የግጥም ጥግ የጆሲ ወግ

Topics related to cultures, arts, languages, arts such as humor, music, traditional literary genres of poems, ግጥም ፣ ቅኔ ፣ ተረትና ምሳሌ)

የግጥም ጥግ የጆሲ ወግ

Postby Jossy1 » Sat Nov 09, 2013 8:40 am

ሀብትን ለመሰብሰብ አብዝቶ ሲዳክር
ሰው ጤናውን ያጣል ሰክሮ በንዋይ ፍቅር::
ከዚያ
ለሀብት በሽታ መድሀኒት ለማግኘት
ገንዝቡን ይሰዋል ደዌውን ለማጥፋት::
ሰው
ዛሬን እንደመኖር ለነገ ይጨነቃል
የቅርቡን እረስቶ ሩቁን ያስባል::
በመጨረሻ
እንደማይሞት ሲያስብ ሳይኖርም ይሞታል
የሌለውን ሲመኝ ያገኘውን ያጣል::

ከዳላይ ላማ ንግግር ተወስዶ ወደ ግጥምነት የተቀየረ
09.11.2003 ዶሀ
Freewill
Jossy1
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 215
Joined: Sun Aug 28, 2005 6:37 am
Location: qatar

Postby ቀዳማይ » Sat Nov 09, 2013 3:32 pm

ቀጥልበት ወንድማችን ጥሩ ቅጥም ነች::
ቀዳማይ
ጀማሪ ኮትኳች
ጀማሪ ኮትኳች
 
Posts: 60
Joined: Thu May 09, 2013 6:02 am

Re: የግጥም ጥግ የጆሲ ወግ

Postby ዲጎኔ » Sun Nov 10, 2013 10:09 pm

ሰላም ለሁላችን በተለይ ለገጣሚያን
የሰውን መንፈስ በስነቃል አስተካካይ
በታሪካችን በጥቁር ህዝቦች ጎራ
እጅግ ብዙ ምጥቅ የጥበብን ስራ
መተንተን ይቻላል በተራ በተራ
ምሳሌና ወጉ የአበሻ ህዝቦች
የጥቁር አንበሳ ባህላዊ ቅሪቶች
እጀግ ብዙ አሉ የጥንት ታሪኮች
የነቶሎ ቶሎ ቤት
ግድግዳው ሰንበሌጥ
ሲሮጡ የታጠቁ ሲሮጡ ይፈታል
የ ሀሰት ነዋይ እያደር ይጠፋል
ከሚስም ጠላት ወዳጅ ይሻላል
ሳጠፋ ሲያየኝ ከልብ ይገስጻል
የግፈኛ ስልጣን እንቡዋይ ይመስላል
ዋናውን አጥፍቶ ለጀሌው ይተርፋል


Jossy1 wrote:ሀብትን ለመሰብሰብ አብዝቶ ሲዳክር
ሰው ጤናውን ያጣል ሰክሮ በንዋይ ፍቅር::
ከዚያ
ለሀብት በሽታ መድሀኒት ለማግኘት
ገንዝቡን ይሰዋል ደዌውን ለማጥፋት::
ሰው
ዛሬን እንደመኖር ለነገ ይጨነቃል
የቅርቡን እረስቶ ሩቁን ያስባል::
በመጨረሻ
እንደማይሞት ሲያስብ ሳይኖርም ይሞታል
የሌለውን ሲመኝ ያገኘውን ያጣል::

ከዳላይ ላማ ንግግር ተወስዶ ወደ ግጥምነት የተቀየረ
09.11.2003 ዶሀ
ዲጎኔ
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 4752
Joined: Fri Aug 19, 2005 2:03 am
Location: united states

Postby Jossy1 » Mon Nov 11, 2013 8:04 am

ለጥንቱ ወዳጄ ሰላም ለዲጎኔ
እንደምን ከርመሀል ሰላም አለሁ እኔ
እነሆ
መጣን ከዋርካችን ከጥበብ ጥላ ስር
ግጥምን ልንጽፍ ወግን ልናጫጭር
የእናንተን ልናነብ ለመማር ለማወቅ
ዋርካ እውቀት ሆናን በጥበብ ለመሞቅ
መጣን ገባን አየን
የጥንት ወዳጆቼ ኑና ሰላም በሉን
Freewill
Jossy1
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 215
Joined: Sun Aug 28, 2005 6:37 am
Location: qatar

Postby ምክክር » Mon Nov 11, 2013 9:05 am

Jossy1 wrote:ለጥንቱ ወዳጄ ሰላም ለዲጎኔ
እንደምን ከርመሀል ሰላም አለሁ እኔ
እነሆ
መጣን ከዋርካችን ከጥበብ ጥላ ስር
ግጥምን ልንጽፍ ወግን ልናጫጭር
የእናንተን ልናነብ ለመማር ለማወቅ
ዋርካ እውቀት ሆናን በጥበብ ለመሞቅ
መጣን ገባን አየን
የጥንት ወዳጆቼ ኑና ሰላም በሉን


ሠላም Jossy1 in Z Warka
አከም ጂርታ ኸመይ አለኻ

ለሆደ ገበርዲን ለዲጎኔም ሠላም:
ግጠሙ ግጥም
ጥሞ 'ሚያጣጥም
ግጥም አናጥላላም

ጆሲ
የመጀመሪያዋ ግጥም ደራሲ ማነው?
የመነሻ ነጥብ የሆነዉን ባለቤት ሥም ብቻ ነው የነገርከን ብዬ ነው::
ምክክር
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 326
Joined: Thu Jun 26, 2008 10:10 am
Location: Super Earth

Postby Jossy1 » Mon Nov 11, 2013 9:27 am

ለምክክር

ድንቅዋ አባባል የዳላይ ላማ
በኔ ቀረበች ተገጥማ
Freewill
Jossy1
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 215
Joined: Sun Aug 28, 2005 6:37 am
Location: qatar

Postby ዲጎኔ » Tue Nov 12, 2013 4:36 am

ሰላም በድጋሚ ለሁላችን ይድረስ
በተለይ ለJosy በጥበብ ይገስግስ
ዋርካ አደባባይ የሌለው ግሳንግስ
ከቅንነት ሌላ ወደሰው የማይደርስ
እዚ ዋርካ ላይ ብዙ ሰዎች አጣን
በክፉዎች ስድብ ጥሩዎች ሲለዩን
ምክር ድጋፋቸው አጅግ ጎደለብን
እኔ እንኩዋን በግል የማውቃቸው
ሞኒካና ትምርት የማከብራቸው
ናጁና ሱልጣን ከቶ አረሳቸው
በጣም ተሳሳቱ ዋርካን መራቃቸው
ለባለጌ ብለው እንዲህ መሆናቸው
ሆደገበርዲን ያለው ምክክር
ስምና ወርቁን ስመረምር
የጦቢያዊያን በጎ መዘክር
ወገናዊ ሳይሆኑ በዝርዝር
ይህን ለማይቀበሉ እኔ የምል
ከላይ እንዳልኩ ባህላዊ ብሂል
በጥባጭ ካለ ማን ጥሩ ይጠጣል
በጠማማ ምክር ህብረት ይፈርሳል
ሀቅ ይከሳል እንጂ መች ይወድቃል
እባብ እንዳይነክሰ ሸኮናው ይመታል
ባለጌ ከማሳደግ ማውገዙ ይበልጣል
እውነት የሚከተል ከሁሉም ይልቃል

Jossy1 wrote:ለጥንቱ ወዳጄ ሰላም ለዲጎኔ
እንደምን ከርመሀል ሰላም አለሁ እኔ
እነሆ
መጣን ከዋርካችን ከጥበብ ጥላ ስር
ግጥምን ልንጽፍ ወግን ልናጫጭር
የእናንተን ልናነብ ለመማር ለማወቅ
ዋርካ እውቀት ሆናን በጥበብ ለመሞቅ
መጣን ገባን አየን
የጥንት ወዳጆቼ ኑና ሰላም በሉን
ዲጎኔ
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 4752
Joined: Fri Aug 19, 2005 2:03 am
Location: united states

Postby መራራ » Tue Nov 12, 2013 9:55 am

አልሞተም ወርቅሰው አልሞተም ቃኘው:
ይሄው በዲጎኔ አይኔ እያየው::
ሞቷል አትበሉኝ ወርቅሰው አልሞተም:
ሄዷል አትበሉኝ ወርቅሰው አልሄደም:
አራምባ እና ቆቦን ሁሌም እንዳንረሳ:
ዛሬም በ ዋርካችን ተቀምጧልሳ::
ሀ-ግስ እና ለ-ግስ እረ እነ ሁካይ:
ይህን ግጥም አይተው በህይወት አሉ ወይ? :lol: :lol:
የ ድንቅነሽ ወዳጅ የ ላርዲ ጓደኛ:
የ ሶስት ሺ ዘመን ቃኚ ዘለሰኛ:
ከ ወዲያኛው ማዶ ሁሌም ነኝ የሚለንን:
ግጥም እንድትደፈር ሁሌም ያኑርልን:: :lol: :lol: :lol:


ዲጎኔ wrote:ሰላም በድጋሚ ለሁላችን ይድረስ
በተለይ ለJosy በጥበብ ይገስግስ
ዋርካ አደባባይ የሌለው ግሳንግስ
ከቅንነት ሌላ ወደሰው የማይደርስ
እዚ ዋርካ ላይ ብዙ ሰዎች አጣን
በክፉዎች ስድብ ጥሩዎች ሲለዩን
ምክር ድጋፋቸው አጅግ ጎደለብን
እኔ እንኩዋን በግል የማውቃቸው
ሞኒካና ትምርት የማከብራቸው
ናጁና ሱልጣን ከቶ አረሳቸው
በጣም ተሳሳቱ ዋርካን መራቃቸው
ለባለጌ ብለው እንዲህ መሆናቸው
ሆደገበርዲን ያለው ምክክር
ስምና ወርቁን ስመረምር
የጦቢያዊያን በጎ መዘክር
ወገናዊ ሳይሆኑ በዝርዝር
ይህን ለማይቀበሉ እኔ የምል
ከላይ እንዳልኩ ባህላዊ ብሂል
በጥባጭ ካለ ማን ጥሩ ይጠጣል
በጠማማ ምክር ህብረት ይፈርሳል
ሀቅ ይከሳል እንጂ መች ይወድቃል
እባብ እንዳይነክሰ ሸኮናው ይመታል
ባለጌ ከማሳደግ ማውገዙ ይበልጣል
እውነት የሚከተል ከሁሉም ይልቃል

Jossy1 wrote:ለጥንቱ ወዳጄ ሰላም ለዲጎኔ
እንደምን ከርመሀል ሰላም አለሁ እኔ
እነሆ
መጣን ከዋርካችን ከጥበብ ጥላ ስር
ግጥምን ልንጽፍ ወግን ልናጫጭር
የእናንተን ልናነብ ለመማር ለማወቅ
ዋርካ እውቀት ሆናን በጥበብ ለመሞቅ
መጣን ገባን አየን
የጥንት ወዳጆቼ ኑና ሰላም በሉን
መራራ
ዋና ኮትኳች
ዋና ኮትኳች
 
Posts: 753
Joined: Sat Sep 25, 2004 9:58 am
Location: united states

Postby ዲጎኔ » Wed Nov 13, 2013 1:18 pm

ኡኡታ ጫጫታ ዋርካ ላይ ተሰማ
የገጣሚ ያለህ ጆሮ ያለው ይስማ
መንፈሱ ከመንፈሳችን የሚስማማ
በዚያኛ አምድ ከያኒ ዋናው ቤት
የሀገር ልጆች ሁሉ ተወያየንበት
ፈልገን አመጣን ዋናውን ካለንበት
እዚህ ቤትም ይህው መጥቻለሁ
የግጥም ወዳጄ አትጥፋ ብያለሁ
ጆስዬ ባካህ ና ጥሪ አቀርባለሁ
ባለጌን እርሳ ይማረው እላለሁ
ዲጎኔ
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 4752
Joined: Fri Aug 19, 2005 2:03 am
Location: united states

Postby Jossy1 » Wed Nov 13, 2013 3:25 pm

ዲጎኔ ወዳጄ አረ እኔስ አልጠፋሁ
አለሁ ይኸው መጣሁ
በቻ ከሰሞኑ ከመካ መዲና
ከበዛበት ቦታ የአላህ ቅድስና
ጩኸት ቢበረክት የወገን ሰቆቃ
ዋይታ ድረሱልን መሞት በኛ ይብቃ
ይብቃ ድረሱልን መደፈር መታረድ
መገፋት መበዝበዝ መገዛት መቀፍደድ
ይብቃ ድረሱልን የሚል የወገን መልእክት
ከሳኡዲ ሲሰማ ስቃይ እና ጩኸት
እረፍት መረጋጋት ሰላሙም ጠፋብኝ
ወገን ተረብሾ እኔም ተረበሽኩኝ::
ማድረግ የምችለው አንድ ነገር ብቻ
አቅሜ ሚችለው ከሆነ ችግር መፍቻ

እሱም
በፌስቡክ በትዊተር እንዲሁም በዋርካ
በብእሬ መጮህ ነው ህልማቸው እንዲሳካ::

አለሁ አለሁ እኔማ አለሁ
በወገን ስቃይ ግን ተሰቃየሁ
አቅም ኖሮኝ አቅምም አጣሁ
አለሁ ዲጎኔ አለሁ
ለወገኔ እኖራለሁ
በወገኔ እኖራለሁ::
Freewill
Jossy1
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 215
Joined: Sun Aug 28, 2005 6:37 am
Location: qatar

Postby ምክክር » Wed Nov 20, 2013 9:36 am

በጣም ይመቸኛል ግጥም ሲደረደር:
በቀለም ባይነቱ በፊደል ሲዋቀር:
ጉሮሮ ላይ ገብቶ ተሰክቶ እንዳይቀር:
ኩልል ብሎ ይፍሰስ በሰምና ወርቅ:
እያመዛዘነ አስታሞ እንዲያርቅ:
ፍቺ ትርጉሙንም ያርቅቅ ያሳብቅ::
ቅቅ
ምክክር
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 326
Joined: Thu Jun 26, 2008 10:10 am
Location: Super Earth

Postby Jossy1 » Wed Nov 20, 2013 3:18 pm

ግጥም ሲገጣጠም
ግጥምጥም ግጥም
ሊቆርጥ የጥበብ ጥም
በሆሄያት ተስሎ በቃላቶች ደምቆ
ስጋና ደም ሊለብስ ከህሊና ፈልቆ
ጥበብ ግጥም ሲሆን በኪነት ሲገለፅ
በከያኒው ክህሎት ከቃላት ሲታነፅ
ታንፆ ነፍስ ሲሆን መልእክትን ተላብሶ
የውስጠትን ስቃይ ሊያወጣ አስተንፍሶ
ትውልድን ሊሻገር ህያው ሲሆን በቃል
በቃላት ለመግለፅ እጅግ ያስቸግራል::
Freewill
Jossy1
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 215
Joined: Sun Aug 28, 2005 6:37 am
Location: qatar

Postby ዲጎኔ » Thu Nov 21, 2013 1:12 am

ይድረስ ለገጣሚያን
የዋርካ በሳል ከያኒያን
ስነቃሉን ከሀሳብ አዋህደው
ሰምና ወርቁን አስማምተው
ዋርካን ህይወት ለሰጧት
እንዳንርቃት ላደረጉዋት
እጥፍ ምስጋናዬ ይድረሳቸው
ቀጣዩ ትውልድ ይከተላቸው
የጦቢያ አምላክ አይለያቸው
የሰሞኑ ጩህታችን ተሰምቶ
የወገኖች እንባ ዋጋ አግኝቶ
በግፈኞች ላይ ብይን ሰጥቶ
ለማየት ያብቃን ፍርዳቸውን
ፈጣሪ ይክፈል የእጃቸውን
ላረመኔ አረቦች ምሳቸውን
ዲጎኔ
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 4752
Joined: Fri Aug 19, 2005 2:03 am
Location: united states

Postby ወርቅነች » Thu Nov 21, 2013 3:10 am

ደከመኝ በረደኝ በቃኝ መረረኝ የማይለው የ 2013 እጩ ዋካዊው ዲጎኔ የተገጠመ

ሁሉም የዋርካ ልጅ ነኝ ብሎ ሲፎክር
የትኛውን ዋርካዊ እንመን ሁሉም የሚቀባጥር
ግጥሙን ገጣጥሞ ማንንም የማያፍር :lol:
ዲጎኔን አገኘን እውነት የሚናገር
ሁሉንም አክብሮ ክብዮም ሳይቀር
ትለሀለች የቸርችል ጎድናዋ ጀሚላ ደህና ውለህ እደር :lol: :lol: :lol:
ወርቅነች
ዋና ኮትኳች
ዋና ኮትኳች
 
Posts: 967
Joined: Sun Oct 03, 2010 10:05 am

Postby ምክክር » Sun Nov 24, 2013 7:34 am

ተስፋ

ተስፋዉ የሟሸሸ:
ወኔዉን የሸና:
ዛሬንም አልኖረም
ነገ የለምና::

ተስፋዬ ለምልሚ:
ያላንቺ አልኖርም
ዘንድሮም ክረሚ:
መጪዉንም ጊዜ
እንደ ሙሽራዬ ሳትሽኮረመሚ:
በተስፋ ብርሃንሽ:
ብሪ ተዝገምገሚ:
ደመቅሽ አበባዬን
በአጀብ አዚሚ::

በጨለማ ቤት ዉስጥ
ብርሃን በሌለበት:
የተስፋ ጭላንጭል
ሰርጎ እንድታይበት:
ከልብህ ላይ ጨረር
ጭረህ ልቀቅበት::

ለተስፈኞች::
ምክክር
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 326
Joined: Thu Jun 26, 2008 10:10 am
Location: Super Earth

Next

Return to Warka Culture and Literature - ዋርካ ባህልና ሥነ ጽሑፍ

Who is online

Users browsing this forum: No registered users and 2 guests