ሴቶች በቁርአን 6

Issues and Articles of General Interests including topics related to religion

ሴቶች በቁርአን 6

Postby ጎነጠ » Fri Jan 17, 2014 7:59 am

2. ወንዶች እስከ አራት ነፃ ሴቶች ለማግባትና ያልተወሰነ ቁጥር ካላቸው ባሪያ ሴቶች ጋር ግን ግብረ ስጋ ግንኙነትን ማድረግ ይችላሉ፡፡ ወንዶች ከአንድ ሴት በላይ እንዲያገቡ እንደሚከተለው ፈቃድ ተሰጥቷቸዋል፡

‹ወላጅ አልባ የሆኑትን (ልጃገረዶች) መንከባከብ የማትችሉ እንደሆነ ከፈራችሁ ከዚያም ጥሩ የሚመስሏችሁን ሌሎችን ሴቶች ልታገቡ ትችላላችሁ፣ ሁለት፣ ሦስት ወይንም አራት የሆኑትን፡፡ ነገር ግን በእነሱ መካከል እኩልነትን አናደርግም ብላችሁ የምትፈሩ ከሆነ አንዲትን ሴት ብቻ አግቡ ወይንም የሚኖራችሁን ማንኛውንም ባሪያ ሴት፡፡ ይህም ፍትሐዊ እንዳትሆኑ የሚያደርጋችሁን ነገር ከእናንተ ላይ ያስወግደዋል› The Qur'an 4:372፡፡

አንዳንዶች ግን ቢሆንም ተከራክረዋል እኩል ማድረግ የማይቻል ስለሆነ በሚቀጥሉት ጥቅሶች መሠረት ከአንድ በላይ ሚስትን ማግባት አይፈቀድም፡ ‹የምትችሉትን ሞክሩ፣ ሚስቶቻችሁን ሁሉ በእኩልነት ልትንከባከቡ አትችሉም፡፡ እራሳችሁንም በማናቸውም ላይ ተቃዋሚዎች አድርጋችሁ አታቅርቡ› The Qur'an 4:129. (Dawood's translation)፡፡

ነገር ግን ብዙዎቹ ተንታኞች የተስማሙበት፡ በቁርአን 4.3 ላይ ያለው እኩልነት የሚመለከተው ጊዜንና ገንዘብን በማከፋፈል ላይ ሲሆን በቁርአን 4.129 ላይ የተጠቀሰው ደግሞ ወንድ ለሚስቶቹ ባለው ፍቅርና ዝንባሌ ላይ ነው Tuffaha, Ahmad Zaky, Al-Mar'ah wal-Islam, Dar al-Kitab al-Lubnani, Beirut, first edition, 1985, p. 58. See also Razi and al-Jalalayn on the above verses. And Ihy'a 'Uloum ed-Din by Ghazali, Dar al-Kotob al-'Elmeyah, Beirut, Vol II, Kitab Adab al-Nikah, p. 54. And Ibn al-'Arabi, Ahkam al-Qur'an, vol. 1, p.504፡፡

በተጨማሪም የሚከራከሩት መሐመድ እራሱ በሚስቶቹ ላይ ባለው አቅርቦት በጣም ያዳላ ነበር፣ ምክንያቱም እርሱ አይሻን ከሌሎቹ ሚስቶቹ ይልቅ ይወዳት ነበርና Razi, At-tafsir al-kabir, commenting on Q. 4:12975፡፡ ስለዚህም ባል ገንዘቡንና ጊዜውን በማከፋፈል ላይ ሚዛናዊ እስከሆነ ድረስ እስከ አራት ድረስ ሊያገባ ይችላል፡፡ ሌሎች ደግሞ የሚያምኑት የሚስቶች ቁጥር እስከ ዘጠኝ ሚስቶች እንደተገደበ ነው፣ ምክንያቱም ሁለት፣ ሦስትና አራት ሲደመሩ የሚሰጡት ዘጠኝ ነውና፣ መሐመድም እራሱ በሚሞትበት ሰዓት ዘጠኝ ሚስቶች ነበሩትና ስለዚህም የእሱን መንገድ መከተል ደግሞ የተፈቀደ የኑሮ መንገድ ነው Razi, At-tafsir al-kabir, commenting on Q. 4:3፡፡

ሌሎችም የሚያምኑት ከዚህ በላይ ያለው ጥቅስ በሚስቶች ላይ የቁጥር ገደብ የሌለ መሆኑን የሚያስረዳ እንደሆነ ነው፡፡ ምክንያቱም ቁጥሩ ሁለት ወይንም ሦስት ወይንም አራት ሳይሆን የሚለው ቃል በቃል ሁለት፣ ሦስትና አራት ነውና ይህም ትርጉሙ ሁለት እና ሦስት እና አራት ወ.ዘ.ተ ነውና Razi, At-tafsir al-kabir commenting on Q. 4:3፡፡ አብዛኛዎቹ የሚያምኑት አንድ ሰው ሊያገባ የሚችለው የሚስቶች ቁጥር በአራት መወሰን እንዳለበት ነው፡፡ ምክንያቱም በሐዲቶች ላይ አስር ሚስቶች ስላለው ሰው በተዘገበው ምክንያት የተነሳ ነው፡፡ እርሱም ሙስሊም ሲሆን መሐመድ ለእርሱ እንዲህ አለው፡ ‹አራቱን አስቀርና ሌሎቹን ፍታ› Razi, At-tafsir al-kabir commenting on Q. 4:3፡፡

ከአንድ በላይ ሚስት የማግባት ምክንያት በታላቁ የሙስሊም ምሁር በጋዛሊ እንደሚከተለው ተሰጥቷል፡ ‹አንዳንድ ሰዎች እንደዚህ የሚያስገድድ የግብረስጋ ፍላጎት ስላላቸው አንድ ሴት ለእነሱ በቂ አይደለችም (ከዝሙት) እነሱን ለመጠበቅ፡፡ እንደዚህ ዓይነት ሰዎች ስለዚህም ሊያገቡ የሚመርጡት ከአንድ ሴት በላይ ነው ስለዚህም እስከ አራት ሚስቶች ሊያገቡ ይችላሉ፡፡ Ihy'a 'Uloum ed-Din by Ghazali, Dar al-Kotob al-'Elmeyah, Beirut, Vol II, Kitab Adab al-Nikah, p.34፡፡

ከዚህም በላይ ወንዶች ከሴቶች ባሪያዎቻቸው ጋር የግብረ ስጋ ግንኙነት የማድረግ መብት አላቸው፡፡ ‹አንድ ሰው ባሪያ ሴትን ቢገዛ የግዢው ስምምነት መጨመር ያለበት ከእርሷ ጋር ግብረስጋ ግንኙነት የማድረግ መብትንም ነው› Abd ar-Rahman al-Gaziri, al-Fiqh 'ala al-Mazahib al-Arba'a, Dar al-Kutub al-'Elmeyah, 1990, vol. 4, p፡፡ ‹ይህም ስምምነት በመጀመሪያ ደረጃ እርሷን ንብረት ለማድረግ ሲሆን በሁለተኛ ደረጃ ደግሞ ከእርሷ ጋር በግብረ ስጋ ግንኙነት በእርሷ መደሰትን ነው›› Abd ar-Rahman al-Gaziri, al-Fiqh 'ala al-Mazahib al-Arba'a, Dar al-Kutub al-'Elmeyah, 1990, vol. 4, p፡፡

እንዲሁም አንድ ሰው ከሚስቱ ውጭ ከሴት ባሪያው ጋር ግብረ ስጋ ግንኙነት የማድረግ ምክንያትም በጋዛሊ እንደሚከተለው ተሰጥቷል፡ ‹በአረቦች መካከል የሚያስገድድ ስሜት የተፈጥሮአቸው አንድ ክፍል ስለሆነ የሃይማኖት ሰዎቻቸው ግብረ ስጋ ግንኙነት የማድረግ ፍላጎት በጣም ከፍተኛ ሆኖ ተገኝቷል፡፡ ስለዚህም ልብን ለእግዚአብሔር አምልኮ ክፍት ለማድረግ ዓላማ እነሱ ከሴት ባሪያዎቻቸው ጋር ግብረ ስጋ ግንኙነትን እንዲያደርጉ ተፈቅዶላቸዋል፣ ሆኖም በሆነ ወቅት ይህንን የሚፈሩ ከሆነ ስሜታቸው ዝሙትን ወደ መፈፀም ሊመራቸው ይችላል፡፡ እንደዚህ ዓይነቱ ተግባር ባሪያ የሚሆን ልጅ ወደ መውለድ የሚመራ መሆኑ እውነት ቢሆንም፣ ማለትም የጥፋት ሁኔታ የሆነው ... ነገር ግን ልጅን ባሪያ ማድረግ ከሃይማኖት ጥፋት ይልቅ የቀለለ ጥፋት ነው፡፡ ምክንያቱም አዲስ የተወለደውን ልጅ ባሪያ ማድረግ ጊዜያዊ ነገር ነው፡፡ ነገር ግን ዝሙትን መፈፀም ዘላለማዊ ጥፋት ነው› Ihy'a 'Uloum ed-Din by Ghazali, Dar al-Kotob al-'Elmeyah, Beirut, Vol II, Kitab Adab al-Nikah, p. 33፡፡

ጋዛሊ የዚህን አስገዳጅ የግብረ ስጋ ግንኙነት ፍላጎትን ምሳሌ እንደሚከተለው ሰጥቷል፡ ‹መናኝና ምሁር የነበረው የኦማር ልጅ፣ ፆምን ይገድፍ የነበረው ከምግብ በፊት ግብረ ስጋ ግንኙነትን በማድረግ ነበረ፡፡ ከመጨረሻውም ምግብ በፊት እርሱ ከሦስት ባሪያዎች ጋር ግንኙነትን አድርጎ ይሆናል› Ihy'a 'Uloum ed-Din by Ghazali, Dar al-Kotob al-'Elmeyah, Beirut, Vol II, Kitab Adab al-Nikah, p. 33፡፡

እንደዚሁም ደግሞ ቡካሪ የዘገበው፡ ‹ነቢዩ የማፍ ልማድ ነበረው (ማለትም የግብረ ስጋ ግንኙነት ማድረግ) በአንድ ሌሊት ከሁሉም ሚስቶቹ ጋር አድርጓል በዚያን ጊዜም እርሱ ዘጠኝ ሚስቶች ነበሩት› Sahih Bukhari, Arabic-English translation, vol. 7, Hadith No. 142. And vol. 1, Hadith No.268. 84፡፡ ምክንያቱም፣ ‹አንድ ጊዜ እራሱ ስለ እራሱ (ሲናገር) ለግብረ ስጋ ግንኙነት የአርባ ወንዶች ኃይል እንደተሰጠው ነው› Mohammad Ibn Saad, al-Tabakat al-Kobra, Dar al-Tahrir, Cairo, 1970, Vol 8, p. 139፡፡

እንዲሁም፣ ‹ከተከታዮቹ ሁሉ በጣም ሃይማኖተኛ የነበረው አሊ አራት ሚስቶች እና አስራ ሰባት ቅምጥ የሴት ባሪያዎች ነበሩት› Ihy'a 'Uloum ed-Din by Ghazali, Dar al-Kotob al-'Elmeyah, Beirut, Vol II, Kitab Adab al-Nikah, p.27፡፡ ይህም ቁጥር የሌላቸው ሌሎች ተከታዮች ሦስትና አራት ሚስቶች እንዲሁም ሁለት ሚስቶች ያሏቸው ሆነው እያለ ነበር› Ihy'a 'Uloum ed-Din by Ghazali, Dar al-Kotob al-'Elmeyah, Beirut, Vol II, Kitab Adab al-Nikah, p.27፡፡

ከላይ ባለው የቁርአን ጥቅስ ውስጥ ከባሪያ ሴቶች ጋር የግብረ ስጋ ግንኙነት መፈቀድን አስመልክቶ ራዚ የተናገረው፡ ‹እግዚአብሔር ከብዙ ባሪያ ሴቶች ጋር የግብረ ስጋ ግንኙነት እንዲደረግ ስጦታን ሰጥቷል ይህም አንዲት ነፃ ሴትን እንደ ማግባት ቀላል የሆነ ነው፡፡ ከዚህም ባሻገር ለባሪያ ሴቶች የሚደረጉት ሃላፊነቶችና ስጦታዎች ጥሎሽ ከሚጣልላቸው (ነፃ ሴቶች) ቀላሎች ናቸው፣ ስለዚህም ጥቂትም ይኑሯችሁ ወይንም ብዙ ምንም አያሳስብም፣ እንዲሁም በእነሱ መካከል ሌሊቶቻችሁን በማደላደል በኩል እኩል ማድረጋችሁና አለማድረጋችሁ ምንም አያሳስብም የግብረ ስጋ ድርጊታችሁን ጨረሳችሁ አልጨረሳችምም ምንም ችግር የለበትም› Razi, At-tafsir al-kabir, commenting on Q. 4:3፡፡

ተንታኙ ኮርቶቢ ያንን ጥቅስ ያየው ማለትም ቁርአን 4.3 በወንድ ሙስሊሞች አገልግሎት ላይ የሚውሉት ባሪያ ሴቶች፡ ‹የግብረ ስጋ ግንኙነትም ሆነ የገንዘብ ምንም መብት የላቸውም፡፡ ምክንያቱም እግዚአብሔር አንዲት ነፃ ሴትን እንዲሁም በአንድ አይነት ሁኔታ ውስጥ ‹የሴት ባሪያን እንዲኖራችሁ› አድርጓል፡፡ ይሁን እንጂ ወንድ በግል ይዞታነት መብት የሴት ባሪያዎች ይኖሩታል፣ እንዲሁም ለባሪያዎች ይደረግ ዘንድ በሚገባው ደግነት› Qortobi, commenting on Q. 4:3፡፡

ስለዚህም ‹ሃይማኖታዊ የሆኑት ሰዎች የግብረ ስጋ ግንኙነት የማድረግ ፍላጎታቸው በጣም ከፍተኛ ነው፣ እንዲሁም እግዚአብሔርን ለማምለክ ልብን ነፃ ለማድረግም አላማ ነው› እነሱም እስከ አራት ሴቶች ድረስ እንዲያገቡ እና ያልተወሰነ ቁጥር ካላቸው የሴት ባሪያዎች ጋርም እንዲገናኙ ተፈቅዶላቸዋል፣ ይህም ስጦታው ‹ባሪያ የሆነን ልጅ ወደ መውለድ የሚያመጣም ቢሆን እንኳን፣ ይህም የጥፋት ዓይነት ቢሆንም እንኳን›፡፡

3. ሚስቱን በመፍታት ላይ የወንድ መብት

ፍቺ በብዙ ማህበረ ሰብ ውስጥ እጅግ አሰቃቂ ነገር ነው፡፡ ይሁን እንጂ በእስልምና የሚታየው እንደ ሕጋዊ መብት ማለትም የተፈቀደ ድርጊት እንደሆነ ተደርጎ ነው፡፡ ሐዲት እንደሚከተለው ይናገራል፡ ‹ከተፈቀዱት ነገሮች ውስጥ በአላህ ዘንድ በጣም የተጠላው ነገር ፍቺ ነው› Mishkat al-Masabih, Book II, Divorce, Hadith No. 137፡፡

የመፍታት ኃይል በአብዛኛው ያለው በወንድ እጅ ውስጥ ነው፡፡ ቡካሪ የዘገበው ሐዲት ያሳየው ምን ያህል ቀላል፣ የተፈቀደ እና የተጠላ ድርጊት እንደሆነ ነው፡፡

አንድ ሰው በእስልምና እንዲህ ሊል ይችላል፣ ‹ማናቸውንም ሚስቶቼን ተመልከት የምትፈልግ ከሆነ እርሷን ለአንተ እፈታልሃለሁ› Sahih Bukhari, English translation by M. Muhsin Khan, Vol. VII, pp. 6&7, see Hadith No. 10፡፡ ይህም ከፈቃድ ውጭ፣ ከሚመለከታቸው ባልና ሚስትም ፍቅር ውጭ ሊሆን ይችላል፡፡

‹የዖማር ልጅ እንደዘገበው፡ በስሬ በጣም የምወዳት ሚስት አለችኝ ነገር ግን ዖማር አይወዳትም እናም ‹ፍታት› በማለት ተናገረኝ፡፡ ነገር ግን እኔ አይሆንም አልኩኝ፡፡ ከዚያም ዖማር ወደ አላህ መልክተኛ መጣና ለእርሱ ጉዳዩን ነገረው፡፡ የአላህም መልክተኛ ‹ፍታት› አለኝ› Mishkat al-Masabih, Book 1, duties of parents, Hadith No. 15፡፡ (Quoted by Tirmizi and Abu Daud) ፡፡

4. ልጆችን በማሳደግ በኩል የወንድ ዕድሎች

ልጆችን በማሳደግ በኩል ወንድ ዕድለኛ ከሆነው ቡድን በኩል ነው፡፡ ጋዚሪር የሚባለው ዘመናዊ የእስልምና ሕግ ምሁር እንደሚከተለው ጽፏል፡

‹ሃናፋውያን ብዙውን የሙስሊም ማህበረ ሰብ የሰጡት የተናገሩት፡ ‹የልጆችን ማሳደግ ሁኔታ እንደሚከተለው ነው፡፡ በቅድሚያ ሚስት እስልምናን መቃወም አይኖርባትም፡፡ እርሷ እስልምናን ከተቃወመች፣ ልጆችን የማሳደግ ምንም መብት አይኖራትም፡፡ ሁለተኛም፣ እርሷ መልካም ባህርይ ያላት መሆን አለባት ምክንያቱም እርሷ በተከለከለ የግብረ ስጋ ግንኙነት መበከሏ ከተመሰከረ፣ ወይንም በስርቆት፣ ወይንም ዝቅተኛ ስራ ካላት ለምሳሌ ለቅሶ አስለቃሽ ከሆነች፣ ወይንም ዳንሰኛ ከሆነች ልጅ ማሳደግ መብቷን ታጣለች፡፡ ሦስተኛ፣ የልጅ አባት ያልሆነን ሰው ለማግባት አይፈቀድላትም፡፡ እርሷም እንደገና ካገባች ልጅ የማሳደግ ምንም መብት አይኖራትም፣ ይህም አዲሱ ባሏ ከልጁ ጋር በአባት በኩል አጎት ሆኖ ካልተዛመደው በስተቀር ነው፡፡ ነገር ግን እርሷ የሌላ አገር ሰውን ካገባች ልጅን የማሳደግ ምንም መብት አይኖራትም፡፡ አራተኛ ልጇን ያለ ጠባቂ መተው አይኖርባትም፡፡ በተለይም ልጇ ሴት ልጅ ከሆነች፣ ምክንያቱም ሴቶች ልጆች ጥበቃ ያስፈልጋቸዋል፡፡ ስለዚህም እናትየዋ ወደ ረዘም ላለ ጊዜ ወደ ውጭ የምትሄድ ከሆነ እና ልጇን የምትረሳ ከሆነ ልጅን የማሳደግ መብት አይኖራትም፡፡ አምስተኛ፣ አባትየው ድሃ ከሆነ እና እናትየው ልጅን ያለ ክፍያ አላሳድግም ካለችና የልጁ አክስት ‹እኔ ልጁን በነፃ እጠብቀዋለሁኝ ካለች› ከዚያም አክስትየዋ ልጁን የማሳደግ መብት ይኖራታል፡፡ የእስልምናን ሃይማኖት መከተል የልጅ ማሳደግን መብት የማግኘት ሁኔታ አይደለም፣ አንድ ባል ከመጽሐፉ ሰዎች አንዲቷን ቢያገባ እርሱ ሃይማኖቱን እስካልካደ፣ ወይንም እስካልረከሰ ድረስ እርሷ ልጅ የማሳደግ መብት ይኖራታል፡፡ ነገር ግን ያ ካልሆነ ማለትም እርሷ ልጇን ወደ ቤተክርስትያን ስትወስድ ቢያያት ወይንም የአሳማ ስጋ ስትመግበው ቢያይ ወይንም ወይንን ጠጅ ስትሰጠው ቢያይ አባትየው ከእርሷ ላይ ልጁን የመንጠቅ መብት ይኖረዋል፣ ጤነኝነት (ንፁህነት) በሁሉም ዘንድ የተደገፈ ቅድመ ሁኔታ ነውና› 'Abd ar-Rahman al-Gaziri, al-Fiqh 'ala al-Mazahib al-Arba'a, Dar al-Kutub al- 'Elmeyah, 1990, vol. 4, p. 522፡፡

የማሳደግን የጊዜ ገደብ በተመለከተ ደግሞ፣ ጋዚሪር የጨመረው፡

‹ሃኒፋይቶች እንደሚከተለው ብለዋል፡ ልጁ ሰባት ዓመት እስከሆነው ድረስ እናትየዋ የማሳደግ ሃላፊነት አለባት፡፡ ሌሎች ደግሞ የተናገሩት፣ ‹ዘጠኝ ዓመት እስኪሆነው ድረስ ነው› ነገር ግን በሕጋዊ ደረጃ ተቀባይነት ያለው የመጀመሪያው ሐሳብ ነው፡፡ ለሴት ልጅ ግን ሁለት ዓይነት አመለካከቶች አሉ፡፡ የመጀመሪያው የወር አበባን እስክታይ ድረስ የሚል ሲሆን፣ ሁለተኛው የታዳጊ ዕድሜ እስክትደርስ ነው ማለትም ዘጠኝ ዓመት እስኪሆናት ድረስ ነው፣ ይህ ነው በሕግ ዘንድ ተቀባይነት ያለው› 'Abd ar-Rahman al-Gaziri, al-Fiqh 'ala al-Mazahib al-Arba'a, Dar al-Kutub al- 'Elmeyah, 1990, vol. 4, p. 522፡፡

እናትየው ልጇን በጣም አስቸጋሪ በሆኑት ዓመታት ውስጥ ልትይዝ ትችላለች በሌሊት በመንቃት ጡት ልታጠባ እና የሽንት ጨርቅ ልትቀይር ሽንት ቤት አጠቃቀምን ልታሰለጥን ወ.ዘ.ተ፡፡ ከዚያም ልጅ ከመረዳት ወጥቶ መርዳት ሲችል አባትየው ይንከባከበዋል፡፡

5. በገነት ውስጥ ያሉ ወንዶች ለዘላለም ውብ ከሆኑ ድንግል ሴቶች ጋር ግብረ ስጋ ግንኙነትን ይደሰታሉ፡

ሙስሊም ወንዶች በዚህ ዓለም ሕይወት ውስጥ ብዙ ሚስቶች ተፈቅዶላቸዋል፡፡ በገነት ውስጥ በውበታቸው ፍፁም በሆኑ በተጨማሪ ሴቶች ይሸለማሉ፡፡ ሙዓዝ የአላህ መልክተኛ ተናገረ ያለውን የሚከተለውን ዘግቧል፡ ‹ሴት በዚህ ዓለም ውስጥ ባሏን ማስቸገር አይኖርባትም፣ ነገር ግን ንፁህ ዓይን ያላት ድንግል የሆነችው ሚስቱ (ሁሪስ) ለእርሷ እንዲህ አትላትም፡ ‹አታስቸግሪው፡፡ አላህ ያጥፋሽና፣ እርሱ ካንቺ ጋር የሚያልፍ እንግዳ ብቻ ነው እንዲሁም አንቺን ጥሎሽ ወደ እኛ ለመምጣት ጊዜው በጣም ቅርብ ነው› Mishkat al-Masabih, Book 1, duties of husband and wife, Hadith No.62፡፡

ለዚህ ልማድ የሚሽካት ኤዲተር የሆነው በግርጌ ማስታወሻው ላይ የሚከተለውን ጽፏል፡ ‹ማንም ሴት ለባሏ ችግርና ጭንቀትን መስጠት አይኖርባትም፡፡ በቤት ውስጥ እርሷ ሰላምንና ምቾትን ልትሰጠው ይገባታል፡፡ ነገር ግን በተቃራኒው መንገድ የምታደርግ ከሆነ በገነት ውስጥ እርሷ የእርሱ ጓደኛ ልትሆን አትችልም፡፡ እዚያ ንፁህ ዓይን ያላቸው ድንግሎች የእርሱ ጓደኞች ይሆናሉ›፡፡ ምክንያቱም ቁርአን ተስፋ የገባው እግዚአብሔርን የሚፈሩት ሰዎች በገነት ውስጥ ውብ የሆኑ ሴቶችን ነውና፡፡ የእነሱም ገለፃ የሚከተለው ነው፡ ‹እነሆ እነዚያ (ወንዶች) ተግባሮቻቸውን የጠበቁት የሚሆኑት በአትክልት ቦታዎች መካከል እና በውሃ ምንጭ መካከል ነው የሚሆኑት ከሐር በተሰሩና በሐር በተጌጡ ልብሶች ለብሰው ፊት ለፊት እየተያዩ፡፡ እንዲሁም ደግሞ (ይሆናል)፡፡ እኛም ከ(ሁሪዎች) ጋር እናጋባቸዋለን ነጭ ከሆኑትና የሚያምሩ ሰፋፊ ዓይኖች ካሏቸው ጋር› The Qur'an 44:51-54 (Pickthall's translation)፡፡ ‹በዚህ ውስጥ የቤት ሰራተኞች እይታቸውን በመገደብ፣ በፊታቸው በማንም ሰው ወይንም ጂኒ ያልተነኩ ሆነው እንደ ቀይ ፈርጥ ተወዳጅ፣ እንደ እምነ በረድ ውብ ሆነው› The Qur'an, 55:56-58 (Arberry's translation)፡፡ ‹ውብ እና ነጭ የሆኑት (ሁሪስ) ... ከትልቅ ጥቁር ዓይን ጋር፣ በአዳራሾቻቸው ውስጥ ተጠብቀው› The Qur'an, 55:72 (Rodwells translation)፡፡

‹በእርግጥ እግዚአብሔርን ለሚፈሩት የዋስትና ቦታ ይጠብቃቸዋል፣ ይህም የአትክልት ቦታና የወይን ቦታ ነው እንዲሁም ጡታቸው ትልልቅ የሆኑ ሴቶች ሰራተኞች Pickthall in his translation of the Qur'an omits this description all together, although it is found in Dawood's, Rodwell's, and Arberry's translations) ዕድሜያቸው ተመሳሳይ የሆነ እንዲሁም ሙሉ የሆነ ፅዋ› The Qur'an, 78:33 (Arberry's translation)፡፡

ከዚህም እግዚአብሔርን የሚፈሩቱ በገነት ውስጥ ካሉ ሴቶች ጋር ይጋባሉ፡፡ እነዚያም ሴቶች ሌሎችን በፍፁም አይመለከቱም፣ ከባሎቻቸው በስተቀር፡፡ እነሱም በአዳራሾቻቸው ውስጥ ይገደባሉ፡፡ እነዚያ ሴቶች በገነት ውስጥ ያሉት ነጮች ናቸው እንደዚሁም በአረቢያ እንዳሉት ጥቁር ቆዳ እንዳላቸው አይደሉም፡፡ የእነሱም ውበት ፍፁም ነው የሚሆነው፡፡ ዓይኖቻቸውም ሰፋፊና ትልልቅ ናቸው እናም ጡቶቻቸውም ‹ካዋ-ኢብ› ናቸው፣ ማለትም ያበጡና ጠንካራዎች እንጂ የሟሸሹ (የወደቁ) አይደሉም› Ibn Kathir, commenting on Q. 78:33፡፡

እንዲሁም ሐዲት የሚነግረን፡ ‹በገነት ውስጥ ... እያንዳንዱ ሰው ሁለት ሚስቶች ይኖሩታል (በጣም ውብ የሆኑ) የጭን አጥንቶቻቸው መቅኒ ከስጋዎቻቸው ስር ያበራሉ እንዲሁም በገነት ውስጥ ሚስት የማይኖረው ማንም አይገኝም› Sahih Muslim, English translation, Hadith No. 6793, see also 6794, 6795 &6797፡፡

ሌላ ሐዲት የሚስቶችን ቁጥር ሰባ ሁለት ያደርሰዋል፡፡ ሰባ ሴቶች በተለይም ተፈጥረዋል ሁለቱም የሰው ሴቶች ናቸው Ibn-Kathir commenting on Q. 56:35-37፣ የምድር ሚስቶቹ ከውቦቹ ውስጥ ሊጨመሩ ይችላሉ፣ ነገር ግን በገነት ውስጥ ለእርሱ ተጨማሪ ሴቶች ይኖሩለታል ይህም እስከ ሰባ ሁለት ድረስም እንኳን ነው፡፡ ‹ቅዱሱ ነቢይ እንዲህ አለ፡- ‹አማኙ በገነት ውስጥ የግብረ ስጋ ግንኙነትን ያደርግ ዘንድ እንዲህና እንዲህ ዓይነት ጥንካሬ (ብርታት) ይሰጠዋል፡፡ ቀጥሎም እንደሚከተለው ተጠይቆ ነበር፡ ‹ኦ የአላህ ነቢይ!` እርሱ ይችላልን?› እርሱም አለ፡ ‹እርሱ የአንድ መቶ ሰዎች ጥንካሬ ይሰጠዋል› Mishkat al-Masabih, English-Arabic translation, Book IV, Chapter XLII, Paradise and Hell, Hadith No.24፡፡ (ይህ ሐዲት የተጠቀሰው ከቲሪምዚ ሲሆን በቲሪምዚ የተመደበውም እንደ ሳሂህ ነው ማለትም ጤናማና ምንም ስህተት የሌለው ሐዲት ተደርጎ ነው›) Sunan at-Tirmizi, kitab sifat al-Ganah, Hadith No. 2536፡፡

ኢብን ካቲር በትንተናው ውስጥ ያተኮረበት በገነት ውስጥ የሚደረገው የግብረ ስጋ ግንኙነትን ተፈጥሮ ልክ እንደ ምድር የሆነ አድርጎ በሌላ ሐዲት እንደተገለፀ ነው፡

‹ነቢዩ እንደሚከተለው ተጠይቆ ነበር፡ እኛ በገነት ውስጥ ግብረ ስጋ ግንኙነት ይኖረናልን? እርሱም መለሰ፡ ‹አዎ በእርሱ ነፍሴን በእጆቹ በያዛት፣ እናም ይደረጋል ዳማን፣ ዳማን (ማለትም በመረበሽና በግፊት የሚደረግ ግብረ ስጋ ግንኙነት ነው Ibn-Kathir, vol. 8, page 11, commentary on Q. 56:35-37, published by Dar Ash-sha'b, editorial footnote by the publisher explaining the meaning of 'dahman'.)፣ ይህም ካለቀ በኋላ እርሷ እንደገና ንፁህ እና ድንግል ወደመሆን ትመለሳለች› Ibn-Kathir, vol. 8, commenting on Q. 56:35-37. 108. The Qur'an 36:55, published by Dar Ash-sha'b, editorial footnote by the publisher explaining the meaning of 'dahman'፡፡

እስልምና የሴትን ድንግልና ለዘላለም የመውሰድን (ማለትም ሁልጊዜ እንደገና) ጉዳይ በባህል የተያያዘው ከገነት ጋር ነው፡፡ በጣም ታዋቂው ተንታኝ አል-ጃላላያን ያየው በቁርአን ጥቅስ ላይ የተጠቀሰውን መደሰትን ነው ‹‹የገነት ነዋሪዎች አሁን በመደሰት ላይ ናቸው› Ibn-Kathir, vol. 8, The Qur'an 36:55, published by Dar Ash-sha'b, editorial footnote by the publisher explaining the meaning of 'dahman'፡፡ ‹ይህም የሴቶችን ድንግልና የመውሰድ ተግባርን ይጨምራል› በማለት ነው፡፡ Tafsir al-Jalalayn on Q. 36:55፡፡

ታላቁ ምሁር ጋዛሊ የጠቀሰው አል-ኦዛይ ከቀደሙት ምሁራን እንዱ የሆነውና ከላይ ያለውን ጥቅስ የተነተነው ‹በደስታ ተጠምደዋል ማለት የድንግሎችን ድንግልና የመውሰድ ነው በማለት ተናግሯል›፡፡ Ihy'a 'Uloum ed-Din by Ghazali, Dar al-Kotob al-'Elmeyah, Beirut, Vol IV, p. 575፡፡ እንዲሁም ደግሞ ታላቁ ተንታኝ ኢብን አባስ ከላይ ስላለው ጥቅስ የተናገረው፡ ‹(ፋክሁን) ማለት የድንግሎችን ድንግልና በመውደስ መደሰት ማለት ነው› ብሎ ነው፡፡ Ibn 'Abbas, Tanweer al-Miqbas, commenting on Q. 36:55፡፡

አንድ ሰው እጅግ በጣም የግብረ ስጋ ግንኙነት ደስታ የሚኖረው በምድር ብቻ ሳይሆን ነገር ግን በገነትም ነው፡፡ በምድር ላይ ብዙ ሴቶችን አግብቶ ሊሆን ይችላል ነገር ግን ምድራዊ ሕይወቱም ካለፈ በኋላ በገነት ውስጥ በጣም ቆንጆ የሆኑ ሴቶች እንዲኖሩት ተስፋ ሊያደርግ ይችላል፡፡ እርሱም እስከ ሰባ ሁለት ውቦች ሊኖሩት ይችላል፣ እንዲሁም የግብረ ስጋ ግንኙነት ለማድረግ እንዲችል የአንድ መቶ ሰዎች ብርታት ይሰጠዋል፡፡ እርሱም ግብረ ስጋ ግንኙነትን በታላቅ ግፊትና ረብሻም ሊያደርግ ይችላል፣ በሌላ ጎኑ ለሴቶች ግን ምንም የተስፋ ቃል አልተገባላቸውም፡፡ ለአንድ ሴት ስለ አንድ ወንድ እንኳን የተገባ የማረጋገጫ ቃል የላትም፡፡

አሁንም እንደገና ሁሉም ጥቅምና ደስታ ያለው ለወንዱ ነው፣ ሴቶቹ ለዘላለም ለእርሱ ዓላማ መጠቀሚያ መሆን አለባቸው፡፡ ደስታ የእሱ ነው ለእርሷ ግን በዚህም ዓለም ሆነ በሚመጣው ዓለም ያላት ረብሻ ነው፡፡

የዚህ ምክንያቱ ምንድነው?

በእስልምና ወንዶች ከሴቶች ይልቅ እንዲህ ዓይነት መብት ያላቸው ለምንድነው? የሚከተለው ጽሑፍ በአብዛኛው የተወሰደው በእስልምና ሕግ ላይ በአሁኑ ጊዜ ባለ በዘመናዊው ምሁር ጋዚሪ ከተዘጋጀው ስራ ነው፣ ይህ የእሱ ስራ ወንዶች በሴቶች ላይ ለምን የበለጠ መብት እንዳላቸው ይገልጥ ይሆናል፡፡

የአዘጋጁ ማሳሰቢያ፡

ሴቶች በንፁህ እስልምና በሚለው ጽሑፍ ስር የቀረቡት እውነታዎች በትክክል እንደሚያስረዱት ከሆነ በሙስሊም ሴቶችና ወንዶች መካከል ያለው ልዩነት እጅግ በጣም የጎላ ነው፡፡ ግን ለምን፣ ልዩነቱስ የመነጨው ከማን ነው? የሚሉ ጥቄዎችን ስናነሳ መልሱ ከእግዚአብሔር ወይንም ደግሞ ከሰዎች መሆን አለበት ነው፡፡ መቼም ከእግዚአብሔር ሊሆን አይችልም ምክንያቱም እግዚአብሔር ወንዶችንም ሴቶችንም እኩል እንደሚያይ ተፈጥሮ እንኳን እራሱ ያስተምረናልና፡፡ ታዲያ ከማን ነው፣ መሆን ያለበት ከሰው ባህላዊ ልማዳዊ አመለካከት እንዲሁም ከባህል ከመነጨ የወንዶች የበላይነትና የእራስ ወዳድነት ነው፡፡ ከዚህ በላይ ያሉት ሐዲቶች እንደሚያመለክቱት የአረብ ወንዶች የግብረ ስጋ ግንኙነት ከፍተኛ ፍላጎት ችግር አለባቸው ይላሉና፡፡

የሆነው ሆኖ፣ የሴቶችና የወንዶች ከፍተኛ ልዩነቶች ምንጭ እግዚአብሔር ከሆነ የሙስሊሞችን አምላክን ፍትሃዊነት ጥያቄ ውስጥ የሚጥል ነው፡፡ ከሰዎች ነው የመነጨው ወደማለት ከመጣን ደግሞ የእስልምናን እውነተኛነት ችግር ውስጥ የሚጥል ነው፡፡

በሁለቱም መንገድ እስልምናን እንደ ትክክለኛ እምነት ለመውሰድና ለመቀበል ለአዕምሮ በጣም ይከብዳል፡፡ እዚህ ላይ ነው ለአንባቢዎች አዕምሮ ግልጥ ጥያቄን ለማቅረብ የምንፈልገው፡፡ የምንከተለውን ሃይማኖት የምንከተልበት አንድ የተጨበጠ ቁም ነገርን ልናገኝበት ያስፈልጋል፡፡ ከዚህም በላይ ለሰዎች ልጆች ሁሉ ማለትም ያለምንም የፆታ ልዩነት የሚሰጠው የተስፋ ቃል ምንድነው የሚለውንም ልንጠይቅ ይገባናል፡፡ እውነተኛው አምላክ እግዚአብሔር ለወንዶችም ሆነ ለሴቶች ያለው አመለካከት ምንድነው? ይህንን በተመለከተ መጽሐፍ ቅዱስ የሰው ዘር ያለምንም የፆታ ልዩነት በእግዚአብሔር ላይ ያመፀና የእግዚአብሔር የፍርድ ቁጣ የሚጠብቀው እንደሆነ ነው፡፡

ነገር ግን ለኃጢአተኛው ለሰው ልጅ እግዚአብሔር ያዘጋጀው አስደናቂ ምህረት እጅግ ግሩም ነው፡፡ ይህም ምህረት የመጣው በልጁ በጌታ በኢየሱስ ወደ ምድር መምጣትና በመስቀል ላይ ኃጢአተኞችን ወክሎ መሞት ነው፡፡ ከዚህ የተነሳ ማንኛውም ሰው፣ ማለትም ወንድም ይሁን ሴት ንስሐ ገብቶ በጌታ በኢየሱስ በኩል ወደ እግዚአብሔር ለምህረት ቢቀርብ ይቅር እንደሚባል አዲስ ሕይወትን እንደሚቀበልና የዘላለምም መንግስት ሕይወትን እንደሚያገኝ ይናገራል፡፡ ይህ መልእክት ወጥ ነው፤ ሎጂካል ነው፤ የእግዚአብሔር ነው፣ አንባቢዎች ሆይ ለዘላለም ሕይወት ወደሚጠቅማችሁ ወደዚህ መልእክት እንድትመጡ መጽሐፍ ቅዱስን በጥንቃቄ እንድታነቡ ወደ ፈጣሪያችሁ ወደ እውነተኛው እግዚአብሔር እንድትመጡ እንጋብዛችኋለን፣ እግዚአብሔር በፍቅሩና በፀጋው ይርዳችሁ አሜን፡፡
I love ethiopia
ጎነጠ
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 103
Joined: Wed Aug 03, 2005 9:07 am
Location: ethiopia

Return to Warka General

Who is online

Users browsing this forum: No registered users and 4 guests