የጥበብ እልፍኝ::

Topics related to cultures, arts, languages, arts such as humor, music, traditional literary genres of poems, ግጥም ፣ ቅኔ ፣ ተረትና ምሳሌ)

Postby ክቡራን » Fri Dec 20, 2013 8:20 am

ቦርቸሌውና ጺላው ሃያት:-
የግጥም አምላክ ትድፋቹ!!
እሷ ብታልፋቹ እንኴን..

እንቅፋት መቶ ይጣላቹ..
የግጥም ቦዘኔዎች..
እንዲሁም በዲጎኔ አሿፊዎች
መሆናችሁን አለም የማያቅ መስሏቹ ..
ግድ የለም ቀልዱ ሸበላዎቹ ...
ጊዜያቹ ደርሶ እስክክትሰለቹ.. :lol:

ወንድሜ ዲጎኔ እንዴት ነው ይሄ ግጥም ያዋጣል...? :D
ክቡራን
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 7971
Joined: Tue Mar 04, 2008 4:24 pm

Postby መራራ » Fri Dec 20, 2013 7:28 pm

ኑ በ አምሳላችን ሰውን እንፍጠረው:
ብሎ ነበር አምላክ አዳምን ሲያበጀው::
ብሂሉም እንደሚል ከ አንድ ይሻላል ሁለት:
ሄዋንንም ሰራት ከ ግራው አቆራኛት:
ለ እሷ የዋለው የግራ ጎን አጥንት:
ቅኚ ተብሎ ደግሞ ለ ካርቦኔ ታደላት::ክቡራን wrote:ቦርቸሌውና ጺላው ሃያት:-
የግጥም አምላክ ትድፋቹ!!
እሷ ብታልፋቹ እንኴን..

እንቅፋት መቶ ይጣላቹ..
የግጥም ቦዘኔዎች..
እንዲሁም በዲጎኔ አሿፊዎች
መሆናችሁን አለም የማያቅ መስሏቹ ..
ግድ የለም ቀልዱ ሸበላዎቹ ...
ጊዜያቹ ደርሶ እስክክትሰለቹ.. :lol:

ወንድሜ ዲጎኔ እንዴት ነው ይሄ ግጥም ያዋጣል...? :D
መራራ
ዋና ኮትኳች
ዋና ኮትኳች
 
Posts: 753
Joined: Sat Sep 25, 2004 9:58 am
Location: united states

Postby ዲጎኔ » Fri Dec 20, 2013 10:27 pm

ሰላም ለሁሉ ለእልፍኝ ቤተኞች
በግራናበቀኝ ግጥም ገጣሚዎች
የጦቢያ አለኘታ ወይም ቀበኞች
የዛሬ አድናቂዎች የነገ ተቺዎች
የግጥም እልፍኝ በቦቺ ሲጀመር
በተገቢ መንገድ በስነቃል ነበር
እኔም ገባሁ ያቅሜ ልወረውር
አሁንግን ቤቱ ተበላሸ ከምር
ረጋሚ ገባ ሌላም ባላሽሙር
እስኪ በጥበብ በውስጠ ወይራ
ቫርካ እንዳደረገ በተራ በተራ
በዘመኑ ቃል ሀቅን እየጠራ
የልማታዊን ብልጽግና ጉራ
ለራሱ ጀሌ ምንም ያልራራ
ቀብር ቦታ ያጣ ጨብራራ
ብሎ በዘዴ ግፍን ሲያብራራ
ምላሹ ሆነ ርግማን ቆጠራ
ግድየለም ምክር ለጠየከኝ
ዛሬም መልሴን ብትቀበለኝ
ጠቢቡ እንዳለ ሰው ሁንነው
ያንጊዜ ብቻ ነው የምታርፈው
ከመባነን ስጋት የምታርፈው
የዘላለም ቤት የምታተርፈው
ክቡራን wrote:ቦርቸሌውና ጺላው ሃያት:-
የግጥም አምላክ ትድፋቹ!!
እሷ ብታልፋቹ እንኴን..

እንቅፋት መቶ ይጣላቹ..
የግጥም ቦዘኔዎች..
እንዲሁም በዲጎኔ አሿፊዎች
መሆናችሁን አለም የማያቅ መስሏቹ ..
ግድ የለም ቀልዱ ሸበላዎቹ ...
ጊዜያቹ ደርሶ እስክክትሰለቹ.. :lol:

ወንድሜ ዲጎኔ እንዴት ነው ይሄ ግጥም ያዋጣል...? :D
ዲጎኔ
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 4752
Joined: Fri Aug 19, 2005 2:03 am
Location: united states

Postby ክቡራን » Sat Dec 21, 2013 2:10 am

ምን ድነው ደሞ ይሄ ኩሊ ዛሬ የጻፈው ..?? :lol: እንደው ባለቤት የሌለበት ቤት እገኘን ተብሎ በግጥም እንዲህ ሰው ይጫወታል..?? ግጥምን አስተኝታቹ ሰረራችኌት ነው የሚባለው...ሰላም ነው ወንድሜ ዲጎኔ.. ?? :lol:


ሀማል ዘለቀ wrote:ኑ በ አምሳላችን ሰውን እንፍጠረው:
ብሎ ነበር አምላክ አዳምን ሲያበጀው::
ብሂሉም እንደሚል ከ አንድ ይሻላል ሁለት:
ሄዋንንም ሰራት ከ ግራው አቆራኛት:
ለ እሷ የዋለው የግራ ጎን አጥንት:
ቅኚ ተብሎ ደግሞ ለ ካርቦኔ ታደላት::ክቡራን wrote:ቦርቸሌውና ጺላው ሃያት:-
የግጥም አምላክ ትድፋቹ!!
እሷ ብታልፋቹ እንኴን..

እንቅፋት መቶ ይጣላቹ..
የግጥም ቦዘኔዎች..
እንዲሁም በዲጎኔ አሿፊዎች
መሆናችሁን አለም የማያቅ መስሏቹ ..
ግድ የለም ቀልዱ ሸበላዎቹ ...
ጊዜያቹ ደርሶ እስክክትሰለቹ.. :lol:

ወንድሜ ዲጎኔ እንዴት ነው ይሄ ግጥም ያዋጣል...? :D
ክቡራን
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 7971
Joined: Tue Mar 04, 2008 4:24 pm

Postby ቦቹ » Sat Dec 21, 2013 5:51 am

ህይወት የምንለው
እንደ ጥሬ እህል ፣
በኑሮ ምጣድ ላይ
ቢቆላ ቢማሰል ፣
የበሰለው ያራል
ጥሬው እስኪበስል ።
ኃይሉ ገ /ዮሀንስ (ገሞራው )
ያ ተፈሪ - በንቲ!
ጀበሲ ኦፍኤጊ!
ኢትዮጵያን ነመገንቲ!
ተፈሪ በንቲ!


ኢጆሌ! ወረ አድአ
ቦቹ
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 357
Joined: Fri Dec 31, 2004 1:26 am

Postby ቦቹ » Sat Dec 21, 2013 6:01 am

ዓይኔን ሰው አማረው
ዓይኔን ሰው አማረው
የሰው ያለህ የሰው !

አያ ደሙ በኔ የሳጥናኤል መሪ
የቀበሮ እንግዳ በቤት አሳዳሪ
ተበግ ተቀበሮ ቀበሮን አክባሪ
ቀበሮን ወደ ቤት በግን ገደል መሪ
የበግ ለምድ ለብሶ በጎች አባራሪ
በቀበሮው አዋጅ አገሩን ወራሪ
በለሰለሰ እርሻ አሜከላ ዘሪ
እጅግ ተጤንቅቆ አባቱን አፍቃሪ
አባቱን አፍቅሮ እናት አቃጣሪ
እናቱን አቃጥሮ አባት አሳሳሪ
አባት አሳስሮ በናቱ መካሪ
በናቱ ላይ መክሮ አዋጅ አስነጋሪ

በግራ የቆመው ሲመለስ ወደ ቀኝ
እኔም በናታችሁ ጎዳናው ሳይርቀኝ
በዚያን ጊዜ እናንተን የሚያይ ሰው ናፈቀኝ ::

(ቀኝ ጌታ ዮፍታሄ ንጉሤ)
ያ ተፈሪ - በንቲ!
ጀበሲ ኦፍኤጊ!
ኢትዮጵያን ነመገንቲ!
ተፈሪ በንቲ!


ኢጆሌ! ወረ አድአ
ቦቹ
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 357
Joined: Fri Dec 31, 2004 1:26 am

Postby ቦቹ » Sat Dec 21, 2013 6:22 am

ብቸኝነት

ከተማ ተይዞ ሲጣል ምድረ በዳ
ሰው ከራሱ በቀር ለሌላው እንግዳ
ሁኖ ሲውል ዲያድር በብቸኝነቱ
ሞተች ይላል አለም ውስጣዊ ፍጥረቱ::

ደበበ ሰይፉ
ያ ተፈሪ - በንቲ!
ጀበሲ ኦፍኤጊ!
ኢትዮጵያን ነመገንቲ!
ተፈሪ በንቲ!


ኢጆሌ! ወረ አድአ
ቦቹ
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 357
Joined: Fri Dec 31, 2004 1:26 am

Postby ዲጎኔ » Sat Dec 21, 2013 3:04 pm

አይኔ ሰው አማረው እጅግ ናፈቀው
ለጦቢያ የሚቆም ወረት የማያውቀው
የወቅቱ ግፈኛ ኮንደሚን ያልገዘው
እስር ማዋከቡ ከቶ ያልበገረው
አይኔ ሰው ያማረው ዛሬ በዘመኔ
ለጦቢያ ህዝብ ለምስኪን ወገኔ
የፊውዳሉ ንቀት እረ ለኔ ለምኔ
ብሎ ከአንጀቱ በእውነት የታገለ
እንደክፉ መሪ አሰሰስ ገሰስ ያላለ
ባፍ ብቻ ብልጠት ወገናችን የደለለ
ለከፋፍለህ ግዛው መጠቀሚያ ያዋለ
የራሱን ዘር ብቻ ወርቃማ ነው ያለ
አይኔን ሰው ያማረው ዛሬ የተመኘ
መቻቻል መግባባት ህዝቦችን የቃኘ
ማንዴላን በደቡብ ባፍሪካ ያገኘ
ለምስራቁ ክፍል ምነው በተገኘ
ኦሮሞ አማራ ከምባታን ያቀፈ
ትግሬ አደሬ ሶማሌ ያተረፈ
ሲዳማ ጌዴኦ ሁሉን ያሳለፈቦቹ wrote:ዓይኔን ሰው አማረው

ዓይኔን ሰው አማረው
የሰው ያለህ የሰው !

አያ ደሙ በኔ የሳጥናኤል መሪ
የቀበሮ እንግዳ በቤት አሳዳሪ
ተበግ ተቀበሮ ቀበሮን አክባሪ
ቀበሮን ወደ ቤት በግን ገደል መሪ
የበግ ለምድ ለብሶ በጎች አባራሪ
በቀበሮው አዋጅ አገሩን ወራሪ
በለሰለሰ እርሻ አሜከላ ዘሪ
እጅግ ተጤንቅቆ አባቱን አፍቃሪ
አባቱን አፍቅሮ እናት አቃጣሪ
እናቱን አቃጥሮ አባት አሳሳሪ
አባት አሳስሮ በናቱ መካሪ
በናቱ ላይ መክሮ አዋጅ አስነጋሪ

በግራ የቆመው ሲመለስ ወደ ቀኝ
እኔም በናታችሁ ጎዳናው ሳይርቀኝ
በዚያን ጊዜ እናንተን የሚያይ ሰው ናፈቀኝ ::

(ቀኝ ጌታ ዮፍታሄ ንጉሤ)
ዲጎኔ
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 4752
Joined: Fri Aug 19, 2005 2:03 am
Location: united states

Postby ክቡራን » Sat Dec 21, 2013 3:39 pm

ግጥሞችን ስንጽፍ የራሳችን ካልሆኑ በኮቴሽን ውስጥ አርገን መጻፍ ይኖርብናል ወይም ምንጩን መጥቀስ ይኖርብናል:: ፕላጂያሪዝም ማለት ቃል በቃል የሌላውን ደራሲ ጽሁፍ ገልበጦ ማምጣት ብቻ አይደለም:: አስተሳሰብን ሰርቆ እንደ ራስ አድርጎ መደቅደቅ ፕላጂያሪስት ያሰኛል:: ቢያንስ የዋናውን ደራሲ ስሜት ላለማበላሸት ""መነሻ ሀሳብ "" በሚል ከእከሌ ብለን ግጥምም ከቻልን በግጥም ካልቻልነ ደሞ በስድ ንባብ ( አሁን ወንድሜ እንዳደረከው ) ጽሁፋችንን መለሽለሽ እንችላለን:: ካዲስ አመትና ከፈረንጆች ገና በፊት ካላገኘሁህ መልካሙን ሁሉ እመኛለሁ ወንድሜ ዲጎኔ ሆይ:: አክባሪ ወንድምህ::

ወንድሜ ዲጎኔ በዮፍታሄ ንጉሴ የግጥም ሌማት ውስጥ ገብቶ wrote:አይኔ ሰው አማረው እጅግ ናፈቀው
ለጦቢያ የሚቆም ወረት የማያውቀው
የወቅቱ ግፈኛ ኮንደሚን ያልገዘው
እስር ማዋከቡ ከቶ ያልበገረው
አይኔ ሰው ያማረው ዛሬ በዘመኔ
ለጦቢያ ህዝብ ለምስኪን ወገኔ
የፊውዳሉ ንቀት እረ ለኔ ለምኔ
ብሎ ከአንጀቱ በእውነት የታገለ
እንደክፉ መሪ አሰሰስ ገሰስ ያላለ
ባፍ ብቻ ብልጠት ወገናችን የደለለ
ለከፋፍለህ ግዛው መጠቀሚያ ያዋለ
የራሱን ዘር ብቻ ወርቃማ ነው ያለ
አይኔን ሰው ያማረው ዛሬ የተመኘ
መቻቻል መግባባት ህዝቦችን የቃኘ
ማንዴላን በደቡብ ባፍሪካ ያገኘ
ለምስራቁ ክፍል ምነው በተገኘ
ኦሮሞ አማራ ከምባታን ያቀፈ
ትግሬ አደሬ ሶማሌ ያተረፈ
ሲዳማ ጌዴኦ ሁሉን ያሳለፈቦቹ wrote:ዓይኔን ሰው አማረው

ዓይኔን ሰው አማረው
የሰው ያለህ የሰው !

አያ ደሙ በኔ የሳጥናኤል መሪ
የቀበሮ እንግዳ በቤት አሳዳሪ
ተበግ ተቀበሮ ቀበሮን አክባሪ
ቀበሮን ወደ ቤት በግን ገደል መሪ
የበግ ለምድ ለብሶ በጎች አባራሪ
በቀበሮው አዋጅ አገሩን ወራሪ
በለሰለሰ እርሻ አሜከላ ዘሪ
እጅግ ተጤንቅቆ አባቱን አፍቃሪ
አባቱን አፍቅሮ እናት አቃጣሪ
እናቱን አቃጥሮ አባት አሳሳሪ
አባት አሳስሮ በናቱ መካሪ
በናቱ ላይ መክሮ አዋጅ አስነጋሪ

በግራ የቆመው ሲመለስ ወደ ቀኝ
እኔም በናታችሁ ጎዳናው ሳይርቀኝ
በዚያን ጊዜ እናንተን የሚያይ ሰው ናፈቀኝ ::

(ቀኝ ጌታ ዮፍታሄ ንጉሤ)
ክቡራን
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 7971
Joined: Tue Mar 04, 2008 4:24 pm

Previous

Return to Warka Culture and Literature - ዋርካ ባህልና ሥነ ጽሑፍ

Who is online

Users browsing this forum: No registered users and 1 guest