የጥበብ እልፍኝ::

Topics related to cultures, arts, languages, arts such as humor, music, traditional literary genres of poems, ግጥም ፣ ቅኔ ፣ ተረትና ምሳሌ)

Postby varka911 » Thu Dec 12, 2013 10:31 pm

ቡቺ ወንድማችን ይህን ግጥም እንደጉድ አዘነብክብን እኮ:: ይቺም ግጥም ናት ግን? :D

ስማ እንጂ የእፍታ ቅጾች አሉህ እንዴ? ካሉህ አንዳንድ ነገር አካፍለን ወንድማችን:: በተለይ የስንዱ አበበ ካለህ ... አመሰግናለሁ::

ቦቹ wrote:ያገረሸ ፍቅር

የሰማይ
አሞራ
ላዋይህ
ችግሬን፡፡
ብረር ሒድ ንገራት”.
ከትልቁ
ዛፍ
ሥር፣
ዱሮ በልጅነት
ከተጫወትንበት
ከትልቁ ዛፍ ሥር አታጣትም ፍቅሬን
ብረር
ሒድ ንገራት፣
ንገር መናፈቄን፣

(ገብረ ክርስቶስ ደስታ፣ 1998)
Get your second chance On my First Aid!
varka911
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 101
Joined: Tue Oct 22, 2013 2:30 pm

Postby ቦቹ » Thu Dec 12, 2013 11:10 pm

ሰላም 911 እህሳ እንዴት ይዞሃል? ግጥሞቹን እንደምታየው እንደ ሀምሌ ዝናብ ማቆሚያም የላቸውም የጠየከኝ ግን የለኝም ቢሆንም ቢሆንም እንዳሉት ሀምሳአለቃ ገብሩ ፈለግ ፈለግ አድርጌ ላገኘው እችላለው:: ከላይ ያሰፈርኩት ግጥም የገብረ ክርስቶስ ደስታ ሲሆን አጻጻፉ ይለይ እንጂ ድንቅ የሆነ ግጥም ነው:: እጥር ምጥን ያለች ስጋን አልፋ ነብስን የምታስደስት ነገር ነች:: አንድ ስለ ግጥም የሚያወራ መጽሀፍ አለኝ አጻጻፉና አይነታቸውን ስለሚጠቅስ እዚሁ እከትበዋለው:: ለዛሬ ግን ባዶ እጄን እንዳልመለስ እንሆ በረከተ::

.........አፍ ከሆድ ይሰፋል.........
ይናገራል እንጂ ውስጡ ቂም አይ'ዝም
አፉ ነው ባለጌ ሆዱ ነገር የለም
ይሉታል ሲክቡት ሲያሞጋግሱት
የአፉን አዳፋ በሆዱ ሲያብሱት
ወትሮም...
የሚያስለቅሰን
የሚያስነክሰን
ወግቶ የሚያደማን አድምቶ ሚገድለን
"ደጉ ሆዱ" ሳይሆን አፉ ነው የፈጀን::

በዘላለም ታደሰ> የግጥም እፍታ
ያ ተፈሪ - በንቲ!
ጀበሲ ኦፍኤጊ!
ኢትዮጵያን ነመገንቲ!
ተፈሪ በንቲ!


ኢጆሌ! ወረ አድአ
ቦቹ
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 357
Joined: Fri Dec 31, 2004 1:26 am

Postby varka911 » Thu Dec 12, 2013 11:22 pm

ያዝ እንግዲህ: እኛም ግጥም እንዲህ እናነባለን :lol:

ሙሌን እያመሰገንን ... እንሆ በረከት :wink:

የባለቅኔው ምህላ!

የጎደለኝን ሳላውቀው የጠፋኝን ሳልረዳ
እንደተለኮስኩ እንደተጋፈጥኩ
አለሁ…..
ሳንጃ ባፈሙዝ ተቀላቅዬ ስመሻለቅ
በቁሜ እንደተራዳ…..
ልንገብገብ እንጂ ልቃጠል
የከርሞ ሰው እስኪለኝ….
ክፉ ክፉ…
ጠፉ እኪመነጠር
አላውቅበት መመሳሰሉን….
አይሆንልኝ ቆርጦ መቀጠል
አልችልበት ደፈጣ….
እንደቆላ እባብ በደረት እየተሳቡ ማነጣጠር
መቼም ያልተብራራልኝ
ምንጊዜም ያልገራልኝ
ይሄ ምስጢር የሚሉት ሰጠር ነው
በጠዋት በማታ ያልጠረጠርነው
ነምን ተዳዬ ያጠርነው!
የማይሰፈር ስለካ
ከማይቀመስ
ስፎካከር
እሰጣ ገባ ስጎሰጥ
ጉንጭ አልፋ
ስከራከር
እየመሸ እየነጋብኝ
ዓይኔ እያየ
ዘጋብኝ!
አታደናክረኝ…
ስቼ ተረስቼ
ተሰንክዬ እንዳልረግብ
አፋፋኝ በእቅፍህ ሙቀት
አውጣኝ ከሰንበት ስደት
ሰውረኝ “ከነይ ነይ” በቀት
ያዝልኝ አዛን…..
ያዝልኝ በጠበሉ እዛው
ከነጀናዛው…
ያዝልኝ እዛው በርቀት
ምንም ይሁን….
ምንም ይሁን ምንም ምንም
የፍቅር ሽልማቱን
በሰላም ካላጎናጸፈ
እንኳን ለዘለዓለም ዓለም
ላፍታ ለእፍታም አይታመንም
ጌታ ሆይ…
ቃለህይወትህን አሰማኝ
በመላእክት ዝማሬ አጅበህ
ፅርሓ አርያምን አሳየኝ
በህያዋን ክብር
በትሃን ስብሃት ተከበህ!
ምላሴን ኩን አድርገህ…
አጣፍጥልኝ ሁለመናዬን
ለምለም ነው ብዬ
ከማንም ጋር ስዳይ ውዬ
እንደኣባያ ሥጵር እንዳልነጭ
ምሬሃለው በለኝ በድንግልህ…..
ዘላለማዊነት….
ከምንቒ በውስጤ እንዲመነጭ!
መቼም ቢሆን ልጅ ያላባቱ
ቁምጣው እንጂ መች ጉልበቱ
ስሜቱ እንጂ… መች ጉልበቱ
ስሜቱ እንጂ መች ምጥባቱ……
አንድዬ
ቤት ለእንግዳ በለኝ በማምላክ
ቤት እንቦሳ እንድል በምስራቅ በር
ከጥሬ ዱለት አላለፈም
የኔ ያልኩት ምላስ ሰንበር
ጥም ለቆብኛል በጠና
አቃጥሎኛል የዕምነት ራብ
ቀላቅለኝ ከብሉይ ማህቶት
አቅርበኝ ወዳንተ ምኩራብ….
ጠብቀኝ ከማላውቀው
አውጣኝ ከፍዳ ናዳ..
መልዓከ ሞት ንፍሴን እንዳይነጥቀኝ
ሳልታጠብ ሳልታጠን…
ቦዥ ሳልሰናዳ…
ስደት ንዴት ሰለቸኝ
አጎጠኝ የኑሮ ሸክሙ
አስረዳኝ
በሃ ግእዝ ሁ ካእብ
አቦጊዳ ሄውዞ….
በመልእክተ ዮሃንስ…
ሃዋርያ ወልደዘብዲዮስ…እዜንወክሙ
ገላግለኝ ከስጋት ስጋት
ከሸክላ ሸክላ መላ….
አንተ እንጂ ማን አለኝ ሌላ
አንተ እንጂ ከዚህ በኋላ!
የንጋት አጥቢያ ጎህ መቅደድ
በኔ መላ እየመሰለኝ
ስንት ዘመን አንጠራውዞ
ስንት ወቅት አብሰለሰለኝ
ስሉዝ ባዛውር
ዕድሜ ሰጥቶ..እያገላበጠ ጠብሶ
በቃህ ሲለኝ ነው መሰለኝ
አበሰለኝ!
ክብር ለሱ..አው በሰልኩ
ጥንት ጥንት በልጅነት የተማርኩትን
ያመንኩትን የታመንኩትን
ከለስኩ…..
ክፉ መሸቴን ምኞቴን ኮለስኩ
ዘንጌን ምርዜን ይዠ
የልቤን ሸለፈት ገረዝኩ….
ሃሌሉያን ቶበትኩ…አማተብኩ….
የጎጆዬን ቀዳዳ ወተፍኩ
ጎታ ጎተራዬን መረግኩ
ስንሃት ለእግዚሃብሄር ብዬ…
ያለፍውን በምስጋና አሳረኩ!
ዝም ብዬ ስቆዝም
ዝም ያልኩ የምመስል ዘገምተኛ
የዱዳ ስሞተኛ….
ሳልናገር ሳልጋገር
እ…የሚለኝ ሃገር..
ነክህን ነው እንጂ እንግዲያ
የምን ወክ እንዲያ ወክ እንዲያ
የምን ወክ እንዲህ…ወክ'ንዲህ
በብርዕ በቀሰም
በወርቅ በሰም…..
በአዲስ ራዕይ…በልዩ ምእራፍ
እንግዲህ ዘራፍ….
እናቴ ጽዮን
ወንዜ ጊዮን
ወፌ ከራዲዮን….
እህና…አዎና!
በቀኙ…አልባረከ
በግራው አልማረከ
ምን ያደርጋል እንቶ ፈንቶ
ትርኪ ምርኪ በተረከ፡፡
Get your second chance On my First Aid!
varka911
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 101
Joined: Tue Oct 22, 2013 2:30 pm

Postby ቦቹ » Thu Dec 12, 2013 11:37 pm

ሀምሣ እግር

የእሁድ ጧት ፀሀይ
የጀርባዬ ሲሳይ
ስትዳስሰኝ
ደስ... ደስ እያለኝ
እልም ...እልም ሲለኝ፣
አንድ የሚድህ ጭቃ
እግሬ ላይ ወድቃ።
እኔም ተገርሜ መች እንዲህ ላበቃ ?
ያልገረመው እሱ በዚያው ፈሰሰ' ሱ
መንገዱን ሲቀልስ
እኔ ማለት ጭስስ።
እኮ እንዴት ቢደፍረኝ ?
«ይቅርታ» ሳይለኝ
ብጨፈላልቀው
ከአጠገቤ አልራቀው።
ነካ ... ነካ በእንጨት
ገልበጥ አደረኩት
(ትንሽ እንደመቅጣት)
ሊነሳ ሲተናነቅ
እኔ ሳቅ በሳቅ።
- - - - - - - -
ግን የኋላ ኋላ ... ወደማታ
ጀንበር ከንፈሯን ስትሰበስብ በለዘብታ
እያሰላሰልሁኝ የጧቱን ሁኔታ
በጣሙን ተከዝኩ
ለዚያ ጭቃ አለቀስኩ።
ሃምሳ እግር እያለው
ቆሞ ለማያውቀው
ድኾ ለሚኖረው።

በደበበ ሠይፉ
ያ ተፈሪ - በንቲ!
ጀበሲ ኦፍኤጊ!
ኢትዮጵያን ነመገንቲ!
ተፈሪ በንቲ!


ኢጆሌ! ወረ አድአ
ቦቹ
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 357
Joined: Fri Dec 31, 2004 1:26 am

Postby varka911 » Fri Dec 13, 2013 12:00 am

የቀረንን እንጫወት

ተኩሰን ብንስትም ሞትን ፈርተን ግን ነፍስ አንሰስትም
ህልም ባንከስትም ራዕይ አለንና አንወሰልትም
ቢያንስ ሰዉ ነንና ሰዉ እነወዳለን
እንዳመጣጡም እናስተናግዳለን
ምድር ከተፈጠረ ምስጢር ከተቋጠረ
እስካሁን እስካለንበት
ከድህነታችን በቀር እኛነታችን
ሰዉፊት የማያስቀርብ ምንም እንከን የለበት
ደማችን ዉስጥ ኢትዮጵያዊነት አለበት……………………

    ባለቅኔው ሙሌ
Get your second chance On my First Aid!
varka911
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 101
Joined: Tue Oct 22, 2013 2:30 pm

Postby ፕላዞግ » Fri Dec 13, 2013 6:43 am

ቡቺ በርታልን!
ፕላዞግ
አዲስ
አዲስ
 
Posts: 38
Joined: Sat Dec 06, 2008 7:21 pm

Postby ቦቹ » Fri Dec 13, 2013 3:08 pm

ሰላም የዚ ቤት ተሳታፊዎች:: ፕላዛግ እናመሰግናለን 911 ደግሞ ምርጥ የሆነ ግጥም ነው ያካፈልከን:: የአማርኛ መጽሀፎች በpdf ያለው ሰውም እዚ ሼር ቢያደርግ በደስታ እንቀበላለን:: ይቀጥላል::

ድምጽ አልባ ፊደላት

ፀጉሩን አንጨብሮ ፂሙን አጎፍሮ
ጥግ ተቀምጦ ለሚታየኝ ወጣት
ሂድና ታዘዘው ስጠው አንድ ድራፍት
ቅዳለት ደብል ጂን ሃሳቡን ይርሳበት
በፂሙ መጎፈር በፀጉሩ መንጨብረር
ቁጥር ፈታ በሚል በግንባሩ መስመር
ይታየኛል ቋንቋ ይታየኛል ነገር
እዛም ከጨለማው ብቸኝነት ውጣት
ሲጋራዋን ይዛ ለቆመችው ወጣት
ሂድና ታዘዛት የሚጠጣ ስጣት
ምጋ በተፋችው በጭሶቹ መሃል
ሴትነት ሲበደል እህትነት ሲጣል
እናትነት ሲጎድል
ይታየኛል ቋንቋ ይታየኛል ፊደል።

በኤፍሬም ስዩም
ያ ተፈሪ - በንቲ!
ጀበሲ ኦፍኤጊ!
ኢትዮጵያን ነመገንቲ!
ተፈሪ በንቲ!


ኢጆሌ! ወረ አድአ
ቦቹ
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 357
Joined: Fri Dec 31, 2004 1:26 am

Postby ቦቹ » Fri Dec 13, 2013 3:15 pm

ጠላቴን ስመርቅ

በስልጣን ከፍ ከፍ
በዝና ከፍ ከፍ
በሀብትም ከፍ ከፍ
ወደላይ ከፍ ከፍ
ከፍ ከፍ.... ከፍ ከፍ
ከዛ የወደቅህ ዕለት አጥንትህ እንዳይተርፍ::

ገጣሚ ታገል ሰይፉ
ያ ተፈሪ - በንቲ!
ጀበሲ ኦፍኤጊ!
ኢትዮጵያን ነመገንቲ!
ተፈሪ በንቲ!


ኢጆሌ! ወረ አድአ
ቦቹ
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 357
Joined: Fri Dec 31, 2004 1:26 am

Postby ቦቹ » Fri Dec 13, 2013 7:56 pm

ጠብቄሽ ነበረ

መንፈሴን አንጽቼ
ገላዬን አጥርቼ
አበባ አሳብቤ
አዱኛ ሰብስቤ
ጠብቄሽ ነበረ፤
ብትቀሪ ጊዜ፣
መንፈሴን አሳደፍኩ
ገላዬን አጎደፍኩ
አበባው ደረቀ
አዱኛው አለቀ፤
ብትቀሪ ጊዜ፣
የጣልኩብሽ ተስፋ
እኔን ይዞ ጠፋ፡፡
(ደበበ ሰይፉ፣)
ያ ተፈሪ - በንቲ!
ጀበሲ ኦፍኤጊ!
ኢትዮጵያን ነመገንቲ!
ተፈሪ በንቲ!


ኢጆሌ! ወረ አድአ
ቦቹ
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 357
Joined: Fri Dec 31, 2004 1:26 am

Postby varka911 » Sat Dec 14, 2013 1:16 pm

ጤና ይስጥልኝ ለባለ አምዱና ወንድማችን ቡቺ እንዲውም ለቤቱ ታዳሚያን የሆናችሁ የጥበብ (የቅርብም የሩቅም) ቤተሰቦች :D

ደግነትና ክፋት

ኣንድ ሰው ነበረ ቅንነትን ወዳድ፤
ለሁሉ ማዘንን ኣድርጎ እንደ ልማድ፤
ይኖር የነበረ ነቅቶ እንደዘበኛ፤
ደግ ስራ ለመስራት ልቦናው ሳይተኛ፡፡

ኣንድ ቀን ማለዳ ተነስቶ ሲሄድ፤
እባብ ወድቆ ኣገኘ ከማኸል መንገድ፤
እመዳይ ጥሎበት ውርጭ ኣቆራምዶት፤
ዓስራ ኣምስት ደቂቃ የቀረው ሊሞት፡፡

ሰውዮውም ኣዝኖ ይህን በማየት፤
ከመሬት ኣንስቶ በጁ ጨብጦት፤
ከቤቱ ገባና በድኑን እባብ፤
ዘርግቶ ኣስቀመጠው ምድጃ ኣጠገብ፡፡

እሳት እየሞቀ ጥቂት እንዳቆዬው፤
እጥፍ ዘርጋ እያለ ሲንቀሳቀስ ኣየው፡፡

ሁለንተናው ሞቆ ሕይወት ሲሰማው፤
ተንኮልና ቁጣ በኣንድነት ሆነው፤
የተፈጥሮው ክፋት በልቦናው መጥቶ፤
የሚነክሰው ሲሻ ምላሱን ኣውጥቶ፤
ሞቶ የነበረ ያ በድን ሬሳ፤
ያዳነውን ሊነድፍ ራሱን ኣነሳ፡፡

ሰውዬውም ኣይቶ ይህን ኣኳሃን፤
በሰራው ደግነት ኣዘነ በውን ፤
ምንም ክፋት ለሱ ገንዘቡ ባይሆን፤
ደጉን ክፉ ኣድራጊ የተገባ ቁጣ፤
እንደ እሳት ተፋጅቶ በልቡ ላይ መጣ፤
መጥረቢያ ኣነሳና አባቡን ቢለው ፤
ከኣራት ላይ ቆርጦ በጣጥሶ ጣለው፡፡

ሰው ድግ ሲውልለት እባብ እየከዳ፤
በደግ ኣድራጊው ላይ መርዙን ኣሰናዳ፤
ክፉም ሰው እንደዚህ የክፋቱ ክፋት፤
ደግ የዋለለትን ያስባል ለማጥፋት፤
ተንኮሉም ባሰበው መንገድ መሄድ ትቶ፤
የገዛ ጥፋቱን ያመጣል ጎትቶ፡፡

ተጻፈ በከበደ ሚካኤል (ብርሃነ ህሊና)
ለዋርካ ቀረበ በ911
ይሆን ዘንድ መታሰቢያነቱ ለገቢረእባብ

Get your second chance On my First Aid!
varka911
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 101
Joined: Tue Oct 22, 2013 2:30 pm

Postby ቦቹ » Sat Dec 14, 2013 8:47 pm

ቅዳሜን ከኛ ጋር ይባል ነበር ድሮ ..........ዛሬ ቅዳሜ ነው ተደብራችሁ እንዳትውሉ በ1962 የተጻፈውና ለብዙ አመታት አነጋጋሪ ሆኖ የቆየውን አደፍርስ የተሰኘውን መጽሀፍ ይዠላችሁ ቀርቤያለው:: መልካም ንባብ::

አደፍርስ

ከዳኛቸው ወርቁ

እንሆ በረከት :lol: http://upload.wikimedia.org/wikipedia/c ... 24-3mb.pdf
ያ ተፈሪ - በንቲ!
ጀበሲ ኦፍኤጊ!
ኢትዮጵያን ነመገንቲ!
ተፈሪ በንቲ!


ኢጆሌ! ወረ አድአ
ቦቹ
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 357
Joined: Fri Dec 31, 2004 1:26 am

Postby መርከቡ » Sun Dec 15, 2013 2:15 pm

ድንቅ ቤት ነው እናመሰግናለን ቀጥሉበት
መርከቡ
ጀማሪ ኮትኳች
ጀማሪ ኮትኳች
 
Posts: 66
Joined: Sat Oct 11, 2003 7:41 am

Postby varka911 » Mon Dec 16, 2013 1:25 am

እንደተለመደው በጥልቀቱም በርዝመቱም ወደር የሌለው የሙሌን ግቅኔ (aka ግጥማዊ ቅኔ) ጀባ ብያለሁ ....

እውነት ከመንበርህ የለህማ!
-------------------------------
ምነዋ መንግሰተ ሰማይ! የምህረትሽ ቀን ራቀ?
ምነው ትንግርትሽ ረቀቀ ?
ምነው ኪዳንሽ ታጠፈ … ወዝሽ ወዘናሽ ነጠፈ?
እንደ ዳጉሳ ድፍድፍ … ላቦትሽ ተንጠፈጠፈ
... አሳርሽ ጠሎ አሰፈፈ
ምነው እርሾው ተማጠጠ …. ጎታው ጎተራው ታጠጠ
ረሀብ ላንቃው ፈጠጠ….ያዳም ልጅ አፅሙ ገጠጠ
ምነው ጭር አለ ቀየው! ሀሩር ነዲዱ በረታ
ኮርማው ጥማዱ ተረታ
ምነው ነበልባሉ አየለ … ማሳው ተንቀለቀለ
ነቀለ ሞፈር ሰቀለ ተግድራ ደቀለ
ምነው ምድር ጨነገፈች ዝላ ተርገፈገፈች?
ካስማ እንደተደገፈች ምነው ተሳታብብ ረገፈች?
ምነው የናት ጡት ደረቀ ... አራስ ልጅ ተስረቀረቀ
ምነው አንጀቱ ታለበ … በውኑ ተበለበ
ኮሶ ስንብቱን ለለበ
ምነው ወላድ ተንሰለሰለ … ልሳነ ቃሉ ሰለለ
በቁሙ ከስሞ ከሰለ
አቤት የርግማን ቁርሾ
በንጣይ እርሾ መነሾ!
ምነው ላይፀድቅ በቀለ!
የሰው ልጅ ዋጋ ቀለለ
ትቢያ አፈር ተቀላቀለ
ሆድና ጀርባው ተጣብቆ አንጀቱ በራብ ተሰብቆ
እንደፈረሰ ክራር ቅኝት ሰርቅ እንዳነቀው ድብኝት
ወለሰ! ስልቱ ስለቱ
ሰው
ያ ሰው ጠንካራው ብረቱ
የጥንት የጥዋት የመሰረቱ
ውሳኔው ተርመጥምጦ
ተፈጥርቆ ተዳምጦ
ተሞዥርጎ ተሸምጥጦ
ምነው ጓሽቶ ሆመጠጠ
እንደበሬ ጨው ሆረጠ
ባፍላው ተዝለፍልፎ አረጠ፡፡
እንደ መወክል አጎዛ በችንካር ተገድግዶ
ይግባኝ እንዳይል ታግዶ
እንደ ወይራ ፍልጥ ተማግዶ
ምነው ኩክ ብሎ ሳይነቃ … ምነው ሳይጠረቃ መከከ
በስሎ ሳይሰላ ደከከ
ተፈጥሮ ፊቱን ጨፍግጎ
እንደግራዋስር መርግጎ
ሁዳዱን እያነደደ
አቤት ባዩን እያሳደደ
እንደ ግራ ግመሬ … በነፍር ጥፍሩ እየለቀመ
የረጨነውን እየቃመ
ጉልማችንን ሲያመክነው
ወረታችንን ሲያባክነው
እኮ ማንን ልንኮንን ነው?
የመቅሰፍት ደመና ሰሮ … ሽቅብ ጠቅሶ ሲያርመሰምስ
እንደወረግ ተደርምሶ እያንቃቃ እኛን ሲያምስ
ወገብ ከፍሎ ደረት ገምሶ አቅም ሲከላን አቅምሶ
እኮ እስከመቸ እግዚኦትነ
እኮ እስከመቸ ኪራራይሶ?
የቀንጨለማ ሲወረን እህል ሸማኔው ደውሮ ለጆቢራ ሲወረውረን
አይቀጡ ቅጣት ቀጥቶ ቀሪ ወሬ ነጋሪ የሚያሳጣን
እኮ ምን በድለን ምን አጥፍተን ምን በወጣን?
የምን ቅጥት ነው ይሄ ቀጥፎ እንደተያዘ ጩልፋት
አርሰው አደፍርሰው በበሉ የምን የራብ ቱርፋት
ከንቱ ውእቱ ልፋት፡፡
እኮ እንደ ኖህ ዘመን ንፍር ውሃ ዘር ሳይተኩ ታክቶ መጥፋት!
ምነው ዲበኩሉ ቤዛ አለም
ጎህ ቀዶ በቀን መጨለም?
በጠኔ ርዶ መስለምለም
እኮ ያንጀትን ባንጀት መፋለም?
ምነው? አዛውንቱ በየጉድባው
ጋሜው ድምድሙ ኮበሌው … በየጥጉ በየደረባው
ወድቆ ደርቆ ሲነፈራ
ምነው ተፈጥሮስ ጡር አትፈራ?
ምን ይሉታል ይሄን ብይን አንቀፅ ገልፆ ሳያጣቅስ
ምን ይሉታል ይሄነን ፍርድ
እንዲህ ያለ ጉድ አለ እንዴ?
እግዜር ወንዱ እግዜር መንዴ!
ደረቅ ጡት እየጠባን ቁረንጮ ስንገተግት
ከመንግስተ ሰማይ የምህረት ግት
ምነው የማርያም ልጅ የስርየት ቀንህ ራቀ
ምነው ታምርህ ረቀቀ
በየጥሻው ተወትፈን እንደተምች ስንረፈረፍ
ቅኔ በበቀቀን ሲዘረፍ
አቀርቅረን ስናንቋርር
ቅሪታችንን ስናንቃርር
እንደ ቀላጤ አከንባሎ ቁልቁል ባፍጢም ተተክለን
በእርኩስ አመዳይ ተበክለን
እንዲህ የትም ስንቀር እያየህ ዝም ካልክማ
እውነት … እውነት ከመንበርህ የለህማ!
እንደ ሰባራ ቅል ደቀን
ድበን በራብ ተደቅድቀን
እርሻው ማረሻው ሲከዳ … ሰማይ መሬቱ ሲያብል
እያየህ ዝም ካልከኝ …. እኔስ እንደሌላው የለህም ብል
ምንተዳየ ብትፈርድብኝ መቸም አሽተህ አትቅመኝ እንደውልብኝ
ናዳ እንደሚጥል ጫላዳ ድርቅ ሲሳለቅብን
እየነዳ እያነደደ የገሞራ ድኝ ሲለቅብን
እያየህ ዝም ካልክማ …
እውነት አውነት ከመንበርህ የለህማ!
ጀንበር ትንታጓ ሰብ አለሙን ስትፈጀው
አብ ወልድህ ካልባጀን
ድርሳን ትንቢትህ ካልዋጀን
አንተስ ምንህ መለኮት እኔስ ለምን ያንተ ባሪያ
ሆዴን ሁዳዴን ላምልክ እንጅ ትንሳኤ እንደሌለው እሪያ
ያንተን ጉድማ አየሁት
ያንተን ጉድልማ ለየሁት
ማረኝ ሲሉት የሚመር የማይታደግ አላልክም
ወትሮም የተማረ ቄስ እንጅ የሰው ልጅ መላክ አይልክም
ለካ ሲያጋልጥ ይቆምጣል … ወራት ሲጥል ይከፋል
እንደ አመለ ጉድጓድ እህል ሞት በክቶ ይከረፋል
ለካስ ሰው መሆን እዳ ነው
ለካስ ሰውነት ባዳ ነው
እህል ውሃ ቢያደነድነው
ሲያጣ ሲነጣ በድን ነው፡፡
የኛስ ይሁን እንዳሻው ለእጥፍ ፈተና ከፈጠርከን
ለፍታችሁ ተፍታችሁ ኑ ካልከን
ለቀብር አፈር ከወጠንከን
ግን ፡- ግን ብላቴኖች ምን በደሉ
የማንን አደራ በልተው የማነን አማና አጎደሉ
እንብርታቸው ያላረረ
አጥንታቸው ያልከረረ
ሰማይ በቀል እንደቋጠረ
እጣቸውን እየመጠረ
መንገዳቸውን በእሾህ እያጠረ
እንደ ደራሽ ውሃ አግተልትሎ
በራብ አኮርማጅ ተልትሎ
ከእናት እቅፍ በግፍ ነጥቆ
ሲሰልፍብን ባጭር ታጥቆ
እያየህ ዝም ካልክማ
እውነት እውነት ከመንበርህ የለህማ!
እንደ ታዛ ስር ሰንሰል አሰልስሎ እያበሰበሰ
እንደ ሙሬ እየጠረገ እያጋበሰ
እንደ ሙሬ እየጠረገ … እያጋበሰ
የዘጸዓት ትንቢቶ ደርሶ ሰብ ዓለም ከል ከለበሰ
በማን ሊዳኝ ነው ቅጣቱ የሰው ዘር አንዲት ቅንጣቱ
ያባወራ ባላውራጣቱ
እንደ በልግ አውድማ ነዶ … ምድር ለቅልቆ ከምሮ
ነፍስ ከእስትንፋስ ነጥሎ … ሲኦል እቶን ውስጥ ሞጅሮ
በነበልባል መንሽ እየዘራ በረሀብ አራገበው
ሰው እርጥቡን አንገበገበው
ነፍስ ይማር እርካቡ ረገበ
ቀብርም አስከሬን ጠገበ
ፀሀፊም ድርሳን ዘገበ፡፡
ጥንብ አንሳን ግብር ጠርቶ በራሪ ጋር ይወዳጅበት
ስለት እንደዋጀበት እያጋፈረ ይባጅበት
ወትሮም የሞት ምሬትን ያልቀመሰ የራብ እሳት አይዋጅብበት
እንዲህ አይንን ጡር እያስከፈለ
እንደ በቆሎ እሸት እየጠበሰ እየፈለፈለ
ባይበላውም ያባለው!
መቸም ተጠቀም አላለው
አይ ወልዴ አባ ግድ የለው!
በየጥሻው ተወትፈን እንደተምች ስንረፈረፍ
ቅኔ በበቀቀን ሲዘረፍ
አቀርቅረን ስናንቋርር
ቅሪታችንን ስናንቃርር
እንደቀላጤ አከንባሎ ቁልቁሉ ባፍጢም ተተክለን
በእርኩስ አመዳይ ተበክልን
እንዲህ የትም ስንቀር እያየህ ዝም ካልክማ
እውነት እውነት ከመንበርህ የለህማ!
Get your second chance On my First Aid!
varka911
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 101
Joined: Tue Oct 22, 2013 2:30 pm

Postby ቦቹ » Tue Dec 17, 2013 5:06 am

911 ይመችህ ግጥሙና ጨዋታው ይቀጥል::

ዛሬ ይዤ የቀረብኩት ከሼህ ሁሴን ጅብሪል ትንቢታዊ ግጥሞች መካከል አንዳንዷቹን መርጬ ነው:: ግጥሙ በትንቢት መልክ እራሳቸው ይግጠሙት ወይም ከሆነ በxላ በሳቸው ስም ይገጠም የማውቀው ነገር የለም:: አጻጻፉ ግን ስለሳበኝ በግጥምነቱ ይዤው ቀርቤያለው::

አንድ ዓመት ሲቀረው ምኒልክ ሊነግሥ
አላህ መተማ ላይ ይስላል መቀስ
በደም አጨማልቃ የምትቆራርስ
እራስ የምትቆርጥ ያውም የንጉሥ
አንደዜ ተመታች የማታላውስ::

***********************************************************************
ተፈሪ መኮንን እንዴት ያለ ሰው ነበር?
መረታቱን ሲያውቀው እርቅ ይወድ ነበር
የወደቀው ይውደቅ ብሎ እንዲህ ሊደናገር
ምን ይበጀው ይሆን ከተማ ባላገር?
ዲንህን አጥፍተህ ዘመድክን ሳትሰትር::
. መሸነፉን ሲያውቀው ጀግና እርቅ ይወዳል
እርቅን እምቢ ካለ አገሩ ይናዳል
ፍቹን ድረስበት እርቁ ይሻልሃል
የተፈሪ ይብቃ መዓት ይወርድብሃል::

*******************************************************************************
ሐበሻ ላም ሆና ታስራ ከታለበች
ጡቷን መዥገር ወሮት ጥጃዋን ገደለች
ላምዋም ትሞታለች እየመነመነች
ወተት ቢሉ አይገኝ አንደዜ ሙታለች
ይዘገያል እንጅ ኋላ ትድናለች::

**********************************************************************
የሐበሻ መሬት ሌት ቀን ሲጨልም
ሐረር ወዲያ ማዶ ይፈሳል ብዙ ደም
ቂሙም አይረሳ እስከ ዘለዓለም
መንገድ ይፈልጋሉ ሐበሻን ሊቀሙ
ከስንቱ ጋር ይሆን ሐበሻ እምትገጥ

**********************************************************************
በአሥመራ ወያኔ ከመጣ ችግር
መጀመሪያ አሥመራ ትሆናለች ቀብር
አክሱም ትጠፋለች በአንድ ቀን ጀንበር
ግሼን ላሊበላ ትሆናለች ቀብር
ሁሉም ይሸፍታል ሴት እናኳን ሳይቀር::

**************************************************************

ነገሩ እማይገባ የተወላገደ
በአሥመራ በትግሬ ሄዶ እየነደደ
እንዴት ያለ እሳት ከሸዋ ነደደ
ቢያጠፉት እምቢ አለ እየተዛመደ

**********************************************************

አንበሳ እግሩን ታሞ ደም ሲያለቃቅስ
ማማው ምስጥ በልቶት ይሆናል ብስብስ
ወደቅ ወደቅ ይላል ወፉን ሊያጨርስ
የዚያን ቀን አሳማ ይሆናል ንጉሥ
ሺምጦ የሚበላ ሰው የሚያስለቅስ::

*************************************************************************
ተፈሪ ክፉ ነው ልቡም አይገኝ
ለሰው ይመስለዋል ይናገራል ቀኝ
ኋላ እንዲህ ሊዋረድ ፍዳውን ሊያገኝ
እሳት ሰደዱበት ዳግሚያ እንዳይገኝ
ዘላለም የማዝበርድ በደም የሚያዋኝ::

**************************************************************************

የተማረ ወድቆ ደንቆሮው ከገዛው
ማን አለብኝ ብሎ አገሩን ወረሰው
ጥሩ አርጎ ባለበት በገዛ እጁ ናደው
ምድር ሊቆረቁር ኋላ እንዲህ ሊቆጨው::

***************************************************************

አሥመራ ልትጠፋ ገመዱ ሲላላ
በሸዋ ከተማ ይኸለቃል በላ
በሦስት ቀን ይያዛል ጎንደር ላሊበላ
አክሱም የዚያን ጊዜ ትሆናለች ሌላ
ማርያም ትጠፋለች አያዋጣም ብላ::

*******************************************************************************

የአሥመራ ወያኔ ከያዘ ጠመንጃ
ደንግጦ ይሞታል የአሥመራ ስልቻ፣
የኋላ የኋላ ከቲማውን እንጃ
ምን አስለፈለፈኝ ላይገኝ ፈረጃ
ነስሩም አይታወቅ ዘላለም ጦር ብቻ::

**************************************************************************************************

አሥመራና ትግሬ ስትል ሰገደይ
እባብ ከተፍ ይላል ማምጫው ሳይታይ
ሸዋ የዚያን ጊዜ ይላል ዋይ! ዋይ!
ጀርባውን ምች መታው ወደ ትግሬ ሲያይ::

*******************************************************************************************************************
ያ ተፈሪ - በንቲ!
ጀበሲ ኦፍኤጊ!
ኢትዮጵያን ነመገንቲ!
ተፈሪ በንቲ!


ኢጆሌ! ወረ አድአ
ቦቹ
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 357
Joined: Fri Dec 31, 2004 1:26 am

Postby ሙዝ1 » Tue Dec 17, 2013 12:15 pm

ቦቹ wrote:ጠብቄሽ ነበረ

መንፈሴን አንጽቼ
ገላዬን አጥርቼ
አበባ አሳብቤ
አዱኛ ሰብስቤ
ጠብቄሽ ነበረ፤
ብትቀሪ ጊዜ፣
መንፈሴን አሳደፍኩ
ገላዬን አጎደፍኩ
አበባው ደረቀ
አዱኛው አለቀ፤
ብትቀሪ ጊዜ፣
የጣልኩብሽ ተስፋ
እኔን ይዞ ጠፋ፡፡
(ደበበ ሰይፉ፣)


ገራሚ ፍጥረት ነበረ'ኮ ደቤ .... ይህቺ ቅጽ 2 ላይ ነች .... የብርሀን ፍቅር ቅጽ 1 ላይ ግራሚ ገራሚ ግጥሞች አሉት ... ከልሽ ጀባ በይና ጉርምስናችንን አስታዉሽን ....
አይን ሁሉን ቢያይም አጠገቡ ያለዉን ቅንድብ አይቶ አያዉቅም ...
ሙዝ1
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 3128
Joined: Wed Feb 22, 2006 9:25 am

PreviousNext

Return to Warka Culture and Literature - ዋርካ ባህልና ሥነ ጽሑፍ

Who is online

Users browsing this forum: No registered users and 5 guests