መጽሀፍ ቅዱስን እንመርምረው !!

Issues and Articles of General Interests including topics related to religion

Postby መርፊው » Sun May 12, 2013 6:32 pm

- ስላሴ እና ፅንሰ ሀሳቡ
ሚስጥረ ስላሴ ምን ይሆን?
ከ ሀገር ውስጥ

መምህር ምህረት አብ ስላሴን አስመልክቶ በሚስጥራዊ ቡድኖች ላይ እንዲህ ሲል ስለስላሴ ነግሮናል "‹‹.. ዛፍ ከላይ ቅርንጫፍ፤ ከመሃል ግንድ፤ ከታች ስር.. ስላለው ሶሰት ዛፍ እንላለን?… አንልም.. አንድ ዛፍ.. አንዱ ዛፍ ግን ስንት ነገር አለው?..ሶሰት… እግዚአብሄር ስንት ነው?.. አንድ… አንዱ አምላክ ግን ስንት አካል አለው?.. ሶስት.. ታድያ ይሄ ምን ይከብዳል..››(4) በመሆኑም የምህረታቡ ትንታኔ መሰረት ስላሴ ማለት የእግዚአብሄር ሶስት አካላት ማለት ናቸው፡፡ እግዚአብሄርን የገነቡ ሶስት አካላት በሌላ ቋንቋ እግዚአብሄር ማለት አብ ሲደመር ወልድ ሲደመር መንፈስ ቅዱስ ………

ቀጣዩ መምህር ኪዳነ ማርያም ጌታሁን ናቸው ፡፡ምን ነበር ያልሉትአ ባቴ?
“ ስላሴ በስም በአካል በግብር(የኢኮኖሚው ግብር እንዳይመስልህ ተግባር ለማለት ተፈልጎ ነው) ሶስት ናቸው፡፡ስማቸውም አብ፣ወልድ መንፈስ ቅዱስ ይባላሉ ፡፡አብ አካል አለው ወልድ አካል አለው መንፈስ ቅዱስ አካል አለው፡፡በግብራቸው አብ ወላዲ ወልድ ተወላዲ መንፈስ ቅዱስ ሰራፂ ነው፡፡……….ስላሴ ሶስት አካል ሶስት ስም ሶስት ግብር ስላላቸው ሶስት አማልክት ናቸው ማለት አይደለም፡፡ሶስቱም በባህሪ፣በህልውና፣ይህን አለም በመፍጠር እና በመግዛት አንድ ናቸው፡፡……”(5)

አባ ሳሙኤልም በበኩሉ የአብ የወልድ እና የመንፈስ ቅዱስ ሶስትነት እና አንድነትን በተነተነበት ሂደቱ አብ ወልድ አይደለም ወልድ አብ አይደለም መንፈስ ቅዱስም አብም ወልድም እንዳልሆነ እና የሶስቱድም ርእግዛብሄርን እንደሚሰጥ በስእላዊ ስእላዊ በሆነ መልኩ ለመግለፅ በመፅሀፉ ሙከራ አድርጓል(6)

ይህን ሀሳብ በመደገፍ መምህር ታሪኩ አበራ እንዲህ ሲል አንድ በሉ ይለናል
“ እግዚአብሄር ማለት የአብ የወልድ የመንፈስ ቅዱስ የአንድነት መጠሪያ ስማቸው ነው፡፡አብ የምንለው የእግዛብሄር ልብ ወልድ የምንለው የእግዛብሄር ቃል መንፈስ ቅዱስ የምንለው ደግሞ እስትንፋስ ነው”(7)

መምህር ብርሃኑ ጎበና በበኩሉ፡-
“የእግዛብሄር አንድነት እና ሶስትነት የሚክዱ ጥቂቶች ሳይሆኑ ብዙዎች ናቸው፡፡እግዚአብሄር አንድ ሲሆን ሶስት ሶስት ሲሆን አንድነው” (8) አያይዞም “……ለሰው በነፍሱ ሶስትነት አለው፡፡ይሀውም ልብነት፣ቃልነት፣ህይወትነት ነው፡፡የሰው ነፍስ በልብነቷ የአብ ምሳሌ ናት፡፡በቃልነቷ የወልድ በህይወትነቷ የመንፈስ ቅዱስ …….”(9)
የመፅሀፍ ቅዱስ መዝገበ ቃላት በስላሴ ስር የሚከተለውን ፅፏል
“እውነተኛ እና ህያው የሆነ አንድ አምላክ አለ በሶስት አካላት ስለሚኖር ስላሴ የሚለው ቃል የአንዱን አምላክ የስም የአካል የግብር ሶስትነት ያመላክታል……..አዲስ ኪዳን ግን በእግዚአብሄር ዘንድ ሶስት አካላት እንዳሉ ስማቸውም አብ ወልድ መንፈስ ቅዱስ መሆኑን ይገልጣል”(10)

በመሆኑም እነዚህ የተደማመሩ የኦርቶዶክስ እምነት መምህራንን አንድ ሚያደርጋቸው ስላሴ ሚለው ቃል የ አንድ አምላክ ሶስት አካላት ናቸው የሚለው ፅንሰ ሀሳብ ነው፡፡ ግን ነውን? ተረጋጋ እንመጣበታለን፡፡

የስላሴ ትርጉም እና ይዘት እና አለማቀፍ ትርጓሜ
የስላሴ ፅንሰ ሐሳብ በተመለከተ ዊኪፒድያ እንዲህ ብሎናል

The Christian doctrine of the Trinity defines God as three divine persons or hypostases:[1] the Father, the Son (Jesus Christ), and the Holy Spirit; "one God in three persons". The three persons are distinct, yet are one "substance, essence or nature (11)

አንዳንድ ኦንላይን ዲክሽነሪዎችም እንዲህ ሲሉ ትንታኔን ሰጥተውታል
Trinity Theology In most Christian faiths, the union of three divine persons, the Father, Son, and Holy Spirit, in one God. Also called Trine.(12)

ካቶሊክ ኢንሳይክሎፒዲያ በበኩሉ
"The Trinity is the term employed to signify the central doctrine of the Christian religion — the truth that in the unity of the Godheadthere are Three Persons, the Father, the Son, and the Holy Spirit, these Three Persons being truly distinct one from another."(13)

Professor of Theology and Religious Studies John T. Ford የስላሴን ፅንሰ ሐሳብ በዚህ መልኩ ይተነትነዋል፡“Trinity. This word (from the Latin trinus, meaning “threefold”) refers to the central mystery of the Christian faith that God exists as a communion of three distinct and interrelated divine persons: Father, Son and Holy Spirit. The doctrine of the Trinity is a mystery that is inaccessible to human reason alone and is known through divine revelation only.”(14)

የሐገር ውስጥ ኦርቶዶክስ ሰባኪያን ስላሴን የእግዚአብሄርን የገነቡ 3 አካላት መሆኑን በምሳሌ አስደግፈው ነግረውናል ይህም ሲባል እግዚአብሄር ማለት አንድ ወጥ አካል ሲሆን ሶስት የተለያዩ ክፍሎች አሉት ማለታቸው ነው፡፡ ልክ አንድ ዛፍ ግንድ ፣ስር እና ቅጠል እናዳለው ሁሉ፡፡ የግንድ ,የስር እና የቅጠል ድምር ውጤት እንደሆነ ሁሉ… እግዚአብሄርም አንድ አካል ሲሆን ያስገኙት ክፍሎች አብ ወልድ መንፈስ ቅዱስ ናቸው ማለታቸው ነው፡፡ . የባህር ማዶ ምሁራን ግን በዚህ አይስማሙም ስላሴን ማለት የአንድ አካል 3 ክፍሎቸ ብለው ሳይሆን ሚተረጉሙት ሶስት የተለያዩ አካላት መሆናቸውን ነው ሲሉ ፅፈው ሲያበቁ ግና በስልጣን በሀይል በግዛት አንድ መሆናቸውን ጨምረው ፅፈዋል ፡፡ ወይም እነዚህ ሶስት የተለያዩ አካለት እያንዳንዳቸው አምላክ መመሆናቸውን ነግረውህ ሲያበቁ ግና ሶስት አምላክ ሳይሆኑ አንድ አምላክ መሆነቸውን ጨምረው ይነግሩሃል፡፡

ካቶሊክ ኢስሳይክሎፒዲያ በዚህ መልኩ የገለፀውን አንብብ" in the words of the Athanasian Creed: "the Father is God, the Son is God, and the Holy Spirit is God, and yet there are not three Gods but one God."(15)
ግራ ቢገባህም ሶብር አርግ!!!

ስላሴ እዚህ ላይ አያበቃም የቀሩ ሌሎች ፍልስፍና ዎች አቅፎ ይዟል፡፡ ከነዚህም ውስጥ አንዱ ዱዋሊሰዘም በሚባል የ እምባሻ ስም ይታወቃል፡፡ ይህ ፍልስፍና ከ አትናሲያን አቂዳ የሚለይ ሲሆን አንዱ ፈጣሪ በሶስት አካላት ተገለጠ የሚል ፍልስፍናን ይዞ ነው ብቅ ያለው ይህም ሲባል ልክ ውሀ ጠጣር ፣ፈሳሽ ፣ እና ጋዝ እንደሚሆነው ፈጣሪም እራሱን ሶስት ገልጾል የሚል እምነትን አንግበውተነስተዋል ማለት ነው ፡፡ ይህን ፅንሰ ሀሳብ አስመልክቶ Scott Dunham እንዲህ ቢል አይገርምም

“Modalism is a conception of the three persons of the Trinity not as distinctly subsisting persons, but as manifestations of the one God, whether the Father or a divine substance.” [16]

Xavier William እንዲህ ቢል አይገርምም
Sebellianism: Christian heresy that was a more developed and less naive form of Modalistic Monarchianism (see Monarchianism); it was propounded by Sebellius (c. 217-c.220), who was possible a presbyter in Rome…Sebellius evidently taught that the Godhead is a monad, expressing itself in three operations: as Father, in creation; as Son, in redemption; and as Holy Spirit, in sanctification.”(17)

እውቁ የመለኮት ጠበብት Samuel Hopkins እንዲህ ሲል ፅፏል
“…Sebellianism; which considers the Deity as but one person, and to be three only out of respect to the different manner or kind of his operations.”(18)

ሶስት አይነት ስላሴ
1. አዲሱ ስላሴ
2. ዱዋሊዝም ስላሴ
3. አትናስያን ስላሴ

Let us examine them ነው ሚባለው?
አዲሱ ስላሴ፡- ይህ የስላሴ አይነት የሀገር ውስጥ ሚሽነሪዎች የሚሰብኩት የ ስላሴ አይነት ነው፡፡ ይህም ሲባል ስላሴ ማለት 3 የተለያዩ እና ራሱን የቻለ አካል ያላቸው ሳይሆኑ ስላሴ ማለት የአንዱ እግዚአብሄር አንድ ወጥ አካል ሶስት ክፍሎች ናቸው የሚል ፍልስፍና ነው፡፡ በዚህ ስላሴ ፅንሰ ሀሳብ አራማጆች ከሚሰጡት ምሳሌ ውስጥ አንዱ በሚስጥራዊው ቡድን ቪድዮ ሲዲ ላይ ተጠቅሶ እናገኘዋለን ይህም
መምህር ምህረተአብ እንዳለው "‹‹.. ዛፍ ከላይ ቅርንጫፍ፤ ከመሃል ግንድ፤ ከታች ስር.. ስላለው ሶሰት ዛፍ እንላለን?… አንልም.. አንድ ዛፍ.. አንዱ ዛፍ ግን ስንት ነገር አለው?..ሶሰት… እግዚአብሄር ስንት ነው?.. አንድ… አንዱ አምላክ ግን ስንት አካል አለው?.. ሶስት.. ታድያ ይሄ ምን ይከብዳል..››(19)


ሹፍ!!! ምህረተ አብ የስላሴን ፅንሰ ሀሳብ ከዛፍ ጋር ተመሳሳይነት እንዳለው ነገረን፡፡ ነግሮንም ሲያበቃ እኛ እውነት ነው ስንል ሐሳቡን መረመርን ሁሉም እንደሚያውቀው አንድ ዛፍ አንድ ወጥ ሙሉ አካል አለው ይህ የዛፍ አካል የተለያዩ ክፍሎች አሉት ለምሳሌ ስሩ ብቻውን ዛፍ አይባልም፡፡ ግና የዛፉ አንድ ክፍል ነው ሚባለው ፡፡ ግንዱም ሆነ ቅጠሉም ዛፍ የሚባለው አንድ ወጥ አካል የተለያዩ ክፍሎች ናቸው፡፡ ለብቻቸው ዛፍ አይደሉም፡፡ ዛፍ የሚባሉት የሁሉም ክፍሎች ጥምረት የሚያስገኘው ድምር ውጤት ነው ይህን እወነታ ስር ቅጠሉ እንኳ ያውቀዋል፡፡ በምህረተ አብ ሎጂክ መሰረት አንዱ አምላክ ልክ እንደዛፍ ሁሉ ሶስት ክፍሎች አሉት፡፡ አንድም አብ የሚባለው ክፍል ነው ሁለትም ወልድ ሚባለው ክፍል ሶስትም መንፈስቅዱስ የሚባለው ክፍል በመሆኑም ይህ አንዱ አምላክ የሚገኘው ሶስቱ ክፍሎቹ ሲደመሩ ነው ማለት ነው፡፡ በተቃራኒው እነዚህ የአንዱ አምላክ ወጥ አካል ሶስቱ ክፍሎች ካልተደመሩ አምላክ ሊባሉ ወይም አንዱን አምላክ ሊሰጡ አይችሉም፡፡ በመሆኑም እንደምህረተአብ ሎጂክ አብ ብቻውን አምላክ አደለም ማለት ነው፡፡ ወልድም ሆነ መንፈስ ቅዱስ ብቻቸውን አምላክ አይደሉም ፡፡ ልክ ስር ብቻውን ዛፍ እንዳልሆነ ግንዱ ብቻውን ዛፍ እንዳልሆነ ቅርንጫፉም ብቻውን ዛፍ እንዳልሆነ ሁሉ!!! የመምህር ታሪኩ አበራን ምሳሌም መመልከት ይቻላል፡፡ መምህር ታሪኩ አበራ ምን ነበር ያልከው?
“እግዚአብሄር(አምላክ፣ቲኦስ) ማለት የአብ የወልድ የመንፈስ ቅዱስ የአንድነት መጠሪያ ስማቸው ነው፡፡አብ የምንለው የእግዛብሄር ልብ ወልድ የምንለው የእግዛብሄር ቃል መንፈስ ቅዱስ የምንለው ደግሞ እስትንፋስ ነው”(20)

መምህር ታሪኩ እንደነገረን እግዚአብሄር ወይም ደግሞ አምላክ በግሪኩ ደግሞ ቲኦስ ሚለው የተገነባው ከሶስት ክፍሎች እንደሆነ ነግሮናል አብ ማለት አምላክ ልብ ነው ወልድ የአንዱ አምላክ ቃል ነው መንፈስ ቅዱስ ደግሞ የአንዱ አምላክ እስትንፋስ ነው፡፡ በዚህም አምክንዮ መሰረት ቃሉ ብቻ አምላክ ሊባል አይችልም እስትንፋም እንዲሁ አምላክ ሊባል አይችልም ልቡም በተመሳሳ መልኩ አምላክ ሊባል አይችልም ፡፡ ምክንያቱም አንዱ የአምላክ አካል አገነባቡ ከነዚህ ሶስት ክፍሎች በመሆኑ፡፡ ለየብቻቸው አምላክ አይደሉም፡፡ ልክ ስር ለብቻው ዛፍ እንዳልሆነ ሁሉ………….

የመምህር ብርሀነ ጎበናም ምሳሌ ይህን ፅንሰ ሀሳብ ያረጋግጥልናል ፡፡ እንዲህ ሲል የፃፈውን ማንበብ ይቻላል “……ለሰው በነፍሱ ሶስትነት አለው፡፡ይሀውም ልብነት፣ቃልነት፣ህይወትነት ነው፡፡የሰው ነፍስ በልብነቷ የአብ ምሳሌ ናት፡፡በቃልነቷ የወልድ በህይወትነቷ የመንፈስ ቅዱስ …….”

በመምህር ብርሀነ ጎበና ምሳሌም ከሄድን ተመሳሳይ ድምዳሜ ላይ እንደርሳለን ሰው የሚባለው አንድ ወጥ አካል ብዙ ውስጣዊ ክፍሎች አጣምሮ ይዟል፡፡ ከነሱም ውስጥ መምህር ብርሀነ ጎበና እንደነገረን ልብ ፣ ቃል ፣ ህይወት ሰው የተባለው አንድ ወጥ ሙሉ አካልን ያስገኙት የነዚህ ድምር ውጤት ነው፡፡ ቃል ብቻውን ሰው አይደለም፡፡ ልብ ብቻውን ሰው አይደለም እንዲሁም ነፍስ ብቻውን ሰው አይደለም፡፡
ቀጣዩ ጥያቄ እየሱስ ብቻውን አምላክ ነው ብለን ክርስትያኑን ስንጠይቀው አዎ ነው፡፡ ሲል ያለ እፍረት ሲመልስ ታየዋለህ ይህ ደግሞ ከላይ በቀረበው ሎጂክ መሰረት አያስኬድም ምክንያቱም ስር ብቻውን ዛፍ ሊባል እንደማይችል እየሱስ ብቻውን አምላክ ሊባል አይችለም ፡፡ ኖ አምላክ ሊባል ይችላል ለማለት የግድ ከሁለቱ ጋር ውህደት መፍጠር አለበት …..
የዛሬው ክርስትና መርህ ግን አብ ብቻውን አምላክ ነው፣ ወልድ ብቻውን አምላክ ነው ፣ መንፈስ ቅዱስ ብቻውን አምላክ ነው የሚል ነው ይህም በምህረታቡ ምሳሌ ሲተረጎም ስር ብቻውን ዛፍ ነው፣ ግንድ ብቻውን ዛፍ ነው ፣ ወይም ቅጠል ብቻውን ዛፍ ነው እንደመለት ነው ………….. ይህ እንግዲህ አዲሱ የስላሴ ስልት መሆኑ ነው፡፡


የሆነ ሆኖ ይህ ፅንሰ ሀሳብ ከ መፅሀፍ ቅዱስ ጋር ይጋጫል ወይም ይቃረናል፡፡ ምክንያቱም መጽሀፍ ቅዱስ እንደሚነግርህ አብ እየሱስ እና መንፈስ ቅዱስ ልክ እንደዛፍ ስር እና ግንድ የተጣመሩ እና የተዋሀዱ አካላት ሳይሆኑ እራሳቸውን የቻሉ እና የተለያዩ መሆናቸውን ነው ሚነግርህ ማለትም አብ የአንዱ አምላክ ልብ እንደሆነ ሳይሆን ሚነግርህ አብ እራሱንየቻለ እንዲሁም ከወልድ የተለየ ሙሉ አካል እንደሆነ ነው ሚነግርህ፡፡ ወልድም የአንዱ እግዚአብሄር ክፍል እንደሆነ ሳይሆን መፅሀፍ ቅዱስ ሚነግርህ እየሱስ የእራን የቻለ አካል እንደሆነ ነው ሚነግርህ በዚህም ስሌት መፅሀፍ ቅዱስን እንመልከተው፡፡
በመፅሀፍ ቅዱስ አብ ብቻውን አምላክ ተብሏል የሚከተለውን ምሳሌ መመልከት ትችላለህ
- " እኔ ወደ አባቴ እና ወደ አባታቹህ ወደ አምላኬ እና ወደ አምላካቹህ ላርግ ነው ብለሽ ንገሪያቸው " (ዮሀ 20፡17)


ይህ ከላይ በአይንህ በብረቱ ያየሀው አንቀፅ በ እየሱስ አንደበት እንደተነገረ የዮሐንስ ወንጌል ፀሀፊ ነግሮናል፡፡ በዚህ ምሳሌ መሰረት በሰማይ የሚገኘው አብ አምላክ ነው ወይም እግዚአብሄር ነው ማለት ነው፡፡ በምህረታብ ሎጂክ እና በታሪኩ ሎጂክ ብንስማማ እንዲህ ወደ ሚል ማጠቃለያ መድረስ መፍፁም አይቻለንም፡፡ ምክንያቱም ምህረተአብ እና ታሪኩ እንደሚሉን አብ የአምላክ አንዱ ክፍል እንጂ አምላክ አደለም፡፡ ልክ ስር የዛፍ ክፍል እንደሆነ እና ለብቻው ተለይቶ ሲመጣ ዛፍ ሊባል እንደማይችለው….
ይህንም ፅንሰ ሀሳብ ከመሰረቱ ለማቆም የሚያስችሉ ብዙ የመፅሀፍ ቅዱስ አንቀፆችን ማቅረብ ይቻላል፡፡
- 1 ጴጥ 1፡3 “የጌታችን እየሱስ ክርስቶስ አባት እና አምላክ ይመስገን" ምን ማለት ነው? ፈለክም አልፈለክም የወልድ አባት እና አምላክ ይመስገን ማለት ነው……. በመሆኑም አብ ብቻውን አምላክ ተባለ እንጂ አምላክ እነ ታሪኩ እንደሚሉህ የሶስቱ ድምር አይደለም
- ኤፍሶን 1፡16 "የጌታችን እየሱስ ክርስቶስ አምላክ እና ክብር የሚገባው አምላክ(እግዚአብሄር)"
- ሮሜ 15፡5-6 "የእየሱስ ክርስቶስ አብት እና አምላክ ይመስገን"
- 2 ቆር 1፡3 "የእየሱስ ክርስቶስ አብት እና አምላክ ይመስገን"
ይህ ሁሉ የመፅሀፍ ቅዱስ አንቀፅ በጉልህ እንዳስቀመጠው አብ ብቻውን አምላክ ወይም እግዚአብሄር ይባላል ፡፡ እግዚአብሄር ወይም አምላክ የሶስቱ አንድ መጠሪያ ስም ነው የሚለው መጫወቻ ካርድ ሚሽነሪዎች ስለማያዋጣቸው ቢቀይሩትሩት መልካም ነው፡፡…………

ሌላው እየሱስ እና አብ ልክ እንደ በዛፉ ምሳሌ እንደተጠቀሰው የተጣበቁ ሳይሆኑ የተለያዩ ነበሩ ለዚህም ምክንያታዊነት በመረጃነት ሚቀርበው መለኮታዊ ስትለው የምታንቆለጳጵሰው መፅሀፍ ነው፡፡ እነሆ መፅሀፍህ እንደነገረን ከሆነ እየሱስ በምድር ላይ ሳለ አብ በሰማይ ነበረ ፡፡ የሚከተሉትን አናቅፅት መመልከት ትችላለህ፡፡
- ማት 5፡45 "በሰማይ ላለው አባታቹህ ዘንድ ልጆች ትባሉ ዘንድ ጠላቶቻችሁን ውደዱ"
- ማት 6፡14 "ሰዎችን ይቅር ብትሉ በሰማይ ያለው አባታቹህ ይቅር ይላቹሀል
- ማት 6፡18 " ስትፆም በሰማይ ላለው አባትህ"
- ማት 6፡32 "ምን እንደሚያስፈል በሰማይ ያለው አባትህ ያውቃል
- ማት 7፡21 በሰማይ ያለው አባቴን ፍቃድ የሚያደርግ እንጂ ጌታ ሆይ ጌታ ሆይ የሚለን መንግስተ ሰማያት አይገባም"

እንዲሁም እየሱስ ያሰስተማረውን ፀሎት መመልከት ይቻላል፡፡አብ በሰማይ እንዳለ ግልፅ የሆነ ይመስለኛል፡፡ በዚህ ስሌት ከተስማማህ ሚቀርብብህ ቀጣዩ ጥያቄ ወልድ የት ነው የነበረው የሚል ይሆናል? ለዚህም ጥያቄ ያለህ ብቸኛ ምላሽህ እየሱስ ይህን ሲያስተምር ምድር ላይ ነበር የሚል ብቻ ይሆናል፡፡ አብ በሰማይ ያለው አንድ አካል ከነበረ ወልድ በምድር ያለው ሌላ አካል ከነበረ የተለያዩ መሆናቸው ግልፅ ነው፡፡ እናም በዛፍ ወይም በ ሰው መመሰሉ መሰረቱ ምንድ ነው? በሰማይ ያለው አብ አንድ በምድር ያለው እየሱስ ሁለት ሆነው ሳሉ እንደ ዛፍ የተጣበቁ አካላትስ አድርጎ ማቅረቡ ምን የሚሉት ፍልስፍና ነው? መሰረቱስ የትኛው የመፅሀፍ ቅዱስ አንቀፅ ነው? ይህ አዲሱ የስላሴ ስልት ሚሽነሪው ተራውን ተከታይ ለማሳት እየተጠቀመበት ያለ ስልት መሆኑን ለማወቅ እንግዲህ ነብይ መሆን አያስፈልግም!!!!!

አብ ማለት እግዚአብሄር ማለት ነው እሱም ከወልድ የተለየ አካል ነው ለምሳሌ ይህን ተመልከት
- ዩሐ 14፡1 “በኔም እመኑ በእግዚአብሄርም (ቲኦስ) እመኑ"
- ሐዋ 10፡38 “እግዚአብሄር እየሱስን በሐይል እና በመንፈስ ቅዱስ ቀባው”
- ሐ.ስራ 2፡36 "እንግዲህ እግዚአብሄር እየሱስን ጌታም መሲህ እንዳደረገው እስራኤል ሁሉ ይወቅ"
- ሉቃስ 12፡8" እየሱስ እንዲህ አለ” ሳያፍር በሰው ፊት ለመሚመሰክርልኝ እኔም በእግዚአብሄር እና በመላእክት ፊት እመሰክርለታለሁኝ"
- 1ጢሞ 2፡5 “እግዚአብሄር አንድ ነው ፣ በመካከል ሆኖ እግዚአብሄር እና ሰውን የሚያስታርቀው አንድ እሱም ሰው የሆነው እየሱስ ክርስቶስ ነው"
- ሉቃ 18፡18 “እየሱስም እንዲህ አለ ለምን ቸር ትለኛለህ ከአንዱ እግዚአብሄር ውጪ ቸር የለም"
- 1 ሐ.ስራ 7፡56 "እስጢፋኖስ ወደ ሰማይ ትኩር ብሎ ሲመለከት የእግዚአብሄር ክብር አየ ፣ እየሱስንም በእግዚአብሄር ቀኝ ቆሞ አየሁ ስለዚህ እነሆ ሰማይ ተከፍቶ የሰው ልጅ በእግዚአብሄር በቀኝ ቆሞ አየሁት”
- ማር 16፡19 “ጌታ እየሱስ ይህን ካላቸው በኋላ ወደ ሰማይ ወጣ፡፡ በ እግዚአብሄርም በቀኝ በኩል ተቀመጠ"

ይህ ለምሳሌነት ብቻ የቀረበ የመፅሀፍ ቅዱስ ጥቅስ ሲሆን እየሱስ የእግዚአብሄር አንዱ ክፍል ነው ሲሉና አምላክ ሚባለው የሶስቱ አካላት ድምር ውጤት ነው ብለው እየተቀባበሉ የሚያስተጋቡትን ሁሉ ይቃወማል፡፡ ለምን? ለምን እንደሆነ በምሳሌ እንመልከተው….
ለምሳሌ ተመልከት 1ጢሞ 2፡5 " እግዚአብሄር አንድ ነው ፣ በመካከል ሆኖ እግዚአብሄር እና ሰውን የሚያስታርቀው አንድ እሱም ሰው የሆነው እየሱስ ክርስቶስ ነው" ይልሀል ይህ እንግዲህ ቅር አለህም ጎረበጠህም የነ ምህረታብን የስላሴ ፅንሰ ሐሳብ ይቃወማል፡፡ እነ ምህረትአብ---- እግዚአብሄር ማለት አብ ሲደመር እየሱስ(ወልድ) ሲደመር መንፈስ ቅዱስ ማለት ነው ሲሉ ቢነግሩንም መልኮታዊ ስትል ምታምንበት መፅሀፍ ግን እግዚአብሄር ማለት የ 3 ቱ ድምር ውጤት ሳይሆን አብ ብቻ እንደሆነ እና አንድ ብቻ እንደሆነ አልፎ ተርፎ ከእየሱስ ጋር እንዲሁም ከመንፈስ ቅዱስ የተለየ አካል እንደሆነ ጨምሮ ነግሮሐል፡፡ እየሱስ ባረገ ወቅት ከ አብ ውስጥ ገብቶ አንዱን እግዚአብሄር መሰረተ ወደሚል ምክንያታዊነት ሚያመራ ሎጂክ ቢያቀርቡም እንነምህረታብ መፅሀፍ ቅዱስህ ግን እየሱስ ባረገ ወቅት ከ እግዚአብሄር በቀኝ ቆመ ወይም ተቀመጠ ይልሀል መለኮታዊ ብለህ ምታንቆለጳጵሰው ፅህፍህ እየሱስ እና እግዚአብሄር ፍፁም የተለያዩ አካለት መሆናቸውን ታውቅ ዘንድ የግድ መንፈስ ቅዱስ እስጊገልፅልህ መጠበቅ የለብህም ምክንያቱም የ እየሱስ እና የ እግዚአብሄርን መለያየት ይገለፅልህ ዘንድ መፅሀፍህን ገልጠህ ማንበብ በቂና በቂ ነው፡፡

እየሱስ በምድር ሳለ እግዚአብሄር በሰማይ ነበር፡፡ የወንጌል ፀሀፊዎች እንደሚነግሩን ከሆነ እየሱስ እና እግዚአብሄር ሁለቱም ሰማይ ላይ ለመጀመሪያ ጊዜ ጎን ለጎን የተቀመጡት በእየሱስ እርገት ወቅት ነበር፡፡ እየሱስ ሲያርግ እና በእግዚአብሄር በቀኝ በኩል ሲሆን እግዚአብሄር ደግሞ በ እየሱስ በ ግራ በኩል ሆነ ...... አስተውለህ ከሆነ እየሱስ " እግዚአብሄር እና እራሱ" እንደሚለያዩ እዚ ምድር ላይ ሳለ ነግሮህ ነበር ፡፡ ተመልከት ሉቃስ 12፡8" እየሱስ እንዲህ አለ " ሳያፍር በሰው ፊት ለመሚመሰክርልኝ እኔም በእግዚአብሄር እና በመላእክት ፊት እመሰክርለታለሁኝ" እግዚአብሄር እና እሱ መለያየታቸውን በግልፅ ነገረህ ፡፡ ሲብስም ሉቃ 18፡18 " እየሱስም እንዲህ አለ ለምን ቸር ትለኛለህ ከአንዱ እግዚአብሄር ውጪ ቸር የለም" በነገራችን ላይ ሳልነግርህ ማላልፈው ነገር ቢኖር በብዙ የመፅሀፍ ቅዱስ አንቀፆች ውስጥ ያገርህ ሰው የቋንቋ ቁማር እየተጫወተ መሆኑን ነው…. እንዴት ከተባለ ግሪከኛውን ቃል ቲኦስ ሲያሰኘው እግዚአብሄር ሲያሰኘው አምላክ እያለ መተርጎሙ እራሱ ትልቅ ጥያቄ ያስነሳል ለምን አላማ ተፈልጎ ነውም ያስብላል፡፡

ሹፍ!! አንድ እግዚአብሄር አለ ይህም እግዚአብሄር ደግሞ ጳውሎስ እንደነገረህ እየሱስ አይደለም እየሱስ ስራው ሰውን ከ ዚህ እግዚአብሄር ጋር ማገናኘት ላይ የተወሰነ ነው፡፡ ማርቆስ ወንጌል ላይ እንደተነገረህ ይህ እግዚአብሄር ደግሞ በሰማይ ነበረ…. እየሱስ ዮሐንስ ወንጌል ላይ እንዲህ ብሏል

"ወደ አባቴ እና ወደ አባታቹህ ወደ አምላኬ(ወይም ወደእግዚአብሄሬና) እና ወደ አምላካችሁ(ወይም ወደ እግዚአብሄራቹህ) ላርግ ነው፡፡" በአንቀፁ ላይ የተጠቀሰው የግሪክ ቃል ቲኦስ የሚል ነው፡፡ ቀጥታ ትርጉሙ አምላክ ወይም እግዚአብሄር ፈጣሪ ማለት ነው ፡፡
የትኛውም ምሁር ከሊቅ እስከ ደቂቅ የሚስማማበት ነገር እዚጋር እንዳለ ላስታውስህ ፡፡ እሱም አምላክ ማለት የእግዚአብሄር ሌላ ስሙ ወይም ደግሞ እግዚአብሄር ማለት የ አምላክ ሌላ ስሙ መሆኑን ነው፡፡ ስለሆነም የፈለከው አንቀፅ ላይ ያለውን ቲኦስ የሚለውን የግሪክ ቃል አምላክ ወይም እግዚአብሄር ብለህ ብትተረጉመው ችግር የለውም፡፡ ምክንያቱም ተቀያያሪ ስሞች በመሆናቸው………!! አይደለም ሚል ተከራካሪ በምሁራን ዘንድ መሳቂያ እና መሳለቂያ ከመሆን የዘለለ ትርፍን አያተርፍም….

በዚህ ከተስማማን ወደ ዋናው ርእስ ስመልስህ በወንጌሎች ውስጥ እጅግ በሚበዙ ስፍራዎች ውስጥ እግዚአብሄር እና እየሱስ የተለያዩ ወጥ አካላት መሆናቸው ተቀምጧል፡፡
ካስታወስክ እየሱስ የዘላለም ህይወትን አስመልክቶ እንደህ ብሎ ተናግሯል “የዘላለም ህይወትም፣ ብቻህን እውነተኛ አምላክ(እግዚአብሄር) የሆንከው አንተ እና የላከውን እየሱስ ክርስትቶስ ማወቅ ነው"(ዮሐ 17፡3) ብቸኛው አምላክ እግዚአብሄር ወጥ አካል ሲሆን ከ እየሱስ የተለየ አካል ነው፡፡ እግዚአብሄር ማለት 3 ሲደመሩ ነው የሚለው የሐገርህ ሚሽነሪዎች ተራ ብሂል አንድ ደረጃ ወደ ላይ እንደሚያስኬድህ በውድ ካልሆነ ደግሞ በግድ ማወቅ ይኖርብሀል!!! አንድ አምላክ አለ በሰዎች እና በአምላክ መሃል አንድ አስታራቂ አለ ይህም አስታራቂ እንግዲህ እየሱስ ነው ሲል ጳውሎስ የተናገረውን ቃል በደንብ አስታውስ….. እንቀጥል……..

እንዳልኩህ እግዚአብሄር እና እየሱስ መለያየታቸውን አስረግጠው የሚያሳዩ የመፅሀፍ ቅዱስ አንቀፆች እጅግ ከመብዛታቸው የተነሳ አንባቢ ይቁጠራቸው በል እንጂ ቆትረህ አትዘልቃቸውም ፡፡ ወደ ጳውሎስ መልእክት ጎራ ብትል እንኳ ጳውሎስ እንዳለው አንድ እግዚአብሄር አለ አንድ ልጅም አለው ፡፡ እግዚአብሄር በሰማይ ---- ልጁ(ወልድ) በምድር------ ጭራሽ ፍፅም የተለያዩ አካላት እንደሆኑ ነው በግልፅ ያስቀመጠው ፡፡ ለማንኛውም አንቀፁ እንዲህ ይነበባል “እግዚአብሄር ለአንድ ልጁ(ወልድን) ሳይራራ ለኛ አሳልፎ ሰጠው"(ሮሜ 8፡32) ወይም በሰማይ ያለው እግዚአብሄር በምድር ያለውን እየሱስ አሳልፎ ሰጠው ብለህ መተርጎም ትችላለህ፡፡ በአንቀፁ መሰረት እነዚህ ሁለት ህልውናዎች የተለያዩ ሆነው ሳለ የነ ምህረታብ በዛፍ የመመሰሉ ሎጂክ ምንጩ መልስ ያጣ አእምሮ እንጂ መፅሀፍ ቅዱስ እንዳልሆነ ደግሜ ደጋግሜ በእርግጠኝነት እነግርሀለው ….. በመሆኑም እግዛብሄር አንድ ራሱን የቻለ አካል እየሱስ እራሱን የቻለ ሌላ አካል ……... ሁለት ናቸው አንዱ በምድር ሌላው በሰማይ ይህ እኮ መፅሀፍ ቅዱስን ያነበበ ተራ ኢለመንገተሪ ተማሪ የሚያውቀው ሀቅ ነው፡፡ እንዴት መንፈስ ቅዱስ ይህን እንዳለገለፀላቸው ለኔ ራሱ ግርምት ሆኖብኛል!!!

ምሳሌ መጨመር ካስፈለገ መፅሀፍህ ውስጥ በሚከተለው መልኩ የተቀመጠውን አንብብ
"እግዚአብሄርን እየሱስን በሐይል እና በመንፈስ ቅዱስ ቀባው"(ሐ.ስራ 10፡38) እግዚአብሄር የአብ የወልድ የመንፈስ ቅዱስ ድምር መጠሪያ ስም ቢሆን ኖሮ አንቀፁ "አብ እየሱስን በሐይል እና በመንፈስ ቅዱስ ቀባው " የሚል ይሆን ነበር፡፡ ነበር ባይሰበር ልበልህና አልሆነም ፡፡ 1ዱ አምላክ ጳውሎስ እንዳለህ አንዱ እግዚአብሄር ነው እየሱስን በሐይል እና በመንፈስ ቅዱስ የቀባው …..

ፅንሰ ሐሳቡን ሳጠቃልለው ስላሴን በዛፍ የመመሰሉ ሎጂክ አእምሮ ስራ ሲፈታ የፈበረከው እንጂ ሰነዳዊ ማስረጃ ያለው ፅንሰ ሐሳብ አይደለም ፡፡ አብ ወልድን እንዲሁም መንፈስ ቅዱስን በ አንድ ወጥ አካል እና በተለያዩ ክፍሎች መመሰሉ ከራሱ ከመፅሀፍ ቅዱስ አንፃር በጭራሽ አያስኬድም ፡፡ ከላይ እንዳየነው አብ እየሱስ እና መንፈስ ቅዱስ የተለያዩ(ያልተጣበቁ) እና እራሳቸውን የቻሉ አካላት መሆናቸውን ነው፡፡ እነዚህ አካላትን አምላክ ናቸው ማለት ሶስት አምላክ አለን ብሎ ከመናገር የዘለለ ትርጉም የለውም፡፡ የሆነ ሆኖ ያገር ውስጥ ሚሽነሪዎች አዲስ ፅንሰ ሐሳብ ፈጥረው የስላሴን ፅንሰ ሐሳብ ወደ አንድ አምላክ ፅንሰ ሐሳብ ለመቀየር ያደረጉት ሙከራን ሳላደንቅ አላልፍም ፡፡ ዘለሉም ፈረጡም ግን ይህ ፅንሰ ሐሳባቸው አዲስ ከመሆኖም ባሻገር ከለው መሰረታዊ ፅሁፍ ወይም መለኮታዊ ነው ሲሉ ከሚያምኑበት ሰነድ አንፃር ተቀባይነት እንደማይኖረው ወይም ውዳቂ አሳብ ከመሆን ባሻገር ሌላ ቦታ አይኖረውም፡፡ ይህ እንግዲህ አንዱ እና የመጀመሪያው የስላሴ ፅንሰ ሐሳበብ ሲሆን ወደ ሁለተኛው እናምራ ነው ሚባለው?

አትናሲያን ስላሴ፡- ይህ የስላሴ ፅንሰ ሐሳብ አብ ወልድ እና መንፈስ ቅዱስ ፍፁም የተለያዩ እና እራሳቸውን የቻሉ አካላት እንደሆነ ያምናል ማለትም አብ ወልድ እንዲሁም መንፈስ ቅዱስ አደለም ወልድም እንዲሁ አብ አደለም መንፈስ ቅዱስ አደለም፡፡ በአካል ይለያያሉ ወልድ ምድር ላይ ሳለ አብ ሰማይ ነበር … ይህ የስላሴ እምነት ምስሉ ከላይ የተመለከትከውን ይመስላል፡፡ ካቶሊክ ኢንሳይክሎፒድያ የአትናሲያንን አቂዳ እንደወረደ በዚህ መልኩ ቢገልፀው አይገርምም፡፡
" in the words of the Athanasian Creed: "the Father is God, the Son is God, and the Holy Spirit is God, and yet there are not three Gods but one God."(21)
ይህ ፅንሰ ሐሳብ እነምህረት አብ ከሚሉህ ስላሴ በእጅጉ ይለያል:: የነ ምህረተአብ እግዚአብሄር አብ ወልድ እና መንፈስ ቅዱስ ተዋቅረው ልክ እንደ ዛፍ ተጣብቀው ያመጡት ውጤት ነው፡፡ ይህ ፎቶ ግን ሚነግርህ አብ እራሱን የቻለ አካል እና ከ ወልድ የተለየ መሆኑን እንዲሁም ወልድ ከ አብም ከ መንፈስ ቅዱስ የተለዩ መሆናቸውን ነው፡፡ ስለ ሆነም እንደ አትናሲያን አቂዳ መሰረት እነዚህ በምስሉ ላይ ምትመለከታቸው ሶስት ሳይሆኑ አንድ አማላክ ናቸው ……… ይህ ነው እንግዲህ አንድ ሲደመር አንድ ሲደመር አንድ እኩል ይሆናል አንድ ማለት …………………. ሶስት መሆናቸውን ለማወቅ መቁጠር ብቻ ይጠበቅብሐል፡፡
ዱዋሊዝም እና ስላሴ ፡- ይህን የስላሴ ፅንሰ ሐሳብ ውግዘት የደረሰበት የስላሴ አይዲዮሎጂ መሆኑ ነው፡፡ የዚህ ፅንሰ ሀሳብ አራማጆች እንደሚያምኑት ስላሴ ማለት በሶስት መልኩ ራሱን የገለጠ አምላክ ነው ሲሉ ያምናሉ ፡፡ አምነውም ሲያበቁ ምሳሌ ለመስጠት ሲሞክሩ ይስተዋላል ፡፡ ይህ ከሚያቀርቡት ምሳሌ አንዱ ምን መሰለህ ውሀ በሶስት ሁኔታ ይገለፅ የለ ይሉሃል አንተም መልሰህ አዎ ስትላቸው አንዱ ፈጣሪ በሶስት መልኩ ቢገለፅ ምና ለበት ይሉሀል፡፡ ይህ ፅንሰ ሐሳብ በ መፅሀፍ ቅዱስ ስሌት ሲለካ ተራ አሉባልታ እንደሆነ ለማወቅ ይቻላል፡፡ ለዚህም ነው ብዙሀን የክርስትና አንጃዎች ይህን ፅንሰ ሐሳብ መርምረውት ሲያበቁ አንድ ደረጃ እንደማያስኬዳቸው ሲገባቸው ወድያውኑ ውድቅ ያደረጉት ወደ ላይም ከፍ ሲሉ ይህን ፅንሰ ሃሳብ የተቀበለን ሁሉ በክህደት የፈረጁት፡፡ ይህ ፅንሰ ሀሳብ ውድቅ ለማድረግ የመፅሀፍ ቅዱስ ሊቅ መሆን አያስፈልግም አንዱን ወንጌል ብቻ ካነበብከው ይህ ፅንሰ ሐሳብ እንደማያስኬድ ትረዳለህ………………….


ማጠቃለያ ፡- በዚህ ፅሁፍ ላይ ለማስገንዘብ የፈለኩት ዋና ነጥብ ስላሴ ፅንሰ ሐሳብ በእጅጉ ራስ ምታት በመሆኑ ሰበብ የተለያየ እና የተቃረነ ፅንሰ ሐሳብ ይነሳበት ዘንድ ምክንያት ሆኗል የመጀመሪያው አዲሱ ስላሴ ስልት ብዬ የሰየምኩት ሶስቱን አካላት ተጣብቀው ልክ እንደ ዛፍ አንድ አካል ሆኑ ሲሉ ማስተማር እንዲሁም ያለ እፍረት መፃፍ ለጀመሩት ያገራችን ሚሽነሪዎች ሲሆን ሐሳቡም ወዴት እንደሚጠያመራ እና ማጠቃለያው እንደማያምር ለማሳየት እና ለማስገንዘብ ነው፡፡ ሁለተኛው የስላሴ ፅንሰ ሐሳብ በ ሀገራችን ኦርቶዶክስ እምነት ተከታዮች ዘንድ ተቀባይነት ያለው ሲሆን አብ ወልድ መንፈስ ቅዱስ እንደ ዛፍ የተጣበቁ አንድ ወጥ አካል ሳይሆን ሶስት የተለያዩ አካላት መሆናቸውን የሚያትተው የስላሴ አካል ነው እንዴት እንደተለያዩ ማወቅ በኦርቶዶክስ ተዋህዶ ለህትመት የበቃውን ፎቶ መመልከት በቂ ነው ፡፡ እንደዛፍ አንድ ወጥ አካል አለመሆናቸውንም ስእሉ ራሱ በቂ ምላሽ ነው፡፡ ሶስተኛው የስላሴ ፅንሰ ሐሳብ ግና ሞዳሊዝም በሚል ስያሜ የሚታወቀው ሲሆን በመሰረቱ ውግዝ የተደረገ ፅንሰ ሐሳብ ነው ፡፡ የሆነ ሆኖ ይህ የስላሴ ፅንሰ ሐሳብ ለአእምሮ የጎረበጠ መሆኑን ምሁራን በ አንድ ድምፅ ይስማሙበታል፡፡

Rev. J.F. de Groot ምን ነበር ያልከው?
“It remains impossible for human intellect how three people has one divine nature.”(22) “ለሰው ልጅ ጭንቅላት (ያለተመለሰ ነገር ቢኖር) እንዴት ሶስት አካላት በመለኮት አንድ ይሆናሉ (ሚለው ጥያቄ ነው)” The new catholic encyclopedia በበኩሉ “One should not speak of tritarianism in New Testament without series qualification …”(23) በኔው አማርኛ “ እንድ (ሰው) በአዲስ ኪዳን ስላሴን አስመልክቶ ሊናገር አይችልም (ብዙ) ማስተካከያዎችን (ካላስከተለበቀር)”አንድ እርምጃ በመራመድ C.F Bergson የሚተለውንብሏል ““To attribute son to God is to deny the perfection of God”(24) “ ለፈጣሪ ልጅ ማረግ የፈጣሪን ሙሉእነት ማጓደልነው”ሙስሊም ምሁራንም በበኩላቸው ይህን ፅንሰ ሀሳብ ተቀባይነት የሌለው ሀሳብ ሲሉ አጣጥለውታል(25) ፡፡ The new catholic encyclopedia ምአክሎ ይህ ፅንሰ ሀሳብበ 4ተኛው ክፍለ ዘመን የተጀመረ መሆኑን አስረግጦ ከትቦልናል(26)

በሙስሊሙ ታሪክ ይህን ፅንሰ ሀሳብ በመቃወም ሼይኸል ኢስላም ኢብኑተይሚያህ (27) በመፅሀፋቸው እራሱን የቻለ መልስ ሲፅፉ ተማሪው አልሀፊዝ ኢስማኢል ኢብኑከሲር (28) በበኩላቸው የእየሱስን ኢስላማዊ ገፅታ አጥርቶ ሚያሳይ ዳጎስ ያለ ኪታብ አዘጋጀተውልናል፡፡ ምዕራፍ ሁለት በቅርቡ ይጠብቁን ………

Reference
4. ሚስጥራዊ ቡድን ቪድዮ፣ መምህር ምህረተአብ
5. ኪዳነማርያምጌታሁን፣ክርስቶስ ከቁርአን ጋር ምን አገናኘው፣1999፣2ተኛእትም ገፅ 78-79
6. አባሳሙኤል፣የሀይማኖት መቻቻል በኢትዮጵያ አለን ፣ቁጥር 1፣2000፣ገፅ 136
7. .መምህር ታሪኩ አበራ፣እየሱስ ማነው?፣3ተኛእትም፣2003፣ገፅ 5
8. መምህር ብርሀኑ ጎበና፣አምደ ሀይማኖት 11ደኛእትም፣2000 ገፅ 39
9. መምህር ብርሀኑ ጎበና፣አምደሀይማኖት 11ደኛእትም፣2000 ገፅ 42
10. የመፅሀፍ ቅዱስ መዝገበቃላት፣8ተኛእትም፣1998 ገፅ64
11. http://en.wikipedia.org/wiki/trinity
12. http://www.thefreedictionary.com/
13. http://www.newadvent.org/cathen/15047a.htm
14. Ford, J. T. (2006). Glossary of Theological Terms. Winnona, Minnesota: Saint Mary’s Press. p. 188
15. http://www.newadvent.org/cathen/15047a.htm
16. Dunham, Scott A. (2008). The Trinity and Creation in Augustine: An Ecological Analysis. Albany, New York: State University of New York Press. p. 41
17. William, X. (2006). Economics, Ethics, Religions & Superstitions. Lincoln, Nebraska: iUniverse. p. 234
18. Hopkins, S. (n.d.). The System of Doctrines Contained in Divine Revelation, Explained and Defended. Showing their Consistence and Connection with each other, Vol. 1. Boston: Isaiah Thomas and Ebenezer T. Andrews. p. 444
19. ሚስጥራዊ ቡድን ቪድዮ፣ መምህር ምህረተአብ
20. መምህር ታሪኩ አበራ፣እየሱስ ማነው?፣3ተኛእትም፣2003፣ገፅ 5
21. http://www.newadvent.org/cathen/15047a.htm
22. Rev. J.F. de Groot , Catholic teaching pp. 101
23. The new catholic encyclopedia ,1967 vol. 14 pp.295
24. C.F Bergson , the creative evolution pp. 16
25. Christianity original and the present , Muhammed Ibn Abdelah as Salim pp. 15
26. The new catholic encyclopedia ,1967 vol. 14 pp.299
27. Al Jewab As Saih Limen Bedele Dinul Mesih
28. Al hafith ibn katheer, the Islamic view of Jesus.
29. የተጠቀምኩት መፅሀፍ ቅዱስ KJV bible ሲሆንየ1816ቱእትም
መርፊው
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 260
Joined: Sat Oct 15, 2011 4:22 pm

Postby መርፊው » Tue Jun 04, 2013 4:20 pm

ተላኪውን (እየሱስ) እና ዕውነታው በራሱ አንደበት ባይብል
From :-Bahise Haqe
~~~~~~~~~~~~
1. ትምህርቱ ከራሱ እይደለም
‹ለዚህ ኢየሱስ መለሰ እንዲህም አላቸው፦ ትምህርቴስ ከላከኝ ነው እንጂ ከእኔ አይደለም፤› ዩሐ 7፡16 ላኪና ተላኪ?

2. ማንነቱ እራሱ ሲገልጽ ((ነቢይ))

‹ዳሩ ግን ነቢይ ከኢየሩሳሌም ውጭ ይጠፋ ዘንድ አይገባውምና ዛሬና ነገ ከነገ በስቲያም ልሄድ ያስፈልገኛል።› ሉቃስ 13፡33

‹ኢየሱስ ግን፦ ነቢይ ከገዛ አገሩና ከገዛ ቤቱ በቀር ሳይከበር አይቀርም አላቸው። ›ማቴ 13፡57

3. አምላክ አላው (ወደ አምላኬና ወደ አምላካችሁ)

‹ኢየሱስም፦ ገና ወደ አባቴ አላረግሁምና አትንኪኝ፤ ነገር ግን ወደ ወንድሞቼ ሄደሽ። እኔ ወደ አባቴና ወደ አባታችሁ ወደ አምላኬና ወደ አምላካችሁ ዓርጋለሁ ብለሽ ንገሪአቸው አላት።›› ዩሐ 20፡17

‹‹እውነተኛ አምላክ ብቻ የሆንህ አንተን የላክኸውንም ኢየሱስ ክርስቶስን ያውቁ ዘንድ ይህች የዘላለም ሕይወት ናት። የዮሐንስ ወንጌል 17፡3

4. ለዚህ አምላክ ይጸልይ ነበር

‹‹ጥቂትም ወደ ፊት እልፍ ብሎ በፊቱ ወደቀና ሲጸልይ።..› ማቴ 26፡39

5. የተላከው

‹‹እርሱም መልሶ፦ ከእስራኤል ቤት ለጠፉት በጎች በቀር አልተላክሁም አለ። ማቴ 15፡24

6. ሰው ነው

‹የእስራኤል ሰዎች ሆይ፥ ይህን ቃል ስሙ፤ ራሳችሁ እንደምታውቁ፥ የናዝሬቱ ኢየሱስ እግዚአብሔር በመካከላችሁ በእርሱ በኩል ባደረገው ተአምራትና በድንቆች በምልክቶችም ከእግዚአብሔር ዘንድ ለእናንተ የተገለጠ ሰው ነበረ፤› የሐዋሪያስራ 2፡22

7. ከራሱ ምንም ማድረግ አይችልም

‹እኔ ከራሴ አንዳች ላደርግ አይቻለኝም፤ እንደ ሰማሁ እፈርዳለሁ ፍርዴም ቅን ነው፥ የላከኝን ፈቃድ እንጂ ፈቃዴን አልሻምና።› ዩሐንስ ወንጌል 5፡30

‹ኢየሱስም እንዲህ አላቸው፦ የእኔስ መብል የላከኝን ፈቃድ አደርግ ዘንድ ሥራውንም እፈጽም ዘንድ ነው።›ዩሐ 4፡34

ታዲያ ለምን ይሆን የተላከ መልክተኛ(ረሱል) ነው ማለታችን መወገዙ ?

8. የመጀመሪያ ያስተማረው ትዕዛዝ
‹ኢየሱስም መልሶ እንዲህ አለው፦ ከትእዛዛቱ ሁሉ ፊተኛይቱ። እስራኤል ሆይ፥ ስማ፤ ጌታ አምላካችን አንድ ጌታ ነው፥ ማር 12፡29

-->አዎ የሱ የኛም የጋራ አምላክ ‹‹አምላካችን›› ማለቱ ለዚያ ነው

9. ዕውቀቱ ከአምላክ ጋር ይነጻጻር ይሆን ?
‹ስለዚያች ቀን ወይም ስለዚያች ሰዓት ግን የሰማይ መላእክትም ቢሆኑ ልጅም ቢሆን ከአባት በቀር የሚያውቅ የለም። › ማር 13፡32

10. ለማን መሰገድ አንዳለበት ሲያስተምር
‹ኢየሱስም መልሶ፦ ለጌታ ለአምላክህ ስገድ እርሱንም ብቻ አምልክ ተብሎ ተጽፎአል አለው። ›ሉቃስ 4፡8

11. እየሱስ እራሱን
* ዩሐ 7፡16፤ ዩሐ 16፡5፤ሉቃስ 10፡16፤ዩሐ 7፡29 .. .. ..ከ10 ያላነሱ ቦታዎች እንደ ሌሎች መልክተኛ(ረሱል) መሆኑን ይገልጻል፡፡

12. ወደፊትም ይችላል የሚል ካለ ወደፊት ያውቃል

‹..እኔ እሆን ዘንድ አባቴም እንዳስተማረኝ እነዚህን እናገር ዘንድ እንጂ ከራሴ አንዳች እንዳላደርግ በዚያን ጊዜ ታውቃላችሁ። ›ዩሐ8፡28

13. ጌታ ነው የሚለው ሁሉ ((የሚለኝ ሁሉ))

‹‹ጌታ ሆይ፥ ጌታ ሆይ፥ የሚለኝ ሁሉ መንግሥተ ሰማያት የሚገባ አይደለም።›› ማቴ 7፡21 ጀምሮ ተመልከቱ በጣም የሚገርማችሁ ይህን የተባሉት በስሙ ትንቢት የሚናገሩ፤አጋንንት የሚያወጡ … ወዘተ አሁን አንደምናየው እልል የሚባልላቸው እንጂ ተራ አማኞች አለመሆኑ ነው ልክ ነኝ ?

14. በተጨማሪም ከንቱነታቸው ሲገለጽ

*ይህ ሕዝብ በከንፈሩ ያከብረኛል፥ ልቡ ግን ከእኔ በጣም የራቀ ነው፤ የሰውም ሥርዓት የሆነ ትምህርት እያስተማሩ በከንቱ ያመልኩኛል ብሎ በእውነት ትንቢት ተናገረ።ማቴዎስ 15፡8-9

15. ቸር ሲባል፡-ቸር ማን መባል አንዳለበት ሲያስተምር

‹‹ኢየሱስም፦ ስለ ምን ቸር ትለኛለህ? ከአንዱ ከእግዚአብሔር በቀር ቸር ማንም የለም።›› ማቴ 10፡18 ሉቃስ 18፡19
16 . ወዘተ

…. ይቀጥላል

ሰላም ቅኑን መንገድ በተከተለ ላይ ይሁን አሚን፡
መርፊው
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 260
Joined: Sat Oct 15, 2011 4:22 pm

Postby መርፊው » Mon Aug 12, 2013 5:10 pm

ኢየሱስ ከሰራቸው ሀጥያቶች ውስጥ ነጥረው የወጡትን እንመለከታለን (ለዚህ ፅሁፍ ሁለቱን ብቻ ለማየት እንገደዳለን )!

1. ስድብ
<<ስድብ ? ይህ ነው ታድያ ትልቁ ወንጀል ?›› የሚል ጥያቄ መነሳቱ አይቀርም፤ አግባብም ነው፡፡ አዎን ! በመጽሃፍ ቅዱስ መሰረት ስድብ እጅግ በጣም ከባድ ከሚባሉት ወንጀሎች ውስጥ ይካተታል !
‹‹ ለቀደሙት አትግደል እንደተባለ ሰምታችኋል፤ የገደለም ሁሉ ፍርድ ይገባዋል፡፡ እኔ ግን እላችኋለሁ፤ በወንድሙ ላይ የሚቆጣ ሁሉ ፍርድ ይገባዋል፤ ወንድሙንም ጨርቅ ለባሽ የሚለው ሁሉ የሸንጎ ፍርድ ይገባዋል፤ ደንቆሮ የሚለውም ሁሉ የገሃነም እሳት ፍርድ ይገባዋል…›› (ማቴ 5፤ 21-23)

ሆኖም ኢየሱስ በማቴዎስ ወንጌል ብቻ በደርዘን ለሚቆጠሩ ግዜያት ይህንን ህግ በጠራራ ፀሀይ መተላለፉ ተዘግቧል፡፡ ለአብነት ያክል የተወሰኑት እንመልከት፡፡

ሀ . ትውልዱን በሙሉ (እሱና ብጽእቱን እናቱን ጨምሮ ) በመዝለፍ
‹‹ ክፉና አመንዝራ ትውልድ ..›› (ማቴ 12፤ 38… )
‹‹ እናንተ የማታምን ጠማማ ትውልድ ..›› (ሉቃ 9፤ 41)
ለ . ጻፎችንና ፈሪሳውያንን በመነጠል
‹‹እናንተ ግብዞች ..›› (ማቴ 23፤ 13 23፤ 16 23፤ 23 23፤ 25 23፤ 27 23፤ 29...)
‹‹እናንተ ደንቆሮዎችና ዕውሮች…›› (ማቴ 23፤ 17 23፤ 19)
‹‹ እናንተ እባቦች፤ የእፉኝ ልጆች ..›› (ማቴ 23፤ 33)
ሐ . ግለሰቦችን በመነጠል
‹‹ አንተ እውር ፈሪሳዊ .. ›› (ማቴ 23፤ 26)
‹‹ ጴጥሮስን፡ - ወደ ኋላዬ ሂድ አንተ ሰይጣን፤ የሰውን እንጂ የእግዚአብሄርን አታስብምና እንቅፋት ሆነህብኛል ..›› (ማቴ 16፤ 23)

ከላይ በሰፈሩት ጥቅሶች መሰረት፤ ኢየሱስ ከባድ ወንጀል መፈፀሙን እንረዳለን፤ ያውም ገሀነም ሊያስገባ የሚያስችል፡፡ ታድያ ይህ ድግስ ተደግሶ፤ እንዴት ኢየሱስን ከሃጥያት ነፃ ነው ልንል እንችላለን ? መልሱን ለአንባቢያን እተዋለሁ፡፡ ነገር ግን ክርስትያን ወንድሞች ይህንን እንቆቅልሽ (puzzle) ለመፍታት የተለያዩ ማምለጫዎችን ለማቅረብ ሞክረዋል፤ እስኪ አንድ በአንድ እንመልከታቸው፡፡

A. ስድብ የተከለከለው ‹‹ለሃይማኖት ወንድም›› እንጂ ለሌላውማ ምን ችግር አለው፡

የማቴዎስ ወንጌል ላይ ‹‹ ለቀደሙት አትግደል እንደተባለ ሰምታችኋል፤ የገደለም ሁሉ ፍርድ ይገባዋል፡፡ እኔ ግን እላችኋለሁ፤ በወንድሙ ላይ የሚቆጣ ሁሉ ፍርድ ይገባዋል፤ ወንድሙንም ጨርቅ ለባሽ የሚለው ሁሉ የሸንጎ ፍርድ ይገባዋል፤ ደንቆሮ የሚለውም ሁሉ የገሃነም እሳት ፍርድ ይገባዋል…›› የሚለውን ጥቅስ እናያለን፡፡ ኢየሱስ በዚህ ጥቅስ መሰረት መግደልንም፤ መሳደብንም በማያሻማ ቋንቋ ከልክሏል፡፡ የሃይማኖት ወንድምን ብቻ ነው የከለከለው የምንል ከሆነ፤ ሌሎች ፈርጀ ብዙ ህግጋት መናዱ አይቀሬ ነው የሚሆነው፡፡ ‹‹በመጀመርያ ደረጃ አትግደል የተባለው ማንን ነው ?›› ለሚለው ጥያቄ መልስ ሊበጅለት የግድ ነው፡፡ ‹‹ለቀደሙት አትግደል›› የተባለው የኦሪት ህግ ማንን ነው የሚመለከተው ? ለአማኞት ብቻ ነው ብለን መልስ በመስጠት ለጊዜው ለማምለጥ እንችል ይሆናል፤ ነገር ግን ሌላ መዘዝ ይዞብን ከተፍ ይላል፡፡ ይህ ህግ በአዲስ ኪዳን መቀጠሉን ከላይ በጠቀስነው አንቀፅ ላይ ተመልክተናል፡፡ በመሆኑም እንደ ክርስትና እምነት መሰረት ‹‹አትግደል›› የሚለው ህግ ለአማኞች ብቻ የተገደበ ነው እንድንል ያስገድደናል፡፡ ከዚህም አልፎ ተርፎ በየመንገዱ የምታገኘውን የሌላ እምነት ተከታይ መስደብም ይፈቀዳል እንደማለት ነው፡፡

ስለዚህ ለክርስትያን ወንድሞቻችን ሁለት ምርጫ ቀርቧል ማለት ነው፡፡ አንደኛው፤ አማኝ ያልሆነን መግደልም ሆነ መስደብ ይቻላል፤ በመሆኑም ኢየሱስ በመሳደቡ ወንጀል አልሰራም፡፡ ሁለተኛው ደግሞ የሌላ እምነት ተከታይን መግደልም ሆነ መስደብ አይፈቀድም፤ ነገር ግን ኢየሱስ ይህንን ህግ ጥሷል፡፡ ምርጫውን እንተውላቸዋለን፡፡ ደግሞም ለሃይማኖት ወንድም ነው ለማለት በቂ መረጃ ማቅረብ ግዴታ ነው፡፡ ሌላውም ወሳኝ ነጥብ ኢየሱስ ሁሉንም ሰው መስደቡን ማሰተዋል ልብ ይሏል፤ትውልዱን በሙሉ፣ አማኙንም ኢ -አማኙንም፡፡ (ማቴ 12፤ 38… ) (ማቴ 16፤ 23)

B. ኢየሱስ እየተሳደበ ሳይሆን፤ እነርሱ የሆኑትን ነው እየነገራቸው ያለው፡፡ ያልሆኑትን ነገር ፈጥሮ አልተናገረም፡፡

ይሄ ብዙ የማያራምድ ምላሽ ነው፡፡በዋናነት መመለስ ያለብን ጥያቄ ‹‹ስድብ ምን ማለት ነው›› የሚለውን ይሆናል፡፡ ለምሳሌ ያክል አንድ መላጣን ‹‹አንተ መላጣ (ቢሊጮ )›› ብንለው ስድብ አይደለምን ? ብዙ የማይገባውንም ሰው ‹‹አንተ ደንቆሮ›› ብንለውስ ? ይህ ስድብ ካልሆነ የስድብ ትርጉም ተለወጠ ቢሉን ይቀላቸዋል፡፡ ሌላው ደግሞ ‹‹እናንተ ግብዞች፤ እባቦች›› እያለ ኢየሱስ ሲዘልፋቸው፤ መቼም እንስሳውን እባብ እንዳልሆነ ማስተዋል ይቻላል፡፡ ባህሪያችሁ ከእባብ ይመሳሰላል፤ መርዘኞች ናችሁ እንደማለቱ ነው፡፡ ታድያ ይሄን ስድብ እንበለው ምክር ?

ሌላው ነጥብ ኢየሱስ ጴጥሮስን የተናገረው ንግግር ነው፡፡‹‹ ..ወደ ኋላዬ ሂድ አንተ ሰይጣን፤ የሰውን እንጂ የእግዚአብሄርን አታስብምና እንቅፋት ሆነህብኛል ..›› (ማቴ 16፤ 23) ሰይጣን ??? ታላቁን ደቀመዝሙር ሰይጣን እያለው መቼም ይህንንም እንደማናስተባብለው ምኞቴ ነው፡፡ ነገር ግን ምኞቴ ምኞት ሆኖ ቀረና ማስተባበሉን ተያይዘውታል፡፡ ‹‹ኢየሱስ እኮ ጴጥሮስን ሳይሆን እንዲህ ያለው በውስጡ መጥፎ የሚያናግረውን ሰይጣንን ነው ..›› ጉድ በሉ !!! መጥፎ ሲሰራ ያየነውን ሰው በሙሉ ‹‹አንተ ሰይጣን›› እያልን መዝለፍ ይቻላል እያሉን ነው፡፡ ከዛም ‹‹ለምን ተሳደባችሁ›› ብንባል ውስጡ ያለውን ሰይጣን እንጂ ሰውዬውን አይደለም ማለት ያቻላልም እያሉን ነው፡፡ ‹‹ጉድ ሳይሰማ… !›› እኔን መውጫ ይጥፋኝ እንጂ ሌላ ምን እንላለን !!

C. ይሳደባ፤ መብቱ ነው፡፡ እሱ ከህግ በላይ ነው፤ እርሱን በህግ መነፅር አንዳኘውም !

ስለ ሃቅ ከተነጋገርን፤ ይህ መልስ ከሁሉም የተሻለ እና ቅንነት የተላበሰ (honest) ምላሽ ነው ! ሊጨበጨብላቸው ይገባል ! ብራቮ ! ይሄ ሁላ ከሚያሽከረክሩን መጀመርያውኑ እንዲህ ቢሉን የተሻለ ነበር፤ ስራችንንም ያቀልልን ነበር፡፡ መልሳቸው ‹‹ኢየሱስ ሃጢያተኛ ቢሆንም እንኳን፤ ከህግ በላይ በመሆኑ እንደ ስህተት አይቆጠርበትም›› የሚል መልዕክት ያዘለ ነው፡፡ እኛም ጥያቄ እናቅርብ፡፡ ታድያ ኢየሱስ ሃጢያት ያልነካው ነው ስትሉን ምን ማለታችሁ ነው ? አግባብ የሆነስ ድንፋታ ነውን ? በአንድ በኩል ነው፤ በሌላ በኩል አይደለም እያሉ መሄድስ ይቻላልን ? በፍፁም ! ስለሆነም ኢየሱስ ከሃጢያት ንፁህ ነው የሚለው ቀረርቶ ወንዝ ስለማያሻግር ሊቆም ይገባዋል ብለን እንመክራለን !

አንዳንዶችም ኢየሱስን ንፁህ ለማለት የጲላጦስን ‹‹ከሀጢያት አንድ እንኳን አላየሁበትም›› የሚለውን የምስክርነት ቃል በመውሰድ እንደመረጃነት ሲጠቀሙበት ይታያል፡፡ የምስክር ሰጪውን ማንነት ፤ የተናገረበትን ሙሉ አውድ እንዲሁም ሌሎች መረጃዎችን በማቅረብ ዕራቆቱን ማስቀረት ይቻላል ! እንዲሁም ከላይ የዘረዘርኳቸው ማብራርያዎች ላይ ተመርኩዘን ብንመለከተው፤ ግጭት ፈጥሯል ማለትንም ያስይዛል፡፡ ‹‹ሃጢያት›› የሚለው አገባብ ከሌሎች መፅሃፍ ቅዱሳዊ አስተምህሮቶች አንጻርም የሚገመገም ይሆናል !
መርፊው
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 260
Joined: Sat Oct 15, 2011 4:22 pm

Postby መርፊው » Mon Sep 09, 2013 11:42 pm

ክርስትናው ዓለም(ባይብል) ስለሴቶች ምን ይላል እስኪ አንዳንድ ጥቅሶች :-
By:Bahise Haqe
~~~~~~~~~>
1፡-ነገር ግን የወንድ ሁሉ ራስ ክርስቶስ፥ የሴትም ራስ ወንድ፥ የክርስቶስም ራስ እግዚአብሔር እንደ ሆነ ልታውቁ እወዳለሁ። (1ኛ ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች 11፡3)

2፡-“ከደረቅ ሴት ጋር ከምትኖር ከምድር አውሪዎች ከ አንበሳዎች ጋር መኖር ይሽላል”።(መጽሐፈ ሲራክ 25:16)

3፡-‹‹ለአምላኩ የተቀደሰ ነውና ጋለሞታን ሴት ወይም የረከሰችውን አያግባ ወይም ከባልዋ የተፈታችውን አያግባ።››ኦሪት ዘሌዋውያን 21፡7

4፡-‹‹ኦሪት ዘፍጥረት 3፡16 ለሴቲቱም አለ፦ በፀነስሽ ጊዜ ጭንቅሽን እጅግ አበዛለሁ በጭንቅ ትወልጃለሽ ፈቃድሽም ወደ ባልሽ ይሆናል፥ እርሱም ገዥሽ ይሆናል።››

5፡-1ኛ ቆሮንጦስ 14፡34 ላይ እንዲህ ይላል«ሴቶች በማህበር ዝም ይበሉ ህግ ደግሞ እንደሚል እንዲገዙ እንጂ እንዲናገሩ አልተፈቀደላቸውምና፡፡ ለሴት በማህበር መካከል መናገር ነውር ነውና ምንም ሊማሩ ቢዱወዱ በቤታቸው ባሎቻቸውን ይጠይቁ፡፡»

6፡-ሴት ግን በዝግታ ትኑር እንጂ ልታስተምር ወይም በወንድ ላይ ልትሰለጥን አልፈቅድም። (1ኛ ወደ ጢሞቴዎስ 2፡12

7፡-ሚስትም ከባልዋ አትለያይ፥ ብትለያይ ግን ሳታገባ ትኑር ወይም ከባልዋ ትታረቅ፥፡፡(1ኛ ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች 7፡10-11)

8፡-ራስዋን ሳትሸፍን ግን የምትጸልይ ወይም ትንቢት የምትናገር ሴት ሁሉ ራስዋን ታዋርዳለች፤ እንደ ተላጨች ያህል አንድ ነውና። (1ኛ ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች 11፡5)

9፡-“ከሴት ቸርነት የወንድ ንፉግነት ይሽላል።ውሽማዋንና ባሏን የምታቃና ሴት አፍረት ናት “። (መጽሐፈ ሲራክ 42:14)

10፡-ሚስቶች ሆይ፥ ለጌታ እንደምትገዙ ለባሎቻችሁ ተገዙ፤ (ወደ ኤፌሶን ሰዎች 5፡22

11፡-ሚስቶች ሆይ፥ በጌታ እንደሚገባ ለባሎቻችሁ ተገዙ። (ወደ ቆላስይስ ሰዎች 3:18)

12፡-ሴት ግን በዝግታ ትኑር እንጂ ልታስተምር ወይም በወንድ ላይ ልትሰለጥን አልፈቅድም። አዳም ቀድሞ ተፈጥሮአልና፥ በኋላም ሔዋን ተፈጠረች። (1ኛ ወደ ጢሞቴዎ11፡12)

13፡-“ከልብስ ብል ይገኛል፤ኃጢያትም ሁሉ ከሴቶች ይገኛል” (መጽሐፈ ሲራክ 42:13-14)

14፡-የተታለለም አዳም አይደለም፥ ሴቲቱ ግን ተታልላ በመተላለፍ ወደቀች፤
ነገር ግን በእምነትና በፍቅር በቅድስናም ራሳቸውን እየገዙ ቢኖሩ በመውለድ ትድናለች። (1ኛ ወደ ጢሞቴዎስ 2፡14-15)

15፡-ወንድ የእግዚአብሔር ምሳሌና ክብር ስለ ሆነ ራሱን መከናነብ አይገባውም፤ ሴት ግን የወንድ ክብር ናት። ሴት ከወንድ ናት እንጂ ወንድ ከሴት አይደለምና። ሴት ስለ ወንድ ተፈጠረች እንጂ ወንድ ስለ ሴት አልተፈጠረምና። ስለዚህ ሴት ከመላእክት የተነሣ በራስዋ ሥልጣን ሊኖራት ይገባል። (1ኛ ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች 11፡7-10)

16፡-ሴት ፈሳሽ ነገር ቢኖርባት በሥጋዋም ያለው ፈሳሽ ነገር ደም ቢሆን፥ በመርገምዋ ሰባት ቀን ትቀመጣለች የሚነካትም ሁሉ እስከ ማታ ድረስ ርኩስ ነው።
መርገምም ስትሆን የምትተኛበት ነገር ሁሉ ርኩስ ነው የምትቀመጥበትም ነገር ሁሉ ርኩስ ነው።
መኝታዋንም የሚነካ ሁሉ ልብሱን ያጥባል፥ በውኃም ይታጠባል፥ እስከ ማታም ድረስ ርኩስ ነው።
የምትቀመጥበትንም ነገር ሁሉ የሚነካ ሁሉ ልብሱን ያጥባል፥ በውኃም ይታጠባል፥ እስከ ማታም ርኩስ ነው። (ኦሪት ዘሌዋውያን 15፡19-22)

17፡-‹ ሴት ልጅ ለአባቷ የተሠወረ ቁርጥማት ናት አሷን ማሰብ እንቅልፍ ያሳጣዋል መጽሐፈ ሲራክ 42.9 ተጨማሪ 42.14

18፡ …--አስገድዶ መድፈር፤ ጋብቻ በሀይል፤ ለጠለፋ እውቅና መስጠት (መጽሐፈ መሳፍንት 21.20-21)( ኦሪት ዘዳግ 25.5-6 & 25.7-9)
19፡- ….ወዘተ


ሰላም ቅኑን መንገድ በተከለተለ ላይ ይሁን አሚን
መርፊው
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 260
Joined: Sat Oct 15, 2011 4:22 pm

Postby መርፊው » Wed Oct 02, 2013 9:11 pm

ኢየሱስ ክርስቶስ በፍላጎቱ ነውን የተሰቀለው? ^*^*^

**** እንደ ክርስቲያኖች እምነት ከሆነ ኢየሱስ ክርስቶስ አዳኝ ሆኖ ነው የመታው ተሰቅሎ በመሞት አለምን አድኗል ይህ ከሆነ የመታበትን ዓላማ ያውቃልና ቀጥታ ዓላማውን አስረድቶ መሰቀል ነበረበት ነገር ግን ከመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅሶች እንደምንረዳው ኢየሱስ ክርስቶስ ያለፍላጎቱ ተፈልጎ በይሁዳ ተሸጦ ነው የተሰቀለው፡፡ ታዲያ ሳይወድ የተሰቀለ ከሆነ እንዴት ለኛ ሲል ተሰቅሎ ምህረትን አደረገ በማለት እሱ ይመለካል? ቢሆን እንኳ የላከው እግዚአብሔር ብቻ ነው መመስገንም በብቸኝነት መመለክም የሚገባው፡፡ በተጨማሪም የኢየሱስ ክርስቶስ መሰቀል ለሰው ልጆች ሀጢያት መሰረይና መዳን ትልቅ ቦታ ካለው፤ ስቅለት ከሌለ መዳን የለም የሚባልም ከሆነ ኢየሱስ ክርስቶስ ወዶ አልተሰቀለም ይልቁንም ይሁዳ ነው ክዶት በ30 ብር አሳልፎ ሰጥቶት እንዲሰቀል ያደረገው፡፡ ታዲያ ይሁዳ አይደል ህ ሁሉ የእምነቱ ተከታይ ድኜበታለሁ ብሎ የሚያስበውን የኢየሱስ ክርስቶስ ስቅለት ተፈጻሚ እንዲሆን በማድረግ መዳን እውን እንዲሆን ታላቅ አስተዋጽኦ ያደረገው፡፡ በኢየሱስ ክርስቶስ መሸሽ ሊቀር የነበረውን የስቅለት ምህረት ይሁዳ አሳልፎ በመስጠት እውን እንዲሆን በማድረጉ ዋነውን ስራ ሰርቷል ታዲያ ይሁዳ ለምን ይነቀፋል፤ ይጠላል፤ ከሀዲ ይባላል? ይሁዳ ባይክድ ኢየሱስ ክርስቶስ ይሰቀል ነበርን?

የሚከተሉትን የኢየሱስን ያለፍላጎት መሰቀል የሚያሳዩ ጥቅሶች እንመልከት፡-

≠ ዮሐንስ 7፡1 ‹‹ከዚያም በኃላ ኢየሱስ አይሁዶች ሊገድሉት ይፈልጉት ነበር በይሁዳ ሲመላለስ አልወደደም ነበርና በገሊላ ይመላለስ ነበር፡፡››

^^ ፈርቶ በሌላ ከተማ ተመላለሰ ለምን?

≠ዮሀንስ 11፡53-54 ‹‹እንግዲህ ከዚያን ቀን ጀምሮ ሊገድሉት ተማከሩ ከዚያ ወዲያ ኢየሱስ በአይሁድ መካከል ተገልጦ አልተመላለሰም››

^^ ፈርቶ ተሸፋፈነ ለምን?

≠ዮሐንስ 10፡39 ‹‹ደግመው ሊይዙት ፈለጉ ከእጃቸው ወጣ››

^^ አመለጣቸው ለምን?

≠ ዮሐንስ 18፡22-23 ‹‹ኢየሱስ መልሶ ክፉ ተናግሬ እንደሆንኩ ስለ ክፉ መስክር መልካ ተናግሬ እንደሆነ ግን ለምን ትመታኛለህ? አለ››

^^ እንዳይመቱት ተማፀነ ለምን?

≠ ማቴዎስ 27፡46 እንዲህ ይላል “በዘጠኝ ሰዓትም ኢየሱስ፦ ኤሎሄ ኤሎሄ ላማ ሰበቅታኒ? ብሎ በታላቅ ድምፅ ጮኸ። ይህም። አምላኬ አምላኬ፥ ስለ ምን ተውኸኝ? ማለት ነው።”፡በሌላም ቦታ በማቴዎስ ወንጌል 26፡39 ላይ እየሱስ “አባት ሆይ! ቢቻል ይህ ፅዋ ከእኔ ይለፍ፤

^^ የእርዳታ ጥሪ አቀረበ ለምን?

*****ሌሎችም በርካታ ሳይፈልግ መሰቀሉን የሚያሳዩ ጥቅሶች ያሉ ሲሆን ከጥቅሶቹ በግልጽ የምንረዳው ያለፍላጎቱ የደረሰበት መከራ ነው፡፡ አንዳንድ የሀይማኖቱ ተከታዮች ትህትና ለማሳየት ብሎ ነው ይላሉ ትህትናን ማሳየት መፍራት፤ መሸሽ፤ ማምለጥ …..ወዘተ ምን አገናኘው ለማሳየት የሚደርስበትን ነገር ሁሉ በጸጋ መቀበል ነው እንጂ በማለጥ፤ በመፍራ ፤ በመደበቅ፤ ብሎም በሌላ ጥቆማ ደርሶበት እስኪያዝ መጠበቅ ነው እንዴ?
መርፊው
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 260
Joined: Sat Oct 15, 2011 4:22 pm

Postby መርፊው » Thu Oct 03, 2013 2:18 pm

መጽሃፍ ቅዱስ በየጊዜው ማሻሻያ ይደረግለታል ይበረዛል ይከለሳል የምንለው በደመነብስ አይደለም

የ 1954 እና የ1980 ዓ.ም መጽሃፍ ቅዱስ እትሞች ውስጥ ካሉ ልዩነቶችንየተወሰኑትን እዚህ ላይ ተመልከቱ፡፡ ውሸት ነው የሚል ካለ በማስረጃ ያስረዳ፡፡ ዝም ብሎ መቃዠት አይፈቀድም፡፡

የዮሀንስ ወንጌል 3፡18 የ 1954 እትም “ አሁን ተፈርዶበታል”
የዮሀንስ ወንጌል 3፡18 የ 1980 እትም “ ገና ድሮ ተፈርዶበታል”

አሁን ተፈረደበት ወይስ ገና ዱሮ?

የዮሀንስ ወንጌል 8፡40 የ 1954 እትም “ እውነት የነገርኳችሁን ሰው ልትገድሉኝ ትፈልጋላችሁ?”
የዮሀንስ ወንጌል 8፡40 የ 1980 እትም “ እውነት ነገርኳችሁ እናንተ ግን ልትገድሉኝ ትፈልጋላችሁ?”

“ ሰው” የሚለው ቃል የኋላኋላ ለምን እንዲወጣ ተደረገ ?

የሐዋርያት ስራ 2፡22 የ 1954 እትም “ ከእግዚአብሄር ዘንድ ለእናንተ የተገለጠ ሰው ነበር”
የሐዋርያት ስራ 2፡22 የ 1980 እትም “ ከእግዚአብሄር ዘንድ ለእናንተ የተገለጠው መለኮታዊ ስልጣን ያለው ነው፡፡

አሁንም የኋለኛው እትም ላይ “ሰው ነበር” የምትለዋ ቃል እንድትሰረዝ የተደረገው ለምንድን ነው?

ኦሪት ዘዳግም 18፡18 የ 1954 እትም “ ከወንድሞቻቸው መካከል እንደ አንተ ያለ ነብይ አስነሳላቸዋለሁ፡፡”

ኦሪት ዘዳግም 18፡18 የ 1980 እትም “ ስለዚህ እንደ አንተ ያለ ነብይ ከህዝቦቻቸው መካከል አስነሳላቸዋለሁ፡፡”

“ከወንድሞቻቸው” የሚለውን የትንቢት ቃል ምን ያህል ግልጽ ያልሆነና የተወሳሰበ ቃል ቢሆን ነው “ከህዝቦቻቸው መካከል” ወደሚለው መቀየር ያስፈለገው?
መጽሃፍ ቅዱስ በየጊዜው ማሻሻያ ይደረግለታል ይበረዛል ይከለሳል የምንለው በደመነብስ አይደለም::
መርፊው
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 260
Joined: Sat Oct 15, 2011 4:22 pm

Postby መርፊው » Thu Oct 03, 2013 9:53 pm

እየሱስ ሰውና ነብይ ስለመሆኑ የመጽሐፍ ቅዱስ ማስረጃ
...
1. ሉቃስ ወንጌል 7:15 “ታላቅ ነብይ በኛ መካከል ተነስቷል።”

2. ዮ ሐንስ ወንጌል 5:26 “የሰው ልጅ ስለሆነ ይፈርድ ዘንድ ስልጣን ሰጠው ”

3. ዮ ሐንስ ወንጌል 5:19 “አብ ሲ ያደርግ ያየውን እንጂ ወልድ ከራሱ ምንም ሊያደርግ አይችልም።”
4. ዮ ሐንስ ወንጌል 5:30 “እኔ ከራሴ ባደርግ አንዳች አይቻለኝም እንደ ሰማሁ እፈርዳለሁ ፍርዴ ቅን ነው። የላከኝን ፍቃድ እንጂ ፍቃዴን አልሻም።”
5. ዮ ሐንስ ወንጌል 4:6 “እየሱስ መንገድ በመሄድ ደክሞ ጉድጓድ አጠገብ ተቀመጠ ጊዜውም ስድስት ሰአት ነበር።”
6. ዮ ሐንስ ወንጌል 8:28 “እኔን ከፍ ከፍ አታድርጉኝ ከራሴ ምንም ማድረግ አልችልም።” ይላል እየሱስ ሙሊ ቃሉን ከመጽሐፍ ቅዱስ ያገኛሉ።
7. ዮሐንስ ወንጌል 14:28 አብ (እግዚአብሔር) ከእያሱስ ይበልጣል “የምትወዱኝ ከሆነ አብ ከኔ ይበልጣል” ይላል እየሱስ።
8. ዮሐንስ 20:17 “እየሱስ ወንድማችን ነው አምላክም አለው። ” ሙሉ ቃሉን ከመጽሐፍ ቅዱስ ያንቡ።
መጽሐፍ ምሳሌ 8:12 “የፍጥረቱ ሁሉ መጀመሪያ አደረገኝ” ይላል (እየሱስ ) የእግዜአብሔር ፍጡር እንጅ ፈጣር አይደለም። 1980 መጽሐፍ ቅዱስ ላይ።
9. 1 ኛ ጢሞቲዎስ 2:5

“አንድ እግዚአብሔር አለና በእግዚአብሔርና በሰው መካከል ያለው መካከለኛ ደግሞ አንድ አለ እሱም ሰው የሆነ ከርስቶስ ነው።” እየሱስ ሰው ነው።

ታዲያ ብዙ ወንጌላውያን ለምን እየሱስ ጌታ ነው ብለው ይሰብካሉ ? ትሉ ይሆናል።
2ኛ ጢማቲዮስ 4:3 “ሕይወት የምገኝበትን ትምህርት ያማትታገሱበት ዘመን ይመጣል።” ነገር ግን ጆሮ አችሁን የሚያሳክክ ስለሆነ እንድ ገዛ ምኞታቸው ለራሳቸው አስተማሪዎችን ያከማቻሉ።
ለዚህ ነው መሰለኝ አስተማሪዎች በዚህ ዘመ ን የበዙትና የገዛ ምኞታቸውን ያለ ማስረጃ የሚሰብኩት
መርፊው
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 260
Joined: Sat Oct 15, 2011 4:22 pm

Postby መርፊው » Sun Oct 20, 2013 4:12 pm

ይህን የፍቅር መልእክት የአምላክ ቃል ነውን?
,============== ==========
“አንቺ የንጉስ ልጅ ሆይ፥ እግሮችሽ በነጠላ ጫማ ውስጥ ሲታዩ
እንዴት ያምራሉ! ዳሌዎችሽ በብልህ አንጥረኛ እጅ የተሰራ
ዕንቁ ይመስላሉ።
እንብርትሽ በወይን ጠጅ የተሞላ ብርሌ ይመስላሉ፡ ወገብሽ
ዙሪያውን በአበባ የተሰረ የስንዴ ነዶ ይመስላል፥
ሁለቱ ጡቶችሽ መንታ የዋልያ ግለገሎች ይመስላሉ።
አንገትሽ በዝሆን ጥርስ እንዳጌጠ ግንብ ነው፡፡ ዓይኖችሽ
በታላቋ ከተማ በሐሴቦን ውስጥ የቅጽር በር አጠገብ እንደ ውኃ
ኩሬዎች ይመስላሉ፤ አፍንጫሽ ወደ ደማስቆ አቅጣጫ
ለመመልከት የተሰራ የሊባኖስ ግንብ ይመስላሉ።
የራስሽ ቅርጽ እንደ ቀርሜሎስ ተራራ ነው፤ የዞማው
ጠጉርሽም የሐር ጉንጉን የመሰለ ነው ንጉሡም በሹርባሽ
ውበት ተማርካል።
ውዴ ሆይ፥ እንዴት ያማርሽ ነሽ! እንዴትስ ውብ ነሽ! ፍቅርሽ
እንዴት ያስደስታል!
ቁመናሽ የዘንባባ ዛፍ ይመስላል፥ ጡቶችሽም የዘንባባ ዘለላ
ይመስላሉ።
ወደ ዘንባባው ዛፍ ላይ ወጥቼ ፍሬውን መልቀም እወዳለሁ
ጡቶችሽ እንደ ወይን ዘለላ እቅፍ ናቸው፤ የእስትፋስሽ መዓዛ
እንደ ፖም ፍሬ ነው! የአፍሽም መዓዛ እንደ መልካም ወይን
ጠጅ ነው።” (መኃልየ መኃልይ ምዕ .7 ቁ.1-9)
--------------- --------------- ---------------
--------------

በሌላ መጽሐፍ ቅዱስ ላይ ደግሞ እንዲህ ተሻሽሎ ቀርቦል፡-
አንቺ ሱላማጢስ ሆይ፥ ተመለሽ፥ ተመለሽ እናይሽ ዘንድ
ተመለሽ፥ ተመለሽ። በሱላማጢስ ምን ታያላችሁ? እርስዋ እንደ
መሃናይም ዘፈን ናት።
አንቺ የመኰንን ልጅ ሆይ፥ እግሮችሽ በጫማ ውስጥ እንዴት
ውቦች ናቸው! ዳሌዎችሽስ በአንጥረኛ እጅ እንደ ተሠሩ እንደ
ዕንቍዎች ይመስላሉ።
እንብርትሽ የወይን ጠጅ እንደማይጐድልበት እንደ ተነጠጠ ጽዋ
ነው ሆድሽ እንደ ስንዴ ክምር፥ በአበባም እንደ ታጠረ ነው።
ሁለቱ ጡቶችሽ እንደ ሁለቱ መንታ እንደ ሚዳቋ ግለገሎች
ናቸው።
አንገትሽ እንደ ዝሆን ጥርስ ግንብ ነው ዓይኖችሽ በሐሴቦን
ውስጥ በባትረቢ በር አጠገብ እንደ ውኃ ኵሬዎች ናቸው
አፍንጫሽ ወደ ደማስቆ አፋዛዥ እንደሚመለከት እንደ ሊባኖስ
ግንብ ነው።
ራስሽ እንደ ቀርሜሎስ ተራራ በላይሽ ነው የራስሽም ጠጕር
እንደ ሐምራዊ ሐር ነው ንጉሡ በሹርባው ታስሮአል።
ወዳጄ ሆይ፥ እንዴት የተዋብሽ ነሽ! እንዴትስ ደስ ታሰኛለሽ!
ይህ ቁመትሽ የዘንባባ ዛፍ ይመስላል፥ ጡቶችሽም የወይን ዘለላ
ይመስላሉ።
ወደ ዘንባባው ዛፍ እወጣለሁ ጫፎችዋንም እይዛለሁ አልሁ
ጡቶችሽ እንደ ወይን ዘለላ የአፍንጫሽም ሽቱ እንደ እንኮይ
ናቸው።
ጕሮሮሽ ለወዳጄ እየጣፈጠ እንደሚገባ፥ የተኙትን ከንፈሮች
ይናገሩ ዘንድ እንደሚያደርግ፥ እንደ ማለፊያ የወይን ጠጅ ነው።
(መኃልየ መኃልይ ምዕ .7 ቁ.1-10
መርፊው
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 260
Joined: Sat Oct 15, 2011 4:22 pm

Postby መርፊው » Sun Dec 01, 2013 12:11 am

ምሳሌ 30፡21-23 እንዲህ ይላል
«ምድር በሦስት ነገር ትናወጣለች፤ እንዲያውም መሸከም የማትችላቸው አራት ነገሮች ናቸው
የተጠላች ሴት ባል ስታገባ፤ ሴት ባሪያ በእመቤቷ እግር ስትተካ፡፡»

በመፅሐፍ ቅዱስ --------------- --------ኦሪት ዘዳግም 21፡15
ላይ እንዲህ ይላል [ለአንድ ሰው አንዲት የተወደደች አንዲት የተጠላች ሁለት ሚስቶች ቢኖሩት….]

ተመልከቱ ባይብል ልክ እንደ TOM & JERRY
አለመስማማቱን ቀጥሎበታል የተጠላች ሴት ስታገባ ምድር እንደምትናወጥ ያውም መሸክም እናደሚከብዳት ከተነገረ መልሶ የተጠላች ሴት ማግባት መልካም እንደሆነ ይናገራል ምን ማለቱ ነው ምድር መናወጡ ነው ጥሩ እስኪ ንገሩኝ :lol:
መርፊው
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 260
Joined: Sat Oct 15, 2011 4:22 pm

Postby መርፊው » Sun Jan 12, 2014 12:18 am

_______ጥቅሶች


1.ልጇን ቀቅላ የበላች እናት መጽሐፈ ነገሥት ካልዕ6፡26-29

2.ባሏ ስለሞተባት ሴት ወንድሙን ታግባ፤በስሙይጠራ፤እንቢካለ ፊቱ ላይትትፋ ኦሪት ዘዳግም25፡5-10

3.በልጁ ላይ ዝሙት ሉጥ (ኦሪት ዘፍጥ 19.30-38 (ይሁዳ ኦሪት ዘፍጥ 38.15-24)

4.እግዚአብሔር በግብጽ ወንዝ ዳርቻ ያለውን ዝምብ በአሦርም አገር ያለውን ንብ በፉጨት ይጠራል። ትንቢተ ኢሳይያስ 7:18

5.ዝሙት አንደ መብት (ኦሪት ዘፍጥ 35.22 & 49.4 )

6.ሶስት አመት በራቁቱ የሄደ ነብይ ትንቢተ ኢሳያስ 20፡1-3

7.ለጸሎት የጥጃ ምስል ጣኦት የሰራ ነብይ አሮን (ኦሪት ዘጽአት 32.2-4)

8.የግል ደብዳቤ እኔ ጋር እንድትመጣ፤የስቀመጥኩትን አምጣልኝ.. ወደ ጢሞቴዎስ 2ኛ 4፡9-13

9.የ 100 ሰዎች ሞት ለዳዊት ጥሎሽ (መጽሐፈ ሳሙኤል ቀዳማዊ 18:25-27)

10.በባሎቻቸው ስለሚጠረጠሩ ሴቶች የተሰጠ የመመርመሪያ ዘዴ ኦሪት ዘኁልቁ 5፡12-25(1980 የተሻለ)

11.የማይሰራበት ጥቅስ ከግብረስጋ ግንኙነት ቡኃላ (አሪት ዘሌዋውያን 15.16-18)

12.ስካር በእርቃን (ኖህ፤ዳዊት..) (ኦሪት ዘፍጥ 9.20-25 )(1 ኛ መጽ ሳሙኤል 19:23-34)

13.በዚያም ቀን ግዚአብሔር ከወንዙ ማዶ በተከራየው ምላጭ በአሦር ንጉሥ የራሱንና የእግሩን ጠጕር ይላጨዋል ምላጩም ጢሙን ደግሞ ይበላል ትንቢተ ኢሳይያስ 7:20

14. እግዚአብሔር ሚስት አላውን ? (ትንቢተ ህዝቄኤል 16: 1-5 & 23.1-5) ትንቢተ ኢሳያስ 54፡5

15.እንደዚህ ታምኜ ስመካ የምናገረው፥ በሞኝነት እንጂ ጌታ እንዳዘዘኝ አልናገርም።2ኛ ቆሮንቶስ 11:17

16.‹…ከእናንተ ጋር ኵሳቸውን ይበሉ ዘንድ ሽንታቸውንም ይጠጡ ዘንድ..›መጽ ነገሥት ካልዕ 18:27

17. ሥጋቸውም እንደ አህዮች ሥጋ ዘራቸውም እንደ ፈረሶች ዘር የሆነውን… ትንቢተ ሕዝቅኤል 23:20

18 ‹…ያለ ቅጣት ብትኖሩ ዲቃላዎች እንጂ ልጆች አይደላችሁም› ወደ ዕብራውያን 12:8

19. የጳውሎስ ዘረኝነት ፡‹እኛ በፍጥረት አይሁድ ነን ኃጢአተኞችም የሆኑ አሕዛብ አይደለንም፤ ገላቲያ 2፡15

20‹ቍላው የተቀጠቀጠ ብልቱም የተቈረጠ ወደ እግዚአብሔር ጉባኤ አይግባ።ኦሪት ዘዳግም 23፡1

21.ሙሴ ኦሪትን ጽፎዋል ? መሞቱን አንዴት ሊጽፍ ቻለ‹.. በዚያ በሞዓብ ምድር ሞተ። ዘዳግም 34፡5
22 etc
መርፊው
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 260
Joined: Sat Oct 15, 2011 4:22 pm

ያልተለመዱ የቁርአን አባባሎች

Postby ጎነጠ » Sun Jan 12, 2014 9:51 am

ያልተለመዱ የቁርአን አባባሎች

በቁርአን ውስጥ እጅግ በጣም ብዙ የሆኑ ያልተለመዱ አባባሎች ይገኛሉ፡፡ በመሐመድ ነቢይነት የማያምኑት (እስልምናን ያልተከተሉት) መሐመድን እንዲተቹት ያደረጓቸው ምክንያቶች እነዚህን ብዙ ተረቶች ሲያስታውሳቸውና ሲቀራቸው ሰምተው ነው፡፡ ተረቶችን እንደ እውነተኛ ታሪክ አድርጎ መደጋገሙ ልክ አለመሆኑን ጠቅሰው የማያምኑት መሐመድን እንደሚከሱት ቁርአን እራሱ በሚከተሉት ጥቅሶች ውስጥ ይናገራል 16.24፣ 25.5፣ 68.15፣ 83.13፡፡

እነዚህ ተረቶችን እንግዳ ያደረጋቸው ነገር ዛሬም እንኳን ቢሆን ሙስሊሞች ላልሆኑት ሁሉ በጣም ግልጥ ነው፡፡ በክፍሉ ውስጥ ‹የሪፕ ቫን ዊንክል› ተብሎ የሚታወቀው ዓይነት ተረት አለበት (‹አንቀላፍቶ መንቃት› ወይንም ‹ለረጅም ጊዜ አንቀላፍቶ ወይንም አዕምሮ ስቶ በድንገት አዲስ በሆነ ሁኔታ ውስጥ መንቃት› የሚባለው ዓይነት ተረት ነው)፡፡ ለምሳሌም ያህል አንዳንድ ወጣቶችን በእንቅልፍ ላይ ለ300 ዓመታት ያህል እንዲቆዩ ለማድረግ ፀሐይ አቅጣጫዋን መቀየሯ ይገኙበታል፡፡ ቁርአን ስለ አንድ ግዙፍ ሰው ይነግረናል፣ እሱም ወደ ምዕራብ አቅጣጫ በጣም ከተጓዘ በኋላ በቀኑ ማብቂያ ላይ ፀሐይ የምትጠልቅበትን ረግረግ ጭቃ ቦታ አይቶ እንደመሰከረ አቅርቦልናል፡፡ ሌላው ተረት ደግሞ በዝሆኖች ይጠቀም የነበረ የጦር ሰራዊት እንዴት በወፎች መንጋ እንደተሸነፈ የሚገልጠው ነው፡፡ ይህም የሆነው የወፎቹ መንጋ በዝሆኖቹ ጦር ሰራዊት ላይ የሸክላ ጠጠሮችን ያለማቋረጥ በመጣል ሙሉ ለሙሉ እንዳጠፏቸው ይናገራል፡፡ ሰንበትን የሻሩ አይሁዶች በአላህ አማካኝነት ወደ ጦጣነት እንዴት እንደተቀየሩ የሚነግረንም ተረት አለበት፡፡

በዚህ ምዕራፍ ውስጥ እነዚያን ተረቶች የሚያሳዩት ስልሳ አራት ጥቅሶች ጠቅለል ተደርገው ቀርበዋል፡፡ በቁርአን ላይ ግን ረጃጅሞች በመሆናቸው አንባቢ ጥቅሶቹን እያገላበጠ ማንበብ ይኖርበታል፡፡

ቁርአን የሚከተሉትን ተረቶች ይናገራል

አንቀላፊዎቹ፡- በአንድ አምላክ በማመናቸው ምክንያት አንዳንድ ወጣቶችና ውሻቸው ሊቀጧቸው ከሚያሳድዷቸው ከጣዖት አምላኪዎች ሲሸሹ በአላህ ወደ አንድ ዋሻ ተመርተው ለብዙ ዓመታት ተኝተዋል፡፡ በዚህም ወቅት እነሱን ለመርዳት ፀሐይ የመዞሪያ መንገዷን ቀይራለች፡፡ በዚያም ምን ያህል ወጣቶች (ቁጥራቸውን) እንደበሩ ከአላህ በስተቀር ማንም አያውቅም ነገር ግን አንዳንዶች ሰባት ነበሩ ይላሉ፡፡ ከውሻቸውም ጋር ሲደመሩ ስምንት ይሆናሉ፡፡ ከአላህ በስተቀር ለምን ያህል ዘመን እንዳንቀላፉ ማንም አያውቅም አንዳንዶች ግን ለ309 ዓመታት ነው ይላሉ፡፡ 18.9-25፡፡

ከመቶ ዓመታት በኋላ ትንሳኤ፡- አንድ ተጠራጣሪ አንዲት የወደመችን ከተማ ተመልከቶ አላህ እንዴት የከተማዋን የጥንት ነዋሪዎች (በትንሳኤ) ሊያነሳቸው እንደሚችል ይደነቅ ይሆናል፡፡ አላህም ያንን ተጠራጣሪ ሰው እንዲሞት አድርጎት ከአንድ መቶ ዓመታት በኋላ እንዲነሳና ወደ ሕይወት እንዲመለስ አድርጎታል፡፡ እሱም ለምን ያህል ዓመታት ከዚህ ዓለም ላይ እንዳልነበረ ተጠይቆ የመለሰው መልስ ለአንድ ቀን ብቻ የሚል ነበር፡፡ ነገር ግን ለአንድ መቶ ዓመታት ተወስዶ እንደበረ ተነግሮታል፣ ከመቶ ዓመታት በኋላም ሲነቃ (ከሞት ሲነሳ) ሲሞት የተወውን ምግቡና መጠጡ አሁንም ትኩስ ነበሩ ነገር ግን አህያው ወደ ደረቅ ድንጋይነት ተቀይሮ ነበር፡፡ በእሱም ላይ የሆነው ነገር ለሰው ልጆች ሁሉ የመጨረሻው ትንሳኤ ምን እንደሚመስል ትልቅ ምልክት ነበር 2.259፡፡

እጅግ ልዩ የሆነው ሰው፡- ታላቅ የሆነና ሁሉን ነገር ለማድረግ እንዲችል ተደርጎ የተፈጠረ አንድ ሰው ነበር፡፡ ስሙም ዱዐል ቃርናይን ነበር፡፡ ካደረጋቸውም ሌሎች ነገሮች ባሻገር እስከ ሩቅ ምዕራብ ድረስ በጎዳና ተጉዞ ፀሐይ በጥቁር የረግረግ ጭቃ ውስጥ ስትጠልቅ ተመለከተ፡፡ እንደገናም በሌላ ጎዳና ወደ ሩቅ ምስራቅ ተጓዘና ፀሐይ ጉዞዋን ስትጀምር ለእሷ በጣም ቅርብ የሆኑ ዓይነት ሰዎችንም ተመለከተ፡፡ እነሱም ከፀሐይ ጨረር ቅርብነት የማቃጠል ኃይል ምንም ዓይነት በከላከያ ያልነበራቸው ሰዎች ነበሩ፡፡ ሌላው የእሱ ስራም ደግሞ አንድ ትልቅ የሆነን ግድብ (ድልድይን) መስራት ነበር፡፡ ይህም ግድብ የተሰራው በሁለት እልም ያለ ገደል ባላቸው ተራራዎች መካከል ያለውን ቦታ ሙሉ ለሙሉ ሞልቶ ነበር፡፡ ግድቡም ተሰርቶ የነበረው በቀለጠ ነሐስ ተለብጦ ከነበረ ብረት ነው፡፡ እሱም እጅግ በጣም ትልቅ ስለነበር የጎግና ማጎግ ሕዝቦች ሊመዝኑት አልተቻላቸውም ወይንም ሊቆፍሩትና ጎረቤቶቻቸውን ለመረበሽ አልቻሉም ነበር፡፡ ይህም ታላቅ ግድብ እስከ ፍርድ ቀን ድረስ የሚኖር ነው 18.83-98፡፡

ዝሆኖችና ወፎች፡- ዝሆኖችን ተጠቅሞ የነበረ አንድ የጦር ሰራዊት አንድ ጊዜ በአላህ ተሸንፎ ነበር፡፡ የወፎች መንጎችን አላህ ልኮባቸው ከተጠበሰ ጭቃ (ሸክላ) በሆነ ድንጋይ አወረዱባቸው ከዚያም ቅጠሉ እንደተበላ አዝመራ ሁሉም ረገፉ 105.1-5::

የተለወጡ ጅኒዎች፡- አንዳንድ ጅኒዎች እስከ ሰማይ ጫፍ ድረስ ይበራሉ ይህም የቁርአን ንባብ የሚሰማበት ቦታ ላይ ለመገኘት በመፈለግ ነው፡፡ በአላህ ዙፋን አካባቢ የሚሆነውን እንዳይመለከቱ ለማራቅ የምትወረወርን ፍላፃ አዩ (ተወርዋሪ ኮከብ)፡፡ እነሱም የሰሙት መልእክት አላህ አንድ እንደሆነና ምንም ሚስት እንደሌለው ልጆችም እንደሌሉት የሚናገረውን መልእክት ነው መልእክቱንም አመኑ፡፡ እነሱም ሙስሊሞች ሆኑ፡፡ ስለዚህም አንዳንድ ጅኒዎች በእስልምና ያምናሉ፡፡ ሌሎች ደግሞ የሲዖል እሳት ማቀጣጠያ ነዳጆች ናቸው 72.1-15፡፡

የአላህን ግመል መግደል፡- የታሞድ ሰዎች በነቢዩ በሳሌህ ማስጠንቀቂያን ተሰጥቷቸው ነበር ይህም ከጣዖታት አምልኮ እንዲመለሱ ነበረ ነገር ግን ከእርሱ ጋር ተከራከሩ፡፡ ሳሌህም ለታሞድ ሰዎች አላቸው፡- ‹አንዲት የአላህ ንብረት የነበረች የሴት ግመል ነበረች እሷም ምንም ጥቃት ሊደርስባት አያስፈልግም› ነገር ግን እነሱ ግመሏን ገደሏት፡፡ ሳሌህም ቀጥሎ እነሱ ከሦስት ቀናት በኋላ እንደሚቀጡ ትንቢትን ተናገረ፡፡ ትንቢቱን በተናገረበት ቀንም ጠዋት በፍንዳታ የተነሳ ሁሉም በቤቶቻቸው ውስጥ ሞተው ተገኙ፡፡ እነሱ ሁሉም ሄደዋል 11.61-68፡፡

ሰንበትን የሻሩቱ ወደ ጦጣነት ተቀየሩ፡- አይሁዶች ማስታዎስ ያለባቸው ነገር አላህ ሰንበትን የሚሽሩትን አይሁዶች እጅግ አስጠሊ ወደሆነ ጦጣነት እንዴት እንደቀየራቸው ነው፡፡ ይህም ለሚመጣው ትውልድ ምልክት ይሆኑ ዘንድ ነው፡፡ 2.65፣66፡፡

የአዘጋጁ ማሳሰቢያ፡

በቁርአን ውስጥ ያሉት ተረት የሆኑ አባባሎች እጅግ በጣም ብዙ ናቸው፡፡ ሙስሊሞች እነዚህን ነገሮች እንዴት ነው የሚመለከቷቸው? በእርግጥ እንደዚህ ዓይነት ተረቶችን የእግዚአብሔር ቃል ይናገራልን? መሐመድ እነዚህን ተረቶች ሲናገር እና ከእግዚአብሔር የመጡ ናቸው ሲል በዘመኑ የነበሩ ሰዎች ተቃውመውታል፡፡ እነዚህ ከእግዚአብሔር አይደሉም ብለዋል ለዚህም ደግሞ በዚህ ጽሑፍ መግቢያ ላይ ያሉት የቁርአን ጥቅሶች ማስረጃዎች ናቸው፡፡ እኛስ እንዴት ነው ልናያቸው የሚገባን ምናልባት ሐሳባችንን እንደሚገባ ለመግለፅ ፍርሃት ወይንም ተፅዕኖ ይኖርብን ይሆንን? ሊሆን ይችላል፣ ነገር ግን ይህ እንደዚህ በቀላሉ የሚታለፍ ነገር አይደለም የምንከተለውና የምናምነው ነገር በእውነት ላይ ያልተመሰረተ ከሆነ የዘላለም ሕይወት ተስፋ የሚባል ነገር ሊኖረን አይችልም፡፡ ማንም በተረት ላይ በተመሰረተ እምነት መንግስተ ሰማይ ሊገባ አይችልም፡፡

መጽሐፍ ቅዱስ ግን የእግዚአብሔር ቃል ነው፡፡ ለእንደዚህ ዓይነት ሰዋዊ የፈጠራ ተረቶች ጊዜና ቦታ የለውም፡፡ ምክንያቱም በመጀመሪያ መጽሐፍ ቅዱስ የመጣው ከእግዚአብሔር ነው የፈጠራ ተረት የለበትም፡፡ በሁለተኛ ደረጃ ደግሞ የሕይወትና የእምነት ነገር የምርና አሳሳቢ በመሆኑ ነው፡፡ ማለትም መጽሐፍ ቅዱስ የሚያስተላልፈው የምርና እውነተኛ ለሕይወት የሚጠቅምን መልክት ነው፡፡

በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ሰዎች ሁሉ ኃጢአተኞች መሆናቸውንና የዘላለምም ፍርድ እንደሚጠብቃቸው በግልጥ ተቀምጧል፡፡ በዕብራውያን መልእክት ምዕራፍ 9.27 ‹ለሰዎች አንድ ጊዜ መሞት ከእርሱም በኋላ ፍርድ ተመድቦባቸዋል› የሚልን ቃል እናነባለን፡፡ ስለዚህም - ከዚያ የዘላለም ፍርድ ኃጢአተኞች የሆኑ ሰዎች እንዴት ሊድኑ ይችላሉ? የሚለውን ጥያቄ መጠየቅ አግባብና ማስተዋል ነው፡፡

መጽሐፍ ቅዱስ ለዚህ ጥቄ መልስ የሚሆን የምስራች መልእክት አለው፡፡ የመጽሐፍ ቅዱስም ወጥ መልእክት እንደሚከተለው ነው፡- ሰዎች በኃጢአታቸው ንስሐ እንዲገቡ፤ ይቅርታን እና ስርየትን ማግኘት እንዲችሉ ዋጋ በከፈለላቸው በጌታ በኢየሱስ ስራ እንዲታመኑ፤ በእርሱም በኩል ብቻ ወደ እግዚአብሔር እንዲመጡ ነው፡፡ ይህንን ያደረጉ ሰዎች ከዚህ በፊት በሕይወታቸው ያላዩትን አዲስ ሕይወትን፣ እውነተኛ ሰላምን፣ የኃጢአት ይቅርታን ከእግዚአብሔር ዘንድ ይቀበላሉ፣ የዘላለምም ሕይወትን ወራሾች ይሆናሉ፡፡

አንባቢ ሆይ መጽሐፍ ቅዱስን ለራስህ አግኝና በልበ ሰፊነት አንብበው፣ የእግዚአብሔር ቃል ስለሆነ እርሱ እራሱ ይናገርሃል፡፡ ለውስጥ ሕይወት የሚናገር መጽሐፍ ነው፡፡ የእግዚብሔርን ፈቃድ እና ዕቅድ በግልፅ የሚናገር የእግዚአብሔር መጠቀሚያ ቃሉ ነው አግኝና አንብበው፡፡ ጌታ ኢየሱስ ቃሉን በማንበብ የሚገኘውን ትልቅ በረከት እንዲሰጥህ ፀሎታችን ነው፡፡ እግዚአብሔር በምህረቱ ይርዳህ አሜን!
I love ethiopia
ጎነጠ
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 103
Joined: Wed Aug 03, 2005 9:07 am
Location: ethiopia

Postby መርፊው » Sun Jan 12, 2014 1:21 pm

የሶስትዮሽ (የስላሴ)ጽንሰ ሃሳብ ከየት መጣ? *^*


** የሶስትዮሽ ጽንሰ ሃሳብ (Concept of Trinity )በመጽሐፍ ‹‹ቅዱስ›› በየትኛውም ምዕራፍ የማይገኝ ሲሆን ከየት መጣ ለሚለው የእምነቱ ተከታዮች እራሳቸው በቂ መረጃ ያለው መልስ የላቸውም(አለን የምትሉ ከሆነ ደግሞ ይህው በሩ ክፍት ነው…..) በመጽሐፍ ‹‹ቅዱስ›› አንድም ቦታ ነብያቶች ሆኑ አምላክ የተባለው እየሱስ ክርስቶስ(ሰላም በሱ ላይ ይሁንና) እንዲሁም ሃዋሪያቶች ማናቸውም ስለ ሶስትዮሽ ያስተማሩት አንድም ትምህርት የለም በመጽሐፍ ‹‹ቅዱስ›› በየትኛውም ጥቅስ የሦስትዮሽ ጽንሰ ሃሳብ አልተጻፈም ይልቁንም የፈጣሪ አንድነት ነው በሰፊው የተነገረው የሶስትዮሽ ጽንሰ ሃሳብ በአንዳንድ ጸሐፊዎች ከየት እንደመጣ ሲገለጽ በመጀመሪያ የተመሰረተው አቴናሲዮስ /Athanasius/ በሚባል የአሌክሳንድሪያ ጳጳስ በ325 ዓ.ል ሲሆን እራሱም ቢሆን ስለ ስላሴ ሲያስረዳ ‹‹ጽንሰ ሃሳቡን በጻፍኩት ቁጥር ሃሳቡን ለማስረዳት ያለኝ አቅም በጣም አናሳ ይሆናል›› ብሎ ጽንሰ ሀሳቡ ለማመን የሚቸግር መሆኑን አምኗል፡፡ በዚያን ግዜም ቢሆን አብና ወልድን ብቻ በመግለጽ ነበር፡፡ ይህንንም ወልድን ከአብ ጋር እኩል የማድረግ ፅንሰ ሀሳብ 300 ጳጳሳት በተሰበሰቡበት የኒቄያ ጉባኤ ላ በድምጽ ብልጫ ተወሰነ ይህ ሀሳብ በአንድ ጳጳስ እስከሚጸድቅበት ጊዜ ቤተክርስቲያንኖችም ሆኑ የሀይማኖቱ ተከታዮች በአንድ እግዚአብሔር ብቻ ነበር የሚያምኑት ፡፡ ይህም ማለት ሃይማት የሚያህል ነገር አብና ወልድ አንድ ናቸው በሚል በአንድ ጳጳስ የቀረበ ሃሳብ የክርስትና እምነት እስከ 325 ዓ.ል ድረስ በአንድ አብ የሚያምነው እምነት በ300 ጳጳሳት ውሳኔ በመነሳት የፈጣሪ ቃል ሳይሆን የእምነቱ አካል ተደረገ፡፡ በመቀጠልም በ381 ዓ.ል ከ56 ዓመታት በኋላ መንፈስ ቅዱስመረ አንደ የአምልኮ አካል እንደሆነና ሶስቱ እንደ አንድ እንደሆኑ በቆስጠንጢያንው ጉባኤ ፀደቀ ፡፡ እንግዲህ የሶስትዮሽ ጽንሰ ሀሳብና አምልኮ የመጣው በዚህ ዓይነት ሁኔታ ነው፡፡ ዶክተር ፓውል እንዝ ታሪካዊ ስነ-መለኮት አመጣጡና ትንታኔው፤ በሚለው መጽሃፋቸው ይህን እውነታ እንዲህ ሲሉ አስቀምጠዋል፡-
‹‹የኒቅያው [nicea} ጉባኤ በ325 ዓ.ም ታሪካዊውን አስተምሮ-ሥላሴን አፀደቀ፡፡በዚህም መሰረት ክርስቶስ ከአብ ጋር የባህሪ እኩልነት ያለው መሆኑ ግንዛቤ አገኘ፡፡›› ሲሉ ጽፈዋል (ዶክተር ፓውል እንዝ ታሪካዊ ስነ-መለኮት አመጣጡና ትንታኔው፤ በአርቲስቲክ ማተሚያ ቤት የታተመ ፤1993 አዲስ አበባ ገጽ-13

ቀጠሉና

“በአርዮስ ትምህርት የተነሳ የተፈጠረው ውዝግብ ለመፍታት በ325 ዓ.ም ኒቂያ በተባለው ስፍራ አንድ ጉባኤ ተካሄደ፡፡በጉባኤው ላይ 300 ጳጳሳት ተገኝተው ነበር፡፡ጉባኤው አርዮስንም ሆነ አርዮሳዊነትን የሚቀበሉትን ሁሉ አውግዟል፡፡ በንጉሱ ካስፀደቀ በኋላም የሚከተለውን መግለጫ አወጣ፡- “ሁሉም በሚችል፤ የማይታየውንና የሚታኘውን በፈጠረ፤ በአንድ አምላ በእግዚአብሔር እናምናለን ፡፡ የእግዚአብሔር ልጅ በሆነው በአንዱ በጌታ በእየሱስ ክርስቶስ፤ ከአብ ብቻውን በተገኘው ከአብ መገኛው (“ኡሲያስ”/ousias) አንድ በሆነው፤ ከአምላክ በተገኘው አምላክ፤ በብርሃ በተገኘው ብርሃ፤ ከእውነተኛ አምላክ በተገኘው እውነተኛ አምላክ፤ በተፈጠረ ሳይሆን በተወለደ፤ ከአብ ጋር በማንነት (homoousion) አንድ በሆነው፤ ሁሉ በእርሱ በሆነ፤ በሰማይም ሆነ በምድር ባለው፤ ለእኛ ለሰው ልጆች ደህነት ወርዶ ስጋ በሆነ፤ ሰውም በሆነ፤ መከራን በተቀበለበት በሶስተኛውም ቀን በተነሳ፤ ወደ ሰማይ ባረገ፤ በሙታንና በህያዋን ላይ ሊፈርድ በሚመጣው እናምናለን፡፡( ዶክተር ፓውል እንዝ ታሪካዊ ስነ-መለኮት አመጣጡና ትንታኔው፤ በአርቲስቲክ ማተሚያ ቤት የታተመ ፤1993 አዲስ አበባ ገጽ-33-34

** መቼም እዚህ ጋር አንድ ጥያቄ ያስነሳል- በኒቂያ ጉባኤ መሰረት “ክርስቶስ ከአብ ጋር የባህሪ እኩልነት ያለው መሆኑ” ግንዛቤ ሳያገኝ በፊት ቤተ ክርስቲያን የስላሴን እምነት ሳይሆን የአንድን አምላክ ኃያልነትና ብቸኝነት ስታስተምር ተሳስታ ነበርን? ከኒቂያ ጉባኤ በፊት የነበሩ አማኞችና ሐዋሪያትና የእየሱስ ባህሪያት ከአብ ጋር መስተካከል ሳይረዱትና ግንዛቤውን ሳያገኙ ቆየረተው በኒቂያ ጉባኤ ተገኝተው በድምጽ ብልጫ የወሰኑት 300 ጳጳሳት ግንዛቤውን አገኙን? እምነት የሚጸድቀው እንደ ፖለቲካ ፓርቲ በጉባኤ ነው ወይስ በአምላክ ትዕዛዝ? ይህስ ትክክለኛ አካሄድ ነውን?

** ከላይ እንደተገለጸው ይህ የኒቅያ ጉባኤ እራሱ “በእግዚአብሔር አብ እናምናለን እንጂ አንድ እግዚአብሔር በሚሆኑት በአብ በወልድና በመንፈስ ቅዱስ እናምናለን እንደማይል እናስተውልን?
“በኒቅያ ጉባኤ የሃይማኖት መግለጫ ውስጥ ከስላሴ አካላት የአንዱ መንፈስ ቅዱስ አስተምሮ በግልጥ አልተቀመጠም፡፡ መግለጫው ያረጋገጠው “በመንፍ ቅዱስ እናምናለን” የሚለው ብቻ ነበር ፡፡ “የቆስጠንጢያው ጉባኤ በ381 ዓ.ም “ጌታ በሆነና ሕይወት በሚሰጥ፤ ከአብ በሚወጣና ከአብና ከወልድ እኩል አምልኮን በሚቀበል፤ በነብያትም በተነገረ መንፈስ ቅዱስ እናምናለን” የሚለውን መግለጫ አውጥቷል፡፡ መግለጫው መንፈስ ቅዱስ በህልውና ከወልድና ከአብ ያነሰ ሳይሆን እኩል መሆኑን በፅኑ አረጋግጧል፡፡” ይላል (ዶክተር ፓውል እንዝ ታሪካዊ ስነ-መለኮት አመጣጡና ትንታኔው፤ በአርቲስቲክ ማተሚያ ቤት የታተመ ፤1993 አዲስ አበባ ገጽ-34፡፡
ታዲያ መንፈስ ቅዱስም እንደ ወልድ ከአብ የሚወጣ ከሆነ መንፈስ ቅዱስም የፈጣሪ ልጅ ነውን? ካልሆነ ለምን?
መጽሐፍ‹‹ቅዱስ›› እንዲህ ይላል ፡- ኢሳያስ 46፡9 ላይ “እኔ አምላክ ነኝና ሌላም የለምና የቀድሞውን የጥንቱን ነገር አስብ፤ እኔ እግዚአብሔር ነኝ እንደ እኔ ያለ ማንም የለም፡፡” ይላል፡፡ ከጥንት ጀምሮ የነበረውን አሃዳዊን እምነት ወይስ ከኒቂያ ጉባኤ በኃላ የመጣውን የስላሴ አስተምሮ እንቀበል? “ ጥቅሱ ግን የጥንቱን ነገር አስብ እኔ እግዚአብሔር ነኝ እንደ እኔ ያለ ማንም የለም፡፡” ነው የሚለው፡፡

^*^ በጣም የሚገርመው በመጽሐፍ‹‹ቅዱስ›› አንድም ቦታ ያልተገለጸው ሦስትዮሽ በተከበረው ቁርአን በበርካታ ቦታዎች ተጠቅሷል፡- ሁለቱን እንመልከት

‹‹እነዚያ አላህ የሶስት ሶስተኛ ነው(ከሶስት አማልክት አንዱ ነው) ያሉ በእርግጥ ካዱ አምላክም አንድ አምላክ እንጂ ሌላ የለም ከሚሉት ነገር ባይከለከሉ እነዚያ የካዱትን አሳማሚ ቅጣት በእርግጥ ይነካቸዋል፡፡›› (ሱረቱ አል-ማኢዳህ 5፡73)

‹‹ እናንተ የመጽሐፉ ሰዎች ሆይ! በሃይማኖታችሁ ወሰንን አትለፉ፡፡ በአላህም ላይ እውነትን እንጅ አትናገሩ፡፡ የመርየም ልጅ አልመሲሕ ዒሳ የአላህ መልክተኛ ወደ መርየም የጣላት «የኹን» ቃሉም ከእርሱ የኾነ መንፈስም ብቻ ነው፡፡ በአላህና በመልክተኞቹም እመኑ፡፡ « (አማልክት) ሦስት ናቸው» አትበሉም፡፡ ተከልከሉ፤ ለእናንተ የተሻለ ይኾናልና፡፡ አላህ አንድ አምላክ ብቻ ነው፡፡ ለእርሱ ልጅ ያለው ከመኾን የጠራ ነው፡፡ በሰማያትና በምድር ያለ ሁሉ የርሱ ነው፡፡ መመኪያም በአላህ በቃ፡፡
(ሱረቱ አል-ኒሳዕ 4፡171)

** ስላሴ የተባለውን ጽንሰ ሀሳብ ለመረዳት እጅግ በጣም አስቸጋሪ ከመሆኑም በላይ ጥርጣሬ ሃሳብ በምንም ዓይነት እርስ በእርሱ የማይጣጣምና የሚጋጭ ከመሆኑም በላይ ማንም ሊረዳው የማይችል ሀሳብ ነው፡፡ይህንንም ሃይማnoት ምንድነው? (What is Religion?) በሚል በሊዩ ቶልስቶይ /Leo Tosloy/ በተጻፈው ጽሁፍ ላይ *‹‹አንድ ሰው በአፉ አምላክ አንድም ሶስትም መሆኑን አምናልሁ ሊል ይችላል ነገር ግን ይህንን ማም ሊያምን አይችልም ምክኒያቱም ቃሉ በራሱ ምንም ስሜት አይሰጥም›› * ሲል ተጠቅሷል፡፡

በተጨማሪ በኤች. ኤ. ዋሽንግተን /H.A Washington/ /Jefferson’s Works/ በሚለው መጽሐፍ ገጽ 269-70 ላይ እንዲህ ይላል፡-

*^*‹‹የሦስትዮሽ እምነት ሶስት አንድ አንድ ሶስት የሚለው ሀሳብ ለሰው ልጅ አዕምሮ ከባድና የማይገባ በደፈናው ወደ መረዳት የሚመራ ሀሳብ ነው፡፡ ማንም ኖርማል ሰው የማይረዳው ምንም ዓይነት መልስ የማያገኝለት ሀሳብ ነው፡፡ ለነገሩ እንዴት መልስ ይገኛል መረጃ ለሌለውና ጠንካራ ሀሳብ ያልያዘ ነገር እንዴት መረዳት ይቻላል? ይህ የሶስትዮሽ ጽንሰ ሀሳብ ገብቶኛል የሚል ሰው ቢኖር እንኳ እራሱን እያታለለለ መሆን አለበት›› *^* ሲል ተጠቅሷል፡፡ ሌሎችም በርካታ አስተያየቶች የተሰነዘሩ ሲሆን ሁለቱ ለናሙና ያህል በቂ ይሆናል በማለት ነው፡፡የዚህና መሰል አስተያየቶች የተዘነዘሩት ሙስሊም ካልሆነ አካለት መሆኑ ደግሞ ግርምት የስጭራል

በሌላ በኩል የፈጣሪ አንድነት በርካታ ሃይማቶች የሚጋሩት ሃሳብ ሲሆን በመጽሐፍ ቅዱስ በራሱ የፈጣሪ አንድነት በርካታ ቦታዎች ላይ ተጠቅሶ ይገኛል ፡፡ የተለያ ሃይማቶች በተለይም የአይሁድና የክርስትና ሃይማት መመሪያዎች ይበልጥ የአንድ አምላን አስተምሮ እንደሚያስተምሩ አላህ(ሱ.ወ)በተከበረው ቁርአን ላይ እንዲህ በማለት ይገልጻል፡- ‹‹ የመጽሐፉ ባለቤቶች ሆይ! በእኛና በእናንተ መካከል ትክክል ወደ ኾነች ቃል ኑ፡፡ (እርሷም) አላህን እንጅ ሌላን ላንገዛ፣ በርሱም ምንንም ላናጋራ፣ ከፊላችንም ከፊሉን ከአላህ ሌላ አማልክት አድርጎ ላይይዝ ነው፤ በላቸው፡፡ እምቢ ቢሉም፡- እኛ ሙስሊሞች መኾናችንን መስክሩ በሏቸው፡፡ ››(ሱረቱ አል-ኢምራን 3፡64)

*^* ኢየሱስ አምላክ ወይስ መልዕክተኛ?*^*
መርፊው
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 260
Joined: Sat Oct 15, 2011 4:22 pm

Postby መርፊው » Sat Jan 25, 2014 11:38 pm

ይህ የፈጣሪ ቃል ነው ብላች ሁ የምታምኑ?
አምላክ ይህን ያደርጋል ብላችሁ ታምናላችሁን???

ትንቢተ ሕዝቅኤል ምዕራፍ 23።

1፤ የእግዚአብሔር ቃል ወደ እኔ እንዲህ ሲል መጣ።
2፤ የሰው ልጅ ሆይ፥ የአንዲት እናት ልጆች የሆኑ ሁለት ሴቶች ነበሩ።
3፤ በግብጽም አመነዘሩ፥ በኰረዳነታቸው አመነዘሩ፤ በዚያ ጡቶቻቸው ምዋሸሹ በዚያም የድንግልናቸውን ጡቶች ዳበሱ።
4፤ ስማቸውም የታላቂቱ ኦሖላ የእኅትዋም ኦሖሊባ ነበረ፥ ለእኔም ሆኑ ወንዶችና ሴቶች ልጆችንም ወለዱ። ስማቸውም ኦሖላ ሰማርያ ናት፤ ኦሖሊባ ደግሞ ኢየሩሳሌም ናት።
5፤ ኦሖላም ገለሞተችብኝ፥ ውሽሞችዋንም ጎረቤቶችዋን አሦራውያንን በፍቅር ተከተለቻቸው።
6፤ እነርሱም ሰማያዊ ሐር የለበሱ አለቆችና ሹማምቶች፥ መልከ መልካሞች ጐበዛዝት፥ በፈረስ ላይ የሚቀመጡ ፈረሰኞች ነበሩ።
7፤ ግልሙትናዋንም ከተመረጡ ከአሦር ሰዎች ሁሉ ጋር አደረገች፥ በፍቅር በተከተለቻቸውም ጣዖቶቻቸው ሁሉ ረከሰች።
8፤ በግብጽም የነበረውን ግልሙትናዋን አልተወችም፤ በዚያ በኰረዳነትዋ ጊዜ ከእርስዋ ጋር ተኝተው ነበር፥ የድንግልናዋንም ጡቶች ዳብሰው ነበር፥ ግልሙትናቸውንም አፍስሰውባት ነበር።
9፤ ስለዚህ በፍቅር በተከተለቻቸው በውሽሞችዋ በአሦራውያን እጅ አሳልፌ ሰጠኋት።
10፤ እነርሱም ኅፍረተ ሥጋዋን ገለጡ፤ ወንዶችና ሴቶች ልጆችዋንም ማርከው ወሰዱ፥ እርስዋንም በሰይፍ ገደሉ፤ ፍርድንም ስላደረጉባት በሴቶች መካከል መተረቻ ሆነች።
11፤ እኅትዋም ኦሖሊባ ይህን አየች፤ ሆኖም ከእርስዋ ይልቅ በፍቅር በመከተልዋ ረከሰች፥ ግልሙትናዋም ከእኅትዋ ግልሙትና ይልቅ በዛ።
12፤ አለቆችንና ሹማምቶችን ጎረቤቶችዋን ጌጠኛ ልብስ የለበሱትን በፈረሶች ላይ የሚቀመጡትን ፈረሰኞች፥ ሁሉም መልከ መልካሞችን ጐበዛዝት አሦራውያንን በፍቅር ተከተለቻቸው።
13፤ የረከሰችም እንደ ሆነች አየሁ፥ ሁለቱም አንድ መንገድ ሄደዋል።
14፤ ግልሙትናዋንም አበዛች፤ በቀይ ቀለምም የተሳለችውን የከለዳውያንን ስዕል፥ በናስ ላይ የተሳሉትን ሰዎች አየች።
15፤ በወገባቸው ዝናር የታጠቁ ራሳቸውንም በቀለማዊ መጠምጠሚያ የጠመጠሙ ነበሩ፤ ሁሉም ከተወለዱባት አገር የሆኑትን የከለዳውያንን ልጆች መስለው መሳፍንትን ይመስሉ ነበር።
16፤ ባየቻቸውም ጊዜ በፍቅር ተከተለቻቸው፥ ወደ ከላውዴዎን ምድር ወደ እነርሱ መልእክተኞችን ላከች።
17፤ የባቢሎንም ሰዎች ወደ እርስዋ ፍቅር ወዳለበት መኝታ መጡ በግልሙትናቸውም አረከሱአት፤ እርስዋም ከእነርሱ ጋር ረከሰች ነፍስዋም ከእነርሱ ተለየች።
18፤ ግልሙትናዋንም ገለጠች ኅፍረተ ሥጋዋንም አሳየች፤ ነፍሴም ከእኅትዋ እንደ ተለየች እንዲሁ ነፍሴ ከእርስዋ ተለየች።
19፤ ነገር ግን በግብጽ ምድር የገለሞተችበትን የኰረዳነትዋን ዘመን አስባ ግልሙትናዋን አበዛች።
20፤ ሥጋቸውም እንደ አህዮች ሥጋ ዘራቸውም እንደ ፈረሶች ዘር የሆነውን እነዚያን ምልምሎች በፍቅር ተከተለቻቸው።
21፤ ስለ ኰረዳነትሽ ምክንያት ግብጻውያን ጡቶችሽን በዳበሱ ጊዜ የኰረዳነትሽን ሴሰኝነት አሰብሽ።
22፤ ስለዚህ፥ ኦሖሊባ ሆይ፥ ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል። ነፍስሽ ከእነርሱ የተለየች ውሽሞችሽን አስነሣብሻለሁ፥ በዙሪያሽም በአንቺ ላይ አመጣቸዋለሁ።
23፤ እነርሱም የባቢሎን ሰዎች ከለዳውያንም ሁሉ፥ ፋቁድ፥ ሱሔ፥ ቆዓ፥ ከእነርሱም ጋር አሦራውያን ሁሉ፥ መልከ መልካሞች ጐበዛዝት፥ አለቆችና ሹማምቶች ሁሉ፥ መሳፍንቶችና አማካሪዎች ሁሉ፥ በፈረስ ላይ የተቀመጡ ናቸው።
24፤ በመሣሪያና በሰረገላ በመንኰራኵርም በአሕዛብም ጉባኤ ይመጡብሻል፤ ጋሻና አላባሽ ጋሻ ራስ ቍርም ይዘው በዙሪያሽ ይዘጋጁብሻል፤ ፍርድንም እሰጣቸዋለሁ፥ እንደ ፍርዳቸውም ይፈርዱብሻል።
25፤ ቅንዓቴንም በአንቺ ላይ አደርጋለሁ በመዓትም ያደርጉብሻል፤ አፍንጫሽንና ጆሮሽንም ከአንቺ ይቈርጣሉ፥ ከአንቺም የቀረ በሰይፍ ይወድቃል፤ ወንዶችና ሴቶች ልጆችሽንም ማርከው ይወስዳሉ፥ ከአንቺም የቀረውን እሳት ትበላቸዋለች።
26፤ ልብስሽንም ይገፍፉሻል የክብርሽንም ጌጥ ይወስዳሉ።
27፤ ሴሰኝነትሽንም፥ ከግብጽ ምድር ያወጣሽውን ግልሙትናሽንም ከአንቺ አስቀራለሁ፤ ዓይንሽንም ወደ እነርሱ አታነሺም ግብጽንም ከዚያ ወዲያ አታስቢም።
28፤ ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላልና። እነሆ፥ በጠላሻቸው እጅ፥ ነፍስሽ በተለየቻቸው እጅ አሳልፌ እሰጥሻለሁ፤
29፤ እነርሱም በጥል ያደርጉብሻል፥ የደከምሽበትንም ሁሉ ይወስዳሉ፥ ዕራቁትሽንና ዕርቃንሽን አድርገውም ይተዉሻል፤ የግልሙትናሽም ነውር፥ ሴሰኝነትሽና ግልሙትናሽም ሁሉ ይገለጣል።
30፤ ከአሕዛብ ጋር ስላመነዘርሽ በጣዖቶቻቸውም ስለ ረከስሽ ይህን ያደረጉብሻል።
31፤ በእኅትሽ መንገድ ሄደሻል፤ ስለዚህ ጽዋዋን በእጅሽ እሰጥሻለሁ።
32፤ ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል። የጠለቀውንና የሰፋውን ብዙም የሚይዘውን የእኅትሽን ጽዋ ትጠጪአለሽ፤ መሳቂያና መሳለቂያም ትሆኛለሽ።
33፤ በእኅትሽ በሰማርያ ጽዋ፥ በድንጋጤና በጥፋት ጽዋ፥ በስካርና በውርደት ትሞልያለሽ።
34፤ ትጠጪዋለሽ ትጨልጪውማለሽ ገሉንም ታኝኪዋለሽ ጡትሽንም ትሸነትሪዋለሽ፤ እኔ ተናግሬአለሁና፥ ይላል እግዚአብሔር።
35፤ ስለዚህ ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል። ዘንግተሽኛልና፥ ወደ ኋላሽም ጥለሽኛልና አንቺ ደግሞ ሴሰኝነትሽንና ግልሙትናሽን ተሸከሚ።
36፤ እግዚአብሔርም እንዲህ አለኝ። የሰው ልጅ ሆይ፥ በኦሖላና በኦሖሊባ ትፈርዳለህን? ኃጢአታቸውንም ታስታውቃቸዋለህ?
37፤ አመንዝረዋልና፥ ደምም በእጃቸው አለና፥ ከጣዖቶቻቸውም ጋር አመንዝረዋልና፥ ለእኔም የወለዱአቸውን ልጆቻቸውን መብል እንዲሆኑላቸው በእሳት አሳልፈዋቸዋልና።
38፤ ይህን ደግሞ አድርገውብኛል፤ በዚያ ቀን መቅደሴን አርክሰዋል ሰንበታቴንም ሽረዋል።
39፤ ልጆቻቸውንም ለጣዖቶቻቸው በሠዉ ጊዜ፥ በዚያው ቀን ያረክሱት ዘንድ ወደ መቅደሴ ገቡ፤ እነሆም፥ በቤቴ ውስጥ እንደዚህ አደረጉ።
40፤ ደግሞ መልእክተኛ ወደ ተላከባቸው ከሩቅም ወደሚመጡ ሰዎች ልካችኋል፤ እነሆም መጡ፥ አንቺም ታጠብሽላቸው ዓይኖችሽንም ተኳልሽ ጌጥም አጌጥሽ፤
41፤ በክብር አልጋ ላይ ተቀመጥሽ፥ በፊት ለፊትዋም ማዕድ ተዘጋጅታ ነበር፥ ዕጣኔንና ዘይቴንም አኖርሽባት።
42፤ የደስተኞችም ድምፅ በእርስዋ ዘንድ ነበረ፤ ከብዙም ሰዎች ጉባኤ ጋር ሰካራሞቹ ከምድረ በዳ መጡ፤ በእጃቸው አንበር በራሳቸውም የተዋበ አክሊል አደረጉ።
43፤ እኔም በምንዝር ላረጀችው። አሁን ከእርስዋ ጋር ያመነዝራሉ እርስዋም ከእነርሱ ጋር ታመነዝራለች አልሁ።
44፤ ወደ ጋለሞታም እንደሚገቡ ወደ እርስዋ ገቡ፤ እንዲሁ ይሰስኑ ዘንድ ወደ ኦሖላና ወደ ኦሖሊባ ገቡ።
45፤ ሴቶቹ አመንዝሮች ናቸውና፥ በእጃቸውም ደም አለና ጻጽቃን ሰዎች በአመንዝሮቹና በደም አፍሳሾቹ ሴቶች ላይ በሚፈረደው ፍርድ ይፈርዱባቸዋል።
46፤ ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል። ጉባኤን አመጣባቸዋለሁ፥ ለመበተንና ለመበዝበዝም አሳልፌ አሰጣቸዋለሁ።
47፤ ጉባኤውም በድንጋይ ይወግሩአቸዋል በሰይፋቸውም ይቈርጡአቸዋል፥ ወንዶችና ሴቶች ልጆቻቸውንም ይገድላሉ፥ ቤቶቻቸውንም በእሳት ያቃጥላሉ።
48፤ ሴቶችም ሁሉ እንደ ሴሰኝነታችሁ እንዳይሠሩ ይማሩ ዘንድ ሴሰኝነትን ከምድር ላይ አጠፋለሁ።
49፤ ሴሰኝነታችሁንም በላያችሁ ላይ ይመልሳሉ፥ እናንተም የጣዖቶቻችሁን ኃጢአት ትሸከማላችሁ፤ እኔም ጌታ እግዚአብሔር እንደ ሆንሁ ታውቃላችሁ
መርፊው
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 260
Joined: Sat Oct 15, 2011 4:22 pm

Previous

Return to Warka General

Who is online

Users browsing this forum: No registered users and 0 guests