:)

The Love Forum (love, relationship) (የኔ ቆንጆ እንተዋወቅ :-)

Postby recho » Sat Jan 18, 2014 7:25 pm

እንኩዋን አደረሳቹ!!!!!

ብርሀነ ጥምቀቱን ለምታከብሩ ሁሉ መልካም የከተራ/የጥምቀት በአል እንዲሆንላቹ ከልብ እመኛለሁ ... ጥምቀት ባለሁበት በታላቅ ሁኔታ ይከበራል .. እና ይሄንንው በማስመልከት አንዱን እዚህ አገር ያደገ ልጅ(ልጅ ስትባሉ ልጅ እናይመስላቹ .. ሰውዬ ነው :lol: ) ስለዛሬው በአል ያውቅ እንደሆነ ጠየቅኩት .. እና ጥምቀት ብል .. ሲጠመቅ ብል ምንም ... እና መጨረሻ ላይ በናንተው Epiphany የሚባለው ስለው ምን ቢለኝ ጥሩ ነው ኦ ኦ ኢዝ ዛት ኢትዩጵያን ኤፕሪል ዘ ፉል? :lol: :lol: እረ ባካቹ ባካቹ ልጆቻቹን አማርኛው ቢቀር ትንሽ እንኩዋን ባህልና ሀይማኖት አስተምሩ !!!!! በዚህ ከቀጠለ እኮ የሚቀጥለው ጀነሬሽን ጥምቀትን እንደ አፕሪል ዘ ፉል ዴይ ሊያከብረው ነው ማለት ነው .. :lol: :lol:

ለማንኛውም .. መልካም በአል ለሁላችን ... :)
"ሰነፍ በልቡ። አምላክ የለም ይላል በሥራቸው ረከሱ ጐስቈሉ በጎ ነገርን የሚሠራ የለም " መዝሙረ ዳዊት ምእራፍ 14:1
recho
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 3171
Joined: Mon Sep 20, 2004 12:28 pm
Location: Earth

Postby ለማ12 » Sun Jan 19, 2014 4:15 pm

ጥምቀት ይሁንልሽ መጀመሪያ:


በተወልድኩበት አካባቢ ወጣቶች የሚተጫጩበት ቀን ዋናውና አንዱ ጥምቀት ነው ታዲያ አንዱ ጎበዝ ምን ሆነ መሰለሽ?
በዚህ ቀን ወጣት ሴቶች ለመታየትና ያው ለመከጀል ያለ የሌለውን ልብስ ልብሰው 1 ኪሎ አምባሬ ጭቃም ቢሆን ተለቅልቀው ይወጣሉ
ታዲያ አንዱ በቅባት ያማርችውን ልጅ አይቶ ማታ እቤቱ ሄዶ ሰዎቹን ያችን ልጅ ካላመጠችሁልኝና ካላጋባችሁኝ ሞቼ እገኛለሁ ይላል:
ያው የወላጅን ነገር ታውቂዋለሽ እንደምንም ብለው ያጋቡታል
ታዲያ አብረው አድረው በነጋው ሲአያት ግራኝ የወረወረው ድንጋይ መስላ ትታየዋለች
በሉ ባመጣችሁበት ውሰዱልኝ ይላል:
እህ እምቢ ካለ ትሂድ እንጂ ምን እናደርጋለን ብለው ዘመዶቹም ይስዱአታል:
እሱም ሁለትኛ አጋቡኝ ሳይል አመቱ ይደርሳል

እንደተለመደው በጥምቀት እለት ወጣቶቹ ለባብሰው ተቀባብተ ው ሲወጡ ከደJ ቁጭ ብሎ ያያል
አየ
ያምናው ጥምቀት እኔን ወጋህ ደግሞ የዘንድሮው ደግሞ ማነን ትወጋ ይሁን አለ
:


ታዲያ የትኛውን ለልጆች እናስተምር ?
ተጠንቀቁ ውይስ በደብ ተመልከቱ
ለማ12
ውሃ አጠጪ
ውሃ አጠጪ
 
Posts: 1147
Joined: Sat Jun 16, 2012 9:46 am

Postby ለማ12 » Thu Jan 23, 2014 4:32 pm

እረ ብቅ በይ ከጉአዳ
የኔ ጎርዳዳ!
ለማ12
ውሃ አጠጪ
ውሃ አጠጪ
 
Posts: 1147
Joined: Sat Jun 16, 2012 9:46 am

Postby recho » Fri Jan 24, 2014 7:25 pm

ለማ12 wrote:እረ ብቅ በይ ከጉአዳ
የኔ ጎርዳዳ!
አለሁ አለሁ አለሜ :lol: :lol:
"ሰነፍ በልቡ። አምላክ የለም ይላል በሥራቸው ረከሱ ጐስቈሉ በጎ ነገርን የሚሠራ የለም " መዝሙረ ዳዊት ምእራፍ 14:1
recho
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 3171
Joined: Mon Sep 20, 2004 12:28 pm
Location: Earth

Postby ለማ12 » Sat Jan 25, 2014 12:05 pm

ርቺ አለሁ በይኝ የኔ ልጅ:.


ሰዎች ይርባቸውና ምን አደረጉ መሰለሽ


ሲጫዎቱ ጅብ በልቶ ያተረፈውን ያገኙና ይበሉታል

ከጠገቡ ወዲያ ሲአስቡት ጅብ የበላው ነው ታዲያ
አንድ አባት ዘንድ ሄደው አባት ጅብ የበላውን ቢበሉት ምን ይላል ብለው ይጠቃሉ
እነዚህ አባትም
ሲርብ ነው ሳይርብ ብለው መልሰው ይጠይቃሉ እነዚያ ሰዎችም ሲርብ ይላሉ
አይ ልጆቼ ሲርብማ እራሱንስ ቢበሉት ምን ይላል አሉ አሁንም
ምን ይላል ርቺ?
ለማ12
ውሃ አጠጪ
ውሃ አጠጪ
 
Posts: 1147
Joined: Sat Jun 16, 2012 9:46 am

Postby recho » Sat Feb 15, 2014 1:13 pm

ለማ12 wrote:ርቺ አለሁ በይኝ የኔ ልጅ:.
አለሁ አለሁ ... ሰላም ነው .. ምን ብቅ እያልኩ እያየሁዋቹ እኮ ዛሬ ነገ ስል :lol:
"ሰነፍ በልቡ። አምላክ የለም ይላል በሥራቸው ረከሱ ጐስቈሉ በጎ ነገርን የሚሠራ የለም " መዝሙረ ዳዊት ምእራፍ 14:1
recho
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 3171
Joined: Mon Sep 20, 2004 12:28 pm
Location: Earth

Postby ለማ12 » Sat Feb 15, 2014 2:25 pm

መልካም ሪቺ ሰላም አለሽልኝ?

ያው ሰው እድሜው ሲገፋ የሚናገረውን አይውቅምና የሚአስቀይም ነገር ስናገር እረ ይተው አባቴ በይኝ:

አሁን አለሁ እዚህ
ለማ12
ውሃ አጠጪ
ውሃ አጠጪ
 
Posts: 1147
Joined: Sat Jun 16, 2012 9:46 am

Postby ዳግማዊ ዋለልኝ » Fri Feb 21, 2014 2:56 pm

"እነሆ መሸም; ነጋም....ዓርብም ሆነ.....ነፍሳችን ሐሴት ታደርግ ዘንድ ወደደች.....ማልዳም ወደ recho ቤት ገሰገሰች.....አንቺ recho; የህዳሴ እናት ወዴት አለሽ? ከሰንጴር እና አልማዝ ይልቅ የከበሩ ጨዋታዎችሽ ወዴት ናቸው? እንደዓባይና አማዞን የሚፈሱት ወጎችሽስ የት ተሰወሩ? እንደቶርኔዶና ሀሪኬን የሚያናውጡት የክለብ ትዝብቶች ለምንስ ራቁን? እንደአዕዋፍ ዝማሬ ለጆሮ ስንቅ የሆኑት ሳቆችሽን ከሰማናቸው ለምን ቆየን? እንደተወረወረ ፍላፃ ልብን የሚያደሙት ስድቦችሽስ ለምን ከአፎታቸው ተከተቱ?.......ውዴ ሆይ; የህዳሴ እናት....ክረምቱ አልፎ; የፀደዩን መምጣት ለማብሰር; ከአቦ ሸማኔ ፈጥነሽ እየገሰገስሽ ትመጪ ዘንድ ያዕቆብ ራሔልን በጠበቀበት ፅናትና ጉጉት እለምንሻለሁ"

መሀልየ መሀልየ ዘዳግማዊ
ያልታተመ መድብል :lol:
"እቺ ለቅሶ ከፍየል በላይ ነች"
ዳግማዊ ዋለልኝ
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 3193
Joined: Wed Oct 20, 2010 12:09 am

Postby ዳግማዊ ዋለልኝ » Fri Feb 28, 2014 3:46 pm

እነሆ ቀናቶች መሹም; ነጉም; ሳምንት ሆነ; ተከታዩም ዓርብ ደረሰ

"recho ሆይ፥ ተነሺ፤ የህዳሴ እናት ሆይ፥ ነዪ።

እነሆ፥ ክረምት አለፈ፥ ዝናቡም አልፎ ሄደ።

አበቦች በምድር ላይ ተገለጡ፥ የዜማም ጊዜ ደረሰ፥ የቊርዬውም ቃል በምድራችን ተሰማ።

በለሱ ጐመራ፥ ወይኖችም አበቡ መዓዛቸውንም ሰጡ፤ recho ሆይ፥ ተነሺ፤ የህዳሴ እናት ሆይ፥ ነዪ።

በምድረ አሜሪካ; በህንፃ ደኖች መሀል ያለሽ ርግብ ሆይ፥ ቃልሽ መልካም ፊትሽም ያማረ ነውና መልክሽን አሳዪኝ፥ ድምፅሽንም አሰሚኝ።" :D

ከመኃልየ መኃልየ ዘሰሎምን ተወስዶ የተሻሻለ :D
"እቺ ለቅሶ ከፍየል በላይ ነች"
ዳግማዊ ዋለልኝ
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 3193
Joined: Wed Oct 20, 2010 12:09 am

Postby recho » Fri Mar 07, 2014 4:42 pm

:lol: :lol: :lol: ኢት ሉክስ ላይክ........ ሳምባዲ ሚስድ ሪቾ ሶ ባድ :lol: :lol: :lol: :lol:


ዳግማዊ ዋለልኝ wrote:እነሆ ቀናቶች መሹም; ነጉም; ሳምንት ሆነ; ተከታዩም ዓርብ ደረሰ

"recho ሆይ፥ ተነሺ፤ የህዳሴ እናት ሆይ፥ ነዪ።

እነሆ፥ ክረምት አለፈ፥ ዝናቡም አልፎ ሄደ።

አበቦች በምድር ላይ ተገለጡ፥ የዜማም ጊዜ ደረሰ፥ የቊርዬውም ቃል በምድራችን ተሰማ።

በለሱ ጐመራ፥ ወይኖችም አበቡ መዓዛቸውንም ሰጡ፤ recho ሆይ፥ ተነሺ፤ የህዳሴ እናት ሆይ፥ ነዪ።

በምድረ አሜሪካ; በህንፃ ደኖች መሀል ያለሽ ርግብ ሆይ፥ ቃልሽ መልካም ፊትሽም ያማረ ነውና መልክሽን አሳዪኝ፥ ድምፅሽንም አሰሚኝ።" :D

ከመኃልየ መኃልየ ዘሰሎምን ተወስዶ የተሻሻለ :D
"ሰነፍ በልቡ። አምላክ የለም ይላል በሥራቸው ረከሱ ጐስቈሉ በጎ ነገርን የሚሠራ የለም " መዝሙረ ዳዊት ምእራፍ 14:1
recho
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 3171
Joined: Mon Sep 20, 2004 12:28 pm
Location: Earth

Postby ለማ12 » Fri Mar 07, 2014 5:07 pm

ርቺ ያልሽ ፈረንጅኛ ባይገባኝም
እንዲሁ መግባብት ይቸግረን አይመስለኝም
ለማ12
ውሃ አጠጪ
ውሃ አጠጪ
 
Posts: 1147
Joined: Sat Jun 16, 2012 9:46 am

Postby recho » Fri Mar 07, 2014 5:58 pm

ለማ12 wrote:ርቺ ያልሽ ፈረንጅኛ ባይገባኝም
እንዲሁ መግባብት ይቸግረን አይመስለኝም
ለምዬ ሆዴዋ .. ሰላም ነህ ወይ? መለስ ቀለስ እያልኩኮ ማንበቤን አልተውኩም .. እንደውም በቀደሙን ለታ አንዱ በውነተኛው አለም ያለውን ለምዬን ብታዩትኮ ምናምን ሲል አይይይይ ምርጫኮ አንደኛ ነኝ ብዬ :D ስል ነበር :lol: እንዴት ነህማ አለሜ? :D
"ሰነፍ በልቡ። አምላክ የለም ይላል በሥራቸው ረከሱ ጐስቈሉ በጎ ነገርን የሚሠራ የለም " መዝሙረ ዳዊት ምእራፍ 14:1
recho
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 3171
Joined: Mon Sep 20, 2004 12:28 pm
Location: Earth

Postby ለማ12 » Fri Mar 07, 2014 6:16 pm

ርቺ አውቃው አረፈች:

ሰላም ነሽልኝ?
ሰሞኑን እፈረንጅ ሀገር ስለሆንኩ ጊዜ በደርዘን ነው ያለኝ
ምን ላጭውትሽ?
ለማ12
ውሃ አጠጪ
ውሃ አጠጪ
 
Posts: 1147
Joined: Sat Jun 16, 2012 9:46 am

Postby ዳግማዊ ዋለልኝ » Fri Mar 07, 2014 6:17 pm

recho wrote:መለስ ቀለስ እያልኩኮ ማንበቤን አልተውኩም


ጉሮሮዬ እስኪደርቅ ስጮህ እያየሽ እንዳላየሽ ማለፈሽ በጣም ይገርማልSMH :D ልብሽን ምን አደነደነው እቴ :?: :lol: ደህና ነሽ ግን :?: :D
"እቺ ለቅሶ ከፍየል በላይ ነች"
ዳግማዊ ዋለልኝ
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 3193
Joined: Wed Oct 20, 2010 12:09 am

Postby recho » Fri Mar 07, 2014 6:25 pm

ዳግማዊ ዋለልኝ wrote:
recho wrote:መለስ ቀለስ እያልኩኮ ማንበቤን አልተውኩም


ጉሮሮዬ እስኪደርቅ ስጮህ እያየሽ እንዳላየሽ ማለፈሽ በጣም ይገርማልSMH :D ልብሽን ምን አደነደነው እቴ :?: :lol: ደህና ነሽ ግን :?: :D
ውይ በስማም ዳጊቾ ይቅርቶች እንዴ እንደዚህማ ባንዴ አትቀየም እንዴ ቅቅቅ አይቻለሁ ግን ቢዚ ሆንኩኛ .. በዛላይ ማክቡክ ጃቫ አይሰራም አሉ .. አሉ ነው .. የኔውም ሎግ ኢን አያስደርገኝም ስለዚህ ያው እያየሁ ማለፍ ነው :( ያው ሲቻል ብቅ አልኩኝ .. አንተ ሰላም ነህ ? ሪቾ እንዳማረባት አለችው :)
"ሰነፍ በልቡ። አምላክ የለም ይላል በሥራቸው ረከሱ ጐስቈሉ በጎ ነገርን የሚሠራ የለም " መዝሙረ ዳዊት ምእራፍ 14:1
recho
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 3171
Joined: Mon Sep 20, 2004 12:28 pm
Location: Earth

PreviousNext

Return to Warka Intimate - ዋርካ ፍቅር

Who is online

Users browsing this forum: No registered users and 4 guests