ሰላም ለሁላችንም ይሁን እህታችንም ማርያም ገንፎ ሰርታ የምታበላና የምታጠነክርሽ ትላክልሽ እያልኩ ( ለምሳሌ እህምምን) :D ወደ ገረመኝ ጉዳይ ቶሎ ልሂድና ቶሎ ልውጣ...
ጥያቄ ነው እንግዲ የዋርካ ጽሁፍ አርትዎት ( አርታዒ) ያስፈልገዋል ማለት ነው..???? ይሄ ማለት እኔ አንድ ጽሁፍ እጽፍና ጽሁፌን እባክህ ለህዝብ ከማቅረቤ በፊት አንብብና ገምግምልኝ እያልኩ ነው የምጽፈው ማለት ነው? :D ...እነ ዚህ አርታውያን ወንድሜ ዋርካ ላይ የሚጽፈውን ሲገመግሙለት ያስከፍሉታል?? ካስከፈሉት እኔ ልጮህ ነው....!!እኔ እዚህ ቁጭ ብዬ ወንድሜ ገባር ህዝቦች በአጸው ዘመን የዘረፉት አንሶ እሱንም ዋርካ ላይ በልጆቻቸው ደሞ ዋሌቱ ትሪፓ ትሪፓፓ ስትደረግ ማየት አልችልም:: :D ጉድ ጉድ ጉድ !! እኔ የማውቀው መጽሀፍ ድርሰት ነበር ሲገመገም ( አርትዎት የሚደረግለት ) እንጂ የዋርካ ቻት እየተገመገመ መጻፉን የሰማሁት ገና ዛሬ ነው:: :lol: ግን ወንድሜ ጋዜጠኛ ስለሆነ ጥራት ያለው ጽሁፍ ለህብረተሰቡ ማቅረብ ስላለበት ቢያስገመግም ግን ክፋት ያለው አይመስለኝም:: ቶሎ ልውጣ ብዬ እዚሁ ቀደዳ ጀመርኩ:: ሰላም አምሹ:: አብደላ እባላለሁ:: :lol:
ከብስራተ ወንጌል ለታሪክና ለቅርስ ብቻውን የቀረ ጋዜጠኛ ካቴድራል ት/ቤት የጋዜጠኝነት ኮርስ የሰጠው ወንድማችን ዲጎኔ እንደጻፈው:
ዋርካ ላይ ጊዜ ስለሚወስድ አርታኢም ስለማያይልኝ እንዳለ ሀሳቤን አቀርባለሁ በተረፈ በስነቃልና ሚዲያ አንዳች ሳላጋንን ነው የምከትበው ::