ትንሹ ዳዊት በበገና ተጫወተ እንደገና

Topics related to cultures, arts, languages, arts such as humor, music, traditional literary genres of poems, ግጥም ፣ ቅኔ ፣ ተረትና ምሳሌ)

ትንሹ ዳዊት በበገና ተጫወተ እንደገና

Postby ቀዳማይ » Mon Nov 11, 2013 9:28 pm

አቤቱ ቃሌን ስማ
ስወተውትህ ከማማ
በማለዳ ተነስቼ
ከፊትህ እቆማለው ተግቼ
አንተ ክፉን ትጠላለህ
ደም አፍሳሹንም ታጠፋለህ
ስምህን የሚወዱ ወደድካቸው
ከፍ ከፍም አደረካቸው
ስለ ጠላቶቼ በጽድቅ ምራኝ
እንደ ጋሻ ሆነም ጠብቀኝ::
...................ከመዝሙረ ዳዊት የተወሰደ
ቀዳማይ
ጀማሪ ኮትኳች
ጀማሪ ኮትኳች
 
Posts: 60
Joined: Thu May 09, 2013 6:02 am

Postby ቀዳማይ » Mon Nov 11, 2013 10:16 pm

ነብሴ ሆይ እግዚአብሄን ባርኪ
ከበረከቱ ምንጭ ተጥተሽ እንድትረኪ
ሕይወትሽን ከጥፋት አድኖ
የሚከልልሽ በቸርነቱ ሸፍኖ
ምኞትሽን በጥበቡ የሚሞላት
ጎልማሳነትሽን እንደንስር ያድሳት::.......ከመዝሙረ ዳዊት
Last edited by ቀዳማይ on Thu Nov 14, 2013 2:18 am, edited 1 time in total.
ቀዳማይ
ጀማሪ ኮትኳች
ጀማሪ ኮትኳች
 
Posts: 60
Joined: Thu May 09, 2013 6:02 am

Postby ቀዳማይ » Wed Nov 13, 2013 5:12 pm

ልጄ ሆይ ቃሌን ብትሰማ
ትጠበቃለህ ከጨለማ
ማስተዋልን ፈልጋት
ጥበብንም አክብራት
እሷን እንደ ብር ብትሻት
እንደ ተቀበረ ወርቅም ብትፈልጋት
ያኔ እግዚአብሄርን መፍራት ታውቃለህ
የሱን ታላቅነትም ትረዳለህ::
ቀዳማይ
ጀማሪ ኮትኳች
ጀማሪ ኮትኳች
 
Posts: 60
Joined: Thu May 09, 2013 6:02 am

Postby ቀዳማይ » Wed Nov 13, 2013 5:24 pm

ንቃ! አትሁን ቸልተኛ
ሀይለኛ ሁን ጦረኛ
የጠላትን ምሽግ የሚያሸብር
ጀግና ሁን የማይበገር
ሊበላውን እንደሚፈልግ አንበሳ
ጠላት ዲያቢሎስ በዚሪያህ ሲያገሳ
የምን መኝታ የምን ቸልታ
የሴጣን ምሽግ ሳይሰበር በልልታ
በአለም ላይ ያሉ ወንድሞችህ
መከራ ሲቀበሉ እያየህ
በእምነት ጸንተህ ተቃወመው
በጌታ እየሱስ ስም ድል አድርገው::
ቀዳማይ
ጀማሪ ኮትኳች
ጀማሪ ኮትኳች
 
Posts: 60
Joined: Thu May 09, 2013 6:02 am

Postby ቀዳማይ » Thu Nov 14, 2013 2:30 am

የጌታ ስም እጅግ ክቡር
ሲወደስ ሲቀደስ የሚኖር
እርኩስ መንፈስ የማይደፍረው
እንደ ታላቅ ማማ የጸና ነው
የጻድቅ መደበቂያ ዋሻ
የደካሞች መሸሻ
ከክቡር ሁሉ የከበረ
ከስሞች ሁሉ ያማረ
የሀይለኞች ሁሉ ሀይለኛ
ስሙ ታላቅ ነው ለኛ::
ቀዳማይ
ጀማሪ ኮትኳች
ጀማሪ ኮትኳች
 
Posts: 60
Joined: Thu May 09, 2013 6:02 am

Postby ቀዳማይ » Thu Nov 14, 2013 2:55 am

የእግዚአብሄርን መቅደስ ያፈረሰ
የንጉሱን ቤት ያረከሰ
ወዮለት ለሱ ለባዘነው
ዲያቢሎስ ለሚጋልበው
እናንተ ግን የጌታን መቅደስ ጠብቁት
የመንፈሱ ቅዱስ ማደሪያው አድርጉት
ከሁሉ ይልቅ የከበረ
በደሙ ታጥቦ ያማረ
ሌላ አይደለም መቅደስ ስላችሁ
ያዳም ዘር እናንተ ናችሁ::
ቀዳማይ
ጀማሪ ኮትኳች
ጀማሪ ኮትኳች
 
Posts: 60
Joined: Thu May 09, 2013 6:02 am

Postby ቀዳማይ » Mon Nov 18, 2013 4:55 pm

የሰው አገር ስደተኛ
ለፍቶ አዳሪ መንገደኛ
በሰው አገር ስቃይ ቢበዛ
ነብሳቹ ብታልፍ እንደዋዛ
የሚከራከርልን ባይኖር ጠበቃ
ስቃያችንን የሚለን በቃ
ወጀቡን አትመልከቱ ወገኖቼ
እናንተ የበረሃው ዘመዶቼ
ቃል ያለው ይሻገራል
በሱ የታመነ ይድናል
ወደ ሰማይ ተመልከቱ
ወደ ጌቶች ጌታ ቃትቱ
በሳት የሚመልስ ሀይለኛ
አባት አለንኮ እኛ
ያስጨነቀንን ያስጨንቀዋል
ሁሉም የጁን ይከፍለዋል
እጃችንን ወደ ላይ ዘርግተን
ወደ እሱ ስንጮህ አብዝተን
እንደ ጉም ያተናቸዋል
ከሰማይ እሳት ይበላቸዋል
እመኑ አትፍሩ ቀኑ ደርሷል
እንክርዳዱ ከስንዴው ይለያል
አህዛብ ሁሉ ይንቀጠቀጣሉ
የኢትዮጲያ አምላክ እንዳለ ያውቃሉ
እናንተ ብቻ ጠንክሩ
በእምነታችሁ ኑሩ
ከሚያልፉት ቀኖች ሁሉ
እግዚአብሄር አያልፍም በሉ::

............የሰራዊት ጌታ እግዚአብሄር ከናንተ ጋር ይሁን በሳውዲ ለምትኖሩ ወገኖቼ በሙሉ::
ቀዳማይ
ጀማሪ ኮትኳች
ጀማሪ ኮትኳች
 
Posts: 60
Joined: Thu May 09, 2013 6:02 am

Postby መንክር » Mon Dec 23, 2013 11:58 pm

ቀዳማይ ወንድሜ ጌታ ይባርክህ ስለ አስተማሪ ግጥሞችህ:: አስተማሪ እና አነቃቂ ናቸው:: እንደዚህ ያሉ ለሰው ልጅ ህይወት የሚጠቅሙ ጽሁፎች ከዋርካም በላይ በፌስ ቡክ ቢሰራጩ ለብዙዎች ጥቅም ይሰጣሉ እና ከፈቅድክልኝ ስምህን ጠቅሼ ፌስ ቡኬ ላይ ለጠፍ ባደርጋቸውስ? ስለሁሉም ነገር የጌታ ስም ይክበር:: ሰላም ሁንልኝ::
መንክር
አዲስ
አዲስ
 
Posts: 28
Joined: Fri Feb 15, 2008 9:23 pm

Postby ቀዳማይ » Tue Dec 24, 2013 2:53 am

ወንድም መንክር የኔ ግጥሞችን ስሜን መጥቀስ ሳያስፈልግ እንደዳሻህ ብታደርጋቸው ደስ የለኛል እንጂ አይከፋኝም:: ዋናው አላማዬ እያዝናኑ ማስተማር ነውና ምንም ችግር የለውም ፍቃዴን ሰጥቼሃለው:: በዚ አጋጣሚም ለሰው እንዲደርስና እንዲሰራጭ በማሰብህ ላመሰግንህ እወዳለው::
Last edited by ቀዳማይ on Tue Dec 24, 2013 7:51 am, edited 1 time in total.
ቀዳማይ
ጀማሪ ኮትኳች
ጀማሪ ኮትኳች
 
Posts: 60
Joined: Thu May 09, 2013 6:02 am

Postby ቀዳማይ » Tue Dec 24, 2013 7:43 am

የማይታይ መሳሪያ
የዲያቢሎስ ማስፈራሪያ
ኢላማውን የማይስት
የክርስቲያኖች ርስት
በቀስታ ተወርዋሪ
የጨለማ ኮከብ አብሪ
የምድረ በዳ ውሃ አፍላቂ
ጠላታችንን አስጨናቂ
ከብርሃን ይልቅ የፈጠነ
ለደካሞች ጋሻ የሆነ
የክርስቲያን መሳሪያ
የችግርን አለት መስበሪያ
ተራራውን ዞር በል በሉት
የጸሎትን ሃይል እወቁት::
ቀዳማይ
ጀማሪ ኮትኳች
ጀማሪ ኮትኳች
 
Posts: 60
Joined: Thu May 09, 2013 6:02 am

Postby ቀዳማይ » Thu Dec 26, 2013 10:11 am

ሕይወቱ በዳንኪራ ደምቆ
በዝሙት ባህር ተጠምቆ
በልቡ ቂምን አርግዞ
የጥላቻ ስንቅን ይዞ
ከጠዋት ጀምሮ እስከ ማታ
ሕግህን ሲያፈርስ በቸልታ
በሰው ፊት አሞግሶህ
ተደብቆ ግን ሲበድልህ
አንተ መች አጠፋኸው
እንደ ሃጢያቱ ብዛት ቀጣኸው
ይልቅስ
ተደብቆ የሰራውን
በጨለማ ያረገውን
በብርሃን አውጥተህ
ጉድ ልታደርገው ስችል አዋርደህ
ሃጢያቱን ደብቀህለት
አንተ ግን ጠበከው በትግስት
ማለዳ ማለዳ አዲስ ሆነህ
ስጠብቀው እጅህን ዘርግተህ
ዛሬም ሳይመጣ ቀረ ጌታ
ከዙፋንህ ሳይወድቅ በይቅርታ::
ቀዳማይ
ጀማሪ ኮትኳች
ጀማሪ ኮትኳች
 
Posts: 60
Joined: Thu May 09, 2013 6:02 am

Postby ክቡራን » Thu May 08, 2014 7:02 pm

ቀዳምይ (666 ያውሬው ምስል ) ሰላም ነው..?? የኦሮምኛ ዘፈን የምታስጨፍርባትን ክፍል ረሳኅው እኮ!! ቅቅቅቅቅ:: ወራዳ!! አንተን አይደለም ደሞ የተሳደብኩት ውስጥህ ያለውን የክፋት መንፈስ ነው:: ኢመ ኅጠራው..ወዱ ኅጠራይቲ!! :lol:
ክቡራን
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 7962
Joined: Tue Mar 04, 2008 4:24 pm

Postby ጌታ » Thu May 08, 2014 8:23 pm

ክቡራን wrote:ቀዳምይ (666 ያውሬው ምስል ) ሰላም ነው..?? የኦሮምኛ ዘፈን የምታስጨፍርባትን ክፍል ረሳኅው እኮ!! ቅቅቅቅቅ:: ወራዳ!! አንተን አይደለም ደሞ የተሳደብኩት ውስጥህ ያለውን የክፋት መንፈስ ነው:: ኢመ ኅጠራው..ወዱ ኅጠራይቲ!! :lol:


:lol: :lol: :lol: :lol: እኔ በበኩሌ 666 ለመሆኑ እርግጠኛ የሆንኩት ቦቹን ነው:: ቀዳማይ ቦቹ ሊሆንም ላይሆንም ይችላል:: አሁን ገልብጤ ባንተ ያጻጻፍ ስታይል ያንተኑ ዌብሳይት ጠቅ አድርጉ ቢለን ክቡራን ነህ ልንለው ነው?

እኔም ገት ፊሊንጌ ቦቹ ቀዳማይ ነው ቢለኝም ሌትስ ጊቭ ሂም ዘ ቤኔፊት ኦፍ ዘ ዳውት...........ይኖዋምሴይን? :lol: :lol: :lol:
ኢትዮጵያ እጆቿን ወደ እግዚአብሄር ትዘረጋለች!!!
ጌታ
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 3029
Joined: Sun Apr 17, 2005 5:35 pm
Location: ዶሮ ተራ

Postby ገልብጤ » Thu May 08, 2014 9:51 pm

ጌታ wrote:
ክቡራን wrote:ቀዳምይ (666 ያውሬው ምስል ) ሰላም ነው..?? የኦሮምኛ ዘፈን የምታስጨፍርባትን ክፍል ረሳኅው እኮ!! ቅቅቅቅቅ:: ወራዳ!! አንተን አይደለም ደሞ የተሳደብኩት ውስጥህ ያለውን የክፋት መንፈስ ነው:: ኢመ ኅጠራው..ወዱ ኅጠራይቲ!! :lol:


:lol: :lol: :lol: :lol: እኔ በበኩሌ 666 ለመሆኑ እርግጠኛ የሆንኩት ቦቹን ነው:: ቀዳማይ ቦቹ ሊሆንም ላይሆንም ይችላል:: አሁን ገልብጤ ባንተ ያጻጻፍ ስታይል ያንተኑ ዌብሳይት ጠቅ አድርጉ ቢለን ክቡራን ነህ ልንለው ነው?

እኔም ገት ፊሊንጌ ቦቹ ቀዳማይ ነው ቢለኝም ሌትስ ጊቭ ሂም ዘ ቤኔፊት ኦፍ ዘ ዳውት...........ይኖዋምሴይን? :lol: :lol: :lol:

ተው እንጂ ጌታ ወዱ ስሜን ምሳሌ ታደርጋለህ....እንደ ዲጎኔ እና ለማ ያሉ አዛውንቶች እያሉ :?:
ደሞ ቦቹ ቀዳማይ ነው....ዛሪ ተነስቶበታል ፖለቲካ ቤት
ዛሩ በረድ ሲልለት ነበር በቀዳማይ የሚቀውጠው...ቂቂቂቂቂ
ያልበሰለ ፖለቲከኛ ስለቀጣዩ ምርጫ ሲያስብ
የበሰለ ፖለቲከኛ ስለቀጣዩ ትውልድ ያስባል
James freeman clarke
ገልብጤ
ዋና ውሃ አጠጪ
ዋና ውሃ አጠጪ
 
Posts: 1680
Joined: Sat Jun 26, 2010 11:24 pm

Postby ክቡራን » Thu May 08, 2014 11:23 pm

ኖ አይዶኖዋችዩርሰይን.. ሴይ ኢት ክሊር ኤንድ ላውድ..! :D

ጌታ wrote:
ክቡራን wrote:ቀዳምይ (666 ያውሬው ምስል ) ሰላም ነው..?? የኦሮምኛ ዘፈን የምታስጨፍርባትን ክፍል ረሳኅው እኮ!! ቅቅቅቅቅ:: ወራዳ!! አንተን አይደለም ደሞ የተሳደብኩት ውስጥህ ያለውን የክፋት መንፈስ ነው:: ኢመ ኅጠራው..ወዱ ኅጠራይቲ!! :lol:
እኔም ገት ፊሊንጌ ቦቹ ቀዳማይ ነው ቢለኝም ሌትስ ጊቭ ሂም ዘ ቤኔፊት ኦፍ ዘ ዳውት...........[u]ይኖዋምሴይን? :lol: :lol: :lol:
ክቡራን
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 7962
Joined: Tue Mar 04, 2008 4:24 pm

Next

Return to Warka Culture and Literature - ዋርካ ባህልና ሥነ ጽሑፍ

Who is online

Users browsing this forum: No registered users and 3 guests