ሰላም ለሁላችን
እርካታ የሚገኘው ከዲጎኔ መልስ ወይም ከአንተ መረዳት ሳይሆን ከእውነቱ ጌታ ከክርስቶስ ነው::በተቻለኝ መጠን ሚዛናዊ ፋክቶችን/ሀቆችን ማቅረቤን እቀጥላለሁ::
ማህበረሰብ ኪነጥበብን የሚጠቀመው እንደባህሉ ለመሆኑ የባህል 101 መማር አያሻንም::ያሬዳዊ ዜማን በኮፒራይት የተዋህዶ ማህበር ስለመያዙ የማቀው የለም እንኩዋ በጦቢያ የኮፒ ራይት ፈጽሞ በማይሰራበት በአውሮፓ የነሞዛርት የነቤትሆቨን ቅኝት ሁሉ ሲጠቀም ክስ አልተሰማም::ጸያፍ ወሲብ ቀስቃሽ ዘፈኖች በያሬዳዊ ዜማ ሲቀርቡ ብታወግዙ ባማረባችሁ::እኛ ግን በሁሉ የዜማ አይነት ራፕ ጭምር ጌታን እናከብራለን::ጸናጽል በገና ማሰንቆ ከበሮ እምቢልታ ወዘተ የጦቢያ ቅርሶች በጦቢያዊነት የሁሉም ጦቢያዊ መጠቅም መብቱ ነው::
የቀበር ስፍራን በተመለከተ ድሮ የተሀድሶ ወገኖች ሲያርፉ የተፈቀደው ጴጥሮስ ወጳውሎስ የሚባለው ጉለሌ ብቻ ነበር እየበዛን ስንሄድ ዮሴፍ-ሳሪስ ተፈቀደ::በግል የማውቀው ግፍ ቀጨኔ መድሀኒያለም ሐረርና ድሬደዋ ቀብርቦታ ስንከለከል አስከሬን ይዘን ከክፍለሀገር ክፍለሀገር ተጉዘናል::
በተረፈ ጥንቡ ወልድ/ክርስቶስ የሌሽ ባለውቃቢና ያለንስሀ ህይወቱን በአለም ሲዳክር ኖሮ ሲሞት በማይፈታ ፍትሀት ፍትሀት የሚባልለት እንጂ በክርስቶስ ያመነና ህይወት ያገኘ ህያው ነው::ለቤተሰቦች ቅዱስቃል ለመካፈልና ለመጽናናት ነው እኛ የቀብር ስርአት የሚያስፈልገን::አንዱ ሀገር ቤት አይኑን ታሞ በሲዊስ ሚሽን ህክምና እንዲያገኝ የረዳሁት 'የእናንተ ጥንብ እኛ ዘንድ አይቀበርም' ብሎኛል::የታደሉት አለቃ ተወልደመድህን ግን ድሮ በለሳ ሚሽን አይን ክሊኒክ ሄደው የስጋም የመንፈስም አይናቸው ተፈውሶ የትግሪኛ መጽሀፍ ቅዱስን ለመተርጎም በቅተዋል እምነቱና በረከቱን ለልጅ ልጆቻቸው አትርፈዋል::ካቶሊኮቹ በቅርቡ በያሬዳዊ ዜማ መዘመር ጀምረዋል እንደ መምራችሁ አለቃ አያሌው 'መች ተለመደና ከተኩላ ዝምድና'ልትሉ ይሆን? ለማጠቃለልና እውነት ለመናገር ያሬድ ለእኔ ከማከብረው የተሀድሶ ፋናወጊ ደቅእስጢፎ አይለይም::ይልቅ አለማመኔ እርዳ የሚለውን መዝሙር ከቻልክ እዚህ አምጣው::
-...- wrote:ወንድም ዲጎኔ መልስህ አላረካኝም : እንደተማመንኩብህ በእውነት አልመለስክልኝም ። ጴንጤን እየተከላከልክ ነው ። የኔን አስተያየት ልንገርህ
መዝሙር በባህል ቢዘመር ማታለል አይደለም አልክ ። ዜማ ያሬድ የኢትዮጵያ ባህል አይደለም ። ዜማ ያሬድ የኦርቶዶክስ ሃይማኖት የግል ስርአተ ዜማ ነው ። የኦርቶዶክስን ዜማ አስመስሎ የጴንጤዎች መዘመር በኔ እምነት ማጭበርበር ማታለል ነው ።
ጸናጽል መቋሚያ ሽብሸባ የኦርቶዶክስ የግል ስርአት ነው ። ጸናጽልና መቋሚያ ይዞ በኦርቶዶክስ ዜማ የጴንጤዎች እንደ ኦርቶዶክስ ማሸብሸብ ማጭበርበር ማታለል ነው።
ባለዘርፍ ለምድ/ካባ የኦርቶዶክስ ስርአተ ልብስ ነው ። ጴንጤዎች ልብሰ ኦርቶዶክስ ለብሰው በኦርቶዶክስ ዜማ ማሸብሸብ ማጭበርበር ማታለል ነው
ከላይ የጠቀስኳቸው ጴንጤዎች ኦርቶዶክስን መስለው የዋህ ኢትዮጵያውያንን ስለማጭበርበራቸው ነው ።
ብቅንነት የምታዳምጠኝ ከሆነ ቀጥዬ ደሞ ብዙ ግዜ ስለምትደጋግማት የመቃብር መከልከል ትንሽ ልበል ። አደራ ሰደበኝ እንዳትል የሚሰማኝን አስተያየት ነው በግልጽ የምገልጸው
ብዙ ግዜ ቤተክርስቲያን መቃብር ተከለከልን ትላለህ ። ኦርቶዶክስ የራሱ መቃብር አለው ፡ እስላም የራሱ መቃብር አለው ሃይማኖት ነን ካላችሁ ለምን የራሳችሁን መቃብር አይኖራችሁም ?
እንዴት ነው ነገሩ እምነታችንን ቤተክርስቲያናችንን አያንቋሽሻችሁ ፡ እመቤታችንን ዝቅ አድርጋችሁና ሰድባችሁ ስትሞቱ ኦርቶዶክስ መቃብር እንቀበር የምትሉት የኛ ቤተክርስቲያን ጥምብ(ሬሳ ለማለት ነው)መጣያ ናት እንዴ ?
ጴንጤ ለኦርቶዶክስ ጸረማርያም/እርኩስ ነው( ሃቁን እምነት ነው የምነግርህ ስድብ እንዳይመስልህ)እና በኦርቶዶክስ መቃብር እንኳን እርኩስ ጸረማርያም ይቅርና ራሱን የገደለ/ያጠፋ ኦርቶዶክስ እንኳን አይቀበርም ። መቃብሩን እንደ ኦርቶዶክስ ፕራይቬት ክለብ ውሰደው ። የክለብ አባል ካልሆንክ አትገባም ። እና ይሄንን እንዴት ማገናዘብ አቅቷችሁ ነው ዘወትር መቃብር ተከለከልን እያላችሁ እሮሮ የምታሰሙት
ይህንን በቅን አንብበህና መርምረህ ቅን መልስህን እንደምትሰጠኝ እተማመናለሁ