by recho » Thu Jan 09, 2014 5:23 pm
እሺ እንዴት ከረማቹሳ? 2014 እንዴት እያረጋቹ ነው? ከጅምሩ በቅዝቃዜ ተቀበለንሳ ... በዚህ አይነት ሙቀቱም ያነደን ይሆናል ... ኤክስትሪሚስት ካይንዳ ይር ነው መሰል .. ደስታችንም አለቅጥ .. ሀዘንም እንደዛው ቅቅቅ ሰውረነ
የ2014 የመጀመሪያዋ ትዝብታዬ .. እናንተዬ አበሾች እንዴት ሰልጥነናል በሉ? የኒውይር ኢቭ እነ ክቡ ማነው ስሙ የሚባለው ሽሻቤት ሲጨሱ እኔም እንዳቅሚቲ አንዲትዋ የ ዲሲ ሀበሻ ኒውይር ሰለብሬሽን ላይ ተገኝቼ ነበር .. ደስ ይላል መቼም .. ሴቶቻችን አሸብርቀውና ተውበው .. አንዳንዶቹ እንደው እንድኩዋን ለወንድ እንደው ለኛም ትንሽ እምም እምምምም ነው ... ታዲያ ሙዚቃው ጨሰ .. መጠጡ በላይ በላይ ሲጠጣ ... አቤት ቻቻታው .. ከሚቀጥለው ክፍል ደግሞ ሽሻው እንደጉድ ይጨስል .. የኩበት ጭስን ያስታውሰናል እና አመትበአሉን አይደምቀዋል ይሁንላቸው መቼም ... ታዲያ ሞቅታው እየመጣ ሳለ እኛው ቆመን ወደምንወዘወዝባት ጥግ ጥንዶቹ መጥተው ግርግዳ ያዙ .. ያወ መቸም መተሻሸቱ ያለ ነው .. አይናችንን ዞር አርጎ እንዳላየ መሆን ነው .. ግን አይን መንቀል የማያስችሉ ጥንዶች ናቸው .. በመጀመሪያ የልጅትዋ እጥረትና የልጁ ርዝመት ለሚፈለገው ጉዳይ ብዙም የሚያግዝ አይደለም .. ቢሆንም እነሱ ማንን ፈርተው ከመሞከር ወደሁዋላ አላሉም .. ልጁ ግርግዳ ያዘ .. አጅሪት መቀመጫዋን ወደሱ አዙራ ዳንስ ይሁን ሌላ የማይገባ ነገር ማድረግዋን ያዘች .. አይንዋ ብልጥጥ ብሎ ተከፍቶ ወደሁዋላዋ ትፈትጋለች .. ሁዋላ ነው እንግዲህ ጥረትዋ በደንብ የገባኝ .. የልጁ አይን ይከፈት ወይንም ይዘጋ ለማወቅ ያቸግራል ... ያደረገው የብርጭቆ ቁጥ የሚያክል መነጽር ሶስት አይን ስለሆነ የሚያሳየኝ የቱ እንደተከፈተ እና የቱ እንደተዘጋ አልገባኝም .. ብቻ እስዋ ስትፈትግ .. እሱ አቅጣጫውን ስታ የተጋጠሙትን እግሮቹን ሳይሆን ጉዳዩ ጋር እንድትደርስ ወደታች ዝቅ ለማለት የሚያደርገው ጥረት .. በዛላይ ከሰው አይን ለመደበቅ የሚያደርጉት ጥረት :lol: :lol: እንዴ ቢቀርስ? ተያይዞ እኮ ጉዳዩን በርግጠኝነት ያለበት ቦታ ድረስ መድረስ የሚቻልበት ቦታ መሄድ ይቻላል ... ነገሩ እንደሪቾ አይነት ፋራ አይኑን አይነቅልምና እነሱ ዩኑቱ .. ብቻ ሲፋተጉ ሲፋተጉ .. የፈጀወ ሰአት ምናልባት ከምር ወተት ቢናጥ ቅቤ ይወጣዋል ... በመሀል እንግዲህ ጭፈራው አዘናጋኝና ቆይቼ ትዝ ቢሉኝ ካለሁበት አይኔን ወርወር ሳደርግ አይ ምስኪኒት አሁንም ትናታለች , ታሻለች .. ትፈትጋለች .. እረ ተይ መቀመጫሽን አታደንዝዢ ልጅቱ ልላት ነበር የተመኘሁት .. በዛላይ ለውጥ ያመጣ መስልዋት ይሁን አላውቅም የሱን የብርጭቆ ቂጥ መነጽር ተቀብላ አርጋዋለች .. መላው ቀለጠ .. አሁን የስዋ አይን ይጨፈን ይገለት አይታይም ልጁ ግን ምንም አይነት የመነቃቃት ስሜት አይታይበትም .. ይልቅዬ ትግል ላይ ነው ያለው .. የተናደደም ይመስላል ... እህ እግሩን አሳመመችዋ ያለ አቅጣጫው እየገፋች .. ለማንኛውም ነገሩ ሚድናይት ላይ ካውንት ዳውን ሲደረግ ልጅት ነገር አለሙን ትታው እየሮጠች አበባየሁሹን ተቀላቀለችና በዛው በረደ .. :lol: :lol: አይ ስልጣኔ .. ይሄ ከሆነ በአፍንጫዬ ይውጣ .. !!!
ሰናይ ቀን ..
"ሰነፍ በልቡ። አምላክ የለም ይላል በሥራቸው ረከሱ ጐስቈሉ በጎ ነገርን የሚሠራ የለም " መዝሙረ ዳዊት ምእራፍ 14:1