ተጠየቅ ዲጎኔ

Topics related to cultures, arts, languages, arts such as humor, music, traditional literary genres of poems, ግጥም ፣ ቅኔ ፣ ተረትና ምሳሌ)

ተጠየቅ ዲጎኔ

Postby -...- » Thu Apr 03, 2014 5:09 pm

ወንድም ዲጎኔ ይችን ቪዲዮ ከለጠፍክበት ከዛኛው ክፍል አመጣኋት ።

http://www.youtube.com/watch?v=csadJdutzbU

ቪዲዮውን ካየሁ በኋላ የሚከተሉትን ጥያቄዎች ልጠይቅህ ፈለግሁ ። ጴንጤን ዲፌንድ ሳታደርግ የህሊናህን እንደምትመልስልኝ እቅጯን ተናግረህ የመሸበት የምታድር ሃቀኝነትህን በመተማመን ነው

1.እነዚህ መዘምራን ካባ ለብሰው ጃኖ አደግድገው መቋሚያ ይዘው ጸናጽል ይዘው ከበሮ ይዘው በኦርቶዶክስ ሽብሸባ ለምን ለመቅረብ ፈለጉ ?

2. አንተ ራስህ ከበሮ ጸናጽል መቋሚያ ስታይ መጀመሪያ በአእምሮህ የሚመጣው የትኛው ሃይማኖት ነው ?

3.ኦርቶዶክስ መስሎ በያረዳዊ ዜማ(ያሬድ ማለት ኦርቶዶክስ ማለት ነው ብለህ ውሰደው ምክንያቱም ያሬድ ህይወቱን በሙሉ በኦርቶዶክስ ዝማሬ/ዜማ ማጠናቀር ያሳለፈ ነው)መቅረቡ ማታለል ነው ውይስ አይደለም ?

ማንንም ጴንጤን ጭምር ሳትፈራ እውነቷን እንደምትነግረኝ አልጠራጠርም

ይህ ቪዲዮ የበግ ለምድ ለብሶ የሚመጣ ተኩላ የሚለውን ጥቅስ ያስታውሰኛል
ሞቼ እየተነሳሁ ልሙት እንደገና
አንድ ሞት ላገሬ አይበቃትምና
-...-
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 401
Joined: Thu Feb 09, 2012 8:36 pm

Re: ተጠየቅ ዲጎኔ

Postby ዲጎኔ » Thu Apr 03, 2014 9:23 pm

ሰላም ለሁላችን ይሁን
በመጀመሪያ ሁለታችን በዚያ ትውልድ ለህዝቦቻችን መብት በለጋነት መታገላችን በቅርቡ ስለበሰርክ ደስ ብሎኛል::
ወደመልሱ በአጭር ባጭሩ ስጉዋዝ:-
1. ልጆቹ የሙሉወንጌል/ ጰንጠቆስጤ መዘምራን ሲሆኑ ብዙዎቹ ኦርቶዶክስ እያሉ ተሀድሶ የጀመሩ ስድብ መወገሩ ሲበዛ ወደዛ የሄዱ ናቸው::አንዱ መሪያቸው እንዳልካቸው ከቅድስት ስላሴ ወደመጥምቃዊያን ማህበር ገብቷል::ሌሎቹ ከነአባ ዮናስ ሙሉ ወንጌል::ይህን ዜማ ያቀረቡት ዜማው ኢትዮጲያዊ በመሆኑ ስላደጉበት ቅዱስ ቃሉን ስላዘለ ነው::
2.ጽናጽል ከበሮ ሳይ ትዝ የሚለኝ አዎ በልጅነት ለዳመራ ለጥምቀት በተዋህዶ ያሳለፍኩዋቸው ዘመናት ናቸው::
3. ያሬዳዊ ዜማ መከተል ማታለል አይደለም::ስለመንፈሳዊ ሙዚቃ በአውሮፓ ተሀድሶ ብዙ ተብሏል::ማርቲን ሉተር ብዙ ካስተማረ በሁውላ ሁሉም ዘመናዊ ሙዚቃ ለጌታ ክብር መዋል ጀምሯል::ድሬደዋ ከሚካኤል የመጡ የእኛን የኪቦርድ ሙዝቃ ሲሰሙ ጋሼ ይህ አያስደንስም? ያሉኝ ትዝ ይለኛል::ነገር ግን ሁሉንም በባህላዊ ብቻ ካደረግን በሳርቤት ልንቀር ነው ድምጽ ማጉያ ላይኖረን ነው::ቅዱስ ቃሉ እስትንፋስ ያለው ሁሉ ይዘምር እንደሚለው ሙዚቃ ሁሉ ጌታን ያክብር እላለሁ::ጥቅሱ የበግ ለምድ ለብሰው የሚለው ያለቦታው የሚደጋገም ጥቅስ ነው::ልጆቹ በውነት ክርስቶስን ከልብ ያመኑ የተረዱትን መመስከርና መኖር ሲጀምሩ ተገፍተው የወጡ ናቸው እንጂ አንዳች ለምድ አለበሱ::እንደውም መከራ ስለክርስቶስ ሲሉ በወላጆቻቸው ሳይቀር የሚደርስባቸው ናቸው::ሀገር ቤት ከእድር ውጡ ስንባል እኔ በእድሩ የተሳተፍኩ ስለነበር ስለምጠቅቸውም አልነኩኝም::ወጣቶችና አንድ አንጋፋ ኮሎኔልን ቤተስብ ግን መብት ሲጋፉ ነበር::እድሩ በህግ የሚያስጠይቀው ቢሆንም ሁሉን ትተን ወጥተን የራሳችንን መረዳጃ እድር መስርተናል::መረሳ የሚባል የፈቃድ ክፍሉ ወያኔ ሀላፊ ዘንድ ቀርበን ነው የተፈቀደልን::ወጣቶቹ ግን ብዙ ይሰቃዩ ነበር::ደ/ብርሀን አንዲት እህት ወደኛ ገብታ እናቷ ሲሞቱ አይቀበሩም ብለው አባ ጳውሎስ ቀብርቦታ የፈቀዱበት ጊዜ ነበር::ድሬደዋ መስጅድም አባላችን የተቀበረበት ጊዘ ነበር!
በነገራችን ላይ ከትግሉ በሁውላ መጀመሪያ ያስቀደስኩት እስረኛው ሚካእል ከሴ/ከርቸሌ ግቢ ነበር ቅቅ በሁውላ እርሱም ተፈቶ ውጭ ተሰርቶለት ነበር ለትዝታ ያህል!

-...- wrote:ወንድም ዲጎኔ ይችን ቪዲዮ ከለጠፍክበት ከዛኛው ክፍል አመጣኋት ።

http://www.youtube.com/watch?v=csadJdutzbU

ቪዲዮውን ካየሁ በኋላ የሚከተሉትን ጥያቄዎች ልጠይቅህ ፈለግሁ ። ጴንጤን ዲፌንድ ሳታደርግ የህሊናህን እንደምትመልስልኝ እቅጯን ተናግረህ የመሸበት የምታድር ሃቀኝነትህን በመተማመን ነው

1.እነዚህ መዘምራን ካባ ለብሰው ጃኖ አደግድገው መቋሚያ ይዘው ጸናጽል ይዘው ከበሮ ይዘው በኦርቶዶክስ ሽብሸባ ለምን ለመቅረብ ፈለጉ ?

2. አንተ ራስህ ከበሮ ጸናጽል መቋሚያ ስታይ መጀመሪያ በአእምሮህ የሚመጣው የትኛው ሃይማኖት ነው ?

3.ኦርቶዶክስ መስሎ በያረዳዊ ዜማ(ያሬድ ማለት ኦርቶዶክስ ማለት ነው ብለህ ውሰደው ምክንያቱም ያሬድ ህይወቱን በሙሉ በኦርቶዶክስ ዝማሬ/ዜማ ማጠናቀር ያሳለፈ ነው)መቅረቡ ማታለል ነው ውይስ አይደለም ?

ማንንም ጴንጤን ጭምር ሳትፈራ እውነቷን እንደምትነግረኝ አልጠራጠርም

ይህ ቪዲዮ የበግ ለምድ ለብሶ የሚመጣ ተኩላ የሚለውን ጥቅስ ያስታውሰኛል
ዲጎኔ
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 4752
Joined: Fri Aug 19, 2005 2:03 am
Location: united states

Postby -...- » Fri Apr 04, 2014 4:39 am

ወንድም ዲጎኔ መልስህ አላረካኝም : እንደተማመንኩብህ በእውነት አልመለስክልኝም ። ጴንጤን እየተከላከልክ ነው ። የኔን አስተያየት ልንገርህ

መዝሙር በባህል ቢዘመር ማታለል አይደለም አልክ ። ዜማ ያሬድ የኢትዮጵያ ባህል አይደለም ። ዜማ ያሬድ የኦርቶዶክስ ሃይማኖት የግል ስርአተ ዜማ ነው ። የኦርቶዶክስን ዜማ አስመስሎ የጴንጤዎች መዘመር በኔ እምነት ማጭበርበር ማታለል ነው ።

ጸናጽል መቋሚያ ሽብሸባ የኦርቶዶክስ የግል ስርአት ነው ። ጸናጽልና መቋሚያ ይዞ በኦርቶዶክስ ዜማ የጴንጤዎች እንደ ኦርቶዶክስ ማሸብሸብ ማጭበርበር ማታለል ነው።

ባለዘርፍ ለምድ/ካባ የኦርቶዶክስ ስርአተ ልብስ ነው ። ጴንጤዎች ልብሰ ኦርቶዶክስ ለብሰው በኦርቶዶክስ ዜማ ማሸብሸብ ማጭበርበር ማታለል ነው

ከላይ የጠቀስኳቸው ጴንጤዎች ኦርቶዶክስን መስለው የዋህ ኢትዮጵያውያንን ስለማጭበርበራቸው ነው ።

ብቅንነት የምታዳምጠኝ ከሆነ ቀጥዬ ደሞ ብዙ ግዜ ስለምትደጋግማት የመቃብር መከልከል ትንሽ ልበል ። አደራ ሰደበኝ እንዳትል የሚሰማኝን አስተያየት ነው በግልጽ የምገልጸው

ብዙ ግዜ ቤተክርስቲያን መቃብር ተከለከልን ትላለህ ። ኦርቶዶክስ የራሱ መቃብር አለው ፡ እስላም የራሱ መቃብር አለው ሃይማኖት ነን ካላችሁ ለምን የራሳችሁን መቃብር አይኖራችሁም ?

እንዴት ነው ነገሩ እምነታችንን ቤተክርስቲያናችንን አያንቋሽሻችሁ ፡ እመቤታችንን ዝቅ አድርጋችሁና ሰድባችሁ ስትሞቱ ኦርቶዶክስ መቃብር እንቀበር የምትሉት የኛ ቤተክርስቲያን ጥምብ(ሬሳ ለማለት ነው)መጣያ ናት እንዴ ?
ጴንጤ ለኦርቶዶክስ ጸረማርያም/እርኩስ ነው( ሃቁን እምነት ነው የምነግርህ ስድብ እንዳይመስልህ)እና በኦርቶዶክስ መቃብር እንኳን እርኩስ ጸረማርያም ይቅርና ራሱን የገደለ/ያጠፋ ኦርቶዶክስ እንኳን አይቀበርም ። መቃብሩን እንደ ኦርቶዶክስ ፕራይቬት ክለብ ውሰደው ። የክለብ አባል ካልሆንክ አትገባም ። እና ይሄንን እንዴት ማገናዘብ አቅቷችሁ ነው ዘወትር መቃብር ተከለከልን እያላችሁ እሮሮ የምታሰሙት

ይህንን በቅን አንብበህና መርምረህ ቅን መልስህን እንደምትሰጠኝ እተማመናለሁ
ሞቼ እየተነሳሁ ልሙት እንደገና
አንድ ሞት ላገሬ አይበቃትምና
-...-
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 401
Joined: Thu Feb 09, 2012 8:36 pm

Postby ዲጎኔ » Fri Apr 04, 2014 1:55 pm

ሰላም ለሁላችን
እርካታ የሚገኘው ከዲጎኔ መልስ ወይም ከአንተ መረዳት ሳይሆን ከእውነቱ ጌታ ከክርስቶስ ነው::በተቻለኝ መጠን ሚዛናዊ ፋክቶችን/ሀቆችን ማቅረቤን እቀጥላለሁ::
ማህበረሰብ ኪነጥበብን የሚጠቀመው እንደባህሉ ለመሆኑ የባህል 101 መማር አያሻንም::ያሬዳዊ ዜማን በኮፒራይት የተዋህዶ ማህበር ስለመያዙ የማቀው የለም እንኩዋ በጦቢያ የኮፒ ራይት ፈጽሞ በማይሰራበት በአውሮፓ የነሞዛርት የነቤትሆቨን ቅኝት ሁሉ ሲጠቀም ክስ አልተሰማም::ጸያፍ ወሲብ ቀስቃሽ ዘፈኖች በያሬዳዊ ዜማ ሲቀርቡ ብታወግዙ ባማረባችሁ::እኛ ግን በሁሉ የዜማ አይነት ራፕ ጭምር ጌታን እናከብራለን::ጸናጽል በገና ማሰንቆ ከበሮ እምቢልታ ወዘተ የጦቢያ ቅርሶች በጦቢያዊነት የሁሉም ጦቢያዊ መጠቅም መብቱ ነው::
የቀበር ስፍራን በተመለከተ ድሮ የተሀድሶ ወገኖች ሲያርፉ የተፈቀደው ጴጥሮስ ወጳውሎስ የሚባለው ጉለሌ ብቻ ነበር እየበዛን ስንሄድ ዮሴፍ-ሳሪስ ተፈቀደ::በግል የማውቀው ግፍ ቀጨኔ መድሀኒያለም ሐረርና ድሬደዋ ቀብርቦታ ስንከለከል አስከሬን ይዘን ከክፍለሀገር ክፍለሀገር ተጉዘናል::
በተረፈ ጥንቡ ወልድ/ክርስቶስ የሌሽ ባለውቃቢና ያለንስሀ ህይወቱን በአለም ሲዳክር ኖሮ ሲሞት በማይፈታ ፍትሀት ፍትሀት የሚባልለት እንጂ በክርስቶስ ያመነና ህይወት ያገኘ ህያው ነው::ለቤተሰቦች ቅዱስቃል ለመካፈልና ለመጽናናት ነው እኛ የቀብር ስርአት የሚያስፈልገን::አንዱ ሀገር ቤት አይኑን ታሞ በሲዊስ ሚሽን ህክምና እንዲያገኝ የረዳሁት 'የእናንተ ጥንብ እኛ ዘንድ አይቀበርም' ብሎኛል::የታደሉት አለቃ ተወልደመድህን ግን ድሮ በለሳ ሚሽን አይን ክሊኒክ ሄደው የስጋም የመንፈስም አይናቸው ተፈውሶ የትግሪኛ መጽሀፍ ቅዱስን ለመተርጎም በቅተዋል እምነቱና በረከቱን ለልጅ ልጆቻቸው አትርፈዋል::ካቶሊኮቹ በቅርቡ በያሬዳዊ ዜማ መዘመር ጀምረዋል እንደ መምራችሁ አለቃ አያሌው 'መች ተለመደና ከተኩላ ዝምድና'ልትሉ ይሆን? ለማጠቃለልና እውነት ለመናገር ያሬድ ለእኔ ከማከብረው የተሀድሶ ፋናወጊ ደቅእስጢፎ አይለይም::ይልቅ አለማመኔ እርዳ የሚለውን መዝሙር ከቻልክ እዚህ አምጣው::

-...- wrote:ወንድም ዲጎኔ መልስህ አላረካኝም : እንደተማመንኩብህ በእውነት አልመለስክልኝም ። ጴንጤን እየተከላከልክ ነው ። የኔን አስተያየት ልንገርህ

መዝሙር በባህል ቢዘመር ማታለል አይደለም አልክ ። ዜማ ያሬድ የኢትዮጵያ ባህል አይደለም ። ዜማ ያሬድ የኦርቶዶክስ ሃይማኖት የግል ስርአተ ዜማ ነው ። የኦርቶዶክስን ዜማ አስመስሎ የጴንጤዎች መዘመር በኔ እምነት ማጭበርበር ማታለል ነው ።

ጸናጽል መቋሚያ ሽብሸባ የኦርቶዶክስ የግል ስርአት ነው ። ጸናጽልና መቋሚያ ይዞ በኦርቶዶክስ ዜማ የጴንጤዎች እንደ ኦርቶዶክስ ማሸብሸብ ማጭበርበር ማታለል ነው።

ባለዘርፍ ለምድ/ካባ የኦርቶዶክስ ስርአተ ልብስ ነው ። ጴንጤዎች ልብሰ ኦርቶዶክስ ለብሰው በኦርቶዶክስ ዜማ ማሸብሸብ ማጭበርበር ማታለል ነው

ከላይ የጠቀስኳቸው ጴንጤዎች ኦርቶዶክስን መስለው የዋህ ኢትዮጵያውያንን ስለማጭበርበራቸው ነው ።

ብቅንነት የምታዳምጠኝ ከሆነ ቀጥዬ ደሞ ብዙ ግዜ ስለምትደጋግማት የመቃብር መከልከል ትንሽ ልበል ። አደራ ሰደበኝ እንዳትል የሚሰማኝን አስተያየት ነው በግልጽ የምገልጸው

ብዙ ግዜ ቤተክርስቲያን መቃብር ተከለከልን ትላለህ ። ኦርቶዶክስ የራሱ መቃብር አለው ፡ እስላም የራሱ መቃብር አለው ሃይማኖት ነን ካላችሁ ለምን የራሳችሁን መቃብር አይኖራችሁም ?

እንዴት ነው ነገሩ እምነታችንን ቤተክርስቲያናችንን አያንቋሽሻችሁ ፡ እመቤታችንን ዝቅ አድርጋችሁና ሰድባችሁ ስትሞቱ ኦርቶዶክስ መቃብር እንቀበር የምትሉት የኛ ቤተክርስቲያን ጥምብ(ሬሳ ለማለት ነው)መጣያ ናት እንዴ ?
ጴንጤ ለኦርቶዶክስ ጸረማርያም/እርኩስ ነው( ሃቁን እምነት ነው የምነግርህ ስድብ እንዳይመስልህ)እና በኦርቶዶክስ መቃብር እንኳን እርኩስ ጸረማርያም ይቅርና ራሱን የገደለ/ያጠፋ ኦርቶዶክስ እንኳን አይቀበርም ። መቃብሩን እንደ ኦርቶዶክስ ፕራይቬት ክለብ ውሰደው ። የክለብ አባል ካልሆንክ አትገባም ። እና ይሄንን እንዴት ማገናዘብ አቅቷችሁ ነው ዘወትር መቃብር ተከለከልን እያላችሁ እሮሮ የምታሰሙት

ይህንን በቅን አንብበህና መርምረህ ቅን መልስህን እንደምትሰጠኝ እተማመናለሁ
ዲጎኔ
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 4752
Joined: Fri Aug 19, 2005 2:03 am
Location: united states

Postby ለማ12 » Fri Apr 04, 2014 3:03 pm

አቶ ዲጎኔ እረ አረማመድህ እንደ ወንድምህ እንደ ታሜ ሆነ:

እባክህ አንተ እንደምትለው አይደለም
ይህ ወጣት ያቀረበልህ ጭብጥ የሚአላውስ አይደለም ስለዚህ የምመክርህ ለጊዜ መታገሱን እመርጣለሁ::

አለባለዚያ አራባና ቆቦ መልስህ ብዙ መዘዝ አለው:
እንዳልኩህ እንመራለን የሚሉአችሁ ደንቆሮወች ናቸው ለዚህ ያበቁአችሁ እነሱን እረፉ ብሎ ዝም ማሰኘት የሚቻል ነው ጊዜ ይወስድ ይሆናል ግን አይቀርም:
አለቃ አያሌውን ልትሳደብ ዳዳህ???????
ቁቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅቅ
የሰው ወልካፋ ሰው ያጠፋ የአህያ ጀላፋ መስክ ያጠፋ ነው የሚሉት?

እባክህ ተው::
ለማ12
ውሃ አጠጪ
ውሃ አጠጪ
 
Posts: 1107
Joined: Sat Jun 16, 2012 9:46 am

Postby -...- » Fri Apr 04, 2014 3:46 pm

ለሚቾ ዲጎኔ የተቀየመና ዳር ዳሩን የሚዞር ነው የመሰለኝ : ልረዳ የፈለኩትን ሊያስረዳኝ አልቻለም

ወንድም ዲጎኔ አሁንም እንደተማመንኩብህ በእውነት አልመለስክልኝም ። ጴንጤን እየተከላከልክ ነው ። እኔ በቅን ስወያይህ አንተ የተቆጣህ የተቀየምክም ይመስላል ፡ እኔ አንተን የማከብርህን ወንድሜን ለመስደብ ለማስቀየም እምነትህንም ለመዝለፍ ከቶ ሃሳቡም የለኝም ፡ በአእምሮዬ የሚብላላውን በግልጽ ካንተ ለመወያየት ነው ፍላጎቴ ፡ ጥያቄዎቼንም አልመለስክም ። አብዛኛው ከላይ የጻፍከው የቅሬታ ወቀሳ ነው

መቃብር ተከለከልን ተገፋን እያልክ አሁንም ታማርራለህ
የኦርቶዶክስ መቃብር ለኦርቶዶክስ ነው ፡ ስለምን ነው ኦርቶዶክስ መቃብር እንቀበር የምትሉት ? የምታንቋሽሹት እምነት መቃብር ለምን በግድ እንግባ ትላላችሁ ? ለምን የራሳችሁን መቃብር አታደራጁም ? ገንዘብ እንደሁ ጴንጤ በሙሉ አስራት ይከፍላል ለምን የራሳችሁ መቃብር አይኖራችሁም ?
ተገፋን ተገፋን እያላችሁ የምታላዝኑት ሊገባኝ አልቻለም ። አንዱ ይሁዲ እዚህ የክርስቲያን ት/ቤት ገብቶ ምን እንዳደረገ ታውቃለህ ? ት/ቤቱ ጠዋት ቀኑን በጸሎት ነው የሚጀምረው እና ይህ ይሁዲ ጸልይ ተብዬ ስለተገደድሁ መብቴን ተገፍፌያለሁ ብሎ ከሰሰ ። ዳኛው ምን እንዳለው ታውቃለህ ክርስቲያን ት/ቤት ገብተህ ጸሎት መብትህን ከገፈፈው ውጣና መብትህ የማይገፈፈበት ይሁዲ ት/ቤት ግባ ነው ያለው ። እናንተም የግድ ኦርቶዶክስ መቃብር በር ሰብረን ካልገባን ከተከለከልን ተገፋን ትላላችሁ ። የኦርቶዶክስ መቃብር ለኦርቶዶክሶች መሆኑን የእስላም መቃብር ለእስላሞች መሆኑን ህጻን ልጅ እንኳን ሊረዳው ሲችል እንዴት እናንተ ይህንን መረዳት አቃታችሁ ? ሆድ አይባስህና ይህንን በቀጥታ መልስልኝ

የኦርቶዶክስን ስርአት አሁንም ባህል ነው እያልክ ነው ። ትልቅ ስህተት ። እስላም ኢትዮጵያዊ የኦርቶዶክስ ስርአት ባህሉ አይደለም : ቃልቻ ኢትዮጵያዊ : እምነት አልባ ኢትዮጵያዊ የኦርቶዶክስ ስርአት ባህሉ አይደለም :: የኦርቶዶክስ ዜማ ፡ ጸናጽል ፡ መቋሚያ ፡ ሽብሸባ የኢትዮጵያ ባህል ሳይሆን የኦርቶዶክስ የእምነቱ ስርአት ነው ። በኔ እምነት ጴንጤዎች ካባ ለብሰው አድግድገው መቋሚያ ይዘው ጸናጽል ይዘው በያሬዳዊ ዜማ እንደ ኦርቶዶክስ ማሸብሸባቸው ስህተት ነው ማታለል ነው ማጭበርበር ነው ነው የምለው ።

አንተስ ምን ትላለህ ?
መመለስ እንዳትረሳ ለምን የራሳችሁ መቃብር የላችሁም ?
ሞቼ እየተነሳሁ ልሙት እንደገና
አንድ ሞት ላገሬ አይበቃትምና
-...-
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 401
Joined: Thu Feb 09, 2012 8:36 pm

Postby ዲጎኔ » Fri Apr 04, 2014 4:57 pm

ሰላም ለሁላችን ይሁን ለባለነጠብጣቡና ለተሳዳቢው ለማ
ለማ አስተማሪዎቼን ደንቆር ብሎ እየሰደበ የአለቃ አያሌው ታምሩ መጽሀፍ ስለጠቀስኩ ብቻ ሰደበ ብሎ ይከሰኛል::ነገሩ ሊበሏት የፈለጉ አሞራ ጅግራ ይሏታል እንደሚል ለማ ሊሰድበ የፈለገ እምነትና ማህበረሰብ ሳልሳደብ ሰደበ ብሎ ቀጠለ::ይሁን ስድቡ ግፉ ሞጣ በቄስ ባድማ የጀመረ ነው::
ወደአምዱ ስንመጣ ዜማ ዘርፈውማንን አወደሱ?በክርስትና አስዛኙ ታሪክ ክርስቲያን ነኝ ባይ ክርስቲያኑን ሲያወግዝ ሲያርድ ነው:: መች ተለመደ ከተኩላ ዝምድና ካቶሊኮችና ተዋህዶዎች በሱሰንዮስ ጊዘ የጀመሩትን መባላት አመልካች ሲሆን ያንን በታሪክ ማውሳት ለመታረም እንጂ ጥላቻውን ለማባባስ ፈጽሞ መጠቅም የለብንም::
የመቃብሩ ጉዳይ መልሸዋለሁ የቀብር ስርአት የሚያስፈልገን መጽሀፍቅዱሳዊ ያልሆነ ፍትሀት ልንፈጽም ሳይሆን ቤተስብ እንዲጽናና ለሟች ክቡር ስንብት ነው::የነበሩት መንግስታት እንደፈልግነው በየቦታው ስፍራ ቢሰጡን መች እናተ ጉዋሮ አስመጣን::አሁን ኢሀዲግን ጌታ ይባርከው አምበሽብሾናል!
'ኤሎሄ ካንተ ተምሬያለሁ ቢሰድቡኝ መች እመልሳለሁ'
https://www.youtube.com/watch?v=MfLofxj7gY
ዲጎኔ
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 4752
Joined: Fri Aug 19, 2005 2:03 am
Location: united states

Postby ለማ12 » Fri Apr 04, 2014 5:14 pm

መልካም አቶ ዲጎኔ

ይህ እናንተ የምትዘፍኑለት ሸቅጥ መሰረት የለውም የፈረንጅ ሸቀጥ እንጂ:

ይህን መሳደቡን ትታችሁ ዝፈኑ እኔ ጉዳየ አይደለም ግን እናንተ የምታስቀድሙት ስድብ ምክንያቱም ሀ ብላችሁ ለ አትሉም:
ለዚህም ነው ተው የምለው አንተ ከምትለው የባሰ ብዙ ነገሮችን እያየሁ ነው ለምን?
ከቻላችሁ መሳደቡን ትታችሁ ዝፈኑ የወንጌል ምሁራን ትለኛለህ
ቁቅቅቅቅቅ
የቱ ምሁር ጎረምሳው ዳኔል ወይስ ቆምጫጫው ታሜ ?

ምንም በዚህ ሸቀጥ ላይ ብዙ ማለት እችላለሁ ግን ጊዜው አይደለም

ትግስት ይኑራችሁ:

ሰሞኑን ወያኔ እናንተን መሳሪያ አድርጎ ነው እነዚህን ወጣቶች የሚአሰቃይ:

ብዙ ማለት ይቻላል ግድ የለህም ተወው ይቆይ::
ለማ12
ውሃ አጠጪ
ውሃ አጠጪ
 
Posts: 1107
Joined: Sat Jun 16, 2012 9:46 am

Postby ገልብጤ » Fri Apr 04, 2014 7:01 pm

ዲጎኔ wrote:ሰላም ለሁላችን ይሁን ለባለነጠብጣቡና ለተሳዳቢው ለማ
ለማ አስተማሪዎቼን ደንቆር ብሎ እየሰደበ የአለቃ አያሌው ታምሩ መጽሀፍ ስለጠቀስኩ ብቻ ሰደበ ብሎ ይከሰኛል::ነገሩ ሊበሏት የፈለጉ አሞራ ጅግራ ይሏታል እንደሚል ለማ ሊሰድበ የፈለገ እምነትና ማህበረሰብ ሳልሳደብ ሰደበ ብሎ ቀጠለ::ይሁን ስድቡ ግፉ ሞጣ በቄስ ባድማ የጀመረ ነው::
ወደአምዱ ስንመጣ ዜማ ዘርፈውማንን አወደሱ?በክርስትና አስዛኙ ታሪክ ክርስቲያን ነኝ ባይ ክርስቲያኑን ሲያወግዝ ሲያርድ ነው:: መች ተለመደ ከተኩላ ዝምድና ካቶሊኮችና ተዋህዶዎች በሱሰንዮስ ጊዘ የጀመሩትን መባላት አመልካች ሲሆን ያንን በታሪክ ማውሳት ለመታረም እንጂ ጥላቻውን ለማባባስ ፈጽሞ መጠቅም የለብንም::
የመቃብሩ ጉዳይ መልሸዋለሁ የቀብር ስርአት የሚያስፈልገን መጽሀፍቅዱሳዊ ያልሆነ ፍትሀት ልንፈጽም ሳይሆን ቤተስብ እንዲጽናና ለሟች ክቡር ስንብት ነው::የነበሩት መንግስታት እንደፈልግነው በየቦታው ስፍራ ቢሰጡን መች እናተ ጉዋሮ አስመጣን:::አሁን ኢሀዲግን ጌታ ይባርከው አምበሽብሾናል
'ኤሎሄ ካንተ ተምሬያለሁ ቢሰድቡኝ መች እመልሳለሁ'
https://www.youtube.com/watch?v=MfLofxj7gY
ያልበሰለ ፖለቲከኛ ስለቀጣዩ ምርጫ ሲያስብ
የበሰለ ፖለቲከኛ ስለቀጣዩ ትውልድ ያስባል
James freeman clarke
ገልብጤ
ዋና ውሃ አጠጪ
ዋና ውሃ አጠጪ
 
Posts: 1680
Joined: Sat Jun 26, 2010 11:24 pm

Re: ተጠየቅ ዲጎኔ

Postby ቀዳማይ » Tue Apr 08, 2014 9:54 pm

-...- wrote:ወንድም ዲጎኔ ይችን ቪዲዮ ከለጠፍክበት ከዛኛው ክፍል አመጣኋት ።

http://www.youtube.com/watch?v=csadJdutzbU

ቪዲዮውን ካየሁ በኋላ የሚከተሉትን ጥያቄዎች ልጠይቅህ ፈለግሁ ። ጴንጤን ዲፌንድ ሳታደርግ የህሊናህን እንደምትመልስልኝ እቅጯን ተናግረህ የመሸበት የምታድር ሃቀኝነትህን በመተማመን ነው

1.እነዚህ መዘምራን ካባ ለብሰው ጃኖ አደግድገው መቋሚያ ይዘው ጸናጽል ይዘው ከበሮ ይዘው በኦርቶዶክስ ሽብሸባ ለምን ለመቅረብ ፈለጉ ?

2. አንተ ራስህ ከበሮ ጸናጽል መቋሚያ ስታይ መጀመሪያ በአእምሮህ የሚመጣው የትኛው ሃይማኖት ነው ?

3.ኦርቶዶክስ መስሎ በያረዳዊ ዜማ(ያሬድ ማለት ኦርቶዶክስ ማለት ነው ብለህ ውሰደው ምክንያቱም ያሬድ ህይወቱን በሙሉ በኦርቶዶክስ ዝማሬ/ዜማ ማጠናቀር ያሳለፈ ነው)መቅረቡ ማታለል ነው ውይስ አይደለም ?

ማንንም ጴንጤን ጭምር ሳትፈራ እውነቷን እንደምትነግረኝ አልጠራጠርም

ይህ ቪዲዮ የበግ ለምድ ለብሶ የሚመጣ ተኩላ የሚለውን ጥቅስ ያስታውሰኛል

ወንድሜ ሰላምታዬ ይድረስህ
ጥያቄው ለዲጎኔ ቢሆንም እኔም ያለኝን እንዳካፍል ቢፈቀድልኝ መልካም ነው:: እኛ ግን የተሰቀለውን ክርስቶስን እንሰብካለን 1ቆሮ1፥23 ይህን የሕይወት ቃል የተናገረው ሐዋርያው ጳውሎስ ነው:: እነዚህ መዘምራን የኦርቶዶክስን አዘማመር ስርአት ተከትለው ክርስቶስን ስላመሰገኑ ቅር አለህ ማለት ነው? ያሬድ ሕይወቱን በሙሉ በኦርቶዶክስ ዝማሬ/ዜማ ማጠናቀር ያሳለፈ ነው ብለሀል:: ለመሆኑ ያሬድ ይዘምር የነበረው ለኦርቶዶክስ ነበር ወይስ ሰማይና ምድርን በቃሉ ላጸና ጌታ:: ይህን ጌታ ነው ያመሰገኑት ይህንንም አምላክ ነው የሚያመልኩት የምናመልከው:: ከክርስቶስ ፍቅር ይልቅ የሀይማኖት ፍቅር ሊያሸንፈን አይገባም:: አንድ ቀን የሆኑ የማውቃቸው ሰዎች የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅስ የተጻፈበት ግድግዳ ላይ የሚሰቀል ጌጥ መሳይ አውጥተው ሲጥሉ አይቼ:: ምነው ለምን ትጥሉታላችሁ ብላቸው አይ ይህማ የጴንጤ ነው ያሉኝን አልረሳውም:: በእውነት የሚበዛው ህዝባችን ወደ ጥንቆላና ባእድ አምልኮ ሲሄድ ዝም ብለን እያየን ዛሬ ክርስቶስ ሲመለክ ለምን ብሎ መጠየቅ ተገቢ አይመስለኝም:: ጨርሻለው ጌታ ይባርክህ::
ቀዳማይ
ጀማሪ ኮትኳች
ጀማሪ ኮትኳች
 
Posts: 60
Joined: Thu May 09, 2013 6:02 am

Postby ክቡራን » Wed Apr 09, 2014 1:02 am

ችግሩ ያለው የሰዎች ትኩረት ያረፈው እምነቱ ላይ ሳይሆን ወጉና ስ ር አ ቱ ላይ ነው:: ሁዳዴ ይጾማል ቤተ ከርስትያን ይታደራል:: ሽር ጉድ ይባላል:: እርስ በርሳችን ግን ፍቅር የለንም:: ጠመንጃ ይዞ ቤተ መቅደስ መግባት አያቻልም እንጂ በጥይት እንጨራርስ ነበረ:: ዘመዴ ገና ካሁኑ ጾም ሳይፈታ ሽንኩር ት ግዛ እያለች በወጣ በገባ እየጨቀጭቀችኝ ነው:: አረ ተይ ይደርሳል ብላት እነ እከሌ እኮ ከትፈው ዲፍሪዘር ውስጥ አስቀምጠውታል ትለኛለች:: ይሀው እኔም እየጾምኩ ነው በሷ የተነሳ:: :D ኦርቶዶክሳዊ ጾም መጾማችን ክፋት የለውም:: ነገር ግን ጾሙ ከውስጥ ይሁን!! ከውጭ አይሁን:: ሰዎች የይቅርታ መንፈስ ሳይኖራቸው ስጋ ስላልበሉ ይነጻሉ ማለት አይደለም:: ባለፈው ያውም በጾም እለት የቤተ ክርስቲያናችን አበ -እምነት ካንዱ መእምን ጋር ተጣልተው ነበር:: የሚያሳታርቅ ጠፍቶ እሳቸውም መምጣት ሁሉ አቁመው ነበር:: የሰደበቻቸው ደሞ የሰውየው ሚስት ናት አሉ::: ምነው ሴቱ ግን እንዲህ በቤተ መቅደስ ውስጥ ሙጢ አፍ ሆነ?? የእጊዚአብሄርን ቤት መፍራት የጠፋበት ዘመን ላይ ደርሰናል:: ሌላ ቦታ ደሞ ሶስት ቄሶች አንዱን ድሮ ጔደናቸው የነበረውን ቄስ አውግዘናል ገዝተናል ብለው ቁጭ አሉ:: :lol: እንደገባኝ ከሆነ ቄሶቹ ስልጣናቸውን ተጠቅመው ሁዴታ ነበረ ያደረጉት:: :lol: አሁን ይሄ ቱሉ ፈርሶ የሚባለው የጎሽ ጔደኛ ( ባለ ነጠብጣቡ ) ያሬዳዊ ዜማ ማዜማቸውን ባህላዊ ወረራ አድርጎ ማቅረቡ መመጻደቁን ከማሳየቱ ውጭ ሌላ ነገር የለውም:: ከነገድ ከቌንቌ የሆኑ ሁሉ እግዚአብሄር አምላካቸውን ያመስግኑት ይላል:: ድቤ አምጥተህ እንደርቢ እስካልጠራህ ድረስ በጸናጽልና በከበሮ በእልልታና በዝማሬ እግዚአብሄር በሰጠህ መረዋ ድምጽ አምላክህን እጊዚብሄርን አመሰግነው ሀለሉያ:: ""ይህ ህዝብ በክንፈሩ ያከብረኛል ልቡ ግን ከኔ የራቀ ነው"" የሚለው ለዘህ አይነቱ ባለ ነጠብጣቡን ለመሰለ ፈረቃሳ ነው:: የስራት ሰው ሳንሆን የእምነት ሰው እንሁን ዘንድ እጊዚብሄር ልባችንን ይክፈትልን:: እመቤታችን አይናችን ታብራልን:: እኛም አይናችንን ከፍተን ለማየት እንሞክር!! ዝም ብለህ አንተ ሆነ ብለህ የጨፈንከውን አይን እመቤቴ ማርያም እያልክ ምንም አትከፍትልህም...አይንህን ራስህ ክፈት ከዛደሞ መነፈሳዊ አይንህን ትከፍትልኅለች:: ሌላው ነገር ደግሞ ሰው ከሞተ ብኌላ ሬሳው ከደጀ ሰላም ስለተቀበረ ይጸድቃል ማለት አይደለም:: ከዛ ውጭ ገንዘብ ወይም ዘመድ አጥቶ የተቀበረ ደሞ ገኅነም ይገባል ማለትም አይደለም:: እነደዚህ ብሎ ማሰብ መንፈሳዊ ጅልነት ነው:: ለሟቹ ምንም የሚያደርግለት ነገር የለም:: ለቌሚ ዘመዶቹ መጽናኛ እንዲሆናቸው ብቻ ነው:: የሞተ ማ አርባ ቀን ባለም ዙሪያ ይዞርና ከአርባ ቀን በኌላ በብርሀን ፍጥነት ነፍሱ ወደ ሰማይ መጔዝ ትጀምራለች:: ስለ ሰማይ ሚስጥር አንድ ቀን እጽፋለሁ:: ጳውሎስ ለጢሞቶዎስ የጻፈውን የመሰለ አንድ ደብዳቤ አረፍ የምልበት ጥላ ሳገኝ የምጽፍ ይመስለኛል:: የማውቀው እውነት አለ::
ክቡራን
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 7988
Joined: Tue Mar 04, 2008 4:24 pm

Re:

Postby ክቡራን » Tue Sep 06, 2016 9:09 pm

Did I write this ? ወይስ እይኔ ነው ??

ክቡራን wrote:ችግሩ ያለው የሰዎች ትኩረት ያረፈው እምነቱ ላይ ሳይሆን ወጉና ስ ር አ ቱ ላይ ነው:: ሁዳዴ ይጾማል ቤተ ከርስትያን ይታደራል:: ሽር ጉድ ይባላል:: እርስ በርሳችን ግን ፍቅር የለንም:: ጠመንጃ ይዞ ቤተ መቅደስ መግባት አያቻልም እንጂ በጥይት እንጨራርስ ነበረ:: ዘመዴ ገና ካሁኑ ጾም ሳይፈታ ሽንኩር ት ግዛ እያለች በወጣ በገባ እየጨቀጭቀችኝ ነው:: አረ ተይ ይደርሳል ብላት እነ እከሌ እኮ ከትፈው ዲፍሪዘር ውስጥ አስቀምጠውታል ትለኛለች:: ይሀው እኔም እየጾምኩ ነው በሷ የተነሳ:: :D ኦርቶዶክሳዊ ጾም መጾማችን ክፋት የለውም:: ነገር ግን ጾሙ ከውስጥ ይሁን!! ከውጭ አይሁን:: ሰዎች የይቅርታ መንፈስ ሳይኖራቸው ስጋ ስላልበሉ ይነጻሉ ማለት አይደለም:: ባለፈው ያውም በጾም እለት የቤተ ክርስቲያናችን አበ -እምነት ካንዱ መእምን ጋር ተጣልተው ነበር:: የሚያሳታርቅ ጠፍቶ እሳቸውም መምጣት ሁሉ አቁመው ነበር:: የሰደበቻቸው ደሞ የሰውየው ሚስት ናት አሉ::: ምነው ሴቱ ግን እንዲህ በቤተ መቅደስ ውስጥ ሙጢ አፍ ሆነ?? የእጊዚአብሄርን ቤት መፍራት የጠፋበት ዘመን ላይ ደርሰናል:: ሌላ ቦታ ደሞ ሶስት ቄሶች አንዱን ድሮ ጔደናቸው የነበረውን ቄስ አውግዘናል ገዝተናል ብለው ቁጭ አሉ:: :lol: እንደገባኝ ከሆነ ቄሶቹ ስልጣናቸውን ተጠቅመው ሁዴታ ነበረ ያደረጉት:: :lol: አሁን ይሄ ቱሉ ፈርሶ የሚባለው የጎሽ ጔደኛ ( ባለ ነጠብጣቡ ) ያሬዳዊ ዜማ ማዜማቸውን ባህላዊ ወረራ አድርጎ ማቅረቡ መመጻደቁን ከማሳየቱ ውጭ ሌላ ነገር የለውም:: ከነገድ ከቌንቌ የሆኑ ሁሉ እግዚአብሄር አምላካቸውን ያመስግኑት ይላል:: ድቤ አምጥተህ እንደርቢ እስካልጠራህ ድረስ በጸናጽልና በከበሮ በእልልታና በዝማሬ እግዚአብሄር በሰጠህ መረዋ ድምጽ አምላክህን እጊዚብሄርን አመሰግነው ሀለሉያ:: ""ይህ ህዝብ በክንፈሩ ያከብረኛል ልቡ ግን ከኔ የራቀ ነው"" የሚለው ለዘህ አይነቱ ባለ ነጠብጣቡን ለመሰለ ፈረቃሳ ነው:: የስራት ሰው ሳንሆን የእምነት ሰው እንሁን ዘንድ እጊዚብሄር ልባችንን ይክፈትልን:: እመቤታችን አይናችን ታብራልን:: እኛም አይናችንን ከፍተን ለማየት እንሞክር!! ዝም ብለህ አንተ ሆነ ብለህ የጨፈንከውን አይን እመቤቴ ማርያም እያልክ ምንም አትከፍትልህም...አይንህን ራስህ ክፈት ከዛደሞ መነፈሳዊ አይንህን ትከፍትልኅለች:: ሌላው ነገር ደግሞ ሰው ከሞተ ብኌላ ሬሳው ከደጀ ሰላም ስለተቀበረ ይጸድቃል ማለት አይደለም:: ከዛ ውጭ ገንዘብ ወይም ዘመድ አጥቶ የተቀበረ ደሞ ገኅነም ይገባል ማለትም አይደለም:: እነደዚህ ብሎ ማሰብ መንፈሳዊ ጅልነት ነው:: ለሟቹ ምንም የሚያደርግለት ነገር የለም:: ለቌሚ ዘመዶቹ መጽናኛ እንዲሆናቸው ብቻ ነው:: የሞተ ማ አርባ ቀን ባለም ዙሪያ ይዞርና ከአርባ ቀን በኌላ በብርሀን ፍጥነት ነፍሱ ወደ ሰማይ መጔዝ ትጀምራለች:: ስለ ሰማይ ሚስጥር አንድ ቀን እጽፋለሁ:: ጳውሎስ ለጢሞቶዎስ የጻፈውን የመሰለ አንድ ደብዳቤ አረፍ የምልበት ጥላ ሳገኝ የምጽፍ ይመስለኛል:: የማውቀው እውነት አለ::
ክቡራን
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 7988
Joined: Tue Mar 04, 2008 4:24 pm

Re: Re:

Postby ቢተወደድ1 » Wed Sep 07, 2016 8:15 pm

ክቡራን እንዴት ሰነበትክ?
ወደኻላ ሄደህ የጳፍካቸውን መቃኘት ከጀመርክ እጅጉን እንደሚደንቅህ ጥርጥር የለውም፡፡
የራሴን መለስ ብዬ ካነበብካቸው ውስጥ አንዳንዶቹን እኔ እይደለሁም የጣፍኩት ለማለት ቃጥቶኝ ነበር፡፡

ክቡራን wrote:Did I write this ? ወይስ እይኔ ነው ??

ክቡራን wrote:ችግሩ ያለው የሰዎች ትኩረት ያረፈው እምነቱ ላይ ሳይሆን ወጉና ስ ር አ ቱ ላይ ነው:: ሁዳዴ ይጾማል ቤተ ከርስትያን ይታደራል:: ሽር ጉድ ይባላል:: እርስ በርሳችን ግን ፍቅር የለንም:: ጠመንጃ ይዞ ቤተ መቅደስ መግባት አያቻልም እንጂ በጥይት እንጨራርስ ነበረ:: ዘመዴ ገና ካሁኑ ጾም ሳይፈታ ሽንኩር ት ግዛ እያለች በወጣ በገባ እየጨቀጭቀችኝ ነው:: አረ ተይ ይደርሳል ብላት እነ እከሌ እኮ ከትፈው ዲፍሪዘር ውስጥ አስቀምጠውታል ትለኛለች:: ይሀው እኔም እየጾምኩ ነው በሷ የተነሳ:: :D ኦርቶዶክሳዊ ጾም መጾማችን ክፋት የለውም:: ነገር ግን ጾሙ ከውስጥ ይሁን!! ከውጭ አይሁን:: ሰዎች የይቅርታ መንፈስ ሳይኖራቸው ስጋ ስላልበሉ ይነጻሉ ማለት አይደለም:: ባለፈው ያውም በጾም እለት የቤተ ክርስቲያናችን አበ -እምነት ካንዱ መእምን ጋር ተጣልተው ነበር:: የሚያሳታርቅ ጠፍቶ እሳቸውም መምጣት ሁሉ አቁመው ነበር:: የሰደበቻቸው ደሞ የሰውየው ሚስት ናት አሉ::: ምነው ሴቱ ግን እንዲህ በቤተ መቅደስ ውስጥ ሙጢ አፍ ሆነ?? የእጊዚአብሄርን ቤት መፍራት የጠፋበት ዘመን ላይ ደርሰናል:: ሌላ ቦታ ደሞ ሶስት ቄሶች አንዱን ድሮ ጔደናቸው የነበረውን ቄስ አውግዘናል ገዝተናል ብለው ቁጭ አሉ:: :lol: እንደገባኝ ከሆነ ቄሶቹ ስልጣናቸውን ተጠቅመው ሁዴታ ነበረ ያደረጉት:: :lol: አሁን ይሄ ቱሉ ፈርሶ የሚባለው የጎሽ ጔደኛ ( ባለ ነጠብጣቡ ) ያሬዳዊ ዜማ ማዜማቸውን ባህላዊ ወረራ አድርጎ ማቅረቡ መመጻደቁን ከማሳየቱ ውጭ ሌላ ነገር የለውም:: ከነገድ ከቌንቌ የሆኑ ሁሉ እግዚአብሄር አምላካቸውን ያመስግኑት ይላል:: ድቤ አምጥተህ እንደርቢ እስካልጠራህ ድረስ በጸናጽልና በከበሮ በእልልታና በዝማሬ እግዚአብሄር በሰጠህ መረዋ ድምጽ አምላክህን እጊዚብሄርን አመሰግነው ሀለሉያ:: ""ይህ ህዝብ በክንፈሩ ያከብረኛል ልቡ ግን ከኔ የራቀ ነው"" የሚለው ለዘህ አይነቱ ባለ ነጠብጣቡን ለመሰለ ፈረቃሳ ነው:: የስራት ሰው ሳንሆን የእምነት ሰው እንሁን ዘንድ እጊዚብሄር ልባችንን ይክፈትልን:: እመቤታችን አይናችን ታብራልን:: እኛም አይናችንን ከፍተን ለማየት እንሞክር!! ዝም ብለህ አንተ ሆነ ብለህ የጨፈንከውን አይን እመቤቴ ማርያም እያልክ ምንም አትከፍትልህም...አይንህን ራስህ ክፈት ከዛደሞ መነፈሳዊ አይንህን ትከፍትልኅለች:: ሌላው ነገር ደግሞ ሰው ከሞተ ብኌላ ሬሳው ከደጀ ሰላም ስለተቀበረ ይጸድቃል ማለት አይደለም:: ከዛ ውጭ ገንዘብ ወይም ዘመድ አጥቶ የተቀበረ ደሞ ገኅነም ይገባል ማለትም አይደለም:: እነደዚህ ብሎ ማሰብ መንፈሳዊ ጅልነት ነው:: ለሟቹ ምንም የሚያደርግለት ነገር የለም:: ለቌሚ ዘመዶቹ መጽናኛ እንዲሆናቸው ብቻ ነው:: የሞተ ማ አርባ ቀን ባለም ዙሪያ ይዞርና ከአርባ ቀን በኌላ በብርሀን ፍጥነት ነፍሱ ወደ ሰማይ መጔዝ ትጀምራለች:: ስለ ሰማይ ሚስጥር አንድ ቀን እጽፋለሁ:: ጳውሎስ ለጢሞቶዎስ የጻፈውን የመሰለ አንድ ደብዳቤ አረፍ የምልበት ጥላ ሳገኝ የምጽፍ ይመስለኛል:: የማውቀው እውነት አለ::
ቢተወደድ1
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 218
Joined: Thu Sep 01, 2016 8:48 am
Location: Bisheftu

Return to Warka Culture and Literature - ዋርካ ባህልና ሥነ ጽሑፍ

Who is online

Users browsing this forum: ቢተወደድ1 and 0 guests