed Oct 20, 2010 12:09 am

Postby መራራ » Wed Sep 04, 2013 10:16 am

ወርቅሰው ነፍስ ዘርቶ ዳግሞ አወራዋለሁ ብዬ አስቤም አልሜም አላውቅም ነበር :lol: :lol: :lol: :lol: ለካ የማንጤሎ ሂጺ (ዳ-ግሞ) ምኞት ዊንጌት መማር እና የባላባት ልጅ መሆን ነበር? :lol: :lol: :lol: አሁን ህንጥሾ ምን ጎሎባት ይሆን ገኒ የተባለችውስ? አይ ህወሀቶች ነፍሳችሁ ይማራል? ይሄን ከ ሉሲ (ድንቅነሽ) ጋር አፈር ፈጭቶ እና ጭቃ አቡክቶ ካደገ ሽምትር ጋር ነበር ለካ ስታዳርቁን የከረማችሁት? :lol: :lol: :lol: እባካችሁ ግን የሚስቱን ህንጥሾን ስም ገኒ ብሎ እንዲቀይር እና ዊንጌትንም ቢያንስ አትክልተኛ ሆኖ ገባ ወጣ እንዲልበት ሳትፈቅዱለት ዳግሞ እንዳትገድሉት:: :lol: :lol: :lol: በ አቡነ አረጋዊ አደራ! እንደው በ አክሱም ጺዮን ማርያም አደራ! :lol: :lol: :lol: እኔ የንጋቷ ኮኮብም እላለሁ አምላክ ሆይ ሞት አፋፍ ላይ ካለ እድሜ ጠገብ ጋር ስለምንስ አዋልከኝ? :lol: :lol: :lol:
መራራ
ዋና ኮትኳች
ዋና ኮትኳች
 
Posts: 753
Joined: Sat Sep 25, 2004 9:58 am
Location: united states

Postby password » Thu Sep 19, 2013 11:47 am

እድገት በህብረት .... ዋው
ስንት ዘመን ሆነው... ሳስበው የተመሰቃቀለ ስሜት በውስጤ ይጋመዳል...
ወጣቶች በተስፋ የተሞላንበት ወቅት, ትንንሽ የታሪክ ልጉዋም በእጃችን ጨብጠን መጻኢውን እድላችንን ልንቀይስ በትኩስ ሀይል የተንቀለቀልንበት ጊዜ ነበር.. ከሁሉ ይበልጥ የነበረው የወንድማማችነት መንፈስ መቼም አይረሳም...

ሁሉም እንደተመኘነው ሳይሆን ቀረና, ያልታሰበ ከባድ ጨለማ ሰፈነ... በዚያ ጨለማ ውስጥ ግን ብርሀን ሆነው ያለፉ ወጣቶች ነበሩ.... ታዲያ ያኔ ዋለልኛችን እንደሚለን ህዋሃትን የሚቀላቀል ቀርቶ ስሙዋን ያሚያውቅ ወጣት- ትግራይ ውስጥ አላውቅም... መሀል አገር ውስጥ ግን በኩራዝ ተፈልጎ አንድ አይገኝም... ወጣቱን ያማለለ ወፍራም ድርጅት ቢኖር ... ኢህአፓ... ብቻ ነበር...

እድገት በህብረትን አንተርሶ የወቅቱን ሁኔታ በልቦለድ መልክ የሚተርክ መጽሃፍ ማያያዣውን ተከትልው በመሄድ ማግኘት ይችላሉ.... ስለኒያ ወጣቶች ትንሽ ያወጋል...

pdf
free
ነው.....

http://babile.wordpress.com

once you are in the website, click on the meny at e-books...

በተረፈ ዋርካዊያን እንዴት ናችሁ...

ፓስ
Last edited by password on Tue Oct 23, 2018 8:39 pm, edited 1 time in total.
password
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 323
Joined: Fri Apr 04, 2008 2:02 am
Location: Europe

Postby ሙዝ1 » Fri Oct 04, 2013 1:34 pm

ፓስ ወንድማችን ...
መጽሀፍህን በነጻ ስላስነበብከኝ ከልብ አመሰግናለሁ .... ደስ ይላል:: ስልዘመንህ እስካሁን ካነበብኩት በዛኛዉ ጥግ ያለ አሪፍ የፍቅር ወግ .... በተለይ ስለዛ ትዉልድ በአስራዎቹ መጨረሻና ሀያዎቹ መጀመሪያ ላይ ያለ ጎረምሳ መቸም ይወለድ መች? የትም ይወለድ ..... ደስ ብሎት እያነበበዉ ስለዘመናችሁ የሚጨብጠዉ ነገር አለ .... የዘመኑ አፍላዎች ደረቅ ታሪካዊ መጽሀፍትን የማንበብ ፍላጎታቸዉ አነስተኛ ስለሚመስለኝ ከነ ክፍሉ ታደሰ መጽሀፍ በተሻለ ካንተ መጽሀፍ የሚወስዱት ስዕል ይኖራል ብየ እገምታለሁ::

ዋርካ ላይም ከናንተ አይነት ሰዎች ጋር በመገናኘቴ ደስተኛ ነኝ ....
አይን ሁሉን ቢያይም አጠገቡ ያለዉን ቅንድብ አይቶ አያዉቅም ...
ሙዝ1
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 3128
Joined: Wed Feb 22, 2006 9:25 am

Postby password » Tue Oct 08, 2013 11:55 am

ሰላም ሙዝ ወንድሜ

ለደጋግ ቃላትህ ምስጋናዬ የላቀ ነው... የክፍሉን "ያ ትውልድ" አይንት መጽሃፍ ገለልተኛ ሆነህ መጻፍ ቃላል አይመስለኝም... በተለይ እንደ እሱ በፖለቲካው ብቻ ሳይሆን በሳንጃ ጭምር የተሞሻለቀ ሚዛናዊ እይታ ማቅረብ የሚቸገር ይመስለኛል.. ክፍሉ የውጣቱ ትግል ፍትሃዊ ነበር ብሎ ይደመድማል... እዚያ ላይ ብዙ ሰው ላይቃወመው ይችላል... ትግሉ ለዲሞክራሲና ለፍትህ ነበር ስለሚባል... ከእንደ እሱ ሶሸሊዝም ካወጀው ደርግ ጋር ያን ያህል የሞት ሽረት ትግል ማድረግ ያስፈልግ ነበርን ? የሚለውን ጥያቄ ግን በግልጽ አይመልስም... አድበስብሶ ነው የሚያልፈው....

ምርኮኛውንስ አነበብከው?

ሰላም ቆይልኝ

ፓስ....
password
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 323
Joined: Fri Apr 04, 2008 2:02 am
Location: Europe

Postby password » Mon Jun 30, 2014 1:01 pm

password wrote:እድገት በህብረት .... ዋው
ስንት ዘመን ሆነው... ሳስበው የተመሰቃቀለ ስሜት በውስጤ ይጋመዳል...
ወጣቶች በተስፋ የተሞላንበት ወቅት, ትንንሽ የታሪክ ልጉዋም በእጃችን ጨብጠን መጻኢውን እድላችንን ልንቀይስ በትኩስ ሀይል የተንቀለቀልንበት ጊዜ ነበር.. ከሁሉ ይበልጥ የነበረው የወንድማማችነት መንፈስ መቼም አይረሳም...

ሁሉም እንደተመኘነው ሳይሆን ቀረና, ያልታሰበ ከባድ ጨለማ ሰፈነ... በዚያ ጨለማ ውስጥ ግን ብርሀን ሆነው ያለፉ ወጣቶች ነበሩ.... ታዲያ ያኔ ዋለልኛችን እንደሚለን ህዋሃትን የሚቀላቀል ቀርቶ ስሙዋን ያሚያውቅ ወጣት- ትግራይ ውስጥ አላውቅም... መሀል አገር ውስጥ ግን በኩራዝ ተፈልጎ አንድ አይገኝም... ወጣቱን ያማለለ ወፍራም ድርጅት ቢኖር ... ኢህአፓ... ብቻ ነበር...

እድገት በህብረትን አንተርሶ የወቅቱን ሁኔታ በልቦለድ መልክ የሚተርክ መጽሃፍ ማያያዣውን ተከትልው በመሄድ ማግኘት ይችላሉ.... ስለኒያ ወጣቶች ትንሽ ያወጋል...http://babile.wordpress.comፓስ
password
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 323
Joined: Fri Apr 04, 2008 2:02 am
Location: Europe


Return to Warka Culture and Literature - ዋርካ ባህልና ሥነ ጽሑፍ

Who is online

Users browsing this forum: No registered users and 0 guests